Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 3

በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም

Patriarchate Monastery of Holy of Holies Mary


ፈለገ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
Felege Hiwot Sunday School

የወላጆች ኮሚቴ ምስረታ ምክረ ሃሳብ ቀን------------------

መግቢያ

አስተዳደር ክፍል ሰንበት ት/ቤቱ ውስጥ ያሇው የሕጻናት አገልግሎት ላይ ድርሻው ሰፊ


እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይህንም አገልግሎት የበሇጠ ሇማጠናከር እና ጊዜው ከሚፈቅደው ሁኔታ
ጋር የተጣጣመ እንዲሆን ተጨማሪ እገዛዎች ያስፈልጋለ፡፡

ሕጻናት በሥጋዊው ዓሇም የሚደርስባቸውን ተፅዕኖዎች በመልካም መንፈሳዊ ሕይወትና ሥነ


ምግባር ተጽእኖውን በመቋቋም ያልፉት ዘንድ የወላጆች ድጋፍና ቁጥጥር ወሣኝ ነው::
በመሆኑም በሰ/ት/ቤቱ የሚማሩና የሚያገሇግለ ሕጻናት ወላጆቻቸው እርስ በርሳቸው እንዲሁም
ወላጆች ከሰ/ት/ቤቱ ጋር በአጋርነት ቢሰሩ ሕጻናቱ የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች አስቀድሞ
ሇመከላከልና ችግሮችም ከተፈጠሩ በኋላ መፍትሄ ሇመፈሇግ ይረዳል ተብሎ ይታመናል።
ሇዚህም ተግባር የሰ/ት/ቤቱ ድርሻና ሚና የላቀ ነው።

ይህ በመሆኑ ከላይ የተገሇጸውን መሠረታዊ ዓላማ ውጤታማ ሇማድረግ ያስችል ዘንድ


በሰ/ት/ቤቱ የበላይነት የሚመራ የሕጻናት ወላጆች ኮሚቴ አስፈላጊ ነው ብሇን እናምናሇን፡፡

ዓላማ

የሕጻናት ወላጆች ሇልጆቻቸው የመንፈሳዊ ሕይወት ሇውጥ ማምጣት ይችለ ዘንድ÷ የወላጆች
የርስ በርስ ትውውቅና አጋርነት እንዲሁም የሰ/ት/ቤቱን መመሪያዎች ማሳወቅ አስፈላጊነት
በመረዳት እና ሰ/ት/ቤቱም ከሕጻናት ወላጆች ጋር ተባብሮ በመስራት ሕጻናቱ
የሚያጋጥማቸውን እክሎች በመቅረፍ ማኅበራዊ ትስስሮሹን በማጠናከር የሰ/ት/ቤቱን
ተደራሽነት እውን ማድረግ ነው።
የወላጅ ኮሚቴ አስፈላጊነት የሚነሱ ሀሳቦች

1. ልጆች ትምህርት ከጨረሱ በኋላ ወደ ቤት (ወላጆች) ያሇምን እንግልት የሚመሇሱበት


መንገዶች በቅርበት እንዲከታተለ፡፡
2. ወላጆች የስነ-ምግባር ችግር ያሇባቸውን ተማሪዎች ስነ-ምግባራቸውን ሚያስተካክለበትን
መንገድ ከሰ/ት/ቤቱ ጋር በጋራ በሚሰሩበት አግባብ መስራት፡፡
3. ልጆች የተሇያዩ የጤና እክሎች ያሇባቸውን ሆነ በመማር ማስተማር ሂደት ወቅት
በአጋጣሚ ሇሚከሰቱ የጤና ችግሮች ላይ ወላጆች የመጀመሪያ ህክምና መስጠትን
ጨምሮ ከሰ/ት/ቤቱ ጋር በጋራ መስራት፡፡
4. በሰ/ት/ቤቱ ሇልጆች ሇሚሰጠው የቀሇም ትምህርትን ጨምሮ በተሇያዩ የሙያ መስኮች
በፈቃደኝነት ሰ/ት/ቤቱን የሚያግዙ ወላጆችን ወደ አገልግሎት ማስገባት፡፡
5. ወላጆች እርስበርስ እንዲሁም ከሰ/ተ/ቤቱ ጋር የሚኖርን ግንኑነቶችን እና አጠቃላይ
መረጃዎችን በተሇየዩ የግንኙነት አማራጮች ማህበራዊ ሚድያን ጨምሮ አንዲገናኙ
ማድረግ፡፡
6. ልጆች የተማሩትን ትምህርት ከወላጆች ጋር የሚከልሱበትን እና ተጨማሪ የቤተሰብ
የጋራ ጥናት በሚያደርጉበት ዙሪያ ክትትል ማድረግ፡፡
7. ወላጆችም ሰ/ት/ቤቱ በሚሰጣቸው መደበኛ የተከታታይ ትምህርቶች ውስጥ እንዲማሩ የማድረግ ስራ
መስራት
8. ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር በቤት ውስጥ የጋራ የፀሎት የተሇያዩ መንፈሳዊ ስራዎችን
የሚሰሩበት መርሃግብር እንዲኖራቸው ምክክር የማድረግ እና ከሰ/ት/ቤቱ ጋር ሆኖ
በጋራ የመስራት ስራ መስራት፡፡
9. የመማሪያ ቁሳቁሶችን ገዝተው መማር ሇማይችለ ተማሪዎች ከበጎ ፈቃደኛ ወላጆች
በአይነትም ሆነ በገንዘብ የመሰብሰብ እና የመደገፍ ስራ መስራት፡፡
10. ኮሚቴው ያከናወናቸውን ስራዎች የገጠሙትን ችግሮች፣ የመፍትሄ ሃሳቦች ወዘተ
ሇሰ/ት/ቤቱ ሪፖርት ማድረግና ከሰ/ት/ቤቱ ጋር በሚኖረው መደበኛ የግንኙነት
መርሃግብር መሰረት መገናኝት፡፡
ከላይ በተጠቀሱት እና በሌሎች አስፈላጊ ምክንያቶች የወላጆች ኮሚቴ አስፈላጊ መሆኑን
የተገነዘብን ስሇሆነ አስተዳደር ጽ/ቤቱ ይህን አይቶ ይህን የወላጆች ኮሚቴ በሚመሰረትበት
ዙሪያ ምክክር እንዲደረግና ወደ ስራ እንዲገባ ስንል ይህን አጭር ምክረሃሳብ አቅርበናል፡፡

አስተዳደር ዏቢይ

ታህሳስ 2016 ዓ.ም

You might also like