Professional Documents
Culture Documents
2
2
2
የትብብር ማህበር
አዲስ አበባ፡ ኢትዮጲያ
ምስረታ
. አድራሻ፡- ን/ስ/ላ/ከ/ከተማ ወረዳ 11 ቀጠና 1
. የምሰረታ ዘመን ፡- መስከረም 3 ቀን 2015 ዓ.ም
. ዘርፍ ፡- ማህበራዊ አገልግሎት
አደረጃጀት
ማህበሩ የተቐቐመበትን ዓላማና ዕቅድ ከግብ ለማድረስ እንዲመቸው በተጨማሪም ግልፅና
ቀልጣፋ አገልግሎቱን ለአባላቱ ለማድረስ በአራት(4)መዋቅር በመደራጀት የተመሰረተ ነው፡፡
1 ኛ. የማህበሩ አስተዳደር ክፍል
2 ኛ. የማህበሩ ፋይናንስ ክፍል
3 ኛ. የማህበሩ ንበረት ክፍል
4 ኛ. የማህበሩ ኦዲት ክፍል
ከላይ በዝርዝር በተቀመጠው የማህበሩ የአደረጃጀት ክፍሎች ከአንድ(1)በላይ የስራ ድርሻ
ያላቸው ሲሆኑ፡የተጠቀሱትን የስራ ሐላፊነቶችን የሚያከናውኑት ሰዎች (አመራሮች)
(ኮሚቴዎች)ከባለቤቶቹና በቐሚነት ነዋሪ ከሆኑት የማህበሩ አባላት ውሰጥ በእጩነት
ቀርበው(ተጠቁመው) የተመረጡት ቢቻ ናቸው፡፡
ማህበሩ በአባላቱ አርቃቂነትና በጠቅላላ ጉባኤ በአፀደቀው የመተዳደርያ ደምብ መሰረት
የሚመራ ሲሆን አጠቃላይ የማህበሩ አባላትም፡ሆኑ የማህበሩ ኮሚቴ፡የማህበሩ አባላት
በመሆናቸው ቢቻ፡ግዴታና ውዴታ እንዲሁም መብትና ጥቅም ያላቸው የሆናሉ፡፡
የዝህ ማህበር የምስረታ ሰነድና የማህበሩ መተዳደርያ ድንብ፡በሁሉም የማህበሩ አባላት ፍሎጎት
እና ሁኔታ የተሳናዳ ስነድ ሲሆን፡ይህ ማህበር በመተዳደርያ ደንቡ ላይ በግልፅ እንዳስቀመጠው
ለንግድ ስራ ወይም ለትርፍ ያላተቐቐመ እና በሃይማኖታዊም ሆነ በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ
እንደ ማህበር ምንም አይነት እንቅስቃሴ ማድረግ የማየፍቀድ መሆኑን የደነገገ ሲሆን፡ነገር ግን
ማንኛውም የማህበሩ አባል በነዚህ ጉዳዮች ላይ የመሳተፍ የመጋበዝና የማዘጋጀት መብትን
የማይነፍግ ነው፡፡
የማህበሩ አገልግሎት
1. በመንኛውም ሁኔታ የአከባቢውን ሰላምና ፀጥታን ለማስከበር ከህግ አካላት ጋር
በትብብር ይሰራል፡፡
2. የአከባቢውን የፅዳት ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ ይቆጣጠራል፡፡
3. በህግ የተከለከሉ ነገሮች በአከባቢው እንዳይሸጡ እንዳይለወጡ ይከላከላል፡፡
4. የነዋሪው መግብያና መውጫ በቤዝ ማፕ በሚታየው ሁኔታ ስፋታቸውን ጠብቀው
እንዲቀጥሉ አሰፈላጊውን ጥረት ያደርጋል፡፡
5. በማህበሩ አባላት መካከል የሚፍጠሩትን አለመግባባቶችን ለመፍታት ጥረት ያደርጋል፡፡
6. በማንኛውም ሁኔታ ከአባላትም ሆነ ከሌላ አካል በአከባቢውም ሆነ በማህበሩ ላይ
የሚፈፀሙ አሉታዊ ተገባሮችን ይቃወማል፤ቅጣት ያስተላልፋ፤በፍ/ቤት ደረጃ
አቤቱታ(ክስ) ያቀርባል፡፡
7. በማህበሩ አባላት ላይ የተለያዩ ከባድ ሁኔታዎች ሲገጥሙ በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ
በተቀመጠው ወጥ አሰራር መሰረት ማህበራዊ ድጋፍ ያደርጋል፡፡
8. የማህበሩን አባላትም ሆነ የአከባቢውን የሳላም ሁኔታን ለማስጠበቅ አሰፈላጊ የሆነውን
ሁሉ ያደርጋል፡፡
9. በመኖሪያዎቹ አከባቢው የ 24 ሰዓት የጥበቃ ሻፋን እንዲኖር ያደርጋል፡፡
10.በማህበሩ አባላት መኖር አከባቢ የተጓደሉ፤የተበለሹ አና ለአደጋ የተጋለጡ መሰረተ
ልማቶች አፋጣኝ መፍቴ እንዲያገኙ አጥብቆ ይሰራል፡፡