Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 2

.

ኢትዮ እስቲልና ፊኒሺንግ ኃ የተ የግል ማህበር

+251 911 951 925 /+251 920 202 062

ቀን 30/03/2015 ዓ.ም
የማሽነሪ ኪራይ ውል
(ውል ሰጪ) አከራይ፡- አሸናፊ ጥላሁን ኮንስትራክሽን ማሽነሪ ኪራይ
አድራሻ፡- አ.አ ክ/ከተማ ቦሌ ወረዳ 13 የቤ.ቁ አዲስ ስ.ቁ 0911951925/0920202062
(ውል ተቀባይ) ተከራይ፡- -------------------------------------------
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ክ/ከተማ ወረዳ የቤ.ቁ ስ.ቁ
የስራ ቦታ፡ አዲስ አበባ የስራው አይነት ፡
የስራው ዓይነት፡- ኤሌክትሪካል ዊንች ማሽን መከራየት
ዝቅተኛ የኪራይ ጊዜ ፡- (15 ቀን)
የአከራይ (ውል ሰጪ) አከራይ ግዴታዎች
 ውል ሰጪ ማሽኑን ሳይት ላይ ሲገባ ለመግጠምና ለመፍታት ባለሙያ ያቀርባል በተጨማሪ ህንጻው ላይ ለመጫኝ እና
ለማውረድ በቂ የሰው ሀይል ውል ተቀባይ ያቀርባል ፡፡
 ክፍያ በተመለከተ ቀድመ ክፍያ ቀን ብር መቀበል እና የኪራይ ቀኑ ከመጠናቀቁ በፊት ለተከራይ
ተጨማሪ ክፍያ እንዲከፍል መጠየቅ ፡፡
 ውል ተቀባይ ከውል ውጪ ሳይከፍል ከተጠቀመ በመጀመሪያ ዙር የከፈለውን የቀን ኪራይ እጥፍ የማስከፈል መብት አለው
፡፡
 ተከራይ ዊንቹን ከመጠቀሙ በፊት ቅድሚያ ክፍያ ካልከፈለ እና ከውል ውጪ ተከራይ ዊንቹን ሲጠቀምበት ካገኘ አከራይ
ዊንቹን ከሳይት የማውጣት መብት አለው ፡፡
 ውል ተቀባይ ካቀረበው በላይ ኤልክትሪክ ገመድ ማቅረብ ግዴታ የለበትም ከዛ በላይ የሚያስፈልግ ከሆነ ተከራይ (ውል
ተቀባይ ) ይሸፍናል ፡፡
የተከራይ (ውል ተቀባይ) ተከራይ ግዴታዎች
 ክፍያ በተመለከተ ቀድመ ክፍያ የ ቀን ብር መፈፀም
 የአከፋፈል ሁኔታ ከመጠቀማቸው በፊት ቅድሚያ ይከፍላሉ ቅድመ ክፍያ ለተፈፀመበት ቀን ብቻ የመጠቀም መብት
አላቸው ፡፡
 ማሽኑን መጫን ማውረድ ፣ፍሎር ላይ ለመስቀልና ለማውረድ በባለሙያው ለስራው የሚያስፈልገውን በቂ የሰው ሀይል
ሊያቀርብ ተስማምቷል ፡፡
 የውል ሰጪ ሙያተኞችን በስራ ሰአት ከድርጅቱ ሲላኩ ማሽኑ ያለበት ሳይት ውስጥ እንዳይገቡ መከልከል የለበትም ፡፡
 ለማሽኑ ስራ የሚያስፈልጉ ማቴያሎች እና ኤሌክትሪክ ሀይል ማዘጋጀት፣
 የዊንቹ የመጫን አቅም ጠቅላላ ክብደት ሰውን ጨምሮ 400 ኪ.ግ በላይ መጫን የለበትም ፡፡
 ውል ተቀባይ ከውል ውጪ ሳይከፍል ከተጠቀመ በመጀመሪያ ዙር የከፈለውን የቀን ኪራይ እጥፍ ሊከፍል ተስማምቷል ፡፡
 በተከራየው ኤልክትሪክ ዊንች ከቀለም ቅብ ስራ ፣ህንጻ ጽዳት፣ እና የህንጻው የውጪ አልሙኒየም ፣ልስን ፣እና ጥርብ ስራ
በሁለት ሰው የሚሰሩ ስራዎች ውጪ ዊንቹ ለእቃ ማጓጓዣነት ያልተሰራ በመሆኑ ምንም አይነት እቃ መጫን የተከለከለ
ነው ፡፡
 የማሽኑን የትራንስፖርት ወጪ በውል ተቀባይ ይሸፈናል /መውሰጃና መመለሻ/ ማውረጃና ፣መጫኛ፣ ቦታ ማዘዋወሪያ
በውል ተቀባይ ይችላል ፡፡
 ማሽኑ በስራ ላይ እያለ በሰራተኞች ቸልተኝነት ለሚደርሰው ጉዳት ኃላፊነቱን ተከራይ ይወስዳል ፡፡
 ማሽኑን በተረከበበት ሁኔታ ለውል ሰጪ ያስረክባል፡፡
.
ኢትዮ እስቲልና ፊኒሺንግ ኃ የተ የግል ማህበር

+251 911 951 925 /+251 920 202 062

 ከውል ሰጪ (አከራይ ) እውቅና ውጪ የቦታ ማዞር ሆነም ጥገና ለሚገጥመው ብልሽቶች ሆነም ንብረት ጉለት ኃላፊነቱን
ውል ተቀባይ ይወስዳል ፡፡
 ማሽኑ /ዊንቹ/ እቃ ሳይት ላይ ቢጎል /ቢሰረቅ/ በተከራይ ቸልተኝነት ጉዳት ቢደርስበት ተከራይ ሙሉ ኃላፊነት ይወስዳል፡፡
የጠፋውን/የተሰረቀውን /የተጎዳውን/ እቃ በተመሳሳይ ለመተካት ተስማምተው ፈርመዋል ፡፡
 ማሽኑ ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ ወይም ለሌላ ባለሞያ አሳልፎ መስጠት አይቻልም፡፡
ይህ ውል በፍ/ብ/ሕ/ቁ/1731/2005 መሰረት በህግ ፊት የፀና ይሆናል ይህንን ውል እንደውሉ አገላለፅ የማይፈጽም ወገን ቢኖር ውሉን
ላከበረ ወገን 1,000.00 ብር ከፍሎ ውልና ገደቡ በፍ/ሕ/ቁ/1889/1990/ መሰረት በህግ ፊት የጸና ይሆናል ፡፡
ውል ሰጪ ውል ተቀባይ
ስም ስም
ፊርማ ፊርማ
እኛም ምስክሮች አከራይ እና ተከራይ ከዚህ በላይ በተገለጸው መሰረት የኪራይ ውል ሲዋዋሉ አይተን በምስክርነት ፈርመናል ፡፡
1.
2.
3.

You might also like