Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 2

ማሳሰቢያ፡-

የትምህርት ክፍያ በመ/ቤቱ ወጪ 75 ከመቶ ሲፈቀድ ከዚህ በታች ያሉትን ዝርዝር መመሪያዎች ለመፈፀም ሰራተኞች ሙሉ በሙሉ
ፈቃደኛ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
1) ማንኛውም በትርፍ ግዜ ትምህርት እንዲማር የተፈቀደለት ሰራተኛ በቅድሚያ የተቋሙ ቋሚ ሰራተኛ መሆኑ
ይጠበቅበታል፡፡
2) ማንኛውም በትርፍ ግዜ የሚማር ሰራተኛ በቅድሚያ ባለስልጣን መ/ቤቱን ቢያንስ አንድ ዓመት ማገልገል አለበት፡፡
3) በተቋሙ ፈቃድ ትምህርት ለመማር የተፈቀደለት ሰራተኛ ትምህርት ከጨረሰ የአገልግሎት ውል ግዴታ ለመግባት ፈቃደኛ
መሆን አለበት፡፡
4) በመደበኛ የትምህርት ግዜ/የሚማር ሰራተኛ ኢ.መ.ባ 75 % ወጪ አይሸፍንም፡፡
5) ማንኛውም ሰራተኛ የሚማረው ትምህርት ከሚሰራው ስራ ጋር ቢያስ 50% ተመሰሳይ መሆን አለበት፡፡
6) ለሚቀጥለው በጀት ዓመት ለመማር የሚያስፈቅድ ሰራተኛ በሚሰራበት ዳይሬክቶሬት የትምህርት በጀት መያዙን ማረጋገጥ
አለበት፡፡
7) ሰራተኛው የከፈለውን የክፍያ ደረሰኝ እና ግሬድ ሪፖርት/የትምህት ውጤት/ በመያዝ በየሰሚስተሩ ማወራረድ ያለበት ሲሆን
አጠራቅሞ የሁለት ሰሚስተር/የመንፈቅ ዓመት/ውጤት የክፍያ ጥያቄ አየስተናግድም፡፡
8) ከዚህ በፊት በተቋሙ ድጋፍ በሌላ ትምህርት ጀምረው ያቋረጡ ሰራተኞች ለመማር ከፈለጉ ከዚህ በፊት ተቋሙ
የከፈለላቸውን የትምህርት ክፍያ ሙሉ በሙሉ አስቀድመው መመለስ ይኖርባቸዋል ፡፡
9) በትርፍ ግዜ ትምህርት እንዲማሩ የተፈቀደላቸው ሰራተኞች የትምህርት ክፍያ ድጎማ ጥያቄ የሚያቀርቡት የትምህርት ክፍያ
በሚከናወንበት በጀት ዓመት ውስጥ ብቻ ሲሆን፤ነገር ግን በበጀት ዓመቱ ትምህርት ያልጀመሩ ከሆነ ለቀጣይ በጀት ዓመት
በድጋሜ ማስፈቀድ ይጠበቅባቸዋል፤ ነገርግን ይህ ሳይሆን ቀርቶ በ 2012 በጀት ዓመት በተያዘ ፈቃድ 2013 በጀት ዓመት
ትምህርት ቢጀምሩ ወጪውን ራሳቸው የሚሸፍኑ ይሆናል፡፡
10) አንድ የተቋሙ ሰራተኛ በግልም ይሁን በኢመባ ከተያዘው የትምህርት ደረጃ ዲፕሎማ ፤ዲግሪ ፤ማስተርስ ተመሳሳይ እያለው
በዛው ደረጃ ሌላ ቢፈቀድ እና ቢማር እና ጉዳዩ እንደታወቀ 75% የትምህርት ወጪውን እንዲከፈል ከማድረግም በላይ
አስተዳደረዊ እርምጃ የሚያስወስድ የስነስርዓት ግድፈት በመሆኑ ያስጠይቃል ፡፡
11) ማንኛውም በትርፍ ግዜ ትምህርት እንዲማር የተፈቀደለት ሰራተኛ ትምህርቱን ከመጀመሩ በፊት ከምረቃ ቦኃላ
በባለስልጣን መ/ቤቱ አሰራር ህግ እና ደንብ መሰረት ባለስልጣን መስራቤቱን ለማገልገል የውል ግዴታ
መግባት አለበት ፡፡
መሟላት ያለባቸው ዶክመንቶች

 የሚማሩበት ተቋሙ የእውቅና ፈቃድ የታደሰ


 ሪጅስትሬሽን ስሊፐ ዋናውን እና ቅጂ
 የክፍያ ደረሰኝ ዋናው እና ቅጂ
 ግሬድሪፖርት/የትምህርት ውጤት/
 ለዲግሪ ተማሪዎች 2 ነጥብ እና ከዚያ በላይ እንዲሁም ለማስተርስ ተማሪዎች በ የአንዳንዱ ትምህርት B እና አጠቃላይ
ውጤቱ 3 ነጥብ እና ከዚያ በላይ ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡

You might also like