Mezmur

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 2

የኳየር መዝሙር

1. አምላኬ ውለታህ

አምላኬ ውለታህ ከአእምሮ በላይ ነው

የሱሴ ውለታህ ከአእምሮ በላይ ነው

አልችልም ልገልፀው የቱን ብዬ የቱን ልተወው(2*)

ውለታህ በዛ ውለታህ (3*)

ከፍበል ከፍበል የኔ ጌታ

መቼም አመስግኜ አልጠግብም ጌታዬ

መቼም አውድሼ አልረካም የሱሴ

እጥፍ ድርብ ምስጋናዬ ይቅረብልህ

አምላኬ በፍጹም ይህ ላንተ አይነስብህ

1. ተወልድክልን ግታ የሱስ በከብቶች በረት


ለምስኪኑ ልትዳኝ ልትሆን ለደሀ አደጉ አባት
ከሰማይ ሰማያት ክብርህን ጥለህ መጣህ ለውርደት
አይዘለቅም ያንተ የፍቅርህ ስፋትና ጥልቀት

አዝ………………

2. ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ሆነን ሳለን


የሱስ መጣህልን ከሞት ከፍርድ ልትታደገን
ከአብ አስታርቀህ የጥልን ግድግዳ አፈረስክ
ምን እንልሀለን ለዘላለም ስምህ ይባረክ
አዝ………………
3. በጨለማ ላሉ ብርሀን በራ ወጣላቸው
የአለም መድሀኒት ስትመጣ አረፈ ልባቸው
ማን ያድነን ያሉ ስትገለጥ ከስጋት አረፉ
የተጠቁ ሁሉ ከሞት አመለጡ ተረፉ

ውለታህ በዛ…

You might also like