9 - Note-1

You might also like

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 3

መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም

ፈለገ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

የማቴዎስ ወንጌል፡ ምዕራፍ 9


(ማቴ 1 – 8) - ክርስቶስ በአልጋ የተኛውን ሽባ ሰው እንደፈወሰው
1/ በታንኳም ገብቶ ተሻገረና ወደ ገዛ ከተማው መጣ።
 ወደ ገዛ ከተማው (አገሩ) ማለት ኢየሩሳሌም ገባ
2/ እነሆም፥ በአልጋ የተኛ ሽባ ወደ እርሱ አመጡ። ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን፦ አንተ ልጅ፥ አይዞህ፥ ኃጢአትህ
ተሰረየችልህ አለው።
 ሃይማኖቶ ማለት፡ አንድም ያድንልናል ብለው መምጣታቸውን፡ አንድም ያድነኛል ብሎ መምጣቱን አይቶ፡
3/ እነሆም፥ ከጻፎቹ አንዳንዱ በልባቸው፦ ይህስ ይሳደባል አሉ።
4/ ኢየሱስም አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አለ፦ ስለ ምን በልባችሁ ክፉ ታስባላችሁ?
5/ ኃጢአትህ ተሰረየችልህ ከማለት ወይስ፦ ተነሣና ሂድ ከማለት ማናቸው ይቀላል?
6/ ነገር ግን በምድር ላይ ኃጢአትን ያስተሰርይ ዘንድ ለሰው ልጅ ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ፥ በዚያን ጊዜ ሽባውን፦ ተነሣ፤
አልጋህን ተሸከምና ወደ ቤትህ ሂድ አለው።
 ሐተታ፡ ኃጢአት ከማስተሠረይ ድውይ መፈወሱን ማስበለጡ ነው፡፡ ኃጢአት ሲሰረይ አይታይም፡ ድውይ ሲፈወስ ግን
ይታያልና፡፡ ሰውም ካላየው ያየውን ማድነቅ ልማድ ነውና፡ ሰው በሚያደንቀው ተናገረ፡፡
 አንድም ድውይ ሲፈወስ አይታችሁ፡ ኃጢአት ያስተሠርያል አትሉም ሲል ነው፡፡ የሥጋ ድህነት ለነፍስ ድህነት ምልክት
ነውና፡፡
 ተነስተህ አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለው፡ ከዓቀብተ ሥራይ ክዩ ነውና፡ እነዚያ አዳንን ካሉ በኃላ እህል ይቅመስ፡ ይዋል፡
ይደር፡ ይጽናና፡ ይላሉ፡፡ እሱ ግን ተረፈ ደዌ የለበትም፡፡
 አንድም እነዚያ አዳንን ብለው የሚመጣበት ጽዋው፡ የሚተኛበት አልጋው፡ ምንጣፉ ይገባናል ይላሉ፡፡ እሱ ግን ይህ ሁሉ
የለበትምና ተነሥተህ አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለው፡፡
7/ ተነሥቶም ወደ ቤቱ ሄደ።
8/ ሕዝቡም አይተው ተደነቁ፥ ለሰውም እንዲህ ያለ ሥልጣን የሰጠ እግዚአብሔርን አከበሩ።
 አላመኑም ቢሉ፡ እንዲህ ያለ ነቢይ ያስነሳልን ብለው፡፡
 አምነዋል ቢሉ፡ ለራሱ ደኅንነት ይሻ የነበረ ሥጋን ከባሕይ ልጅህ ጋር አዋህደህ ለሌላው ደኅንነትን እንዲያድል ያደረከው
ብለው፡፡

(ማቴ 9 – 13) - ክርስቶስ ማቴዎስን ተከተለኝ እንዳለው


9/ ኢየሱስም ከዚያ አልፎ በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረ ማቴዎስ የሚባል አንድ ሰው አየና፦ ተከተለኝ አለው። ተነሥቶም ተከተለው።
 ወይቤሎ ትልወኒ
 ሲያስገብር አላለም የሰው ገንዘብ ይዞ ሄደ ብለው ምክንያት እንዳያደርጉበት፡፡
 ተከተለኝ ማለት ለጊዜው በእግር ፍጻሜው ግን በግብር ምሰለኝ አለው፡፡
10/ በቤቱም በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ እነሆ፥ ብዙ ቀራጮችና ኃጢአተኞች መጥተው ከኢየሱስና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር አብረው
ተቀመጡ።
 መጽሑ ብዙኃን ኃጥአን መጸብሓን
 ተከተለኝ ካልከኝስ ከቤት ገብተህ ምሳ ብላልኝ ብሎታል፡፡ የቤቴን ትዳር ያየ እንደሆነ አክብሮ ያኖረኛል ብሎ፡፡
 አንድም ትምህርተ ምናኔ ነው፡፡ (1ኛ ነገ 9፡9) ኤልሳዕ 12 ጥንድ በሬ አስጠምዶ ሲያሳርስ ኤልያስ ሐሜለቱን ከራሱ ላይ ጥሎ
ተከተለኝ አለው፡፡ እሱም ቆየኝ ብሎ ሁሉንም አርዶ ለነድያን አብልቶ ተከትሎታል በዚያ ልማድ፡፡
11/ ፈሪሳውያንም አይተው ደቀ መዛሙርቱን፦ መምህራችሁ ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር አብሮ ስለ ምን ይበላል? አሉአቸው።
12/ ኢየሱስም ሰምቶ፦ ሕመምተኞች እንጂ ባለ ጤናዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም፤
13/ ነገር ግን ሄዳችሁ፦ ምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም ያለው ምን እንደ ሆነ ተማሩ፤ ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ
ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና አላቸው።
 ሕሙማን ይፈቅድዎ ለዓቃቤ ወአኮ ጥዑያን
 አንድም ሕመምተኞች እንዲፈውሳቸው ይፈልጉታል
 አንድም ሕሙማን ነን የሚሉ ኃጥአን መጸብሐን ይሹኛል፡ ደኅነኞች ነን የምትሉ እናንተ ግን አትሹኝም፡፡

ማቴዎስ ወንጌል አንድምታ 03 ገጽ 1


መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም
ፈለገ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

 አንድም ጻድቃን ነን የምትሉ እናንተን ልጠራ አልመጣሁምና፡ ኃጥአን ነን የሚሉ እኒህን ወደ ንስሐ ልጠራ መጥቻለሁ እንጂ፡

(ማቴ 14 – 17) - የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ስለጾም እንደጠየቁት


14/ በዚያን ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው፦ እኛና ፈሪሳውያን፥ ብዙ ጊዜ የምንጦመው፥ ደቀ መዛሙርትህ ግን
የማይጦሙት ስለ ምንድር ነው? አሉት።
 ሐተታ፡ ምን ጾም አላቸው ቢሉ እሁድና ማክሰኞ ሐሙስ ይጾማሉና፡ አንድም ጾመ ረቡዕ፡ ጾመ ሐሙስ፡ ጾመ ሰቡዕ፡ ጾመ
አሱር የሚባል ጾም አለና፡፡
15/ ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት
ወራት ይመጣል፥ በዚያ ጊዜም ይጦማሉ።
 አንድም፡ የኔ ደቀ መዛሙርት ከኔ ጋር ሳሉ መጾም ማልቀስ አይቻላቸውም፡ እኔ ከእነሱ የምለይበት ሰዓት ይደርሳል፡ ያን ግዜ
ይጾማሉ፡ በስቅለት 2 ቀን፡ በዕርገት 40 ቀን መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው ይጾማሉ፡፡
16/ በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚያኖር የለም፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና፥ መቀደዱም የባሰ ይሆናል።
 አንድም፡ ሐዋርያት በመንፈስ ቅዱስ ባልታደሰ ሰውነታቸው ጾምን ጹሙ የሚላቸው የለም፡፡ ጾሙም ይቀራል ሰውነታቸውም
ይጎዳልና፡፡
17/ በአረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ አቁማዳው ይፈነዳል፥ የወይን ጠጁም ይፈሳል አቁማዳውም
ይጠፋል፤ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል፥ ሁለቱም ይጠባበቃሉ።
 አንድም፡ ሐዋርያትን በልጅነት ባልታደሰ ሰውነታቸው ሕግ ጠብቁ የሚላቸው የለም፡፡ ጠብቁ ቢሉአቸው ሕጉም ይፈርሳል
ሰውነታችሁም ይጎዳልና፡፡ በልጅነት በታደሰ ሰውነታቸው ግን ወንጌልን ጠብቁ ይላቸዋል፡ እርስ በእርሳቸውም ይጠባበቃሉ፡፡
እነሱ ሕጉን ይጠብቁታል፡ ሕጉም እነሱን ይጠብቃቸዋል፡፡

(ማቴ 18 – 26) - ክርስቶስ የመኮንኑን ልጅ እንደፈወሳት


18/ ይህንም ሲነግራቸው፥ አንድ መኰንን መጥቶ፦ ልጄ አሁን ሞተች፤ ነገር ግን መጥተህ እጅህን ጫንባት፥ በሕይወትም ትኖራለች
እያለ ሰገደለት።
19/ ኢየሱስም ተነሥቶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተከተለው።
20/ እነሆም፥ ከአሥራ ሁለት ዓመት ጀምሮ ደም የሚፈስሳት ሴት በኋላው ቀርባ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፤
21/ በልብዋ፦ ልብሱን ብቻ የዳሰስሁ እንደ ሆነ፥ እድናለሁ ትል ነበረችና።
22/ ኢየሱስም ዘወር ብሎ አያትና፦ ልጄ ሆይ፥ አይዞሽ፤ እምነትሽ አድኖሻል አላት። ሴቲቱም ከዚያች ሰዓት ጀምራ ዳነች።
 ወይቤላ ተአመኒ ወለትየ ሃይማኖትኪ አሕየወተኪ
 እንዲያው አይደለም ወደ ኃላ ተመልሶ ደቀ መዛሙርቱን መኑ ገሠሠኒ ጽንፈ ልብስየ አላቸው፡
 እነሱም ናሁ ብዙኀ ሰብእ ይጸዓቅ ወይጣወቅ አንተሰ ትብል መኑ ገሠሠኒ ጽንፈ ልብስየ አሉት፡፡
 ተአምራት ያደርጋል እንጂ ነገር ግን ይሠርቀዋል እንዳይሉ አአምር ከመ ወጽአ ኃይል እምኔየ ብሎአቸዋል፡፡ ነገሩ ካልቀረስ
ብላ ወደ ፊቱ አልፋ ሰገደችለት፡፡
 ከዚህ በኃላ ተአመኒ ወለትየ ብሎአታል፡፡
 ምሳሌ፡ /ይህች ሴት - የቤተ አይሁድ፡ /ጽንፈ ልብስ - ከሐዋርያት ቀጥሎ የተነሡ መምህራን /ቤተ አይሁድ ስብ
ማጤሳቸውን፡ ደም ማፍሰሳቸውን መተዋቸውን መናገር ነው፡፡
23/ ኢየሱስም ወደ መኰንኑ ቤት በደረሰ ጊዜ፥ እምቢልተኞችንና የሚንጫጫውን ሕዝብ አይቶ፦
 ብዙኃን መብክያነ አንዘ ይትሀወኩ፡ ሹም ቢሞት ሃምሳ፡ የሹም ልጅ ቢሞት መቶ ታምሳ እንዲሉ፡
24/ ብላቴናይቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችምና ፈቀቅ በሉ አላቸው። በጣምም ሳቁበት።
 አላ ትነውም፡ አንድም፡ እንዲያስነሳት ያውቃልና፡ አንድም፡ በነፍስ ሕያዊት ናትና ትቀድሰዋለችና፡፡
 ወሰሐቅዎ፡ አንድም፡ በኢያኢሮስ ሳቁበት፡ የሞተና ያልሞተ የማያውቅ፡ ጭራሽ ያስነሳልኛል ብሎ ይዞ መጣ ብለው፡፡ አንድም
የጌታን ነገሩን እንደዋዛ አዩበት፡ ያጠብን፡ የገነዝን፡ እኛ እያለን አልሞተችም ይለናል እንዴ ብለው፡፡
25/ ሕዝቡን ግን ከአስወጡ በኋላ ገብቶ እጅዋን ያዛት፥ ብላቴናይቱም ተነሣች።
 ይህች ብላቴና የታመመችበት፡ የተወለደችበት፡ የተፈወሰችበት፡ የተነሳችበት ቀኑ አንድ ነው፡፡
26/ ያም ዝና ወደዚያ አገር ሁሉ ወጣ።
 ቀድሞ መሞትዋ ኃላ መነሳትዋ ባራቱም ማዕዘን ተነገረ፡፡

ማቴዎስ ወንጌል አንድምታ 03 ገጽ 2


መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም
ፈለገ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

(ማቴ 27 – 31) - ክርስቶስ ሁለቱን ዓይነ ሥውሮችን እንደፈወሳቸው


27/ ኢየሱስም ከዚያ ሲያልፍ ሁለት ዕውሮች፦ የዳዊት ልጅ ሆይ፥ ማረን ብለው እየጮሁ ተከተሉት።
 እንዘ ይጸርሑ ወይብሉ "ተሣሃለነ ወልደ ዳዊት" እያሉ - በየሰዓቱ ልንደጋግመው የሚገባ ድንቅ ኦርቶዶክሳዊ ጸሎት፡፡
28/ ወደ ቤትም በገባ ጊዜ ዕውሮቹ ወደ እርሱ ቀረቡ፥ ኢየሱስም፦ ይህን ማድረግ እንድችል ታምናላችሁን? አላቸው። አዎን፥ ጌታ ሆይ
አሉት።
 ለዕውራን ርቆ መሄድ አይሆንላቸውምና ከቤት ገብቶ ቆይቶአቸዋል፡፡ ከቤት በገባ ጊዜ ዕውራን ወደ እርሱ መጡ፡፡
 ታምናላችሁን አላቸው፡ ጌታ የጠየቃቸው አንድም አላዋቂ ሥጋን እንደተዋሐደ ለማጠየቅ፡ አንድም አወቅሁት ብሎ ሥራውን
አይተውምና፡ በዛው ሥራውን ለመስራት አንድም፡ ሃይማኖታቸውን ለመግለጽ፡፡
29/ በዚያን ጊዜ፦ እንደ እምነታችሁ ይሁንላችሁ ብሎ ዓይኖቻቸውን ዳሰሰ።
30/ ዓይኖቻቸውም ተከፈቱ።
31/ ኢየሱስም፦ ማንም እንዳያውቅ ተጠንቀቁ ብሎ በብርቱ አዘዛቸው። እነርሱ ግን ወጥተው በዚያ አገር ሁሉ ስለ እርሱ አወሩ።
 እንዘ ይብል ዑቁ ኢትንግሩ ለመኑሂ፡ አንድም ውዳሴ ከንቱ አይሻምና አንድም የሚያምኑበት ጊዜው አልደረሰምና፡፡ አንድም
እስከ ትንሣኤ፡፡
 ወጥተው ለሰው ሁሉ ተናገሩ፡ አትንገር ያሉትን መንገር ልማድ ነውና፡ አንድም ጊዜው ቢደርስ
 ምሥጢር ስናወራ እንጠንቀቅ፡ በተለይ በሕይወታችን መልካም ነገር ሊሆን ሲል፡፡

(ማቴ 32 – 38) - ክርስቶስ ጋኔን ያደረበትን ዲዳ ሰው እንደፈወሰው


32/ እነርሱም ሲወጡ እነሆ፥ ጋኔን ያደረበትን ዲዳ ሰው ወደ እርሱ አመጡ።
 ጋኔን አድሮበት ድዳ ደንቆሮ ያደረገው ሰውን አመጡ፡፡ አንዳንዴ ድዳ ደንቆሮ ጋኔን ሲያድርበት ሰውም ድዳ ደንቆሮ ይሆናል፡
፡ በስጋ የታመሙትን አይመለከትም፡፡
 አንድም ጽሙም ወበሐም ይላል፡ ቀድስ ቢሉት አልቀድስም ብሎአልና፡ ድዳ አለው፡፡ ቃለ እግዚአብሔርን ስማ ተማር ቢሉት
አልሰማም ብሎአልና፡ ደንቆሮ አለው፡፡
33/ ጋኔኑንም ካወጣው በኋላ ዲዳው ተናገረ። ሕዝቡም፦ እንዲህ ያለ በእስራኤል ዘንድ ከቶ አልታየም እያሉ ተደነቁ።
34/ ፈሪሳውያን ግን፦ በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል አሉ።
 ፈሪሳውያን ግን ታምራት ይደረጋል ሰው ይሰበሰባል፡ ኦሪት ትጠፋለች ወንጌል ትሰፋለች ብለው፡ ካለቃቸው ከቡዔል ዘቡዔል
ተጨዋውቶ ያስወጣቸዋል፡ እንጂ አያስወጣቸውም አሉ፡፡ ለነዚህ አሁን አይመልስላቸውም በሚቀጥለው ጉባዔ
ይመልስላቸዋል፡፡
35/ ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ፥ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ፥ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ፥
በከተማዎችና በመንደሮች ሁሉ ይዞር ነበር።
36/ ብዙ ሕዝብም ባየ ጊዜ፥ እረኛ እንደ ሌላቸው በጎች ተጨንቀው ተጥለውም ነበርና አዘነላቸው።
 ወተሣሃሎሙ፡ አዘነላቸው ማለት፡ በፃማ ኦሪት፡ በፃማ ኃጢአት ደክመዋልና፡፡
 ወግዱፋን ከመ አባግዕ ዘአልቦ ኖላዊ፡ እረኛ እንደ ሌላቸው በጎች ተጨንቀው ተጥለውም ነበርና አዘነላቸው።
37/ በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፦ መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤
38/ እንግዲህ የመከሩን ጌታ ወደ መከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት አላቸው።
 ማዕረሩሰ ብዙኀ፡ ወገባሩ ኀዳጥ፡ ሰአልዎ ለበዓለ ማዕረር፡ ከመ ይወስክ ገባረ ለማዕረሩ
 አንድም፡ /ማዕረሩሰ ብዙኀ፡ ሰማዕያኑ ብዙ ነው፡ /ወገባሩ ኀዳጥ፡ ሠራተኛው አገልጋዩ ግን ትንሽ ነው፡፡ /ሰአልዎ ለመከሩ
አጫጅ ሠራተኛ ይጨምር ዘንድ
 አንድም /ማዕረሩሰ ብዙኀ ሰማዕያኑ ብዙ ናቸው፡ /ወገባሩ ኀዳጥ፡ መምህሩ ግን አንድ ዩሐንስ ነው፡፡ /ሰአልዎ የመምህርነት
ባለቤት እኔን ለምኑኝ፡ እናንተን ሐዋርያትን መምህር አድርጌ አስነሳችሁ ዘንድ፡፡
 ሹመት አትለምኑ ብሎ የለምን አሁን ስለምን ለምኑኝ ይላል ቢሉ፡ አንድም ያ ሥጋዊ ነው፡ ይህ ግን መንፈሳዊ ነውና፡ አንድም
አስፈቅዶ ለመሾም በኃላ መከራ ብንቀበል ወደን ተሹመነዋል እንዲሉ፡፡
 አንድም /ማዕረሩሰ ብዙኀ፡ መጽሐፍት ንባባቸው ብዙ ነው፡ /ወገባሩ ኀዳጥ፡ ትርጉዋሜአቸው ግን ጥቂት ነው፡ /ሰአልዎ
የብሉይ የሐዲስ ባለቤት እኔን ለምኑኝ መተርጉማን አድርጌ አስነሳችሁ ዘንድ፡ ድህነትን እንድታሰጡ አደርጋችሁ ዘንድ፡

ማቴዎስ ወንጌል አንድምታ 03 ገጽ 3

You might also like