Professional Documents
Culture Documents
1-1-1
1-1-1
መርዕድ በሻህ
0968573578
1.አለም አቀፍ የመንገድ ዳር ምልክቶች
17 በአጭር እርቀት ውስጥ የተደጋገመ የባቡር ሐዲድ ማቋረጫ መኖሩን የሚያስጠነቅቅ ምልክት
ነው፡፡
ሀ. ባለሦስት ሠረዙ በ25ዐ ሜትር ለ. ባለሁለት ሠረዙ 170 ሜትር
ሐ. ባለአንድ ሠረዙ በ1ዐዐ ሜትር ርቀት ላይ የባቡር ሐዲድ ማቋረጫ ስለሚያጋጥምህ
ተጠንቅቀህ አሽከርክር፡፡
18 በመንገድ ላይ የባቡር ሐዲድ ማቋረጫ ስለአለ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
27 ወደ ፊት ክብ አደባባይ አለ፡፡
40 ለሁለት ተከፍሎ የነበረው መንገድ ማብቂያ ስለሆነ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
41 ቁም የሚል ምልክት ወደ ፊት ስለአለ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
43 በጎን በኩል ማዕዘናዊ ቅርፅ ሰርቶ የሚገኝ መንገድ ስለአለ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ
እለፍ፡፡
47 በቀኝ በኩል የባቡር ሐዲድ ማቋረጫ ስለአለ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
48 በጎን በኩል ከተገናኘ መንገድ ትይዩ የባቡር ሐዲድ ማቋረጫ ስለአለ ፍጥነትህን በመቀነስ
ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
49 T ቅርፅ ካለው መንገድ ትይዩ የባቡር ሐዲድ ማቋረጫ ስለአለ ፍጥነትህን በመቀነስ
ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
59
ከፊት ለፊትህ የዱር አራዊት መንገዱን የሚያቋርጡ ስላሉ ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡
5 ከሁለት እግር በላይ ያላቸውን አነስተኛ ተሽከርካሪዎች ምልክቱ ከተተከለበት ሥፍራ ጀምሮ
«መጨረሻ» የሚል ሌላ ምልክት እስከሚታለፍበት ድረስ መቅደምየተከለከለ ነው፡፡
6 መቅደም ክልክል ነው የሚል ምልክት መጨረሻ፡፡
7 ከሁለት እግር በላይ ያላቸው የሞተር ተሽከርካሪዎች በዚህ በኩል እንዳይሄዱ ተከልክለዋል፡፡
10 ጠቅላላ ክብደቱ በኪሎ ግራም በምልክቱ ላይ ከተመለከተው በላይ ለሆነ የጭነት ተሽከርካሪ
ማለፍ የተከለከለ፡፡
11 ጠቅላላ ክብደቱ በምልክቱ ላይ ከተመለከተው በላይ ለሆነ ማንኛውም ዓይነት ተሽከርካሪ ማለፍ
የተከለከለ፡፡
15 ለማንኛውም እንሰሳና በእንሰሳት ለሚሳቡ ተሽከርካሪዎች ጭምር በዚህ በኩል ማለፍ የተከለከለ ነው
18 የአክስሉ ጭነት በምልክቱ ላይ ከተመለከተው ኪሎ ግራም ክብደት በላይ ለሆነ ተሽከርካሪ ማለፍ
የተከለከለ፡፡
19 ጠቅላላ ስፋቱ በሜትር በምልክቱ ላይ ከተመለከተው በላይ ለሆነ ተሽከርካሪ ማለፍ የተከለከለ፡፡
20 ጠቅላላ ከፍታው በሜትር በምልክቱ ላይ ከተመለከተው በላይ ለሆነ ተሽከርካሪ ማለፍ የተከለከለ፡፡
28 መኪና ለማቆም የሚከለክለው ምልክት ትዕዛዝ መጨረሻ መሆኑን የሚገልጽ ምልክት ነው፡፡
38
በሰዓት የተሰጠው ፍጥነት መጨረሻ
2 ቴሌፎን/ስልክ/
3 የነዳጅ መቅጂያ/ማደያ/
8 የወጣቶች መኖሪያ
13 የማቆሚያ ቦታ
2 ወደ ቀኝ የሚወስደው መንገድ ዝግ ነው
3 ወደ ግራ የሚወስደው መንገድ ዝግ ነው
4
የመንገድ አቅጣጫ አመልካች
4 5 6 7
1 ከፊት ለፊት የሚመጡትን አሽከርካሪዎች እንዲቆሙ ያዛል
2 ከኃላ የሚመጡ ተሽከርካሪዎች እንዲቆሙ ያደርጋል
3 ከፊት ለፊትና ከኃላ ወደ መስቀለኛ መንገደ የሚመጡትን ተሽከርካሪዎች ያስቆማል
4 ከቀኝ ወደ ግራና ቀጥታ ታጥፈው ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች ይፈቀዳል
5 ፊት ለፊት ቆመው ከነበሩ አሽከርካሪዎች ወደ ፊትና ወደ ቀኝ አንዲጓዙ ይፈቅዳል
6 ከኌላ ቆመው የነበሩ አሽከርካሪዎች ቀጥታ ወደ ፊትና ወደ ቀኝ ታጥፈው እንዲጓዙ
ይፈቀዳል
7 ከግራ ወደ ቀኝና ቀጥታ ታጥፈው ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች ይፈቀዳል
5.የፍጥነት ወሰን ገደብ
የፍጥነት ወሰን ገደብ
የፍጥነት ወሰን ገደብ በሁለት ይከፈላል። እነርሱም
1.የከተማ ውስጥ
2.የከተማ ውጪ
ከከተማ ውጪ በሶስት መንገዶች ይገኛሉ። እነርሱም
ሀ.አንደኛ ደረጃ መንገድ፡- ሀገርን ከሀገር ያገናኛል።
ለ.ሁለተኛ ደረጃ መንገድ፡-ክልልን ከክልል ያገናኛል።
ሐ.ሶስተኛ ደረጃ መንገድ፡-ወረዳን ከወረዳ ያገናኛል።
የሀራችን የፍጥነት ወሰን ገደብ ሲደነገግ መነሻ የሚያደርገው ሁለት ነገሮችን ነው።
1.የተሽከርካሪ ክብደት/አይነት
2.የመንገድ ደረጃ
የተሽከርካሪ ክብደት/አይነት የከተማ ውስጥ የከተማ ውጪ
1ኛ 2ኛ 3ኛ
ከ3500 ኪ.ግ. በታች 60 100 70 60
አውቶሞቢል/አነስተኛ
ተሽከርካሪዎች
ከ3500 ኪ.ግ. -7500 ኪ.ግ. 40 80 60 50
የንግድ/መለስተኛ የህዝብና የደረቅ
ጭነት ተሽከርካሪዎች
ከ7500 ኪ.ግ. በላይ 30 70 50 40
ከፍተኛ የህዝብና የደረቅ ጭነት
ተሽከርካሪዎች
1.ከተፈቀደው የፍጥነት ወሰን በታች ማሽከርከር ይቻላል ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
2.አነስተኛ አውቶሞቢል ከከተማ ክልል ውጪ በዋና መንገድ በሰዓት ማሽከርከር የሚችለው የፍጥነት
ወሰን? ሀ. በ8ዐ ኪ.ሜትር ለ. በ7ዐ ኪ.ሜትር ሐ. በ1ዐዐ ኪ.ሜትር መ. በ6ዐ ኪ.ሜትር
3. አነስተኛ የጭነት ተሽከርካሪ ወይም አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ በአንደኛ ደረጃ መንገድ ላይ በሰዓት
የፍጥነት ወሰኑ ሀ. 8ዐ ኪ.ሜትር ለ. 75 ኪ.ሜትር ሐ. 6ዐ ኪ.ሜትር መ. 7ዐ ኪ.ሜትር
4. በከተማ ክልል ውስጥ ከ75ዐዐ ኪ.ግ በላይ ክብደት ያላቸው ተሽከርካሪዎች በከተማ መንገድ ላይ
በሰህት የፍጥነት ወሰኑ በኪ.ሜትር ነው፡፡
ሀ. 65 ኪ.ሜትር ለ. 8ዐ ኪ.ሜትር ሐ. 3ዐ ኪ.ሜትር መ. 6ዐ ኪ.ሜትር
5. በከተማ ክልል ውስጥ ከ35ዐዐ - 7ዐዐዐ ኪግ ክብደት ያላቸው ተሽከርካሪዎች በሰዓት የፍጥነት
ወሰኑ በኪ.ሜትር ሀ. 4ዐ ኪ.ሜትር ለ. 3ዐ ኪ.ሜትር ሐ. 6ዐ ኪ.ሜትር መ. 8ዐ ኪ.ሜትር
6.ማንኛውም አሽከርካሪ ተሽከርካሪውን በፍጥነት ለማሽከርከር የማይፈቀድለት ምክንያት?
ሀ. የመንገዱ ሁኔታ ሐ. ተላላፊውን ለማየት በማይቻልበት የአየር ፀባይ
ለ. የትራፊኩ ብዛትና ሁኔታ መ. ሁሉመ ምልስ ነው
7.መሃከለኛ ክብደት ያላቸው ተሽከርካሪዎች በሁለተኛ ደረጃ አውራ ጐዳና ላይ የተፈቀደላቸው
የፍጥነት ወሰን በሰዓት ነው፡፡ ሀ. 8ዐ ለ. 6ዐ ሐ. 5ዐ መ. 4ዐ
8.ለከባድ ተሽከርካሪዎች ከነተሳቢው በሁለተኛ ደረጃ አውራ ጐዳና ላይ የተፈቀደላቸው የፍጥነት
ወሰን በሰዓት ነው፡፡
ሀ. 1ዐዐ ኪ.ሜ ለ. 6ዐ ኪ.ሜ ሐ. 5ዐ ኪ.ሜ መ. 4ዐ ኪ.ሜ
9.ለአነስተኛ ተሽከርካሪ ከከተማ ክልል ውጭ በ3ኛ ደረጃ አውራጐዳና የተፈቀደለት የፍጥነት
ገደብ ኪ.ሜ በሰዓት ነው፡፡ ሀ. 6ዐ ለ. 5ዐ ሐ. 1ዐዐ መ. 7ዐ
10.ለከፍተኛ ተሽከርካሪ በአንደኛ ደረጃ አውራ ጐዳና ላይ የተፈቀደለት ከፍተኛ የፍጥነት ወሰን፡፡
ሀ. 3ዐ ኪ.ግ በሰዓት ለ. 8ዐ ኪ.ግ በሰዓት ሐ. 7ዐ ኪ.ግ በሰዓት መ. መልስ አልተሰጠም
11.ጠቅላላ ክብደታቸው ከ3,5ዐዐዐኪ.ግ በታች ለሆኑ ተሽከርካሪዎች በ2ኛ ደረጃ አውራጎዳና ላይ
የተፈቀደለት ከፍተኛ ፍጥነት ወሰን፡፡
ሀ. 7ዐ ኪ.ሜ በሰዓት ሐ. 4ዐ ኪ.ሜ በሰዓት
ለ. 6ዐ ኪ.ሜ በሰዓት መ. 5ዐ ኪ.ሜ በሰዓት
12.የአገራችን የፍጥነት ወሰን ገደብ ሲደነገግ መነሻ የሚያደረገው የቱን ነው
ሀ/ የመንገዱን ሁኔታ ሐ/ የተሸከርካሪውን የመቀመጫ ብዛት
ለ/ የተሸከርካሪውን ጠቅላላ ክብደት መ/ ሁሉም መልስ ነው
6.የመንገድ ስነ-ስርዓት
ተሽከርካሪ ለጊዜው ወይም ለረጅም ግዜ ማቆም የተከለከለባቸው
ስፍራዎች
• ከከተማ ክልል ውጪ በሆነ በማናቸውም መንገድ ላይ ተሽከርካሪ የሚያሽከርከር ማናቸውም
ሰው ከመንገዱ ላይ ለተሽከርካሪ ማቆሚያ ቦታ ከሌለ በስተቀር ከመኪና ቢወርድም
ባይወርድም ትራፊክ በብዛት በሚተላለፍበት መንገድ ላይ ለጊዜው ወይም ለረጅም ግዜ
ተሽከርካሪ ማቆም የለበትም።
• ማንኛውም ሰው የመንገዱ ስፋት ከ12ሜትር በላይ ካልሆነ በቀር ተሽከርካሪውን ከሌላ
ተሽከርካሪ ተቃራኒ አንጻር ከመንገድ ላይ ለጊዜው ለረጅም ግዜ ማቆም የለበትም።
• ማንኛውም የተሽከርካሪ አሽከርካሪ በዚያው መንገድ የሚነዳ የሌላ ተሽከርካሪ አሽከርካሪ
ከሁለቱም አቅጥጫ በ50ሜትር ርቀት ላይ ለማየት በማይችልበት ስፍራ ከመንገድ ላይ
ተሽከርካሪ ማቆም የለበትም።
• ከእሳት አደጋ ጣቢያ ወይም የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ ከሚሰጥበት ጣቢያ ወይም ከሆስፒታል
መግቢያ በ12 ሜትር ውስጥ ወይም ከመግቢያው መካከል ጀምሮ ከመንገድ ግራና ቀኝ በ25ሜትር
ውስጥ መቆም ክልክል ነው
• ከአውቶቢስ ማቆሚያ በስተኃላ በስተፊት በ15ሜትር ውስጥ የመንገዱ ስፋት ከ12ሜትር በላይ ካልሆነ
በስተቀር በመንገዱ አንጻር ከአውቶቢስ ማቆሚያ በ30 ሜትር ውስጥ መቆም ክልክል ነው።
• በመስቀለኛ መንገድ ውስጥ ወይም ከመስቀለኛ መንገድ በ12ሜትር ውስጥ መቆም ክልክል ነው።
• በሃዲድ መንገድ ማቋረጫ ከሚቀርበው ሀዲድ በ20 ሜትር ክልል ውስጥ መቆም ክልክል ነው
• ከባቡር ሀዲድ ማቋረጫ በ6ሜትር ክልል ውስጥ ማርሽ መለወጥ ክልክል ነው።
• ቁም የሚል ምልክት ወይም የመንገድ ምልክት ካለበት ስፍራ በ12 ሜትር ውስጥ መቆም ክልክል ነው።
• በግል መንገድ ተሽከርካሪ በሚተላለፍበት የቤት መውጫ ወይም መግቢያ ወይም የመንገዱ ስፋት 12
ሜትር ያነሰ ሆኖ ሲገኝ መቆም ክልክል ነው።
• ከጎርፍ ማስተላለፊያ ፉካ ካለበት በ5 ሜትር ውስጥ መቆም ክልክል ነው።
• በቤንዚን ማደያ አከባቢ ተሽከርካሪዎች ወደ ማደያ ገብተው ለመቅዳት በሚያዳግታቸው ሁኔታ
በ12 ሜትር ውስጥ መቆም ክልክል ነው።
• በመገናኛ መንገድ አከባቢ አቅጣጫን ለመለየት የቀስት ምልክት በተቀባበት መስመር ላየ
በቅድሚያ መስመራቸውን ለይተው ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች ያልተቆራረጠውን የመስመር ክልል
የግድ እነንዲያቀዋርጡ በሚያስገድዳቸው ርቀት ውስጥ አቅሞ መሔድ የተከለከለ ነው።
• ከአጥር ክልል ወይም ከግቢ ውስጥ ሌሎች ተሽከርካሪዎች እንዲወጡበት በተሰራ መንገድ ላይ
መተላለፊያ ዘግቶ መቆም ክልክል ነው።
• ከመንገድ ጠርዝ ከ40 ሴ.ሜ. በላይ መቆም ክልክል ነው።
• በድልድይ ወይም በመለኪያ ላይ መቆም ክልክል ነው።
• በሶስተኝነት ተደርቦ መቅደም ክልክል ነው።
• በቀኝ በኩል መቅደም ክልክል ነው።
• በመንገዱ ቀኝ ዳርቻ መኪናን ለማቆሚያ አመቺ በሚሆን አይነት በመንገድ ባለስልጣን ለአንድ መኪና
ስፈቱም ቁመቱም ይበቃል ተብሎ በተቀባ ክልል ውስጥ አለአግባብ አቁሞ መሄድ ክልክል ነው።
• የመንገዱ ቀኝ ጠርዝ አስጠግትው በአግባቡ በቆሙ ተሽከርካሪዎች ጎን በተደራቢነት መቆም ክልክል
ነው።
• መንገዱ ባለ አንድ አቅጣጫ ካልሆነ በስተቀር በማናቸውም ጎዳና በስተግራ ወገን መቆም ክልክል ነው።
• በእያንዳንዱ አቅጣጫ ለትራፊክ አንድ ነጠላ መንገድ ብቻ ባለበትና መንገዱም በነጭ በተከፋፈለበት
ስፍራ መቆም ክልክል ነው።
አቅጣጫ ስለመለወጥ
ማናቸውም የተሽከርካሪ አሽከርካሪ
• አርቆ ወይም አሻግሮ ማየት ባልቻለ ጊዜ
• ከኮሮብታ ጫፍ፣ቁልቁለት፣ከድልድይ፣ተነድሎ ከተሰራ መሻለኪያ/ታነል/ ወይም ከጎባጣ
መንገድ ሲደርስ
• ከመስቀለኛ መንገድ ወይም ከሀዲድ መንገድ በ30 ሜትር ርቀት ውስጥ
• የማያቋርጥ የቀለም መስመር በተደረገበት መንገድ ለይ ወደ ግራ መጠምዘዝ
አይፈቀድለትም።
ስለአደጋ አገልግሎት ተሽከርካሪዎች የተሰጠ ልዩ ደንብ
ማንኛውም የአደጋ አገልግሎት ተሽከርካሪ ተግባሩን በሚያከናውንበት ግዜ
• በዚህ ደንብ ወይም በሌላ ደንብ የተጻፈውን ግዴታ ሳይጠብቅ ተሽከርካሪን ለማቆም
• ቁም በሚል ምልክት ላይ ሳይቆሙ ለማለፍ
• ከተወሰነው ፍጥነት በላይ ለመንዳት እና
• ተግባሩን ለመፈጸም በሚያስፈልገው መጠን ስለትራፊክ የወጡ ደንቦችንና የመንገድ ምልክቶችን
ሳይመለከት በፈቀደው አቅጣጫ ለመጠምዘዝ ተፈቅዶለታል።
• ቀድሞ የሚሄድ የአደጋ አገልግሎት ተሽከርካሪ በሚፈጽመው ተግባር ተካፋይ የሆነ የሌላ የአደጋ
አገልግሎት ተሽከርካሪ ካልሆነ በስተቀር ማናቸው ሰው ከ100 ሜትር ባነሰ ርቀት ከአንድ
የአደጋ አገልግሎት ተሽከርካሪ ተጠግቶ መንዳትየለበትም።
የማስጠንቀቂያ ድምጽ ስለመጠቀም
• ማናቸውም የተሽከርካሪ አሽከርካሪ የሚገጥመውን አደጋ ለመከላከል ግድ አስፈላጊ
ካልሆነ፣አደጋውን የሚከላከልበት ሌላ መንገድ ከሌለውና የሚያሰማውም የማስጠንቀቂያ
ድምጽ በተቻለ መጠን አጭር ካልሆነ በስተቀር፣ በከተማ መንገድ ውስጥ የማስጠንቀቂያ ድምጽ
ማሰማት አይፈቀድለትም። ተሽከርካሪ በቆመበት ግዜ በማናቸውም አኳኃን የማስጠንቀቂያ
ድምጽ ማሰማት ክልክል ነው።
• ሆስፒታልና ትምህርት ቤት አከባቢ የማስጠንቀቂያ ድምጽ ማሰማት ክልክል ነው።
ነዳጅ ስለመሙላት
• ማንኛውም ሰው የተሽከርካሪው ሞተር እየሰራ፣ ተሽከርካሪው የህዝብ ማመላለሻ ከሆነ
በተሽከርካሪ ውስጥ መንገዶች እያሉ ማናቸውም ነዳጅ መሙላት ወይም ማስሞላት
የለበትም።
• በተሽከርካሪው አጠገብ እሳት ወይም ሲጋራ የሚያጨስ ሰው ሲኖር በሞተር
ተሽከርካሪው ነዳጅ እንድሞላ ወይም የነዳጅ መክደኛ እንዲከፈት ወይም ሌላ ስው
ይህንን እንዲያደርግ መፍቀድ ክልክል ነው።
• ማናቸውም ሰው ተሽከርካሪውን ነዳጅ ሲሞላ በሞባይል ስልክ ማነጋገር ወይም ሌሎች
ኤሌክትሮኒክስ ነክ መሳሪያዎችን መጠቀም የለበትም።
የተበላሸ ተሽከርካሪ መንገድ ላይ ስለመጠገን
1.ማንኛውም ሰው በመንገድ ላይ ተሽከርካሪን ለመጠገን ወይም ለማደስ አይፈቀድለትም፣ከዚህም
ሌላ ተሽከርካሪው በማናቸውም አከኃን ያለ ማቀረጥ፣
• በከተማ ውስጥ ሲሆን ከ6 ሰአት በላይ
• ከከተማ ውጪ ሲሆን ከ48 ሰአት በላይ በአንድ ቦታላይ መቆቆት የለበት
2. ማንኛውም ተሽከርካሪ በመንገድ ላይ ቢበላሽ አሽከርካሪው ከተሽከርካሪው ፊትና ኃላ ባለው
መንገድ በ50 ሜትር ርቀት ላይ ለሌላ ትርፊክ በግልጽ በሚታይ መልኩ ባለ 3/ሶስት ማእዘን
አንጸባራቂ ሰሌዳ ማስቀመጥ አለበት
3. ማንኛውም ሰው የተጎዳ ወይም የተበላሸ ተሽከርካሪ መኪና ከመንገድ ላይበሚያነሳበት ግዜ
በመንገድ ላይ የወዳደቁን የመስታወትና ሌሎች ተላላፊ ላይ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ነገሮችን ሁሉ
ከመንገድ ማስወገድ አለበት።
ረጅም የግንባር መብራት መጠቀም የሚከለከልባቸው ሁኔታዎች