Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 35

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ

የተሻሻለው የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር


አፈጻጸም መመሪያ
መመሪያ ቁጥር 01/2015

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ


የካቲት 2015 ዓ.ም
አሶሳ
ማውጫ
ክፍል አንድ ......................................................................................................................... 1
አጠቃላይ ሁኔታ.................................................................................................................. 1
አንቀጽ 1 አጭር ርዕስ ........................................................................................................ 1
አንቀጽ 2 የመመሪያው አስፈላጊነት ................................................................................... 1
አንቀጽ 3 የቃላት ትርጓሜ ................................................................................................. 1
ክፍል ሁለት ........................................................................................................................ 4
ዝውውር የሚፈጸምባቸው ደረጃዎችና የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች .................................. 4
አንቀጽ 4. ዝውውር የሚፈጸምባቸዉ ደረጃዎች ................................................................ 4
አንቀጽ 5. የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች .............................................................................. 4
አንቀጽ 6. ዝውውርና ምደባ ከመፈፀሙ በፊት ትኩረት ሊሰጥባቸው የሚገቡ ጉዳዮች፡. 5
አንቀጽ 7. የወረዳዎችና ዞኖች የምድብ ክፍፍል ................................................................ 6
አንቀጽ 8 የአገልግሎት ስሌት፡ ........................................................................................... 6
ክፍል ሶስት ......................................................................................................................... 8
የዝውውርና ምደባ ዓይነቶችና መስፈርቶች ....................................................................... 8
አንቀጽ 9. የዝውዉርና ምደባ መስፈርቶች ........................................................................ 8
አንቀጽ 10. የዝዉዉርና ምደባ ዓይነቶችና አፈጻጸም ........................................................ 8
10.1 በአገልግሎት የሚፈፀም ዝውውር ................................................................................ 8
10.2 በትዳር ምክንያት የሚፈጸም ዝውውር፡ ..................................................................... 10
10.3 . በሙያ ብቃት የሚደረግ ዝውውር፡ ....................................................................... 11
10.4 በጤና ምክንያት የሚደረግ ዝውውር፡ ........................................................................ 11
10.5 በመምህራን ማህበር ተመራጭነት እና ተሿሚነት የሚሰራ ዝውውር ..................... 12
10.6 በስራ አስፈላጊነት እና ትምህርት ደረጃ ማሻሻል የሚደረግ ዝውውርና ምደባ፡ ........ 12
ክፍል አራት፡ ..................................................................................................................... 14
የዝውውር ፍላጎት ማሳወቂያ፣ መስሪያ እና ቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ ................................ 14
አንቀጽ 11 የዝውውር ፍላጎት ማሳወቂያ ጊዜ ............................................................... 14
አንቀጽ 12 የዝውውር መስሪያ ጊዜ ................................................................................. 14
አንቀጽ 13 ቅሬታ ስለማቅረብ ........................................................................................ 15
ክፍል አምስት.................................................................................................................... 16
በየደረጃው የሚገኙ ፈፃሚ አካላት ተግባርና ኃላፊነት ..................................................... 16
አንቀጽ 14 የክልል ትምህርት ቢሮ ተግባርና ኃላፊነት ................................................... 16
አንቀጽ 15. የዞን ትምህርት መምሪያ ተግባርና ኃላፊነት፡ .............................................. 16
አንቀጽ 16. የወረዳ/ከተማ አስተዳደሮች/ልዩ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ተግባርና ኃላፊነት፡17
አንቀጽ 17. የት/ቤት ተግባርና ኃላፊነት .......................................................................... 17

ii
የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 01/2015
አንቀጽ 18. በየደረጃው የመምህራን ማህበር ተሳትፎ ................................................. 18
አንቀጽ 19. የዝውውር እና ምደባ ኮሜቴ አባላት ........................................................... 18
አንቀጽ 20. ልዩ ልዩ ሁኔታዎች ...................................................................................... 18
አንቀጽ 21. ተጠያቂነት፡ ................................................................................................... 19
አንቀጽ 22. መመሪያውን ስለማሻሻል፡ ........................................................................... 20
አንቀጽ 23. የተሻሩ መመሪያዎች፡ ................................................................................... 20
አንቀጽ 24. የመመሪያው ተፈፃሚነት ወሰን .................................................................. 20
አንቀጽ 25. መመሪያው ስለሚፀናበት ጊዜ፡ ................................................................... 20
አባሪ፡ የዝውውር ፍላጎት መሙያ ቅጻ ቅጾች:- ከት/ቤት - ት/ቤት የመምህራን ዝውውር
መጠየቂያ ቅጽ (ቅጽ ዐ1-1) .............................................................................................. 21
ከት/ቤት - ት/ቤት የር/መምህራን፣ ም/ር/መምህራን ዝውውር መጠየቂያ ቅጽ (ቅጽ ዐ1-2)
........................................................................................................................................... 22
ከጉድኝት ማዕከል - ጉድኝት ማዕከል የሱፐርቫይዘሮች ዝውውር መጠየቂያ ቅጽ (ቅጽ ዐ1-3)
........................................................................................................................................... 23
ከወረዳ - ወረዳ የመምህራን ዝውውር መጠየቂያ ቅጽ (ቅጽ ዐ2-1) ............................... 24
ከወረዳ - ወረዳ የር/መምህራን፣ ም/ር/መምህራን ዝውውር መጠየቂያ ቅጽ (ቅጽ ዐ2-2)25
ከወረዳ - ወረዳ የሱፐርቫይዘሮች ዝውውር መጠየቂያ ቅጽ (ቅጽ ዐ2-3) ........................ 26
ከዞን/ከተማ አስተዳደር - ዞን/ከተማ አስተዳደር የመምህራን ዝውውር መጠየቂያ ቅጽ (ቅጽ ዐ3-
1) ....................................................................................................................................... 27
ከዞን/ከተማ አስተዳደር - ዞን/ከተማ አስተዳደር የር/መምህራን፣ም/ር/መምህራን ዝውውር
መጠየቂያ ቅጽ (ቅጽ ዐ3-2) .............................................................................................. 28
ከዞን/ከተማ አስተዳደር - ዞን/ከተማ አስተዳደር የሱፐርቫይዘሮች ዝውውር መጠየቂያ ቅጽ (ቅጽ
ዐ3-3) ................................................................................................................................. 29
ከክልል/ከተማ አስተዳደር - ክልል/ከተማ አስተዳደር የመምህራን ዝውውር መጠየቂያ ቅጽ (ቅጽ
ዐ4-1) ................................................................................................................................. 30
ከክልል/ከተማ አስተዳደር - ክልል/ከተማ አስተዳደር የር/መምህራን፣ም/ር/መምህራን ዝውውር
መጠየቂያ ቅጽ (ቅጽ ዐ4-2) .............................................................................................. 31
ከክልል/ከተማ አስተዳደር - ክልል/ከተማ አስተዳደር የሱፐርቫይዘሮች ዝውውር መጠየቂያ ቅጽ
(ቅጽ ዐ4-3)........................................................................................................................ 32

iii
የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 01/2015
ክፍል አንድ
አጠቃላይ ሁኔታ

አንቀጽ 1 አጭር ርዕስ


ይህ መመሪያ “የተሻሻለው የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር አፈጻጻም መመሪያ
ቁጥር 02/2015” ተብሎ ሊጠራ ይችላል፡፡

አንቀጽ 2 የመመሪያው አስፈላጊነት


2.1 መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች በተመደቡበት ቦታ ተረጋግተው የመማር ማስተማሩን
ስራ ለማከናወን እንዲችሉ ለማድረግ፣
2.2 መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ የመስራት መብትን ለማረጋገጥ፣
2.3 በአንድ ቦታ አላስፈላጊ የሰው ሃይል ክምችት እንዳይፈጠር በማድረግ የሰው ኃይል ፍላጎት
ስርጭትን ፍትሃዊነት ለማረጋገጥ፣
2.4 መምህራን የማስተማር ተግባራቸዉን በብቃት እንዲወጡ፣ ርዕሳነ መምህራን የሚመሩትን
ትምህርት ቤት በብቃትና በዉጤታማነት እንዲመሩና ሱፐርቫይዘሮች ት/ቤቶችን በብቃት
እንዲደግፉ በማድረግ የተማሪዎችን ዉጤት ለማሻሻል፣ የስራ ተነሳሽነት ለመፍጠር፣
2.5 ታታሪና ብቃት ያላቸውን መምህራን፣ ርዕሳነ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች ወደ ሙያው
ለመሳብና በሙያው እንዲቆዩ ለማድረግ፣
2.6 በክልሉ ውስጥ የመምህራን፣ ር/መምህራንና ሱፐርቫይዘሮችን ዝውውር ግልጽነትና ተጠያቂነት
የሰፈነበት፣ ወጥነትና ፍትሃዊነት ያለዉ እንዲሆን ለማድረግ፣

አንቀጽ 3 የቃላት ትርጓሜ


የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ
3.1. ‘’መምህር’’ ማለት እውቅና ካለው ተቋም በሰርትፊኬት፣ በዲኘሎማ፣ በመጀመሪያ ዲግሪ
ወይም በሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት ደረጃ ተመርቆ በመንግስት ት/ቤት የሚያስተምር ማለት
ነው፡፡
3.2. ‘’ር/መምህር’’ ማለት ት/ቤትን በኃላፊነት የሚመራ የትምህርት ቤት አመራር ማለት ነው፡፡
3.3. ‘’ም/ር/መምህር’’ ማለት ት/ቤትን በምክትል ኃላፊነት የሚመራ የትምህርት ቤት አመራር
ማለት ነው፡፡
3.4. ‘’የትምህርት ባለሙያ ’’ ማለት በየደረጃው የሚገኝ ትምህርት መዋቅር በዓላማ ፈጻሚነት
ተመድቦ በመስራት ላይ የሚገኝ ማለት ነው፡፡
3.5. ‘’ሱፐርቫይዘር’’ ማለት የጉድኝት ትምህርት ቤቶችን በመደገፍና በማስተባበር ተቋማዊ
ለውጥ እንዲመጣ የሚያደርግ የትምህርት ቤት አመራር ማለት ነው፡፡
3.6. ‘’አመቻች’’ ማለት በአማራጭ መሰረታዊ ትምህርት ጣቢያዎች ተመድበው ተማሪዎችን
በማስተማር/በማመቻቸት ላይ ያሉ ማለት ነው፡፡
3.7. ‘’የት/ቤት አመራሮች’’ ማለት በርዕሰ መምህርነት፣ በምክትል ርዕሰ መምህርነት ወይም
በጉድኝት ማዕከል ሱፐርቫዘርነት ተመድበው የሚሰሩ ባለሙያዎችን ማለት ነው፡፡
3.8. ‘’አገልግሎት ’’ ማለት ህጋዊ እውቅና ካላቸው የግል፣ የመንግስት እና/ወይም መንግስታዊ
ያልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ በመቀጠር በመደበኛ የስራ ሰዓት የተወሰነ ስራ በማከናወን፣
መደበኛ ደመወዝ እየተከፈለው የሥራ ግብር የተከፈለበት የስራ ልምድ ነው፡፡
3.9. ‘’አግባብ ያለው አገልግሎት ’’ ማለት በመምህርነት፣ በት/ቤት አመራርነት ወይም
በትምህርት ባለሙያነት የተገኘ የስራ ልምድ ማለት ነው፡፡
3.10. ‘’ዝውውር’’ ማለት መምህራን፣ ር/መምህራን፣ ምክትል ር/መምህራን እና ሱፐርቫይዘሮች
ከሚሰሩበት ት/ቤት፣ ወረዳ/ከተማ አስተዳደር፣ ዞን ወይም ክልል ወደ ሌላ ት/ቤት፣
ወረዳ/ከተማ አስተዳደር፣ ዞን ወይም ክልል በትምህርት ዘመኑ አንድ ጊዜ የሚደረግ የስራ
ቦታ ለውጥ ነው፡፡
3.11. ‘’ለኑሮ አስቸጋሪ ቦታ’’ ማለት በአንጻራዊነት የአየር ጠባይ ተስማሚ አለመሆንና የመሰረተ
ልማት አዉታሮች ያልተሟላበት ቦታ ማለት ነው፡፡
3.12. ‘’ተመራጭ’’ ማለት ከቀበሌ እስከ ክልል በሕዝብ ምርጫ ወይም በመምህራን ማህበር
ተመርጠው የሚሰሩ ማለት ነው፡፡
3.13. ‘’ተሿሚ’’ ማለት በመንግስት አካላት በሹመት በኃላፊነት ቦታ ላይ ተመድበው የመንግስት
ተቋማትን በመምራት ላይ የሚገኙ ማለት ነው፡፡
3.14. ‘’የትምህርት ደረጃን ያሻሻሉ’’ ማለት በመደበኛው፣ በክረምት ተከታታይ፣ በማታ ትምህርት፣
ቅዳሜና እሁድ ፕሮግራም በመከታተል ከሴርትፊኬት ወደ ዲፕሎማ ወይም ከዲፕሎማ
ወደ መጀመሪያ ዲግሪ ወይም ከመጀመሪያ ዲግሪ ወደ 2ኛ ዲግሪ የትምህርት ደረጃቸዉን
ያሻሻሉ ማለት ነዉ፡፡
3.15. ‘’የጋብቻ ማስረጃ’’ ማለት ህጋዊነት ባላቸው ተቋማትና በባህላዊ ሥርዓት ማለትም በማዘጋጃ
ቤት፣ በወሳኝ ኩነቶች ኤጀንሲ፣ በፍርድ ቤት ወይም በሃይማኖት ድርጅት ወይም የአገር
ሽማግሌዎች ባሉበት ተፈጽሞ የሚሰጥ የጋብቻ ማስረጃ ማለት ነው፡፡

2
የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 01/2015
3.16. ‘’የጤና ማስረጃ’’ ማለት አንድ መምህር ወይም የት/ቤት አመራር በሚሰራበት ቦታ በጤና
ምክንያት የጤና ተቋም የቅርብ ክትትል የሚያስፈልጋቸው ስለመሆናቸው በመንግስት
ሆስፒታሎች የሐኪሞች ቦርድ ተረጋግጦ የሚሰጥ የህክምና ማስረጃ ማለት ነው፡፡
3.17. ‘’የርስ-በርስ ዝውውር’’ ማለት ሁለት መምህራን፣ ወይም የት/ቤት አመራሮች በትምህርት
ዓይነት፣ ዝግጅት ደረጃ ተመሳሳይ እና በደመወዝ ተቀራራቢ ሆነው በመደበኛ የዝውውር
ወቅት ታይቶ ማዛወር አሰቸጋሪ ሆኖ ሲገኝ ሁለቱ ለመቀያየር ጥያቄ ሲያቀርቡ እና
የሚሰሩባቸው ወረዳዎች ሲስማሙ የሚፈፀም የዝውውር ዓይነት ነው፡፡

3
የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 01/2015
ክፍል ሁለት
ዝውውር የሚፈጸምባቸው ደረጃዎችና የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች
አንቀጽ 4. ዝውውር የሚፈጸምባቸዉ ደረጃዎች
4.1 ከክልል-ክልል እና ተጠሪነታቸዉ ለፌዴራል መንግስት ወደ ሆኑት ከተማ አስተዳደሮች፣
4.2 ከዞን-ዞን/ከተማ አስተዳደር/ልዩ ወረዳ
4.3 ከወረዳ-ወረዳ፣
4.4 ከት/ቤት ት/ቤት/ከጉድኝት ጉድኝት፣
4.5 በተ.ቁ 4.1 እና 4.2 ደረጃ የሚከናወኑ ዝውውሮች በክልል ትምህርት ቢሮ ደረጃ የሚሰራ ፣ በተ.ቁ
4.3 የተጠቀሰው በዞን ትምህርት መምሪያ ደረጃ እንዲሁም በ4.4 የተጠቀሰው ዝውውር
በወረዳ/ከተማ አስተዳደር/ልዩ ወረዳ ደረጃ የሚከናወን ይሆናል፡፡

አንቀጽ 5. የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች


5.1 ከሚሰሩበት ትምህርት ቤት ወደ ሌላ ትምህርት ቤት ለመዛወር ፍላጐት ያላቸውን መምህራን፣
ር/መምህራንና ሱፐርቫይዘሮችን ለማስተናገድ እንዲቻል የወረዳ/ከተማ አስተዳደሮች ትም/ጽ/ቤት
የሚፈፀመውን ዝውውርና ቅጥር በመመሪያው ጥምርታ ስሌት መሠረት ማጣጣም ይጠበቅባቸዋል፡፡
5.2 የወረዳ ትም/ጽ/ቤቶች ያላቸውን ክፍት የመምህራን፤ የርዕሳነ መምህራንና የሱፐርቫይዘሮች የሥራ
መደቦችና ለቀጣዩ ዘመን የሚያስፈልጋቸውን ተጨማሪ የሰው ኃይል በዝውውርና በቅጥር
ማስፈጸሚያ ጥምርታ ስሌት መሠረት ከቀጣዩ የበጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጅት በፊት ለዞን ትምህርት
መምሪያ ያሳውቃሉ፣
5.3 የወረዳ ትም/ጽ/ቤቶች፣ አንቀጽ 5. ተራ ቁጥር 5.1 ላይ በተጠቀሰው መሠረት ከወረዳ ወደ
ወረዳ/ከተማ አስተዳደር፣ ከዞን ወደ ዞን ወይም ከክልል ወደ ክልል ዝውውር የሚጠይቁትን
መምህራን፣ እና የት/ቤት አመራሮች ካላቸው ክፍት የሥራ መደቦች የደመወዝ በጀት 7ዐ%
በዝውውር ቀሪውን 3ዐ% ደግሞ በቅጥር ያሟላሉ፡፡ ሆኖም ከወረዳ-ወረዳ፣ ከዞን-ዞን፣ ወይም
ከክልል-ክልል ዝውውር በየደረጃው ተሰርቶ 70% በዝዉዉር ማሟላት ካልተቻለ እና የተጠየቀውን
በየደረጃው የዝውውር ፈጻሚ አካላት ከገለፁ በአዲስ ቅጥር መምህራን ቦታዉን መሸፈን ይቻላል፡፡
5.4 የከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያዎች ከት/ቤት-ት/ቤት ዝውውር ከሰሩ በኋላ የሚከፈትን
ክፍት የሥራ መደብ 100% በዝውውር ያሟላሉ፡፡

4
የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 01/2015
5.5 የወረዳ ትም/ጽ/ቤቶች በክፍት የሥራ መደቦች የመምህራንን፣ እና የት/ቤት አመራሮች ዝውውርና
ቅጥር ሲፈጽሙ ለሚመለከታቸው ክፍሎች በደብዳቤ ሲያሳውቁ በቅጂ የክልሉ ትምህርት ቢሮ
እንዲያውቀው ያደርጋሉ፡፡
5.6 በአንድ ወረዳ ላይ ከሌላ ወረዳ የዝውውር ጥያቄ ሳይቀርብ ቢቀር በወረዳው ውስጥ ከት/ቤት ወደ
ት/ቤት ዝውውር ከተፈጸመ በኋላ በቀሪ ክፍት ቦታዎች ላይ የዲፕሎማ መምህራን ቅጥር መፈጸም
ይቻላል፡፡ የድግሪ መምህር ቅጥር ፍላጎት ካለ በክልሉ ትምህርት ቢሮ በኩል እንዲፈፀም መጠየቅ
ይገባል፡፡
5.7 በክልሉ ውስጥ ከወረዳ ወደ ወረዳ ፣ ከዞን ወደ ዞን ወይም ከሌላ ክልል ወደ ክልላችን በሚዛወሩ
መምህራን፣ እና የት/ቤት አመራሮች ምክንያት ሊያጋጥም በሚችለው የደመወዝ መብለጥና ማነስ
የሚፈጠሩ ችግሮችን ለማቃለል እንዲቻል የወረዳ ትም/ጽ/ቤቶች የደመወዝ በጀት ሲያስይዙ ይህን
በቅድሚያ ታሳቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
5.8 ይህ የዝውውር መመሪያ በሁሉም ትምህርት ቤቶች መኖሩ ይረጋገጣል፡፡

አንቀጽ 6. ዝውውርና ምደባ ከመፈፀሙ በፊት ትኩረት ሊሰጥባቸው የሚገቡ


ጉዳዮች፡
6.1 ተጨማሪ የሰው ሃይል ማስፈለጉና አላስፈላጊ ክምችት የማይፈጥር መሆኑን፣ በጀት
መኖሩን/መያዙን ማረጋገጥ፣
6.2 የዝውውር መጠየቂያ ፎርም ለሚመለከታቸው ሁሉ በወቅቱ እንዲደርስ መደረጉን ማረጋገጥ፣
6.3 ዝውውርን በአግባቡ ለመፈጸም መምህራን፣ እና የት/ቤት አመራሮች የዝውውር መጠየቂያ ቅጽ
በወቅቱ በየደረጃው ለሚገኙ አካላት መድረሱ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
6.4 የዝውውር ፍላጎት ማሳወቂያ ፎርሞች በአግባቡ እና በትክክል መሞላታቸውን ማረጋገጥ፣
6.5 መምህራን፣ ር/መምሀራን እና ሱፐርቫይዘሮች የዝውውር ፍላጎት ማሳወቂያ ቅጽ ለመሙላት እና
ከሚሰሩበት ትምህርት ቤት ወደ ሌላ ቦታ ለመዛወር በትምህርት ቤት ደረጃ የተከታታይ ሙያ
ማሻሻያ ስልጠና የተሳተፈ እና የተደራጀ ማህደረ-ተግባር ማደራጀቱ በትምህርት ቤቱ ር/መምህር እና
ሱፐርቫይዘር መረጋገጥ አለበት፡፡
6.6 መምህራንና የት/ቤት አመራሮች የዝውውር ፍላጎት ከት/ቤት-ት/ቤት አንድ ቅጽ፣ ከወረዳ-ወረዳ
አንድ ቅጽ፣ ከዞን-ዞን/ከተማ አስተዳደር/ልዩ ወረዳ አንድ ቅጽ፣ እንዲሁም ከክልል-ክልል/አ.አ/ድሬድዋ
አንድ ቅጽ እንዲሞሉ ይደረጋል፡፡ (አባሪ ቅጽ 01-1 እስከ ቅጽ 04-02)
6.7 የመምህራን፣ ር/መምህራን እና ሱፐርቫይዘሮች ዝውውር በተለያዬ ቅጽ መሞላት አለበት፡፡

5
የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 01/2015
6.8 አንድ መምህር፣ ወይም የት/ቤት አመራር በወረዳው/ከተማ አስተዳደሩ ከት/ቤት-ት/ቤት ዝውውር
ሲሞላ ባለበት ወረዳ/ከተማ አስ/ር ሶስት ት/ቤቶች፣ ከወረዳ-ወረዳ የዝውውር ፍላጎት ሲሞላ ባለበት
ዞን ካሉ እስከ ሶስት ወረዳዎች፣ ከዞን-ዞን የዝውውር ፎርም ሲሞላ ዝውውር ለጠየቀበት ዞን እስከ
ሶስት ወረዳዎች/ልዩ ወረዳ/ ከተማ አስተዳደር፣ ከክልል-ክልል የዝውውር ፍላጎት ሲሞላ እስከ ሶስት
ክልለሎች/ከተማ አስተዳደሮች አማራጭ ማቅረብ ይችላል፡፡ ውድድሩም እንደምርጫው ቅደም
ተከተል ይፈጸማል፡፡
6.9 አገልግሎት አሁን በሚሰራበትና ቀድሞ የሰራበት፣ የቅጥር ዘመን በቀን/ወር/ዓ.ም፣ የቦታ ስሌት፣
የትዳር ሁኔታ መረጃ፣ የዝውውር ምክንያት እና የአገልግሎት፣ የትዳር እና የሙያ ብቃት ነጥብ
በትክክል ካልተሞላ ዝውውሩ ፈጽሞ አይታይም፡፡
6.10 የዝውውር ፍላጎት ቅጽ ህጋዊ ውክልና ባለው አካል በፍትህ ወይም ትም/ጽ/ቤት በአካል
በመቅረብ በውክልና መስጫ ፎርም ላይ በመወከል ማስሞላት ይችላል፡፡
6.11 የዝውውር ፍላጎት መረጃ ወደ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ከመላኩ በፊት በትምህርት ቤቱ
ማስታወቂያ ሰሌዳ ቢያንስ ለሶስት የስራ ቀናት በግልጽ ተለጥፎ እንዲመለከቱት መደረግ አለበት፡፡

አንቀጽ 7. የወረዳዎችና ዞኖች የምድብ ክፍፍል


7.1 ወረዳዎችና የዞን ማዕከላት ከክልሉ ማዕከል ካላቸው ርቀት፣ የአየር ንብረት፣ ለኑሮ ምቹነት፣
የመገናኛና የመሠረተ ልማት አውታር አቅርቦት አንፃር ከዚህ በታች በምድብ ተከፍለዉ ተቀምጠዋል፡፡

ምድብ 1 ምድብ 2 ምድብ 3 ምድብ 4


 አሶሳ ከተማ  ሆሞሻ  ማኦ ኮሞ ልዩ  ኩርሙክ
አስተዳደር  መንጌ  ዳንጉር  ጉባ
 ከማሽ ከተማ  ኡንዱሉ ድባጤ  ዛይ
አስተዳደር  ማንዱራ  ቡለን  ሸርቆሌ
 ግ/በለስ ከተማ  አቡርሃሞ  ካማሽ  ሰዳል
አስተዳደር  ኡራ  ወምበራ  ዳምቤ
 ፓዌ  ባምባሲ ምዥጋ  ቢልድግሉ
 ባምባሲ ከተማ አስ/ር

አንቀጽ 8 የአገልግሎት ስሌት፡


8.1 አንድ መምህር፣ ር/መምህር ወይም ሱፐርቫይዘር ከሚሰራበት ት/ቤት ዝውውር ወደ ሚጠይቅበት
ት/ቤት፣ ወረዳ ወይም ዞን ለመዛወር ከሚሰራበት ቦታ በተሰጠው ነጥብ የአገልግሎት ዘመኑን በማባዛት
የአገልግሎት ነጥብ ያገኛል፡፡

6
የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 01/2015
ምድብ የማባዣ ስሌት
ምድብ 1 1.0
ምድብ 2 1.2
ምድብ 3 1.4
ምድብ 4 1.6

8.3 በዝውውር ፍላጎት መሙያ ቅጽ ላይ አሁን በሚሰራበት ቦታ ያለው አገልግሎት በቦታ ነጥብ
የሚባዛ ሲሆን ሌላው አገልግሎት በአንድ ነጥብ ይባዛል፡፡
8.4 ለባለትዳሮች የቦታ አገልግሎት የሚባዛው የሁለቱ ባለትዳሮች አገልግሎት ተደምሮ ለሁለት
ተካፍሎ የሚገኘው ነጥብ ይሆናል፡፡ ይህ ግን የሚፈፀመው የተናጠል ዝውውር የሚሰራለት
መምህር አገልግሎት ከትዳር አጋሩ ዝቅተኛ ከሆነ ብቻ ነው፡፡

7
የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 01/2015
ክፍል ሶስት
የዝውውርና ምደባ ዓይነቶችና መስፈርቶች
አንቀጽ 9. የዝውዉርና ምደባ መስፈርቶች
9.1 ዝውውር የሚፈፀመው በሚፈለገው የሰው ሃይል ብዛት፣ የትምህርት ዝግጅትና
የትምህርት ደረጃ መነሻነት ይሆናል፡፡
9.2 በውድድር ብቻ የሚፈፀሙ የዝውውር ዓይነቶች በአገልግሎት፣ በሙያ ብቃት፣ እና
በትዳር ናቸው፡፡
9.3 ያለውድድር በቀጥታ ዝውውር የሚፈፀምባቸው የዝውውር ዓይነቶች በመምህራን ማህበር
ተመራጭነት፣ እና በሹመት ብቻ ይሆናሉ፡፡
9.3 የጤና እና ሌሎች ህጋዊ አካል ባረጋገጠው ማህበራዊ ችግር ምክንያቶች የሚቀርቡ
የዝውውር ጥያቄዎች የዝውውር ኮሚቴ የቀረቡ ማስረጃዎችን በመገምገም በተቀመጠው ድርሻ
መሰረት ዝውውር የሚፈፀም ይሆናል፡፡
9.4 በሥራ አስፈላጊነት እና በዲሲፕሊን ውሳኔ ምክንያት በጊዜየዊነት ዝውውር ሊከናወን
ይችላል፡፡
9.5 በውድድር ለሚከናወን ዝውውር የማወዳደሪያ መስፈርቶች ክብደት 70 ነጥብ
ለአገልግሎት፣ 20 ነጥብ ለትዳር፣ 10 ነጥብ ለሙያ ብቃት ውጤት ይሆናል፡፡
9.6 በተ.ቁ 9.5 በተጠቀሱት መስፈርቶች ድምር ውጤት አንድ ወንድና አንዲት ሴት እኩል
ካመጡ ቅድሚያ ለሴት ይሰጣል፡፡
9.7 በተ.ቁ 9.5 በተጠቀሱት መስፈርቶች ድምር ውጤት ባለትዳርና ትዳር የሌለው እኩል
ካመጡ ቅድሚያ ለባለትዳሩ ይሰጣል፡፡

አንቀጽ 10. የዝዉዉርና ምደባ ዓይነቶችና አፈጻጸም


10.1 በአገልግሎት የሚፈፀም ዝውውር
10.1.1 አንድ መምህር ወይም የት/ቤት አመራር የዝውውር ፍላጎት መሙላት የሚችለው የአመቱ
መደበኛ ዝውውር እስከሚሰራበት ሰኔ 30 ድረስ ሁለት ዓመት እና ከዚያ በላይ የሚሆነው ከሆነ
ብቻ ይሆናል፡፡ ይህም የቦታ ነጥብን እና ከሌላ ቦታ የተገኘን የሥራ ልምድ አያካትትም፡፡

8
የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 01/2015
10.1.2 በአንቀጽ 10 ተ.ቁ 10.1.1 የተጠቀሰው እንዳለ ሆኖ የዝውውር አገልግሎት ከክልል-ክልል
5 ዓመታት፣ ለዞን-ዞን 3 ዓመታት፣ ከወረዳ-ወረዳ እና ከት/ቤት-ት/ቤት 2 ዓመታት ከተቀጠረበት
ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ድረስ መሙላት አለበት፡፡
10.1.3 የእያንዳንዱ ዓመት አገልግሎት የቦታ ነጥብን ጨምሮ በማባዣ ነጥብ 3 (ሶስት) ተባዝቶ
የሚገኘው ውጤት ከ70% ይያዛል፡፡
10.1.4 ዝውውር ጠያቂ መምህራንና የት/ቤት አመራሮች በሚሰሩበት ት/ቤት ወይም ወረዳ
በዝውውር ዓመቱ ሞልተው በሚልኩት የዝውውር ፍላጎት መሠረት ብቻ ይፈፀማል፡፡
10.1.5 አካባቢውን ለመልቀቅ የሚያስገድድ ችግር ካልተፈጠረ በስተቀር በግል ማመልከቻ ያለወቅቱ
የሚቀርብ የዝውውር ጥያቄ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
10.1.6 በወረዳ አዲስ መምህራን፣ እና የት/ቤት አመራሮች ተቀጥረው ምደባ ከመከናወኑ በፊት
በቅድሚያ የዝውውር ፎርም ሞልተው ለጠየቁት ነባር መምህራን እና የት/ቤት አመራሮች
ዝውውር እንዲፈፀም ይደረጋል፡፡
10.1.7 በተ.ቁ 10.1.6 የተጠቀሰው እንዳለ ሆኖ ዝውውር ከተሰራ በኋላ የሚቀጠሩ አዲስ
መምሀራን በጊዜያዊነት በተገኘው ክፍት ቦታ የሚመደቡ ይሆናል፡፡ በቀጣይ መደበኛ የዝውውር
ወቅት አገልገሎታቸው ተይዞላቸው በሚመጥናቸው ቦታ ተወዳድረው ይመደባሉ፡፡
10.1.8 በተ.ቁ 10.1.7 የተጠቀሰው ቢኖርም በተለያዬ ምክንያት ወረዳው መደበኛ ዝውውር ሳይሰራ
ቢቀር በቀጣይ የዝውውር ወቅት በሚመጥናቸው ቦታ ተወዳድረው ይመደባሉ፡፡
10.1.9 አመቻች መምህራን ወደ መደበኛ መምህርነት ከተሸጋገሩ በኋላ ከሌሎች መምህራን ጋር
ቀደም ሲል በአመቻችነት የሰጡት አገልግሎት ተይዞላቸውና ተወዳድረዉ ዝውውርና ምደባ
ይደረግላቸዋል፡፡
10.1.10 የሚያስተምሩበት ጣቢያ ወደ መደበኛ ትምህርት ቤት ከተለወጠና ሌሎች በአገልግሎት
የሚበልጡ ሆነው ዝውውር የሚጠይቁ መምህራን ከሌሉ በዚያው ት/ቤት ተመድበው እንዲቀጥሉ
ይደረጋል፡፡
10.1.11 ህጋዊ እውቅና ካላቸው የግል፣ የመንግስት እና/ወይም መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች
ውስጥ በመቀጠር በመደበኛ የስራ ሰዓት የተወሰነ ስራ በማከናወን፣ መደበኛ ደመወዝ
እየተከፈላቸው የሥራ ግብር እየተከፈለበት የተገኘ የአገልግሎት የስራ ልምድ ለዝውውር ውድድር
እኩል ያገለግላል፡፡
10.1.12 ከክልላችን ወደ ሌሎች ክልሎች ዝውውር ፍላጎት ያሳወቁ መምህራን መረጃ ለጠየቁባቸው
ሁሉም ክልሎች ይላካል፡፡ በዚሁ መሰረት ሌሎች ክልሎች ያለትክ/በትክ ለመውሰድ/ለመስጠት

9
የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 01/2015
የሚፈልጓቸውን መምህራንና የት/ቤት አመራሮች በመደበኛው የዝውውር ወቅት በቢሮው
ማረጋገጫ ሲሰጥ ብቻ የሚፈፀም ይሆናል፡፡
10.1.13 ሁለት መምህራን፣ ወይም የት/ቤት አመራሮች በአገልግሎት፣ በትምህርት ዓይነት፣
የትምህርት ዝግጅት ደረጃ ተመሳሳይ እና በደመወዝ ተቀራራቢ ሆነው በመደበኛ የዝውውር
ወቅት ታይቶ ማዛወር አሰቸጋሪ ሆኖ ሲገኝ ሁለቱ ለመቀያየር ጥያቄ ሲያቀርቡ እና የሚሰሩባቸው
ወረዳዎች ሲስማሙ ዝውውር መፈፀም ይቻላል፡፡
10.1.14 የት/ቤት አመራሮች ዝውውር የሚፈፀመው በአቻ ሙያና ደረጃ ር/መምህር ከር/መምህር፣
ም/ር/መምህር ከም/ር/መምህር፣ ሱፐርቫይዘር ከሱፐርቫይዘር ጋር በመወዳደር ይሆናል፡፡
10.1.15 ለት/ቤት አመራሮች በመምህርነት፣ ር/መምህርነት፣ ም/ር/መምህርነት እና በሱፐርቫይዘርነት
የተገኘ አገልግሎት እኩል ክብደት ይኖረዋል፡፡
10.1.16 በአንደኛ ደረጃ፣ በመካከለኛ ደረጃ እና በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በማገልገል የተገኘ ልምድ እኩል
ክብደት ይኖረዋል፡፡
10.1.17 አንድ የት/ቤት አመራር ሙያውን ወደ መምህርነት አዙሮ ለመዛወር ከፈለገ መደበኛ
ዝውውር ከመስሪያ ጊዜ አንድ ወር ቀድሞ ለሚመለከተው ክፍል በማሳወቅ ወደ መምህርነት ሙያ
ስለመዛወሩ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡

10.2 በትዳር ምክንያት የሚፈጸም ዝውውር፡


10.2.1 ባልና ሚስት የዝውውር ወይም የምደባ ጥያቄ ሲያቀርቡ ጋብቻ የመሰረቱ መሆኑን የሚያረጋግጥ
ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የአገልግሎት ነጥባቸውም የሚጠቅማቸው ከሆነ የሁለቱ
አገልግሎት ድምር ለሁለት ተካፍሎ የሚገኘው አማካይ ውጤት በ3 ተባዝቶ፣ 20 ነጥብ ተጨምሮ
ይወዳደራሉ፡፡
10.2.2 ባልና ሚስት መምህራን፣ ር/መምህራን ወይም ሱፐርቫይዘሮች የሆኑ ወይም ከሁለቱ አንዱ
መምህር፣ ር/መምህር ወይም ሱፐርቫይዘር ሌላው የትምህርት ባለሙያ/አመራር የሆነ ወይም
የሌላ መ/ቤት ባልደረባ ከሆኑ ያለ ልዩነት ዝውውሩ በተመሳሳይ የአገልግሎት ነጥብ አሰጣጥ
ይፈፀማል፡፡ ጠቅላላ ውጤታቸው እኩል ከሆነ ለትምህርት ባለሙያዎች/አመራሮች/ ቅድሚያ
ይሰጣል፡፡
10.2.3 በየትኛውም ደረጃ በመምህርነት፣ በር/መምህርነት ወይም በሱፐርቫይዘርነት እያገለገሉ ያሉ
ባልና ሚስት ዝውውር በተናጠል እንዲታይላቸዉ ችግራቸውን በአካል ቀርበው ፈቃደኛ
መሆናቸው ካልተረጋገጠ በስተቀር ዝውውር በተናጠል አይፈፀምም፣

10
የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 01/2015
10.2.4 ባል ወይም ሚስት አብረው ከሚሰሩበት ት/ቤት፣ ወረዳ ወይም ዞን አንዳቸው ወደ ሌላ ት/ቤት፣
ወረዳ ወይም ዞን ከተዛወሩና አብሮ ለመኖር ዝውውር ከጠየቁ ለጋብቻ በተሰጠው ነጥብ
ተወዳድረው መዛወር ካልቻሉ ፈቃደኝነታቸው ተጠይቆ ተቀራርበው ለመኖር ከሚያስችል ት/ቤት፣
ወረዳ ወይም ዞን እንዲዛወሩ ማድረግ ይቻላል፡፡
10.2.5 ባል ወይም ሚስት በዝውውር መጠየቂያ ቅጽ ላይ መረጃውን በትክክል መሙላት ይገባቸዋል፡፡
መረጃውን በትክክል ሳይሞሉ ቀርተው ዝውውሩ በተናጠል ከታየ በኃላ የሚቀርብ የዝውውር
ጥያቄ/ቅሬታ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
10.2.6 ባልና ሚስት አብረው ሲሰሩበት ከነበረው ት/ቤት፣ ወረዳ ወይም ዞን አንዱ ወገን በሹመት
ወይም በህዝብ ተመራጭነት ቢነሳ ከላይ በተቀመጠው ስሌት አብረው መዛወር ካልቻሉ
ተቀራርበው እየሰሩ ለመኖር ከሚያስችላቸው ት/ቤት፣ ወይም ወረዳ እንዲዛወሩ ይደረጋል፡፡
10.2.7 በተሿሚነት፣ በመምህራን ማህበር ወይም በህዝብ ተመራጭነት የተዛወሩ መምህራን፣
ር/መምህራን እና ሱፐርቫይዘሮች ከተመራጭነት ወይም ከተሿሚነት አገልግሎታቸውን አጠናቀው
ሲነሱ የወረዳ በወረዳው ማዕከል፣ የዞን በዞን ማዕከል ከተማ አስተዳደር እና ለክልል በክልል
ማዕከል ከተማ ባለ የመምህርነት ቦታ ይመደባሉ፡፡
10.3 . በሙያ ብቃት የሚደረግ ዝውውር፡
የሙያ ብቃት ምዘና ወስዶ ያለፈ እና ሰርተፊኬት ያቀረበ መምህር ወይም የት/ቤት
አመራር በአንቀጽ 9 ተ.ቁ 5 በተቀመጠው የዝውውር መስፈርት መሰረት 10 ነጥብ
ተጨምሮት ዝውውር እንዲሰራለት ይደረጋል፡፡
10.4 በጤና ምክንያት የሚደረግ ዝውውር፡
10.4.1 በጤና ችግር ምክንያት የሆስፒታል የቅርብ ክትትል እንደሚያስፈለገው በሀኪሞች ቦርድ

የተረጋገጠ ማስረጃ በማቅረብ ዝውውር ለጠየቁ የዝውውር ኮሚቴ ገምግሞ ለስድስት


ወራት ሲሰሩበት ለነበረው ወረዳ ቅርብ ሆስፒታል ወይም ጤና ጣቢያ ባለበት ቦታ
ዝውውር ሊሰራለት ይችላል፡፡
10.4.2 በተ.ቁ 10.4.1 የተጠቀሰው ቢኖርም በበጀት ዓመቱ ወደ አንድ ወረዳ/ከተማ አስተዳደር

በጤና ችግር ምክንያት የሚዛወሩ ከአጠቃላይ ወደ ወረዳው/ከተማ አስተዳደሩ ከሚዛወሩት


1/4ኛ መብለጥ የለበትም፡፡
10.4.3 በተ.ቁ 10.4.1 መሠረት ዝውውር የተፈጸመላቸው መምህራን፣ ርዕሳነ መምህራንና
ሱፐርቫይዘሮች በየ6 ወሩ የጤናቸውን ሁኔታ የሚገልጽ ማስረጃ ህመሙን ከሚከታተለው ሐኪም
ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

11
የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 01/2015
10.4.4 በጤና ችግር ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ ዝውውር ለሚጠይቁ የዘመኑ በጀት ወደ ተዛወሩበት ወረዳ
እንዲዛወርላቸው ይደረጋል፡፡ ሆኖም ህመሙ በቀላሉ የማይድን በመሆኑ፣ ወይም ለረዥም ጊዜ
የሐኪም ክትትል የሚያስፈልገው መሆኑ በሐኪሞች የተረጋገጠ ማስረጃ ከቀረበ በቋሚነት
እንዲዛወሩ ማድረግ ይቻላል፡፡
10.4.5 የመምህርነት ሙያ የሚጠይቀውን አካላዊና ውስጣዊ ብቃት በማሟላት አገልግሎት መስጠት
የማይችል መሆኑ በሐኪሞች ቦርድ ከተረጋገጠ በሲቪል ሰርቪስ ህግ መሰረት ቦርድ እንዲወጣ
ይደረጋል፡፡
10.5 በመምህራን ማህበር ተመራጭነት እና ተሿሚነት የሚሰራ ዝውውር
10.5.1 በየደረጃው ያለ የመምህራን ማህበር ተመራጭ፣ ወይም የተሿሚ የትዳር አጋር ዝውውር
የሚፈፀመው ካለውድድር ይሆናል፡፡
10.5.2 የወረዳ መምህራን ማህበር ተመራጮች በወረዳው ርዕሰ ከተማ ባሉት ት/ቤቶች፣ የከተማ
አስተዳደር መምህራን ማህበር ተመራጭ በከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ፣ የዞን
መምህራን ማህበር ተመራጮች በዞን ርዕሰ ከተማ፣ የክልሉ መምህራን ማህበር በክልሉ ርዕሰ
ከተማ እንዲመደቡ ይደረጋል፡፡ ሆኖም ያልተጠበቀ የመምህራን ክምችት የሚፈጥር ሆኖ ከተገኘ
ከሊቀመንበርና ፀሐፊ በስተቀር ሌሎቹ ለተወሰነ ጊዜ የሙያ ስራቸውን ለማከናወን
በሚያስችላቸዉ በወረዳው ከተማ /ከተማ አስተደር ዙሪያ ባሉ ት/ቤቶች ሊመደቡ ይችላሉ፡፡
10.5.3 የዞን ወይም የክልል መምህራን ማህበር ተመራጮች በተመረጡበት የበጀት ዘመን ይሰሩበት
ከነበረው /ከተመረጡበት/ ወረዳ/ከ/አስተዳደር ደመወዛቸው እንዲከፈል ይደረጋል፡፡ ከቀጣዩ የበጀት
ዘመን ጀምሮ የምርጫ ዘመኑ እስኪጠናቀቅ ድረስ ተመድበው በሚሰሩበት የከተማ አስተዳደር
ወይም ወረዳ ትም/ጽ/ቤት በጀት ተይዞ እንዲከፈል ይደረጋል፡፡

10.6 በስራ አስፈላጊነት እና ትምህርት ደረጃ ማሻሻል የሚደረግ ዝውውርና ምደባ፡


10.6.1 በመንግስት ወጪ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ መምህራን ሁለት የክረምት ኮርስ ካጠናቀቁበት
ጊዜ ጀምሮ በሚሰለጥኑበት የትምህርት አይነት እጥረት ካለ በሚመጥናቸው ደረጃ አስፈላጊ ሆኖ
ሲገኝ ሊመደቡ ይችላሉ፡፡ ለአንድ ት/ቤት ተወዳዳሪዎች ከአንድ በላይ ከሆኑ እጥረት በሚታይበት
የትምህርት አይነት እና ካላቸዉ አገልግሎት አንጻር ታይቶ ዝዉዉር ሊፈጸም ይችላል፡፡
10.6.2 በግላቸዉ ሁለት የክረምት ኮርስ ወይም በማታ፣ በቅዳሜና እሁድ ፕሮግራም የትምህርት
ደረጃቸዉን ለማሻሻል ሶስት ዓመትና ከዚያ በላይ በመማር ላይ የሚገኙ መምህራን በሚከታተሉት
የትምህርት አይነትና ደረጃ እጥረት ባለበት ቦታ ተዛዉረዉ ሊመደቡ ይችላሉ፡፡

12
የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 01/2015
10.6.3 ለ2ኛ ደረጃ መምህርነት የሚያበቃውን በዲግሪ/2ኛ ዲግሪ/ የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ በመንግስት
ወጭ የተከታተሉና ያጠናቀቁ ወይም በመከታተል ላይ ያሉ መምህራን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ባሉበት ቦታ
በማወዳደር ተዛውረው እንዲሰሩ ማድረግ ይቻላል፡፡
10.6.4 በአንድ ት/ቤት ለአንድ መምህር በሳምንት ከ20-30 ክፍለ ጊዜ ታሳቢ በማድረግ ከፍተኛ
የመምህር ክምችት ካለበት ት/ቤት ከአንድ ዓመት ለማይበልጥ ጊዜ ለስራ አስፈላጊነት አዛውሮ
ማሰራት ይቻላል፡፡ ዝውውሩ የሚሰራው ወደ ተሻለ ምድብ ከሆነ የተሻለ አገልግሎት ያለው ሲሆን
ካለበት ቦታ ወደ ዝቅተኛ ምድብ ዝውውር የሚሰራ ከሆነ ዝቅተኛ አገልግሎት ያለው እንዲዛወር
ይደረጋል፡፡
10.6.5 በፌደራል መንግስት ወጪ በክረምት ተከታታይ ወይም በማታ፣ በቅዳሜና እሁድ ኘሮግራም
ትምህርት በመጀመራቸው ምክንያት መምህራን ወደ ሌላ ክልል፣ ዞን፣ ወረዳ ወይም ት/ቤት
ለመዛወር አይታገዱም፡፡ ሆኖም በክልል መንግስት ወጪ ትምህርት የጀመሩ ከሆነ በገቡት ውል
መሰረት ግዴታቸውን ሲወጡ ብቻ ከክልል-ክልል ዝውውር ይታይላቸዋል፡፡
10.6.6 የአማራጭ መሰረታዊ ትምህርት አመቻቾች በኮሌጅ ደረጃ የሚሰጠውን የክረምት ወይም የማታ፣
ቅዳሜና እሁድ ትምህርት በዲፕሎማ ደረጃ ሲያጠናቅቁ በመደበኛ መምህርነት ዝውውር
ይታይላቸዋል፡፡

13
የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 01/2015
ክፍል አራት፡
የዝውውር ፍላጎት ማሳወቂያ፣ መስሪያ እና ቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ
አንቀጽ 11 የዝውውር ፍላጎት ማሳወቂያ ጊዜ
11.1 ከጥር 1-15 በት/ቤት ደረጃ የዝውውር መጠየቂያ ቅጽ በመምህራን፣ ርዕሳነ መምህራንና
ሱፐርቫይዘሮች ይሞላል፡፡
11.2 እስከ ጥር 30 በት/ቤት ደረጃ የዝውውር መሙያ ቅጽ ተጠናቅሮና ተረጋግጦ ለወረዳ/ ከተማ
አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት በሀርድ ኮፒ ይላካል፡፡
11.3 ከጥር 21-30 የወረዳ/ከተማ አስተዳደር ትም/ጽ/ቤት ከትምህርት ቤቶች የተላከውን የዝውውር
ፍላጎት መረጃ ያደራጃል፡፡
11.4 ከየካቲት 1-15 የወረዳ/ከተማ አስተዳደር ትም/ጽ/ቤት የዝውውር ፍላጎቱን መረጃ በማደራጀት
በሀርድና በሶፍት የወረዳ-ወረዳ ዝውውር ፍላጎት ለዞን ትም/መምሪያ፣ የክልል-ክልል፣ ዞን-ዞን/ከተማ
አስተዳደር/ልዩ ወረዳ ዝውውር ፍላጎት ለክልል ትምህርት ቢሮ በማጠናቀርና በማረጋገጥ በሀርድ እና
ሶፍት ኮፒ ይልካል፡፡ ወረዳ ትም/ጽ/ቤቶች በዝውውር ለመቀበል ያላቸውን ፍላጎትና ሌሎች አስፈላጊ
መረጃዎች በዚሁ ወቅት ይልካሉ፡፡
11.5 ከግንቦት 25-30 የክልል ትምህርት ቢሮ የክልል-ክልል ዝውውር ፍላጎት መረጃ ዝውውር
ለተሞላባቸው ክልሎች/የፌደራል ከተማ አስተዳደሮች ይልካል፡፡
11.6 በተ.ቁ 13.4 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በክልሉ ባሉ የከተማ አስተዳደሮች ክፍት የስራ መደቦች
የሚያሟሉት በዝውውር ብቻ በመሆኑ በዝውውር መቀበል የሚፈልጉትን መምህር ወይም የት/ቤት
አመራር በየሩብ ዓመቱ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አንቀጽ 12 የዝውውር መስሪያ ጊዜ


12.1 ከሰኔ 01-15 ትምህርት ቢሮ የክልል-ክልል፣ ዞን-ዞን/ከተማ አስተዳደር/ልዩ ወረዳ ዝውውር በመስራት
በየደረጃው ማሳወቅ አለበት፡፡
12.2 ከሰኔ 20-30 የዞን ትምህርት መምሪያ ወረዳዎች በዝውውር ለማሟላት በጠየቋቸው ቦታዎች እና
በለውጥ ዝውውር የወረዳ-ወረዳ የት/ቤት አመራሮች ዝውውር በመስራት ለወረዳ ትም/ጽ/ቤቶች
ማሳወቅ አለበት፡፡
12.3 ከሐምሌ 1-10 የወረዳ ትም/ጽ/ቤት ከት/ቤቶች የተላኩለትን ዝውውር በመስራት ይፋ ማድረግ
አለበት፡፡

14
የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 01/2015
12.4 በክልሉ ያሉ የከተማ አስተዳደሮች የተፈጠረውን ክፍት የስራ መደብ ለማሟላት በሩብ ዓመት አንድ
ጊዜ እንደጠየቁ ዝውውር ይሰራላቸዋል፡፡
12.5 የት/ቤት አመራሮች ዝውውር በመደበኛ የዝውውር ወቅት ወይም ክፍት ቦታ ከተገኘ በዓመቱ
አጋማሽ ሊሰራ ይችላል፡፡
12.6 ት/ቤቶች ለተዛወሩ መምህራን እና የት/ቤት አመራሮች ዝውውር የተሰራላቸው መሆኑ ሲገለጽላቸው
የተሟላ ክሊራንስ፣ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ የተሰጣቸው/ያልተሰጣቸው መሆኑን በመግለጽና
በሙያ ማሻሻያ የሰሩትን ስራዎችን በማካተት መሸኛ በመስጠት ለወረዳ/ከተማ አስተዳደር
ትም/መምሪያዎች ይልካሉ፡፡
12.7 እስከ ሐምሌ 20 የወረዳ ትም/ጽ/ቤት የወረዳ-ወረዳ፣ የዞን-ዞን እና የክልል-ክልል ዝውውር ላገኙ
መምህራን፣ ርዕሳነ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የተሟላ መሸኛ በመስጠት ይሸኛል፡፡

አንቀጽ 13 ቅሬታ ስለማቅረብ


13.1 በየደረጃው ዝውውር የሰራ አካል የተሰራውን ዝውውር በማስታወቂያ ይገልጻል፡፡
13.2 በተሰራው ዝውውር ቅሬታ ያለው ማስታወቂያው ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በአምስት የሥራ ቀናት
ውስጥ በጽሑፍ ማቅረብ አለበት፡፡
13.3 በአፈፃፀም ላይ ቅሬታ ያለው በቅድሚያ ዝውውር ለሰራዉ አካል ከዚያም ዝውወሩን በሰራው ተቋም
ውስጥ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ በጽሑፍ ያቀርባል፡፡
13.4 ዝውውሩን የሰራ አካል የቀረበውን ቅሬታ ከሶስት ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ምላሹን በማስታወቂያ
መግለጽ አለበት፡፡
13.5 በዚህ ያልረካ አንድ ደረጃ ከፍ ብሎ ላለዉ የትምህርት መዋቅር አቤቱታውን የማቅረብ መብት
አለዉ፡፡ ይህም አቤቱታ የቅሬታው ምላሽ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሶስት የስራ ቀናት ይሆናል፡፡
ቅሬታን እስከ አስተዳደር ፍ/ቤት እና መደበኛ ፍርድ ቤት መጠየቅ ይቻላል፡፡
13.6 ቅሬታ የሚቀርበው መደበኛ ሥራን እያከናወኑ መሆን አለበት፡፡

15
የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 01/2015
ክፍል አምስት
በየደረጃው የሚገኙ ፈፃሚ አካላት ተግባርና ኃላፊነት
አንቀጽ 14 የክልል ትምህርት ቢሮ ተግባርና ኃላፊነት
14.1 የዝውውርና ምደባ አፈፃፀም መመሪያ በማዘጋጀት ያፀድቃል፣ ያሻሽላል፣ ስለመመሪያው አፈፃፀም
ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፣ መመሪያዉ በአግባቡ ሥራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣
14.2 የዝውውር መመሪያውን ለሚመለከታቸው አካላት ያስተዋውቃል፡፡ ለመምህራንና የት/ቤት
አመራሮች ተደራሽ የሚሆንበትን ስልት ይቀይሳል፡፡
14.3 የየዘመኑን የዝውውር ማስፈፀሚያ እቅድ ያዘጋጃል፤ ሲፀድቅለትም ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
14.4 የዞን-ዞን/ከተማ አስተዳደሮች/ልዩ ወረዳ፣ የክልል ክልልና ተጠሪነታቸዉ ለፌዴራል መንግስት
የሆኑትን የከተማ አስተዳደሮች ዝውውር ይፈጽማል፣ ዝውውር ያገኙትን መምህራን እና የት/ቤት
አመራሮች ዝርዝር ለወረዳ ትም/ጽ/ቤቶች፣ ለዞን ትምህርት መምሪያዎች፣ ለከተማ አስተዳደር
ትምህርት መምሪያዎች፣ ለልዩ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ያሳውቃል፡፡
14.5 የዞን-ዞን ወይም ከተማ አስተዳደር/ልዩ ወረዳ የመምህራንና የት/ቤት አመራሮች ዝውውር
ለማቀላጠፍ እና በተሻለ ለማከናወን ከዞን/ከተማ አስተዳደር/ልዩ ወረዳ የመ/ራን/ትም/አመራር
ባለሙያዎች እና የሙያ ማህበር ተወካዮችን ሊጠቀም ይችላል፡፡
14.6 የመምህራን፣ ርዕሳነ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች ዝውውር በየደረጃው በተቀላጠፈ ሁኔታ
ለመፈፀም እንዲቻል የመረጃ ልውውጥ የሚጠናከርበትን መንገድ ያመቻቻል፣
14.7 በዝውውር ምክንያት የሚቀርብ ቅሬታን በወቅቱ ያስተናግዳል፣ ምላሽ ይሰጣል፡፡

አንቀጽ 15. የዞን ትምህርት መምሪያ ተግባርና ኃላፊነት፡


15.1. የመምህራን፣ ርዕሳነ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮችን የወረዳ-ወረዳ ዝውውር ለመስራት የድርጊት
መርሃ ግብር ያዘጋጃል፣ አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ ይሰጣል፡፡
15.2. በዝውውር መጠያቂያ ቅጽ መሰረት መረጃ መጠናቀሩን ያረጋግጣል፡፡
15.3. የወረዳ-ወረዳ ዝውውርን ያከናውናል፣ በየደረጃው ዝውውር ያገኙትን መምህራንና የት/ቤት
አመራሮች ዝርዝር ለወረዳ ትም/ጽ/ቤት ያሳውቃል፡፡
15.4. የወረዳ-ወረዳ የመምህራንና የት/ቤት አመራሮች ዝውውር ለማቀላጠፍ እና በተሻለ ለማከናወን
ከወረዳ የመ/ራን/ትም/አመራር ባለሙያዎች እና የሙያ ማህበር ተወካዮችን ሊጠቀም ይችላል፡፡
15.5. በዝውውር ምክንያት የሚቀርብ ቅሬታን በወቅቱ ያስተናግዳል፣ ምላሽ ይሰጣል፡፡

16
የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 01/2015
አንቀጽ 16. የወረዳ/ከተማ አስተዳደሮች/ልዩ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ተግባርና
ኃላፊነት፡
16.1 መመሪያውን ያስተዋውቃል፤የክልሉን መመሪያ በማይጥስ መልኩ ወረዳዊ የዝውውር መመሪያ
ያዘጋጃል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
16.2 በመመሪያው ውስጥ በተቀመጠው 7ዐ በ 3ዐ የዝውውርና የቅጥር ጥምርታ ስሌት መሠረት የሰዉ
ኃይል ፍላጎታቸዉን ለዞን ትምህርት መምሪያ ያሳዉቃሉ፡፡
16.3 በክልሉ ትምህርት ቢሮ የተዘጋጀውን የዝውውር ቅጽ በማባዛት ለየት/ቤቶች ያሰራጫል፣ ግንዛቤ
እንዲያዝበት ያደርጋል፡፡
16.4 የወረዳ ወረዳ የዝውውር ፍላጎት አጠናቅሮ ለዞን ትምህርት መምሪያ ከዚህ መመሪያ ጋር በተያያዘው
ቅጽ በ/HARD COPY & SOFT COPY/ይልካል፡፡
16.5 የዞን ዞን፣ የከተማ አስተዳደሮችን፣ የክልል ክልልና ተጠሪነታቸዉ ለፌዴራል መንግስት የሆኑትን
የከተማ አስተዳደሮችን የዝውውር ፍላጎት አጠናቅሮ ለክልል ትምህርት ቢሮ ከዚህ መመሪያ ጋር
በተያያዘው ቅጽ በ/HARD COPY & SOFT COPY/ይልካል፡፡
16.6 በዝውውር ከወረዳው/ከተማ አስተዳደሩ በተነሱ መምህራን ትክ የሚላኩለትን መምህራን በትምህርት
ዓይነት ለዞን/ለክልል ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡
16.7 በየደረጃው ለተዛወሩ መምህራን፣ ርዕሳነ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች ዝውውራቸውን ያሳውቃል፣
ለተዛወሩትም የተሟላ መሸኛ በመስጠት ይልካል፡፡ዝውውር ያገኙትን መምህራን፣ ርዕሳነ መምህራንና
ሱፐርቫይዘሮች ዝርዝር በማስታወቂያ ሰሌዳ ከ5 ቀናት ላላነሰ ጊዜ በመለጠፍ ያሳዉቃል፡፡
16.8 በዝውውር ምክንያት የሚቀርብ ቅሬታን በወቅቱ ያስተናግዳል፣ ምላሽ ይሰጣል፣ አስፈላጊውን
ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፡፡

አንቀጽ 17. የት/ቤት ተግባርና ኃላፊነት


17.1 በት/ቤት ደረጃ ስለመመሪያው ግንዛቤ ለመምህራን ግንዛቤ ይፈጥራል፡፡ መመሪያውን ተግባራዊ
ያደርጋል፡፡
17.2 በተዘጋጀው የዝውውር ቅጽ መሰረት የመምህራን እና የት/ቤት አመራሮች የዝውውር ቅጹን
በተቀመጠው የጊዜ ገደብ በትክክል ሞልተው እንዲያጠናቅቁ ያደርጋል፡፡
17.3 መምህራንና የት/ቤት አመራሮች የሞሉት የዝውውር ፍላጎት መጠየቂያ ቅጽ የተሞላው መረጃ
ትክክለኛነት ያረጋግጣል፡፡
17.4 በዝውውር መጠያቂያ ቅጽ መሰረት የመምህራን እና የት/ቤት አመራሮች ዝውውር በማስሞላትና
መረጃውን በማጠናቀር በHARD COPY ለትምህርት ጽ/ቤት ይልካል፡፡

17
የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 01/2015
17.5 የተዛወሩ መምህራን፣ ር/መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች በተከታታይ የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና የሰሩትን
ስራዎች በፖርትፎልዮ በማስደገፍ፣ ሶስት የቅርብ ሥራ አፈፃፀም ግምገማ ውጤት በማካተትና
የተሟላ መሸኛ በመስጠት ለወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ይልካል፡፡

አንቀጽ 18. በየደረጃው የመምህራን ማህበር ተሳትፎ


18.1 በየደረጃው በሚካሄደው የመምህራን፣ የርዕሳነ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች ዝውውርና ምደባ ሁለት
የመምህራን ማህበር ተወካዮች ይሳተፋሉ፡፡
18.2 ዝውውርና ምደባን በተመለከተ ለሚቀርብ ቅሬታ በየደረጃው ከሚገኝ የትምህርት መዋቅር ጋር
በመቀናጀት ወቅታዊ ምላሽ ያሰጣል፡፡

አንቀጽ 19. የዝውውር እና ምደባ ኮሜቴ አባላት


በክልል ትምህርት ቢሮ
 የመ/ንና ትም/አመ/ር ልማት ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር (ተወካይ) …. ሰብሳቢ
 የክልል መም/ማህበር ፕረዝዳንት -------------------------------- ጸሀፊ
 የክልል መም/ማህበር ም/ፕረዝዳንት --------------------------------አባል
 የመ/ንና ትም/አመ/ር ልማት ዳሬክቶሬት ባለሙዎች (4) --- አባል
 የዞን/ከተማ አስተዳደር ትም/መምሪያ የመ/ራንና ትም/አመራር ልማት ባለሙያዎች
(እንደአስፈላጊነቱ)
በዞን ትምህርት መምሪያ
 የዞን የመ/ንና ትም/አመ/ር ልማት ባለሙያ --- ሰብሳቢ
 የዞን መም/ማህበር ሊቀ-መንበር -------------------- ጸሀፊ
 የዞን መም/ማህበር የሴቶች ተጠሪ -------------------- አባል
 የወረዳ ትም/ጽ/ቤት የመ/ራንና ትም/አመራር ልማት ባለሙያዎች (እንደአስፈላጊነቱ)
በወረዳ/ከተማ አስ/ር ትምህርት ጽ/ቤት
 የወረዳ የመ/ንና ትም/አመ/ር ልማት ቡድን መሪ --- ሰብሳቢ
 የወረዳ መም/ማህበር ሊቀ-መንበር ----------------------- ጸሀፊ
 የወረዳ የመ/ንና ትም/አመ/ል ባለሙያ/ዎች (2/1) --- አባል
 የወረዳ መም/ማህበር የሴቶች ተጠሪ --------------------- አባል

አንቀጽ 20. ልዩ ልዩ ሁኔታዎች


20.1 ከመምህራን እና የት/ቤት አመራሮች የቀረበዉ የዝዉዉር ጥያቄ የሚያገለግለው ለአንድ የትምህርት
ዘመን ብቻ ነው፡፡

18
የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 01/2015
20.2 ዝውውር ከተፈፀመ በኋላ እንዲሰረዝ የማቅረብ ጥያቄ ተቀባይነት የለውም፡፡ ሆኖም ዝውውር
ከመፈፀሙ በፊት የዝውውር ጥያቄ ለመሰረዝ የሚያስችል በቂ ምክንያት ካለ የዝውውር ጥያቄ
ለቀረበለት ክልል፣ ዞን ከተማ አስተዳር ወይም ወረዳ ከዞን ትምህርት መምሪያ ወይም ከወረዳ
ትምህርት ጽ/ቤት በደብዳቤ ከተገለፀና ዝውውር ከመሰራቱ አንድ ቀን ቀድሞ ከደረሰ፣ በትክ ዝውውር
የተሰራለት መምህር፣ ወይም የት/ቤት አመራር ከቀረ፣ ወይም ወረዳው ሁለቱንም ተቀብሎ
ለማስተናገድ ፈቃደኛ ከሆነ የዝውውር ጥያቄዉ ሊሰረዝ ይችላል፡፡
20.3 ከሌላ ክልል፣ ዞን እና ወረዳ በዝውውር የመጡ መምህራን፣ ወይም የት/ቤት አመራሮች ከሌሎች
ዝውውር ጠያቂዎች ጋር ልዩነት ሳይኖር ዝውውር ይሰራላቸዋል፡፡
20.4 ክልል/ወረዳ/ከተማ አስተዳደር ትም/ጽ/ቤቶች በአደጋ ጊዜ መምህራንና የት/ቤት አመራሮች ህዝብ
በሰፈረበት አካባቢ ወይም የተሻለ ደህንነት ባለበት ቦታ በጊዜያዊነት አዛውሮ ማሰራት ይችላል፡፡
20.5 በትምህርት ዓይነት ዝግጅትና ደረጃ ተመሳሳይነት ያላቸው ሁለት መ/ራን ወይም የት/ቤት
አመራሮች በአገልግሎት ነጥብ እኩል ነጥብ ካመጡ በዕጣ ይለያሉ፡፡
20.6 ሁለት ባለትዳር መምህራን ወይም የት/ቤት አመራሮች በጥቅል ነጥብ እኩል ካመጡ በዕጣ
ይለያሉ፡፡
20.7 አንድ መምህር/የትምህርት ቤት አመራር ከሌላ ባለትዳር መምህር/ትምህርት ቤት አመራር በጥቅል
ነጥብ እኩል ነጥብ ካመጡ ለባለትዳሩ ዕድሉ ይሰጣል፡፡
20.8 ወንድ እና ሴት መምህር/ትምህርት ቤት አመራር በጥቅል ነጥብ እኩል ነጥብ ካመጡ ለሴቷ ዕድሉ
ይሰጣል፡፡
20.9 በተመሳሳይ የትምህርት ደረጃ በሁለት የተለያየ ት/ቤት ደረጃ ሲያስተምሩ የነበሩ ተወዳዳሪዎች
በጠቅላላ ነጥብ እኩል ሲያመጡ በከፍተኛው ደረጃ ሲያስተምር ለነበረው ቅድሚያ ይሰጣል፡፡
20.10 አካል ጉዳተኛ መምህር/የትምህርት ቤት አመራር ከሌላ መምህር/የትምህርት ቤት አመራር
በጠቅላላ ነጥብ እኩል ካመጣ ለአካል ጉዳተኛ ቅድሚያ ይሰጣል፡፡

አንቀጽ 21. ተጠያቂነት፡


21.1 በዚህ መመሪያ ዉስጥ ከተገለፀው አግባብ ውጪ ዝውውር መፈጸምና እንዲፈጸም ማድረግ
አይቻልም፡፡
21.2 ይህ መመሪያ የሚያዘውን የዝውውር አፈፃፀም ሂደት ወደ ጐን በመተው የሚፈጸም ዝዉዉር በህግ
የሚያስጠይቅ ይሆናል፡፡
21.3 የሐሰት መረጃ የሞላ መምህር/የት/ቤት አመራር የተሰራለት ዝውውር ተሰርዞ በዲሲፕሊን
የሚጠየቅ ይሆናል፡፡

19
የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 01/2015
አንቀጽ 22. መመሪያውን ስለማሻሻል፡
ይህን መመሪያ የማሻሻል ስልጣን ያለዉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ትምህርት
ቢሮ ነዉ፡፡

አንቀጽ 23. የተሻሩ መመሪያዎች፡


የተሻሻለው የመምህራን፣ ርዕሳነ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የዝውውር አፈጻጸም መመሪያ
ቁጥር 03/2011 በዚህ መመሪያ ተተክቷል፡፡

አንቀጽ 24. የመመሪያው ተፈፃሚነት ወሰን


ይህ መመሪያ በክልሉ በሚገኙ ቅድመ አንደኛ፣ አማራጭ መሠረታዊ ትምህርት ጣቢያዎች፣
በአንደኛ ፣ መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በሚገኙ መምህራን እና የት/ቤት አመራሮች
ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

አንቀጽ 25. መመሪያው ስለሚፀናበት ጊዜ፡


ይህ መመሪያ ከየካቲት 21/2015 ዓ.ም ጀምሮ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

ቢኒያም መንገሻ
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ

20
የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 01/2015
አባሪ፡ የዝውውር ፍላጎት መሙያ ቅጻ ቅጾች:- ከት/ቤት - ት/ቤት የመምህራን ዝውውር መጠየቂያ ቅጽ (ቅጽ ዐ1-1)

ወረዳ-----------------------ት/ቤት---------------------------
መምህሩ/ሯ ዝውውር የጠየቁበት
አገልግሎት (1) ባለትዳር ከሆኑ ጠ/ድምር
ባለቤታቸው (2) ት/ቤት

የባልና ሚስት አገልግሎት አማካይ

የአገልግሎት (ሰ) 70%=መ*3 ወይም

ድምር 100% =መ+ሰ+ቀ ወይም


የቅጥር ዘመን (ቀ/ወ/ዓ)

ተባዝቶ የተገኘ ውጤት (ለ=ሀ*የቦታ


አገልግሎት ከቦታ ነጥብ ጋር

የብቃት ምዘና 10%=10


ረ=(መ+ሠ)/2
የተመረቀበ ዝ/የጠ/በ
ተ የዝውውር

ደመወዝ

የትዳር (ቀ)20%=20
የትም/ደ ት ት ፊር

ድምር (መ=ለ+ሐ)
. ጠያቂው ሙሉ ፆታ
ረጃ ትምህርት አሁን በሌላ የሚሰሩ ያላቸው ምክንያ ማ

=ረ+ሰ+ቀ
ቁ ስም
አይነት ባለበት ት/ቤ በት አገልግ ት

ነጥብ)

ረ*3
1ኛ 2ኛ 3ኛ
ት/ቤት ት ተቋምና ሎት
(ሀ) (ሐ) ቦታ (ሠ)

መረጃዉን ያጠናቀረዉ ተጠሪ መረጃዉን ያረጋገጠዉ

ስም-------------------ፊርማ-------------ቀን----------- ስም------------------ ፊርማ--------- ቀን---------


ማህተም

21
የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 01/2015
ከት/ቤት - ት/ቤት የር/መምህራን፣ ም/ር/መምህራን ዝውውር መጠየቂያ ቅጽ (ቅጽ ዐ1-2)
ወረዳ-----------------------ት/ቤት---------------------------
የር/መምህሩ/ሯ ዝውውር የጠየቁበት

የባልና ሚስት አገልግሎት አማካይ


አገልግሎት (1) ባለትዳር ከሆኑ ጠ/ድምር
ባለቤታቸው (2) ት/ቤት

የቅጥር ዘመን (ቀ/ወ/ዓ)

አገልግሎት ከቦታ ነጥብ ጋር

ድምር 100% =መ+ሰ+ቀ


የብቃት ምዘና 10%=10
ረ=(መ+ሠ)/2

70%=መ*3 ወይም ረ*3


የተገኘ ውጤት (ለ=ሀ*)
ተ የዝውውር ዝ/የጠ/በ

ደመወዝ

የትዳር (ቀ)20%=20
ፆ የትም/ የተመረቀበት

ወይም =ረ+ሰ+ቀ
ድምር (መ=ለ+ሐ)

የአገልግሎት (ሰ)
. ጠያቂው ያላቸ ት ፊርማ
ታ ደረጃ ትምህርት አይነት አሁን በሌላ
ቁ ሙሉ ስም የሚሰሩበት ው ምክንያት

ተባዝቶ
ባለበት ት/ቤ
ተቋምና አገልግ 1ኛ 2ኛ 3ኛ
ት/ቤት ት
ቦታ ሎት
(ሀ) (ሐ)
(ሠ)

መረጃዉን ያጠናቀረዉ ተጠሪ መረጃዉን ያረጋገጠዉ

ስም-------------------------ፊርማ-------------ቀን----------- ስም------------------ ፊርማ--------- ቀን---------


ማህተም

22
የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 01/2015
ከጉድኝት ማዕከል - ጉድኝት ማዕከል የሱፐርቫይዘሮች ዝውውር መጠየቂያ ቅጽ (ቅጽ ዐ1-3)
ወረዳ-----------------------ት/ቤት---------------------------
ዝውውር የጠየቁበት
ሱፐርቫይዘሩ ባለትዳር

የባልና ሚስት አገልግሎት አማካይ


አገልግሎት (1) ጠ/ድምር
ከሆኑ ባለቤታቸው (2) ጉድኝት ማዕከል

የቅጥር ዘመን (ቀ/ወ/ዓ)

አገልግሎት ከቦታ ነጥብ ጋር

ድምር 100% =መ+ሰ+ቀ


የብቃት ምዘና 10%=10
ረ=(መ+ሠ)/2
ዝ/የጠ/

70%=መ*3 ወይም ረ*3


የተገኘ ውጤት (ለ=ሀ*)
የዝውውር

ደመወዝ

የትዳር (ቀ)20%=20
የትም/ደ የተመረቀበት በት ፊር

ወይም =ረ+ሰ+ቀ
ድምር (መ=ለ+ሐ)

የአገልግሎት (ሰ)
ተ.ቁ ጠያቂው ሙሉ ፆታ
ረጃ ትምህርት አይነት አሁን ምክንያ ማ
ስም በሌላ የሚሰሩበት ያላቸው

ተባዝቶ
ባለበት 3 ት
ት/ቤት ተቋምና አገልግሎ 1ኛ 2ኛ
ት/ቤት ኛ
(ሐ) ቦታ ት (ሠ)
(ሀ)

መረጃዉን ያጠናቀረዉ ተጠሪ መረጃዉን ያረጋገጠዉ

ስም--------------------ፊርማ-------------ቀን----------- ስም------------------ ፊርማ--------- ቀን---------


ማህተም

23
የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 01/2015
ከወረዳ - ወረዳ የመምህራን ዝውውር መጠየቂያ ቅጽ (ቅጽ ዐ2-1)
ወረዳ----------------------
ዝውውር
መምህሩ/ሯ ባለትዳር የጠየቁበት

የባልና ሚስት አገልግሎት አማካይ


አገልግሎት (1) ጠ/ድምር
ከሆኑ ባለቤታቸው (2)
ወረዳ

የቅጥር ዘመን (ቀ/ወ/ዓ)

አገልግሎት ከቦታ ነጥብ ጋር

ድምር 100% =መ+ሰ+ቀ


ረ=(መ+ሠ)/2

የብቃት ምዘና 10%=10


70%=መ*3 ወይም ረ*3
ተ የዝውውር ዝ/የጠ/በ

የተገኘ ውጤት (ለ=ሀ*)


ደመወዝ
የተመረቀበት ፊር

የትዳር (ቀ)20%=20

ወይም =ረ+ሰ+ቀ
ድምር (መ=ለ+ሐ)
. ጠያቂው ሙሉ ፆታ የትም/ደረጃ ት

የአገልግሎት (ሰ)
ትምህርት አይነት አሁን ማ
ቁ ስም በሌላ የሚሰሩበት ያላቸው ምክንያት

ተባዝቶ
ባለበት
ት/ቤት ተቋምና አገልግሎት 1ኛ 2ኛ 3ኛ
ወረዳ
(ሐ) ቦታ (ሠ)
(ሀ)

መረጃዉን ያጠናቀረዉ ተጠሪ መረጃዉን ያረጋገጠዉ

ስም----------------------ፊርማ-------------ቀን----------- ስም------------------ ፊርማ--------- ቀን---------


ማህተም

24
የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 01/2015
ከወረዳ - ወረዳ የር/መምህራን፣ ም/ር/መምህራን ዝውውር መጠየቂያ ቅጽ (ቅጽ ዐ2-2)
ወረዳ-----------------------
ዝውውር የጠየቁበት
ር/መምህሩ/ሯ ባለትዳር

የባልና ሚስት አገልግሎት አማካይ


አገልግሎት (1) ጠ/ድምር
ከሆኑ ባለቤታቸው (2) ወረዳ

የቅጥር ዘመን (ቀ/ወ/ዓ)

አገልግሎት ከቦታ ነጥብ ጋር

ድምር 100% =መ+ሰ+ቀ


የብቃት ምዘና 10%=10
ረ=(መ+ሠ)/2
ዝ/የጠ/

70%=መ*3 ወይም ረ*3


የተገኘ ውጤት (ለ=ሀ*)
ተ የዝውውር

ደመወዝ

የትዳር (ቀ)20%=20
የትም/ደ የተመረቀበት በት

ወይም =ረ+ሰ+ቀ
ድምር (መ=ለ+ሐ)

የአገልግሎት (ሰ)
. ጠያቂው ሙሉ ፆታ ፊርማ
ረጃ ትምህርት አይነት አሁን ምክንያ
ቁ ስም በሌላ የሚሰሩበት ያላቸው

ተባዝቶ
ባለበት ት
ት/ቤት ተቋምና አገልግሎት 1ኛ 2ኛ 3ኛ
ወረዳ
(ሐ) ቦታ (ሠ)
(ሀ)

መረጃዉን ያጠናቀረዉ ተጠሪ መረጃዉን ያረጋገጠዉ

ስም--------------------ፊርማ-------------ቀን----------- ስም------------------ ፊርማ--------- ቀን---------


ማህተም

25
የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 01/2015
ከወረዳ - ወረዳ የሱፐርቫይዘሮች ዝውውር መጠየቂያ ቅጽ (ቅጽ ዐ2-3)
ወረዳ-----------------------
ዝውውር
ሱፐርቫይዘሩ ባለትዳር የጠየቁበት

የባልና ሚስት አገልግሎት አማካይ


አገልግሎት (1) ጠ/ድምር
ከሆኑ ባለቤታቸው (2)
ወረዳ

የቅጥር ዘመን (ቀ/ወ/ዓ)


ዝ/የ

አገልግሎት ከቦታ ነጥብ ጋር

ድምር 100% =መ+ሰ+ቀ


ረ=(መ+ሠ)/2

የብቃት ምዘና 10%=10


ጠ/በ

70%=መ*3 ወይም ረ*3


የዝውውር

የተገኘ ውጤት (ለ=ሀ*)


ደመወዝ
ተ. የትም/ደረ የተመረቀበት ት ፊር

የትዳር (ቀ)20%=20

ወይም =ረ+ሰ+ቀ
ድምር (መ=ለ+ሐ)
ጠያቂው ሙሉ ፆታ

የአገልግሎት (ሰ)
ቁ ጃ ትምህርት አይነት አሁን ምክ ማ
ስም በሌላ የሚሰሩበት ያላቸው ንያ

ተባዝቶ
ባለበት
ት/ቤት ተቋምና አገልግሎ 1ኛ 2ኛ 3ኛ ት
ወረዳ
(ሐ) ቦታ ት (ሠ)
(ሀ)

መረጃዉን ያጠናቀረዉ ተጠሪ መረጃዉን ያረጋገጠዉ

ስም-------------------------ፊርማ-------------ቀን----------- ስም------------------ ፊርማ--------- ቀን---------


ማህተም

26
የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 01/2015
ከዞን/ከተማ አስተዳደር - ዞን/ከተማ አስተዳደር የመምህራን ዝውውር መጠየቂያ ቅጽ (ቅጽ ዐ3-1)
ወደ መተከል /አሶሳ/ካማሽ/ከተማ
ወረዳ-----------------------
አስተዳደር
ዝውውር የጠየቁበት ዝ/የጠ/
መምህሩ/ሯ ባለትዳር በት ፊር

የባልና ሚስት አገልግሎት አማካይ


አገልግሎት (1) ጠ/ድምር
ከሆኑ ባለቤታቸው (2) ወረዳ/ከተማ አስ/ር ምክንያ ማ

የቅጥር ዘመን (ቀ/ወ/ዓ)


አገልግሎት ከቦታ ነጥብ ጋር

ድምር 100% =መ+ሰ+ቀ


የብቃት ምዘና 10%=10
ረ=(መ+ሠ)/2

70%=መ*3 ወይም ረ*3


የተገኘ ውጤት (ለ=ሀ*)
ተ የዝውውር

ደመወዝ

የትዳር (ቀ)20%=20
የትም/ደ የተመረቀበትትምህርት

ወይም =ረ+ሰ+ቀ
ድምር (መ=ለ+ሐ)

የአገልግሎት (ሰ)
. ጠያቂው ሙሉ ፆታ
ረጃ አይነት አሁን
ቁ ስም በሌላ የሚሰሩበት ያላቸው

ተባዝቶ
ባለበት
ት/ቤት ተቋምና አገልግሎ 1ኛ 2ኛ 3ኛ
ት/ቤት
(ሐ) ቦታ ት (ሠ)
(ሀ)

መረጃዉን ያጠናቀረዉ ተጠሪ መረጃዉን ያረጋገጠዉ

ስም-----------------------------ፊርማ-------------ቀን----------- ስም------------------ ፊርማ--------- ቀን---------


ማህተም

27
የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 01/2015
ከዞን/ከተማ አስተዳደር - ዞን/ከተማ አስተዳደር የር/መምህራን፣ም/ር/መምህራን ዝውውር መጠየቂያ ቅጽ (ቅጽ ዐ3-2)
ወደ መተከል /አሶሳ/ካማሽ/ከተማ
ወረዳ-----------------------
አስተዳደር
ዝውውር ዝ/የጠ/
ር/መምህሩ/ሯ ባለትዳር የጠየቁበት በት ፊር

የባልና ሚስት አገልግሎት አማካይ


አገልግሎት (1) ጠ/ድምር
ከሆኑ ባለቤታቸው (2) ምክንያ ማ
ወረዳ

የቅጥር ዘመን (ቀ/ወ/ዓ)


አገልግሎት ከቦታ ነጥብ ጋር

ድምር 100% =መ+ሰ+ቀ


ረ=(መ+ሠ)/2

የብቃት ምዘና 10%=10


70%=መ*3 ወይም ረ*3
ተ የዝውውር

የተገኘ ውጤት (ለ=ሀ*)


ደመወዝ

የትዳር (ቀ)20%=20
የትም/ደ የተመረቀበትትምህርት

ወይም =ረ+ሰ+ቀ
ድምር (መ=ለ+ሐ)
. ጠያቂው ፆታ

የአገልግሎት (ሰ)
ረጃ አይነት አሁን
ቁ ሙሉ ስም በሌላ የሚሰሩበት ያላቸው

ተባዝቶ
ባለበት
ት/ቤት ተቋምና አገልግሎት 1ኛ 2ኛ 3ኛ
ት/ቤት
(ሐ) ቦታ (ሠ)
(ሀ)

መረጃዉን ያጠናቀረዉ ተጠሪ መረጃዉን ያረጋገጠዉ

ስም------------------------ፊርማ-------------ቀን----------- ስም------------------ ፊርማ--------- ቀን---------


ማህተም

28
የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 01/2015
ከዞን/ከተማ አስተዳደር - ዞን/ከተማ አስተዳደር የሱፐርቫይዘሮች ዝውውር መጠየቂያ ቅጽ (ቅጽ ዐ3-3)
ወደ መተከል /አሶሳ/ካማሽ/ከተማ
ወረዳ-----------------------
አስተዳደር
ዝውውር የጠየቁበት
ሱፐርቫይዘሩ ባለትዳር

የባልና ሚስት አገልግሎት አማካይ


አገልግሎት (1) ጠ/ድምር
ከሆኑ ባለቤታቸው (2) ወረዳ

የቅጥር ዘመን (ቀ/ወ/ዓ)

አገልግሎት ከቦታ ነጥብ ጋር

ድምር 100% =መ+ሰ+ቀ


የብቃት ምዘና 10%=10
ረ=(መ+ሠ)/2
ዝ/የጠ

70%=መ*3 ወይም ረ*3


የተገኘ ውጤት (ለ=ሀ*)
ተ የዝውውር የተመረቀበት ፊ

ደመወዝ

የትዳር (ቀ)20%=20
የትም/ደረ /በት

ወይም =ረ+ሰ+ቀ
ድምር (መ=ለ+ሐ)

የአገልግሎት (ሰ)
. ጠያቂው ሙሉ ፆታ ትምህርት ር
ጃ አሁን የሚሰሩበ ምክን
ቁ ስም አይነት በሌላ ያላቸው ማ

ተባዝቶ
ባለበት ት ያት
ት/ቤት አገልግሎት 1ኛ 2ኛ 3ኛ
ት/ቤት ተቋምና
(ሐ) (ሠ)
(ሀ) ቦታ

መረጃዉን ያጠናቀረዉ ተጠሪ መረጃዉን ያረጋገጠዉ

ስም---------------------ፊርማ-------------ቀን----------- ስም------------------ ፊርማ--------- ቀን---------


ማህተም

29
የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 01/2015
ከክልል/ከተማ አስተዳደር - ክልል/ከተማ አስተዳደር የመምህራን ዝውውር መጠየቂያ ቅጽ (ቅጽ ዐ4-1)
ወረዳ-----------------------
ዝውውር የጠየቁበት
መምህሩ/ሯ ባለትዳር ከሆኑ

የባልና ሚስት አገልግሎት አማካይ


አገልግሎት (1) ጠ/ድምር ክልል/ከተማ
ባለቤታቸው (2)
አስተዳደር

የቅጥር ዘመን (ቀ/ወ/ዓ)

አገልግሎት ከቦታ ነጥብ ጋር

ድምር 100% =መ+ሰ+ቀ


የብቃት ምዘና 10%=10
ረ=(መ+ሠ)/2
ዝ/የጠ

70%=መ*3 ወይም ረ*3


የተገኘ ውጤት (ለ=ሀ*)
ተ የዝውውር

ደመወዝ

የትዳር (ቀ)20%=20
የትም/ደ የተመረቀበት /በት ፊር

ወይም =ረ+ሰ+ቀ
ድምር (መ=ለ+ሐ)

የአገልግሎት (ሰ)
. ጠያቂው ሙሉ ፆታ
ረጃ ትምህርት አይነት አሁን ምክን ማ
ቁ ስም በሌላ ያላቸው

ተባዝቶ
ባለበት የሚሰሩበት 1 ያት
ት/ቤት አገልግሎት 2ኛ 3ኛ
ት/ቤት ተቋምና ቦታ ኛ
(ሐ) (ሠ)
(ሀ)

መረጃዉን ያጠናቀረዉ ተጠሪ መረጃዉን ያረጋገጠዉ

ስም-----------------------ፊርማ-------------ቀን----------- ስም------------------ ፊርማ--------- ቀን---------


ማህተም

30
የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 01/2015
ከክልል/ከተማ አስተዳደር - ክልል/ከተማ አስተዳደር የር/መምህራን፣ም/ር/መምህራን ዝውውር መጠየቂያ ቅጽ (ቅጽ ዐ4-2)
ወረዳ-----------------------
ዝውውር የጠየቁበት
መምህሩ/ሯ ባለትዳር

የባልና ሚስት አገልግሎት አማካይ


አገልግሎት (1) ጠ/ድምር ክልል/ከተማ
ከሆኑ ባለቤታቸው (2)
አስተዳደር

የቅጥር ዘመን (ቀ/ወ/ዓ)

አገልግሎት ከቦታ ነጥብ ጋር

ድምር 100% =መ+ሰ+ቀ


የብቃት ምዘና 10%=10
ረ=(መ+ሠ)/2
ዝ/የጠ

70%=መ*3 ወይም ረ*3


የተገኘ ውጤት (ለ=ሀ*)
የዝውውር የተመረቀበት

ደመወዝ

የትዳር (ቀ)20%=20
ተ. /በት

ወይም =ረ+ሰ+ቀ
ድምር (መ=ለ+ሐ)

የአገልግሎት (ሰ)
ጠያቂው ሙሉ ፆታ የትም/ደረጃ ትምህርት ፊርማ
ቁ አሁን ምክን
ስም አይነት በሌላ የሚሰሩበት ያላቸው

ተባዝቶ
ባለበት ያት
ት/ቤት ተቋምና አገልግሎት 1ኛ 2ኛ 3ኛ
ት/ቤት
(ሐ) ቦታ (ሠ)
(ሀ)

መረጃዉን ያጠናቀረዉ ተጠሪ መረጃዉን ያረጋገጠዉ

ስም---------------------ፊርማ-------------ቀን----------- ስም------------------ ፊርማ--------- ቀን---------


ማህተም

31
የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 01/2015
ከክልል/ከተማ አስተዳደር - ክልል/ከተማ አስተዳደር የሱፐርቫይዘሮች ዝውውር መጠየቂያ ቅጽ (ቅጽ ዐ4-3)
ወረዳ-----------------------
ዝውውር
ሱፐርቫይዘሩ/ሯ ባለትዳር የጠየቁበት

የባልና ሚስት አገልግሎት አማካይ


አገልግሎት (1) ጠ/ድምር
ከሆኑ ባለቤታቸው (2) ክልል/ከተማ

የቅጥር ዘመን (ቀ/ወ/ዓ)


አስተዳደር

አገልግሎት ከቦታ ነጥብ ጋር

ድምር 100% =መ+ሰ+ቀ


ረ=(መ+ሠ)/2

የብቃት ምዘና 10%=10


ዝ/የጠ/

70%=መ*3 ወይም ረ*3


የዝውውር የተመረቀበት

ተባዝቶ የተገኘ ውጤት


ደመወዝ
በት

የትዳር (ቀ)20%=20

ወይም =ረ+ሰ+ቀ
ድምር (መ=ለ+ሐ)
ተ.ቁ ጠያቂው ሙሉ ፆታ የትም/ደረጃ ትምህርት ፊርማ

የአገልግሎት (ሰ)
አሁን በሌላ ምክንያ
ስም አይነት ያላቸው ት

(ለ=ሀ*)
ባለበት ት/ቤ የሚሰሩበት
አገልግሎ 1ኛ 2ኛ 3ኛ
ት/ቤት ት ተቋምና ቦታ
ት (ሠ)
(ሀ) (ሐ)

መረጃዉን ያጠናቀረዉ ተጠሪ መረጃዉን ያረጋገጠዉ

ስም-----------------------ፊርማ-------------ቀን----------- ስም------------------ ፊርማ--------- ቀን---------

ማህተም

32
የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር አፈጻጻም መመሪያ ቁጥር 01/2015

You might also like