Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 1

የሂሳብ ክፍል ሃላፊነት ሥለ ድርጅቱ ጠቅላላ ወጭ እና ገቢ የማስላት ሃላፊነት አለበት። በተጨማሪም ስለግብአት

አስፈላጊነት ስለ ምርት መጠን እንዲሁም ስለ ድርጅቱ ትርፍ እና ኪሳራ በተገቢው መንገድ ለድርጅቱ ስራ አስኪያጅ
ማቅረብ አለበት። ከዚህም በተጨማሪ የሂሳብ ክፍል እለታዊ ሳምንታዊ እና እንዲሁም ወርሀዊ የስራ አፈፃፀም ማስላት
እና ለድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ማሳወቅ አለበት።ይህ ማለት በቀን ምን ያህል ጥሬ እቃ ወይም ግብአት አስገባን ከገባውስ
ጥሬ እቃ ወይም ግብአት መካከልስ ምን ያህሉ ወደ ምርት ተቀየረ እንዲሁም ከተመረተው ምርት መካከል ምን ያህሉ ወደ
ደንበኛ ተሰራጨ የሚለውን እለታዊ ሳምንታዊ እና ወርሀዊ መረጃ በመያዝ የድርጅቱን ወጪ ገቢ እና ከወጪ ቀሪ ወይም
እለታዊ ሳምንታዊ እንዲሁም ወርሀዊ ብሎም ጠቅላላ አመታዊ የድርጅቱን ትርፍ በግልፅ እና በጥራት የመስራት እና
ለድርጅቱ ሰራተኞች በዋነኝነት ለድርጅቱ ስራ አስኪያጅ የማሳወቅ ሃላፊነት አለበት።ከዚህ በተጨማሪ የሰራተኞች
ደመወዝም በሂሳብ ክፍሉ አማካኝነት ታስቦ በወጪ መልኩ ይመዘገባል። የድርጅት
ስራ አስኪያጅ የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ
ስለ ድርጅቱ ጠቅላላ ቁጥጥር የማድረግ ሃላፊነት አለበት። ስለድርጅቱ እለታዊ ሳምንታዊ እና ወርሀዊ እንዲሁም
አመታዊ ስራ አፈፃፀም መገምገም አለበት። የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ የድርጅቱን ሰራተኞች የመቆጣጠር እና
የስራቸውንም ብቃት ጥራት እና አፈፃፀም መገምገም እና በስራቸው ላይ አስተያየት የመስጠት ሃላፊነት አለበት። ስለ
ድርጅቱ አመታዊ በጀት የመበጀት ሃላፊነት ከበጀቱም ላይ ለተለያዪ ወጭወች ማለትም ለግብአት ግዢ መፈፀሚያ
ለሰራተኞች ደመወዝ ክፍያ እንዲሁም ለድርጅቱ አስፈላጊ ወጪወች ከድርጅቱ በጀት ላይ ለእያንዳንዱ የመመደብ
ሃላፊነት አለበት። እንደአስፈላጊነቱ ሰራተኞች ፍቃድ ሲጠይቁ ፍቃድ የመስጠት ጥፋት ሲያጠፉ የምክር አገልግሎት
በመስጠት ከጥፋታቸው እንዲታረሙ ማድረግ ከጥፋታቸው ከልታረሙ የመጨረሻ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ የመስጠት
ሃላፊነት አለበት። የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ከተሰጣቸው በዃላም ከስህተታቸው ካልታረሙ ከስራ የማስወጣት እና
ማስታወቂያ በማውጣት በእነርሱ ቦታ ሌላ ሰራተኛ አወዳድሮ የመቅጠር ሃላፊነት አለበት። የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ
ከድርጅቱ ግብአት አቅራቢ ደንበኞች እና እንዲሁም ከድርጅቱን ምርት ተቀባዮች ጋር ጥሩ የሆነ ግንኙነት እና ውይይት
ማድረግ አለበት። ስለ ድርጅቱ ምርት ጥራት አቅርቦት እና መጠን አስተያየት እንዲሰጡ እድል ወይም ቦታና ጊዜ መስጠት
ምክንያቱም ከደንበኞች አስተያየትን ሲቀበል የድርጅቱን ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ለማወቅ ስለሚያስችል እንዲሁም
ምርትን ለደንበኞች በሚያመች ሁኔታ ለማቅረብ ይረዳል።

You might also like