5 7

You might also like

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 5

1ኛ.

ዕብ 5፥7-10
"እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና
ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት፤

ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤

ከተፈጸመም በኋላ በእግዚአብሔር እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካህናት ተብሎ ስለ


ተጠራ፥ ለሚታዘዙለት ሁሉ የዘላለም መዳን ምክንያት ሆነላቸው።" ይለናል ቅዱስ ጳውሎስ።

ስለቃሉ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን! አሜን።

፨ ይህንንን የቅዱስ ጳውሎስ ጥቅስ


- ጂዎቫ ዊትነስ "ፍጡር ስለሆነ ነው ከሞት እንዲያድነው የለመነው" በማለት
ይጠቅሱታል።

- ፕሮቴስታንቶች "ጸሎትና ምልጃን አቀረበ" የሚለውን ብቻ በማየት አማላጅ ነው ለማለት


ይጠቅሱታል።

- ሙስሊሞች ቅዱስ ጳውሎስን ባይወዱትም ትምህርቱንም ባይቀበሉ ይህንን ጥቅስ ግን


"እንዳይሞት ፈጣሪን የለመነው እርሱ ፍጡር ስለሆነ ነው" ብለው ይጠቅሱታል።
ግን ትክክለኛ መልሱ ምንድነው?

መልስ!

1ኛ ~~~ "በስጋው ወራት ይላል" ይህም ማለት በዚህ ምድር የኖረበትን 33 ዓመት ከ3 ወር
የሚያመላክት ነው። ከሞት ከተነሳ በኋላማ ወደ ቀደመ ክብሩ ስለተመለሰ በስጋው ወራት
እንዳወቅነው አሁን አናውቀውም፡፡ ለዚህም ነበር ቅዱስ ጳውሎስ አንዲህ ያለን፡-

2ኛ.ቆሮ.5፡16 ‹‹ስለዚህ እኛ ከአሁን ጀምሮ ማንንም በሥጋ እንደሚሆን አናውቅም፤


ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ
እንደዚህ አናውቀውም።››

ዕብ.1፡3 ‹‹ እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል


እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ››

ራዕ.4፡9-11 ‹‹ እንስሶቹም በዙፋን ላይ ለተቀመጠው ከዘላለምም እስከ ዘላለም በሕይወት


ለሚኖረው ለእርሱ ክብርና ውዳሴ ምስጋናም በሰጡት ጊዜ፥
ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም
በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ፦ ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ስለ
ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኃይልም ልትቀበል ይገባሃል እያሉ በዙፋኑ
ፊት አክሊላቸውን ያኖራሉ።›› ተባልን፡፡

2ኛ~~~ "ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትና ምልጃን


አቀረበ"

ቅዱስ ማቴዎስ እንዲህ ይለናል፦ የማቴዎስ ወንጌል 26:39


"ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በፊቱ ወደቀና ሲጸልይ። አባቴ፥ ቢቻልስ፥ ይህች ጽዋ ከእኔ
ትለፍ፤ ነገር ግን አንተ እንደምትወድ ይሁን እንጂ እኔ እንደምወድ አይሁን አለ።" ይላልና፡፡
ጸሎቱ ይህቺ ናት፡፡

3ኛ --- እግዚአብሔር እርሱን ከሞት የሚያድነው ኢየሱስ ክርስቶስ እራሱን ማዳን


ስለማይችል ነው? አይደለም፡፡ ምክንያቱም

" ነፍሴን ደግሞ አነሣት ዘንድ አኖራለሁና ስለዚህ አብ ይወደኛል። እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ
እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም። ላኖራት ሥልጣን አለኝ ደግሞም ላነሣት ሥልጣን አለኝ"
የዮሐንስ ወንጌል 10 : 17-18/ ለምን አለ?

" ነፍሴን ደግሞ አነሣት ዘንድ አኖራለሁና ስለዚህ አብ ይወደኛል። " የዮሐንስ ወንጌል 10 :
17

ከቅድስት ድንግል ማሪያም ከስጋዋ ስጋን ከነፍሷም ነፍስን ነስቶ ሰው ሆኖ የመጣው ይህን
የሞት ጽዋ ጠጥቶ በእርሱ ሞት እኛ ህይወትን እንድናገኝ አልነበረምን?

አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ይለናል፦

" አሁን ነፍሴ ታውካለች ምንስ እላለሁ? አባት ሆይ፥ ከዚህ ሰዓት አድነኝ። ነገር ግን ስለዚህ
ወደዚህ ሰዓት መጣሁ። "የዮሐንስ ወንጌል 12: 27

፨ ኢየሱስ ክርስቶስ እኮ ሁሉን ማድረግ የሚችል ኃያል አማላክ ነው። ነቢየ እግዚአብሔር
ኢሳያስ እንዲህ ይለናል፦
"ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤
ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።
"ትንቢተ ኢሳይያስ 9 :6

ይህ ኃያል ተብሎ የተጠራው ህጻን ከማን የተወለደው ነው? ካልን ከቅድስት ድንግል
ማሪያም የተወለደው ነው።

" ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም


ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።"
ትንቢተ ኢሳይያስ 7 : 14

" በነቢይ ከጌታ ዘንድ።

እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው


ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል
ነው።/ማቴዎስ ወንጌል 1፥22-23

፨ ኢየሱስ እኮ ልብን የሚመረምር ኩላሊትንም የሚፈትን አምላክ ነው።


" እኔ እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱ፥ እንደ ሥራው ፍሬ እሰጥ ዘንድ ልብን
እመረምራለሁ ኵላሊትንም እፈትናለሁ። "ትንቢተ ኤርምያስ 17 : 10

"ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ ኵላሊትንና ልብን


የምመረምር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፥ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።"
የዮሐንስ ራእይ 2 : 23
፨ እኛ ግን እሱ "አባት ሆይ ብትወድስ ይህቺ የሞት ጽዋ ከእኔ ትለፍ" ብላልና ብለን እንደ
ደካማ ወይም እንደ ፍጡር ቆጠርነው። ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳያስ እንዲህ ይለናል፦

ትንቢተ ኢሳይያስ 53 : 1-4


"የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገልጦአል?

በፊቱ እንደ ቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል። መልክና ውበት የለውም፥
ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም።

የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን


እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም።

በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ


በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው። "

--- ትንቢተ ኢሳይያስ 1 : 3

" በሬ የገዢውን አህያም የጌታውን ጋጣ አወቀ፤ እስራኤል ግን አላወቀም፥ ሕዝቤም


አላስተዋለም። "

~~~ "ከዚችም ዓለም ገዦች አንዱ እንኳ ይህን ጥበብ አላወቀም፤ አውቀውስ ቢሆኑ
የክብርን ጌታ ባልሰቀሉትም ነበር"1ኛ.ቆሮ 2 : 8/

----- ስለኢየሱስ ክርስቶስ ለማወቅ በስጋዊ እውቀት ሳይሆን የእግዚአብሔር አብ የመንፈስ


ቅዱስ እርዳታ ያስፈልገናል፡፡ ለዚህም ነበር ጌታችን ለቅዱስ ጴጥሮስ እንዲህ ያለው፡-

‹‹ እርሱም፦ እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? አላቸው።


ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ፦ አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ።

ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ
ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ።

እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥


የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።›› ማቴ.16፡15-18

‹‹ዳሩ ግን እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ
በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል›› ዮሐ.15፡26

ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ ከክብሩ ውበት ከጽዮን/መዝ.50፥2/ ወደ ዓለም የመጣው በሞቱ


ህይወትን ሊሰጠን ሆኖ ሳለ ለምን "ከሞት አድነኝ" አለ ታዲያ? ካልን መልሱ

‹‹እሱ የለመነው በአዳም ተገብቶ(አዳምን ወክሎ) የአዳምን ለ5 ሺህ 5 መቶ ዓመታት በሲዖል


ሆኖ ይጮህ የነበረውን ጩኸት እየጮኸ፣ የአዳምን ልመና አያሰማ ነበር›› የሚል ነው።

--- ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግማዊ አዳም ተበሏልና፡፡

∙ "እንዲሁ ደግሞ፦ ፊተኛው ሰው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ ተብሎ ተጽፎአል፤ኋለኛው


አዳም ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ።" 1ኛ.ቆሮ.15፡45

∙ "ነገር ግን በአዳም መተላለፍ ምሳሌ ኃጢአትን ባልሠሩት ላይ እንኳ፥ ከአዳም


ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ፤ አዳም ይመጣ ዘንድ ላለው ለእርሱ አምሳሉ
ነውና።" ሮሜ.5፡14

4ኛ--- ዕብ.5፥8 " እግዚአብሔርን ስለመፍራቱ ተሰማለት" ይላል። ይህ ማለት ጸሎቱ "ከሞት
አድነኝ" ያለው ተሰምቶለታል። ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ሞቷል፡፡

2ኛ.ቆሮ.5፡14 ‹‹ አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ›› ተብለናል፡፡

ጸሎቱ ከተሰማለት ዘንድ፣ ታዲያ ለምን ሞተ?

ጥቅሱን ስንመለከት ቅኔያዊ ነው። ከላይ ከላይ የሚናገረው ስለኢየሱስ ክርስቶስ ይምሰል
እንጂ በዋነኝነት የሚነግረን ግን ስለአዳም ነው።

~ አልታዘዝ ያለው አዳም ነው


"በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደ ሆኑ፥ እንዲሁ ደግሞ በአንዱ መታዘዝ
ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ።"
ወደ ሮሜ ሰዎች 5 : 19

--- ኢየሱስማ ታዛዥ ነበር!!!


"ከእነርሱም ጋር ወርዶ ወደ ናዝሬት መጣ፥ ይታዘዝላቸውም ነበር። እናቱም ይህን ነገር ሁሉ
በልብዋ ትጠብቀው ነበር።" ሉቃ.2፥51/

‹‹እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደ ጠበቅሁ በፍቅሩም እንደምኖር፥ ትእዛዜን ብትጠብቁ

በፍቅሬ ትኖራላችሁ።›› ዮሐ.15፡10

"በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ


የታዘዘ ሆነ። ፊልጵ.2፥8/ ነው የሚለን ቅዱስ ጳውሎስ።

ኢየሱስማ ‹‹ከተፈጸመም በኋላ በእግዚአብሔር እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካህናት


ተብሎ ስለ ተጠራ፥ ለሚታዘዙለት ሁሉ የዘላለም መዳን ምክንያት ሆነላቸው›› ነው
የተባለው፡፡ ለማን የሚታዘዙ? ለኢየሱስ ክርስቶስ፡፡

ስለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ በዕብ. 5፡7-10 የሚነግረን ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከቅድስት ድንግለ ማሪያም ከስጋዋ ስጋን ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ ሰው
ሆኖ ስለአዳም(የሰው ልጆች) መከራን መቀበሉ፣ በእለተ ሐሙስ በጌቴ ሴማኒ ለ5500
ዓመታት ሲዖል ሆኖ በሞተ ነፍስ ሲሰቃይ የነበረውን የአዳምን ልመና በማስተጋባት ‹‹ ይህቺ
የሞት ጽዋ ከእኔ ትለፍ›› አለ፡፡ አዳምም ከተቀበለው መከራ የተነሳ መታዘዝን ስለተማረ
እግዚአብሔር ልመናውን ሰማው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስም በዕለተ አርብ 9 ሰዓት ላይ በመስቀል
ላይ ሆኖ ‹‹ ተፈፀመ›› ብሎ ነፍሱን ከስጋው በፈቃዱ ለይቶ፣ በስጋው ወደ መቃብር በነፍሱ
ወደ ሲዖል ወርዶ በሲዖል ለነበሩት የምስራችን ሰበከለቸው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ እንዲህ
ይለናልና፡-

‹‹ ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ


ጊዜ በኃጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፥ በእርሱም
ደግሞ ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው›› 1ኛ.ጴጥ.3፡18-19

ይህ ነው ወንድሜ !!!

You might also like