ባህረ ሐሳብ ቀመር ስልት በዘመናዊ ዘዴ

You might also like

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 12

ባሕረ ሀሳብ

የእስክንድርያ ዐሥራ ሁለተኛ ጳጳስ የነበረው ቅዱስ ድሜጥሮስ ባሕረ ሀሳብን ሲደርሰው የቤተ ክርስቲያን
ዕውቀት ያልነበረው በግብርና ሥራ የሚተዳደር ሰው ነበር፡፡ ሆኖም ለዘመናት ቤተ ክርስቲያን በዚህ
ሥርዓት የተመራችበትን የዘመን አቆጣጣር በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ ሊደርሰው ችሏል፤ ታሪኩም እንዲህ
ነው፡፡

ቅዱስ ድሜጥሮስ አባቱ ደማስቆ ወይም እንድራኒቆስ አጎቱ ደግሞ አርማስቆስ ወይም አስተራኒቆስ ይባላሉ፡፡
ሁለቱም በዘመነ ሰማዕታት ከኢየሩሳሌም ርቀው በባዕድ ሀገር በፋርስ ባቢሎን በስደት ለረጅም ዘመናት
ይኖሩ ነበር፡፡ በዚህ የስደት ዘመናቸው ከሁለቱ (ደማስቆና አርማስቆስ) በስተቀር በሀገሩ የሚኖሩት አሕዛብ
ነበሩ፡፡ ለድሜጥሮስ አጎት አርማስቆስ ልዕልተ ወይን የምትባል ሴት ልጅ ነበረችው፤ መሞቻው ጊዜ
በደረሰም ጊዜ ለወንድሙ እንድራኒቆስ ‹‹ልጄን ለአሕዛብ እንዳትድራት›› ብሎ አምሎት ሞተ፡፡ ልዕልተ
ወይን ለአቅመ ሔዋን በደረሰችበት ወቅት ድሜጥሮስም ለአቅመ አዳም ደርሶ ነበርና አባቱ ደማስቆ ‹‹ልጄን
ከአሕዛብ ጋር አጋብቼው የሃይማኖት ዝምድና ከሚፈርስ የሥጋ ዝምድና ቢፈርስ ይሻላል›› ብሎ ከወንድሙ
ልጅ ከልዕልተ ወይን ጋር አጋባቸው፡፡ እነዚህ ሁለት የታላቅና የታናሽ ልጆች ከተጋቡ በኋላ እንደወጉ
ሥርዓተ መርዓት ወመርዓዊ እንዲፈጽሙ በሰርጋቸው ዕለት ማታ በጫጉላ ቤት ትተዋቸው ሳለ ሁለቱም
ሀዘን ገብቷቸው ያለቅሱ ጀመር፡፡ የሀዘናቸው ምክንያት ደግሞ የወንድማማች ልጆች ሆነው ሩካቤ ሥጋ
ለመፈጸም ባለመፈለጋቸው ነበር፡፡ ያን ጊዜም ልዕልተ ወይን እንዲህ ስትል ጠየቀች፤ ‹‹ለመሆኑ ይህንን
ያደረከው አኔን ንቀህ ነው ወይስ ዝምድናችንን ንቀህ?›› ድሜጥሮስም መለሰ እንዲህ በማለት ‹‹አንቺንም
ዝምድናችንንም ንቄ ሳይሆን የአባቴን ለቃድ ለመፈጸም ነው፡፡›› ከዚህ በኋላ ሁለቱም ከስምምነት ላይ
ደረሱ፤ ይኸውም ያለሩካቤ ሥጋ በድንግልና ለመኖር ነበር፡፡ በሰዎች ዘንድ ግን እንደባልና ሚስት በመምሰል
ለመኖር ተስማሙ፤ በዚህ ሁኔታ ዐርባ ስምንት ዓመታትን በድንግልና ኖረዋል፡፡

ከዕለታት በአንድ ቀን ድሜጥሮስ ገበሬ እንደመሆኑ ወደእርሻው በሚገባበት ወቀት ያለጊዜያቸው ያፈሩ
ሦስት የስንዴ ዛላ እና አንድ የወይን ዘለላ አግኝቶ በመገረሙ ከልዕልተ ወይን ጋር ተመካክሮ ወደ ቤተ
እግዚአብሔር ወሰደው፡፡ በዚህን ዕለት የመንበረ እስክንድርያ ዐሥራ አንደኛ ጳጳስ የነበረው ቅዱስ ዩልያኖስ
/ዩልዮስ/ ከዕድሜ ብዛት የተነሣ በማርጀቱ ከእርሱ ቀጥሎ የሚሾመውን ጳጳስ በሱባዔ አየ፡፡ ሕዝቡን በቤተ
እግዚአብሔር ቤት ሰብበስቦ ሊነግራቸው ባሰበበት ወቅት ቅዱስ ድሜጥሮስ ከእርሻው ያገኘውን አንድ
የወይን ዘለላ እና ሦስት የስንዴ ዛላ ይዞ መጣ፡፡ ለጳጳሱ በሰጠው ጊዜ ከእርሱ ቀጥሎ እንደሚሾም በሱባዔ
ስለተገለጠለት ቅብዓ ሜሮን ቀብቶ ሥርዓተ ጵጵስናን ፈጽሞለታል፡፡ ይህ ሲሆን ግን ድሜጥሮስ አላወቀም
ነበር፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላ ቅዱስ ዩልያኖስ አረፈ፡፡ ሕዝቡም ቅዱስ ድሜጥሮስ ጳጳስ እንደሚሆን ቅዱስ
ዩልያኖስ ነግሯቸው ስለነበር ወንበር ባዶውን አያድርምና ‹‹በአባታችን ቦታ ተቀመጥ (ተሾምልን)›› ብለው
ያዙት፡፡ ቅዱስ ድሜጥሮስም ‹‹እኔ ገበሬ፤ ሕጋዊ ሚስት ያገባሁ ነኝ፤ እንዴት በንጹሕ በማርቆስ ወንበር ላይ
እቀመጣለሁ? በምን ዓይነት ሁኔታስ ጳጳስ እሆናለሁኝ?›› ቢላቸው ግድ አሉትና ሾሙት፡፡
ከዚህ በኋላ ቅዱስ ድሜጥሮስ ቅዳሴና መጻሕፍት (ብሉይና ሐዲስ) ተገልጾለት ሕዝቡን አስተምሯል፡፡
የሕዝቡ ኃጢአት እየታየውም ‹‹አንተ በቅተሀል ቁረብ፤ አንተ ግን ገና ነህ›› እያለ ይመልስ ነበር፡፡ በዚህም
የተነሣ ሕዝቡ ‹‹ጋለሞታውን አቅፎ በማርቆስ ወንበር ላይ ብናስቀምጠው እኛን አትቁረቡ ይለናል›› ብለው
በሀሜት ወደቁ፡፡

ከዚያም በኋላ ቅዱስ ሚካኤል ‹‹ዝም በማለትህ ሕዝቡ በሀሜት ተጎዱ፤ በአንተና በሚስትህ መካከል
ያለውን ነገር ግለጽ›› ብሎ አዘዘው፡፡ ቅዱስ ድሜጥሮስም ሕዝቡ አንድ አንድ እንጨት ይዘው ይመጡ ዘንድ
አዘዛቸው፡፡ እንጨቱንም አስደምሮ (አቃጥሎ) ቅዳሴ ገባ፤ ከቅዳሴ ሲወጣም በእሳት ውስጥ እየተመላለሰ
አጠናቸው፡፡ ልዕልተ ወይንን ከሴቶች መቆሚያ ጠርቶ ‹‹መጐናጸፊያሽን ዘርጊ›› በማለት ልብሷ ላይ
ፍሕሙን ዘግኖ ቢያስቀምጠው ከዘሃው ላይ አንዲት እንኳን ሳይጠቁር ቀርቷል፡፡ ካህናቱና ሕዝቡም ይህንን
አይተው ‹‹አባታችን ሆይ ይህንን የሠራኸውን ሥራ ታረዳን ዘንድ ከቅድስናን እንሻለን›› ቢሉት ‹‹የሠራሁት
ከንቱ ውዳሴን ሽቼ አይደለም፡፡ እናንተ እኔን አምታችሁ ስለእኔ እንዳትጐዱ እንድትድኑም ከዚህች ሴት ጋር
በመካከላችን ተሠውሮ ያለውን ምሥጢር እገልጽላችሁ ዘንድ የእግዚአብሔር መልአክ ስለአዘዘኝ ነው
እንጂ›› አላቸው፡፡ በዚያን ጊዜም በደላቸውን ይቅር ይላቸው ዘንድ ከእግሩ ሥር ወድቀው ለመኑት እርሱም
ይቅር አላቸው፤ አጽናናቸውም፡፡

ቅዱስ ድሜጥሮስ መቶ ሰማንያ አስከ ሁለት መቶ ሃያ ሁለት ዓ.ም በመንበረ እስክንድርያ ላይ ሲቆይ ትልቅ
ምኞትን ይመኝ ነበር፡፡ ይኸውም ጾመ ነነዌ፣ ዐቢይ ጾምና ጾመ ሐዋርያት ከሰኞ፤ በዓለ ደብረ ዘይት፣ በዓለ
ሆሳዕና፣ በዓለ ትንሣኤና በዓለ ጰራቅሊጦስ ከእሑድ፤ በዓለ ርክበ ካህናትና ጾመ ድኅነት ከረቡዕ፤ በዓለ
ዕርገት ከሐሙስ፤ በዓለ ስቅለት ከዓርብ ባይወጡ፤ ባይነዋወጡ ይመኝ ነበር፡፡ ምክንያቱም እነዚህ በዓላት
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በነበረበት ዘመን በእነዚህ ቀናት ስለዋሉ ነው፡፡ ቅዱስ ድሜጥሮስ በዓላትና
አጽዋማት ከጥንት ዕለታቸው እንዳይወጡ ሲመኝ የታዘዘ መልአክ ወደ እርሱ መጥቶ ‹‹ነገር በምኞት
ይገኛልን? ሱባዔ ገብተህ አግኘው›› ብሎ ነገረው፡፡ ‹‹ከሌሊቱ ሃይ ሦስት ሱባዔ ግባና አበቅቴ ይሁንህ፡፡
ከቀኑ ሰባት ሱባዔ ገብተህ መጥቅዕ ይሁንህ›› ብሎም አዘዘው፡፡ ‹‹ሌሊቱን አብዝቶ ቀኑን ለምን አሳነሰው››
ቢሉ ቀን የታመመ ሲጠይቅ፣ የታሰረ ሲጎበኝ፣ ወንጌል ሲያስተምር ስለሚውል ቀኑን አሳጥሮ ሌሊቱን
አስረዝሞታል፡፡›› አወጅ፡- ማንኛውም ቁጥር ከሰላሣ ከበለጠ በሠላሳ (በዐውደ ወርኅ) እንግደፈው ወይንም
ለሠላሳ እናፍለው፡፡ እንደሚታወቀው አንድ ሱባዔ ማለት ሰባት ቀናት ናቸው፡፡ ሰባት ጊዜ ሃያ ሦስት መቶ
ስድሳ አንድ ይሆናል፡፡ መቶ ስድሳ አንድን በሰላሳ ስንገድፈው/ስናካፍለው/ አምስት ዐውደ ወርኅ ሆኖ ዐስራ
አንድ ይቀራል፡፡ ዐስራ አንድን ‹‹አበቅቴ›› ብሎታል፡፡ የቀኑን ሰባት ሱባዔ በሰባት ስናባዛው ዐርባ ዘጠኝ
ይሆናል፡፡ በሰላሳ ስንገድፈው /ስናካፍለው/ አንድ ጊዜ ደርሶ ዐሥራ ዘጠኝ ይተርፋል፤ ይህንን ‹‹መጥቅዕ››
ብሎታል፡፡ ከዚህ በኋላ ቅዱስ ድሜጥሮስ ኢየዓርግና ኢይወርድ ተገልጾለት ባሕረ ሐሳብን አስተምሯል፡፡
ከሁለት ጥምር ቃል የተገኘው ባሕረ ሀሳብ ‹‹ቁጥር ያለው ዘመን›› የሚል ትርጓሜ እንዳለው ከዚህ
እንረዳለን፡፡ የእያንዳንዱን ቃላት ፍቺ በተናጠል ብናይ ‹‹ባሕር›› ዘመን ‹‹ሀሰበ›› ደግሞ ቆጠረ ማለት ነው፡
፡ በዚህም ባሕረ ሀሳብ የዘመን አቆጣጠር ማለት ይሆናል፡፡
ባህረ ሐሳብ ቀመር ስልት በዘመናዊ ዘዴ የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር
የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ከየት ይጀምራል?
የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የሚጀምረው ከፍጥረተ ዓለም፣ ከፍጥረተ ጸሐይ፣ ከፍጥረተ ጨረቃ ጋር
የተያያዘ ሲሆን የሚጀምረውም ጥንት ከሚለው ነው። ጥንትነቱም ከእነዚሁ ከዓለም፣ ከጸሀይ፣ ከጨረቃና
ከዋክብት መፈጠር ጋር የተያያዘ ሲሆን በጸሐይ ሶስት ጥንታት አሉ። እነሱም፦

 ጥንተ ዕለት፦ጥንተ ዕለት እሑድ ሲሆን በዚህ ቀን ዓለም ማለትም ሰማይና ምድር የተፈጠረበት ቀን
ነው።
 ጥንተ ቀመር፦ይህ ዕለት ሠሉስ /ማክሰኞ/ ሲሆን በዚህ ቀን በዓለም ውስጥ የሚገኙ ፍጥረታት
/ዕፅዋት፣ አዝርዕት፣ አታክልት / ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈጠሩበት ቀን ነው።
 ጥንተ ዮን፦ ጥንተ ዮን ዕለተ ረቡዕ ሲሆን በዚህም የቀንና የሌሊት መክፈያ የሆኑት ጸሐይ፣ ጨረቃና
ከዋክብት የተፈጠሩበት ቀን ነው። ዮን ማለት ጸሐይ ማለት ነው። “ዮን ይዕቲ ስማ ለጸሐይ ሀገረ
ጸሐይ ዮን ይዕቲ ” እንዲል።
እንግዲህ የኢትዮጵያ ዘመን መቆጠር የጀመረው ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ነው። ስለ ዘመን ቆጠራም
ስንናገር ዓለም ከተፈጠረ ዘመን ከተቆጠረ እንላለን። ስለዚህ ዘመን ቆጠራችን ከሥነ ፍጥረት ጋር የተያያዘ
ነው።

ባሕረ ሐሳብ
ባሕረ ሐሳብ ከሁለት የግዕዝ ቃላት የተገኘ ሲሆን “ባሕር” ማለት ዘመን ማለት ሲሆን “ሀሳብ” ቁጥር ማለት
ነው።
 ባሕረ ሐሳብ ማን ደረሰው ?

የእስክንድርያ 12ኛ ሊቀ ጳጳስ (ፓትርያርክ) የነበረው ቅዱስ ድሜጥሮስ ከ180 – 222 ዓ.ም ድረስ ለ 42
ዓመት ሊቀ ጳጳስ ነበር። ሊቀጳጳስ ከመሆኑ በፊት መስተገብረ ምድር (ገበሬ) ነበር። ዲኮ አርቆ፣ በአጭር
ታጥቆ የሚሰራ ትጉህ ገበሬ ነበር። ከልዕልተ ወይን (የቤተክርስቲያን ለቃውንት የሚጠሯት ስም) ጋር
አጋብተዋቸው ነበር። የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ ዩልዩስ (ዩልያኖስ) ሹሞታል።
 ባሕረ ሐሳብ በመጽሐፍት ቤት
ቤተ ክርስቲያን አራት ጉባዔ ቤቶች አሏት። እነሱም፡-
 ብሉይ ኪዳን
 ሐዲስ ኪዳን
 መጽሐፈ መነኮሳት (ማር ይስሐቅ፣ ፈልክዲዳዩስ ) እና
 ሊቃውንት (ሃይማኖተ አበው) ሲሆኑ አምስተኛ ጉባዔ ተደርጐ በሁለት መንገድ ይሰጣል።
አቡከክር (አቡካኻር) ባሕረ ሀሳብ ተብሎ አቡካኻር (ወልደ አቤል ሄሬም ) የተባለ መነኩሴ ሲሆን
ባሕረ ሐሳብን ጨምሮ ሌሎች የሥነ ጸሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት ሊቅ ነው። ባሕረ ሀሳብም አብሮ
ተገልጾለታል።
 ከዲሜጥሮስ በተጨማሪ ባሕረ ሀሳብን ለማወቅ የተመኙ
 ሰዒድ ወልደ ጰጥሪቅ
 መሀቡብ ወልደ መንጋ
 ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
 ኤጲፋንዮስ ዘመንፈስ ቅዱስ
 ጊዮርጊስ ወልደ አሚድ
 ማርቆስ ወልደ ቀምበር
 ዮሐንስ ወርልደ አቤልሔሬም (አቡካክር) … እና ሌሎችም
 የቅዱስ ድሜጥሮስ ምኞት
በዓላትና አጽዋማት ከጥንተ ዕለታቸው ባይጡ ባይነዋወጡ እያለ ይመኝ ነበር። ይኸውም
1. ጾመ ነነዌ፣ ዐብይ ጾም፣ ጾመ ሐዋርያት፣ ከሰኞ፣
2. በዓለ ርክበ ካህናት፣ ጾመ ድኅነት ከረቡዕ፣
3. በዓለ ዕርገት ከሐሙስ፣
4. በዓለ ደብረ ዘይት፣ ሆሳዕና፣ ትንሳኤ፣ ጰራቅሊጦስ ከእሁድ
መልአከ እግዚአብሔር ነገር በምኞት አይሆንም ሱባዔ ገብተህ አግኘው አለው። ከሌሊቱ 23 ሱባዔ ገብተህ
አበቅቴ፣ አቀኑ 7 ሱባዔ መጥቅዕ ይሁንህ ብሎታል።
አዋጅ፡-
• ማንኛውም ቁጥር ከ30 በ30 ይገድፋል፡፡
• 1 ሱባዔ = 7 ቀናት
ሌሊት 23 ሱባዔ ማለት:-
23 ሱባዔ × 7 ቀናት = 161 ቀናት
(161 በ30 ስንገድፈው) 161 ÷ 30 = 5 ደርሶ 11 ይቀራል
11 ጥንተ አበቅቴ ይባላል።
ቀን ሰባት ሱባዔ ማለት፦
7 ሱባዔ × 7 ቀናት = 49
በ 30 ስንገድፈው (49÷30) =1 ደርሶ 19 ይቀራል፡፡
19 ጥንተ መጥቅዕ ይባላል።
መጥቅዕና አበቅቴ ተደምረው ከ 30 አይበልጡም ፣ ከ 30 አያንሱም አዋጅ “አበቅቴ ወመጥቅዕ ክልዔሆሙ
ኢየዓርጉ እም፴ ወኢይወርዱ እም፴ ወትረ ይከውኑ ፴" ይላል።
 ሕዝቡስ ከድሜጥሮስ በፊት እንዴት ያከብር ነበር ?
አዕዋዳት:አዕዋድ ዖደ ከሚል የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ዞረ ማለት ሲሆን በየጊዜው እየዞረ የሚመጣ ማለት
ነው። ዓመተ ዓለም የሚሠፈርበት ሰባት አዕዋዳት አሉ። እነሱም፦

1. ዓውደ ዕለት 7 ቀናት ከሰኞ - እሁድ


2. ዓውደ ወርኅ በፀሐይ 30 ቀናት፤ በጨረቃ 29 ና 30
3. ዓውደ ዓመት- በፀሐይ 365 ቀናት 6 ሰዓት (15 ኬክሮስ)፤ በጨረቃ 354 ከ 22 ኬክሮስ
4. ዓውደ አበቅቴ (ንዑስ ቀመር) = 19 ዓመት
5. ዓውደ ፀሐይ = 28 ዓመት
6. ዓውደ ማኅተም (ማዕከላዊ ቀመር) = 76 ዓመት
7. ዓውደ ዐቢይ ቀመር (ዐቢይ ቀመር) = 532 ዓመት፤
ዓውደ ቀመር ዘላለም የሚመላለስ ሲሆን፤ ከ5500 ዓ.ዓ. ጀምሮ 14 ጊዜ ተመላልሷል፡፡
 የበአላትና የአጽዋማት ተውሳኮች
የነነዌ ጾም መነሻ (የበአላት ሁሉ መሠረት) ስለሆነ ጾሙ የሚጀምርበት ቀን በባህረ ሐሳብ ዘዴ መፈለግ
አለብን፡፡ የነነዌ ጾም የሚጀምርበት ቀን ካገኘን ሌሎቹ በአላትና አጽዋማት ከእሱ የሚርቁበት በተውሳካቸው
ስለሆነ ተውሳካቸው እየተደመረበት የሚውሉበት ቀን ይገኛል፡፡ በዚህም መሠረት የበአላቱና የአጽዋማቱ
ተውሳካቸው እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡

በአላቱና የአጽዋማቱ ተውሳካቸው


ነነዌ (መባጃውና ሐመር)
በአተ ጾም (ሁዳዴ የሚገባበት) 14 (14)
ደብረ ዘይት 11 (41)
ሆሣዕና 2 (62)
ስቅለት 7 (67)
ትንሣኤ 9 (69)
ረክበ ካህናት 3 (93)
ዕርገት 18 (108)
ጰራቅሊጦስ (ጴንጠቆስጤ) 28 (118)
ጾመ ሐዋርያት (የሰኔ ጾም) 29 (119)
ጾመ ድኅነት 1 (121)
የዕለታት ተውሳክ ዕለታቱ ተውሳካቸው

ቅዳሜ 8
እሑድ 7
ሰኞ 6
ማክሰኞ 5
ረቡዕ 4
ኀሙስ 3
ዓርብ 2

የ2013 ዓ.ም. የበአላቱና የአጽዋማቱ ስሌት በዘመናዊ ዘዴ


1. A በአላቱን የምናሰላበት ዓመተ ምህረት ይሁን፡፡
2. AA = 5500 + A [የምንፈልገውን ዓመት በዓመተ ዓለም ሲተነተን]
3. W = MOD(AA – 1, 19) [ወይም W = AA – 1 MOD 19 ተብሎም ሊጻፍ ይችላል፤(MOD
= ተረፍ?) (W+1=ወንበር)]
4. AB = MOD(W*11, 30) [AB = አበቅቴ]
5. M = 30 – AB [M = መጥቅዕ]
6. M<15 ከሆነ WR =2 (WR = ወር)
አለዚያ WR = 1
7. LY = INT((AA – 1)/4) ይህም ስንት ባለ6 ቀን ጳጉሜን እንዳለፈ ይነግረናል፡፡ (INT = ሙሉ
ቁጥር፡፡)
8. MOD(A, 4) = 0 ከሆነ P = 1 አለዚያ P = 0 (P = ጳጉሜ 6 ሲሆን የሚደመር ቀን ነው፡፡)
9. TD = (AA-1)*365+LY+P [ይህም ያለፉት ቀናት ቁጥር ነው - ምንፈልገውን ዓመት ትቶ)
10. S = MOD(TD+1, 7)+1 (መስከረም 1 የዋለበት ቀን፡፡ 1 = ሰኞ፣ 2 = ማክሰኞ፣ 3 = ረቡዕ፣ 4 =
ሐሙስ፣ 5 = አርብ፣ 6 = ቅዳሜ እና 7 = እሑድ) ሁለት የተጨመረበት ምክንያት - አንዱ ዘመን መቁጠር
የተጀመረው ማክሰኞ ስለነበር ሁለተኛው ቀኑን መስከረም 1 ለማድረግ ነው፡፡
11. TDM = TD + (WR – 1)*30+M (ከዘመን መጀመሪያ እስከ መጥቅዕ ያሉት ቀናት ቁጥር ነው፡፡)
12. D = MOD(TDM, 7) + 1 [ይህ ደግሞ መጥቅዕ የዋለበት ዕለት ነው፡፡1 = ሰኞ፣ 2 = ማክሰኞ፣ 3
= ረቡዕ፣ 4 = ሐሙስ፣ 5 = አርብ፣ 6 = ቅዳሜ እና 7 = እሑድ]
13. F = 129 – (MOD(D + 1, 7) + 1 [ይህ ነነዌ ከመጥቅዕ የሚርቅበት ቀናት ቁጥር ነው፡፡]
አስራ አንዱ ተውሳኮች የሚከተሉት ናቸው፡፡ እነሱም 0፣ 14፣ 41፣ 62፣ 67፣ 69፣ 93፣ 108፣ 118፣ 119
እና 121 ናቸው፡፡ እነዚህ ተውሳኮች ነነዌ በዋለበት ቀን ላይ ሲደመሩ በአላቱ የሚውሉበትን ቀናት
ይሰጡናል፡፡ Ti (I = 1, …., 11) ብለን እንሰይማቸው፡፡
14. TDBi = TDM+ F+ Ti [Ti የበአላቱ ተውሳክ ስለሆነ (i) ከ1 እስከ 11 ሊለዋወጥ እንደሚችል
አስተውል፡፡ በአሉ የሚውልበት ቀን ከዘመን መጀመሪያ አንስቶ ሲቆጥር - መጥቅዕ የዋለበት ቀን፣ ነነዌ
ከመጥቅዕ የሚርቅበት ቀናት ቁጥር እና የበአሉ ተውሳክ አንድ ላይ ሲደመሩ ነው፡፡
15. WRi = INT((TDBi – TD)/30) (i)ኛው በዓል የሚውልበት ወር፡፡
16. Di = MOD((TDBi – TD), 30) (i)ኛው በዓል የሚውልበት ቀን፡፡
17. Di> 0, WRi = WRi + 1 ቀኑ ከአልቦ ከበለጠ በዓሉ የሚውለው በሚቀጥለው ወር ነው፡፡
18. Di = 0 Di = 30 ቀኑ አልቦ ከሆነ ደግሞ ቀኑ የዚህ ወር መጨረሻ ነው፡፡
19. ISi = MOD(TDBi, 7) + 1 በዓሉ የዋለበት ዕለት (1 = ሰኞ፣ 2 = ማክሰኞ፣ 3 = ረቡዕ፣ 4 =
ሐሙስ፣ 5 = አርብ፣ 6 = ቅዳሜ እና 7 = እሑድ)፡፡
የ2013 ዓ.ም. የበአላቱና የአጽዋማቱ ስሌት
አዲሱ ዓመት በየትኛው ወንጌላዊ እንደሚሰየም
ዘመኑ:
• ዘመነ ማቴዎስ(1 ከሆነ)፣
• ዘመነ ማርቆስ(2 ከሆነ)፣
• ዘመነ ሉቃስ(3 ከሆነ)፣ ወይም
• ዘመነ ዮሐንስ(4 ከሆነ) መሆኑን ለማወቅ በመጀመሪያ ከክርስቶስ ልደት በፊት የነበረውን 5500 ዘመንን
እና ከክርስቶስ ልደት በኋላ ለማስላት (ለማወቅ) የምንፈልገውን ዓመተ ምህረት እንደምራለን። ከዚያ
ድምሩን ለ4 እናካፍላለን። ወይም በቀላሉ ከክርስቶስ ልደት በኋላ የምንፈልገውን ዓመተ ምህረት ለ4
አካፍለን ቀሪው (1 ከሆነ ዘመነ ማቴዎስ፣ 2 ከሆነ ዘመነ ማርቆስ፣ 3 ከሆነ ዘመነ ሉቃስ፣ 4 ከሆነ ዘመነ
ዮሐንስ) ይባላል።
 የ2013ን ብንወስድ 5500+2013= 7513 ይሆናል። ለ4 ስናካፍለው 7509/4 = 1878 ደርሶ
ቀሪ 1 ይሆናል። ወይም በቀላሉ መንገድ 2013/4 = 503 ደርሶ ቀሪ 1 ይሆናል። ስለዚህ በ2013
ዘመኑ ዘመነ ማቴዎስ ነው።
አዲሱ ዓመት የሚውልበት ዕለት
 ሰኞ፣ ማክሰኞ፣ ረቡዕ፣ ሐሙስ፣ አርብ፣ ቅዳሜ፣ ወይም እሁድ መሆኑን ለማወቅ አሁንም
በመጀመሪያ ከክርስቶስ ልደት በፊት የነበረውን 5500 ዘመንን እና ከክርስቶስ ልደት በኋላ
ለማስላት (ለማወቅ) የምንፈልገውን ዓመተ ምህረት እንደምራለን። ከዚያ ድምሩን ለ4 እናካፍልና
ድርሻውን ከመጀመሪያው ድምር ላይ እንደምረዋለን። ከዚያ ድምሩን ለ7 ስናካፍል ቀሪው (0 ከሆነ
ሰኞ ፣ 1 ከሆነ ማክሰኞ ፣ 2 ከሆነ ረቡዕ ፣ 3 ከሆነ ሐሙስ ፣ 4 ከሆነ አርብ፣ 5 ከሆነ ቅዳሜ፣ 6
ከሆነ እሁድ) ዕለት መስከረም 1 ቀን ይሆናል።
 ምሳሌ፦ 2013ን እንውሰድ 5500+2013=7513 ከዛም 7513/4 = 1878 (ድርሻ ነው) ዕለቱን
ለማወቅ 7513+1877=9391 ይህንን ለሰባት እናካፍለው 9391/7=1341 ቀሪ 4 ነው። ስለዚህ
በ2013 ዘመኑ ዘመነ ማቴዎስ ዕለቱ ዕለተ አርብ ይሆናል።
1. A በአላቱን የምናሰላበት ዓመተ ምህረት ይሁን፡፡

A = 2013 ዓ.ም.

2. AA = 5500 + A [የምንፈልገውን ዓመት በዓመተ ዓለም ሲተነተን] = 5500 + 2013

AA = 7513 ዓ.ዓ.

3. W = MOD(AA – 1, 19) [ወይም W = AA – 1 MOD 19 ተብሎም ሊጻፍ ይችላል፤(MOD


= ተረፍ?) (W+1=ወንበር)]
W = MOD(AA – 1, 19)
W = MOD(7513 – 1, 19) = MOD(7512, 19) = 7512/19= 395 ይወስድና ቀሪው 7
ይገድፋል፡፡
ስለዚህ W+1 = ወንበር
7 + 1 = 8 (ወንበር)
7 = (እውነተኛ ወንበር)
4. AB = MOD(W*11, 30) [AB = አበቅቴ]
AB = MOD(7*11, 30) = MOD(77, 30) = 77/30 = 2 ይወስድና ቀሪው 17 ይገድፋል፡፡
AB = 17 (አበቅቴ)
5. M = 30 – AB [M = መጥቅዕ]
6. M = 30 – 17 = 13 መጥቅዕ]
M = 13 መጥቅዕ
መጥቅዕ በሌላ መልኩ ለማስላት (እውነተኛ ወንበር*19, 30)
መጥቅዕ = (እውነተኛ ወንበር*19, 30) = (11*19, 30) = 133/30 = 4 ይደርስና 13 ይገድፋል፡፡
ስለዚህ 13 መጥቅዕ ነው፡፡
አዋጆች፡-
• አበቅቴ + መጥቅዕ = 30፡፡ (አበቅቴ ወመጥቅዕ ክልኤሆሙ ኀቡረ ኢይበዝኁ እም፴፤ ወኢይውኅዱ
እም፴፤ ወትረ ይከውኑ ፴)
• አበቅቴ ከነሐሴ 8 (እና ከዚያም) አያንስም፤ ከጳጉሜ 5 (እና ከዚያም) አይበልጥም፡፡
• መጥቅዕ ከመስከረም 15 አይወርድም፤ ከጥቅምት 13 በላይ አይበልጥም፡፡
• የጨረቃ ዓመታዊ እድሜዋ 30 ቀን የሚሞላው በመስከረም ወይም በጥቅምት ወር ውስጥ ነው፡፡ ያ
እድሜዋ 30 የሚሞላበት ቀን መጥቅዕ ይባላል፡፡
• የመጥቅዕ ቁጥር መጥቅዕ 15 ከሆነ የሚውለው መስከረም ላይ ነው፡፡
• የመጥቅዕ ቁጥር ከ 2 እስከ 13 ከሆነ ግን የሚውለው ጥቅምት ላይ ነው፡፡
M<15 ከሆነ WR =2 (WR = ወር)
አለዚያ WR = 1
መጥቅዕ 13 ነው ይህም M<15 ስለሆነ ጥቅምት ወር ውስጥ ይውላል፡፡
ስለዚህ ጥቅምት 13 መጥቅዕ ይውላል፡፡
7. LY = INT((AA – 1)/4) ይህም ስንት ባለ6 ቀን ጳጉሜን እንዳለፈ ይነግረናል፡፡ (INT = ሙሉ
ቁጥር፡፡)
LY = INT ((AA – 1)/4) = INT((7513 – 1)/4) = 1878
8. MOD(A, 4) = 0 ከሆነ P = 1 አለዚያ P = 0 (P = ጳጉሜ 6 ሲሆን የሚደመር ቀን ነው፡፡)
MOD (2013, 4) = 1 ስለሆነ P = 0
9. TD = (AA-1)*365+LY+P [ይህም ያለፉት ቀናት ቁጥር ነው - ምንፈልገውን ዓመት ትቶ)
TD = (7513-1)*365+1878+0
TD = 2743758 [ይህም ያለፉት ቀናት ቁጥር ነው - ምንፈልገውን ዓመት ትቶ)
10. S = MOD(TD+1, 7)+1 (መስከረም 1 የዋለበት ቀን፡፡ 1 = ሰኞ፣ 2 = ማክሰኞ፣ 3 = ረቡዕ፣ 4 =
ሐሙስ፣ 5 = አርብ፣ 6 = ቅዳሜ እና 7 = እሑድ) ሁለት የተጨመረበት ምክንያት - አንዱ ዘመን መቁጠር
የተጀመረው ማክሰኞ ስለነበር ሁለተኛው ቀኑን መስከረም 1 ለማድረግ ነው፡፡
S = MOD (TD+1, 7) +1 = ((2743758+1)/7)+1 = 391965 ይደርስና 4 ይተርፋል + 1 = 5
ስለዚህ 5 = አርብ፣ መስከረም 1 ቀን አርብ ይውላል፡፡
11. TDM = TD + (WR – 1)*30+M (ከዘመን መጀመሪያ እስከ መጥቅዕ ያሉት ቀናት ቁጥር ነው፡፡)
TDM = 2743768 + (2 – 1)*30+13
TDM = 2743801
12. D = MOD(TDM, 7) + 1 [ይህ ደግሞ መጥቅዕ የዋለበት ዕለት ነው፡፡1 = ሰኞ፣ 2 = ማክሰኞ፣ 3
= ረቡዕ፣ 4 = ሐሙስ፣ 5 = አርብ፣ 6 = ቅዳሜ እና 7 = እሑድ]
D = MOD(2743803, 7) + 1 = (2743803/7) + 1 = 2743797 ይደርስና ቀሪ 4 ሲሆን + 1
D=5
ስለዚህ መጥቅዕ አርብ ጥቅምት 13 ይውላል፡፡
13. F = 129 – MOD(D + 1, 7) + 1 [ይህ ነነዌ ከመጥቅዕ የሚርቅበት ቀናት ቁጥር ነው፡፡]
F = 129 – MOD(5 + 1, 7) + 1 = 129 – (MOD(5 + 1, 7) + 1
F = 122 ቀናት ነነዌ ከመጥቅዕ የሚርቅበት ቀናት ቁጥር ነው፡፡
አዋጆች፡-
• የነነዌ ጾም የሚጀምረው በጥር (ወደ መጨረሻው) ወይም በየካቲት (ወደ መጀመሪያው) ነው፡፡
• መጥቅዕ በጥቅምት ከዋለ (ከ2 እስከ 13 ከሆነ) የነነዌ ጾም በየካቲት ወር ውስጥ ይጀምራል፡፡
• መጥቅዕ መስከረም ላይ ሲውል (15 ወይም ከዚያ በላይ) የሚደመርበት የዕለት ተውሳክ ከ30
ካላስበለጠው የነነዌ ጾም በጥር ውስጥ ይጀምራል፡፡ ከ30 ካስበለጠው ግን 30ውን ገድፎ፣ የተረፈው ቁጥር
መጥቅዕን በጥቅምት እንደዋለ ያደርግና የነነዌ ጾም በየካቲት ይውላል፡፡
ከመጥቅዕ እስከ ነነዌ በቀን ብዛት ሲቆጠር የመጥቅዕ ዕለት ከመጥቅዕ እስከ ነነዌ የእለታት ተውሳክ
ቅዳሜ ---------------------128 ---------------------------- 8
እሑድ --------------------- 127 --------------------------- 7
ሰኞ ------------------------ 126 -------------------------- -6
ማክሰኞ -------------------- 125 --------------------------- 5
ረቡዕ ---------------------- 124 ------------------------ ---4
ሐሙስ --------------------- 123 --------------------------- 3
አርብ ---------------------- 122 ------------------------- --2
14. የ2013 ዓ.ም. የነነዌ ጾም መቼ ይገባል?
• የነነዌ ጾም የሚገባው = መጥቅዕ + የመጥቅዕ ተውሳክ [የ2013 ዓም. መጥቅዕ አርብ ጥቅምት 13
ይውላል፡፡]
የነነዌ ጾም የሚገባው = 13+2 = 15 ቀን ነው፡፡
• የ2013 ዓም. መጥቅዕ አርብ ጥቅምት 13 ይውላል፡፡ ስለሆነም የነነዌ ጾም የሚገባው (13+122 =135)
ይህም ማለት የመጥቅዕ ጥቅምት ወር ጀምሮ ከ135 ቀን በኋላ ነነዌ ይገባል ማለት ነው፡፡ (ጥቅምት=30፣
ህዳር =30፣ ታኅሳስ = 30፣ ጥር = 30 እና የካቲት 15 ቀናት በድምሩ 135 ቀናት) ወይም መጥቅዕ
ጥቅምት 13 ቀን ላይ 122 ቀናት ሲጨመርበት ( ጥቅምት = 17፣ ህዳር = 30፣ ታኅሳስ = 30፣ ጥር =30
እና የካቲት = 15 ቀናት በድምሩ 122 ቀናት) የነነዌ ጾም መግቢያ ቀን ነው ማለት ነው፡፡
ስለዚህ የካቲት 15 ቀን የነነዌ ጾም መግቢያ ነው፡፡
15. ከነነዌ ጾም በመነሳት የሌሎቹን በአላትና አጽዋማት ቀኖችን ማወቅ ይቻላል፡፡
በአላቱና አጽዋማቱ ተውሳካቸው
ነነዌ ---------------------------------- (መባጃውና ሐመር)
• በአተ ጾም (ሁዳዴ የሚገባበት) ------------ 14 (14)
= የነነዌ ጾም + 14 = 15+14 =29
ስለዚህ አቢይ ጾም የካቲት 29 ቀን ይጀምራል፡፡
• ደብረ ዘይት ---------------------------------- 11 (41)
= የነነዌ ጾም + 41 = 15+41 =56 ቀናት
ስለዚህ ደብረ ዘይት መጋቢት 26 ቀን ይውላል፡፡
• ሆሣዕና ------------------------------------- 2 (62)
= የነነዌ ጾም + 62 = 15+62 =77
ስለዚህ ሆሣዕና ሚያዝያ 17 ቀን ይውላል፡፡
• ስቅለት ------------------------------------- 7 (67)
= የነነዌ ጾም + 67 = 15+67 =82
ስለዚህ ስቅለት ሚያዝያ 22 ቀን ይውላል፡፡
• ትንሣኤ ------------------------------------ 9 (69)
= የነነዌ ጾም + 69 = 15+69 =84
ስለዚህ ትንሣኤ ሚያዝያ 24 ቀን ይውላል፡፡
• ረክበ ካህናት ----------------------------- 3 (93)
= የነነዌ ጾም + 93 = 15+93 =108
ስለዚህ ረክበ ካህናት ግንቦት 18 ቀን ይውላል፡፡
• ዕርገት ------------------------------------ 18 (108)
= የነነዌ ጾም + 108 = 15+108 =123
ስለዚህ ዕርገት ሰኔ 3 ቀን ይውላል፡፡
• ጰራቅሊጦስ (ጴንጠቆስጤ) --------------- 28 (118)
= የነነዌ ጾም + 108 = 15+118 =133
ስለዚህ በዓለ ፶ (ጰራቅሊጦስ) ሰኔ 13 ቀን ይውላል፡፡
• ጾመ ሐዋርያት (የሰኔ ጾም) --------------- 29 (119)
= የነነዌ ጾም + 118 = 15+119 =134
ስለዚህ ጾመ ሐዋርያት (የሰኔ ጾም) ሰኔ 14 ቀን ይውላል፡፡
• ጾመ ድኅነት ------------------------------ 1 (121)
= የነነዌ ጾም + 118 = 15+121 =136
ስለዚህ ጾመ ድኅነት ሰኔ 16 ቀን ይውላል፡፡
አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የጤና፣ የአንድነት እና የንስሐ ዘመን ያድርግልን፡፡ አምላከ ቅዱሳን የዘመናት
ባለቤት፣ ዘመናትን የሚያቀዳጅ ልኡል እግዚአብሔር ዘመኑን የፍስሐ፣ ስለ ቤተክርስቲያናችንና ስለ
ክርስቲያኖች መጥፎ ዜና የማንሰማበት አመት ያድርግልን፣ የአምላክ እናት ቅድስት ድንግል ማርያም ዓውደ
ዐመቱን ትባርክልን፡፡ አሜን!!!

You might also like