Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 59

አጫጭር ታሪኮች

የ12 ዓመቷ ታዳጊ ዘውትር በእጇ ቅጠላ ቅጠልና የተለያዩ ዕቃዎች ይዛ በዚህ መንገድ
ታልፋለች:: በአካባቢው ወዳለው የቀበና ወንዝ በመውረድ መጫወት ያስደስታታል:: እናቷ ግን አይለቋትም:: ቢሆንም
እሳቸውን ተደብቃ መሔዷን አላቋረጠችም:: የአዕምሮ
ህመምተኛ ናት:: ይህቺን ልጅ አይቶ የማያዝንላት ሰው የለም:: ቀይ ቆንጆና የደስደስ ያላት ታዳጊ ናት:: የምታወራውን
ነገር አታውቀውም:: እናቷ ዘውትር እያዩዎት ያለቅሱ የነበር ቢሆንም አሁን አሁን የሆነውን በፀጋ ከመቀበል ሌላ አማራጭ
እንደሌላቸው በመገንዘባቸው ዝምታን
መርጠዋል:: ብዙ ጸበል ሞክረው አልተሳካላቸውም::

ይቺን ህፃን የሚወዳት የዚህ ሰፈር ወጣት አለ ቀበና ሰፈር 24 ዓመቱ ነው:: ዘውትር
ከረሜላ ይገዛላታል:: እሷም ትወደዋለች:: ያጫውታታል:: ሣንቲም ይሠጣታል:: ብዙ
ጊዜ ከአይኑ እንድትጠፋ አይፈልግም:: አንድ
ቀን ከመንገድ ሲመለስ ወንዝ አካባቢ ጫወታ ላይ ሳለች ከረሜላ እንደሚገዛላት
ነግሮ ይዟት ወደ ቤቱ መጣ:: በዚህ ወቅት ግን የለመደችውን ከረሜላ አልገዛላትም:: የገባውን ቃል አላከበረም:: ይልቅስ
መጥፎ
ድርጊት ተፈጠረ::

አልጋው ላይ ካስወጣት በኇላ ልብሶቿን አስወልቆ ደፈራት:: ክብረ ንፅህናዋ ተገሰሰ:: አሟታልና ጮኸች:: ከዚያን በኋላ
ግን ከኪሱ ከረሜላ አውጥቶ ሲሰጣት ረሳችው:: ከቤቱ አውጥቶ ወደ ቤቷ ሰደዳት::

ከአንድ ሰዓት በኋላ ቤቱ በሀይል ተደበደበ:: ደነገጠ:: ወጣቶች ናቸው:: አንገቱን ይዘው አወጡት:: ፖሊስ ነበር:: ይዘውት
ሄዱ:: የፈፀመውን ድርጊት አመነ:: ታዳጊዋ ቀሚሷ ላይ ደም ስለታየ እናቷ ምን እንደሆነች ጠይቀዋት ይህ ግለሠብ
ያደረጋትን ነግራቸው ስለ ነበር ነው ለጎረቤት ሁኔታውን አሳውቀው ፖሊስ ጣቢያ የሄዱት:: ይህ ጨዋ መሳይ ወጣት
ለፍትወቱ ጥማት ሲል ህፃን ለዚያውም የአዕምሮ ህመምተኛዋን በመድፈሩ : ይህም በራሱና በማስረጃ በመረጋገጡ ፍርድ
ቤት የ12 ዓመት ፅኑ እስራት አከናንቦ ዘብጥያ ልኮታል:: ዕውን የአዕምሮ ህመምተኛው ከህፃኗና ከርሱ ማነው?

+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
+++++++++++++++

የዘናጭ ልጅ ልቅሶ

እናቱ ለአሥራ አምስት ዓመት ልጇ የአክስቱን ሞት እንዴት እንደምትነግረው ተጨንቃለች፡፡ ይህቺ የአባቱ እኅት
የሆነችው የልጁ አክስት ልጅ አልነበራትምና እንደ ልጇ ታየው ነበር፡፡ አብራው ኳስ ታያለች፤ አብራው ትዝናናለች፣
አብራው ታጠናለች፣ አብራው ትዋኛለች፣ አብራው ፊልም ታያለች፣ አብራው ኳስ ትጫወታለች፡፡
እንዲህ የምትሆንለትን አክስቱን ሞቷን ሲሰማ ያብዳል ብላ እናቱ ተጨንቃለች፡፡ እናም ትንቆራጠጣለች፡፡ ከትምህርት
ቤት ሲመጣ መጀመርያ መክሰስ አበላችውና ወደ መኝታ ቤት ወሰደችው፡፡ ከዚያም በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ መኖርና
መሞት ያለ መሆኑን፤ አንዳንድ ጊዜ የምንወዳቸው ሰዎች ሊሞቱ እንደሚችሉ ትነግረው ጀመር፡፡ ልጁ ግራ ገባው፡፡
‹እይውልህ ልጄ› አለች እናቱ ድምጽዋ ሆድዋ ውስጥ ገብቶ ሊጠፋ እየደረሰ፡፡ ‹‹ያች የምትወድህና የምትወዳት አክስትህ
በድንገት ትናንት ማታ ዐረፈች›› አለችው፡፡
‹‹ምን?›› አለና ሶፋው ላይ ተደፍቶ ድምጽ ሳያወጣ አለቀሰ፡፡ ከዚያም ከተደፋበት ተቃንቶ አንገቱን ሰበረና ይነቀንቅ
ጀመር፡፡
እናቱ የሚያደርገውን ሁሉ እንዲሁ ትከታተላለች፡፡ እንደሰማ አገር ይያዝልኝ ይላል፤ በድንጋጤ አቅሉን ይስታል፤ መሬት
ላይ ይፈጠፈጣል፤ ዓባይ ዓባዩን ያነባዋል ብላ ነበር የጠበቀችው፡፡ እንዲህ ቢሆንባት ምን ማድረግ እንደምትችል ነበር
ስትጨነቅ የቆየችው፡፡ አንዳንድ ጎረቤቶቿንም ስትጠራቸው መጥተው እንዲረዷት ተማጽናቸው ነበር፡፡
ሁሉም ግን እንዳሰበችው አልሆነም፡፡
‹‹አንተ፣ ያች እንደዚያ የምታሞላቅቅህ አክስትህ ሞታ እንዲህ ነው የምትሆነው›› አለችው ተናድዳ፡፡
‹‹ምን ሆንኩ?››
‹‹አታለቅስም እንዴ?››
‹‹እያለቀስኩ አይደል እንዴ፤ ዕንባዬን አታይውም››
‹‹ለእርሷ እንደዚህ ነው የምታለቅስላት፤ ማፈሪያ ነህ፡፡ እርሷኮ ላንተ ያልሆነችው የለም፡፡ እንደ ሕጻን አብራህ
ትጫወታለች፤ እንደ ጓደኛ ፊልም ቤት ይዛህ ትገባለች፤ እንደ እናት ትሳሳልሃለች፤ ለእርሷ እንደዚህ ነው የምታለቅሰው››
እናቱ አዝና ሶፋው ላይ ዘርፈጥ ብላ ተቀመጠች፡፡
‹‹ታድያ እንዴት ነው ለርሷ የሚለቀሰው?›› አላት ዕንባውን እየጠረገ፡፡
‹‹እትዬ እትዬ፤ ጉድ አደረግሽኝ፤ ሳትነግሪኝ፤ ምነው ጥለሽኝ ሄድሽ፤ እየተባለ ነዋ››
‹‹እንዴ እማዬ እንዴት ልትነግረኝ ትችላለች? በድንገት ነው የሞተችው አላልሽኝም? ደግሞስ ጥለሽኝ ሄድሽ ማለት ምን
ማለት ነው? እና ይዛኝ እንድትሄድ ፈለግሽ?››
እናቱ አፏን እጇ ላይ ጭናለች፡፡
‹‹አይ የዛሬ ዘመን ልጆች፤ የልቅሶው ወግ እንደዚህ ነው፤ የቅርብ ዘመድ እንዲህ ነው የሚያለቅሰው፤ የሸንኮሬ ልጅ ‹ጥሪኝ
አክስቴ ጥሪኝ› እያለ ጠዋት ሲያለቅስ ባየኸው››
‹‹እንዴ እርሱ ደግሞ ምን ነክቶታል፡፡ ባለፈው ‹ና ግቢውን እናጽዳ› ብላ ስትጠራው ያልመጣውን አሁን የት ነው ጥሪኝ
የሚላት? ውሸታም ነው፡፡ አሁን አንቺ ብትጠራሽ ትሄጃለሽ?››
እናቱ አማተበች፡፡ ‹‹ደረቅ ነህ ልጄ፤ ደረቅ ነህ፤ ነውር ነው፣ በእውነት ነውር ነው እንደዚህ አይባልም፡፡ በዚህ ዓይነት
ለእኔም ጊዜ እንደዚሁ ነው›› ከልቧ አዘነች፡፡ ደግሞም ታያት፡፡ እርሷ ሞታ፤ ልጇ ዝም ሲል፤ ሰው ሁሉ ዓይንህን ላፈር
ሲለው፡፡ ‹አሁን የርሷ ልጅ ይኼ ይሁን› እያለ በዓይኑ አፈር ድሜ ሲያበላው፡፡ ታያት፡፡
‹‹እማዬ ግን አንቺ የምትፈልጊው ካሰብሽው ቦታ የሚደርስልሽ ልጅ ነው ወይስ ስትሞቺ የሚያለቅስልሽ? እኔን ሠራ ነው
ወይስ እንዳለቅስ? ደግሞም ያኔ የምሆነውን ያኔ ነው ማወቅ የሚቻለው፡፡ እኔ ማዘን ያለብኝ ለራሴ ነው ወይስ ለሰው?
ኀዘን እንደ ፊልምና ድራማ ለሕዝብ መታየት አለበት?››
‹‹እርሱማ ልክ ነበርክ ልጄ፤ ግን ሰው ይቀየምሃል፤ ዘመዶቻችን ይቀየሙሃል፡፡ በልቶ ካጅ፣ ወጭት ሰባሪ፣ እጅ ነካሽ
ይሉሃል ልጄ፡፡››
‹‹ይበሉኛ፤ እኔ የት እሰማቸዋለሁ››
‹‹እኔ እሰማለኋ››
‹‹አትስሚያቸዋ፤ ተያቸው››
‹‹እንዴት አድርጌ ልጄ፡፡ የሰው ምላስ መርዝ ነው ይገድላል፡፡ ዱላ ነው ይሰብራል፡፡ እኔ ልጄን በክፉ እንዲያነሡብኝ
አልፈልግም፡፡ የሰው ጥርስ ውስጥ ትገባለህ ልጄ፡፡ ደግሞ እርሷ ናት እንዲህ ያደረገችው ይሉኛል፡፡ የአባትህ ዘመዶች
ይጠምዱኛል፡፡ አንተስ ብትሆን አክስትህ ናት፤ እንዲያ የምትወድህ አክስትህ ናት፤ ምናለ ብታለቅስላት?››
‹‹ቆይ ግን አሁን ማልቀስ ያለብኝ ለእርሷ ነው ለእኔ››
‹‹እንዴት እንዴት?››
‹‹አጉራሼ፤ አልባሼ፤ ጠያቂዬ፤ ሆዴ፤ ደጋፊዬ እያሉ የሚያለቅሱት ለሟቹ አዝነው ነው ወይስ እነርሱ ስለቀረባቸው?
ማረፊያችን ነበርሽ፤ ማን ላመትባል ይጠራናል ብሎ ማልቀስ አሁን ለሟች ነው ለራስ? ቆይ ግን ሰው ስለ ሰው
የሚመሰክረው ሲሞት በልቅሶ ዜማ ብቻ ነው እንዴ?››
‹‹የዛሬ ልጆች መፈላሰም ትወዳላችሁ እንዴው፤ አለቀሰ አላለቀሰም? የሚል እንጂ ለምን አለቀሰ? የሚል ዕድር እስካሁን
የለም፡፡ አቤት እገሌ እንዴት ቢወዳት ነው፤ አቤት እገሌ አለቃቀሱን ስትችልበት ይባላል እንጂ ለራሱ ነው ወይስ ለሟች?
ተብሎ ድንኳን ውስጥ አይጠየቅም፡፡ ይኼው በቀደም አንዱ የነ እትዬ የሰው ሐረግ ድንኳን ገብቶ ለያዥ ለገራዥ
እስኪያስቸግር መሬት እየወደቀ ሲያለቅስ ቆየ፡፡ ሰው ሁሉ ምን ቢዋደዱ ነው እስኪል ድረስ፡፡ ማን ይገላግለው፡፡ ሰውን
ሁሉ ዕንባ በዕንባ አራጨው፡፡ በመጨረሻ በቄስ ተገዝቶ አቆመና ቀና ሲል ሰዎቹንም አያውቃቸውም፤ ፎቶዋን
አያውቀውም፡፡ ለካስ ድንኳን ተሳስቶ ኖሯል፡፡ ይቅርታ ጠይቆ ወጣ አሉ፡፡ እዚያኛውም ሄዶ እንዲሁ ሲያለቅስ ነበረ
አሉ፡፡››
‹‹እና አሁን ይኼ በማያገባውና በማያውቀው ልቅሶ ገብቶ የሚያለቅሰው የፍቅር መግለጫ ነው?››
‹‹ባህሉ ነዋ ልጄ፡፡ መቼም ቢሳሳትም ልቅሶውን ሁላችንም አደነቅንለት፡፡ ወንድ ልጅ እንደዚህ ሲያለቅስ እኔ አይቼ
አላውቅም፡፡ ‹ዘመዶቹ ታድለው› ነው ያልነው፡፡ አስለቃሽም አያስፈልጋቸው፡፡ እኛን እንኳን የረሳነውን ሁሉ እያስታወሰ
አስለቀሰንኮ፡፡››
‹‹እሺ አሁን ምን አድርግ ነው የምትይኝ››
‹‹እንሂድና አንድ ጊዜ ብቻ ሰው እንዲያይህ ‹አጉራሼ አልባሼ› ብለህ ጯጩኸኽ እንገላገል››
‹‹እኔንኮ አላጎረሰችኝም፣ አላለበሰችኝም››
‹‹ይኼ ልጅ ምን ሆኗል ዛሬ፡፡ አብራህ አልነበረም ኳስ የምታየው? ከርሷ ጋር አልነበረም ፊልም የምትገባው? ደውለህ
ለርሷ አልነበረም እገሌ አገባ፤ እገሌ ተሸነፈ ትላት የነበረው? ሶደሬ አልወሰደችህም? ጌም አልጋበዘችህም? ዋና
አላስዋኘችህም? በጣም ታሳዝናለህ፡፡ እንዴት እንደዚህ ትላለህ?›› ተቀየመችው፡፡
‹‹እና ይኼ ማጉረስ ማልበስ ነው? የምጎርሰው ራሴ ነኝ፣ የምለብሰውም ራሴ ነኝ›› አላት፡፡
‹‹ኤዲያ፤ የስምንተኛው ሺ ልጆች፤ አባባሉንም አታውቁትም፡፡ ይህኮ አባባል ነው፡፡በል አሁን ከሄድክ እንሂድ ሰው ጥርስ
ውስጥ እንዳታስገባኝ፡፡ ››
‹‹እኔኮ አልችልበትም፡፡ እንደናንተ ማድረግ አልችልበትም፡፡ እናንተኮ የብዙ ዓመት ልምድ አላችሁ››
‹‹ሆሆይ›› ሳቋ መጣ ‹‹የመሥሪያ ቤት ቅጥር አደረግከው እንዴ ልምድ ምናምን የምትለው፡፡ ከልብ ካለቀሱ እንባ
አይገድም ሲባል አልሰማህም፡፡››
‹‹እሺ ሄጄ ምን ላድርግ?››
‹‹ድንኳን እስክንደርስ ዝም ትላለህ፡፡ ልክ ድንኳኑ አካባቢ ስንደርስ እኔ እጮኻለሁ፣ አንተም እኔን ተከትለህ ትጮህና
‹አልሰማሁም ነበር፤ አልሰማሁም ነበር› እያልክ ኡኡ ትላለህ››
‹‹እንዴ እማዬ ይኼው ሰማሁ አይደል እንዴ፤ ይኼማ ውሸት ነው፡፡››
‹‹ልጄ እኔ እናትህን ስማኝ፤ እንደዚያ ነው የሚባለው፡፡ አባባል ነው፡፡ ደግሞ በገላጋይ ካልሆነ በቀር ልቅሶህን
እንዳታቆም››
‹‹እንዴ ዝም በል እያሉኝ ልቀጥል? እንዲያውም ምክንያት ካገኘሁ ተገላገልኩ››
‹‹እንዲያውም ከቻልክ መሬት ውደቅ››
‹‹እንዴ እማዬ እኔ በረኛ አይደለሁ ለምን መሬት እወድቃለሁ››
‹‹በርህ ይጥፋና ባህል ነው አልኩህ፡፡ ሰው ያደንቅሃል፤ እንዲያውም ትንሽ ተንከባለል››
‹‹እማዬ አሁንስ አበዛሽው፣ ሳቄ ቢመጣስ፡፡ አንቺኮ የድራማ አክት የምታስጠኚኝ ነው የመሰልሽኝ››
‹‹በል ተወው ደግሞ ታዋርደኛለህ›› አለችና ወደ ምኝታ ቤት ገብታ ጋቢና ፎጣ ይዛ መጣች፡፡
‹‹በል እንካ ጋቢውን ትከሻህ ላይ፣ ፎጣውን አንገትህ ላይ አድርግ፡፡ ስታለቅስ በፎጣው ተሸፈን፡፡ ዕንባ እንኳን
ባይመጣብህ የሚያይህ የለም፡፡››
‹‹የልቅሶ ቤት ዩኒፎርም መሆኑ ነው›› አላት፡፡ ‹‹ሆሆ›› አለች አንገቷን እየነቀነቀች፡፡
ሄዱ፡፡ ልቅሶው ቤት በር ላይ ከመድረሳቸው በፊት አንድ ጓደኛው ደወለና የሆነ የእግር ኳስ ውጤት ነገረው፡፡ ውጤቱ
አስደሳች ነበር፡፡ እርሱን እያሰበ ድንኳኑ በር ላይ ሲደርሱ እናቱ ያስጠናችው ነገር ተረሳው፡፡ ጉዱ ፈላ፡፡ መኪናዋን ሲያዩ
ለቀስተኞቹ ተንጋግተው ከድንኳኑ ወጡና ከበቧቸው፡፡ እናት ከመኪናዋ እየጮኸች ወረደች፡፡ ልጁ ግን የሚባለው ነገር
ጠፍቶታል፡፡ ከእናቱ ጎን ሆነና በፎጣው ተሸፍኖ ‹‹እማዬ ምን ነበር ያልሽኝ፤ ስቴፑ ጠፋኝኮ›› አላት፡፡ እናቱ በዓይነ መዓት
አየችውና ጩኸቷን ቀጠለች፡፡
እርሱ ግን በአፉ እየጮኸ በልቡ ስቴፑን አሰበው፡፡ አልመጣለት አለ፡፡ ቀና ሲል የአክስቱን ፎቶ በአንድ አልቃሽ እጅ ላይ
አየው፡፡ ያን ጊዜ የሆነ የኀዘን ስሜት መጣበት፡፡ ልቡ ተንቦጨቦጨ፡፡ ትዝ አለው ነገር ዓለሙ፡፡ እናም ወደራሱ ልቅሶ
ተመለሰ፡፡
‹‹እትዬ እትዬ አይስክሬም ማን ይገዛልኛል፤ ሶደሬ ማን ይወስደኛል፤ ጌም ማን ያጫውተኛል፤ እትዬ እትዬ ኳስ ከማን ጋር
አያለሁ፡፡ ሩኒ ሲያገባ ለማን እነግራለሁ፤ ሮናልዶ ሲስት ከማን ጋር አወራለሁ፤ ሜሲ ሲያገባ ለማን እደውላለሁ፡፡ እትዬ
ደውይልኝ፤ ማን አገባ በይኝ፤ ማን ተጫወተ በይኝ፤ እትዬ፡፡ እትዬ ዛሬኮ ማንቼ ይጫወታል፤ ከማን ጋር አያለሁ፡፡ እትዬ
የዛሬው ጨዋታኮ ወሳኝ ነው›› አስነካው፡፡
ወዲያው አንድ በእርሱ እድሜ ያለ ልጅ ነጠር ነጠር እያለ መጣና በጆሮው ‹‹ማንቼ ተጫውቶ ቅድም ተሸነፈኮ›› አለው፡፡
ይህን ጊዜ መሬት ላይ ወድቆ እየተንከባለለ ‹‹እርምሽን ባትኖሪ ማንቼ ተሸነፈልሽ፤ እርምሽን ባትኖሪ ቫምፐርሲ ሳያገባ
ቀረ፡፡ እርምሽን ባትኖሪ ማንቼ ነጥብ ጣለ፡፡ የፈራሁት ይኼን ነበር፡፡›› ለቀስተኛው ሁሉ ልቅሶውን ቀስ በቀስ እየተወ
እርሱን ያየው ጀመር፡፡ እናቱ ግን ሾልካ የት እንደገባች አልታወቀም፡፡

+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++

እናቴ አንድ እይን ብቻ ነው ያላት በዛም የመጣ


በጣም እጠላታለው::አባቴ…አ ባቴ ደሞ የአራስ
ቤት ልጅ እያለው ነው የሞተው እሱ ከሞተ በኋላ
እኔና እናቴ በደሳሳ ጎጆዋችን ከድህነትጋ መኖር
ጀመርን::አባዬ ያስቀመጠው ገንዘብ ሲያልቅ
እናቴ በራችንጋ ትንሽዬ ሱቅ ከፍታ
መስራትጀመረች እማ ለኔ የማታደርግልኝ ነገር
የለም እኔ ግን በሷ አፍር ነበር ትዝ ይለኛል 5ኛ
ክፍል የወላጆች ቀን እናቴ ትምህርት ቤት አበባ
ይዛልኝ መጣች “እንዴት እንዲ ታደርገኛለች?
ማን ነይልኝ አላት?” ተሸማቀኩ በጥላቻ አይን
ገልምጫት እየሮጥኩ አዳራሹን ለቅቄ ወጣው::
በሚቀጥለው ቀን ት/ቤት ስመጣ ጓደኞቼ”እናቱ
1 አይን ነው ያላት”እያሉ ሲያወሩ ሰማዋቸው
በውስጤ ምናለ እናቴ ከዚች አለም ብጠፋ ብዬ
ተመኘው እቤት ስደርስም “ደስይበልሽ በጓደኞቼ
አሳቅሽብኝ….ቆይ እንድ አይንሽ የት ሄዶነው?
ሁሌ እንዲ ከምታሸማቂኝ ለምን አትሞቺም?”
ብዬ ጮህኩባት ምንም መልስ ሳትሰጠኝ
ወጣች::እንዲ ማለቴ ስሜቴን ቢኮረኩረኝም
ለረጅም ጊዜ ልላት ያሰብኩትን በማለቴውስጤን
ቀለል አለኝ
ብዙም ስሜትዋን የጎዳሁት አልመሰለኝምነበር
ያን ቀን ማታ ከእንቅሌፌ ተነስቼ ውሃ ልጠጣ
እቃ ቤትስገባ እናቴ እኔን ላለመቀስቀስ ቅስ ብላ
ስታለቅስ አገኘዋት ቅድም ባልኳት ነገር
እንደሆነ ገባኝ::
አሳዘነችኝ!
ድምፄን ሰምታ ቀና ስትል ካንዱ
አይንዋየሚወርዱ እንባዎቿን እየዋቸው::አይንዋ
በእንባ ተሞልቶ ሳየውይበልጥኑ ጠላኋት! በዛው
ቅፅበት ለራሴ እንድ ነገር ቃል ገባው አድጌ
ስኬታማ ስሆን እንድ አይናማዋን እናቴን ጥያት
እንደምሄድ!
ከዛን ቀን ጀምሮ ጠንክሬ መማር ጀመርኩ
እናቴን ትቻት ወደ ከተማ በመሄድ አለ በሚባል
ዩንቨርስቲ ውስጥ ስኮላርሺፕ አግኝቼ በነፃ
ትምህርቴን ተከታትዬ ጨረስኩ ጥሩ ስራ
ያዝኩ፤የራሴን ቪላ ገዛው ሚስት
አግብቼምልጆች ወለድኩ::አሁን የተመኘሁትን
የልጅነት ህይወት እየኖርኩ እገኛለው::በጣም
ደስተኛ ነኝ ምክንያቱም ገንዘብ አለኝ፤ቆንጆ ቤት
አለኝ፤ደስተኛ ቤተሰብ አለኝ ከሁሉም በላይ ግን
የምጠላትን እናቴን የማላገኝበት ሩቅ ቦታ
ነውናየምኖረው ደስተኛ ነኝ:: አንድ ቀን ግን
ያላሰብኩት ዱብ እዳ መጣብኝ “ምን?!
ማነው ?!” እናቴ ነበረች ፀጉሮችዋ ሸብተው
ከስታና የተቀዳደዱ ቆሻሻ ልብሶች ለብሳ መጣች
ላምን አልቻልኩም ቤቴን እንዴት አወቀችው?!
ህፃንዋ ልጄ ፈርታት ሮጣ ወደቤት ገባች
እንዳላወቀ በመምሰል “ሴትዮ ምን ፈልገሽ
ነው?
የሰው ቤት ዝም ተብሎ እይገባም እሺ ውጪልኝ
ከቤቴ!!”አልኳት ኮስተር ብዬ እናቴ ደነገጠች “
ይቅርታ ጌታዬ አድራሻ ተሳስቼ ነው” ብላኝ
ወጣች…..ተመስገን አላወቀችኝም::ይህ ከሆን
ካንድ ወር በኋላ ለድሮ ት/ቤቴ የመዋጮ
ፕሮግራም ተዘጋጅቶ የት/ ቤቱ ዳይሬክተር
ደውለው ጠሩኝና ሄድኩ ፕሮግራሙ ሲያልቅ
በዛውም ያደኩበት ቤት ምን እንደሚመስል
ለማየት ስሄድ እናቴ መሬት ላይ ተዘርራ
አገኘዋት::ሞታለች!! ምንም
አላላቀስኩም::እጇ ላይ ወረቀትአየውና አንስቼ
ማንበብ ጀመርኩ
ለኔ የፃፈችው ደብዳቤ ነበር…እንዲህ ይላል “ውድ
ልጄ,ካሁን በኋላ ሕይወት ማለትለኔ ምንም
አይደለችም::እንተ ወደምትኖርበት ከተማም
ተመልሼ አልመጣም::ልጄ ከምንም በላይ ግን
ናፍቆትህ ሊገድለኝ ነው ለምን አንድ አይን ብቻ
እንዳለኝ ጠይቀከኝ አልነገርኩክም ነበር
እውነታው ይህ ነው ልጄ…..ልጅ እያለክ ከባድ
የመኪና አደጋ ይደርስብክና አንድ አይንክ ይጠፋል
እንደማንኛውም እናት ያለ አንድ አይን ስታድግ
ማየት አልችልምና የኔን አይን አውጥተው ላንት
እንዲያረጉልህ ዶክተሮቹን ጠይቄ ፈቃደኛ ሆነው
አደረጉልህ…..
ለዚ ነው እንድ አይናማ የሆንኩብክ::እይዞህ ልጄ
ባደረካቸው ነገሮች ተቀይሜህ አላውቅም ነበር
ባለፈው እቤትክ መጥቼ የልጄን ልጅ በማየቴ
በጣም ተደስቻለው::ለወደፊትም በደስታ
እንደምትኖርም ተስፋ አደርጋለው::ልጄ እናትህ
በጣም ትወድሃለች”
…..አንብቤ ስጨርስ በሁለት እግሮቼ መቆም
አቃተኝ.እማ…..እማ……..እማ እንባዬን እየዘራው
ምስኪኗን እናቴን አቅፌ ተንሰቀሰኩ ለኔ ብላ
ህይወትዋን የሰጠችውን እናቴን በራሴ እጅ
ገደልኳት…
ሞራል: እናት ማለት እውነተኛ ፍቅር ናት::
ክብር ይገባታል የሷን ብድር በምድር ላይ ማንም
በምንም ሊከፍለው አይችልምና ከመሞቷ በፊት
የሚገባትን ክብር እንስጣት::
እስታውስ:ሁላችንም አንድ እናት ነው ያለችን::

አጫጭር ቀልዶች

ሚስት( ትደውልና) የማትረባ! ደደብ! የት አባክ ነው ያለከው?


-ባል፦ ፒያሳ ነኝ!
-ሚስት፦ እዛ ምን ትሰራለሀ?!
-ባል፦አንዴ ትዝ ካለሽ የሆነ ወርቅ ቤት አልጎበኘንም?
-ሚስት፦ አስታወስኩት ውዴ
ባል፦ የወርቅ ሀብል አይተሽ ወደድኩት ስትይ ገንዘብ ሳገኝ
እገዛልሻለው አላልኩም?
ሚስት፦አዎ የኔ ፍቅር.
ባል፦ ወርቅ ቤቱን አወቅሽው?
ሚስት፦አዎ ወለላዬ
ባል፦ከእሱ አጠገብ ያለው ግሮሰሪ ነኝ
የውሸታሞች ሙግት
አንደኛው ውሸታም፤
“የዛሬ 10 ዓመት አባቴ በህንድ ውቅያኖስ ላይ በመርከብ
ሲንሣፈፍ የእጅ ሰዓቱ ወድቆበት ከ10 ዓመት በኋላ ሲመለስ
በዋና ውኃ ውስጥ ገብቶ ሲፈልግ ሰዓቱ ምንም ሳይሆን
እየሠራ አገኘው ይለዋል”
ሁለተኛው ውሸታም፤
“ይገርምሃል የኔም አባት በዚሁ ውቅያኖስ ላይ ሲንሳፈፍ ወድቆ
ከ10 ዓመት በኋላ ምንም ሳይሆን በሕይወቱ ዋኝቶ
ወጣ፡፡”
አንደኛው ውሸታም፤
“እንዴት ያንተ አባት ሳይሞቱ ውኃ ውስጥ ሊኖሩ ቻለ፡፡ደግሞስ
ምን እየሠሩ ይሕን ያህል ዓመት ቆዩ” ብሎ ይጮህበታል፡፡
ሁለተኛው ውሸታም፤
“ውኃ ውስጥ እንኳን ሳይሆን አሣ ነባሪ ሆድ ውስጥ ነው
የቆዬው፣ ብቻ አንዳንድ ጊዜ ያንተን አባት ሰዓት እንዳይቆም
እየወጣ ይሞላ ነበር ሲል መለሰለት፡፡
————— ——

አንደኛው ውሸታም፤
“የኔ አባት በርሻው ቦታ ላይ አውሮፕላን የሚያህል ጥቅል
ጐመን አምርቶ አንደኛ ወጣ፡፡
ሁለተኛው ውሸታም፤
“የኔም አባትኮ በጋራዣችን ውስጥ ትልቅ አፍሪካን የሚያህል
ብረት ድስት አምርቶ ተሸለመ፡፡”
አንደኛው ውሸታም፤
“እንዴት! አፍሪካን የሚያህል ብረት ድስት ምን ያደርግላቸዋል?
ብሎ ጠየቀው፡፡
ሁለተኛው ውሸታም፤
“ታዲያ! ያንተ አባት ጥቅል ጐመን በምን ይቀቀላል ሲል
መለሰለት፡፡”

እሷ: ስንጋባ ጫት መቃምህን ታቆማለህ.


እሱ: እሺ
እሷ: ሲጋራም ማጨስ አትችልም
እሱ: እሺ
እሷ: የሰካራም ሚስት እንድባልም አልፈልግም ስለዚህ
መጠጥም ማቆም አለብህ
እሱ: እሺ
እሷ: ኧ!!! …ሌላ ደሞ ምን ነበር?? አዎ! እያመሸህ መግባት
አትችልም
እሱ: እሺ
እሷ: እም…ሌላ? ሌላ? ምንድነው የረሳሁት??? ሌላ
የምትተወው ነገር ምን ነበር???
እሱ: አንቺን ማግባት

ሚስት አምሽታ ወደቤት እየገባች ነው …


ወድያው የመኝታ ቤቷን ከፍታ ስትገባ
አልጋዋ ላይ ሁለት የተኙ ሰዎችን
ትመለከታለች፤ አራት እግሮች ከብርድ ልብሱ
ስር ወተው ይታያሉ
ከዝያም ወድያውኑ አጠገቧ ያለውን ዱላ አንስታ
ከብርድ ልብሱ ውስጥ ያሉትን ሁለቱን ሰዎች
ባላት ኃይል መደብደብ ትጀምራለች ..ወድያው
መደብደቡን ታቆምና ወደ ሳሎን ቤት ስትሄድ
ባሏ ሶፋ ላይ ቁጭ ብሎ ጋዜጣ ያነብ ነበር
ከዝያም ባልየው ” hi darling…ቤተሰቦችሽ
መተዋሉ
የኛ መኝታ ቤት ተኝተዋል ሰላም አልሻቸው ..?
ሲላት ሚስት በድንጋጤ እራሷን ስታ ወደቀች ::
“የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል አሉ”

Love In A Digital Age


ጎግዬ አስጎግዬ ያን ሰሞን ያጣኋት
አወይ አጋጣሚ CHAT ላይ አገኘኋት
ADD ያረኳትን ልጅ አምናና ካቻምና
አየኋት FACEBOOK ላይ ያቻትና ያቻትና
ONLINE አየናት ሲሉኝ ትላንትና
FACEBOOK LOGIN ብዬ አጣኋት ሄድኩና
አገኛት እንደሆን TWITTER ላይ ሄድኩኝ
አይኔ እንደናፈቃት ሳላያት አደርኩኝ
YOUTUBE ገብቼ SEARCH አድርጌ አጣኋት
TODAY እንደ ድንገት FACEBOOK ላይ አየኋት
ጎግዬ አስጎግዬ ዛሬ አጊንቻታለሁ
CHAT አድርጊው በሏት እኔ እሻላታለሁ

አለቃ ገብረ ሃና ከዕለታት አንድ ቀን መንገድ እሄዳለሁ ብለ ይነሣሉ፡፡ “ማዘንጊያ” ይላሉ ሚስታቸውን “አቤት” ይላሉ
ሚስት “መንገድ ልሄድ አስቤያለሁ” “ወዴት?” “ወደ ቆላ ወርጄ የታመመ ጠይቄ፣ የተጣላ አስታርቄ እመለሳለሁ!”
“እንግዲያው ባዶ ሆድዎን አይሄዱም ቆይ ቁርስ ደርሷል፡፡” “ባዶ ሆዳችንን አደል የተፈጠርን? “ቢሆንም ወንድ ልጅ
የሚገጥመው ስለማይታወቅ ባዶ ሆዱን አይወጣም” “ሴትስ የሚገጥማት ታጣለች ብለሽ ነው? ካልሽ እንግዲህ ቶሎ
አቅርቢልኝና ፀሃዩ ሳይገርር ልነሳ” ወ/ሮ ማዘንጊያ ጉድ ጉድ ብለው ቁርስ አቀረቡና አብረ በልተው ተሰነባብተው ተለያዩ፡፡
አለቃ ቆላ ወርደው የታመመ ጠይቀው የተጣሉትን ሁለት ሰዎች ሊያስ…ታርቁ ግቢያቸው ሲደርሱ ጭራሽ ተጋግለው
ቡጢ ሊቀማመሱ ግራ ቀኝ ሲሉ ያያሉ፡፡ ሰዎቹ አንደኛው የተማረና አዋቂ የሚባል ሰው ነው፡፡ ሌላኛው ምንም ያልተማረ
መሀይም ነው፡፡ መሀይሙ የተማረውን፡ “አንተ ደንቆሮ! ዶሮ ራስ!” ይለዋል፡፡ “አፍህን ዝጋ ነግሬሃለሁ!” ይላል
የተማረው “ደንቆሮ! ደደብ! ቆርቆሮ!” ይላል መሀይሙ፡ “ምንም ልሁን አፍህን ካልዘጋህ ዋጋህን ታገኛለህ!” አለቃ፤
“ተው እንጂ ተው አይሆንም!” ይላሉ ሊገላግ መካከል ገብተው፡፡ መሀይሙ አሁንም “ደንቆሮ! አለቃ፤ ይሄኮ ደደብ ነው!
ይላል፡፡ አለቃ፤ ሁለቱንም በተለያየ አቅጣጫ ገፍተይለያዩዋቸዋል፡፡ ይሄኔ አንድ መንገደኛ ድንገት ይደርሳል፡፡ አለቃ
ያውቃቸዋል፡፡ ወደሳቸው ቀረብ ብሎ፤ አለቃ ምን እያደረጉ ነው?” ሲል ይጠይቃቸዋል፡፡ አለቃም፤ “ስድብ ቦታውን
ስቶብኝ፤ ቦታ ቦታው እየመለስኩ ነው!” አሉ፡፡

የ80 ዓመት አዛውንት ለጠቅላላ የጤና ምርመራ (Checkup) ሆስፒታል ይሄዱና ሃኪማቸው “እንዴት ነው
ጤንነትዎ?” ሲል ይጠይቃቸዋል፡፡
ሽማግሌውም “በጣም ጤና ነኝ —እንደውም የ18 ዓመት ኮረዳ አግብቼልህ አርግዛልኛለች—-ልጅ ላገኝ ነው —
መታደል ነው አይደል?” ይሉታል – ለሃኪሙ፡፡ ሀኪሙ ነገሩ አልተዋጠለትምና ትንሽ ሲያስብ ከቆየ በኋላ “አንድ ታሪክ
አስታወሱኝ” በማለት ይነግራቸዋል፡፡
“አንድ እኔ የማውቀው አደን የሚወድ ሰውዬ ነበር፡፡ በቃ የአደን ነገር ጨርሶ አይሆንለትም፡፡

አንድ ቀን ለአደን ሲወጣ ታዲያ ጠብመንጃውን አነሳሁ ብሎ ዣንጥላውን ይዞ ይወጣል፡፡ ገና ጫካ ውስጥ እንደገባም
ከየት መጣ ሳይባል አንድ የተበሳጨ ድብ ፊትለፊቱ ገጭ ይልበታል፡፡ ከመቀፅበት ዣንጥላውን እንደጠመንጃ አስተካክሎ
ድቡ ላይ ያነጣጥርበትና እጀታውን ይጫነዋል—-ድቡ ወዲያው መሬት ላይ ጠብ ይላል” አላቸው ሃኪሙ፡፡
ሽማግሌውም “ይሄማ ሊሆን አይችልም! ድቡ ላይ የተኮሰው ሌላ ሰው መሆን አለበት!” አሉ – ጮክ ብለው፡፡
ሀኪሙም “የእርስዎም ነገር እኮ እንደዚያ መስሎኝ ነው” አላቸው፡፡

“የባል ኑዛዜ”

ባል ጣዕረ-ሞት ይዞት እያጣጣረ ሳለ ሚስቱን ያስጠራና “እንግዲህ እኔ መሞቴ ነው፤ አንቺ ግን ያለ ባል መቅረት
የለብሽም፤ እንዲያውም ያንን ኩራባቸውን አግቢ” ይላታል። በዚህ አባባል የተናደደችው ሚስት “አንተን ይማርልኝ እንጂ
እኔ አሁን ስለ ባል አላስብም! ደግሞ ባገባስ እንዴት ያንተን ዋነኛ ጠላት ኩራባቸውን አግቢ ትለኛለህ?” ስትል
ትጠይቀዋለች። በዚህ ጊዜ ጣር የያዘው ባል እያቃሰተ መለስ ብሎ “አንቺ ደሞ አይገባሽም እንዴ? ጠላቴ መሆኑንማ መች
አጣሁት? ልክ እንደ እኔ አንገብግበሽ እንድትገድይልኝ ነው እንጂ! አላት ይባላል። ኑዛዜ ይልሃል ይህ ነው! ከእንዲህ
አይነቱ ኑዛዜ ይሰውራችሁ ይሰውረን አሜን አሜን በሉ።

አንድ ሰካራም ለሚስቱ ይደውልና “መኪናዬን


መርካቶ አቁሜ ፣ ሌቦቹ አወላልቀው
ወሰዱት” አላት… “ምን ማለትህ ነው?”..
“በቃ ምንም አልተረፋቸውም! መሪው ፣
ሬዲዮኑ ፣ ምን አለፋሽ? ፊት ለፊት ያለው
ቦርዱን ጭምር ነው የዘረፉኝ።
እነዚህ ቅማላሞች! ፍሬኑና የቤንዚን
መስጫው እንኳን አልቀራቸውም”…
“እሰሰሰሰይ! ደግ አደረጉ! እየሰከሩ ማምሸት
ይቅርብህ ብዬህ አልነበረም!” ስትል ፤ ከት
ብሎ መሳቅ ጀመረ። “ምን ያስቅሃል?”…
“ይቅርታ! ለካ በኋላ በር ገብቼ ነው”
ልጅቷ በማታ ወደ ልጁጋ ትደውላለች

”እባክህ ሰሞኑን አንድ እረፍትና እንቅልፍ የነሳኝን ነገር ልጠይቅህ


ምናልባት ጥያቄው ሊከብድህ ይችላል(ልጁ ደንግጧል!!!) ምናልባት ደግሞ ከዚህ በኃላ ስለኔ የተለየ አመለካከት ሊኖርህ
ይችላል::ነገር ግን
በቃ ምንም ማድረግ አልችልም አንተ ምን እንደሚሰማህ ማወቅ ስለምፈልግ ነው..(……..ፊቱ ላብ በላብ)በጣም ለረጅም
ጊዜ ለመጠየቅ ፈርቼ በውስጤ አምቄው ኖሪያለው አሁን ግን ይበቃኛል..በቃ ከራስህ አንደበት ማወቅ አለብኝ እኔ ከዚ
በላይ መጎዳት የለብኝም..(ሰውነቱ እየተንቀጠቀጠ ነው) ብቻ አንተ ምንም ይህል ከባድ ቢሆን እውነቱን
ንገረኝ እኔ ምፈልገው ግልፅ እንድትሆንልኝ ብቻ ነው..
.
.
.
እናንተ ሰፈር በያይነት ስንት ነው?

አባት ወደቤት ሲገባ ሚስቱ ልጃቸውን እየመታችው ያገኛታል

አባት፡-” ለምንድነው የምትመችው? ምን አደረገ?”

ሚስት፡- “ይሄ ደደብ 1×1 ስንት እንደሆነ አያውቅም!”

አባት፡- “እና ለዛ ነው እንዲ ምትደበድቢው? አንቺ ታውቂያለሽ ስንት ነው 1×1?”

ሚስት፡- “11”

አባት፡- “በይ ተረፍሻል:: ብትሳሳቺ ኖሮ የሱን ያህል ነበር የምደበድብሽ”


አሮጊቷ ለዶክተሩ እይነገረችው ነው
“ዶክተር የሆነ ችግር አለብኝ እሱም ፈሴን መቆጣጠር
አልችልም በቃ በሄድኩበት ሁሉ መፍሳት ነው..በርግጥ ፈሴ ምንም አይነት ድምጽም ሆነ ሽታ የለውም ባይገርምህ ዶክተር
አንተ ቢሮ ከገባው ጀምሬ እንኳን 20 ጊዜ ያህል ፈስቻለው ግን አላወክም ምክንያቱም ፈሴ ሽታም ሆነ ድምጽ ስለሌለው
ነው::”
ዶክተር: “እቺን ክኒን ውሰዷት እና በሚቀጥለው ሳምንት ተመሱ”
አሮጊቷ ከ ሳምንት በኋላ ተመለሰች
አሮጊቷ:(በቁጣ) ምነው ዶክተር ምን አረኩህ የሰጠህኝን ኪኒን ከዋጥኩ ጀምሮ ፈሴ መሽተት ጀመረ በርግጥ ድምዕ
የለውም ቢሆንም በጣም ነው ሚሸተው”‘
ዶክተር:”በጣም ጥሩ አፍንጫዎት ተሽሎታል ማለት ነው አሁን ደሞ የጆሮ ልስጦት?

ሰውየው የሚስቱን ድመት በጣም ይጠላ ነበር….አንድ ቀን


ሚስቱ ሳታየው ድመቱን አውጥቶ ለመጣል ይወስናል በጠዋት
ተነስቶም ድመቱን 20 ኪሎሜትር ያህል ራቅ አድርጎ ይጥልና
በደስታ ይመለሳል እቤቱ ሲደርስ ግን ድመቱ ሶፋ ላይ ተኝቶ
ያገኘዋል..
በነጋታው ጠዋት ይነሳና ድመቱን 40 ኪሎሜትር ራቅ አድርጎ
ጥሎት ተመለሰ እቤት ሲደርስ ድመቱ እንደ ትላንቱ ሶፋ ላይ
ተኝቶ ያገኘዋል
በየቀኑ ራቅ ራቅ ወዳለ ቦታ እየጣለው ያመጣል ድመቱ ግን
ሁሌም ቀድሞት እቤት እንደገባ ነው::
በመጨረሻም በጣም ይመረውና ድመቱ አያውቀውም ብሎ
ወደሚያስብበት ሩቅ ቦታ ሊጥለው ይወስናል ብዙ
ኪሎሜትሮችን ከተጓዘ በኃላ ወደ ቀኝ ታጠፈ ከዛ ወደ ግራ ከዛ
ወንዙን ተሻግሮ ወደ ቀኝ ድጋሜ ወደ ግራ አሁንም ጥቂት
ተጉዞ ወደ ቀኝ እንዲ እንዲ እያለ የሆነ ቦታ ሲደርስ አሁን
ተገላገልኩ ብሎ ድመቱን ይለቀዋል….
ከሰሀታት በኃላ ሰውየው ሚስቱጋ ደውሎ “ሆዴ ድመቱ አለ
እንዴ?”
ሚስት:” አዎ ምነው….?
“እስቲ አንዴ አቅሪቢልኝ መንገድ ጠፍቶብኛል

አልኮል ፋብሪካ ውስጥ የነበረ አልኮል ቀማሽ


ይሞትና ማናጀሩ አዲስ ቀማሽ ለመቅጠር
ክፍት የስራ ማስታወቂያ ያወጣል:: አንድ
በጣም የሰከረና ድሪቶ የለበሰ ሰው
ማስታወቂያውን አይቶ ሊፈተን ይመጣል::
ማናጀሩ ገና እንዳየው የሰውዬው ሁኔታ
ይደብረውና ላለመቅጠር ወስኖ ከባድ ጥያቄ
ሊያባርረው ይወስናል:: በብርጭቆ የተሰጠውን
አልኮል ምንነት በመቅመስ እንዲለይ
የመጀመሪያው መጠጥ ተሰጠው:: ሰውየው
መጠጡን ቀመሠና :- *ቀይ ወይን ነው::
*የተሰራው ከነጭ የወይን ፍሬ ነው::
*ከተጠነሰሰ 3 ዓመቱ ነው:: *በደቡብ ሸለቆ
ውስጥ በብረት በርሜሌ የተጠመቀ ነው ሲል
መለሰ:: ማናጀሩ በመልሱ ፍፁም ትክክለኛነት
ተደንቆ ሌላ ብርጭቆ ሰጠው:: ይህንንም
ቀመሠና:- * ከደረቅ ቀይ ወይን የተሰራ ነው::
* ከተጠነሰሰ 8 ዓመቱ ነው:: * በደቡባዊ
ፈረንሳይ *በእንጨት በርሜል የተጠመቀ
ቀይ ወይን ነው” አለ:: ማናጀሩ ገርሞት ቢሮ
ውስጥ የሚያሽኮረምማትን ፀሐፊ ጠርቶ
ያንሾካሹክላታል:: እሷም ወጣ ብላ ሽንቱዋን
በብርጭቆ ይዛ ትመጣና ትሰጠዋለች::
ተፈታኙም ይቀምሰውና:- * ብሎንዲ /ቢጫ
ነገር/ ነው:: * ከተጠነሰሰ 3 ወሩ ነው:: *
የተሠራው ቢሮ ውስጥ ነው:: ካልቀጠርከኝ
ደግሞ አባትዬውንም /የፅንሱንም አባት/
እናገራለሁ ብሎ ቁጭ..

.አንዱ ከመርካቶ ዶሮ ገዝቶ እቤት ከመመለሱ በፊት እግረ


መንገዱን ሲኒማ ቤት መግባት ፈለገ። ሲኒማ ቤት “ከነዶሮህ
አትገባም” ሲሉት ፣ ይወጣና ዶሮውን ሱሪው ውስጥ ደብቆ
ይገባል። ፊልሙ ሲጀመር ፣ ጨለማን ተገን አድርጎ ፣ ዶሮው
እንዳይታፈን ብሎ ዚፑን ከፈት ሲያደርግ ፤ አጠገቡ
የተቀመጠች ሴት ታስተውልና ፣ ጓደኛዋን ጠጋ ብላ “ወይኔ
ጉዴ! እረ አጠገቤ ያለው ሰውዬ ዚፑን ከፈተው” አለቻት… “
በቃ አትይዋ! የወንድ ብልት እንደሆነ ፣ አንዱን ካየሽ ሁሉንም
አይተሻል ማለት ነው!” ስትላት…. “እሱማ አዎ። ግን ይሄኛው
እኮ ፈንዲሻዬን እየበላብኝ ነው!”

100 ብርና ተማሪ

አስተማሪ፦ አንተ ምን ሆነህ ነው ያረፈድከው

ተማሪ፦ አንድ ሰውዬ 100 ብር ጠፍቶት ነው::

አስተማሪ፦ ታዲያ አንተ ብሩን


ስታፈላልገው ነበር?

ተማሪ፦ አይ! በእግሬ ብሩ ላይ ቆሜበት ነበር።

የወንዶች እሮሮ በቀልድ

ባል ከሚስቱ ጋር መርካቶ ሄዶ ሁለቱ የተለያየ ሱቅ ገብተው ተጠፋፉ።

ቢቸግረው አንድዋን ቆንጆ ልጅ ያስቆምና …”ሚስቴ ስለጠፋችብኝ በናትሽ ትንሽ ግዜ አብረሺኝ ሁኚ”…

“እንዴ?ለምን?” ብትለው… “ሁል ግዜ ከቆንጆ ሴት ጋር


ከሆንኩ ፣ ከየት መጣች ሳትባል ነው ብቅ የምትለው”

ጋባዡ……
አንድ ሰውዬ ፊቱ በደስታ ጥርስ በጥርስ ሆኖ መጠጥ ቤት
ውስጥ ይገባና ደብል ውስኪ ያዛል ::

ከዛም ጮክ ብሎ መጠጥ ቤት ውስጥ ላሉት ሰዎች ” ዛሬ


የደስታዬ ቀን ነው ስለዚህ እኔ ስጠጣ ሁሉም ይጠጣ “
ይላል :: ሰዎቹም በጭብጨባና በሁካታ ቤትዋን ሞቅ
አድርገውለት ስለግብዣው ምስጋናቸውን ከገለጹ በውሀላ
ተቀድቶላቸው መጠጣት ይጀምራሉ ::

ከጥቂት ጊዜ በውሀላም ሰውዬው በድጋሚ ደብል አስቀድቶ


አሁንም ጮክ ይልና ‘እኔ ስጠጣ ሁሉም ይጠጣ ‘ ይላል ::
በድጋሚ በጭብጨባ ቤትዋ ሞቅ ትላለች መጠጣቱ
ይቀጥላል :: ለሶስተኛ ግዜም ያን ካደረገ በውሀላ ከኪሱ
ቦርሳውን አውጥቶ “በሉ አሁን እኔ ስከፍል ሁሉም ይክፈል “

አንድ ሰካራም ሰውየ መንገድ ላይ አጥር ተደግፎ ሽንቱን ይሸናል…ድንገት ዞር ሲል ደንብ አስከባሪ አጠገቡ ቆሞ ደረሰኝ
ቆርጦ ይሰጠዋል፡፡

ሰውየው ፡- ምንድ ነው ?
ደንብ አስከባሪው፡- እዚህ ጋር መሽናት 5 ብር ያስቀጣል
ሰውየው ወንጀለኝነት በተሰማው መንፈስ 5 ብር ከ50 ሳንቲም ይሰጠዋል ፡፡
ደንብ አስከባሪው፡-..ሃምሳ ሳንቲሙ የምንድን ነው ?
ሰውየው፡- ፈስቻለው

አንድ ሰውዬ ሰው ሲዋሽ በጥፊ የሚማታ ሮቦት ገዝቶ ቤቱ ሄዶ


ለመሞከር ለልጁ እንዲህ አለው
አባት> ዛሬ ምን ስትሰራ ዋልክ
ልጅ>ከጏደኞቼ ሳጠና
ቹቹዋዋ ሮቦቱ ልጁን በጥፊ አጮለው
ልጁ>እሺ ፊልም ሳይ ነበር
አባት>ምን አይነት ፊልም
ልጅ>አድቬንቸር
ቹቹዋዋ ሮቦቱ ልጁን በጥፊ አጮለው
ልጅ>እሺ porno ፊልም ሳይ
አባት>እንዴ እኔ ባንተ እድሜ እያለሁ porno ምን እንደሆነ
አላውቅም ነበር
ቹቹዋዋ ሮቦቱ አባትን በጥፊ አጮለው
እናት>HaHaHa ለነገሩ አትፍረድበት ያንተ ልጅ አይደል ባንተ
ወቶ ነው
ቹቹዋዋ ሮቦቱ እናትን በጥፊ አጮላት

1 ሰካራም ሌሊት 5 ሰዓት ኣካባቢ መርካቶ ላይ 50 ሳንቲም


ይጠፋውና ፒያሳ ላይ
ፍለጋውን ይጀምራል:: መኪናዎችን ኣላሳልፍ ብሎ ሲያሥቸግር
የተመለከተው ፖሊሥ እንዲህ ሲል ይጠይቀዋል
ፖሊሥ – ምን እየፈለግክ ነው?
ሰካራም – ፍራንክ ጠፍቶኝ ነው
ፖሊሥ – የት ነው ያጠፋሀው?
ሰካራም – መርካቶ ላይ
ፖሊሥ – እና መርካቶ ላይ ጠፍቶህ እንዴት ፒያሣ ትፈልጋለህ?
ሰካራም – ፒያሣ መብራት ስላለ ነው :
የጠበቃ ውሻ የታሰረበትን ገመድ በጥሶ ከቤት በመውጣት በቀጥታ ወደ አቅውራቢያው ስጋ ቤት ካመራ በኋላ ሙዳ ስጋ
በጭቆ ያመልጣል፡፡
በውሻው ድርጊት የበገነው የስጋ ቤቱ ባለቤት በቀጥታ ወደ ውሻው ባለቤት ጠበቃ ቢሮ ካመራ በኋላ የሚከተለውን ጥያቄ
ይጠይቀዋል፡፡

“የታሰረበትን ገመድ የፈታ ውሻ ከኔ ስጋ ቤት ስጋ ሰርቆ ቢሄድ የውሻውን ባለቤት የስጋዬን ዋጋ ልጠይቀው እችላለሁ?”

ጠበቃውም በእርጋታ ካዳመጠ በኋላ

“ያለጥርጥር!”
በማለት እርግጠኛ መልስ ይሰጠዋል::

የስጋ ቤቱ ባለቤትም እምቅ ፈገግታ ፊቱ ላይ እየተነበበ በልቡም “ሰራሁልሽ!” እያለ “ዛሬ ጠዋት ያንተ ውሻ ማሰሪውን
በጥሶ ግማሽ ኪሎ ስጋ ይዞብኝ ሮጧል፡፡
ስለዚህ 20 ብር ልትከፍለኝ ይገባል፡፡” (የስጋው ዋጋ አዲስ በወጣው የመንግስት የዋጋ ተመን መሰረት ነው!)

ጠበቃውም ያለተቃውሞ ከኪሱ 20 ብር አውጥቶ ይሰጠዋል፡፡ የስጋ ቤቱ ባለቤት በጠበቃው ቅንነት እየተገረመ ሊወጣ
ሲል ጠበቃው አስቆመውና አንድ ደረሰኝ ጽፎ…

“አንተም ለኔ የምትከፍለው 100 ብር


አለብህ !” ይለዋል

“የምን መቶ ብር?”

“የህግ ምክር የሰጠሁበት ነዋ”

የእንግሊዛውያን የምንጊዜም ቀልድ

አንዲት ሴት ልጇን ይዛ ባቡር በመሳፈር ላይ እያለች የባቡሩ ሹፌር እንዲህ አይነት አስቀያሚ ልጅ አይቼ አላውቅም
ይላታል እሷም በጣም ትበሳጭና ከባቡሩ መሀል ሄዳ ስቅስቅ ብላ ታለቅሳለች ከዛም ከተሳፋሪዎች አንዱ ለምን
እንደምታለቅስ ይጠይቃታል

ሴትየዋ – ሹፌሩ በተናገረኝ ንግግር በጣም ተበሳጭቼ ነው

ተሳፋሪ – ታድያ ለሱ ነው እንዲህ የምታለቅሽው ሄደሽ ልክ ልኩን አትነግሪውም እስከዛ ጦጣውን ልያዝልሽ ::

አላት ይባላል

ታሪክን የኅሊት

አበበ ቢቂላ ጣሊያን ሮማ ውስጥ ባለው stadio olimpico ውስጥ በባዶ እግሩ ማራቶን ያሸነፈ ጊዜ…

አንድ የተሸነፈ ሯጭ “ለምን በባዶ እግሩ እንዲሮጥ ፈቀዳችሁለት?” “እሱ እኮ ያሸነፈው ሸክም ስለቀለለት ነው” ብሎ ክስ
በማቅረብ ዳኞቹን ሲጠይቃቸው ጊዜ ምን ብለው መለሱለት መሰላችሁ?
.
.
.
.
.
.
“አንተም ሸክም እንዲቅልልህ ከፈለግህ ለምን
ራቁትህን ሮጠህ አታሸንፍም ነበር?”

ሰውዬው ላዳ ታክሲ ተኮናትሮ ከቦሌ እየመጣ ነው፡፡ ሗላ ወንበር ተቀምጦ እየመጣ እያለ የሚያውቀው ሰው ያይና
ታክሲውን እንዲያቆምለት ለሹፌሩ ለመንገር ትከሻውን ነካ ያደርገዋል፡፡ ይሄኔ በቅፅበት ውስጥ ታክሲዋ እንዳልነበረች
ሆነች… ትከሻውን የተነካው ሹፌር በድንጋጤ መጮህ ጀመረ… ታክሲዋን መቆጣጠር አቅቶትም አንዴ ወደ ግራ ከዛ
ወደ ቀኝ ካንገላታት በሗላ በከባዱ እየተነፈሰ እንደምንም የመንገዱ ጥግ ላይ አቆማት፡፡

ወዲያውም “ሰውዬ ያምሃል እንዴ? ምን ነካህ?” እያለ መነጫነጭ ጀመረ፡፡ በሁኔታው የተደናገጠው ተሳፋሪም ይቅርታ
እየጠየቀ ..

“እንደዚህ ትደነግጣለህ ብዬ ፈፅሞ አላሰብኩም ነበር፤ እንድትቆምልኝ ፈልጌ ስለነበር ነው” ብሎ ለማስረዳት ሞከረ::

በመጠኑ የተረጋጋው ሹፌርም “ነገሩስ አንተ አይደለህም ጥፋተኛው፤ ገና ዛሬ ለመጀመርያ ጊዜ ታክሲ ስለያዝኩ ነው
የተደናገጥኩት መሰለኝ…”

ተሳፋሪ፡- ኧረ! ከዚህ በፊት ምንድነው ትሰራ የነበረው?

ሹፌር፡- የቀብር አስፈፃሚ ድርጅት ውስጥ ሬሳ በመኪና ማጓጓዝ፡፡

‹‹አንድ ጠርሙስ አረቄ . . . !››

በጠጪነቱ የታወቀ የአንድ መሥሪያ ቤት ሠራተኛ ጧት ሥራከመግባቱ በፊት ከቤቱ ጀምሮ ባሉ አንድ አራት መጠጥ
ቤቶች
ጎራ እያለ ፉት ይላል፡፡ ማታም እንዲሁ አትለፍ የተባለ ይመስል የደንቡን ሳያደርስ ቤቱ አይገባም፡፡ ይህ ልምዱ
እንደማያዋጣው በብዙ ሰዎች ከተነገረው በኋላ አንድ ጧት
ለራሱ ቃል ገባ፣ ሳይጠጣ ቢሮው ገብቶ ሳይጠጣ ቤቱ ለመመለስ፡፡ እናም፣ ምሎ እና ተገዝቶ እኒያን መጠጥ ቤቶች ጧት
ላይ እየገላመጠ እና እየረገማቸው አልፎ መሥሪያ ቤቱ
ደረሰ፡፡ በውሳኔው ተደስቶ በሰላም ሲሠራ ከዋለ በኋላ ማታም ወደ ቤቱ ሲመለስ የጧቱኑ ዕርምጃ ወሰደ፡፡ ሳይቀምስ
ውሎ ሳይቀምስ በመግባቱ ተደስቶ፣ ‹‹ጀግና ነኝ! ቆራጥ! ለዚህ
ጀግንነቴ አንድ ጠርሙስ አረቄ ይገባኛል በማለት ወደ አረቄ ቤት በረረና አረፈዋ!

‹‹ተሜ ተቀምጬ ልስጥህ?››


Funny-if u Understand
አንድ የቅኔ ተማሪ ለእራት የሚሆነውን ቁራሽ ለመለመን ወደ ገጠር ነዋሪዎች /ወደ መንደር/ ብቅ ይልና ‹‹በእንተስማ
ለማርያም ስለ ቸሩ እግዚአብሔር ብለው›› ይልና ይለምናል፡፡

ቁራሽ በሚለምንበት መንደር ‹‹ተቀምጬ›› የሚባል የምግብ ዓይነት ነበርና አንዲት ሴት ወይዘሮ እንጀራ አልጋገረች ኖሮ
‹‹ተማሪ እንጀራ አልጋገርኩምና ተቀምጬ
ልስጥህ?›› ትለዋለች፡፡ ተማሪውም መልሶ ‹‹ኧረ እመይቴ የሚዘክሩኝስ ከሆነ ተኝተውም ቢሆን ቢሰጡኝ አልጠላም››
አላቸው ይባላል፡፡

“አትደርስበትም” great Answer

አንድ ጥጥ የመሰለ ነጭ ሽበት ያለባቸው አዛውንት ቁልቁል


ሲወርዱ አንድ ወጣት ሊተርባቸው አስቦ “አባባ፣አባባ የቃጫ
ፋብሪካ መንገድ በዚህ በኩል ነወይ?” ብሎ ሲጠይቃቸው፣
እሳቸውም ነገሩ ስለገባቸው “አዎን ልጄ መንገዱስ ይኼው፤
ነገር ግን አንተ አትደርስበትም” ብለው መለሱለት፡፡

ባል ለሚስት በሞባይል መልዕክት… “ነገ ለስብሰባ ወደ ክፍለ ሃገር ስለምሄድ ከውስጥ የምለብሳቸውን ልብሶች ቅያሬ
እና ሸሚዝ እንዲሁም ካልሲ በመካከለኛው ሻንጣ አዘጋጂልኝ::”
ትንሽ ቆይቶ እንደገና ሌላ መልዕክት “ውይ ሳልነግርሽ እረስቼው: ባለፈው የተወዳደርኩበትን ቦታ እኮ አለፍኩ:: የደስ ደስ
ያንን የእራት ቀሚስ ገዝቼልሽ እመጣለሁ::”

ሚስት በመልዕክት: “አረ: እስቲ ሙች በለኝ?”

ባል ከእንደገና በመልክት: “አረ ውሸቴን ነው:: የመጀመሪያውን መልዕክት እንደደረሰሽ ለማረጋገጥ ነው::”

ባል የሰሞኑን የሚስቱ ሁኔታ አልጥምህ ብሎት እንዳይነግራት ትዳራቸውን እንዳያቀዘቅዝ ፈርቶ ሀኪም ለማናገር ፈለገ::

“ዶክተር ሚስቴ የመስማት ችግር ሳይኖርባት አይቀርም:: በግልፅ እንዳልነግራት ደግሞ እንዳታኮርፈኝ ፈራሁ::

” ሀኪሙም ከአምስት ሜትር ርቀት ጀምሮ አንድ ሜትር ርቀት እየቀነስክ አንድ ጥያቄ ጥይቃት እና የችግሩን ክብደት
እንለያለን ብሎ መክሮ ይሸኘዋል::

ባልም እቤት እንደገባ ከአምስት ሜትር ርቀት “ውድ, ዛሬ ምሳ ምንድን ነው?” ብሎ ይጠይቃታል:: ምን መልስ የለም::

ከአራት ሜትር ጥያቄውን ደገመ:: አሁንም መልስ የለም:: ከሶስት ሜትር: ከሁለት ሜትር: ተመሳሳይ ሞከረ:: ምንም
መልስ የለም::

ከአንድ ሜትር ላይ “ሆዴ, ምሳ ዛሬ ምንድን ነው?” ሲላት..

ሚስት “እህ አንተ ሰውዬ ዛሬ ምን ሆነሃል? አሁን እኮ ስትጠይቀኝ ለአምስተኛ ጊዜህ ነው:: ምስር ወጥ አልኩህ አይደል!”

ከ 18 አመት በታች ይህን ጨዋታ እንዲያነቡ አይፈቀድላቸውም !!!

ልጅቷ አምራና ተውባ ከቤት ልትወጣ ስትል አያቷ አስቆሟትና “ ወዴት ልትሄጂ ነው የኔ ልጅ አሏት”

“ከወንድ ጓደኛዬ ጋር ቀጠሮ አለኝ አያቴ”

“ እንደዛ ከሆነ ማድረግ ስለሚኖርብሽ ጥንቃቄ ልንገርሽ ቁጭ በይ፡፡ እነዚህ ወጣቶ ወንዶች ተንኮለኞች ናቸው ሊያሳስቱሽ
ይችላሉ፡፡” አሉ አያትየው የወጣትነት ዘመናቸውን በትውስታ እየተመለከቱ፡፡

“አንዴት አያቴ”

“ መጀመሪያ ከንፈርሽን ሊስምሽ ይሞክራል፡፡ እሱ ደሞ ደስ ይላል፡፡ ግን ፈፅሞ ወደ ከንፈሮችሽ እንዲጠጋ


እንዳትፈቅጂለት፡፡”

“አሺ ……”

“ሲቀጥል ደግሞ ጡቶችሽን እያሻሸ’ ስሜት ውስጥ ሊያስገባሽ ይሞክራል፡፡ ይሄም በጣም ደስ ይላል፡፡ ግን እንደዛ
እንዲያደርግ እንዳትፈቅጅለት፡፡”’

“አሺ ……”

“ሲቀጥል ጣቶቱን በእግሮችሽ መሀል አስገብቶ ሊነካካሽ ይሞክራል፡፡ በእርግጥ ይሄም ጥሩ ስሜት ይፈጥራል፡፡ ሆኖም
ልትፈቅጅለት አይገባም፡፡”

“አሺ ……”
“ ይሄም ሁላ አልበቃ ብሎት አንቺን አስተኝቶ እላይሽ ላይ ሊደሰት ይሞክራል፡፡ ስለዚህ ይሄንንም እንዳትፈቅጅለት
ቤተሰባችንን ያዋርዳል፡፡”

ከዛ ልጅቷ ምክሩን ሁሉ ከሰማች በኋላ ወደ ወንድ ጓደኛዋ ሄደች፡፡ በማግስቱ አድራ ስትመለስ ደረቷን ነፍታ በድል
አድራጊነት ስሜት እያለከለከች ነበር፡፡

“አያቴ መጀመሪያ ላይ ምክሮችሽን ሁሉ ለመተግበር የሚቻለኝን ሁሉ ብሞክርም ተግባራዊ ማድረግ አልቻልኩም ነበር፡፡

አዘናግቶ ከሳመኝ በኋላ የተፈጠረብኝ


ስሜት ቀጣዮቹን ነገሮች ሁሉ ለማስቆም አስቸጋሪ አድርጎብኝ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ስሞኝ ጡቶቼን አሻሽቶ፣ ፓንቴን
አውልቆ አስተኝቶኝ……. ከላይ ሆኖ ቤተሰባችንን
ሊያዋርድ ሲል ምን እንዳረኩ ታውቂያለሽ አያቴ?”

“ ምን አደረግሽ ልጄ”

“ገለበጥኩትና ከላይ ሆኜ የእራሱን ቤተሰቦች


አዋረድኩለት……”

አያትየዋ በድንጋጤ አፍጥጠው ቢመለከቷትም ያለፈውን ሌሊት ገድሏን ከመተረክ


አላቆመችም

“ ……ሌሊቱን ሙሉ እንደፈረስ ስጋልበው አደርኩ….

ማን በለጠ?

እንግሊዛዊው፣ አየርላንዳዊውና ስኮትላንዳዊው ጩኸት የበዛበትና በጭስ የታፈነ በርካታ ሰዎች የተሰበሰቡበት መጠጥ
ቤት ውስጥ ተቀምጠዋል፡፡

የእንግሊዙ ተወላጅ ‹‹የአገሬ የእንግሊዝ መጠጥ ቤቶች ምርጦች ናቸው፡፡ አንደ ነገር የጠጣ ሰው ሁለተኛውን በነፃ
ይጋበዛል!›› አለ፡፡ ጠጪዎቹ በመገረም ራሳቸውን ነቀነቁ፡፡

አየርላንዳዊው በበኩሉ፣ ‹‹በኔ አገር አንድ ነገር የወሰደ ሰው ሁለት በነፃ ይጋበዛል›› በማለቱ ጠጪዎቹ ይበልጥ በመደነቅ
አጨበጨቡ፡፡

በመጨረሻ ስኮትላንዳዊው፣ ‹‹የናንተ መዝናኛ ሥፍራዎች ጥሩ ቢሆኑም እንደ ስኮትለንድ ሊሆኑ ግን አይችሉም፡፡
ስኮትላንድ ውስጥ አንድ መለኪያ በሒሳባችሁ ከጠጣችሁ፣
ሦስት በነፃ ትጋበዙና ባክብሮትና በፍቅር ቤታችሁ ድረስ ትሸኛላችሁ!›› አለ፡፡

እንግሊዛዊው በሸቀ፡፡ ‹‹አታጋን እባክህ፤ አሁን የተናገርከው አጋጥሞህ ያውቃል? በዓይንህ በብረቱ አይተሃል?››
በማለትም በቁጣ ጠየቀው፡፡

ስኮትላንዳዊው እየሳቀ፣ ‹‹እኔን ባያጋጥመኝም፤ እህቴን አጋጥሟታል›› አለው፡፡

-አረፈዓይኔ ሐጎስ ‹‹የስኮትላንዳውያን ቀልዶች (2005)

በድሮ ጊዜ ነው አሉ፡፡ ከብዙዎቹ ጦርነቶች በአንዱ ጊዜ፡፡ እንደተለመደው ሴቶች ለወታደሩ ሁሉ ቆሎ ቆልተው፣ አምሰው
ያሳድራሉ፡፡

በማግስቱ ፤በዘመን ብዛት ቃልም ‹‹እንደሚባልግ›› ያልተረዳ አንዱ የዘመኑ ወታደር ጡሩምባውን ይዞ የሚከተለውን
ለፈፈ፡፡

‹‹ጡ! ጡ! ጡ! ትላንትና የቆላችሁ፣ ያመሳችሁ ሴቶች ዛሬ ለሽክሸካ ትፈለጋላችሁ እና እንዳትቀሩ >>


እትዬ ትሁኔ ጉልት ሻጭ ባልቴት በመሞቻቸው ሰዓት እንዲህ ተናገሩ፡-

‹‹አባ እንግዲህ መሞቴ ነው፤ እንደሚያዩት እንኩዋን የሚወረስ የሚላስ የሚቀመስ ተቤት የለም! ያም ቢሆን ለሁለቱ
ልጆቼ ምንም ሳላወርሳቸው አልሞትም፡፡ እዚህ
ከቤቴ በስተግራ ካለው ጎረቤቴ ጋር ያልቋጨሁት ጠብ አለኝ፣እሱን ልጆቼ እንዲጨርሱልኝ ተናዝዣለሁ››

ጊዜን በስላቅ

የሥዕል አስተማሪ ክፍል ውስጥ ይገቡና ለተማሪዎቻቸው የክፍል ሥራ ይሰጣሉ፡፡ መምህሩ ተማሪዎቻቸው ስለው
እንዲያሳዩዋቸው የጠየቁት በሀዲዱ ላይ የሚጓዝ ባቡር ወይም ባቡሩን ከነሀዲዱ ቁጭ እንዲያደርጉላቸው ነው፡፡ ክፍለ
ጊዜው
ከማለቁ በፊት እንዲታረምላችሁ በፍጥነት ሥሩ ይሉና ወደ መቀመጫቸው ያመራሉ፡፡ ቁጭ እንዳሉ እንቅልፍ ሸለብ
ያደርጋቸውና ክፍለ ጊዜው ሊያልቅ 5 ደቂቃ ሲቀረው
ይነቃሉ፡፡ ወዲያውም ተማሪዎቻቸው የሠሩትን በየተራ እየተመለከቱ ሲያርሙላቸው ከተማሪዎቹ መካከል አንደኛው
ሐዲዱን ብቻ ሥሎ ያሳያል፡፡ መምህሩ ሲመለከቱት ባቡሩ
የለም ሀዲዱን ብቻ ይመለከቱና ጥያቄ ያነሳሉ፡፡

መምህሩ፡-ስላችሁ አሳዩኝ ያልኳችሁ በሀዲድ ላይ የሚጓዝ ባቡር ነው፣ አንተ የሣልከው ደግሞ ሀዲዱን ብቻ ነው፤ ባቡሩስ
ሲሉ
ይጠይቃሉ፡፡

ተማሪ፡- አይ ቲቸር እርስዎ እኮ እንቅልፍ ወስዶዎት እያለ ባቡሩ አልፏል፡፡ ለዚህ ነው ሀዲዱን ብቻ የሚመለከቱት

ፍቅር በሒሳብ

በአንዳች ቅጽበት set ነትሽን አድንቄ ቀርቤ ላወራሽ ብፈልግ ስለፍቅርሽ እኔ ለፍቅር negative ነኝ ብለሽ
ብታስደነግጭኝም እኔ ግን ለፍቅር positvie ሳስብም እኔ
radical ውስጥ የገባሁ ነኝ ብትይም ተማመንኩ፡፡ ከcomplex system ላስቀር negative ፍቅርሽን sub set ሆነሽብኝ
ፍጹም ብታስቸግሪኝም በsine መስመር ወደ
አንቺ ብመጣ የአንቺ ምርጫ በcosine መስመር ሆኖ ቢያስከፋኝም ተስፋ ባለመቁረጥ በhorizontal line ወይስ
በsymptote ወደ አንቺ ለመቅረብ አንድ ሐሳብ መጣልኝ፤ ሳሰላስል ድንገት ወስኜ ለራሴ እንደ polynomila በ power
በዝቼ rationalize ሆነ inverse ሆኜ በመምጣት እንዳለብኝ ወሰንኩ አንቺን ፈልጌ፡፡

የምር ግን አስቸጋሪ ነሽ ለፍቅር empty set ነሽ፡፡ በሂሳብ ቀመር በ subtracton ኧረ እባክሽ በmultiplication
ደግሞም በaddition እኔ ልሆንልሽ የፍቅርሽ division:: የፍቅርሽ ውስብስብነት በlimit “x” goes to beta
አለመፈታቱ ቢሆንብኝ ስቃይ በሐሳብ ብዞር በቁጥሮች ጎራ በgraph ዎች መንደር በcircle አደባባይ በquadratic ሰፈር
በcalculus እና በመደመር አንቺ ግን ክፋትሽ አሁንም undifined ነሽ፡፡ ግን solve ማድረጊያው የፍቅርሽ መንገዱ
sequence አይደለም፤ አቤት ክፋቱ እኔ ግን ተስፋ
ባለመቁረጥ logarithm ተጠቅሜ exponentialን አብዝቼ በsolution set ቦታ ሆኜ perimeter ሽን አቅፌ vertical
line ሽን አይቼ upper and lower
bounedሽን አረጋግጩ remainder ሽን በድካም አግኝቼ square root ሳላበዛ ተስፋ አደርጋለሁ እንደማግኝሽ፡፡
በfunction ቦታ ካልተገኘሽ የፍቅር slope ካልገባሽ የ
“x” “y” ዋጋ ካልሆንሽ የምር አሁንም ለፍቅር empty set ነሽ፤ ለፍቅር undefined ነሽ፤ ለፍቅር one over
zero ነሽ፤ ሁሌም ነሽ፡፡

ሚስት ለበሏ እራት አቅርባ እየበላ እያለ “ጉዳችንን አልሰማህም” አለችው.

“ምን ተፈጠረ?”

“ልጅ”..

.“የምን ልጅ?”
“የ 15 አመት ልጃችን እኮ አረገዘች”

አሁንም ዝም ብሎ እየበላ “ከማን?” አለ…

“ከአለቃህ” ስትለው ፣ በድንገት


አባት ‘በስመአብ’ ብሎ የበላውን ‘ቱፍ’ ብሎ ይተፋል።

“ያናድዳል አይደል?” ስትለው…

“አይ ለሱ አይደለም ፣ ያልበሰለ


ድንች ልውጥ ነበር”

፹_ለውበትሽ አድናቆቴ ይህ ነው_(2)፹


……..እድሜ የአፍሽ ዘበኞች ሆነው እንደሰራዊት ከፊት ለተሰለፉት ጥርሶችሽ፣ሊቃጠል የደረሰ አምፖል ለሚመስለው
አይንሽ፣ጉንጭሽን መስሎ ከፊትሽ ለተለጠፈው አፍንጫሽ፣በዶማ እንደተፈነከተ ድንጋይ ለተተረከከው ሎሚ መሳይ
ተረከዝሽ፣እንደጎሽ መውጊያ ለሚኮሰኩሰው ፀጉርሽ፣ምስጋና ይግባቸውና እነሆ ዛሬ የአለም ታላቋ አስቀያሚ
አሰኝተውሻል።
……..

ቲቸር: “እስቲ በአዕምሮቹ ሳሉት: ውሃ ውስጥ ናችሁ: ዋና አትችሉም: ምን ታደርጋላችሁ?”

ቾንቤ እጁን አወጣ::

ቲቸር: “እሺ ቾንቤ!”

ቾንቤ “እኔ በአዕምሮዬ መሳሌን አቆማለሁ::”

#ትንሹ ማሙሽ እድሜው ለትምህርት ሲደርስ አባቱ ትምህርት ቤት ይዞት ይሄድና ለተቀበለችው መምህርት እንዲህ
የሚል መስጠንቀቂያ ይነግራታል::

” ይህ ልጅ ቁማር በጣም ነው የሚወደው:: እስከ ዛሬ እንዳየሁት የሚሸነፍ አይነት አይደለም:: ስለዚህ ምንም ነገር
እናሲዝ ቢልሽ እሺ እንዳትይ ብሎ ይነግራታል::

አባት ገና እግሩ ከክፍሉ እንደወጣ ማሙሽ ቲቸሩን ጠርቶ “ቲቸር ከፊትሺ ፈገግታ ተነስቼ: ያረግሺውን ፓንት መገመት
እችላለሁ::”

“እስቲ ገምት?” አለችው:: “ሃምሳ ብር አናሲዝ?” አላት:: ተስማምታ ከክላስ በሁላ ተቃጠሩ:: ክላሱ ሲያልቅ “እስቲ
ግምትህ ምንድን ነው?” ማሙሽ “ነጭ!” አይደለም ብላ ቀሚሱአን ገልባ ስታሳየው ቀይ ነው::

“በቃ እሺ አባዬ ጋር አድርሽኝና ብሩን እሰጥሻለሁ::” አላት::

አባትየውን ገና ስታየው አስተማሪዋ “ዛሬ ማሙሽ አንድ ትምህርት ተማረ!”

አባት:- “ምን? “

አስተማሪ:- “መሸነፍን! ሃምሳ ብር አሸነፍኩት::”

አባት:- “በምን?”

አስተማሪዋ:-“ፓንትሽ ነጭ ነው ብሎ::”
አባት:- “እና ፓንትሽን አሳየሽው?”

አስተማሪዋ :- “አዎ!”

አባት:- “እናቱ አፈር የበላች! ከእኔ ጋር እኮ ክላሱ ከማለቁ በፊት ፓንቱአን አያለሁ ብሎ 100 ብር አሲዞኛል!”

አንድ ሀብታም ሰው ፓርቲ አዘጋጅቶ ብዙ ሰው ጋበዘ:: በፓርቲው መሃል “አንድ ውድድር አለኝ” ብሎ አስታወቀ::
“ውድድሩ እዚህ የዋና ገንዳ ውስጥ አዞዎች አሉ:: በእነዚህ አዞዎች ውስጥ ዋኝቶ በህይወት የወጣ ሰው 3 ፍላጎቶችን
ላሙዋላለት ቃል እገባለሁ::” አለ::

በመጀመሪያ ፍቃደኛ የሆነ ሰው ጠፋ:: በመኅል ግን የሆነ ሰው ዘሎ ገብቶ በፍጥነት መዋኛት ጀመረ:: ምንም አዞ ሳይነካው
በህይወት ወጣ::

ባለሀብቱም ወደ ሰውዬው ጠጋ ብሎ “እንካን ደስ አለህ! ሶስቱ የምትፈልጋቸው ነገሮች ምንድን ናቸው?”

ሰውዬውም ልብሱን እየጨማመቀ …. ” ሽጉጥ : ጥይት እና የገፈተረኝን ሰው ማንነት!”::

ስፍራው የአዕምሮ ህመም ችግር የለባቸው ሰዎች (ወይኔ እርዝመቱ – እብዶች ማለቴ ነው) ሆስፒታል ግቢ ውስጥ ነው፡፡

በግቢው ውስጥ ያሉት እብዶች በጋራ ድምፅ “….13…..13….13…13….” እያሉ ይጮሃሉ፡፡ በዚህ ግዜ ወደ ስራው
ለመሄድጫማውን እንኳን በደምብ ሳያስር ተጣድፎ ከቤቱ የወጣ አንዱ ወሬ ወዳድ ግለሰብ የፈለገው ሰዓት ይርፈድ እንጂ
ይሄንንማ ምን እንደሆነ ማየት አለብኝ ብሎ ወደ ሆስፒታሉ ተጠግቶ ወደ ግቢው ውስጥ ለማየት የሚያስችለውን ቀዳዳ
መፈለግ
ይጀምራል፡፡ ከትንሽ ፍለጋ በኋላ በበሩ ቁልፍ ስር ትንሽዬ ቀዳዳ አግኝቶ ወደ ውስጥ ለማየት አይኖቹን ሲያቁለጨልጭ
ከውስጥ
ካሉት አንዱ እብድ በጣቱ አይኑን ይወጋዋል፡፡

ይሄን ግዜ ሌሎቹ ከኋላ “….14…..14….14 …14….” እያሉ መቁጠራቸውን


ቀጠሉ፡፡

አንድ አባት ልጃችውን ይዘው ሆስፒታል ይሄዳሉ:: ከዛምለዶክተሩ…

አባት : “ልጄ ቁልፍ ውጦአል ዶክተር::”

ዶክተር: “መቼ ነው የዋጠው?”

አባት: “ከ20 ቀን በፊት::”

ዶክተር: “እና ዛሬ ነው ይዘህ የምትመጣው?”

አባት: “ሌላ ቁልፍ ስለነበረን ነው:: ዛሬ እሱ ስለጠፋብኝ ነው::”

በአንድ የኤርትራ ትምህርት ቤት ነው መምህሩ ተማሪወችን ይጠይቃል::

ከተማሪወች መሃል የፕሬዝዳንት ኢሳያስ ልጅ አለ እናም መምህር ጠየቀ”እስኪ ተማሪወች ከበራሪ እንስሳት መካከል ጥቀሱ
“ይላል

ከተማሪወች መሃል እጁን ላወጣው የኢሳያስ ልጅ አንተ ሲባል “ዝሆን” ይላል አስተማሪውም አጨብጭቡለት
ይላል፣ታላቅ ጭብጨባ በመሃል ጭብጨባውን የሰማ ረእስ መምህር ሲመጣ ምንድን ነው ሲል ጉዳዩ ይነገረዋል እናም
ደግማችሁ አጨብጭቡለት ይልና ለመምህሩ”ወንድሜ እኛ ከምንበር ዝሆኑ ቢበር ይሻላል !!!!!አለው ይባላል!!
የሳይንስ ክፍለ ጊዜ ነዉ መምህሩ ‘ሰልፈሪክ አሲድ’ ስለ ሚባለዉ የአሲድ አይነት በማስተማር ናቸዉ: :

”ልጆች አሁን ይህን የወርቅ እንክብል እዚህ አሲድ ዉስጥ ልከተዉ ነዉ እና አሲዱ ወርቁን የሚያበላሸዉ ወይም
የማያበላሸዉ መሆኑን አስቀድሞ ሊነግረኝ የሚችል አለ”

“አያበላሸዉም ቲቸር” አለ አንዱ ልጅ ተሽቀዳድሞ

“ለምን”

“አሲዱ የሚያበላሸዉ ቢሆን ኖሮ እርሶ ቀዱሞዉኑ አሲዱ ዉስጥ አይከቱትማ” : :

ለምን ደወልሽው ?
————— —
አንድ ሴት ዉሀ ልትቀዳ ጎንበስ ስትል አንድ ጊዜ ያመልጣትና (Feswan) ድዉ ታደርገዋለች።

ዘወር ብላ ስታይ አለቃ ገብረሀና ከኋላዋ ቆመዋል። ከዛም ደንገጥ ብላ…

«አለቃ ለመሆኑ ሰአት ስንት ሆነ ስትላቸው?»

«አይ አንች ካላወቅሽዉ ለምን ደወልሽዉ?»


አሏት

አንድ ልጁ ታስሮበት ብቻዉን የቀረ ገበሬ እስር ቤት ላለ ልጁ እንዲህ ሲል ፃፈ፦

“ዉድ ልጄ ፤ ይኸዉልህ አንተ በመታሰርህ ምክንያት በዚህ አመት እርሻ ቦታዉ ላይ ድንች ሳልዘራ ጊዜዉ ሊያልፍብኝ
ነዉ፤ እኔ እንደሆንኩ ከእንግዲህ ደክሜያለሁ፤ምነዉ
በኖርክልኝ ኖሮ” አፍቃሪ አባትህ።

ከሳምንት በኋላ ገበሬዉ መልስ መጣለት፤

ምላሹም፡- “አባባ፤ የድንቹን መደብ እንዳትቆፍር፤ ሰወቹን የቀበርኳቸዉ


እዚያ ነዉ፡፡ ያንተዉ ልጅህ” ይላል፡፡

በሚቀጥለዉ ንጋት ላይ የፖሊስ መዓት መጥቶ የድንቹ ማሳ ላይ ፈሰሰ፤ የተቀበሩትን አስክሬኖች ለመፈለግ ሲቆፍሩ
ቢዉሉም ምንም ሊያገኙ አልቻሉም ፡፡ ስለዚህ ገበሬዉን ይቅርታ ጠይቀዉ ሄዱ፡፡ ወዲያዉ ልጁ ለአባቱ እንዲህ የሚል
ሌላ ደብዳቤ ፃፈ፡-

“አባቴ፤ አሁን ድንችህን መዝራት ትችላህ፤ ካለሁበት ችግር አንፃር ላደርግልህ የምችለዉ ነገር ቢኖር ይሄ ብቻ ነዉ”

ብልጥ ለብልጥ

እናት፡- ዮሐንስ እዚያ ኬክ ያስቀመጥኩበት መሳቢያ ውስጥ ጭራቅ መኖሩን አትርሳ፤ እሺ?

ዮሐንስ፡- እሺ እማምዬ አልረሳም፤ ግን ሁልጊዜ ኬክ ሲጠፋ ጭራቁን ለምን አትጠይቂውም? እኔን ብቻ ነው


የምትገርፊኝ ?

የፊደሏ ጣጣ

ጎልማሳው ለሥራ ጉዳይ ካለበት ብርዳማ የአሜሪካ ግዛት ወደ ሌላ ሞቃታማ ግዛት ይጓዛል፡፡ ባለቤቱም በቀጣዩ ቀን
እንደምትመጣ ተነጋግረው ነበር፡፡
ጎልማሳውም ታዲያ የሆቴል ክፍሉ ውስጥ ሆኖ ለባለቤቱ የኢ-ሜይል መልዕክት ይልክላታል፡፡ ሆኖም ግን አድራሻዋን
ሲጽፍ አንዲት ፊደል ይስትና የኢ-ሜይል መልዕክቱ ወደ ባለቤቱ መሄዱ ቀርቶ አቅጣጫውን ስቶ ወደ አንዲት ባለቸው
ወደ ሞቱባቸው ባልቴት ዘንድ ይሄዳል፡፡

ሴትዬዋ የሃይማኖት ሰባኪ ባላቸው ከሞቱ ገና አንድ ቀናቸው ነበር፡፡


ሐዘን ላይ ያሉት ባልቴት የኢ-ሜይል መልዕክቶቻቸውን ሲፈትሹ (ቼክ ሲያደርጉ) ይህን መልዕክት ያዩና ይከፍቱታል፡፡

ወዲያው ግን ጮኸው መሬት ላይ ይዘረራሉ፡፡


ልጆቻቸውም ተሯሩጠው መጥተው ሲያዩ እናታቸው መሬት ላይ ወድቀዋል፡፡ በምን ምክንያት እንደሆነ ለማወቅ ወደ
ኮምፒዩተሩ ተጠግተው ተመለከቱ፡፡

ኮምፒዩተሩ ስክሪን ላይ የተጻፈው መልዕክት:-

“ውድ ባለቤቴ እኔ ደርሻለሁ፡፡ ይገርምሻል፤ እዚህ በጣም ይሞቃል፡፡ ላንቺም ነገ መምጣት ሁሉም ነገር ተዘጋጅቶ
እየጠበቀሽ
ነው! ከልጆችሽ ተለይቶ መምጣቱ እንዳይከብድሽ ! ያንቺው!
የሚል ነበር፡፡

የፍቅር ጣዕም
ያልነገርኩሽ ነገር

እንዴት ነው የምወድሽ እንኳ?


እንደ አበቦቹ ሽታ፣
እንደ ቢራቢሮ እስክስታ፣
እንደ ጥርኝ ጭቃ፣
ልክ እንደ ስጦታ እቃ፣
እወድሻለሁ እኔ እወድሻለሁኝ፡፡
እንደ ፍልስፍና ሃሳብ፣
ሊጠግብ እንዳለ ረሀብ፣
እንደ ህፃን ልጅ ሳቅ፣
እንደ ዘላለማዊ ሀቅ፣
እወድሻለሁ እኔ፣ እወድሻለሁኝ፡፡
እንደ ሎጂክ፣
እንደ ተፈጥሮ ህግ፣
እንደ ቋንቋ፣
ልክ እንደ ሙሉ ጨረቃ፣
እወድሻለሁ እኔ፣ እወድሻለሁኝ፡፡
እንደ ሙዚቃ ቅንጣት፣
እንደ አልጋ ውስጥ ትኩሳት፣
ልክ እንደ እናቴ ስም፣
እንደ ልጅነቴ ህልም፣
እወድሻለሁ እኔ፣ እወድሻለሁኝ፡፡
እንደ ግጥም ስንኝ፣
አንጀሎ እንደጠረበው ቋጥኝ፣
እንደ ጠዋት እንቅልፍ፣
እንደ አየር ራንድ ፅሁፍ፣
እወድሻለሁኝ እኔ፣ እወድሻለሁኝ፡፡
እንደ ብርቱካን ውሃ፣
እንደ ብርሃን ዘሃ፣
እጄ ላይ እንደያዝኩት ሲጋራ፣
እንደ ቀዝቃዛ ቢራ፣
እንደ ሊዮናርዶ ስራ፣
እወድሻለሁ እኔ፣ እወድሻለሁኝ፡፡
ፍቅሬ ሁሉን እንደ እርሺ
ይህን እንደ ብቻ ያዢ፤
አፈቅርሻለሁ ነፍሴ፣
ልክ እንደ እራሴ፡፡

++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++

ሰላም ለኪ እናታችን ባለሽበት እንዳለሽ ከዘመኑ


ሴቶች ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ
ሠላም ለዐይኖችሽ ከጭስ ጋራ ለሚሟገቱ
ከእንቅልፍ ጋራ ለተፋቱ::
ተቅበዝባዥ ፍጡር ሆኜ ኑሮየን ከምገፋ:
ምነው እንባሽን በኾንኩ ካይኖችሽ ስር
እንዳልጠፋ::
ሰላም ለከንፈሮችሽ ትላንት ለማውቃቸው:
ዛሬ ለምናፍቃቸው::
ውዳሴ ክብር ምርቃት
ጭብጨባ ሙገሳ ሽልማት በተረፈበት ቀዬ:
ምነው ያንቺን እርግማን ይናፍቃል ጆሮዬ::
ከሌሎች ውዳሴ ና ክብር እልፍ ጊዜ የተሻለ:
ለካ በ’ርግማንሽ ውስጥ እናትነትሽ አለ::
ሰላም ለጣቶችሽ
ለሰዎች የቀረቡ ከራስሽ ግን የራቁ መስጠት
መለገስ እንጂ መቀበልን ለማያውቁ::
ሰላም ለኪ!
ባለሽበት እንዳለሽ:

+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
++++++

ፍቅር እስከ መቃብር

ሰብለ ሰብለ ሰብለ ወዳጀ እመቤቴ


የመአልት ምርኩዜ የሌሊት መብራቴ
ስራብ እንጀራዬ ስጠማ ወተቴ
ሳዝን መጽናኛዬ ስደክም ጉልበቴ
ሳጣ አለኝታዬ ስጠቃ ኩራቴ
የስጋ የመንፈስ ያለሽኝ አንድ ሀብቴ
ቁርጥ ከሆነማ እኔ አንችን ማጣቴ
ምን ዋጋ ሊኖረዉ ከእንግዲህ ሂወቴ
የለም ህይወት በቃኝ ይገላግለኝ ሞቴ
ተቀማሁ ወይኔ ድሃ በመሆኔ
ጥየሽ የሄድኩለት ወንዝ ተሻግሬ
የደም እምባ አልቅሼበድሌአማርሬ
የሁዋሊት ስጎተት በፍቅርሽ ታስሬ
ወደ ፊት መራመድ እያቃተዉ እግሬ
አሁንም አሁንም ቆሜ እያየሁ ዞሬ
ምን ልቤ ቢፈራ ባይቀር መጠርጠሬ
በተስፋ ነበረ የወጣሁ ካገሬ
እስከ ዛሬም ድረስ በህይወት መኖሬ
ተስፋ ሆኖኝ ነበር ፍቅርሽና ፍቅሬ
ግን እዉነት ከሆነ የነገሩኝ ወሬ
ሊያገባሽ ነዉ ብለዉ ባለብዙ በቅሎ ባለብዙበሬ
በፍቅር ለሞተ መታሰቢያ ሆኖ እንዲቀር መቃብሬ
መኖር አልፈልግም ሞቸ ልደር ዛሬ

+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
++++++++

ጣቶችሽ አለንጋ
አቤት ሲያናዝዙ
ካንቺ ጋራ ፍቅር
ብዙ ነው መዘዙ

መግነጢሳዊ ኃይል
ገላሽ እየሳበኝ
ለማምለጥ አልቻልኩም
እንደ ወጥመድ ይዞኝ

ያው መቸም እኔም እንደሰው

አንዳንዴ÷ አንዳንዴ ብቻ÷ ሕሊናዬን እውነት ሲያምረው

ሰብሰብ ብዬ እማስበው

“ቀድሞስ ቢሆን ለኔ ብጤ÷ ለኔ ብጤ የሔዋን ዘር

አዳሜ በኔ ላይ በቀር÷ ለኔ መስክሮ አይናገር”

ብዬ ከልቤ ስማከር

እኔው ከኔው ስከራከር

ተጨብጨ እማብላላው

ያው መቸም እኔም እንደሰው

የሐቅ ራብ ነፍሴን ሲያከው

ልቤ ልቤን ሲሞግተው….

“እውነትስ ምንትስ ማነው?”

እያለ ነው፡፡ …..

ያም ሆኖ ነገሬ ከልብ

ያልወጣነውና ለሕዝብ

ለማንም ያልተገለጠ÷ የራሴ ድብቅ ሱባኤ


ልቤ ከልቤ ጋር ብቻ÷ ያደረገው የዝግ ጉባኤ

ከቶ የናንተን ዳኝነት÷ አልጠይቅምና ስሙኝ

ፋይል ከፋች እንዳትሉኝ፡፡ ……

ያው ብቻ በዘልማድ ሕግ÷ በእንቶ ፈንቶአችሁ ልረታ…….

እውነቱ ከእውነቱ ተፋጭቶ÷ ሐቅ ሆኗልና ሽውታ

ስለዚህ አንዳንዴ ብቻ÷ አልፎ አልፎ ብቻ ላንዳፍታ

አሳቤም ሥጋዬም አብሮ÷ ትንፋሼም ሲያገኝ እፎይታ

ምንትሶች ለምትሉን÷ የለንምና ጸጥታ

ከዚያ ከሌት ውጣ ውረድ÷ ከቀን መኝታው ድውታ

ላመል ታህል ብቻ ድንገት÷ ለሃሣብ ንቃት ለትዝታ

ገለል ቀለል ሲለኝቨለስንቱ ሆይታና ዋይታ

ከዳር ዋጋው ካንድ ጊዜው÷ ከሂሣብ ዛቻው ቆይታ

ከግራ-ማ-ፎን ቀረርቶው÷ ከድም-ድሙ ካካታ

ከሙዚቃው ሆያ ሆዬ÷ ከናላ-ወቀጣው ፋታ

ከዳንኪራው ውትር ግትር

ከመጠጡ ብዥ ድንብር

ትንሽ የህሊና ሰላም÷ አገኘሁ ስል …. የሚለኝ ቅር

እንደገና ለብቻዬ÷ ልቤን ቁስል የሚያጭር

አለብኝ የሐቅ ብትር

ነፍሴን ከስሶ እሚያከራክር

እንደዛር እሚጎነትል÷ ሐቅ እንድጠይቅ የሚያስጥር÷

ያራቡኝ÷ ያጠሙኝ÷ የነሱኝን የሐቅ ዕድር

እንድጠይቅ÷ እንድጠይቅ÷ የሚያረገኝ እርር ክርር

ነፍሴን ከልቤ እሚያሟግት÷ በሐቅ ራብ እስካጣጥር

መንፈሴ ውስጥ የሚያቃጭል

‘እውነትስ ማን ነው ምንትስ?’÷ አስቲ እንጠያየቅ የሚል…..


ሕመም አለኝ÷ …. ይኸም ሆኖ÷ እግዜር ያሳያችሁ ላልል

ለይታችሁ አጥራችሁኝ÷ ከዳኝነታችሁ ባህል

ከፍርድ አደባባይ ክልል÷

ለኔ ከቶ ላታውቁልኝ

ነውር በቀር ላታዩብኝ

ጠር በቀር ላታስቡኝ

የሕሊናችሁን በደል÷ በኔ ለምትወጡብኝ

ምንትስ ከማለት በቀር÷ ሌላ ምን ላታስገኙልን

መቸም ቢሆን እኔ እናንተን÷ እግዜር ያሳያችሁ ላልል

እዘልቃት እንደሁ ነው እንጂ÷ ከልቤ ጋር አለብካይ…..

መሃላ አለኝ÷ ትናንት አንኳ÷ የእህቴ ልጅ እንኳ ትላንት÷

የስጋ ዘመድ ያጥንት÷ የደም መተሣሠር ገፍቷት

አገር አቋርጣ ልታየኝ

ልታጫውተኝ ልትጠይቀኝ

ልታዋየኝ ልታቀርበኝ

ችግርሽ ገባኝ ልትለኝ

ከዘመድ ልትደባልቀኝ

የወግ መሰላል ልትሆነኝ

ካገር ልታመሳስለኝ

አዲስ ዘዴ ልታሳየኝ

እንደመጻሕፍቷ ብርሃን÷ አርቃ ልታሳስበኝ

በመንፈስ ውድቀት እነዳልርቅ÷ በርቺ ልትል ልታቀርበኝ

መጣች ብዬ ሳሳስቃት

ሳጎርሳት ስገባብዛት

ልቤ ፈክቶ ሳደምጣት÷

… የእህቴ ልጅ እንኳ ትላንት


ለካ እሷስ ‘ቦይ-ፍሬንድ’ ብጤ÷ ‘ዳር-ልግ’ እምትሉት ሽቷት

ምሥጢር የሚያመሳጥራት

አሳስቧት÷ አሰኝቷት

የሚያሳውቅ÷ የሚያስተምር÷ ልቦና የሚከፍትላት

ለጊዜው÷ ለጊዜው ብቻ÷ በኔው ቴፕ እያራመዳት

በኔው መጠጥ እያጣጣት

በኔው ሶፋ እያስጠናት

ችግሯን ከተረዳላት

ኋላ …. ደብተር መግዣ እሚላት

አሰኝቷት÷ አሳስቧት

ነበር ለካ የደከመችው

ያገር የወገወ ድልድል÷ ድንበሩን የዘለለችው

የባህሉን የሥርዓቱን÷ ክልል የተሸገረችው

የሥልጣኔ መጽሐፏን÷ ድርሳኗን የዘረጋችው …..

እና አንዳንዴ÷ አንዳንዴ ብቻ÷ እኔው ከኔው ስመካከር

ከልቤ ጋር ስከራከር

ያው መቸም እኔም እንደሰው

የሐቅ ራብ ነፍሴን ሲያመው

እኔንስ ያሉትን አሉኝ÷ “ግን የእውነት ምንትስ ማን ነው?”

እያልኩ ነው፡፡

ይህ ነው አንዳንዴ እሚያጽናናኝ

ከሀሰት ሀፍረት የሚያዋጣኝ

ከንፈሩን ለሚመጥልኝ÷ ለሚያዝንልኝ እንዳዝንለት

ከንፈሩን ለሚነክስብኝ÷ በሚያዝንብኝ እንዳዝንበት

ለወረት ይፍታሽ ለሚለኝ÷ ወረት ይፍታህ እንድልበት

በሚያሾፍ እንዳሾፍበት
በሚስቅ እንድስቅበት

በቀን ለሚንበላጠጡ

በሌት ለሚብለጠለጡ ….

እንደቀንድ አውጣ ሰንኮፈን÷ እንጭጭ ሕሊና ያወጡ ….

የሴቶች አብሮ አደጎቸም÷ ባሎች እየፈረጠጡ

በጨለማ እየወጡ÷ እያዋጡ እየዋጡ

ሁሉም በተራ ከመጡ

በወሬም በማሽቃበጡ

በኔው ሥራ እኔን ሲበልጡ

ሴቶቻቸው ፈንታቸውን÷ ከኛው ጋር ሊበላለጡ

ለይስሙላ ለወግ ብቻ÷ እኛኑ እያሽሟጠጡ

ስልካቸውን መዋዋያ÷ እያረጉ ቢያሽቃብጡ

ቢሮአቸውን ሱቅ አድርገው÷ እየዋሉ ቢጋለጡ

ያው አልፈው በወረታችን÷ በእንጀራችን ላይ በመጡ

በገንዘቡም በሌላውም÷ ስጦታ እየተሰጣጡ

በምሥጢር ሲቀማመጡ

ባልና ሚስቱ በገሃድ÷ በንግዳችን በገቡብን

ገቢያችንን ወስደውብን

ስሙን ብቻ በተውልን ….

በዚህ ላይ ጩኸታችንን÷ ጭምር ነጥቀው ሲጮኹብን

መልሰው ደሞ ሲያዝኑልን

ለወግ ሲመጻደቁብን ….

ህሊናቸውን ባይሹት÷ ኀዘን የሚሹት እነሱ

ለሰባት እምነት ሲምሱ÷ በሰባት ምላስ ሲያወሱ

ባንደኛው ሲነካከሱ

በሌላው ሲሞጋገሱ
በሦስተኛው ሲነካከሱ

ሌት ዓይኑን ላፈር ያሉትን÷ ሳይነጋ የሚያወድሱ

እነሱን አርጎብን ጨዋ÷ የሸንጎ የባህል አዋይ

የሥነ-ሥርዓት ደላዳይ

መራጭ ቆራጭ ቀናን ከአባይ

ጨዋ መሳይ÷ ንጹህ መሳይ

ከኔ ምንም ላይሻሉ÷ ደሞ እኔን ምንትስ ባይ!

“ከሌባ ሌባ ቢሰርቀው

ምን ይደንቀው” እንደሚባለው

እኔንም የሚያስደንቁኝ

ከኔ አንሰው እኔን ሲያወግዙኝ፤

በገዛ ስማቸው እኔን÷ ባፍ ሙሉ ምንትስ ሲሉኝ፤

ይደነቅላቸው እንጂ÷ ያም ቢሆን በቃን ላይሉ

ወኔአችንን ካልበከሉ

በሥጋችን እንደጣሉን÷ መንፈሳችንን ካልጣሉ

ቅስማችንን ልባችንን÷ ሌት-ተቀን ካላቃለሉ

ዓሜን ብለን እስክናምን÷ ምንትስ ነን በሉ እያሉ

ሲያሽቃብጡ ሲያዳልሉ …

ስንቱን በኛ ላይ ማጋፈር÷ ለይስሙላ መካካሻ

ወይ ለንዴት መቀነሻ

ወይ ለበቀል ማስታገሻ

ወይ ለመሃላ ማፍረሻ ….

ኧረ ስንቱ÷ ሞልቶ ስንቱ÷ ብኩን የመንፈስ ምንትስ

ለስጋውም አብሮን ወድቆ÷ ዳግም በአእምሮው ሲረክስ

በልቦናውም ሲሴስን÷ በሕሊናው ሕግ ሲድስ

‘ፍሪ-ደሜ’ ነው እያለ÷ የኔኑ ደም ሲያልከሰክስ


በቃሉና በመንፈሱ÷ ወድቆ ደቅቆ ሲበሰብስ

ቴህ ወዲያ ማነው ምንትስ!

ከስጋው አልፎ በአእምሮው

ዘምቶ ወድቆ ተሰብሮ

ከኔ እኩል ለገንዘብ ሰክሮ

በቃልና ባንደበቱ÷ ከኔ ይበልጥ አመንዝሮ

ገበናውን እንዳዋጅ ቅዳጅ÷ ከቤት ሾልኮ የትም ስታይ

ልቅሶ ላይ ሆነ አደባባይ

ጎረቤት ሆነ ገበያ÷ ቤተ-ታቦት ቤተ-ጠንቋይ

በመኪና ወይ በጫካ÷ በጭለማ ወይ ጣይ ለጣይ ….

ዝም ብንል ብናደባ÷ ዘመን ስንቱን አሸክሞን

የጅልነት እኮ አይደለም÷ እንድንቻቻል ነው ገብቶን

ገልጦ ታይቶን ሁሉ ታውቆን

እንጂ÷ አይደለም ተስኖን

ጨዋ እሚባል ማን አለና÷ ደሞ ማን ምንትስ ሊሆን÷ ….

እማማና አባባ እንኳ÷ የልቤን የምነግራቸው

ምንም የማልደብቃቸው

አንዳንዴም ሲቸግራቸው ….

ገንዘብ ቋጥሬ ይዤላቸው

መጦሪያ እሚሆናቸው

ድካምና ሽምግልና÷ ጎረቤት ፊት ሳይጥላቸው

ጎጆ ልቀልስላቸው

የግብር ልከፍልላቸው

ሄጀ÷ ዘመድ አዝማድ መሃል÷ ተፈራርቀው ሲመርቁኝ

ጉልበታቸውን እንደሳምኩ÷ ቡራኬአቸውን ሳይሰጡኝ÷

… አባባና እማማ እንኳን÷ ካንድ ልቤ … እኩል የሚያውቁኝ


ዝቅ እንዳልኩ ሳልነሳ÷ ተንበርክኬ ሲመርቁኝ

እዚያው ተጠቃቅሰው አሙኝ÷

በዓይንና በግንባር ጥቅሻ÷ ከዘመድ አዝማድ ጋር በሉኝ÷

ጉድ ብለው እያስታወሱ

በገጻቸው እያወሱ

ከንፈር እየተናከሱ

በዓይን እየተጠቃቀሱ

የልጅነቴን ሳይረሱ

ከጎረቤቱ መሃከል÷ እነማን እንደለመኑኝ

እንቢ ስልም የሰደቡኝ

እሺ ስል ጉድ-ፈላ ያሉኝ

ወይም ከኔው አድረው ውለው÷ ኋላ ያች ምንትስ ያሉኝ

እነማን እንደነበሩ÷ ሁሉንም አስታውሰው አሙኝ÷

በጎረቤቱ መሃከል÷ አንዳችም ወሬ ሳይረሱ

በዓይን እየተጠቃቀሱ

ከግራቸው ሥር ሳልነሳ÷ ቡራኬውን ሳይጨርሱ ….

አሙኝ

ሥጋዬን ከተፉኝ

ከዘመድ አዝማድ ጋር በሉኝ፡፡ ….

ታዲያን እኔንም እንደሰው

አንዳንዴ÷ አንዳንዴ ብቻ÷ ሕሊናዬን ሀቅ ሲያምረው

ዳኝነት የእግዜር ነውና÷ ልቤን ፍረደኝ የምለው

“እውነትስ ምንትስ ማነው?”

እያልኩ ነው፡፡ ….

ግን አንዳንዴ እምዘነጋው÷ ሳስታምም የስሜን ቁስል

አለነሱም የለኝም ብል
ቢያሙኝ ነውና የባህል ….

ምነው በተለይ በነሱ÷ ብቻ ለምን ይቅርባቸው

እያልኩም ነው፡፡

… ደሞ ያባባም የእማማም÷ አልፎ ቀርቶ ደሞ ዛሬ

እንዲህ የስም ማቅ ለብሼ÷ ነፍሴን ጭምር ተዘክሬ

ተገንጥዬ ተነውሬ

አይሰበሩት ስብራት÷ የስም ቅጭት ተሰብሬ

ክብሬን አንገቴን ቀብሬ

አንድ ልጄን አስተምሬ

አስጨርሼ ተቸግሬ

አልፎ÷ ‘ግራ-ዱኤት’ ሲሆን÷ ደሞ አዲስ ችግር ያሳየኝ!

የሠርጉ ዕለት ከእጮኛው ጋር÷ ጠርቶ እንዳያስተዋውቀኝ

…. ማን ይበለኝ÷ ምን ይበለኝ

ስም አጠረው÷ ስም አጠረኝ፡፡

እኔን÷ ልጄን÷ ግራ ይግባኝ!

እኔን እናትክን ስም ይጥፋኝ÷

አትጥራኝ አልኩት÷ አትጥራኝ

አታስታውሰኝ አልኩት እርሳኝ ….

ይህም ሆኖ እኔ ልጄን÷ እግዚአብሔር ያሳይህ አልል

ቢከብደው ይሆናልና÷ ማለፍ ከትምህርቱ ክልል

ከሥልጣኔውን ኬላ ደፍ÷ እሱም ከሱ ዘመን ባህል÷

እግዜር ያሳይህም ብለው÷ ቢጥርም ሊያሳየኝ ላይችል

በእውቀቱ ብስለት ተቆርጦ÷ ተበጣጥሶበት የኔ ውል

እንደገና የሱም ዘመን÷ አዲስ ባወጣው ድልድል ….

ታጥሮ የኔ ዕድል ከሱ ዕድል÷

እና ምንም ቢሆን ልጄን


ፍቅሬን የመጨረሻዬን

ስም ያጣልኝን አንድዬን

ባላዋለኝ ውል እንዳልውል

ያውጣህ እንጂ ከዚህ እክል

ይኸው ቃል ለምድር ለሰማይ÷ እግዜር ያመልክትህ ላልል!

ብቻ አንዳንዴ እየረሳሁት

አንዳንዴ እኔም እንደሰው÷ ልቤን እያስዘነጋሁት

ለትንፋሽ ያህል ለእፎይታ÷ ፋታ ብጤ እየሰጠሁት

ከዳንሱ ዳንኪራ ርግደት

ከሙዚቃው ዋይታ ግዝፈት

ከፍካሬ ኢየሱስ ጥሪ÷ ከፋንፍር ነጋሪት ግለት

ከሃሳዊ መሲሃን ጩኸት

ከነጉግ ማንጉግ መለከት

እኔም እንደሰው አንዳንዴ÷ ልቤን እያስዘነጋሁት

ሕሊናዬ እያመለጠኝ÷ ያ በመጠጥ የሸፈንኩት

በውስኪ እንፋሎት ያፈንኩት

በዕድሜ ቁስል የጠቀምኩት

ተግ ይልና÷ ብቅ ይልና÷ በገሃድ እያስተዋልኩት

የሐቅ ራብ እንደፈራሁት

ግትር ብሎ ግንባሬ ላይ÷ በቁም እየተፋጠጥኩት

ልቤን ልቤን ሲያማክረው

“በቁም መረሳት÷ መጥፎ ነው!”

እንኳ ቢለው

ዳኝነት የእግዜር ነውና÷ እኔም ፍረደኝ የምለው

“እውነትስ ምንትስ ማነው?”

እያልኩ ነው፡፡
የ አማርኛ ተረት እና ምሳሌ ዝርዝር
ሀ ሳይሉ ጥፈት ውል ሳይዙ ሙግት
ሀ ባሉ ተዝካር በሉ
ሀ ባሉ ደሞዝ በሉ
ሀሜተኛ ነው ከዳተኛ
ሀሜተኛ ያፍራል ሀስተኛ ይረታል
ሀሜት አይቀር ከድሀም ቤት
ሀሜትና ጅራት በስተኋላ ነው
ሀምሌ ቢያባራ በጋ ይመስላል
ሀምሌና ሙሽራ ሳይገለጡ ነው
ሀምሌን በብጣሪ ነሀሴን በእንጥርጣሪ
ሀምሳ ሎሚ ለሀምሳ ሰው ጌጡ ለአንድ ሰው ሸክሙ
ሀረጉን ሲስቡት ዛፉ ይወዛወዛል
ሀረጉን ሳብ ዛፉ እንዲሳሳብ
ሀረግ ለመዳፍ አልጋ ለምንጣፍ
ሀሰተኛ ምስክር ጉልበት ይሰብር
ሀሰተኛ ሲናገር ይታወቃል ስሱ ሲበላ ይታነቃል
ሀሰተኛ ሲናገር ይታወቃል በሶ ሲበሉት ያንቃል
ሀሰተኛ በቃሉ ስደተኛ በቅሉ
ሀሰተኛ ብርቱ ወንጀለኛ
ሀሰተኛ ያወራውን ፈረሰኛ አይመልሰውም
ሀሰተኛን ሲረቱ በወንድም በእህቱ
ሀሰት ስለበዛ እውነት ሆነ ዋዛ
ሀሰት ቢናገሩ ውቃቢ ይርቃል
ሀሰት ነገር ክፉ ገሀነም እሳት ትርፉ
ሀሰት አያቀላ እውነት አያደላ
ሀሰት አያድንም መራቆት መልክ አያሳምርም
ሀሰትና ስንቅ እያደረ ያልቅ
ሀሳቡ ጥልቅ ነገሩ ጥብቅ
ሀሳብ ከውለታ አይቆጠርም
ሀሳብ ከፊት አይፈታ ሙት አይመታ
ሀሳብ ያገናኛል ፍራት ያሸኛኛል
ሀሳብ ያገናኛል ፍርሀት ያሸኛኛል
ሀሳብህን ጨርቅ ያድርገው
ሀሳብና መንገድ ማለቂያ የለውም
ሀስት እያደር ይቀላል እውነት እያደር ይበራል
ሀስት እያደር ይቀላል እውነትና ውሀ እያደር ይጠራል
ሀብታም ለሀብታም ይጠቃቀሱ ድሀ ለድሀ ይለቃቀሱ
ሀብታም ለሰጠ የድሀ ሙርጥ አበጠ
ሀብታም ለሰጠ የድሀ ሙርጥ ያብጣል
ሀብታም ለሰጠ ደሀ ምንጭሩ አበጠ
ሀብታም ለሰጠው ደሀ ይንቀጠቀጣል
ሀብታም ሊሰጥ የደሀ ቂጥ ያብጥ
ሀብታም ሊሰጥ የደሀው ሙርጥ ያብጣል
ሀብታም ሊሰጥ ደሀ ምርጥ ያወጣል
ሀብታም ሲወድቅ ከሰገነት ድሀ ሲወድቅ ከመሬት
ሀብታም በመመጽወቱ ድሀ በጸሎቱ
ሀብታም በከብቱ ድሀ በጉልበቱ
ሀብታም በወርቁ ድሀ በጨርቁ
ሀብታም በገንዘቡ ይኮራል ድሀ በጥበቡ ይከብራል
ሀብታም በገንዘቡ ድሀ በጥበቡ እርስ በርስ ይቃረቡ
ሀብታም ቢሰጥ አበደረ እንጂ አልሰጠም
ሀብታም ቢያብር ድህነትን ያጠፋል
ሀብታም ነው መባል ያኮራል ድሀ ነው መባል ያሳፍራል
ሀብታም እንደሚበላለት ድሀ እንደሚከናወንለት
ሀብታም ያለ ድሀ አይኮራም ድሀ ያለ ሀብታም አይበላም
ሀብታም ገንዘቡን ያስባል ድሀ ቀኑን ይቆጥራል
ሀብት እና እውቀት አይገኝ (ም ) አንድነት
ሀብት የጠዋት ጤዛ ነው
ሀኪም ሲበዛ በሽተኛው ይሞታል
ሀኪም የያዘው ነፍስ ባያድር ይውላል
ሀኪሞች እስኪመካከሩ በሽተኛው ይሞታል
ሀዘንሽ ቅጥ አጣ ከቤትሽ አልወጣ
ሀዘንና ደስታ ጎን ለጎን ናቸው
ሀዘንን የፈራ በደስታ የተጣራ
ሀይለኛ ውሀ አሻቅቦ ይፈሳል
ሀይለኛ ዱቄት ከነፋስ ይጣላል
ሀይማኖቱ ከጅማት ጉልበቱ ከብረት የጠና
ሀይማኖት ከግብር ጸሎት ከፍቅር
ሀይማኖት የሌለው ሰው ልጓም የሌለው ፈረስ ነው
ሀይማኖት ያለ ፍቅር ጸሎት ያለ ግብር
ሀጢአት ለሰሪው ምህረት ለአክባሪው
ሀጢአት ሲደጋገም ጽድቅ ይመስላል
ሀጢአት ሳያበዙ በጊዜ ይጓዙ
ሀጢአት በንስሀ በደል በካሳ
ሀጢአት በንስሀ እድፍ በውሀ
ሀፍረት ያከሳል ያመነምናል

ሁለተኛ ደሞ ለዘበኛ ! አሉ
ሁለተኛ ግፌ ጫንቃዬን ተገርፌ ልብሴን መገፈፌ
ሁለተኛ ግፍ ልብሴን ይገፍ ጀርባዬን ይገርፍ
ሁለተኛ ጥፋት ቆሞ ማንቀላፋት
ሁለተኛ ጥፋት ከገበያ ማንቀላፋት
ሁለተኛ ጥፋት ከገበያ ቆሞ ማንቀላፋት
ሁለቱን ወንበዴ በአንድ ዘዴ
ሁለቱን የተመኘ አንዱንም አላገኝ
ሁለቴ ሰላምታ አንዱ ለነገር ነው
ሁለት ሆነው የተናገሩት በመሬት የቀበሩት
ሁለት ሞት መጣ ቢለው አንዱን ግባ በለው አለ
ሁለት ሞግዚት ያለው ህጻን ያለጥርጥር በእሳት ይቃጠላል
ሁለት ቁና ሰጥቼ አንድ ጥንቅል
ሁለት ባላ ትከል አንዱ ሲስበር ባንዱ ተንጠልጠል
ሁለት ባላ ትከል አንዱ ሲነቀል ካንዱ ተንጠልጠል
ሁለት ብልጥ ኑግ አያደቅ
ሁለት አይወዱ ከመነኩሴ አይወልዱ
ሁለት አይወዱ ከመነኮሱ አይወልዱ
ሁለት አይወዱም ከመነኮሱ አይወልዱም
ሁለት አገር አራሽ ለባልንጀራው አውራሽ
ሁለት አፎች ባይናከሱ ይናቀሱ
ሁለት እግር አለኝ ብሎ ሁለት ዛፍ አይወጡም
ሁለት እግር አለኝ ብሎ እሁለት ዛፍ አይወጣም
ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ አይወጣም
ሁለት ወፎች ባይናከሱ ይናቀሱ
ሁለት የተመኘ አንድም አላገኘ
ሁለት የወደደ አንዱን ሳያገኝ ሄደ
ሁለት ጉድጓድ ያላት አይጥ አትሞትም
ሁለት ጊዜ በላህ ተፋህ
ሁለት ጊዜ ተናገርህ ከፋህ
ሁለት ጊዜ ተናግረህ ከፋህ
ሁለት ጊዜ ነው የዶሮ ልደት አንዱ በእንቁላል አንዱ በጫጩት
ሁለት ጊዜ ይፈርዱ ጉድ ይወልዱ
ሁለት ጥፉ ካገር ይጥፉ
ሁሉ ሄደ ተበተነ እህና እኔ ቀረነ አለ ያዘነ
ሁሉ ሄዶ ተበተነ እህና እኔ ቀረነ አለ እያዘነ
ሁሉ ሆነ ቃልቻ ማን ይሸከም ስልቻ
ሁሉ በእጄ ሁሉ በደጄ
ሁሉ ቢናገር ማን ይሰማል
ሁሉ አማረሽን ዲስኮ (disco) አታውጧት
ሁሉ አማረሽን ገበያ አታውጧት
ሁሉ አማረኝን ገበያ አታውጣት
ሁሉ አረሰ ማን ይሸምት
ሁሉ የሚገኝ ከእሱ የሚገኝ የለም ያለእርሱ
ሁሉ ያልፋል እስኪያልፍ ያለፋል
ሁሉ ያልፋል እውነት ብቻ ይተርፋል
ሁሉም ሰው መምሰሉ ባይታይ አመሉ
ሁሉም ሸክሙን ፍቅርም ያዥውን
ሁሉም በየዘመድህ ቢሉት አክንባሎ ጋጥ ገባ
ሁሉም በየዘርህ ቢሉት አከንባሎ ጋጣ ገባ
ሁሉም አካል ነው ግን እንደአይን አይሆንም
ሁሉም ከልኩ አያልፍም
ሁሉም ከኋላው ያገኘዋል እንደስራው
ሁሉም ወንፈሉን ፈታይም ድውሩን
ሁሉም ያልፋል እውነት ብቻ ይተርፋል
ሁሉም ያልፋል የሚኮርጅም ቢሆን
ሁሉም ያልፋል ግን እስኪያልፍ ያለፋል
ሁሉን ለእኔ አትበል
ሁሉን ቢናገሩት ሆድ ባዶ ይቀራል
ሁሉን አውቆ አሳውን እሾህ ከስጋው ለይቶ
ሁል ጊዜ ባሬራ ትበያለሽ ወይ አንዳንድ ጊዜ እንኳ ወጥ አትይሞይ
ሁል ጊዜ ከመደንገጥ አንድ ጊዜ መሸጥ

ሂዳ ጉበት ቢነሷት ታናሽ ታላቅ ስደዱልኝ አለች
ሂዳ ጉበት የነሷት ታናሽ ታላቅ ስደዱልኝ አለች
ሂዳ ጉበት ይነሷታል ታናሽ ታላቅ ላኩልኝ አለች
ሂድ አትበለው እንደሚሄድ አርገው
ሂድ አትበለው እንዲሄድ አድርገው
ሂድ ካገር ኑር ካገር

ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም
ህልም አለ ተብሎ ሳይተኛ አይታደርም
ህመሙ ቀርቶ ሞቱን በሰጠኝ
ህመሙ ቀርቶ ሞቱን በተወኝ
ህመሙን የሸሸገ መድሀኒት የለውም
ህመሙን የደበቀ መድሀኒቱም አልታወቀ
ህመሙን የደበቀ መድሀኒት የለውም
ህያዋን ለነገስታት ሙታን ለካህናት ይገብራሉ
ህዳር መማረሪያ ሰኔ መቃጠሪያ
ህግ ይኖራል ተተክሎ ስርአት ይኖራል ተዛውሮ

ሆሆሆ ስቄ ልሙት አለ ሰውየው
ሆቴል ቢያብር ገንዘብ ያስገኛል
ሆደ ሰፊ ነገር አሳላፊ
ሆደ ሰፊ ይሻላል ከአኩራፊ
ሆዱ ሲሞላ ፍቅሩ ሌላ
ሆዱ ሲጎድል ሰው ያጋድል
ሆዱ ናረት ሙያው ከጅረት
ሆዱ ወድዶ አፉ ክዶ ክፉ ለምዶ
ሆዱ ፈሪ እግሩ ዳተኛ አዳም ሲዋጋ እርሱ ይተኛ
ሆዱን የወደደ ማእረጉን የጠላ
ሆዱን የወደደ ማእረጉን ይጠላል
ሆዱን ያለ ሆዱን ተወጋ
ሆዳም ሰው እንብርት የለውም
ሆዳም ቢሸከም የበላ ይመስለዋል
ሆዳም ቢፈተፍት የጠገበ ይመስለዋል
ሆዳም ፍቅር አያውቅም
ሆዴ ሆዴ የሚለውን ጌታ ያየዋል አይኔ አይኔ የሚለውን ሰው ያየዋል
ሆዴ በጀርባዬ ቢሆን ገፍቶ ገደል በጣለኝ
ሆዴ ኑር በዘዴ
ሆዴ አታጣላኝ ከዘመዴ
ሆዴን በልቶኝ ጎኔን ቢያኩኝ አይገባኝ
ሆድ ሆዴን የምትል ወፍ አለች ምናለች
ሆድ ለማታ በልቶ ለጠዋት
ሆድ ለባሰው ማጭድ አታውሰው
ሆድ ለባሰው ቢላዋ አታውሰው
ሆድ ለተተባሰው ማጭድ አታውሰው
ሆድ ሲሞላ ራስ ባዶ ይቀራል
ሆድ ሲያር ጥርስ ይስቃል
ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ
ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ጠዋት
ሆድ ባዶ ይጠላል
ሆድ ባዶን ይጠላል
ሆድ እንዳሳዩት ነው
ሆድ ከሁዳድ ይስፋል
ሆድ ካገር ይስፋል
ሆድ ወዶ አፍ ክዶ ክፉ ለምዶ
ሆድ ዘመድ ሳይወድ አፍ እህል ሳይለምድ
ሆድ የሸሸገውን ብቅል ያወጣዋል
ሆድ የኔ ነው ሲሉት ቁርጠት ሆኖ ይገድላል
ሆድ ያበላውን ያመሰገናል
ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል
ሆድህን ጎመን ሙላው ጀርባህን ለጠላት አታሳየው
ሆድና ግንባር አይሸሸጉም
ሆድና ግንባር አይሸሸግም
ሆድን በጎመን ቢደልሉት ጉልበት በዳገት ይለግማል
ሆድን በጎመን ቢደልሉት ጉልበት ዳገት ላይ ይለግማል
ተረት ለ
ለሀምሳ ጋን አንድ አሎሎ ይበቃል
ለሀብት መትጋት ሰውነትን ያከሳል ገንዘብን ማሰብ እንቅልፍ ይነሳል
ለሀጥአን የወረደ ለጻድቃን ይተርፋል
ለሁሉም ጊዜ አለው
ለሂያጅ የለውም ወዳጅ
ለህልም ምሳሌ የለውም
ለሆዳም ሰው ማብላት ውቅያኖስን ለመደልደል መቃጣት
ለሆዳም በሬ ገለባ ያዝለታል
ለሆዳም በሬ ጭድ ያዝለታል
ለሆዳም በሬ ቫት ተከፈለ
ለሆዳም በቅሎ ጭድ ያዝለታል
ለሆዴ ጠግቤ በልብሴ አንግቤ
ለሆድ ቁርጠት ብላበት ለራስ ምታት ጩህበት
ለላሙ መንጃ ለሸማው መቅደጃ
ለላሙ መንጃ ለሸማው መከንጃ
ለላም ቀንዷ አይከብዳትም
ለላም ከጥጃዋና ከአላቢዋ ማን ይቀርባታል
ለላም የሳር ለምለም
ለላም ጥጃዋ ለአህያ ውርንጭላዋ
ለሌለው ምን ትለው
ለሌባ ቅሌት ልብሱ ነው
ለልደት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ
ለልጅ ሲሉ ይበሉ ለወዳጅ ሲሉ ይጠሉ
ለልጅ ሲሉ ይበሉ ለወገን ሲሉ ይጠሉ
ለልጅ አይስቁለትም ለውሻ አይሮጡለትም
ለልጅ ከሳቁለት ለውሻ ከሮጡለት
ለልጅ ጥርስህን ለዝንብ ቁስልህን
ለልጅ ጨዋታ ለባለጌ ቧልታ
ለሎሌው ምን ትለው
ለመሀን እምዬ ለአገልጋይ እትዬ ብርቋ ነው
ለመሄድና ለመላወስ አዛዥ ራስ
ለመሄድና ለመመለስ አዛዥ ራስ
ለመሆኑ ሳይሆን እንዴት ይሆናል ቢሆን
ለመማር ክፍል መግባት ለመኮረጅ ካሮት መብላት
ለመማር ክፍል መግባት ለማለፍ ካሮት መብላት
ለመስማት የፈጠንህ ለመናገርና ለቁጣ የዘገየህ ሁን
ለመስማት የፈጠንህ ለመናገር የዘገየህ ሁን
ለመስራት የሚያፍር መብላት አይደፍርም
ለመስራት ያፈረ ለመብላት ደፈረ
ለመስጠት አለመቸኮል ከሰጡም ወዲያ አለመጸጸት
ለመነኩሴ መልካም ሎሌ
ለመታማት መፍራት
ለመከራ ያለው መነኩሴ ዳዊቱን ሸጦ አህያ ይገዛል
ለመከራ የጣፈው ቢነግድ አይተርፈው
ለሙት የለው መብት
ለሚመለከት ለሚያየው ሞት ቅርብ ነው
ለሚስት ያጎርሷል ለተመታ ይክሷል
ለማረም ማን ብሎት ሲሰራው ግን ግድፈት
ለማን አለው ፈጣሪ አለው ጠጅ ለሌለው ውሀ አለው
ለማን ይፈርዱ ለወደዱ አይደለም ለወለዱ
ለማኝ ቢያብድ ስልቻውን አይጥልም
ለማኝ አያማርጥም ማር አይኮመጥጥም
ለማየት የፈለገ አይኑን ይገልጣል
ለማያቅህ ታጠን ብሎሀል ሀሰን
ለማያውቅ ፎገራ ዱሩ ነው
ለማያውቁሽ ታጠኚ
ለማያውቁሽ ታጥበሽ ቅረቢ
ለማይሞት መድሀኒት አለው
ለማይሰጥ ሰው ስጡኝ ማለትን ማን አስተማረው
ለማይሰጥ ሰው ስጡኝን ማን አስተማረው
ለማእበል ወደብ ለነፋስ ገደብ የለውም
ለምሽት መብራት ለመከራ ጊዜ ብልሀት
ለምክንያት ምክንያት አለው
ለምን ላለው ፈጣሪ አለው ጠጅ ለሌለው ውሃ አለው
ለምን ሰርግ ይሄዳል ሰርግ አለ በቤቱ
ለምን ተክዤ አምላክን ይዤ
ለምን ያለው ስልቻውን ጫን ያለው ኮርቻውን
ለምን ያለው ስልቻውን ጫን ያለው ኮርቻውን አያጣም
ለምን ጊዜው ነቀዝሽ
ለምኖ ለማኝ ቆቤን ቀማኝ
ለሞኝ ሰኔ በጋው መስከረም ክረምቱ
ለሞኝ ንገረው ምን ይሰማ ብዬ ለብልህ ንገረው ምን ይሳተው ብዬ
ለሞኝ ከሳቁለት ለውሻ ከሮጡለት
ለሞኝ ጉድጓድ አያሳዩትም ቤት ነው ብሎ ይገባበታል
ለሞፈር ቆራጭ እርፍ አይታየውም በግላጭ
ለረዥም ሰው ልብ እና ልብስ ያጥረዋል
ለረዥም መንገድ አትሩጥበት ለረዥም ነገር አትቸኩልበት
ለራሱ አያውቅ ነዳይ ቅቤ ለመነ ላዋይ
ለራሱ አያውቅ ጠንቋይ መድሀኒቱ ላዋይ
ለራሱ ጥላ ለእግሩ ከለላ
ለራሱ የማይረባ ለሌላም አይረባ
ለራሱ የማይረባ ለሰውም አይረባ
ለራስ ምታት ጩህበት ለሆድ ቁርጠት ብላበት
ለራሱ አያውቅ ሰው አይጠይቅ
ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ
ለራስ ቢያወሩ ለቅንቅን ይዘሩ
ለራስ ቢያወሩ ለቅንቅን ይዘሩ አለች ዶሮ
ለራስ ከበጁ አይታጡ ደጁ
ለራበው ሰው ቆሎ ለቁልቁለት በቅሎ
ለራበው ባዶ መሶብ ማቅረብ
ለራት የማይተርፍ ዳረጎት
ለርስት ሴቶች ስንኳ ይሞቱበታል
ለሰማይ ምሰሶ የለው ለባእድ ስር የለው
ለሰለባ የመጣ ልብስ ቢጥሉለት አይመለስ
ለሰለባ የመጣ ልብስ ቢጥሉለት አይመለስም
ለሰበበኛ ቂጥ መረቅ አታብዛበት
ለሰባቂ ጆሮህን አትስጠው
ለሰው ልጅ ሲያበሉ ለውሻ ልጅ ያብሉ
ለሰው ልጅ ከሚያበሉ ለውሻ ልጅ ያብሉ
ለሰው ልጅ ከማብላት ለውሻ ልጅ ማብላት
ለሰው ልጅ እውቀት ለጦጣ ብልጠት
ለሰው ሞት አነሰው
ለሰው ሞት አነሰው ውሻውንስ ፈሴ መለሰው አለች ቀበሮ
ለሰው ቢነግሩት ለሰው
ለሰው ቢናገሩ መልሶ ለሰው ጫር ጫር አድርጌ አፈር ላልብሰው
ለሰው ብሎ መሞት አምላክነት ያሻል
ለሰው ብሎ ሲያማ ለኔ ብለህ ስማ
ለሰው ብትል ትጠፋለህ ለእግዜር ብትል ትለማለህ
ለሰው እንግዳ ላገሩ ባዳ
ለሰው እንዴት F አነሰው
ለሰው ከበሬታው ሰው ለወጥ ማጣፈጫው ጨው
ለሰው ጠላቱ ይወጣል ከቤቱ
ለሰው የማይል ሰው ሞትም ሲያንሰው
ለሰው ብሎ ሲያማ ለእኔ ብለህ ስማ
ለሴትና ለጉም አይዘነጉም
ለሰይጣን አትስጠው ስልጣን
ለእሳት ውሀ ለጸጉር ቡሀ
ለሴት ልጅ እስከአርባ ቀን ሞቷን ከዚያ ወዲያ ሀብቷን
ለሴት ምስጢር ማውራት በወንፊት መቅዳት
ለሴት ምክር አይገባትም
ለሴትና ለጉም አይዘነጉም
ለሴት ጠላ ለፈረስ ቆላ
ለስሟ መጠሪያ ቁና ሰፋች
ለስሱ ፍትፍት አሳይቶ እበት ያጎርሷል
ለሸማኔ ማገጃ ስለት ማረጃ
ለሹመት ካልመከሩለት ለጥርስ ካልነከሩለት
ለሹመት ካልመከሩለት ለጥርስ ካልከደኑለት
ለሹመት ያደለው የለማኝ አለቃ ይሆናል
ለሺ ፍልጥ ማሰሪያው ልጥ
ለቀላል ምስጢር መንገር በቀዳዳ ጤፍ መቋጠር
ለቀላል ሰው ምስጢር መንገር በቀዳዳ ጤፍ መቋጠር
ለቀላል ሰው ምስጢር መንገር በቀዳዳ አቁማዳ ጤፍ መቋጠር
ለቀማኛ የለውም እጅ ለበቅሎ የለውም ልጅ
ለቀበጠች አማት ሲሶ በትር አላት
ለቀባሪው አረዱት
ለቀን ቀጠሮ ለሴት ወይዘሮ
ለቀንዳም በሬ ቤት አትከልክለው ቀንዱ ይከልክለው
ለቀንዳም በሬ ቤት አትከልክለው ቀንዱ ይከለክለዋል
ለቁንጫ ለምጽ ያወጣል
ለቁንጫ መላላጫ
ለቂጡ ጨርቅ የለው ቆንጆ ያባብላል
ለቅልብልብ አማት ሲሶ በትር አላት
ለቅሶ ሳለ ከቤት ይሄዳል ጎረቤት
ለቅናት የለውም ጥናት
ለቅዘን እግር አንስተውለት ለውሻ ሮጠውለት
ለቆመ ሰማይ ቅርቡ ነው
ለቆማጣ አንድ ጣት ብርቁ ናት
ለበራ ወለባ ለውሻ ገለባ
ለበጋ ጥጃ ውስ አነሰው ወይ
ለበግ ደጋ ለምቾት አልጋ
ለቡናሽ ቁርስ የለሽ ለነገርሽ ለዛ የለሽ
ለባለጌ ገድሉ ውርደቱ
ለቤት ሳማ ለውጭ ቄጤማ
ለቤት ሳንቃ ለሰው አለቃ
ለቤት ሳንቃ ለነገር ጠበቃ
ለቤት ባላ ለችግር ነጠላ
ለብልህ ንገረው ምን ይስተው ብዬ ለሞኝ ንገረው ምን ይገባው ብዬ
ለብልህ አይነግሩ ለድመት አያበሩ
ለብልህ አይነግሩ ላንበሳ አይመትሩ
ለብልህ አይነግሩ ለንጉስ አይመክሩ
ለብልህ አይነግሩም ለንጉስ አይመክሩም
ለብልህ አይነግሩ ካልጠየቀ በስተቀር
ለተማሪ ቆሎ ለወታደር በቅሎ
ለተሟጋች መዘዘኛ የዳኛ ትእግስተኛ
ለተረታው ያበደረ እሳት ጨመረ
ለተራበ ግብር ለተበደለ ነገር
ለተራበ በግብር ለተበደለ በነገር
ለተራበ ቂጣ ለተጠማ ዋንጫ
ለተሸሸገ ምግብ የተሸሸገ ሆድ አይጠፋለትም
ለተሾመ ይሟገቱለታል ለተሻረ ይመሰክሩበታል
ለተሾመው ይመሰክሩለታል ለተሻረው ይመሰክሩበታል
ለተሾመ ይመሰክሩለታል ለተሻረ ይመሰክሩበታል
ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው
ለተባባሰው ማጭድ አታውሰው
ለተንኮለኛ ሲሉ ይሰበስባሉ ለቅን ይፈርዳሉ
ለተወገረ የማያዝን እንብርት የለውም
ለትኋን ልጓም ማጉረስ ላፈኛ ሰው መመለስ
ለትኋን ልጓም ማጉረስ ላፈኛ ሰው መመለስ አይቻልም
ለቸኮለ ሰው ዋንጫ አስጨብጠው
ለችግር የፈጠረው ቢነግድ አይተርፈው
ለነገረኛ ሰው ጀርባህን ስጠው
ለነገረኛ ነገር ተውለት ለሆዳም እህል አቅርብለት
ለኔ ነግ በኔ
ለንጉስ የማይገዛ ለእግዚአብሄር አይገዛ
ለንጉስ ያልረዳ ከባህር የማይቀዳ
ለንጉስ ያልረዳ ከባህር ያልቀዳ
ለንፉግ ሰው የገበያ መንገድ ይጠበዋል
ለንፉግ ሰው የገበያ መንገድ ይጠበው
ለአህያ ማር አይጥማትም
ለአምላክ ልንገረው ለማያስቀረው
ለአበባ የለው ገለባ
ለአቤቱታ የለው ይሉኝታ
ለአንበሳ አታበድር ካበደርክ አትጠይቅ
ለአንተ ያለውን እንጀራ ይሻግታል እንጂ ማንም አይበላውም
ለአኩራፊ ምሳው እራት ይሆነዋል
ለአይነ ስውር መስተዋት
ለአይንና ለወዳጅ ጥቂት ይበቃል
ለአይን የሚከፋ ለአፍንጫ ይከረፋ
ለአዋጅ ነጋሪት ለጥጥ ልቃቂት
ለአገሩ እንግዳ ለሰው ባዳ
ለአፈ ግም አፍንጫ ድፍን ያዝለታል
ለአፉ ለከት የለውም
ለአፍታ የለውም ፋታ
ለአፍ ዳገት የለውም
ለእሳት እንጨት ካልነሱት አይጠፋም
ለእሳት እንጨት ካልነፈጉት አይጠፋም
ለእሳት ውሀ ለጸጉር ቡሀ
ለእሳት ፍላት ለጮማ ስባት
ለእበጥ ፍላት ለእንጨት እሳት
ለእባብ እግር የለው ለሞኝ መላ የለው
ለእብለት ስር የለው ለእባብ እግር የለው
ለእብለት ስር የለውም ለእባብ እግር የለውም
ለእበጥ ፍላት ለእንጨት እሳት
ለእኔ እናት ምን ደላት ያም አፈር ያም ድንጋይ ጫነባት
ለእውር ዝማሜ ለመላጣ ጋሜ
ለእጅ ርቆ ለአይን ጠልቆ
ለእግሩ የተጠየፈ ለቂጡ አተረፈ
ለእግር የፈሩት ለቂጥ ይተርፋል
ለእግዚአብሄር የቀነቀነ ለጽድቅ ለጌታ የቀነቀነ ለወርቅ
ለእውነት ማማ ለውሸት ጨለማ
ለከለላ ጥላ ቢርብህ ብላ
ለከሳሽ የለው መላሽ
ለካህን ጥምቀት ለገበሬ ግንቦት
ለክፋት ያደለው አሳዳጊ የበደለው
ለኮ መሳቢያ ወፍጮ ማላሚያ
ለወሬ ሞትሁ
ለወሬ ሞትሁ ለእህል ሰለፍኩ
ለወሬ ወዳጁ ወሬ ለመነኩሴ ጥሬ
ለወሬ የለው ፍሬ
ለወሬ የለው ፍሬ ለአበባ የለው ገለባ
ለወሬ የቸኮለ እናቱን በመንገድ ይረዳል
ለወርቅ ያሉት አንገት ላሽክት
ለወታደር ሰፊ መንደር ለወዲላ መልካም ዱላ
ለወይዘሮ መልካም ዶሮ
ለወደላ መልካም ዱላ
ለወዳጅ የማር ወለላ ለጠላት አሜኬላ
ለወዳጅና ለአይን ትንሽ ይበቃዋል
ለወጡም እዘኑለት ከእንጀራውም ጉረሱለት
ለወጡ ጊዜስ ከደረቁም
ለወጡም እዘኑለት ከደረቁም ብሉለት
ለወጥ የሚሻል ቅልውጥ
ለዋንጫ ቡሽ ለውሀ ጉሽ የለውም
ለዋስ አፍ የለው ለጉንዳን ደም የለው
ለውሻ ምሳ የለው ራት ብቻ
ለውሻ ሞት ፊት አይነጩለትም
ለውሻዬ ያልሁትን ልጄ ቢበላብኝ አልወድም
ለውሽማ ሞት ፊት አይነጩለትም
ለውጡኝ ባይ የሚሻለውን አውቆ
ለዘመዴ ያዝናል ሆዴ
ለዚህ ሆዴ ጠላኝ ዘመዴ
ለዝናም ጌታ ውሀ ነሱ
ለዝናም ጌታ ውሀ ነሱት
ለዝንብ ከትላንት ወዲያም ድሮ ነው
ለይቶ እንደፈፋ አንጓሎ እንዳረፋ
ለይቶት አባ ንጉሷ
ለደህና ሰው ዋጋ አነሰው
ለደህና ሰው ውሸት ለጅብ እሸት
ለደብተራ መቋሚያና ጭራ
ለደደብ ማስረዳት ድንጋይ ቅቤ መቀባት
ለደግ ንጉስ እለት እለት ማልቀስ
ለዳርቻው ሲሳሱ መካከሉን ተነሱ
ለዳርቻው ሲሳሱ ከነመሀሉም ተነሱ
ለዳባ ለባሽ ነገርህን አታበላሽ
ለዳኛ አመልክት እንዲሆን መሰረት
ለዳኛ የነገሩት በርጥብ ያቃጠሉት
ለዳኛ ዳኛ አለው ለአንበሳ ተኩላ አለው
ለድሀ ማን ሰጠው ውሀ
ለድህነት የፈጠረው ቢነግድ አይተርፈው
ለድህነት የፈጠረው ቢነግድ አያተርፍም
ለድሪ ያሉት አንገት ለአሸንክታብ
ለድሪ ያሉት አንገት ላሽክት
ለድካም የጣፈኝ ብነግድ አይተርፈኝ
ለዶሮ ሲነገሩ ምጥማጥ ይሰማል
ለጆሮ ጥርስ ለሆዳም ስስ
ለገላጋይ ደም የለውም
ለገበሬ መልካም በሬ
ለገቢህ ተንገብገብ
ለገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ
ለገደለ ጎፈሬ ላረጋገጠ ወሬ
ለገዳም የረዳ አይጎዳ
ለጉንዳን ደም የለው ለዝንብ ቤት የለው
ለጉንዳን ደም የለው ለገንዘብ ቤት የለው
ለጋስ ቢለግስ አበደረ እንጂ አልሰጠም
ለጋስ ቢለግስ አበደረ እንጂ እንዲያው አልሰጠም
ለእግዜር የተቀናቀነ ጽድቅ ለንጉስ የተቀናቀነ ወርቅ
ለጎበዝ ስጠው ሰንጋ ፈረስ
ለጠላትህ እንደ ዳቦ እስኪገምጥህ አትመቸው
ለጠቢብ አንድ ቃል ይበቃል
ለጠጪ ሰው የመጠጥ ወሬ አውራው
ለጥልና ለዳኛ ያለው ገንዘብ አፋፍ ይቆያል
ለጥርጣሬ ምንጣሬ
ለጥቅም ሲታጠቁ ከጎን ይጠንቀቁ
ለጥቅምት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ
ለውጠኝ ባይ የሚሻለውን አውቆ
ለጨለማ ጊዜ መብራት ለመከራ ጊዜ ብልሀት
ለጨቅጫቃ ሰው ከማበደር ይሻላል በጄ ማደር
ለጭሰኛ መሬት ለሳር ቤት ክብሪት
ለጾም ግድፈት ለበአል ሽረት
ለጾም ግድፈት ለባል ሽረት
ለፈረስህ አንገት ለጋሻህ እንብርት
ለፈሪና ለንፉግ እያደር ይቆጨዋል
ለፈሪ ሜዳ አይነሱም
ለፈሪ ምድር አይበቃውም
ለፈሪ ይበቃል ፍርፋሪ
ለፈሪ ስጠው ፍርፋሪ
ለፋሲካ የተዳረች ሁል ጊዜ የፋሲካ ይመስላታል
ለፍቅር ብተኛት ለጠብ አረገዘች
ለፍቅር የለውም ድውር
ለፍየል ቆላ ለሙክት ባቄላ
ለፍየል ህመም በሬ ማረድ
ለፍየል ስም አውጣ ቢለው ሞት አይደርስ አለው
ሊበሉዋት ያሰብዋትን አሞራ ይሏታል ጂግራ
ሊወጋ የመጣ ጌታዬ ቢሉት አይመለስም
ሊያልፍ ውሀ አደረገኝ ድሀ
ሊያስቡት አይገድም
ሊጣላ የመጣ ሰብብ አያጣም
ላህያ ፈስ አፍንጫ አይዙለትም
ላህያ ማር አይጥማት
ላህያ ያልከበደው ለመጫኛ ከበደው
ላለው ቅንጭብ ያረግዳል
ላለው ይጨመርለታል
ላለፈ አይጸጸቱም ለሚመጣው አይበለጡም
ላለፈው አይጸጸቱም ለሚመጣው አይበለጡም
ላለፈው ክረምት ቤት አይሰራለትም
ላለፈው ክረምት ውሀ ማቆር አይቻልም
ላለፈው ጸሎት ከንቱ ጩኸት
ላሊበላ ሄደሽ ከህንጻው ብትሰፍሪ አይገኝም ጽድቅ አለ ባህሪ
ላሊበላ አደራውን አይበላ
ላሊበላ የቃሉን አይበላ
ላሊበላን ካላጠገቡት ይጮሀል ሎሌም ካልሰጡት ይከዳል
ላላየ ልጅ ዳቦ ፍሪዳው
ላላየው የሚያስገርም ለሰማው የሚያስደንቅ
ላላዩ ልጅ ዳቦ ፍሪዳው
ላላወቀው ፎገራ ዱር ነው
ላመት ልብስ ለእለት ጉርስ
ላሜ ቦራ የልጆቼን ነገር አደራ
ላም ሲበዘበዝ ጭራዋን ያዝ
ላም ቀንዷ አይከብዳትም
ላም በረቱን የሰው ልጅ አባቱን አይረሳም
ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ
ላም አለኝ በሰማይ ወተትዋንም አላይ
ላም አለኝ በሰማይ ገመድ እፈልጋለሁ
ላም እሳት ወለደች እንዳትልሰው ፈጃት እንዳትተወውም ልጅ ሆነባት
ላም ከወንዝ ልጅ ከቦዝ
ላንተ መምከር ጥቁር ድንጋይ ላይ ውሀ ማፍሰስ ነው
ላንቺ ቁምነገርሽ በሶብላ ወጥሽ
ላንቺ ብርቅሽ በሶቢላ ወጥሽ
ላያዘልቅ ጸሎት ለቅስፈት
ላይቀርልኝ እዳ በጊዜ ልሰናዳ
ሌባ ላመሉ ቅድመ እውቅና አገኘ
ሌባ ላመሉ ንግድ ይላል
ሌባ ላመሉ ዳቦ ይልሳል
ሌባ እናት ልጇን አታምንም
ሌባን ሌባ ቢሰርቀው እንዴት ይደንቀው
ልባም ሴት ለባልዋ ዘውድ ናት
ልብስህን በውሀ ገንዘብህን በድሀ
ልብ ካላየ አይን አያይም
ልብ ካላየ አይን አይፈርድም
ልትደርቅ የደረሰች ምንጭ ጭልጭል ትላለች
ልትሰራ ሂዳ ተላጭታ መጣች
ልጅም ከሆነ ይገፋል ድንችም ከሆነ ይጠፋል
ልጅ ለናቷ ምጥ አስተማረች
ልጅ ምን ቢሮጥ አባቱን አይቀድምም
ልጅ ሳለህ አጊጥ ሞል ሳይዘጋ ሸምት
ልጅ ቢያኮርፍ ቁርሱ እራት ይሆናል
ልጅና እሳት ባለቤቱ ያጠፋዋል
ልጅን አሳዳጊ እሳትን ውሀ ያጠፋዋል
ልጅና ወረቀት የያዘውን አይለቅም
ልጅና ጦጣ ውሀ ይጠጣ
ልጅ ያቦካው ለእራት አይሆንም
ልጅ ይወለዳል ከቦዝ ላም ይገዛል ከወንዝ
ልጅ ደረሰ ቤት ፈረሰ
ልግመኛ ባሪያ መጇን ትደብቃለች
ልግመኛ አጋዥ ብታገኝ መጅ ደበቀች
ልግመኛን መምከር ውሀ በወንፊት ማኖር
ልፋት ቢያምርህ መሬት ግዛ ችግር ቢያምርህ ልጅ አብዛ
ልፋ ያለው ሊስትሮ እግር ስር ይውላል
ልፋ ያለው ምረጡኝ አለ
ልፋ ያለው በህልሙ ሲሸከም ያድራል
ልፋ ያለው አንድ እንጨት ያስራል
ልፋ ያለው በሬ ቆዳው ለከበሮ
ልፋ ያለው ቢን ላደንን ይፈልጋል
ልፋ ያለው አንድ እንጨት ያስራል
ሎሌ ለስህተት ጌታ ለምህረት
ሎሌ ሲከብር ጌታውን ይከሳል ሙክት ሲሰባ ሾተሉን ይልሳል
ሎሌ ያገለገለውን ይቆጥራል ጌታ ያስቀየመውን ያስባል
ሎሌና አሞሌ ካዘዙት ይውላል
ሎሚ ካልመጠጡት እምቧይ ነው
ሎሚ ካልመጠጡት እምቧይ ዳቦ ካልገመጡት ድንጋይ
ሎሚና ትርንጎ ሞልቶልህ ባገር እንቧይ ታሸታለህ የድሀ ነገር
ሎሚና ትርንጎ ሞልቶ ባገር እንቧይ ያሸታል አወይ የድሀ ነገር
ሎሚ ቢያብብ ቢኖርና መልካም ሽታ ቢሰጥ መኮምጠጡን አይተውም

ተረት መ

መሄድ በጋ ነው መቀመጥ ክረምት ነው


መሄጃ የሌለው መውጫውን ያበስራል
መልከ ጥፉ በስም ይደግፉ
መልከ ጥፏ ቆንጆዋን አስናቀች
መልካም ባል መጥፎ ሴት ይገራል
መልካም ሴት ለባሏ ዘውድ ናት
መልካም ስም ከመቃብር በላይ ይውላል
መልካም ስም ከመቃብር በላይ ይቆማል
መልካም አባት ለልጆቹ እጁን ኪሱ ይከታል
መልካም ባል መጥፎ ሴት ይገራል
መልኳ ባያምር አመሏ ይመር
መልክ ታጥቦ አይጠጣ ወይ አይበላ
መልክ ስጠኝ እንጂ ሙያ ከጎረቤቴ እማራለሁ
መመራመር ያገባል ከባህር
መሞት የፈለገ ግልገል ቀበሮ ቤት ሄዶ ይጨፍራል
መራጭ ይወድቃል ከምራጭ
መቀመጥ በአልጋ ታላቅ ደጋ
መቅረቧን ሳታውቅ እጇን ታጠበች
መብላቷን ሳታውቅ እጇን ታጠበች
መተው ነገሬን ከተተው
መቼ መጣሽ ሙሽራ መቸ ቆረጠምሽ ሽንብራ
መካር የሌለው ንጉስ አለ አንድ አመት አይነግስ
መንገድ ካገር ልጅ ምክር ከጨዋ ልጅ
መወለድ ቋንቋ ነው
ሚስቱ ክፉ ባቄላ እራቱ ብሳና እንጨቱ ሀዘን ነው እቤቱ
ሚስቱ ደግ ስንዴ እራቱ ወይራ እንጨቱ ደስታ ነው እቤቱ
ሚስቱን ጠልቶ ካማቱ ልጁን ከሶ ካባቱ
ሚስቱን ገድሎ አማቱ ቤት ተሽሽገ
ሚስት ባታብል ባሏን ትወልዳለች
ሚስት ከፈቷት ባዳ ማሽላ ከተቆረጠ አገዳ
ሚስትህ አመዳም ጎራዴህ ጎመዳም
ሚስትህ አረገዘች ወይ ቢለው ማንን ወንድ ብላ አለው
ሚስትህን ስደድ በሬህን እረድ ይላል የባለጌ ዘመድ
ሚስትና ዳዊት ከብብት
ሚስት ፈትቶ ካማት መቀለብ በእንፉቅቅ መሄድ
ሙቅ ውሀና የሰው ገንዘብ አይጠቅምም
ሚስጥርህን ለባእድ ለምን አዋየኸው ወንፊት ወሀ ይዞ የት ሲደርስ አየኸው
ማሞ ሌላ መታወቂያው ሌላ
ማር በበላሁበት በጣፈጠው አፌ ጎመን ጎረስኩበት አይ አለማረፌ
ማሽላ ሲያር ይስቃል
ማሽላ እየፈካ ያራል
ማቅ ይሞቃል ጋቢ ይደምቃል ገቢውን ባለቤት ያውቃል
ማን ሙሽራ ቢልሽ ትኳያለሽ
ማን ያውራ የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ
ማን ያውራ የነበረ ማን ይጨፍር የሰከረ
ማእድ ጠፋና አንድ ላይ በላን
ማግባቱ ቀርቶብኝ በታጨሁ
ማጣት ከሰማይ ይርቃል
ምላጭ ቢያብጥ በምን ይበጡ ውሀ ቢያንቅ በምን ይውጡ
ምን ያመጣ ድሀ ምን ያገሳ ውሀ
ምን ቢያርሱ እንደጎመን አይጎርሱ
ምንም ቢጠም መንገድ ምንም ቢከፋ ዘመድ
ምን ቢፋቀሩ አብረው አይቀበሩ
ምከረው ምከረው እንቢ ካለህ መከራ ይምከረው
ሞት በጥር በነሀሴ መቃብር
ሞት ቢዘገይ ሲኦል ስለሞላ ነው
ሞት ቢዘገይ ነው የምሄደው
ሞት ቢዘገይ የቀረ ይመስላል
ሞት የሰጠው ቀባሪ አያሳጣውም
ሞኝ ሲስቁበት የሳቁለት ይመስለዋል
ሞኝ እከኩን እያየች ስትስቅበት ወደደችኝ ብሎ ይፈነድቃል
ሞኝና ወረቀት ሊደራደሩ ነው
ሞኝና ወረቅት ኢንተርኔትን ናቁ
ሞኝና ወረቅት የያዘውን አይለቅም
ሞኝ ውሀ ሲወስደው ይስቃል
ሞኝ ዘመድ ከልጅህ እኩል አድርገኝ ይላል
ተረት ረ
ሬሳ በምኑ ይከበራል በዝምታው
ራስ ሳይጠና ጉተና
ራስ ተላጭቶ ወለባ ልባልባ ታጥቆ አዛባ
ተረት ሰ

ሰለሞን ሳባን ውሀ ባያስጠማት ኖሮ የሱ ጥም ባልበረደ ነበር


ሰውን ፈላጊ በምርጫ ይሽነፋል
ሰማይ አትረስ ንጉስ አትክሰስ
ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ
ሰባት አመት ባይማሩ ሰባ አመት ይደንቁሩ
ሰነፍ ሴት ያገባ በሬው በሰኔ ገደል የገባ
ሰነፍ በዓል ያበዛል
ሰነፍ ቢመክሩት ውሀ ቢወቅጡት
ሰነፍ ገበሬ በሰኔ ይሞታል
ሰነፍ ገበሬ ክረምት በጋው በጋው ክረምቱ
ሰኔ መቃጠሪያ ህዳር መገናኛ
ሰኔ ሰላሳ የለውም ካሳ
ሰኔና ሰኞ
ሰኔን በዘራዘር ሃምሌን በጎመን ዘር
ሰካራም ቤት አይሰራም
ሰካራም ዋስ አያጣም
ሰው መሳይ በሸንጎ
ሰው በዋለበት ውሀ በወረደበት
ሰው ቢማር ቄስ እንጂ መላክ አይሆንም
ሰው ባለው ይሰለፋል
ሰውን ማመን ቀብድ ተቀብሎ ነው
ሰውን ሰው ናቀው የራሱን ሳያውቀው
ሰውን ሰው ያሰኘው እቁብ ነው
ሰውን ሲወዱ ከነንፍጡ እና ልጋጉ
ሰውን ሲያማ ለእኔ ብለህ ስማ
ሰው አለብልሀቱ ገደል መግባቱ አለጉልበቱ ውሀ መግባቱ
ሰው አለወንዙ ብዙ ነው መዘዙ
ሰው እንደ እውቀቱ ነው
ሰው ከሞተ የለ ንስሀ ከፈሰሰ አይታፈስ ውሀ
ሰውየው ውሀ ሲወስደው እኔም ወደ ቆላ እወርዳለሁ ብዬ ነበር አለ
ሰው ያመነ ውሀ የዘገነ
ሰው ያስገድላል አባይ ውሀ ያስጮሀል ድንጋይ
ሰው ያለስራው የተሰረቀ አህያ ይነዳል
ሰው ጥራ ቢሉት መራራን ጠራት
ሰው ጥራ ቢሉት እራሱ መጣ
ሰዶ ማሳደድ ቢሻህ ዶሮህን ለቆቅ ለውጥ
ሰዶ ማሳደድ ካማረህ ዶሮህን በቆቅ ለውጥ
ሲሉ ስምታ ዶሮ ሞተች ዋና ገብታ
ሲመክሩት ያልሰማ ሲያጮሉት ይሰማ
ሲመች ያማት ተዝካር ይወጣል ሳይመች ያባት ይቀራል
ሲሞቱ ብታይ አንቀላፋች
ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል
ሲሮጡ የፈቱት ሲቀመጡ ለማስተካከል ቀላል ነው
ሲሮጥ የመጣን አህያ አጥብቀህ ጫነው
ሲሰርቀኝ ያየሁትን ቢጨምርልኝ አላምነውም
ሲስሟት ትታ ሲስቧት
ሲስሟት እንቢ ብላ ሲጎትቷት
ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል
ሲበሉ አድርሰኝ ሲጣሉ አርቀኝ
ሲበሉ አድርሱኝ ሲጣሉ መልሱኝ
ሲቃ የቀስቀስው ነቅቶ አይተኛም
ሲታጠቡ እስከ ክንድ ሲታረቁ ከሆድ
ሲቸኩሉ የታጠቁት ለወሲብ አይመችም
ሲቸግር ጤፍ ብድር
ሲያውቀኝ ናቀኝ
ሲያዩት ያላማረ ሲበሉት ያቅራል
ሲያደርጉ አይታ ዶሮም ጡት መያዣ ገዛች
ሲጠሩት ወዴት ሲልኩት አቤት
ሲጠባ ያደገ ጥጃ ቢይዙት ያጓራል
ሲገደገድ ያልበጀው ሲወቀር እሳት ፈጀው
ሳል ይዞ ስርቆት ቂም ይዞ ጸሎት
ሳትወልድ ብላ
ሳያሽ የበላ ዝንጀሮ ሲስል ያድራል
ሳያውቁ የቆረጡት አበባ የፈለጉት ቀን ይደርቃል
ሳያጣሩ ወሬ ሳይገሉ ጎፈሬ
ሳይርቅ በቅርቡ ሳይደርቅ በቅርቡ
ሳይሰሙ ወሬ ሳይገሉ ጎፈሬ
ሳይቃጠል በቅጠል
ሳይተርፋት አበድራ ሳትቀበል ሞተች
ሳይቸግር ጤፍ ብድር
ሳይቸግር ጤፍ ብድር መከበር በከንፈር
ሳይቸግር ጤፍ ብድር በስተርጅና ሙሽርና
ሳይከካ ተቦካ
ሳይደግስ አይጣላም
ሳይጠሩት አቤት የሰይጣን ጎረቤት
ሳይጠሩት ወይ ባይ ሳይሰጡት ተቀባይ
ሴቱ ሲበዛ ጎመን ጠነዛ
ሴትና ዶሮ ዱር ከሄዱ ቤታቸውን ይክዳሉ
ሴት ከወንድ እህል ከሆድ
ሴት ለቤት ወፍጮ ለዱቄት
ሴትና መሬት የማይችሉት የለም
ሴት ማገዶ ሲቸግራት ምሰሶ ትነቅላለች
ሴት ሲበዛ ልማት ይፋጠናል
ሴት ሲበዛ ወንዶች ይፈራሉ
ሴት በማጀት ወንድ በችሎት
ሴት በጳጳስ ኳደሬ በንጉስ
ሴት ብታውቅ በወንድ ያልቅ
ሴት ሲያፏጩላት ያረሱላት ይመስላታል
ሴት ታውቅ በወንድ ያልቅ
ሴት አማት የመረዘው ኮሶ ያነዘዘው
ሴት አግብተው ሴት ቢወልዱ የት አለ ንግዱ
ሴት ከወንድ እህል ከሆድ
ሴት ከጠላች በቅሎ ከበላች አመል አወጣች
ሴት ካላበለች ባልዋን ትወልዳለች
ሴት ካልወለደች ቋንጣ አትጠብስም
ሴት ካልዋሸች ባልዋን ትወዳለች
ሴትና መሬት የማይችሉት የለም
ሴት የወደደ ጉም የዘገነ
ሴት ያመጣው ጠብ አይበርድም
ሴት ይወዷል ማጀት ያንጎዳጉዷል
ሴትና ቄስ ቀስ
ሴትና በቅሎ እንደገሪዋ ነው
ሴትና አህያ በዱላ
ሴትና አህያ ዱላ ይወዳል
ሴትና ድመት ወደ ሞቀበት
ሴትና ዶሮ ሳይጣላ አይውልም
ሴትና ድስት ወደ ማጀት
ሴትና ዶሮ ሳያብድ አይውልም
ሴትና ፈረስ እንደኩሬ ውሀ እያደር ማነስ
ሴትና ፈረስ የስጡትን ይቀምስ
ሴትን ያመነ ጉም የዘገነ
ሴት የላከው ምልክቱን አይረሳም
ሴት የላከው ሞት አስፈራራው
ሴት የላከው ሞት አይፈራም
ሴት የላከው በር አያንኳኳም
ሴት የላከው አልቃይዳን አይፈራም
ሴት የላከው ጅብ አይፈራም
ሴት የላከው ፓርላማ ይገባል
ሴትየዋ እንደፈራሁት ተቀደደብኝ አለች
ስለ ጨሰ አይነድም ስለዳመነ አይዘንብም
ስልቻ ቀልቀሎ ቀልቀሎም ስልቻ
ስምህ ማነው ላገር አይመች ማን አወጣልህ ጎረቤቶች
ስምሽ ማነው ሲሏት ቂጤ ትልቅ ነው አለች
ስምን መላክ ያወጣዋል
ስም ከመቃብር በላይ ይቆማል
ስም ያለው ሞኝ ነው
ስም ይወጣል ከቤት ይሄዳል ጎረቤት
ስም ይወጣል ከቤት ይከተላል ጎረቤት
ስራ ለሰሪው ምርጫ ለመራጭ
ስራ ለሰሪው እሾህ ላጣሪው
ስራ ከመፍታት ምርጫ መወዳደር
ስራ ከምፈታ ልጄን ላፋታ
ስራ ያጣ መለኩሴ አደገኛ ቦዘኔ ተባለ
ስራ ያጣ መነኩሴ ቆቡን ቀዶ ይሰፋል
ስራ ያጣ መነኩሴ “አደገኛ ቦዘኔ” ተብሎ ታሰረ
ስራ ያጣ መነኩሴ የምርጫ ቅስቀሳ ጀመረ
ስራ ያጣ ቄስ ቆቡን ቀዶ ይሰፋል
ስብ ሊያርዱ ጉፋያ ይነዱ
ስትወልድ የምትበላውን በርግዝናዋ ጨረስችው
ስትግደረደሪ ጾምሽን እንዳታድሪ
ስደትና አግዳሚ ሁሉንም እኩል ያረጋል
ስጋ ቁጠር ቢሉት ጣፊያ አንድ አለ
ስጋው ያሳማ እንኳን ለበላው ለሰማው ገማ
ስጋው ያሳማ ከበላው የሰማው ገማ
ሶስቴ ከመፍሳት አንዴ መቅዘን

ተረት ሸ
ሸማ ለብሶ ስልቻ በቅሎ ጭኖ ለብቻ
ሸማ ማዋስ ለባላገር በቅሎ ማዋስ ለወታደር
ሸማ በውሀ ሰው በንስሀ
ሸማን በውሀ ሰውነትን በንስሀ
ሸማ በየፈርጁ ይለበሳል
ሸማና ምስጥ ወደ ውስጥ
ሸማኔ በመኑ ጠይብ በከሰሉ
ሸማኔ በድሩ ጠይብ በመንደሩ
ሸማኔ ድውሩን ባለስልጣን ክብሩን
ሸማን ጠምዞ ያሰጧል እህልን አላምጦ ይበሏል
ሸምበቆ በመርዘሙ አይሆንም ምሰሶ
ሸምበቆ በመርዘሙ ምሰሶ አይሆንም
ሸርሙጣ ስታረጅ አቃጣሪ ትሆናለች
ሸርሙጣን የወደደ ልብሱን ጥሎ አበደ
ሸርሙጣን የወደደ ልብሱን ጥሎ ያበደ
ሸኚና ጥላ ቤት አይገባም
ሸኚ ቤት አያደርስም
ሸኝ ቤት አይገባም
ሸክላ ቢጥሉት ገለባ
ሹመት ላወቀው ይከብደዋል ላላወቀው ያሳብደዋል
ሹመት ሲገኝ ዘመድ አይገድም
ሹመት ሺህ ሞት
ሹመት በተርታ ስጋ በገበታ
ሹመት የለመደ ወንዝ ዳር ይወርዳል
ሹመትና ቁመት ከልኩ አያልፍም
ሹመትና ቁመት አይገኝም በምኞት
ሹም ለመነ አዘዘ
ሹም ለሹም ያወርሳል ጉም ተራራ ያለብሳል
ሹም ለሹም ይጎራረሳል ድሀ ለድሀ ይለቃቀሳል
ሹም መክሰስ ወጀድ ማረስ አይቸግርም
ሹም ሲቆጣ ማር ይዞ እደጁ ደስ ሲለው ማር ይዞ እደጁ
ሹም ቢሞት ሀምሳ የሹም ልጅ ቢሞት መቶ ሀምሳ
ሹም ቢሞት ቀባሪው ሀምሳ የሹም ልጅ ቢሞት መቶ ሀምሳ
ሹም ያዛል ቄስ ይናዝዛል
ሹምና ማር እያደር ይከብዳል
ሹምና የጋማ ከብት በጊዜ ይከተት
ሹምና ጥጥ እያደር ይከብዳል
ሹምና ጥጥ እያደር ይከዳል
ሹሩባ ትሰራ ሄዳ ጠጉሩዋን ተላጭታ መጣች
ሹክሹክታ የጠብ ወለምታ
ሺ መት ሺ ሞት
ሺም ታለበ አንድ ያው በገሌ
ሺ በመከረ አንድ በወረወረ
ሺ በመከር አንድ በወረወር
ሺ አውል ሲሞት ሺህ ይሙት
ሺ አውል ከሚሞት ሺ ይሙት
ሺ አውል ኪሞት ሺ ይሙት
ሺ ይሙቱ ሺ አውል አይሙት
ሺ ዝንብ መሶብ አይከፍትም
ሺህ ቢታለብ አንድ በገሌ አለች ድመት
ሺ ቢታለቡ ከገሌ አላልፍም አለች ድመት
ሺ ቢያጩሽ አንድ ያገባሽ
ሺ ያጭሽ አንድ ያገባሽ
ሻማ ራሱ ነዶ ራሱ ብርሀን ይሰጣል
ሻሽ ይደምቃል ማቅ ይሞቃል የሚበጀውን ባለቤቱ ያውቃል
ሻጭ ገዥ ሆኖ ይገምታል
ሽልም እንደሆን ይገፋል ቂጥም እንደሆን ይጠፋል
ሽል ከሆነ ይገፋል ቂጣም ከሆነ ይጠፋል
ሽል እንደሆን ይገፋል ቂጣም እንደሆን ይጠፋል
ሽመልና ዘንግ ቂልና በግ
ሽማግሌ ሳለ ምክር አይጠፋም ጎልማሳ ሳለ ላም አይነዳም
ሽማግሌ በምክሩ አርበኛ በሰናድሩ
ሽማግሌ ካለበት ነገር አይናቅበት
ሽማግሌ ካለበት ነገር አይሰረቅ ጎበዝ ካለበት በትር አይነጠቅ
ሽማግሌ ካልሞተ ስንዴ ካልመረተ
ሽማግሌ ካልሞተ ስንዴ ካልሸተ
ሽማግሌ ይገላግላል የተጠቃ አቤት ይላል
ሽማግሌና ስልቻ ሳይሞሉ አይቆሙም
ሽማግሌና ጅብ በላላባት ይገባል
ሽማግሌን ከምክር ከመለየት ከምግብ መለየት
ሽሮን ሲሸውዷት ፕሮቲን ነሽ አሏት
ሽሽት ከኡኡታ በፊት
ሽበት ምን ታረግ መጣህ ቢሉት እኖር ብዬ አለ
ሽበት እኖር ብዬ መጥቻለሁ አለ
ሽታና ግማት ላልሰማ ማውራት
ሽንብራ መኖር በመከራ
ሽንኩርት አንድም በሉት ገማ ደገሙትም ገማ
ሽንኩርት የባህሪውን ይሸታል
ሾላ በድፍን
ሾተልን ወደ ሰገባህ ቁጣህን ወደ ትእግስት
ሾተልን ወደ አራዊት ቁጣህን ወደ ትእግስት
ሾተልን ወደ አፎት ቁጣን ወደ ትእግስት
ሽሮ ቢደነፋ እንጀራ እስኪቀርብ ነው

ተረት ቀ
ቀለም ሲበጠበጥ ብርእ ሲቀረጥ
ቀለም በቀንድ ውስጥ ጨለማ ነው ሲፃፍ ግን ብርሃን ነው
ቀለም ሲበጠበጥ ብርእ ቅረጹልኝ
ቀለበት ለቆማጣ ሚዶ ለመላጣ
ቀሊል አማት ሲሶ በትር አላት
ቀላጅ የሰይጣን ወዳጅ
ቀላዋጭ ወጥ ያውቃል
ቀልብ የሌለው ውሻ ጠዲቅ አምጡልኝ ይላል
ቀልድና ቅዘን ቤት ያጠፋል
ቀልደኛ አልቅሶ ካልተናገረ የሚያምነው የለም
ቀልደኛ ገበሬ ሲያስቀን አደረ
ቀልደኛ ገበሬ ናይት ክለብ ከፈተ
ቀልደኛ ጎረምሳ እያራ ያፏጫል
ቀልድና ቅዘን ቤት ያበላሻል
ቀሙን ላይቀር ከነጫማቸው
ቀማኛና ሽፍታ ጭለማና ማታ
ቀርቀሬ ወርጄ ማር ስልስ ማር ልከፍል
ቀስ በመቀስ አንቁላል በአግሩይሂዳል
ቀስ እንዳይደፈረስ
ቀስ እንዳይፈስ
ቀስ በቀስ እንቁላል በእግሩ ይሄዳል
ቀስ በቀስ አባይም ዝናብ ይሆናል
ቀበሮ ናት የገጠሩዋ ሚዳቋ ናት የሰፈሩዋ
ቀበሮ የበሬ ቆለጥ ይወድቅልኛል ብላ ስትከተል ዋለች
ቀበቶ ለማፈኛ ሰንሰለት ለማቆራኛ
ቀበኛ ማሰሪያውን በልቶ ያሳጥራል
ቀበኛ ከብት ዋጋውን ያደርስ
ቀባሪ በፈጣሪ
ቀብረው ሲመለሱ እግዜር ይማርዎ
ቀብሮ የሚመለስ የሚመለስ አይመስለውም
ቀኑ የጨለመበት መንገዱ ዘንግ ነው
ቀና ሲታጣ ይመለመላል ጎባጣ
ቀና ቢታጣ ይመለመላል ጎባጣ
ቀናውን ብነግራት ውልግድግዱን አለች
ቀን ስው መስሎ ማታ ጅራት አብቅሎ
ቀን ሲከፋ በግ ይነክሳል
ቀን ሲጥለው ሁሉ ይጠላው
ቀን ሲገለበጥ ውሀ ወደ ላይ ይፈሳል
ቀን ሲደርስ አምባ ይፈርስ
ቀን ሳይቆጥሩ ውሻ ሳይጠሩ ደረሰ በእግሩ
ቀንበር ታርቆ ጣውንት ታርቆ ምን ይሆናል
ቀንበር ታንቆ ጣውንት ታርቆ ምን ይሆናል
ቀን በበቅሎ ማታ በቆሎ
ቀን በቅሎ ማታ ቆሎ
ቀን ቢረዝም ልብ ያደክም
ቀን ቢረዝም ልብ ይደክም
ቀን ቢቆጥሩ ውሻ ቢጠሩ ደረሰ በእግሩ
ቀን ቢቆጥሩ ውሻ ቢጠሩ ይደርሳል በእግሩ
ቀን ባጀብ ሌት በዘብ
ቀን አይጥለው የቀለም ሰረገላ አያሰናክለው
ቀን አይጥለው ጠጅ አያስክረው
ቀን አይጥለው ጠጅ አያሰክረው የለም
ቀን እስኪወጣ ያባቴ ገበሬ ያግባኝ
ቀን እስኪያልፍልሽ ያባትሽ ሎሌ ያግባሽ
ቀን እስኪያልፍ ያለፋል
ቀን እስኪያልፍ ያባቴ ባሪያ ያግባኝ
ቀን እስኪያልፍ ያባቴ ባሪያ ይግዛኝ
ቀን እንደተራዳ ሌት እንደ ግርግዳ
ቀን ከህዝብ ሌት ከጅብ
ቀን ከጣለው ሁሉ ይጥለው
ቀን ካልለቀሙ ሌት አይቅሙ
ቀን ካለቀሙ ሌት አይቅሙ
ቀን የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል
ቀን የጎደለበት ጠገራ አይጥ ይበላዋል
ቀን ይነዳ እንደ ፍሪዳ
ቀንና ጨርቅ እንደምንም ያልቅ
ቀንና ጨርቅ ያልቃል ብልህ ያውቃል
ቀንዳምን በሬ ቀንድ ቀንዱን
ቀንዱ ሰማይ ጠቀስ ጭራው ምድር አበስ
ቀንድ ካላት ላም ጎዳ ትከፋለች
ቀንድና ጅራት ለዋንጫ አለፉ
ቀንድ እገባበት ጅራት አይቀርም
ቀንድ ውስጥ ገብቶ ጅራት አይቀርም
ቀኝም ሰገሩ ግራም ሰገሩ መገናኛው ኮሩ
ቀድሞ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ
ቀድሞ ነበር እንጂ ተራምዶ ማለፍ አሁን ምን ይሆናል ተይዞ መለፍለፍ
ቀይ ምላሱ ጥቁር እራሱ
ቀይ ሰው መልክ አይፈጅም
ቀይ እንደበርበሬ ጥሩ እንደ ብርሌ
ቀዳዳ ያፈሳል ግቢ ያፈርሳል
ቀድሞ ሰኞን አለመሆን ነው
ቀድሞ የሸተውን ወፍ ይበላዋል ቀድሞ የሚናገረውን ሰው ይጠላዋል
ቀድሞ የሸተውን ወፍ ይበላዋል ቀድሞ የተናገረውን ሰው ይጠላዋል
ቀዶ ያለበሰ ቆርሶ ያጎረሰ
ቀጥኜ ቢያየኝ ጅማት ለመነኝ
ቀጥኜ ቢያዩኝ ጅማት ለመኑኝ
ቀጥኜ ቢያዩኝ ሞዴል ነሽ አሉኝ
ቁልቢጥ የላት ቁና አማራት
ቁልቢጥ የላት ድርጎ አማራት
ቁመህ ተከራከር ዙረህ ተመካከር
ቁመህ ተናገር ዙረህ ተመካከር
ቁመቷ ቢያጥር እንደ ድምብላል ውዷ ክፉ ነው ይደበልላል
ቁም እንደአላማ ቁረጥ እንደጫማ
ቁም እንዳላማ ጥልቅ እንደጫማ
ቁም ነገረኛ መምሰል የተለመደ አመል
ቁም ነገር ይዞ ተረት ቂም ይዞ ጸሎት
ቁራ ሲነጣ አህያ ቀንድ ያወጣ
ቁራ ስሙን የጠራ
ቁርበት ምን ያንቋቋሀል ቢሉት ባያድለኝ ነው እንጂ የነጋሪት ወንድም ነበርኩ አለ
ቁርበት ምን ያንጓጓሀል ቢሉት ባያድለኝ ነው እንጂ የነጋሪት ወንድም ነበርኩ አለ
ቁርጥማት ቢያብር አልጋ ላይ ያማቅቃል
ቁርጥ ያጠግባል ተስፋ ያታልላል
ቁቅም ከፈስ ተቆጠረች
ቁና ለመስፈሪያ ብርብራ ለማስከሪያ
ቁንጥጫ ይሻላል ከግልምጫ
ቁንጫ ለትልቅ ሰው ይበረታል ይባላል
ቁንጫ መሄድ ሳትማር መዝለል ትማራለች
ቁንጫ ሞኝ ናት ቀን ትበራለች ተለቃቅማ ታልቃለች
ቁንጫ ውሀ ወረጅ ቢሏት ስፈናጠር የሰው ዶጮ እሰብር አለች
ቁጥቋጦም ሲያድግ ዛፍ ይሆናል
ቁጥቋጦ ሲያድግ ዛፍ ይሆናል
ቁጥቋጦ ያለዛፍ አይሆንም
ቁጩና ብስጩ አልማችሁ ፍጩ
ቁጭትና መረቅ ለጊዜው ይጣፍጣል
ቁጭትና መጠጥ ለጊዜው ይጣፍጥ
ቁፍ ቁፍ አሰኘሽ እንደቄብ ዶሮ ለመከራ ላሳርሽ ኖሮ
ቂል ሲረግሙት የመረቁት ይመስለዋል
ቂል አይሙት እንዲያጫውት
ቂልን ለብቻው ስደበው ራሱን ባደባባይ እንዲሰደብ
ቂልን አንድ ጊዜ ስደበው ሲሰደብ ይኖራል
ቂልን ድንጋይ ተማትቶ ጌታና ሎሌ ተሟግቶ የማይሆን ነው ከቶ
ቂል ከጠገበበት አይወጣም
ቂል ያገኘው ፈሊጥ ውሻ የደፋው ሊጥ
ቂምህን አትርሳ የወደቀን አንሳ
ቂም ይዞ ጸሎት ሳል ይዞ ስርቆት
ቂም ይዞ ጸሎት ጭድ አዝሎ ወዘት
ቂጡን የተወጋ ውሻ እንደልቡ አይጮህም
ቂጡ የቆሰለ ውሻ እንደልቡ አይጮህም
ቂጥ ቢወድል ፈስ አያድን
ቂጥ ቢያብጥ ልብ አይሆንም
ቂጥኛም ከውርዴ ይማከራል
ቂጥኛም ከውርዴ ይውላል
ቂጥ ገልቦ ክንብንብ
ቂም ቂም ያሰኘሽ እንደዶሮ ለካስ ለመከራሽ ላሳርሽ ኖሮ
ቂፍ ቂፍ ያሰኘሽ እንደ ቄብ ዶሮ ለመከራሽ ላሳርሽ ኖሮ
ቃልህ ሳይዘጋ እግርህ ሳይዘረጋ
ቄሱም ዝም መጽሀፉም ዝም
ቄስ ለኑዛዜ ፍቅር ለሚዜ
ቄስ ምን ይሻል ጠላ ነገር ምን ይሻል ችላ
ቄስ ኤርክሶን መምህሩ እናት አያስቀብሩ
ቄስ እበር አረመኔ ከማህበር
ቄስ ካናዘዘው እድሜ ያናዘዘው
ቄስ ካፈረሰ ዲያቆን ከረከሰ
ቄስና ንብ እያዩ እሳት ይገባሉ
ቄስና ንብ እያየ እሳት ይገባል
ቄስ ያዘዘህን አድርግ እንጂ ቄስ ያደረገውን አታድርግ
ቅል ባገሩ ድንጋይ ይሰብራል
ቅል ባገሩ ደንጊያን ይሰብራል
ቅልና ድንጋይ ተማትቶ ሎሌና ጌታ ተሟግቶ
ቅልና ድንጋይ ተማትቶ ሎሌና ጌታ ተሟግቶ የማይሆን ነው ከቶ
ቅልና ድንጋይ ተማትቶ ጌታና ሎሌ ተሟግቶ የማይሆን ነው ከቶ
ቅልውጥ አሳስቦ ይጥላል ዘመቻ
ቅምሙ የበዛበት ወጥ አይፋጅ አይኮመጥጥ
ቅማል እንኳን ካቅሟ ጥብጣብ ታስፈታለች
ቅማል ውሀ ውረጅ ቢሏት ስንዳሰስ ለመቼ ልደርስ ቁንጫ ውሀ ውረጅ ቢሏት ስፈናጠር የሰው ዶጮ እሰብር አሉ
ቅማል በጥፍር ቢድጧት ራስ ደህና አለች
ቅማል ከአካላት ምስጢር ከቤት
ቋንጣና ባለሟል ሳያር አይቀርም
ቅዝምዝም ወዲያ ፍየል ወዲህ
ቅርብ ያለ ጠበል ልጥ ይነከርበታል
ቅርናታም ለቅርናታም ሰንቡሌ ሰንቡሌ ይባባላል
ቅርንጫፉ እንደዛፉ
ቅቤ መዛኝ ድርቅ ያወራል
ቅቤ ሲለግም ወስፌ አይበሳውም
ቅቤ ተነጥሮ ለመብላት ያባት የናት
ቅቤና ቅልጥም ወዴት ግጥምጥም
ቅቤ ይፍሰስ ከገንፎ አይተርፍ
ቅቤ ይፍሰስ ከገንፎ አይለፍ
ቅብጥና ቅልጥ አንድ ላይ ሲሄዱ ቅልጥ ብላ ቀረች ሶራስ ክመንገዱ
ቅል በአገሩ ድንጋይ ይሰብራል
ቅናት ያደርሳል ከሞት
ቅናት ጥናት አያገናኝ ካባት ከናት
ቅናት ጥናት አይገኝም ከናት ካባት
ቅና ያለው በአባቱ ከረባት ይቀናል
ቅና ያለው በናቱ ብልት ይቀናል
ቅን በቅን ከማገልገል ፊት ለፊት ማውደልደል
ቅንቡርስ የት ትሄዳለህ መተማ ትደርሳለህ ልብማ
ቅንነት ለነፍስ መድሀኒት
ቅንድብ ለአይን ጥቅሻ አስተማረች
ቅዝምዝም ሲወረወር ጎንበስ ብለህ አሳልፈው
ቅዠት ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም
ቆላና ደጋ እመቤትና አልጋ
ቆሎ ለዘር እንዶድ ለድግር አይሆንም
ቆሎን ቢቆረጥሙት እንጂ ቢያሹት አያልቅም
ቆመው የሰቀሉትን ቁጭ ብለው ለማውረድ ይቸግራል
ቆማጣ ቤት አንድ ጣት ብርቅ ናት
ቆማጣ ብለው ያው ቁምጥና ነው ሌላ ምን ይመጣል አለ
ቆማጣን ቆማጣ ካላሉት ገብቶ ይፈተፍታል
ቆሩ መቀበሪያው ያው ፈሩ
ቆሩ በማን ምድር ትለፋ
ቆርሶ ያላጎረሱትን ቀዶ ያላለበሱትን ብላቴና ማዘዝ አይገባም
ቆቅ ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ
ቆንጆና እሸት አይታለፍም
ቆዳ ማንጓጓቱን ስሱ መጓጓቱን
ቆዳ ማንጓጓቱን ስሱ መጓጓቱን አይተውም
ቆዳ ሲወደድ በሬህን እረድ
ቆጥሮ የማይሰጥ ሌባ ቆጥሮ የማይቀበል ሌባ

ትኩስ ቀልዶች
አንድ እብድ በስጋ መሽጫ ሱቅ በር ላይ ቆም ሲል ያየ ስጋ ሻጭ በጭራው ሊያስፈራራው አየሞከረ አትሄድም ከዚህ አንተ
አብድ ብሎ ይጮህበታል :: አብዱም ሳቅ ብሎ <የሞተ ፣እሬሳ ስቅለህ ዝንቡን አሽ , , አሽ ስትል የምትውል አብድስ አንተ

+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
++++
አንድ በጣም ወፍራም ሴትዮ የእንጦጦን ጋራ በእግራቸው ለመውጣት ይያያዙታል ሲደክማቸው ኋላቸውን ዞር በማለት
እየተመለከቱ በማረፍ ሲጓዙ አንዴ ፈሳቸውን ብው ሲያደርጉ «ጎጃምን ምታ ! ይላሉ አሁንም ወጥተው ወጥተው
ሲደክማቸው ዞር ብለው በማየት ፈሳቸውን ብም ..ብም ..ቡዋ !» ሲያደርጉት «ጎንደርን ምታ !» ይላሉ። በመጨረሻም
ዞር ዞር ብለው በመመልከት ፈሳቸውን «ጣጣጣጣጣ ..ጥጥጥጡዋ » ሲያደርጉት «ትግራይ ላይ ወያኔን ምታ !» ብለው
ዞር ሲሉ አንድ ዱርዬ ተማሪ ከኋላቸው ቆሞ ያዩታል ። ከዚያም «ውይ ! ልጄ የት ነበርክ ?» ሲሉት «ጎጃምም ሲወጋ
እዚሁ ነበርኩ : ጎንደርም ወያኔም ሲወጋ እዚሁ ነበርኩ» ሲላቸው : «ውይ ልጄ ! እናትም የለህ ?» ሲሉት ምን እንዳለ
ታውቂያለሽ ? ቂቂቂቂቂ … «ታዲያ እናት ቢኖረኝ ይታራብኛል እንዴ ብሏቸው አረፈው…..

+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
+++++++

ሰውዬው ያንዱን አጥር ያፈርሳል፤ ባለቤቱም ዝም ይላል፡፡ ይቀጥልና ደግሞ ግቢውን ያርስበታል፤ አሁንም ዝም ይላል፡፡
በመጨረሻም በሩን ያርስበታል፣አሁንም ዝም ይላል፡፡ የኼኔም ሚስቱ፣ “አንቱ ሰውዬ ዝምታዎ አልተዋጠልኝም፣ ሰውየው
መጀመርያ አጥርዎን አፈረሰ፣ ዝም አሉ፣ ቀጠለና ግቢዎን አረሰ፣ ዝም አሉ፣ ሰለሰናም በሮን አረሰ አሁንም ዝም አሉ፣ ከዚህ
በኋላ ምንዎን እስኪያርስሎት ነው የሚጠብቁት?” ብትለው፣

“እውነትሽንኮነው” ይልና ሰውየውን፣ “እኔ ምልህ ምንድነው ጉዳይህ፣ በመጀመሪያ አጥሬን አፈረስህ፣ ዝም አልኩህ፤
ቀጥሎ ግቢዬን አረስህ፣ ዝም አልኩህ፤ በመጨረሻም በሬን አረስህ፣ አሁንም ዝም አልኩህ፤ ለመሆኑ ማላውቅ መሰለህ
እንዴ?” ሲለው፣

ሰውዬው፣ “ታዲያ ምን ልትሆን ነው?!” ይለዋል

“ልክ ልክህን ነግሬህ ልሄድ ነዋ!” አለው ይባላል፡፡

+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
++++++

ባል እቤት ሲገባ ውሽምዬን ያገኘዋል፣ ግብግብም ይያዛሉ፡፡ ባልም መሸነፍ ሲጀምር፣ ሚስቱን፡- “ማነሽ ዕቃዎቹን
ከመንገድ ላይ ዞር ዞር አድርጊያቸው እስቲ” ይላታል፡፡

ሚስትም፣ “አንቱዬ ልትወድቁ ነው መሰል?” ብትል

“ታዲያ ተገትሬ አድንሻለሁ እንዴ?” አላት ይባላል፡፡

+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
+++++++

ሴትየዋ ዓለም በቃኝ ብለው መነኮሱ፡፡ እናም አንድ ዕለት ጸሎታቸውን አድርሰው ከማደሪያቸው ሲወጡ ሳይፈልጉ
አይናቸው አንድ መልከ መልካም ጎረምሳ ፍየል ተሸክሞ ከጫካ ሲወጣ ያያል፡፡

ፈተና ውስጥም ገቡ፡፡ ስጋቸውና ሩህያቸውም ሙግት ገጠሙ፡፡ ኋላ ላይ ሥጋቸው ድል ነሳ፤ እናም ጎረምሳውን፣

“ና ውረድ” ይሉታል

“ፍየል ተሸክሜያለሁ”

“ፍየሉን አውርደው”

“ጫካ ይገባብኛል”

“በመቀነቴ አቁመው”
ከዚያ በኋላ ያለውን መናገር ጊዜ ማባከን ነው፡፡

+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++

ሰውየው ውሻቸው ግቢ መጠበቋን ትታ ከሰፈር ውሻ ጋ እየተጣበቀች

የሰፈር መሳቂያ አደረገችኝ ብለው ቤንዚል አርከፍክፈው ይለቌታል

የለመዳት ውሻ ሲቀርባት ሽታው አስጠልቶት ይተዋታል።የሚሰሩትን

ያይ የነበረ ጎረቤትም እንደልማዷ ስትጣበቅ ጠብቆ ሊያበሽቃቸው

” ውሻህ ቤንዚል አልቆባት እየተጎተተች መጣች” አላቸው

+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++

ብርቱካን

እትዬ ብርቱካን !!

እንዴት አለህ ሁሴን እንደምን ዉለሀል

ድምጥህ አልተሰማም ያንን ጫት ይዘሀል ?

ሁሴን !!

እትዬ ብርቱካ ምኑ ጫቱ ያዝኩት

ድምብሎም አጥቼ ዳቦ ምብላበት

አዬ የርሶ ነገር !!

ስኩዋር ጣራ ወጣ ጋዙ ከዛፍ ላይ

እኛ ምድር ሆነን አሻቅበን ስናይ

መምጣቱ አይደለም ወይ አምላክ ከሰማይ

የተባለው ተረት እርሶ አልሰሙም ወይ ?

እትዬ ብርቱካን !!

እኔኮ የምልህ !!

ለጋዙ መወደድ ምክንያት አያጣም

እዛ አረቡ አገር ይጣላሉ በጣም

እኔን ግራ የገባኝ ስኩዋር ምን ሆኖ ነው ?


እንዲህ ጣራ ልንካ ውድ ልሁን ያለው ?

ሸንኮራው ከወንጂ ፋብሪካው የኛ ነው

ሁሴን !!

አልሰሙም እንዴ ርሶ ?

መልሱ ተመልሶ !!!!!!

አሁን መቼ ለታ ተሌቭዥን ብከፍት

ገንዘብ ሚንስትሩ ቁልጭ ብለው ድንገት

ለኑሮ መወደድ የሆነው ምክንያት

እንደያዙት ጽሁፍ ሌሎች እንዳጠኑት

በተከታታዩ ላለፈው ሶስት አመት

ኢኮኖሚ አድጎነው በ 7 ፐርሰንት

ኤትዬ ብርቱካን !!!

በል እኮ ንገረኝ ኢኮኖሚ ማን ነው ?

የማን ልጅ ነው እሱ እንዲ የተመዘዘው ?

የሱ ማደግ ጦሱ ለኛም የተረፈው

ሁሴን !!

ኢኮኖሚዉማ ማደጉ የተሰማ

የኢትዮፕያ እኮ ነው የዚች የደካማ

እትዬ ብርቱካን !!!

አሄሄ ልደታ አንቺ ያምላክ እናት

ኑሮ እሳት ሆኖ ፈጅቶን በሱ ምክኒያት

ዝም ብለሽ ታያለሽ ይሄ የኢትዮፕያ ልጅ ወደላይ ሲጎተት ?

ምነው ያኔ ድሮ

በዚያች ባሰለፍ ልጅ ሰዉ ሁሉ ተማሮ

እኔ ደጅሽ ቆሜ ጩህእቴን ባሰማ

ፍግም አላለም ወይ ታፍሶ ሄዶ ጅማ


ደሞስ ይሄ አጭሩ

ልጆቹ ሚጠሩት እያሉ ኩሩሩ

የዛ የኑሪ ልጅ አቡሉ ሚባለው

እንዲህ ድብን ብሎ አጭር ሆኖ የቀረው

እረሳሽው እንዴ ? ስለት አስገብቼ እኔ ረግሜው ነው

አሁንም ልደታ አንቺ ልደትዬ

ቀርቸ እንኩዋን አላቅ ሳልከፍል ተስዬ

እኮ ያምላክ እናት አንቺ የነ መለኛ

የኮኖሚን ነገር ሳታሳይኛማ እንቅልፍም አልተኛ

ታዲያ ልደትዬ !!

ለዚህ ለብጣሻም አድጉዋል ለሚባለው

እንኩዋን ለኔ ቀርቶ ለናቱም ላልበጀው

ከቶ ያንቺ መራራት አሁን ተግቢ ነው ?

እናም አንቺ ልደታ ይሄን ኢኮኖሚ !!

ወይ እንዳሰለፍ ልጅ ፍግም አርጊዉና

…….. ቀብር ለቅሶው ይመር

አሊያም እንዳቡሉ እጥር ይበልና

……… እዛው ደብኖ ይቅር

ካልሆነ እንደመንጌ አገር ጥሎ ይብረር

እኛም እፎይ ብለን እንዳቅም እንደር ::

ብቻ የሱን ክፉ አንቺ ካሳየሽኝ

እኔም አንድ ፓኮ ሻማ አስገባለሁኝ :::

ኑሮን ያስወደድከው አንተ ነህ!


ኑሮን ያስወደድከው አንተ ነህ!

ከምሽቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ ነው… ከኦሎምፒያ ወደ አጎና ሲናማ ለመሄድ በመከራ የተገኘች ሚኒ ባስ ውስጥ ለመግባት
ሰዉ ይጋፋል… ምንም እንኳን ታሪፉ 1ብር ከ35 ቢሆንም ረዳቱ “ሁለት፣ ሁለት ብር ነው… ሰምታችኋል!” እያለ
እያስጠነቀቀ በተገኘው ክፍት ቦታ ተሳፋሪውን ይጠቀጥቃል… እንደምንም ብዬ ታክሲው ውስጥ ከገባሁ በኋላ…
የረዳቱን ማስጠንቀቂያ ማንም ቁም ነገሬ አለማለቱ በጣም አስገርሞኝ ለረዳቱና አብሮኝ ለነበረ ጓደኛዬ በሚሰማ ድምፅ…
“ለምን ሲባል!” ብዬ አጉረመረምኩ… ተሟግቼም… “አንተ ከማን ትበልጣለህ…” ተብዬም ለኔና ለጓደኛዬ 2ብር ከ70
ከፈልኩ…

እዛው ታክሲ ውስጥ ሳለን… ጓደኛዬን እንዲህ አልኩት… “ኑሮን ግን ማን እንዳስወደደብን ታውቃለህ?” መልስ
እስኪሰጠኝ አልጠበኩም… ንግግሬን ቀጠልኩ…

“ኑሮን ያስወደድነው እኛው እራሳችን ነን… አንተና እኔ!” ጓደኛዬ ጆሮውን ሰጠኝ… ቀጠልኩ…

“እዚህ ታክሲው ውስጥ ስንት አይነት ሰው ሊሳፈር እንደሚችል አስበኸዋል?”

“ለምሳሌ… ታክሲ ውስጥ ከተሳፈሩት አንዱ ዶክተር ነው እንበል… ይሄ ዶክተር ክሊኒክ አለውም ብለን እናስብ…
ታዲያ… ባለ ታክሲውና ረዳቱ ስለመሸ ብለው 65ሳንቲም እዚህ ዶክተር ላይ ሲጨምሩበት… ዶክተሩ በተራው ወደ
ክሊኒኩ ይገባና 50ብር የነበረውን የካርድ ማውጫ ዋጋ ከሁለት ሰዓት በኋላ 60ብር ያደርገዋል… ምክንያቱም የታክሲ
ዋጋ ጨምሮበታላ!

ሌላም… የዳቦ ቤት ባለ ቤት የሆነ ግለሰብ እዚህ ታክሲ ውስጥ አለ እንበል… እሱም… ምናልባትም… ከሶስትና አራት
ዳቦ የሚያተርፋትን 65ሳንቲም በትራንስፖርት ላይ ስለተጨመረበት እሷን ለማካካስ ሲል 1ብር የነበረውን ዳቦ 1ብር
ከ10ሳንቲም ያደርገዋል… ምክንያቱም የታክሲ ዋጋ ጨምሮበታላ!

አንዷ ደግሞ እንጀራ ሻጭ ናት እንበል… 2ብር ከ50 ትሸጥ የነበረውን እንጀራ 2ብር ከ75 ታደርገዋለች… ምክንያቱም
የታክሲ ዋጋ ጨምሮባታላ!

ሌላው ደግሞ ባለ ሱቅ ነው እንበል… 25ብር የነበረውን የስኳር ዋጋ 26 ብር ያደርገዋል… ምክንያቱም የታክሲ ዋጋ


ጨምሮበታል!

እንዲሁም… ሌላኛው ተሳፋሪ ትምህርት ቤት አለው እንበል… ታዲያ ይሄ ግለሰብ… 150ብር የነበረውን ወርሃዊ
የትምህርት ቤት ክፍያ 160ብር ያደርገዋል… ምክንያቱም የታክሲ ዋጋ ጨምሮበታል!

ሌላኛው… ባለ ስጋ ቤት ነው፣ ሌላው… ባለ ወፍጮ ቤት… ሌላው… እህል ነጋዴ… ሌላው… አትክልት ነጋዴ…
ሌላው… ባለ ምግብ ቤት… ሌላው… ጠበቃ… ሌላው… ጥበቃ… ሌላዋ የቤት ሰራተኛ… ሌላም… ሌላም…

ታዲያ ባለታክሲውና ረዳቱ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ሆነው ሳሉ እነሱ በጨመሯት 65 ሳንቲም ምክንያት ህክምና
ይጨምርባቸዋል፣ ዳቦ ይጨምርባቸዋል፣ እንጀራ ይጨምርባቸዋል፣ ስኳር ይጨምርባቸዋል… ሌላም… ሌላም…

ሾፌሩና ረዳቱ ዛሬ ማታ የለኮሷት ትንሽ ክብሪት ሌሊቱን ሙሉ ስትቀጣጠል አምሽታ… አንዱ፣ ለሌላው እያቀበላትና
እየተቀባበላት አድራ በነጋታው ሰደድ እሳት ሆና እነሱኑ ትፈጃቸዋለች፡፡

የሚገርመው ነገር… ባለታክሲው ትርፍ የጫናቸውን ጨምሮ በአጠቃላይ 20 ሰዎችን ጭኗል እንበል… ታዲያ
በ65ሳንቲሟ ተሰልቶ ዛሬ ማታ 13ብር አትረፎ ሊሆን ይችላል… ነገር ግን… በንጋታው… ከላይ ከጠቅስኳቸው፣ እሱ
እራሱ ከሚጠቀማቸው አምስት አገልግሎቶች ብቻ 21ብር ከ35ሳንቲም ተጨማሪ ሊከፍል ግድ ይሆንበታል ማለት ነው፡፡

ወንድሜ ሆይ! ኑሮ ተወደደ እያልክ እያማረርክ ነው? እኔ ግን አንድ ነገር ልንገርህ… ኑሮን ያስወደደው ማንም ሳይሆን…
አንተው እራስህ ነህ!

አንቺ እህቴስ! ኑሮ ንሮብሻል? እንግዲያውስ አንድ ነገር ልምከርሽ… ኑሮሽ የተወደደው አንቺ በወደድሽው ልክ ነው…
አንቺ በመረጥሽውና በፈቀድሽው ልክ… ኑሮሽ የተወደደው ያለ በቂ ምክንያት 70ሳንቲም ሳታንገራግሪ የጨመርሽ ጊዜ
ነው… ኑሮሽ የተወደደው የጋገርሽው እንጀራ ላይ ያለ አግባብ ዋጋ የጨመርሽ ጊዜ ነው… ኑሮሽ የተወደደው የጋገርሽው
አምባሻ ላይ የተጋነነ ዋጋ የጨመርሽ ጊዜ ነው… ኑሮሽ የተወደደው ከጓሮሽ ያበቀልሽው ጎመን ላይ የማይገባ ዋጋ የጫንሽ
ጊዜ ነው…
አንተ ኑሮ የተወደደብህ፣ አንቺ ኑሮ የተወደደብሽ… ያልተረዳኸው፣ ያልተረዳሽው ነገር ቢኖር ህይወት የቅብብሎሽ
ሰንሰለት መሆኗን ነው… ኑሮ የገዢና የሻጭ፣ የአገልግሎት ሰጪና ተቀባይ ቀለበት መሆኗን ነው… ታዲያ! ዛሬ በሌላው
ላይ የወረወረከው ጠጠር ነገ ከሌሎች ጠጠሮች ጋር ተደማምሮ አንተ ላይ ከባድ አለት ሆኖ ይመጣብሃል…
የማትሸከመው ቀንበር ይሆንብሃል… አንገትህን ያስደፋሃል… አንተ ዛሬ የከፈትካት ቀዳዳ ነገ በሌሎች ሰፍታ የአውሬዎች
ሲሳይ ታደርግሃለች… አንተ ዛሬ የፈጠርካት ጠብታ ነገ ጎርፍ ሆና ይዛህ ትሄዳለች…

ታዲያ ያኔ ማን ላይ ልታላክክ ነው? መንግስት ላይ? ባለ ሃብት ላይ? ነጋዴ ላይ? ገበሬ ላይ? እኔ ግን ልምከረህ…
የመንግስትም፣ የነጋዴም፣ የገበሬም፣ የመምህርም፣ የአስተማሪም፣ ስልጣን ሰጪና ነፋጊ አንተ ነህ! ማንም የሚገዛህም ሆነ
የሚሸጥልህ አንተ በሰጠኸው ዋጋና ተመን ልክ ነው፡፡ እሱ ያወጣው ዋጋ ካልተስማማህ እያጉረመረምክ አትግዛ!
ይልቁንም በኢትዮጲያዊ ቆራጥነት ቆፍጠን ብለህ… “አልገዛህም!” በለው ያኔ እሱም የሚገዛው ነገር አለና ብር
ስለሚያስፈልገው አንተ በተመንክለት ዋጋ ይሸጥልሃል…

ምናልባት… ዛሬ የተጣለችብህን ጭማሬ የመግዛት አቅሙ ስላለህ ከመጨቃጨቅ ብለህ ጭማሬዋን ከፍለህ ልትሄድ
ትችላለህ… ነገር ግን ካንተ በታች ያለውን ወንድምህን ደግሞ አስብ!

አንተ ዛሬ ለደካማው ወንድምህ ዘብ ካልቆምክለት፣ ነገ… ትላንት የናቅካት ጭማሪ አንተው ላይ እጥፍ ሆና ስትመጣብህ
ማን ከጎንህ ሊቆም ነው? ስለዚህ… አንድ ነገር ተረዳ… የማንኛውም ነገር አስጨማሪም ጨማሪም አንተ ነህ! ኑሮህን
ያስወደድከው አንተው እራስህ ነህ!

Leave a comment

የለሊት ወጎች
21. August 2014Allgemein

ሁለት በ ሁለት ፍቅር

ተወልጄ ያደኩት ከእናቴ ጋር ነው… እናቴም የምትኖረው ከኔና ከእናትና-ልጅ(አረቄ) ጋር ነው… በ ሁለት በ ሁለት
ቤታችን ውስጥ…

ታዲያ… ፍቅር የሚገለፀው ሁሌም በሁለትዮሽ ብቻ ይመስለኛል… ለምሳሌ እኔና እናቴ… ሁለት ብቻ ነን… የአረቄ
ጠርሙሱ ላይ ያሉት እንስሶች… አጋዘን መሰሉኝ… እናትና ልጅ ይሏቸዋል… እነሱም ሁለት ናቸው… እኛ ግድግዳ ላይ
የተሰቀለው የእመቤታችንና የልጇ ምስል… እነሱም ሁለት ናቸው… ከሩቅ ደግሞ… የነዚህን ሁለት ነገሮች ፍቅር ከላይ
ሆነው የሚጠብቁ… ሁለት መልዓክት አሉ… ልክ የእመቤቴና የልጇ ምስል ላይ እንዳሉት…

የሰፈር ልጆች… “አባትህ የት ነው? አባት የለህም እንዴ?” እያሉ ይጠይቁኝና ሊያበሽቁኝ ይሞክራሉ… እኔ ግን
አልበሽቅላቸውም… እንደውም እንደኔና እማዬ ሁለት ባለመሆናቸው አዝን ነበር… ምክንያቱም ሁሉም ጎረቤቶቻችን
ሲጨቃጨቁ… ሲጣሉ… ሲደባደቡ አያለው… እናም እንደኔና እማዬ ሁለት ባለመሆናቸው ነው ብዬ አስባለው… እኔና
እማዬ አንድም ቀን ተጣልተን አናውቅም… ሁለት በ ሁለት ቤታችን ውስጥ ሁልጊዜም ደስ የሚል ፍቅር አለ… ጥልና
ፀብ እራሱ ምን እንደሆነ ያወኩት በጎረቤቶቻችን ምክንያት ነው…

አንዳንድ ጊዜ ቤታችን ከሁለት በ ሁለት ትንሽ ብትሰፋ እኔና እማዬ እራሱ ዝም ብለን የምንጣላ ይመስለኛል… ምንም
እንኳን ሁለት ሰው ባይጣላም…

አባት ግን ምን ይሰራል? አባት ኖሮኝ ባያውቅም… የሌሎች ልጆች አባቶች ሁሌም ሲቆጧቸውና ሲገርፏቸው… ልጆቹም
አባቶቻቸውን ሲፈሩ ነው የማውቀው… አባቶች ልጆችን ብቻ አይደለም የሚቆጡትና የሚገርፉት እናቶችንም ጭምር
ነው… አንዳንድ ጊዜ ሳስበው… ግድ ሆኖባቸው እንጂ… እንደኔና እማዬ እደለኛ ሳይሆኑ ቀርተው እንጂ… የጎረቤት
ልጆችና እናቶች እራሱ አባት ባይኖራቸው የሚመርጡ ይመሰልኛል…
አባቶችም ለክፋትና ለፀብ ብቻ የተፈጠሩ ይመሰልኛል… ለዛም ነው… ጦር ሜዳ የሚልኳቸው… ለምሳሌ እኛ አረቄ
ቤት የሚመጡት ሁሉም አባቶች ናቸው… ታዲያ… ሰክረው ጮክ ብለው ከማውራትና ከመሰዳደብ ውጪ ሌላ ስራ
የላቸውም… ታዲያ አባት ምን ይሰራል? የእመቤቴ ማሪያምና የልጇ ምስል ላይ እራሱ አባት የለም… ስለዚህ ፍቅር
የሚገለፀው በሁለት ነው ብዬ አስባለው…

ሰው ከሁለት በላይ ከሆነ ሁሌም የሚጨቃጨቅ ይመስለኛል… ለምሳሌ የኛ ቤት… ሁለት በ ሁለቷ… አረቄ ጠጪዎች
ሲመጡባት… ወዲያው ቀውጢ ትሆናለች… እኔና እማዬ ለሁለት የዘራንባት ፍቅር ወዲያው በጭቅጭቅና በፀብ
ይደፈርሳል…

እናም… በቃ… ሰው ከሁለት በላይ ሆኖ መኖር የለበትም ብዬ አስባለው… ለዚህም ይመስለኛል የሰውነት ክፍሎቻችን
እራሳቸው በአብዛኛው ሁለት ሁለት ሆነው የተፈጠሩት… ሁለት እጅ… ሁለት እግር… ሁለት ጆሮ… ሁለት አይን…
እንዲሁም… እንደ ነገረኛ ጎረቤታችን… ሁለት ምላስ…

You might also like