Professional Documents
Culture Documents
5 - 1
5 - 1
የጌጅ ንባብ ከስታንዳርድ ጋር ማነፃፀር በዳሽ ቦርዴ ላይ የሚገኙትን የመቆጣጠሪያና ጠቋሚ መሳሪያዎች
በፍተሻ ወቅት የተገኘው ንባብ በማንዋለ ላይ ከተቀመጠው ስታንዳርድ ጋር በማነፃፀር ልዩነቱን በማወቅ
የሚስተካከልበት እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል ለምሳሌ የሞተር ውሃ መጠን በማስተካከል፣ የሞተር ዘይት
መጠን በማስተካከል፣ የሚያፈስ አየር ካለ ፌሳሹን በመዝጋት፣ የተቃጠለ ፉዮዞች ካለ በመቀየር፣ በነዳጅ ጋን
ውስጥ ያለውን የነዳጅ መጠን ሁኔታ በማየትና በማስተካከል፣ ጠቋሚ መብራቶች አለመቃጠላቸውን በማየትና
በመቀየር ሊያጠቃልል ይችላል፡፡
የፍሬን እና የመሪ ሁኔታ አፈታተሽ
ፍሬንና መሪ የተሽከርካሪ ዋና ዋና የመቆጣጠሪያ ክፍሎች በመሆናቸውና ብልሽት በሚያጋጥም ጊዜ
የሚደርሰው ጉድለት (አደጋ) ከፍተኛ ሊሆን ስለሚችል በእነዚህ ክፍሎች ላይ ዘወትር የሚከተሉትን ፍተሻዎች
ማድረግ ይገባል፡፡
የፍሬን ብቃት አፈታተሽ
የፍሬን ንፋስ አለመጉደልን
የፍሬን ዘይት አለመጉደልን
የፍሬን መርገጫ ፔዳል ነፃ እንቅስቃሴ ያለው መሆኑን
የፍሬን ሸራ አለማለቁን
የዘይት ፈሳሽ አለመኖሩን
የአየር /የንፋስ/ ፈሳሽ አለመኖሩን
የእጅ ፍሬን የሚሰራ መሆኑን
ተሽከርካሪውን በማንቀሳቀስ የእግር ፍሬን ብቃትን መፈተሸ
የተሽከርካሪ መሪ ብቃት አፈታተሽ
በተሽከርካሪ ላይ መሪ በሜካኒካል ወይም በዘይት ኃይል በሚታገዝ ሲስተም በሁለት መንገድ ሊሰራ
የሚችል ሲሆን ከዚህ የሚከተሉትን ፍተሻ በማድረግ ከባድ ብልሽት የመከላከል ተግባር ማከናወን
ይገባል፡፡
በቂ የመሪ ዘይት መኖሩን ማረጋገጥ
የሚያንጠባጥብ ወይም የሚያፈስ የዘይት መስመር አለመኖሩን መፈተሽ
የመሪ አገናኝ ዘንጎች አለመጣመማቸውን መፈተሸ
የመሪ መገጣጠሚያ ክፍሎች አለመስፋታቸውን መፈተሸ
የመሪ እንቅስቃሴ አለመጠንከሩን መፈተሸ
ተሽከርካሪን በማንቀሳቀስ የመሪን እና የፍሬን ብቃት መፈተሽ
የፍሬን እና የመሪ ክፍሎች ተሽከርካሪ በቆመበት ብቻ ሳይሆን ተሽከርካሪውን በማንቀሳቀስ
ብቃታቸውን መፈተሽ ይገባል፡፡ ሆኖም የፍሬንና የመሪ ሁኔታ ተሽከርካሪውን በማንቀሳቀስ አደጋ
በማያስከትል ሁኔታ መፈተሸ ይኖርበታል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን ቅድም ተከተል በመጠበቅ ፍሬንና
መሪን ፍተሻ ማድረግ ይቻላል፡፡
ሜዳማና ከትራፉክ ነፃ የሆነ መንገድ መምረጥ
በአነስተኛ ፍጥነት የፍሬን ብቃት መፈተሽ
በመካከለኛ ፍጥነት የፍሬን ብቃት መፈተሸ
ወደ ቀኝና ወደ ግራ በማዞር የመሪ ብቃት መፈተሽ
መሪን በመልቀቅ ወደ አንድ አቅጣጫ የሚጎትት አለመሆኑን መፈተሽ
የተሸከርካሪውን አጠቃላይ ይዘት፣ ክብደት፣ ስፋት፣ ቁመት፣ ሞዴል፣ የጭነት ልክ፣ ሲሲ፣
የሚጠቀመውን ነዳጅ፣ የመሪ ሁኔታ፣ ማርሽ..
አንዳድ ስርዓት
ይጥገና ቀን የሚደረግበትን ቀን
የዳሽቦርድ ምልክቶችን የሚተነትን አሽከርካሪው በቀላሉ እንዲያውቅ ይረዳል
ማንዋሎች ን መለየት እና በትክክለኛ ቦታ መጠቀም እና በውስጡ የተጻፉትን መረዳ የትራፊክ አደጋን
ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው፡፡