Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 23

ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ

ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ CRYPTOTALK-ET


ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ

ክፍል 2
ምዕራፍ 1
1. የጃፓናውያን ካንድል ስቲክ
በመጀመሪያው ክፍል ትምህርት ላይ እንደተገለፀው በጃፓናውያን ካንድልስቲክ በተሰራ ቻርት ላይ የሬዚስታንስ እና ሰፖርት
መስመሮችን በመንተራስ እንዴት ትርፋማ ንግድን ማድረግ እንዳለብን ተወያይተናል።

በዚህ ክፍል ደግሞ ስለካንድልሲቲኮች በተናጠል ጠለቅ ተብሎ ምልከታ የሚሰጥበት ይሆናል።

ለመግቢያ ያህልም ፡

የጃፓናውያን ካንድል ስቲኮችን በመጠቀም መገበያየት ፡

ምናልባትም በግብይቱ አለም እድሜ ጠገቡ የግብይት አደራረግ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። በ18ኛው ክ/ዘመን ጃፓን የሩዝ
ነጋዴ የነበረው ሙኔሂሳ ሆማ ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ ይህንን የጃፓን ካንድልስቲክ ጥቅም ላይ ያዋለው። ትውልዶች ካለፉ በኋላ
ከምእራቡ አለም ወገን የነበረው ስቲቭ ኒሶን ይህንን ቲክኒክ በቅርበት መከታተል ጀመረ። ስቲቭ ኒሰን የዚህ ግብይት ዘዴ ሙሉ
ለሙሉ በሚባል መንገድ እስከሚገባው ድረስ ጥረቱን ቀጠለ። በኋላም በተግባር ያረጋገጣቸውን የካንድል ስቲክ የአገበያየት
መንገዶች በፅሁፍ መልክ መፃፍ ጀመረ።

ቀስ በቀስም ይህ ሚስጥራዊ ቴክኒክ በ1990ዎቹ እውቅናን ማግኘት ጀመረ። ረጅሙን ታሪክ አጭር ለማድረግ ያህልም ስቲቭ
ኒሰን ባይኖር ምናልባትም ካንድል ስቲክ ጭራሹን በዚህ ትውልድ ባልታወቀ ነበር። ለዚህም ይመስላል ኒሰንን ብዙዎች Mr.
CandleStick ብለው የሚጠሩት።

የጃፓናውያን ካንድል ስቲኮች ታዲያ ምንድናቸው?

የጃፓናውያን ካንድልስቲኮችን ለመረዳት በስእል ላይ የተደገፈ ማድረግ ይበልጡኑ ይቀላል።

የጃፓናውያን ካንድልስቲኮች በተለያዩ የጊዜ ገደቦች/Time Frames በስራ ላይ ሊውሉ ይችላሉ። በአንድ ቀን፤ በአንድ ሰዓት፤ 30
ደቂቃ፤ 15 ደቂቃ ወዘተ በሁሉም የጊዜ ገደቦች መቀመጥ ይችላሉ።

የጃፓናውያን ካንድልሲትኮች በአንድ በተወሰነ የጊዜ ገደብ ውስጥ የነበረን የዋጋ ሁነት የሚያሳይ የቻርት ግብዓት ነው።

ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ CRYPTOTALK-ET


ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ

የጃፓናውያን ካንድል ስቲክ በአንድ የጊዜ ገደብ ውስጥ ያለውን የመክፈቻ ዋጋ[Open Price]፤ ከፍተኛ ዋጋ[High Price]፤
ዝቅተኛ ዋጋ[Low Price] እና መዝጊያ ዋጋ[Close Price] ያካትታል። ይህንን በተለምዶ በእንግሊዘኛው OHLC ብለው በምህፃር
ሲጠራ ይሰተዋላል። እኛ በአማርኛ መከፍዝቅመዝ ብንለውስ?!

እነዚህ የዋጋ መጠቆሚያ ካንድል ስቲኮች የሚኖራቸውን ገፅታ ለመግለፅ ያህልም ፡-

- የካንድልስቲኩ መዝጊያ የዋጋ እርከን ከመክፈቻው የዋጋ እርከን በላይ ከሆነ ካንድልስቲኩ በባህላዊ መንገድ በሙሉ
ነጭ መደብ በዘመንኛው የተለመደ አቀማመጡ ደግሞ በአረንጓዴ ቀለም የተሞላ ይሆናል።
- የካንድልስቲኩ መዝጊያ የዋጋ እርከን ከመክፈቻው የዋጋ እርከን በታች ከሆነ ደግሞ ካንድልስቲኩ በባህላዊ ወይም
በነባሩ መንገድ በሙሉ ጥቁር መደብ በዘመንኛው የተለመደ ግራፊካዊ አቀማመጥ ደግሞ በቀይ ቀለም የተሞላ
ይሆናል።
- ይህ በቀለም የሚሞላው የካንድልስቲኩ ክፍል በተለምዶ “Body” ብለን የምንጠራው ሲሆን የቦዲ ቅጥያ በመሆን
የሚታዩትንና የዚያ የጊዜ ገደብ ከፍተኛ እና ዝቅተኛ ነጥቦችን የሚያሳዩንን ቀጫጭን መስመሮች ደግሞ በተለምዶ
“Shadow” ብለን እንጠራቸዋለን።
- የላይኛው “Shadow” የላይኛው ነጥብ “High” የምንለው እና በዚያ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተመዘገበው ከፍተኛ የዋጋ
ተመን ሲሆን የታችኛው “Shadow” የታችኛው ነጥብ ደግሞ “Low” የምንጠራው እና በዚያ የጊዜ ገደብ ውስጥ
የተመዘገበውን ዝቅተኛ የዋጋ ተመን የሚያሳየን ነጥብ ማለት ነው።

ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ CRYPTOTALK-ET


ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ

ምዕራፍ ሁለት
2. የጃፓናውያን ካንድል ስቲክ ስነ-ብልት [Anatomy]
በዚህ ክፍል በተቻለ የጃፓናውያን ሙሉ ቅርፅ ለየብቻ በታትነን ለማየት እንሞክራለን።

2.1. የሚያምር የሰውነት ቅርፅ ያላቸው ካንድል ስቲኮች …?!


ልክ እንደሰው ልጅ የሰውነት ቅርፅ ሁሉ የጃፓናውያን ካንድልስቲኮችም የሰውነት ቅርፅ የራሱ የሆነ መልእክት አለው። እስቲ
የተወሰኑትን እንመልከት፡

- ረጅም የሚባሉ ቦዲ ያልቸው ካንድልሲቲኮች ጠንካራ የሚባልን የመግዛት ወይም የመሸጥ ሁነት አመላካች ነው።
- የካንድልስቲኩ ቁመት በረዘመ ቁጥር የበለጠ የመግዛት አልያም የመሸጥ ግፊት እንዳለ ማወቅ ይቻላል። ይህም ማለት
ያ ረጅም ካንድልስቲክ በተፈጠረበት የጊዜ ገደብ ውስጥ[ቀለሙ እንድሚያመለክተው] ወይ ሻጮች አልያም ገዢዎች
ያንን ክፍለጊዜ በሀያልነት አሳልፈውታል ማለት ነው።
- አጫጭር የሚባሉ የካንድልስቲክ ቦዲ አይነቶች ደግሞ በዚያ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ እዚህ ግባ ሊባል የማይችል
ያን ያህል እምብዛም ጠንካራ ያልሆነ የግብይት እንቅስቃሴ እንደነበር ማሳያ ነው። በትሬዲንግ ብዙ ያሳለፉ ሰዎች
ምናልባትም ገዢዎችን ኮርማዎቹ[Bulls] ሻጮችን ደግሞ ድቦቹ[Bears] እንደሚሏቸውም ልብ ይሏል።
- ረጅም ነጭ[አረንጓዴ] ካንድልስቲኮች ጠንካራ የሆነን የመግዛት ግፊት ማሳያ ናቸው። ነጩ አልያም አረንጓዴው
ካንድልስቲክ በረዘመ ቁጥር የመዝጊያ ዋጋው ከመክፈቻ ዋጋው እየራቀ መምጣቱም ገበያው ሊያድግ[Bulllish]
መሆኑን ማሳያ ነው።
- ይህም በዋጋናነት ዋጋው ከመክፈቻው አንስቶ እስከ መዝጊያው ድረሽ ገዢዎች ሙሉ ለሙሉ ገበያውን
መቆጣጠራቸውን ማሳያ ነው። በሌላ ቋንቋ ኮርማዎቹ ድቦቹን በቀንዳቸው እያባረሯቸው እንደሆነ የሚነገርልእት
የገበያ ሁነት ነው።
- ረጅም ጥቋቁር[ቀያይ] ካንድልስቲኮች ጠንካራ የመሸጥ ግሪትን ያሳያሉ። ቀያዩ[ጥቁሩ] የጃፓናውያን ካንድልስቲክ
በረዘመ ቁጥር የመክፈቻ ዋጋው ከመዝጊያው ዋጋው እጅጉን እያነሰ መምጣቱም ገበያው ሊውርድ መሆኑ[Bearish]
መሆኑን ማሳያ ነው።
- ይህም በዋናነት ዋጋው ከመክፈቻው ጅምሮ እስከ መዝጊያው ድረስ በሻጮች የበላይነት ማለቁን የሚያሳይ ሲሆን
በሌላ ቋንቋ ድቦቹ[Bears] ኮርማዎቹን እየነካከሱ እነደፈጇቸው በምናብ የምንስልበት የገበያ ሁነት ነው።

2.2. ተአምራዊ ጥላዎች [shadows]

- ሻዶው ይባላሉ ያልናቸው በካንድልስቲክ ላይ ቀጥን መስመሮችን እጅግ ጠቃሚ የሚባልን ኢንፎርሜሽን ይሰጡናል።
- የላይኛው ሻዶው በዚያ የጊዜ ገደብ ውስጥ ከፍተኛውን ነጥብ ያሳየናል።
- የታችኛው ሻዶው በዚያ የጊዜ ገደብ ውስጥ ዝቅተኛ ነጥብ ያሳየናል።
- ረጃጅም የሆኑ የካንድልስቲክ ሻዶዎች የግብይት ሀነት የመክፈቻ እና መዝጊያ ዋጋው እጁጉን የራቀ ከፍተኛ እና ዝቅተኛ
ነጥቦች እንዳስመዘገበ ማሳያ ይሆናሉ።
- አጫጭር የካንድልስቲክ ሻዶዎች ደግሞ በዚያ በተሰጠ የጊዜ ገደብ ውስጥ ያን ያህል የግብይት እንቅስቃሴ
እንካልነበር፤ ኖሮም ቢሆን እንኳን ከመክፈቻ እና መዝጊያው የዋጋ ተመን ግን እምብዛም ያልራቀ እንደነበር የሚያሳዩ
የካንድልስቲክ ሁነቶች ሆነው እናገኛቸዋለን።

ረጃጅም ሻዶዎች

ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ CRYPTOTALK-ET


ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ

- አንድ ካንድ ስቲክ ረጅም የሚባል የላይኛህው ቀጭን መስመር [Upper Shadow] እና አጭር የታችኛው ቀጭን
ቅጥያ መስመር[Lower Shadow] ሲኖረው ገዢዎች ጡንቻቸውን በማርዘም በተቻላቸው ዋጋው ከፍ እንዲል
እንዳደረጉ ያሳየናል። ይሁንና በአንድ ወይም በሌላ ምክንያት ግን ሻጮች በዚያው የጊዜ ገደብ ውስጥ በገበያው ውስጥ
በመምጣት ዋጋው ወደተከፈተበት የዋጋ መጠን ተጎትቶ እንዲወርድ ማድረጋቸውን ማሳያ ነው።
- አንድ የጃፓናውያን ካንድልስቲክ ረጅም የታችኛው ቀጭን ቅጥያ መስመር እና አጭር የሚባል የላይኛው ቀጭን
ቅጥያ መስመር ሲኖረው ሻጮች ያላቸውን ሁሉ አቅም ተጠቅመው ወደታች ዋጋውን እንዳወረዱት ያሳያል። ይሁንና
በአንድም ሆነ በሌላ ምክንያት ግን ገዢዎች በዚያው የጊዜ ገደብ ውስጥ በገበያው ውስጥ በመምጣት ዋጋው
ወደተከፈተበት የዋጋ መጠን ተጎትቶ እንዲወጣ ማድረጋቸውን ማሳያ ነው።

ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ CRYPTOTALK-ET


ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ

ምዕራፍ ሶስት
መሰረታዊ የጃፓናውያን ካንድልስቲክ ስርዓተ-ጥለት

ስፓይኒንግ ቶፕ፤ ማሩቦቹ እና ዶጂ የሚሉትን መጠሪያዎች ከቴክኒካል አናሊስስ ጥናት ጋር ቁርኝት ላላችው ጆሮዎች አዲስ
አይደሉም። ለመሆኑ እነዚህ ነገራት ምን የሚያመሳስላቸው ምን የሚለያያቸውስ ነገር ይኖር ይሆና?

ሶስቱም ከመሰረታዊ የጃፓናውያን ካንድልስቲክ አይነቶች ውስጥ መመደባቸው የሚያመሳስላቸው ነገር ሆኖ እናገኘዋለን።
እስቲ ስለእያንዳንዱ ምንነት እና ትርጓሜ ለመወያየት እንሞክር። በሂደትም ምንነታቸውን በማወቅ በግብይት ላይ ትርፋማ
ልንሆን የምንችልበትን መንገድ በመቀየስ እንሞክራለን።

3.1. ስፓይኒንግ ቶፕ

- ረዘም ያለ የታችኛው እና የላይኛው ሻዶው ያላቸው ሆነው ቦዲ የምንለው አካላቸው አጭር የሆኑ የካንድል ስቲክ
አይነቶች ስፓይኒንግ ቶፕስ ይባላሉ። በዚህ አይነቱ ቅርፅ ባለው ካንድል ስቲክ ወቅት የካንድሉ የቀለም አይነት አረንጓዴ
ይሁን ቀይ ምንም አይነት የተለየ ለውጥ አይፈጥርም።
- ይህ ስፓይኒንግ ቶፕ ፓተርን የምንለው የካንድል ስቲክ አመሰራረት አይነት በገዢዎች እና ሻጮች መካከል ያለውን
ፉክክር ተመጣጣኝነት እና የበላይነቱ በማን እጅ እንደሆነ እርግጠኛ ያልሆነ ሁነት የሚታይበት የፓተርን አይነት ነው።

- በዚህ አይነቱ የካንድል ስቲክ ምስረታ ላይ ያለው አነስተኛ የቦዲ ክፍል መጠን በዚያ የጊዜ ገደብ ውስጥ የገበያ ዋጋው
ከተከፈተበት እምብዛም ያልራቀ እና ሲዘጋም ከመክፈቻ የዋጋ ተመን ነጥቡ እምብዛም ያልራቀ የዋጋ ተመንን ይዞ
የሚጨርስ የካንድልስቲክ ፓተርን ምስረታ አይነት ነው።
- ቀጫጭኖቹ ቅጥያ ሻዶው በመባል የሚታወቁት በካንድሉ የላይኛው እና የታችኛው ክፍል የሚታዩት ረጃጅም
ቀጫጭን መስመሮች ደግሞ ገዢዎችም ሆኑ ሻጮች በዚያ የጊዜ ገደብ ውስጥ የበላይነት ለመያዝ እጅጉን ጥረት
እንዳደረጉ ነገር ግን ሁለቱም እንዳልተሳካላቸው የሚያመላክት የካንድል ስቲክ ፓተርን አይነት ነው።
- ሻጮችም ሆኑ ገዢዎች በገበያው አሸናፊነታቸው ለረጋገጥ ባለመቻሉም የገበያውን ሁነት በእኩልነት ተቆጣጥረው
ለመጓዝ ይገደዳሉ።
- ስፓይኒንግ ቶፕ ወደላይ እየተጓዘ ባለ የገበያ ሂደት ላይ የሚከሰት ከሆነ ብዙ ገዢዎች በገበያው እንደሌሉ የምንረዳበት
ሁነት ሲሆን በዚህ አይነት አጋጣሚዎች ገበያው የሚጓዝበትን አቅጣጫ የመቀየር እድሉ የሰፋ መሆኑንም አስቀድመን
መገመት እንችላለን። በዚህም ወደላይ እያደገ ባለ የገበያ ሁነት ይህ አይነቱ የካንድል ስቲክ ምስረታ ሲያጋጥም የገበያ
ዋጋው አቅጣጫ ወደታች ሊቀየር መዘጋጀቱን በመረዳት አስፈላጊውን የግብይት ጥንቃቄም ሆነ ቅድመዝግጅት
ለማድረግ ይረዱናል ማለት ነው።
- ስፓይኒግ ቶፕ ካንድልስቲክ ፓተርን ገበያው ወድታች እየወረደ ባለበት ሁነት የሚከሰት ከሆነ ደግሞ የሻጮች ቁጥር
እየቀነሰ ስለመምጣቱ የምንረዳበት ሁነት ሲሆን በዚህም ገበያው እየሄደበት ከነበረው የዋጋ መውረድ አቅጣጫውን
በመቀየር ወደ ማደግ ሊቀየርበት የሚችለው አጋጣሚ የሰፋ መሆኑን እንድረዳ ይረዳናል ማለት ነው።

ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ CRYPTOTALK-ET


ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ

3.2. ማሩቦዙ

- በቅጥታ ከመጣበት የጃፓንኛ ቋንቋ ስንተረጉመው ማሩቦዙ የሚለው ቃል መላጣ ወይም የተላጨ ጭንቅላት
የሚለውን ትርጉም ይሰጠናል።
- ከስሙ በመነሳት እንደምንረዳውም ይህ አይነት ካንድል ስቲክ አይነት ሻዶው እንደሌለው መረዳት ይቻላል።
- እንደካንድሉ አይነት ቀለሙ ሊለያይ ቢችልም በዚህ አይነቱ ካንድል ስቲክ ምስረታ ወቅት ሁሌም የመክፈቻ እና
መዝጊያ ዋጋዎች ከከፍተኛ እና ዝቅተኛ የዚያ ካንድል የዋጋ እርከኖች ጋር እኩል ነው። በዚህም በዚህ አይነቱ ካንድል
ምንም አይነት ሻዶው የማይኖረው ይሆናል ማለት ነው።

- ነጩ[አረንጓዴው] ማሩቦዙ ካንድል ረጅም ነጭ ሰውነት ያለው እና ምንም አይነት ሻዶው የሌለው ካንድል ሲሆን
መክፈቻ ዋጋው ከዝቅተኛ ዋጋው ጋር እንዲሁም መዝጊያ ዋጋው ከከፍተኛው የዚያ የጊዜ ገደብ ካንድል ዋጋ ጋር እኩል
ነው። ይህም ማለት ይህ ካንድል በዚያ የጊዜ ገደብ ውስጥ በነበረው ዝቅተኛ ዋጋ መክፈቻነት የጀመረ የካንድሉን ሁነት
የዘጋው በከፍተኛ ነጥቡ ላይ ነው ማለት ነው።
- ይህ አይነቱ ካንድል እጅግ ጠንካራ ከሚባሉ ቡሊሽ የካንድል አይነቶች ውስጥ ይመደባል። ይህም በዚህ የካንድል ስቲክ
ምስረታ ወቅት ገዢዎች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ሁኔታ ብልጫ እንደነበራቸው ማሳያ ነው። በዚህም የአንድን ቡሊሽ
የገበያ አካሄድ መቀጠል[Bullish Continuation] አልያም ወደታች እየተጓዘ ከነበረ የወደታች የገበያ ጉዞ ወደላይ
አቅጣጫ መቀየርን[Bullish Reversal] የሚያመላክት ካንድል ሆኖ እናገኘዋለን።
- ጥቁሩ[ቀዩ] ማሩቦዙ ካንድል ረጅም ጥቁር ሰውነት ያለውና ምንም አይነት ሻዶው[ተቀጥላ ጭራ] የሌለውን የገበያ
ቅርፅ የያዘ የካንድል ስቲክ አይነት ነው። የመክፈቻው ዋጋ ከዚያ የጊዜ ገደብ ከፍተኛ ዋጋ እኩል ሲሆን የመዝጊያ ዋጋው
ደግሞ ከዝቅተኛው ዋጋ ጋር እኩል ሆኖ እናገኘዋለን። ይህም ካንድሉ በነበረው የምስረታ ቆይታ ከፍተኛ በነበረው ዋጋ
የተከፈተ ሲሆን ያለማቋረጥ ዋጋው እየቀነሰ ሄዶም በዝቅተኛ ዋጋው ሲዘጋ የሚፈጠር የካንድል አይነት ነው ማለት
ነው።
- ይህ አይነቱ ካንድል ጠንካራ የዋጋ መቀነስን የሚያሳይ ካንድል ሲሆን በዚህም በዋናነት እንደምክንያት የምንወስደው
ካንድሉ ከተከፈተበት ቅፅበት ጀምሮ ሻጮች ገበያውን ሙሉ ለሙሉ የተቆጣጠሩበት ሁነት ስለሚፈጠር እና ዋጋውም
ያለማቋረጥ የመውረድ ሁነትን ስለሚያሳይ ነው። ከሞላ ጎደል ይህ አይነቱ ካንድል ስቲክ ወደታች አቅጣጫ እየተጓዘ
ያለን የገበያ አካሄድ እንደሚቀጥል[Bearish Continuation] የሚያሳየን አልያም ደግሞ እያደገ ባለ ወደላይ የሚጓዝ
የገበያ ሁነት ቅርፅ ውስጥ ያ የማደግ ሁነት ወደታች መጓዝ ሊጀምር እንደሆነ እና ወደዳውንትሬንድ የገበያ ሁነት
ሊቀየር ስለመሆኑ ማሳወቂያ[Bearish Reversal] ካንድል ስቲክ ነው።

በዚህም ጠቅለል አርጎ ለማስቀመጥ ሊፈጠር ከሚችለበት ቦታ እና ካለው ቀለም አንፃር ተነስተን ስለማሩቦዙ ካንድል
ስቲኮች የሚከተሉትን ነጦች ማስታወስ ተገቢ መሆኑ ልብ ይሏል።

3.2.1 ነጩ ማሩቦዙ ፡

- ነጩ ማሩቦዙ ወደላይ እያደገ ባለ የአፕትሬንድ ሁነት ከተከሰተ ይህ ወደላይ የሚሄድ የገበያ ሁነት ቀጣይነት እንዳለው
እና በቀጣይነት አሁንም የማደግ እድል እንዳለው ያመላክታል።

ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ CRYPTOTALK-ET


ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ

- ወደታች እየተጓዘ ባለ የዳውንቲሬንድ ላይ ከተከሰተ ደግሞ ያ ወደታች የሚሄድ የገበያ ሁነት መልሶ ወደላይ መጓዝ
የሚጀምርበት እና የገበያ ቅርፁም አቅጣጫውን ወደላይ የሚቀይርበት እድል የሰፋ መሆኑ የምንለይበት ቦታ ነው።

3.2.2 ጥቁሩ ማሩቦዙ ፡

- ጥቁሩ ማሩቦዙ ወደታች እየተጓዘ ባለ ዳውንትሬንድ የገበያ ሁነት ላይ ከተከሰተ የዚያ ወደታች የሚሄድ የገበያ
እንቅስቃሴ እና ቅርፅ ሊቀጥል የሚችልበት እድል የሰፋ መሆኑን ያሳያል።
- ወደላይ እያደገ ባለ የአፕትሬንድ የገበያ ቅርፅ ወቅት ከተከሰተ ደግሞ ገበያው አቅጣጫ የመቀየር እና ወደታች የመሄድ
እድሉ የሰፋ መሆኑን ያሳያል።

3.3 ዶጂ ካንድል ስቲክ

ዶጂ ካንድል ስቲኮች ደግሞ የመክፈቻ እና መዝጊያ ዋጋቸው አንድ አይነት የሆኑ ካንድል ስቲኮች ናቸው። ምንም እንኳን
በሁሉም አጋጣሚዎች ግዴታ ይህ የመክፈቻ እና የመዝጊያ ዋጋ እኩል መሆን ባይኖርበትም እንኳን እጅጉን በጣም ትንሽ
የሚባል ለውጥ ብቻ ሊኖራቸው ግን ግድ ይላል። በዚህም የዶጂ ካንድል ቅርፅ በተለይም ሰውነቱ [Body] የምንለው ክፍል
እጅግ በጣም ቀጭን ወይም በመስመር ብቻ ሊገለፅ የሚችል ሆኖ እናገኘዋለን።

ዶጂ ካንድል ስቲኮች በእርግጥም በአብዛኛው በቀጥታ ትርጉማቸው በገበያ የገዢዎችም ሆነ የሻጮች የበላይነት አለመወሰዱን
እና እርግጠኛ ለመሆን አስቸጋሪ የሆነ የገበያ ሁነት ማሳያ ካንድል ስቲኮች ተደርገው ሲወሰዱ ይስተዋላል።

በዚህ ካንድል ስቲክ ምስረታ የገበያ ዋጋው ወደላይ ከፍና ወደታች ዝቅ ሲል ከቆየ በኋላ መጨረሻ ላይ የመዝጊያ ዋጋው ግን
ከመክፈቻው እኩል አልያም በጣሙን ተቀራራቢ ሆኖ ይዘጋል/ያልቃል። በዚህም ገዢዎችም ሆኖ ሻጮች በዚያ የጊዜ ገደብ
አሸናፊዎች መሆን ሳይችሉ በእኩል ውጤት የግብይት ሂደታቸውን መጨረሳቸውን አመላካች ካንድል ስቲክ ነው ማለትም
ይቻላል።

በቻርት ጥናት ውስጥ “በዋነኝነት” አራት አይነት የዶጂ ካንድል ስቲኮች ሲከሰቱ ይስተዋላሉ። እዚህ ጋር በዶጂ ምስረታ ወቅት
ማስታወስ ከሚገቡን ነጥቦች መካከል የላይኛው እና የታችኛው ሻዶው የምንላቸው የካንድል ስቲክ አካላት የመስቀለኛ ቅርፅ
ያለው፤ የተገለበጠ የመስቀለኛ ቅርፅ ያለው[Inverted Cross]፤ እንዲሁም የመደመር የሚመስል ቅርፅ ያለውን ዶጂ ካንድሎችን
እንድናገኝ ያደርጋሉ። [*የእንግሊዘኛው Doji የተሰኘ ቃል የነጠላንም የብዛትም ይዘት የሚወክል እንደሆነ ልብ ይሏል።]

በማንኛውም የገበያ ሁነት የዶጂ ካንድል በሚያጋጥም ጊዜ ተገበያዮች ከዚያ ዶጂ በፊት በተከታታይ የተመሰረቱትን ካንድል
ስቲኮች የበለጠ ትኩረት ሰጥቶ መከታተል ይኖርበታል።

አንድ ዶጂ ካንድል ስቲክ ከረጃጅም ቡሊሽ ካንድሎች ለምሳሌ ከነጩ ማሩቦዙ ካንድሎች መፈጠር በኋላ የመጣ ከሆነ፤ ገዢዎች
እየተዳከሙ እና አቅም እያጡ መሆኑን የምናይበት ሊሆን ይችላል። በዚህ ሂደት ገበያው ባለበት ይቀጥል ዘንድም ገዢዎች
መጠንከር እና የሚያንቀሳቅሱት ቮሊዩምም መጨመር የሚኖርባቸው ቢሆንም የካንድሉ ባህሪ እንደሚያሳየው [ቮሊዩም
ባለበት እንደቀጠለ በማሰብ] ቀድሞ በገበያው ላይ የነበራቸውን ጥንካሬ በማጣት ሂደት ላይ መሆናቸውን መረዳት እንችላለን።
በዚህም ዋና ምክንያትነት ነው እንግዲህ በዚህ አይነቱ የዶጂ ካንድል ምስረታ ወቅት ዋጋ ሊቀንስ ስለመሆኑ ማመላከቻ ቅድመ
ምልከታ ነው ልንል የምንችለው።

ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ CRYPTOTALK-ET


ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ

በተቃራኒው አንድ የዶጂ ካንድል በተከታታይ ከተመሰረቱ ቢሪሽ ማሩቦዙ ካንድል ስቲኮች በኋላ የመጣ ከሆነ በገበያው ውስጥ
ያሉ ሻጮች አቅም እያጡ እና ገዢዎች ለሚያቀርባቸው የመግዣ ዋጋም ሊሸነፉ እየተዘጋጁ ስለመሆናቸው ቅድመ ምልከታን
የሚያሳየን ሆኖ እናገኘዋለን። በዚህም የገበያ ቅርፅ ምስረታ የገበያ ዋጋው መውረዱን እንዲቀጥል የሻጮች አቅም ጠንካራ
መሆን የነበረበት ቢሆንም ከዶጂው ምስረታ እንደምንረዳው የሻጮች አዝም እያነሰ ስለመምጣቱ ማሳያ ስለሚሆን ያ የገበያ
ሁነት ቅርፁን እና አቅጣጫውን ወደላይ አቅጣጫ የመቀየር እድሉ የሰፋ መሆኑን መረዳት እንችላለን። ምንም እንኳን የሻጮች
ጥንካሬ እየቀነሰ ስለመምጣቱ በዶጂው አማካኝነት ምልክትን ብናይም የገዢዎች አቅም እና ግፊት መጠንከሩን እና የገበያ
አቅጣጫ ቅያሪን[Reversal] የሚያረጋግጡልን ተጨማሪ የገበያ ሁነት ማሳያ ኢንዲኬተሮች እና የገበያ ሁነቱ ቅርፅ እንዲሁም
የዋጋ ንቅናቄ [Price Action] ከግምት ማስገባት ግዴታ መሆኑ ልብ ይሏል። ይህ ሁነት በየትኛው አይነት የገበያ ቅርፅ እና
አቅጣጫ በቅድሚያ ማሰብ ያለብን የዶጂ ካንድል ጥናት አካል መሆኑንም ከግንዛቤ ማስገባት ያስፈልጋል።

ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ CRYPTOTALK-ET


ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ

ምዕራፍ አራት
4.1. ነጠላ [ባለአንድ ካንድ ስቲክ] ፓተርኖች
ይህ አይነቱ ካንድል ስቲክ በቻርት ላይ ሲመሰረት በመሰረታዊነት ሊመጣ ወይም ሊከሰት የሚችልን የገበያ አቅጣጫ ለውጥ
ያመለክታል።

በብዛት ጥቅም ላይ ከመዋላቸው አንፃር አራት መሰረታዊ የሚባሉ ነጠላ የጃፓናውያን ካንድል ፓተርኖች አሉ። ሀመር፤
ሀንጊንግ ማን፤ ኢንቨርትድ ሀመር እና ሹቲንግ ስታር።

4.1.1. ሀመር እና ሀንጊንግ ማን ካንድል ስቲኮች

መዶሻ [Hammer] እና የተሰቀለ ሰው[Hanging Man] የምንላቸው የካንድል ስቲክ አይነቶች በቅርፅ እጅጉን ተመሳሳይ ግን
በትርጉም እጅጉን የተለያዩ የካንድል አይነቶች ናቸው።

ሁለቱም አነስ ያለ ሪል ቦዲ፤ ረጃጅም የታችኛው ሻዶው ወይም ዊክ እና እጅግ በጣም አጭር ወይም ጭራሹን የሌለ የላይኛው
ሻዶው ያላቸው የካንድል አይነቶች ናቸው።

ገበያው ወደታች አቅጣጫ እየወረደ ባለበት ሁነት ሀመር የምንለው የካንድል ስቲክ ከተፈጠረ የቡሊሽ ሪቨርሳል የገበያ ሁነት
የምንለው ገበያው ተገልብጦ ወደላይ ጉዞውን ሊጀምር ስለመሆኑ ማመላከቻ የሆነ የካንድል አይነት ነው። ይህ ካንድል ስሙ
የተሰጠው የገበያ ሁነቱን ለመገልበጥ ጥረት ላይ መሆኑን አመልካች ካንድል ከመሆኑ የመጣ ነው።

ዋጋ እየወረደ ባለበት ሁነት ሀመር ካንድሎች የሚፈጠሩ ከሆነ የዚያ ገበያ ጊዜያዊ ዝቅተኛ ዋጋ መዳረሱንና ዋጋው ወደማደግ
ሁነት ሊቀየር ስለመቃረቡ ቅድመ ምልከታ ይሰጡናል።

ረጅሙ የታችኛው ሻዶው መፈጠሩ የሚያመላክተን ሻጮች የግብይቱን ዋጋ ዝቅ እንዲል ጫና መፍጠራቸውን ነገር ግን ገዢዎች
ይህንን ከበድ ያለ ግፊት ተቋቁመው እና መልሰው የዚያ የጊዜ ገደብ መዝጊያ ዋጋ ወደተከፈተበት ዋጋ እንድሚጠጋ አድርገው
የሚጨርሱበት ሁነትን ያሳያል።

ይሁንና ከዚህ የካንድል አይነት ጋር ተያይዞ አንድ ማወቅ ያለብን ጉዳይ ሀመር ካንድል ስላየን ብቻ የመግዛት ትእዛዝ ማድረግ
አለብን ማለት እንዳልሆነ ልብ ማለት ያስፈልጋል። በዚህም ተጨማሪ የማደግ ሁነቱ ማረጋገጫ አመላካች ጉዳዮችን ማየት
ያስፈልገናል። ከእነዚህ ማረጋገጫዎች መካከል ለምሳሌ ያህል ከሀመሩ ካንድል ምስረታ በኋላ የሚመጣው ካንድል ቡሊሽ ባህሪን

ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ CRYPTOTALK-ET


ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ

የያዘ እና ከሀመሩ መክፈቻ የዋጋ እርከን በደንብ ከፍ ብሎ የተዘጋ ነጭ ወይም አረንጓዴ ካንድል መፈጠሩ የቡሊሽ ሪቨርሳል
ማረጋገጫ ይሆነናል ማለት ነው።

የሀመር ካንድል ስቲክን መለያ ቅድመ ሁኔታዎች

- ረጅሙ ሻዶው ከትክክለኛ የካንድል ስቲኩ ሰውነት ቅርፅ በልኬት ከሁለት እስከ ሶስት ጊዜ መብለጥ አለበት።
- እጅግ በጣም አጭር ወይም ጭራሹን የሌለ ሻዶው
- ሪል ቦዲ በላይኛው የዚያ የጊዜ ገደብ የግብይት እርከን አካባቢ የሚፈጠር ነው።
- የሪል ቦዲ የቀለም አይነት የተለየ የሚባል ተፅእኖ በግብይት ጥናቱ ላይ አይኖረውም።

በእንግሊዘኛው The Hanging Man የምንለው የካንድል ስቲክ አይነት ደግሞ ቢሪሽ ሪቨርሳል የቻርት ምስረታ የምንለውን
የዋጋ እርከኑ ወደታች ሊወድቅ ስለመሆኑ ቅድመ ግምት እንድናስቀምጥ የሚረዳን የካንድል ስቲክ አይነት ነው። በዚህም የዚያ
የገበያ ዋጋ አካሄድ ከፍታው ላይ እንደደረሰ እና የጠነከረ ሬዚስታንስ እንደገጠመው የሚያሳይ የካንድል አይነት ነው።

ዋጋ እያደገ ባለበት ሁነት ሃንጊንግ ማን የካንድል አይነት ሲፈጠር ሻጮች በገዢዎች ላይ የበላየንትን ማሳየት መጀመራቸውን
የሚያሳይ ነው።

ረጅሙ የታችኛው ሻዶው መፈጠሩ ሻጮች የገበያ ዋጋውን በተቻላቸው መጠን እያወረዱት ስለመሆኑ ማሳያ ነው። በዛውም ልክ
ገዢዎች ያለ የሌለ ሀይላቸውን ተጠቅመው ካንድል ስቲኩ በዚያ የጊዜ ገደብ ወደተከፈተበት የዋጋ ተመን መመለሳቸውን
ያሳያሉ። ይሁንና በዚህ ሂደት ግን የገበያ ሁነቱ እያደገ በመጣበት ሂደት የነበረው የገዢዎች ሀይል ግን እየተዳከመ ስለመምጣቱ
አንዱ ማሳያም ጭምር ነው።

በዚህም፤ በዚህ አይነቱ ክስተት የገዢዎች ቁጥር ወይም ሀይል መመናመኑን በመገመት እና የገበያ ንቅናቄውን የሚያሳልጥ ሀይል
ሀይል እያነሰ መምጣቱን ማሳያ በመሆኑ ቅድመ ግምት እና ጥንቃቄ መውሰድ ግድ ይላል።

የሀንጊንግ ማን ካንድል ስቲክን መለያ ቅደመ ሁኔታዎች

- ረጅሙ ሻዶው ከሪል ሰውነቱ ቅርፅ በልኬት ከሁለት እስከ ሶስት ጊዜ መብለጥ አለበት።
- እጅግ በጣም አጭር ወይም ጭራሹን የሌለ ሻዶው
- የሪል ሰውነቱ ቀለም ያን ያህል በግብይት ሁነቱ ላይ እዚህ ግባ የሚባል ተፅእኖ የሌለው ቢሆንም ቀለሙ ጥቁር[ቀይ]
በሚሆንበት ወቅት ግን ከነጩ[አረንጓዴው] በበለጠ ሁነት ቢሪሽ የሆነ ባህሪ እያሳያ መሆኑን የሚያመላክተን ሁነት
አድርገን መውሰድ እንችላለን።

4.1.2. የተገለበጠ መዶሻ [Inverted Hammer] እና ተወርዋሪ ኮከብ [Shooting Star]

እነኚህም ሁለት ካንድሎች በቅርፅ አንድ አይነት ሲሆኑ ብቸኛ ልዩነታቸው የሚከሰቱበት የቻርት ላይ ቦታ ነው። ይህም ማለት
አንደኛው ወደታች እየተጓዘ ባለ ገበያ ሌላኛው ደግሞ ወደላይ እየተጓዘ ባለ የገበያ ሁነት ላይ መፈጠራቸው ነው።

የተገለበጠ መዶሻ [Inverted Hammer] ገበያው ካለበት የእንቅስቃሴ ሁነት ወደላይ አቅጣጫ ሊገለበጥ ስለመሆኑ የሚያሳየን
በተለምዶ ቡሊሽ ሪቨርሳል የምንለው የካንድል አይነት ሲሆን ተወርዋሪ ኮከብ ብለን የምንጠራው የካንድል አይነት ደግሞ
ገበያው ወደላይ አቅጣጫ እየተጓዘ ባለበት ቅፅበት በመከሰት ገበያው የአቅጣጫ ለውጥ በማሳየት የደቡብ አቅጣጫ ጉዞ
ሊጀምር ስለመሆኑ ማሳያ የሚሆነን በተለምዶ ቢሪሽ ሪቨርሳል የምንለው አይነት የካንድል ስቲክ ነው።

እነኚህ ካንድሎች ትንሽ የሚባል ሰውነት ያላቸው ሲሆን [ነጭም ይሁን ጥቁር]፡ ረጃጅም የላይኛው ሻዶው እና ምንም ወይም
እጅግ አነስተኛ የሚባል የታችኛው ሻዶው ያላቸው ናቸው።

ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ CRYPTOTALK-ET


ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ

የተገለበጠ መዶሻ [Inverted Hammer]:


ይህ የካንድል አይነት እየወረደ ባለ የገበያ ሁነት ላይ በብዛት የሚፈጠር የካንድል አይነት ሲሆን ገዢዎች በዚያ የጊዜ ገደብ
ዋጋውን በተቻላቸው ከፍ ለማድረግ የጣሩበት ሁነት የሚታይበት የካንድል አይነት ነው። ይሁንና በዚሁ የጊዜ ገደብ ሻጮች ያለ
የሌለ ሀይላቸውን ተጠቅመው ገበያውን ያወረዱበት ሁነት የሚታይ ይሆናል።

ይሁንና እየወረደ ባለበት የገበያ ሁነት ሀይል የነበራቸው ሻጮች ሀይላቸው እይተዳከመ ስለመምጣቱ በሌላ በኩል ደግሞ
በሚወርደው የገበያ ሁነት ደግሞ ደካማ የነበረው የገዢዎች ሀይል እየተጠናከረ ስለመምጣቱ የምናይበት ሁነት ነው።

በዚህም ሻጮች ከዚያ የገበያ ዋጋ በላይ ወደታች ማውረድ አለመቻላቸው ከዚያ የዋጋ እርከን በታች ለመሸጥ የሚፈልጉ
ተጨማሪ ቁጥር ያላቸው የሻጮች ቁጥር እየተመናመነ ስለመሆኑ አንድ ማሳያ ነው። በዚህም ሻጭ ከሌለ በገበያው ገዢ ነውና
የሚኖረው ከፍላጎቱ እና አቅርቦቱ አንፃር ዋጋ የመጨመር እድሉ የሰፋ ነው።

4.1.3. ተወርዋሪ ኮከብ [Shooting Star]፡


ይህ አይነቱ ካንድል ወደታች አቅጣጫ የገበያ ሁነትን የሚገለብጥ ፓተርን[Bearish Reversal Pattern] አመላካች የካንድል
አይነት ሲሆን ከተገለበጠው መዶሻ[Inverted Hammer] ጋር ቅርፁ አንድ አይነት የሆነ ቅርፅ ያለው ነው። ይሁንና የተወርዋሪ
ኮከብ በሚል ቅፅል የሚታወቁት የካንድል አይነቶች የሚፈጠሩበት[የሚከሰቱበት] የገበያ እርከን ግን ወደላይ እያደገ ባለ የገበያ
እንቅስቃሴ ወቅት ነው።

ቅርፁ እንድሚያመለክተው ዋጋው የከፈተው በዚያ የጊዜ ገደብ ዝቅተኛ ሊባል በሚችለው የዋጋ እርከን አካባቢ ሲሆን በገዢዎች
ግፊት አምክኝነትም ዋጋው በተቻለው ወደላይ ለማደግ የሞከረበት ሂደት ታይቷል። በዛው ሂደትም ተመልሶ ወደመክፈቻው
አካባቢ ተመልሶ ሊወርድ እንደቻለ መመልከትም ይቻላል።

ይህም ማለት ገዢዎቹ እያደገ የነበረውን የገበያ ሁነት ለማስቀጠል ሙከራቸውን ቀጥለው የነበረ ቢሆንም በተወሰነ ደረጃ ግን
እየተዳከሙ መምጣቸውን በስተመጨረሻም ረዘም ካለ ወደላይ የሚደረግ ጉዞ በኋላ በሻጮች ብልጫ የተወሰደባቸውን ሁነት

ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ CRYPTOTALK-ET


ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ

ማየት ይቻላል። በዚህም ይህ አይነቱ ካንድልስቲክ ወደላይ እየተጓዘ ባለ የገበያ ሁነት በሚያጋጥምበት ወቅት ሙሉ ለሙሉ
እርግጠኛ ሊባል በሚችል መልኩ የዋጋ መውረድ ሁነትን አመላካች ካንድል ስቲክ መሆኑን መናገር ይቻላል።

4.2. ባለሁለት ካንድ ስቲክ ፓተርን ምስረታዎች

በመጀመሪያው የዚህ ክፍል ርዕስ ላይ ለመዳሰስ እንደተሞከረው ባለነጠላ የካንድል ስቲክ ምስረታዎችን ተዳሷል።
ታዲያ ከእነዚህ ባለአንድ የካንድል ምስረታዎች የተሻለ ሊባል የሚችልን እይታ የሚሰጡን ፓተርን ምስረታዎች
ሆነው የምናገኛቸው ባለሁለት የካንድል ስቲክ ምስረታ ፓተርኖችን ይሆናል።

እነዚህን የካንድል ስቲክ ፓተርኖች ለመለየት በቻርት ምስረታው ላይ ቢያንስ ሁለት ካንድል ስቲኮችን ከግምት
ማስገባት ግድ ይለናል። በዚህ የካንድል ፓተርን ምስረታ ስር በዋናነት እና በመሰረታዊነት ከሚታወቁ የባለሁለት
የካንድል ስቲክ ፓተርን ምስረታዎች ውስጥ ከዚህ በታች በተወሰነ መልኩ መግቢያ ለመስጠት ይሞከራል።

4.2.1 ኢንገልፊንግ ካንድል ስቲክ ፓተርን

ይህንን አይነቱን የካንድል ፓተርን ለሁለት ከፍለን መመልከት እንችላለን። እነሱም ቡሊሽ ኢንገልፊንግ እና ቢሪሽ
ኢንገልፊንግ የምንላቸው ሁለት የተለያየ የገበያ ሁነትን የሚያሳዩ የካንድል ፓተርን አይነቶች ናቸው።

ቡሊሽ ኢንገልፊንግ ፓተርን [Bullish Engulfing pattern] የምንለው የካንድል ፓተርን በሁለት ካንድሎች አማካኝነት
የሚመሰረት የካንድል ስቲክ ፓተርን አይነት ሲሆን በቻርቱ የገበያ ዋጋ ግንባታ ላይ በተለይ የዋጋ እንቅስቃሴው ወደታች አቅጣጫ
እየተጓዘ ባለበት ሁነት የሚከሰትና በዋናነትም እንደሪቨርሳል የፓተርን አይነት የሚወሰድ ጠንካራ የዋጋ ማደግ ሁነት ሊከሰት
ስለመሆኑ አስቀድመን ስለገበያው ግምታችንን ልናስቀምጥበት የሚያስችለን የግብይት ማጥኛ መንገድ ነው።

ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ CRYPTOTALK-ET


ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ

ይህ የካንድል ስቲክ ፓተርን ምስረታ የሚከሰተው የመውረድ ባህሪን የሚያሳያን “ቢሪሽ” የሆነ ካንድል በተመሰረተ ቅፅበት እጅግ
ጠንካራ የሆነ የማደግ ባህሪን የሚያሳይ ረጅም “የቡሊሽ” ነጭ ወይም አረንጓዴ የካንድል ስቲክ ምስረታ በቀጣይነት ሲመሰረት
ነው። ይህ ሁለተኛ ረጅም እና የገዢዎች ሀይል መበራከቱን የሚያመላክት ካንድል የመጀመሪያውን ቢሪሽ ካንድል ስቲክ
መዋጡን[ሙሉ ለሙሉ የበላይነት መውሰዱን] መመልከት እንችላለን። ይህም ማለት በገዢው በኩል ያሉ የገበያው ተሳፊዎች
ከተወሰነ የዋጋ መውደቅ ሁነት አልያም ወደጎን ብቻ የመጓዝ አጋጣሚ በኋላ በገበያው ውስጥ ያላቸው የበላይነት ጎልቶ
የሚታይበት እና ጡንቻዎቻቸውም መፈርጠሙን የሚያሳዩበት የገበያ ክስተት ነው።

ሁለተኛው አይነት የኢንገልፊንግ ካንድል ፓተርን ምስረታ የሆነው የቢሪሽ ፓተርን ደግሞ ከላይ የተዳሰሰው ቡሊሽ ካንድል ስቲክ
ፓተርን ምስረታ ተቃራኒ የገበያ ሁነት የሚታይበት ነው። ይህ አይነቱ የካንድል ስቲክ ፓተርን የሚመሰረተው ቡሊሽነትን የሚያሳይ
የካንድል አይነት በተለይ ወደላይ እየተጓዘ ባለ የገበያ እርከን ላይ ሲከሰትና ከዚህ ካንድል በኋላ ደግሞ ሙሉ ለሙሉ የበላይነት
የሚወስድበት እና የሚውጠው[engulf] ቢሪሽ ካንድል ቀጥሎ ሲከሰት ነው። ይህም ማለት በሻጭ በኩል ያሉ የገበያው
ተሳታፊዎች የገዢዎችን ሀይል ሙሉ ለሙሉ እንደበለጡ እና ገበያው ይሄድበት ከነበረው የወደላይ አቅጣጫ ወደደቡብ አቅጣጫ
ማሽቆል ሊጀምር ስለመሆኑ ቅድመ ግምታችንን የምንወስድበት ቅፅበት ይሆናል ማለት ነው።

4.2.2 የወረንጦ [ትዊዘር] ቦተም እና ቶፕ የካንድል ስቲክ ፓተርን

ትዊዘር ቦተም እና ቶፕ የምንላቸው የፓተርን አይነቶችም ልክ እንደኢንገልፊንጉ ሁሉ ለመመስረት ግዴታ ሁለት የካንድል
ስቲኮችን ከግምት ያስገቡ ሆነው እናገኛቸዋለን። Tweezer የሚለውን ቃል በግርድፉ ወደአማርኛ አቻው ስንተረጉመው
“ወረንጦ” የሚባለውን ቃል ትርጉም የሚሰጠን ሲሆን በተለምዶ መቀንደቢያ ብለን የምንጠራውን የሴቶች ውበት መጠበቂያ
መሳሪያ አልያም የህክምና/የላብራቶሪ ባለሙያዎች የተለያዩ ለጥናት የሚያወስዷቸውን ጥቃቅን ግብአት ለማንቀሳቀስ
የሚጠቀሙበት መሳሪያ ሆኖ እናገኘዋለን። ከታች በምስሉ እንደሚታየው ይህ የመቀንደቢያ መሳሪያ ጫፎቹ እኩል እና
ከበታችሁ እኩል ቁመና እንዳለው መመልከት ይቻላል። ልክ እንደአብዛኛዎቹ የትሬዲንጉ አለም ስሞች ይህም የፓተርን አይነት
ከእውነተኛው የመቀንደቢያ መሳሪያ ጋር ተመሳሳይ የቅርፅ ይዘት ስላለውም ይህ ስም ሊወጣለት ችሏል።

የትዊዘር የካንድል ፓተርን በብዛት የሚከሰተው ረዘም ላለ ጊዜ የቀጠለ የገበያ ዋጋ የማደግ አልያም የመውደቅ ሁነት
በሚኖርበት ወቅት ሲሆን በዋነኝነትም የገበያ ዋጋ አካሄዱ አቅጣጫ ሊቀይር ስለመሆኑ ቅድመ ግምታችንን እንድናስቀምጥ
የሚያመላክተን የካንድል ስቲክ ፓተርን ምስረታ ነው።

ሁለት አይነት የ”ወረንጦ”[Tweezer] ፓተርን ምስረታዎች ሲኖሩ እነሱም ትዊዘር ቦተም እና ትዊዘር ቶፕ ብለን የምንጠራቸው
የፓተርን አይነቶች ናቸው። ይህም በዋነኝነት ስለምንነቱ ከላይ በተገለፀበት አረፍተ ነገር እንደተካተተው የገበያ ሁነቱ ወደታች
አቅጣጫ ለረጅም ጊዜ እየሄደ ባለበት ሁነት ትዊዘር ቦተም ሊከሰት የሚችል ሲሆን ገበያው ረዘም ላለ ጊዜ ወደላይ አቅጣጫ
ሲጓዝ ከቆየ በኋላ ደግሞ ትዊዘር ቶፕ ሊከሰት ይችላል ማለት ነው።

ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ CRYPTOTALK-ET


ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ

በጣም ጠንካራ እና ውጤታማ ሊባሉ የሚችሉ የትዊዘር ፓተርን ምስረታዎች የሚከተሉትን ባህሪያት ያማከሉ መሆን
ይጠበቅባቸዋል።
1/ የመጀሪያው ካንድል ስቲክ የገበያ ሁነቱ እየሄደበት ካለው የገበያ አቅጣጫ ትሬንድ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ባህሪ ሊኖረው
ይገባል። ይህም ማለት ገበያው እያደገ ባለበት ሁነት ትዊዘር ተከሰተ ለመባል የመጀመሪያው ካንድል ቡሊሽ ባህሪን የሚያሳይ
መሆን ያለበት ሲሆን ገበያው እየወደቀ ባለበት ሁነት ተከሰተ ለመባል ደግሞ ይኸው የዚህ ፓተርን የመጀመሪያ ካንድል ስቲክ
ቢሪሽ ባህሪ ያለው ካንድል ስቲክ ሊሆን ይገባል።

2/ ሁለተኛ የሚመሰረተው የካንድል ስቲክ ደግሞ በተቃራኒው ገበያው እየሄደ ከነበረበት የገበያ አካሄድ አቅጣጫ በተለየ
አቅጣጫ የመጓዝ ባህሪን ሊያሳይ ይገባዋል። ይህም ማለት ወደታች አቅጣጫ በሚሄድ የገበያ ዋጋ አካሄድ በመጀመሪያ ቢሪሽ
የሆነ ካንድል ከተመሰረተ በኋላ ተመሳሳይ ይዘት ያለው ነገር ግን በገዢዎች ብልጫ የተወሰደበት አረንጓዴ ካንድል ሊሆን
ይገባዋል አልያም ወደላይ አቅጣጫ በሚሄድ የገበያ ሁነት ደግሞ እንደዚሁ የመጀመሪያው ካንድል ቡሊሽ ባህሪን የሚያሳይ
ምስረታ ካሳየ በኋላ በአንድ አይነት ይዘት ነገር ግን ሻጮች ብልጫውን መውሰዳቸውን የሚያሳይ ቀይ የካንድል ስቲክ ምስረታ
ሊኖር ይገባዋል ማለት ነው።

3/ የካንድል ስቲኮቹ ተቀጥላ ጭራዎች [Wicks/Shadows] ርዝመት በሁለቱም የካንድል ስቲኮች ላይ እኩል አልያም እጅግ
በጣም አነስተኛ ለውጥ ብቻ ሊኖራቸው ይገባል። ይህም ማለት ትዊዘር ቶፕ የምንለው የካንድል ፓተርን እኩል የሆነ ከፍተኛ
የዋጋ እርከንን[same highs] የሚያመላክቱ ሲሆን ትዊዘር ቦተም በምንለው የካንድል ፓተርን ምሰረታ ላይ ደግሞ እኩል የሆነ
ዝቅተኛ የገበያ ዋጋ እርከንን[same lows] የሚያመላክቱ መሆን ይኖርባቸዋል ማለት ነው።

4.3. ባለሶስት ካንድልስቲክ የፓተርን ምስረታዎች

እስካሁን ካየናቸው የባለአንድ እና ባለሁለት የካንድል ስቲክ ፓተርን ምስረታዎች በተሻለ ጥቅም ሊሰጥ የሚችል ሌላ ከካንድል
ስቲኮች የዋጋ ምስረታ እና የቅርፅ ምስረታ ጋር በተያያዘ ሊነሳ የሚችለው የፓተርን ሁነት ባለሶስቱ የካንድልስቲክ ፓተርን የቻርት
ሁነት ነው።

እነዚህን መሰሎቹን የሶስትዮሽ የካንድል ስቲክ ፓተርን ምስረታ ለመለየት ይህ አይነቱ የገበያ አጠናን መንገድ ቢያንስ ሶስት
ተከታታይ የካንድል ስቲኮችን ከግምት ማስገባት ይኖርብናል። የእነዚህ ካንድልስቲኮች የአመሰራረት ሁነት፤ የሰውነት ቅርፅ እና
የተመሰረቱበት ቦታ ሁሉ በአንድ ላይ የገበያ ዋጋው በቀጣይ ወደየት አቅጣጫ ሊሄድ እንደሚችል የሚጠቁሙ ሆነው
እናገኛቸዋለን።

አንዳንድ የካንድል ስቲክ ምስረታዎች የገበያ ሁነቱ እየሄደበት ካለው አቅጣጫ ሙሉ ለሙሉ ወደተቃራኒው ሊቀየር ስለመሆኑ
የሚያሳዩ እና በተለምዶ Reversal Patterns የምንላቸውን ገበያው አሁን ያለበትን ሁነት ሊለውጥ ስለመሆኑ የሚያሳዩ የፓተርን
አይነቶች ሲሆኑ ሌሎቹ የሶስትዮሽ የካንድል ስቲክ ምስረታ የፓተርን አይነቶች ደግሞ በተለምዶ Continuation Patterns
የምንላቸው እና ለተወሰነ ቅፅበታት ገበያው ጋብ ሊል እንደሚችል ግን እየሄደ በነበረበት አቅጣጫ ተጠናክሮ ጉዞውን ሊቀጥል
እንደሚችል ቅድመ ግምታችንን እንድናስቀምጥ የሚረዱን የካንድል ስቲክ ፓተርን አይነቶች ናቸው።

ከዚህ በመቀጠል ዋና ዋና እና መሰረታዊ የሚባሉትን የሶስትዮሽ የካንድ ስቲክ ፓተርን አይነቶችን የምንመለከት ይሆናል።

4.3.1 የንጋት ኮከብ እና የአጥቢያ ኮከብ የሶስትዮሽ የካንድል ስቲክ ፓተርን ምስረታዎች

የንጋት እና የአጥቢያ ኮከብ ባለሶስት ካንድል ስቲክ ፓተርኖች በብዛት ሁነቶች የሚከሰቱት በአንድ የገበያ ትሬንድ አካሄድ
መጨረሻ አካባቢ ነው። በዚህም በይበልጥ በሪቨርሳል ፓተርንነታቸው ተለይተው የሚታወቁ ሆነው እናገኛቸዋለን። ለዚህም
ሶስት ዋና ዋና መሰረታዊ ባህሪያቶቻቸውን እንደማሳያ ማንሳት ይቻላል።

ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ CRYPTOTALK-ET


ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ

የአጥቢያ ኮከብ የፓተርን ምስረታ


1/ በዚህ ፓተርን ምስረታ ወቅት የመጀመሪያው ካንድል ቡሊሽ ካንድል ሆኖ ይገኛል። ይህም በዋናነት ፓተርኑ ወደላይ እየሄደ
የነበረ አፕትሬንድ እንደነበር ማሳያ ነው።

2/ ሁለተኛው ካንድል አነስተኛ የሚባል የካንድል ሰውነት ያለው ሲሆን ይህም በዋናነት በገበያው ውስጥ በሁለቱም የገበያው
ተሳታፊዎች ወገን [በገዢም ሆነ በሻጭ በኩል] እርግጠኛነት ያልተሞላበት እና አጠራጣሪ የገበያ ስነልቦና እንዳለ ያሳያል።

3/ ሶስተኛው ካንድል ስቲክ ይህ ትሬንድ ሊያበቃ ስለመሆኑ እና አቅጣጫ ሊቀይር ስለመሆኑ የምናረጋግጠበት የconfirmation
ካንድል አድርገን መውሰድ የምንችልበት ነው። ለዚህ ሁነት መከሰት ሁነኛ ማረጋገጫችን ይኸው ሶስተኛ ካንድል ስቲክ
ከመጀመሪያው ካንድል ስቲክ ቁመት አጋማሽ በታች ባለ የገበያ ዋጋ እርከን ላይ የሚዘጋ ከሆነ ይሆናል።

የንጋት ኮከብ የፓተርን ምስረታ


በተቃራኒው የንጋት ኮከብ ፓተርን ምስረታ ደግሞ የሚከተሉት የምስረታ ሁነቶችን የሚያጠቃልል ይሆናል።
1/ በዚህ ፓተርን ምስረታ ወቅት የመጀመሪያው ካንድል ቢሪሽ ካንድል ሆኖ እናገኘዋለን። ይህም በዋናነት ፓተርኑ ወደታች
አቅጣጫ እየሄደ የነበረ ዳውንትሬንድ እንደነበር ማሳያ ነው።

2/ ሁለተኛው ካንድል አነስተኛ የሚባል የካንድል ሰውነት ያለው ሲሆን ይህም በዋናነት በገበያው ውስጥ በሁሉቱም የገበያው
ተሳታፊዎች ወገን [በገዢም ሆነ በሻጭ በኩል] እርግጠኝነት ያልተሞላበት እና አጠራጣሪ የገበያ ስነልቦና እንዳለ ያሳያል።

3/ ሶስተኛው ካንድል ስቲክ ይህ ትሬንድ ሊያበቃ ስለመሆኑ እና አቅጣጫ ሊቀይር ስለመሆኑ የምናረጋግጥበት የconfirmation
ካንድል አድርገን መውሰድ የምንችልበት ነው። ለዚህ ሁነት መከሰት ሁነኛ ማረጋገጫችን ይኸው ሶስተኛ ካንድል ስቲክ
ከመጀመሪያው ካንድል ስቲክ ቁመት አጋማሽ በላይ ባለ የገበያ ዋጋ እርከን ላይ የሚዘጋ ከሆነ ይሆናል።

4.3.1 ሶስት ነጫጭ ወታደሮች እና ሶስት ጥቋቁር ወታደሮች ባለሶስት ካንድልስቲክ ፓተርን

የሶስት ነጫጭ ወታደሮች የፓተርን ምስረታ


ባለሶስቱ የነጭ ወታደሮች የፓተርን ምስረታ ሶስት ቡሊሽ የሆኑ ተከታታይ ካንድል ስቲኮች የገበያ ሁነቱ ወደታች አቅጥጫ
እየሄደ ባለበት የዳውንትሬንድ ሁነት የሚፈጠር እና የገበያ እንቅስቃሴው አቅጣጫውን ሊቀይር ስለመሆኑ ቅድመ ግምትን
እንድንወስድ የሚረዳን የሪቨርሳል ፓተርን አይነት ነው።

ይህ አይነቱ የፓተርን ምስረታ በተለይ በተለይ ቀጣይነትን ባሳየ የዳውንትሬንድ እንቅስቃሴ እና ከዚህ ሁነት ቀጥሎ ከተከሰተ
የተወሰነ የጎንዮሽ የገበያ እንቅስቃሴ በኋላ የሚፈጠር ከሆነ እጅግ በጣም ጠንካራ የሆነ የቡሊሽ የገበያ ሁነት ሊከሰት ስለመሆኑ
ማሳያ የሆነ የካንድል ስቲክ ፓተርን ምስረታ ሆኖ እናገኘዋለን። አንድን የባለሶስት ነጫጭ ወታደሮች የካንድል ስቲክ ፓተርን
ትክክለኛ የሆነ ምስረታ ነው ብሎ ለመወሰን የሁለተኛው ካንድል ስቲክ የሰውነት መጠን ከመጀመሪያው ካንድል ስቲክ ሰውነት
መጠን የበለጠ መሆን ያለበትና ሁለተኛው ካንድል ስቲክ ምስረታውን ሲጨርስ ከከፍተኛ የዋጋ እርከኑ[High Price] ጋር አንድ
አይነት ወይም እጅጉን የተቀራረቡ መሆን ይኖርበታል። በዚህም ምንም አልያም አነስተኛ የሚባል ተቀጥላ[wick] ይኖረዋል።

ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ CRYPTOTALK-ET


ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ

በተጨማሪነትም ይኸው የባለሶስት ነጫጭ ወታደሮች የካንድል ፓተርን ሙሉ ለሙሉ ምስረታውን ጨረሰ ለመባል፤
የመጨረሻው ካንድልስቲክ ቢያንስ ቢያንስ ከሁለተኛው ካንድል ስቲክ በሰውነት መጠኑ እኩል መሆን አልያም መብለጥ
ይኖርበታል። ይኸው ሶስተኛ ካንድል ስቲክ እጅግ አነስተኛ የሚባል አልያም ምንም አይነት የካንድል ተቀጥላ[Shadow/Wick]
የማይኖረው መሆን ይኖርበታል።

የሶስት ጥቋቁር ወታደሮች የፓተርን ምስረታ


ይህ አይነቱ የካንድል ስቲክ ፓተርን ምስረታ ከስሙ ልንረዳ እንደምንችለው ከሆነ ከላይ የተመለከተነው የባለሶስት ነጫጭ
ወታደሮች የካንድል ስቲክ ፓተርን ተቃራኒ ሆኖ እናገኘዋለን። በዋናነት ይህ አይነቱ የፓተርን አይነት በዋናነት ሶስት ቢሪሽ
የሚባል ባህሪ ያላቸው ተከታታይ የካንድል ስቲኮች ጠንካራ ከሆነ የወደላይ አቅጣጫ የገበያ ምስረታ [Uptrend] ሲመሰረቱ
ሲሆን ይህም የገበያ ዋጋ እንቅስቃሴው ሙሉ ለመሉ አካሄዱን ወደታች አቅጣጫ ሊቀይር ስለመሆኑ ቅድመ ግምት
የምንወስድበት የካንድል ስቲክ ፓተርን ምስረታ አይነት ነው።

አንድን የባለሶስት ጥቋቁር ወታደሮች የካንድል ስቲክ ፓተርን ትክክለኛ የሆነ ምስረታ ነው ብሎ ለመወሰን የሁለተኛው ካንድል
ስቲክ የሰውነት መጠን ከመጀመሪያው ካንድል ስቲክ ሰውነት መጠን የበለጠ መሆን ያለበትና ሁለተኛው ካንድል ስቲክ
ምስረታውን ሲጨርስ ከዝቅተኛ የዋጋ እርከኑ[Low Price] ጋር አንድ አይነት ወይም እጅጉን የተቀራረቡ መሆን ይኖርበታል።
በዚህም ምንም አልያም አነስተኛ የሚባል ተቀጥላ[wick] ይኖረዋል።

በስተመጨረሻም ይህ የፓተርን ምስረታ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቋል ለማለት በሶስተኝነት የሚመሰረተው የካንድል ስቲክ
ከሁለተኛው ካንድል ስቲክ ጋር በሰውነት መጠኑ ቢያንስ እኩል አልያም የሚበልጠው መሆንና የመሰረተው ካንድልም እጅግ
አነስተኛ አልያም ምንም የካንድል ተቀጥላ ጭራ/ጥላ [Wick/Shadow] የሌለው መሆን ይኖርበታል።

4.3.2 ባለሶስት ውስጣዊ ክፍታ[Three Inside Up] እና ባለሶስት ውስጣዊ ዝቅታ [Three Inside Down]
የካንድልስቲክ ፓተርኖች

ባለሶስት ውስጣዊ ከፍታ[Three Inside Up] የካንድል ስቲክ ፓተርን ምስረታ


ይህ አይነቱ የካንድል ስቲክ ምስረታ በዋነኝነት የሚያመለክተን የገበያ ዋጋ አካሄዱ የአቅጣጫ ለውጥ ሊያሳይ መሆኑ ሲሆን
በዋናነትም ልናገኘው የምንችለው ወደታች አቅጣጫ እየተጓዘ ባለ የገበያ ሁነት[Downtrend] ላይ ነው። በዚህም ይህ የሶስትዮሽ
የካንድል ስቲክ ምስረታ በዋናነት ወደታች እየሄደ ያለ የገበያ ሁነት መዳከሙንና አቅጣጫውን ወደላይ ሊቀይር ስለመሆኑ
ቅድመ ግምትን የምንወስድበት የፓተርን አይነት ሆኖ እናገኘዋለን።

ትክክለኛ ሊባል የሚችልን የዚህ ፓተርን ምስረታ ለመገምገምና ለማረጋገጥ የሚከተሉትን የገበያ ላይ ሁነቶች/ባህሪያት ያሟላ
መሆን ይኖርበታል።
1. ከሶስቱ ካንድሎች በቀዳሚነት የሚመሰረተው ካንድል ወደታች ረዘም ላለ ጊዜ ሲጓዝ በነበረ የገበያ ሁነት ላይ መፈጠር
ያለበትና ረጅም የሚባል ቢሪሽ ካንድል ስቲክ መሆን ይኖርበታል።
2. ሁለተኛው ካንድል ስቲክ በባህሪው ምንም እንኳን በጣም ጠንካራ የሚባል ባይሆንም ወደቡሊሽነት ያደላ ካንድል
መሆን ያለበት ሲሆን ቢያንስ ከመጀመሪያው ካንድል ስቲክ አጋማሽ በላይ ባለ የዋጋ እርከን ላይ መዝጋት ይኖርበታል።

ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ CRYPTOTALK-ET


ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ

3. የሶስተኛው እና የመጨረሻው የካንድል ምስረታ ደግሞ ከመጀመሪያው የካንድል ስቲክ መዝጊያ የዋጋ እርከን በላይ
ሆኖ መጨረስ እና መዝጋት የሚኖርበት ይሆናል። ይህም በዋናነት በገበያው ውስጥ የሚሳተፉ ገዢዎች ሀይል ከሻጮቹ
ሀይል ሙሉ ለሙሉ እንደበለጠ ተጨማሪ ማረጋገጫ የሚሆነን ይሆናል ማለት ነው።

ባለሶስት ውስጣዊ ዝቅታ[Three Inside Down] የካንድል ስቲክ ፓተርን ምስረታ


በተቃራኒው ይህ አይነቱ የካንድል ስቲክ ፓተርን ምስረታን የምናገኘው የገበያ እንቅስቃሴው ወደላይ አቅጣጫ እየሄደ ባለበት
ሁነት እና ረዘም ላለ ጊዜ በዚሁ የገበያ አካሄድ የቆየ ከሆነ ይሆናል። ይህም ማለት በዋናነት ይህ አይነቱ የካንድል ፓተርን ምስረታ
ከፍ ባለ የገበያ ዋጋ እርከን አካባቢ በሚፈጠርበት ጊዜ የገበያ አካሄዱ አቅጣጫውን ወደታች ሊቀይር ስለመሆኑ አስቀድመን
ቅድመ ግምታችንን እንድናስቀምጥ የሚረዳን የካንድል ስቲክ ፓተርን አይነት ነው።

ትክክለኛ ሊባል የሚችልን የዚህ ፓተርን ምስረታ ለመገምገምና ለማረጋገጥ የሚከተሉትን የገበያ ላይ ሁነቶች/ባህሪያት ያሟላ
መሆን ይኖርበታል።
1. ከሶስቱ ካንድሎች በቀዳሚነት የሚመሰረተው ካንድል ወደላይ ረዘም ላለ ጊዜ ሲጓዝ በነበረ የገበያ ሁነት ላይ መፈጠር
ያለበትና ረጅም የሚባል ቡሊሽ ካንድል ስቲክ መሆን ይኖርበታል።
2. ሁለተኛው ካንድል ስቲክ በባህሪው ምንም እንኳን በጣም ጠንካራ የሚባል ባይሆንም ወደቡሪሺነት ያደላ ካንድል
መሆን ያለበት ሲሆን ቢያንስ ከመጀመሪያው ካንድል ስቲክ አጋማሽ በታች ባለ የዋጋ እርከን ላይ መዝጋት ይኖርበታል።
3. የሶስተኛው እና የመጨረሻው የካንድል ምስረታ ደግሞ ከመጀመሪያው የካንድል ስቲክ መዝጊያ የዋጋ እርከን በታች
ሆኖ መጨረስ እና መዝጋት የሚኖርበት ይሆናል። ይህም በዋናነት በገበያው ውስጥ የሚሳተፉ ሻጮች ሀይል ከገዢዎቹ
ሀይል ሙሉ ለሙሉ እንደበለጠ ተጨማሪ ማረጋገጫ የሚሆነን ይሆናል ማለት ነው።

ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ CRYPTOTALK-ET


ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ

ምዕራፍ አምስት
5.1. ካንድል ስቲኮች፤ ሰፖርት እና ሬዚስታንስ
በዚህ ምዕራፍ በመሰረታዊነት ምንነታቸውን ለማንሳት የሞከርናቸው የካንድል ስቲክ ፓተርኖች በግብይት ውስጥ እንዴት
ጥቅም ላይ ሊውሉ እንደሚችሉ እና እንዴት በእነዚህ ጥናቶች ላይ ተመስርተን ትርፋማ የሚያረገንን የግብይት ውሳኔዎች
መወሰን እንደምንችል የሚዳሰስ ይሆናል።

እዚህ ጋር መታወስ ያለበት እና ተሰምሮበት ሊታለፍ የሚገባ ጉዳይ ቢኖር ካንድል ስቲኮችን ለብቻቸው ከግምት በማስገባት
እነሱ የሚሰጡንን የገበያ ባህሪይ በመመልከት ብቻ መገበያየት ፈፅሞ ሊሆን የማይገባው፤ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ የሚያመዝን
እና ለኪሳራ የሚያጋላጥም ጭምር ሊሆን እንደሚችል ነው። በዚህም አንድ ተገበያይ ሁሌም ቢሆን እነዚህ ካንድል ስቲኮች
ከሚያሳዩት ባህሪያት ባለፈ የገበያውን ከባቢ መገምገም እና የገበያ ዋጋው እያሳየ ያለው ባህሪ ቀረብ ብሎ ማጥናት በግብይት
ጥናታችን ውስጥ የውዴታ ግዴታ ሆኖ እናገኘዋለን። በዚህም ልክ እንደማንኛውም የገበያ ማጥኛ ቴክኒካል ኢንዲኬተር ወይም
ማጥኛ ግብአት ካንድል ስቲኮች ገበያው አቅጣጫውን ሊቀይር ስለመሆኑ አልያም በነበረበት አካሄድ እንደሚቀጥል ቢያሳየን
እንኳን ሁሌም ይህ ሁነት ሲከሰት ይሆናሉ ያልናቸው ሁነቶች ይከሰታሉ ማለት እንዳልሆነ ልብ ሊባል ይገባል። ማስታወስ ያለብን
የፎሬክስም ሆነ አብዛኛዎቹ የፋይናንሳዊ ግብይቶች ምንም አይነት የገበያ ስነ ልቦና ሊፈጠርባቸው የሚችል እና በጣም ብዙ
ተለዋዋጭ ሁነቶች ሊታዩባቸው የሚችሉ ሁነቶች መኖራቸውን ነው።

5.2. ካንድል ስቲኮችን ከሰፖርት እና ሬዚስታንስ ጋር በማዋሀድ እንዴት መገበያየት ይቻላል?

ካንድል ስቲኮችን በመጠቀም ከሚደረጉ የገበያ ጥናቶች ውስጥ እጅግ ቀላሉ እና ለመረዳት ከባድ ያልሆነው ሁነት ከሰፖርት እና
ሬዚስታን ጋር ጥቅም ላይ ስናውላቸው ነው። ይህም የሆነበት ዋናው ምክንያት የሰፖርት እና ሬዚስታንስ የዋጋ እርከኖች በዋናነት
በገበያ ውስጥ ያሉት ገዢዎች እና ሻጮች ራሳቸውን ከኪሳራ የሚከላከሉበትን እርከን የሚያሳዩን እንደመሆናቸው እና በዚህም
እነዚህ የዋጋ እርከኖች አካባቢ የሚመሰረቱ የካንድል ስቲኮችን ባህሪያት በመመለከት የገበያ አቅጣጫውን አስቀድመን
ለመገመት ስለሚያስችሉን ነው።

ከዚህ በታች ትክክለኛ የሆነ የፎሬክስ ግብይት ምሳሌን እንውሰድ፤


በዚህ ምሳሌ ላይ ከታች በምስሉ እንደተመለከተው 1.4900 የዋጋ እርከን አካባቢ ጠንካራ የሆነ የሬዚስታንስ መስመር እንዳለ
መመለከት ይቻላል። የገበያ ምስረታው በዚህ ሁነት ባለበት ቅፅበት ጠንካራ ሬዚስታንስ በማየታችሁ ወደግብይቱ ለመግባት
ብትፈልጉም ይህንን የሬዚስታንስ እርከን የነካው የካንድል ስቲክ እጅግ ጠንካራ ባህሪ ያለው ቡሊሽ ካንድል በመሆኑ የገበያውን
ሁነት እና ምስረታ በትእግስት ለመጠበቅ ወሰናችሁ እንበል።

ይኸው ትእግስታችሁ ፍሬ አፍርቶ ከሁለት ካንድል ስቲኮች ምስረታ በኋላ አሪፍ የሚባል እና ከዚህ በፊት በነበረው ምእራፍ ላይ
የተመለከትነውን የባለሶስት ውስጣዊ ዝቅታ ፓተርን [Three Inside Down Pattern] ምስረታ ተመለከታችሁ እንበል። በዚህ
የፓተርን ምስረታ ዙሪያ ለመዳሰስ እንደተሞከረው ጠንካራ የሆነ የገበያ መውረድ ቅድመ ማስጠንቀቂያ መሆኑን

ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ CRYPTOTALK-ET


ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ

ተመልክተናል። የዚህን የፓተርን ምስረታ ልክ እንደአንድ የገበያ ሁነት ማረጋገጫ በመውሰድም በገበያው ውስጥ የነበራችሁ
ሸጣችሁ ወጣችሁ እንበል። በእርግጥም ብልህ ትሬደር በመሆናችሁ ከሬዚስታንስ እርከኑ ከፍ ብሎ ሪስካችሁን ለመቀነስ
በማሰብም ስቶፕ ሎስ አድርጋችኋል እንበል።

ከፍተኛ በሆነው የትእግስተኝነት አካሄዳችሁ እና በካንድል ስቲክ ምስረታ ላይ ባላችሁ እውቀት አማካኝነት የዚህን ግብይት
የአሸናፊነት እጣ ፈንታ ወደናንተ እንዲዞር ማድረጋችሁ እሙን ነው። ከሸጣችሁ በኋላ የሆነው እንመልከት ….

በሚያስገርም ሁነት የገበያ አካሄዱ ልክ አስቀድማችሁ ቅድመ ግምታችሁን እንዳስቀመጣችሁት ጥሩ የሚባል ትርፍን
ሊያስገኝላችሁ እንደቻለ መመልከት ይቻላል። ምናልባት በዚህ ምሳሌ ላይ ስለምን ሬዚስታንስ እና ሰፖርትን መመልከተ
ይጠበቅብኛል? ስለምን ካንድልስቲኮችን በመጠቀም ብቻ ትርፋማነቴን የትዬለሌ አላሳድግም? በካንድል ስቲኮች ብቻ ይህን
መሰሉን የግብይት ቅድመ ግምት መውሰድ ከቻልኩ እነዚህን የፓተርን ምስረታዎች ብቻ በመጠቀም ገንዘቤን ለምን
አላካብትም የሚል ጥያቄ ሊመጣባችሁ እንደሚችል እሙን ነው።

ለነዚህ እና መሰል ተያያዥ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ያህል ይህንኑ በምሳሌነት የወሰድነውን ሃሳባዊ የግብይት ምሳሌ
እንመልከትና በቀጣይ የመጡትን የገበያ ምስረታ ሁነቶች ለመመልከት እንሞክር።

ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ CRYPTOTALK-ET


ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ

የካንድል ስቲክ ምስረታዎቹን በማየት እና የተለየ ባህሪን የሚያሳዩትን ካንድሎች ነጥሎ ምልክት በማድረግ የትርፋማነት
እድላቸው የሰፋ ምስረታዎችን ለይታችሁ አስቀመጣችሁ እንበል።

ይሁንና ከላይ በምልክት የተቀመጡትን የካንድል ምስረታዎች ሁሉ ከካንድል ስቲኮቹ ባህሪያት አንፃር ትክክልኛ አካሄድ ቢሆንም
እንኳን ተገበያይታችኋቸው ከሆነ በእያንዳንዱ ግብይቶቻችሁ ሁሉ ኪሳራን ተከናንባችኋል ማለት ነው። በቀላሉ ግን ጠንካራ
የሚባሉ የሬዚስታንስ እና ሰፖርት እርከኖችን በመለየት በእነዚህ የዋጋ እርከኖች የታገዘ ግብይት የሚደረግ ከሆነ ካንድሎቹን
ለብቻ በመጠቀም ከሚደረገው ግብይት በብዙ እጥፎች በግብይቱ ትርፋማ ልንሆን የምንችልበትን እድል ማስፋት እንችላለን
ማለት ነው። ይህንን ሁነት እንደፊቦናቺ የዋጋ እርከኖች በመሳሰሉ በተለይ በዋናነት የሰፖርት እና ሬዚስታንስ ቦታዎችን ለመለየት
በሚያገለግሉን የገበያ ማጥኛ ግብኣቶች በመታገዝ የበለጠ ውጤታማ የሆነ ግብይትን ማከናወን እንደሚቻልም ልብ ይሏል።
ይህ መድብል በዋነኝነት ለአዳዲስ አንባቢያን እንደመዘጋጀቱ መጠን የተለያዩ መደናግሮችን እንዳይፈጥር ለዚህ ክፍል በአጭሩ
እንቋጨው እንጂ፤ ይህንን እና መሰል የአጠናን ዘዴዎች እሳቤዎቹ ወደሚያሰረዳው የመፅሀፉ ክፍል ስንደርስ በድጋሚ ሰፋ ባለ
ሁነት የምናነውሳው ይሆናል።

5.2. አዳዲስ ትሬደሮች ላይ የሚስተዋሉ ካንድልስቲኮችን በመጠቀም ዙሪያ የሚደረጉ ስህተቶች

እንደሚታወቀው የጃፓናውያን ካንድል ስቲኮች እጅጉን ስሙ የገነነ የቴክኒካል አናሊስስ ጥናት ማድረጊያ የቻርቲንግ ቴክኒክ
ሲሆን በተለይም የገበያ ዋጋው ያደረገውን ያለፈ እንቅስቃሴ በመመልከት ወደፊት ወዴት አቅጣጫ ሊሄድ እንደሚችሉ በቀላሉ
ቅድመ ግምት ለመስጠት የሚያገለግሉን ግብአቶች እንደሆኑ ይታወቃል። ምንም እንኳን በትክክለኛው መንገድ ላጠናቸው እና
ለተጠቀማቸው እጅጉን ጠቃሚ የገበያ ማጥኛ ግብአቶች ቢሆኑም ብዙ አዳዲስ ትሬደሮች ግን እነዚህኑ የገበያ ዋጋ ማጥኛ
የቻርት ግብአቶች በተሳሳተ መልኩ ሲጠቀሙት ማስተዋል አዲስ አይደለም። እስቲ ከእነዚህ የተለመዱ ስህተቶች መካከል ዋና
ዋናዎቹን እና በብዛት በትሬደሮቹ ሲከወኑ የምንመለከታቸውን ስህተቶች ከዚህ በታች በተወሰነ መልኩ ለማንሳት ይሞከራል።

5.2.1. አዳዲስ ትሬደሮች በእያንዳንዱ በተመሰረቱ ካንድል ስቲኮች ውስጥ የሆነ አንዳች የገበያ ትርጉም
መፈለጋቸው እና በሁሉም ላይ ሁሌም የሆነ ትርጉም ይኖራል ብለው ማሰባቸው፡
በብዙሀኑ የገበያ ሁነቶች የገበያ ዋጋው ዝም ብሎ በስነልቦና ላይ ጫና ከመፍጠር ባለፈ የተለየ ሁነት ላይፈጠርበት መቻሉ ለዚህ
ስህተት መበራከት እና የተለመደ መሆን አንዱ ምክንያት ነው። በተለይም የወደፊቱን የገበያ ዋጋ ሁነት እና እንቅስቃሴ ለማወቅ
እያንዳንዱ በገበያው ውስጥ የሚፈጠሩ የካንድል ስቲኮች ሁሉ የሚሰጡትን ትርጉም መለየት ይቻለኛል ይቻለኛል ማለት ዘበት
ነው። ይህም በዋናነት በገበያው ውስጥ ያለው ስነልቦናዊ መዋቅር እጅጉን የተለያየ መሆኑ አንዱ ምክንያቱ ነው።

ታዲያ እያንዳንዱን የካንድል ስቲክ ምስረታዎች ከግምት ውስጥ ከማስገባት ይልቅ፤ በተለየ ሁነት በተለይም ጠንካራ በሚባሉት
የሰፖርት እና ሬዚስታንስ እርከኖች አካባቢ የሚመሰረቱትን የካንድል ስቲክ ምስረታዎች ትኩረት በመስጠት ተመልከቷቸው።

ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ CRYPTOTALK-ET


ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ

በዚህም ከዚህ መሰሉ ስህተት ለመታቀብ በመጀመሪያ በአንደኛ ክፍል ትምህርት ላይ እንደተመለከተው እነዚህን የሰፖርት እና
ሬዚታንስ መስመሮች ከለዩ በኋላ በዚህ ክፍል የተዳሰሱትንም ሆነ ሌሎች የካንድል ፓተርን ምስረታዎችን በመፈለግ ግብይቶችን
ማድረግ ብልሀትን የቀላቀለ ግብይት ነው ማለት ይቻለናል።

5.2.2. አዳዲስ ትሬደሮች በገበያው ውስጥ ያላችው ምልከታ አዲስ እንደመሆናቸው እጅጉን
የጠነከረ/የከረረ መሆኑ
በአንዳንድ ሁነቶች አዳዲስ ትሬደሮች በቻርቱ ላይ የተለየ የካንድል ምስረታ የተመለከቱ ይመስላቸውና ቻርቱን በማግዘፍ ብዙ
አተያዮችን ሲያዩት፤ ለመረዳትም ሲሞክሩ ይስተዋላል። ይሁንና በዚህ መሰሉ ሁነት ከሞላ ጎደል ምንም አይነት የተለየ የገበያ
እንቅስቃሴ የማያዩበት እድል የሰፋ ሆኖ እናገኘዋለን። በመፅሀፍት ላይ የተማርናቸው የካንድል ስቲክ ፓተርን ምስረታዎች
እራሳቸውን እንዲመስሉ እና እዚም እዛም እንድናገኛቸው መፈለግም ሌላው የአዳዲስ ትሬደሮች የተሳሳተ ምልከታ ሲሆን
ለግብይት አዲስ የሆኑ ተገበያዮች በዋናነት ትኩረት መስጠት የሚኖርባቸው በገበያው ውስጥ ለመግዛት በሚወስኑበት ወቅት
ጠንካራ የሆነ የግዢ ግፊት መኖሩን የሚያረጋግጥላቸው የገበያ ሁነት፤ ለመሸጥ በሚወስኑበት ወቅትም ጠንካራ የሆነ የመሸጥ
ግፊት መኖሩን የሚያረጋግጥላቸውን የገበያ ሁነት ማግኘቱ ላይ መሆን ይገባዋል።

5.2.3. አዳዲስ ትሬደሮች በገበያው ውስጥ ያላችው ምልከታ አዲስ እንደመሆናቸው እጅጉን የተዳከመ
መሆኑም ሌላው ችግር ሆኖ ይስተዋላል።
በአንዳንድ የገበያ ሁነቶች በሶስት ካንድል ስቲኮች አማካኝነት መመስረት የሚኖርባቸው የጃፓናውያን ካንድል ስቲኮች በአምስት
ካንድል ስቲኮች ምስረታ ሊጠናቀቁ ይቻላሉ። ይህ ማለት በተለይ ከትምህርቱ እና ከጀረባ ከያዘው የስነልቦናዊ እውቀት ጋር
ይበልጥ በተቆራኛችሁ ቁጥር የምትመለከቱት ሁነት እንዳለ ማመላከቻ ነው። ይህም ለምሳሌ በዋናነት በመፅሀፉ እሳቤ በሶስት
ካንድል ስቲኮች ይመሰረታል ያልነው የገበያ ሁነት በአራት ካንድል ስቲኮች ያንኑ የገበያ ባህሪይ ሊያሳይ እንደሚችል ማወቅ
ያስፈልጋል። ለዚህም ነው በተለይ የነዚህ የግብይት ምስረታ ሁነቶች ከመሸምደድ ይልቅ ከአመሰራረታቸው ጀርባ ያለውን
ስነአመንክዮአዊ ምክንያት መረዳት እና ማወቅ ላይ ማተኮር አስፈላጊ እና ወሳኝ ሆኖ የሚገኘው።

5.2.4. አዳዲስ ትሬደሮች ዛፎቹ ላይ በማተኮር ተጥደው ደኑን ለማየት ሲቸገሩ ይስተዋላል።
ለምሳሌ በአጭር የጊዜ ገደብ ባለ አምስት ደቂቃ ቻርትን የሚገበያይ የአጭር ጊዜ ትሬደር የሆነ አንድ አዲስ ትሬደር በተለየ ሁነት
ከፍ ባሉት የግብይት የጊዜ ገደቦች ላይ ያለውን የዋጋ እንቅስቃሴ ማየት ግድ ይለዋል። ይህም በዋናነት የሆነበት ምክንያት
በአንድ የጊዜ ገደብ ለምሳሌ በአምስት ደቂቃው ታይም ፍሬም ላይ የምንመለከተው የገበያ ዋጋ ምስረታ ሙሉ ለሙሉ በሚባል
ደረጃ ከ15 እና 30 ደቂቃው አልያም ከአንድ ሰዓቱ እና ከአራት ሰዓቱ ቻርት እጅጉን የተለያየ መሆኑ ነው። በዚህም እንደአዲስ
ተገበያይ የገበያ ላይ ምልከታችሁን እጅግ የጠበበ አልያም በአንድ ማዕዘን በኩል ብቻ የሚመለከት መሆን እንደሌለበት
ማስታወስ ግድ ይላል።

5.2.5. አዳዲስ ትሬደሮች የግብይት ማረጋገጫዎችን አይመለከቱም።


ከካንድል ስቲክ ፓተርን ምስረታ ጥናት ጋር በተነናኘ ልናነሳቸው የምንችላቸው በመመስረታቸው ብቻ በራሳቸው
እንደማረጋገጫ ሊወሰዱ የሚችሉ የካንድል ፓተርኖች ሊኖሩ ቢችሉም አብዛኛዎቹ የካንድል ፓተርን ምስረታዎች ግን ተጨማሪ
የማረጋገጫ ሁነቶችን መመልከት የሚያስገድዱ ሆነው እናገኛቸዋለን። በዚህም ካንድል ስቲክ ላይ የተመሰረተ ግብይት
በማድረጉ ሂደት ፓተርኑ ተመስርቶ አልቋል የሚል ውሳኔን ለመወሰን ከዚህ ውሳኔም በመነሳት ወደግብይት ለመግባት በፓተርን
ምስረታ ውስጥ ከግምት የሚገቡት ካንድሎች ሁሉ መዘጋታቸው እና ምስረታቸው ማለቁን ማረጋገጥ ግድ ይላል። ሁሌም
ቢሆን የገበያ ዋጋው እኛ ወደምንፈልገው አልያም ይሄዳል ብለን ቅድመግምታችንን ወዳስቀመጥንበት አቅጣጫ እየሄደ
ስለመሆኑ ትክክለኛ ማረጋገጫን ልንይዝ ይገባናል። ለምሳሌ በምናጠናው የገበያ ቻርት ላይ የቲዊዘር ቦተም የካንድል ፓተርን
ሲመሰረት ብናስተውልም ትክክለኛው የአገበያየት ሁነት ግን ይኸው ባለሁለት ካንድል የፓተርን ምስረታን በልጦና ከፍ ብሎ
የሚዘጋ ሌላ ተጨማሪ የካንድል ምስረታ መኖሩን አረጋግጦ ወደገበያው መግባት የተሻለ የትርፋማነት እድል እና አነስተኛ
የመክሰር ሁነት እንዲኖርብን ሊረዳን ይችላል ማለት ነው።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በተለይ በቀጣይ ክፍሎች ላይ የሚነሱ የተለያዩ የግይብት እሳቤዎች በመጨመሩ ሂደት ለማረጋገጫነት
የሚያገለግሉንን ግብአቶች የሚዳሰሱ ይሆናሉ።

ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ CRYPTOTALK-ET


ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ

ለተጨማሪ የክሪፕቶከረንሲ እና ፎሬክስ ግብይት እንዲሁም የብሎክቼይን ቴክኖሎጂ የአማርኛ መማሪያ ግብአቶች
ቀጣይ በተቀመጡት ሊንክ ላይ የኮሚዩኒቲያችንን አጠቃላይ የማህበራዊ ሚዲያ መገኛዎች በአንድ ላይ ማግኘት
ይችላሉ። https://www.linktr.ee/cryptotalket

ፎሬክስ 101 በጩጬ ፒፕስ ፡ ካንድል ስቲክ CRYPTOTALK-ET

You might also like