Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 19

አቤት የዚያን ጊዜ!

አቤት የዚያን ጊዜ
ክርስቶስ ሲመጣ (2)
ትንሹም ትልቁም (3)
መድረሻውን ሲያጣ 1
አቤት የዚያን ጊዜ ክርስቶስ ሲመጣ (2)
ትንሹም ትልቁም(3) መድረሻውን ሲያጣ
ከምስራቅ ከምዕራብ ከሰሜን ከደቡብ (2)
አየራት ሲላኩ (3) ማአትን ለማዝነብ
ሰማይና ምድር በአንድ ሲዋሐዱ (2)
የት ይሆን መድረሻው (3) የት ይሆን መንገዱ
2
አቤት የዚያን ጊዜ ክርስቶስ ሲመጣ (2)
ትንሹም ትልቁም(3) መድረሻውን ሲያጣ
ጻድቃን በቀኝ በኩል ሃጣን በግራ (2)
ሲነፋ መለከት(3) ሲደለቅም እንዚራ፣
ምድር ቀውጢ ስትሆን አጽም ሲሰበሰብ(2)
ሐፍረት ይይዘዋ(3) ሰው ለፍርድ ሲቀርብ
3
አቤት የዚያን ጊዜ ክርስቶስ ሲመጣ (2)
ትንሹም ትልቁም(3) መድረሻውን ሲያጣ
ጩኸት ሲበረታ የማይጠቅም ለቅሶ (2)
እንደ ቁራጠቁሮ(3) ጽልመትን ተላብሶ፣
ገነትን ሲያገኙ ጻድቃን በስራቸው (2)
ኃጣን ወደ ሲኦል(3) ተፈረደባቸው 4
አቤት የዚያን ጊዜ
ክርስቶስ ሲመጣ (2)
ትንሹም ትልቁም (3)
መድረሻውን ሲያጣ
5
ከመላዕክት ጋራ!
ከመላዕክት ጋራ ሲገለጥ በሰማይ
ፀንተን እንጠብቀው ክብሩን ሁሉ እንድናይ
በግርማ ሲመጣ ባስደንጋጭ ሁኔታ
ወዮልሽ ነፍሴ ሆይ ወየው የዛን ለታ
6
አኽ
ምስጋና ይድረሰው ሁልጊዜ ጠዋት ማታ
ሃሌ ሃሌ ሉያ የሰራዊት ጌታ (2)
ሰማይና ምድር ከፌቱ ሲሸሹ
መግቢያ አጥቶ ይጮኻል ትልቁ ትንሹ
ፃድቃን ሲደሰቱ የኃጣን ፋንታ
ሆኖ ጠበቃቸው ለቅሶና ዋይታ 7
አኽ
ምስጋና ይድረሰው ሁልጊዜ ጠዋት ማታ
ሃሌ ሃሌ ሉያ የሰራዊት ጌታ (2)
ስለማይታወቅ የአምላኬ አመጣጥ
በመንፈስ አፅናን ፀንተን እንጠብቅህ
ሠይጣን እንዳይገዛን በመንግስትህ ቦታ
እግዚኦ ሰውረን ከመሰውር ጌታ 8
" አምላክ ሆይ ወደኛ ባትመጣ"
አምላክ ሆይ ወደኛ ባትመጣ
ለብሰህ የማርያምን ስጋ (2)
ባክኖ የነበረው የሰው ልጅ ወጤቱ
ነበር የሚያሰጋ (2) 9
በዚያ ዓመት በዚያች ወር በዚያች ቀን
ድኅነትን ለሰው ልጅ ስትሰጥ (2)
ምን ይበዛ ነበር ትህትናህ ትዕግስትህ
የማይለወጥ (2)
10
የሾህ አክሊል ደፍተው
በራስህ ጎንህን ሲወጉህ በጦር (2)
አንተ ግን ለእነርሱ
ከአባትህ ምህረትን ትለምን ነበር (2)
11
ግን መቼ አወቁህ
በሀጥያት ደንድኖ ልባቸው (2)
መድኃኒታቸውን ገረፉህ ሰቀሉህ
አንተም ሞትክላቸው (2)
12
ዳግም ስትመጣ ለፍርድ
ከአለም ፍጻሜ በኋላ (2)
ኧረ እዴት ዕድለኞች ናቸው
በፊትህ የሚያገኙ ተድላ (2)
13
በዚያች በደብረ ዘይት ቦታ
ደስታና ለቅሶ ሲፈልቅ (2)
ከቶ ከየት ይሆን ዕጣዬ
ያንጊዜ የእኔ አወዳደቅ (2)
14
የጸጸት እሮሮ በፊትህ
እንዳያቃጥለኝ እኔን (2)
እርዳኝ ፈጣሪዬ ካሁኑ
አድሰው የዛገው ልቤን (2)
15
" አምላክ ሆይ ወደኛ ባትመጣ"
አምላክ ሆይ ወደኛ ባትመጣ
ለብሰህ የማርያምን ስጋ (2)
ባክኖ የነበረው የሰው ልጅ ወጤቱ
ነበር የሚያሰጋ (2) 16
" አትለይን"
አትለይን (2) ድንግል ሆይ ድረሽልን
ምህረት ከልጅሽ ለምኝልን
ከዲያብሎስ እጅ አንቺ አድኝን (2)
17
መሐሪው አምላክ ለሰው ልጅ
ብለህ መከራን አየህ (2)
ለፈለጉህ አንተው ብርሃን ነህ (2)

18
ከጠላት ፈተና ከጠላት መከራ
ሰውረን ከኃጢአት (2)
መንገድህ መንገድህን
እንዳንሳሳት (2)
19

You might also like