Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 3

የቃለ-መጠይቁ ዓላማ፡-

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ኢንፎርሜሽንና ስትራቴጅክ ኮሚኒኬሽን ም/ፕሬዘዳንት ጽ/ቤት በየወሩ ለሚያሳትመው


የቀድሞ ስሙ "ናይል" በአሁኑ "ዓባይ" ጋዜጣ የሕዳር ወር 2016 ዓ.ም እትማችን ላይ ስለ ክፍላችሁ የስራ
እንቅስቃሴና ተግዳሮቶችም ካሉ ተጠቅሰው ለጋዜጣ ግብዓት የሚውል ፅሁፍ /መረጃ/ ለማግኘት ታልሞ ነው፡፡

1. በቅድሚያ ለቃለ-መጠይቁ ፈቃደኛ በመሆንዎ በዝግጅት ክፍላችን ስም እያመሰገን ስምዎትንና የስራ


ኃላፊነዎትን ቢነግሩን?
 ስሜ፡ አቶ ማሙሽ ገ/ሥላሴ ይባላል
 ኃላፊነቴ፦ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የፊዚካል ፕሮጀክቶች ጽ/ቤት ኃላፊ ነኝ
2. የስራ ክፍላችሁ መቼ ተቋቁሞ ስራ እንደጀመረ ቢገልፁልን?
 እስከ 2000 ዓ.ም ድረስ በዩኒቨርሲቲዎች የሚከናወኑ ግንባታዎችን ሲካተትል የቆየው ት/ት
ሚኒስቴር ሲሆን የዩኒቨርሲቲዎች የግንባታ መስፋፋት ተከትሎ ፊዚካል ፕሮጀክቶች ጽ/ቤት
እንዲቋቋም በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት በ 2001 ዓ.ም ተቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
3. ባሳለፍናቸው የስራ ጊዜያት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ቢያሳውቁን?

የግንባታ ስራ በባህሪው በአንድ የበጀት አመት ተጀምሮ የሚጠናቀቅ ባለመሆኑ በጥቅሉ ባለፉት የስራ ጊዜያቶች
የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት
 ዩኒቨርሲቲው በት/ት ሚኒስቴር የተልእኮ ልየታ መሰረት የምርምር ዩኒቨርሲቲ ተብሎ መሰየሙን ተከትሎ
ለዩኒቨርሲቲው የወደፊት ራዕይ መሳካት ያስፈልጋሉ ተብለው ለተለዩ ሰባት የግንባታ ፕሮጀክቶችን በጀት
ለማስተከል እንዲቻል የአዋጭነት ጥናት ተዘጋጅቶ ለፕላንና ልማት ሚኒስቴር ተልኳል
 የአዳዲስ ግንባታዎች ዲዛይን በአማካሪ ድርጅቶች ተሰርቷል
 ወሰን ያልነበራቸው የዩኒቨርሲቲያችን ግቢዎች ወሰን እንዲኖራቸው ተደርጓል
 የግንባታ ስራቸው በሂደት ላይ የሚገኙትን የግንባታ ክትትልና የውለታ ማስተዳደር ስራዎች ተሰርተዋል
 ግንባታቸው የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን የመረከብ እና አገልግሎት እንዲጀምሩ ተደርጓል
4. በክፍላችሁ ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል በዩኒቨርሲቲው የተለያዩ ግቢዎች ያሉ የግንባታ ስራዎች
ሲሆኑ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስራው የተስተጓጎለበትን ምክንያቱን ቢያጫውቱን?
 በዩኒቨርሲቲው የተለያዩ ግቢዎች ውስጥ ልዩ ልዩ አገልግሎት የሚሰጡ ግንባታዎች እየተከናወኑ ይገኛል፡፡
እነዚህ ፕሮጀክቶች አሁን ላይ አፈፃፀማቸው ከፕሮጀክት ፕሮጀክት የተለያዩ ቢሆንም በጥቅሉ ሲታዩ ግን
አፈፃፀማቸው ዝቅተኛ ነው፡፡ ለስራው መጓተትና መዘግየት በርካታ ምክንያቶች ያሉ ቢሆንም በዋናነት
በመንግስት የተወሰነው የገንዘብ የመግዛት አቅም ማነስ፣ተገማች ያለሆነ የግንባታ ግብዓቶች ዋጋ መናር፣
የተቋራጮች የማስፈፀም አቅም ማነስ እና ከ 2013 ጀምሮ ያልተረጋጋው የሰላም ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ
ግንባታዎች እንዲዘገዩ ብሎም እንዲቆሙ አስተዋጽኦ አድርጓል
5. እነዚህ በጅምር የቆሙት ህንፃዎች ከሙያዎ አንፃር ምን ያህል ጉዳት ሊደርስባቸው ይችላል ይላሉ?
 ሁሉም ጅምር ህንፃዎች አልቆሙም ከነዚህ ውስጥ አንፃራዊ በሆነ መልኩ እየተሰሩ ያሉ አሉ፡፡ ነገር ግን
ጅምርና ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸው ግንባታዎች ያሉበት የስነ መዋቅር (Structure) ስራ ላይ ሲሆኑ
በመቆማቸው ምክንያት ህንፃዎቹ ላይ ሊጠቀስ የሚችል ጉዳት አይደርስባቸውም፡፡ በሌላ መንገድ ግን
ጉዳቱን በሁለት ከፍለን ልናየው እንችላለን፡፡ አንደኛው፦ ግንባታዎቹ በታቀደላቸው ጊዜ
ባለመጠናቀቃቸው ለታቀደላቸው አገልግሎት በወቅቱ አለመድረሳቸው ነው፡፡ ሁለተኛው፦ በተከሰተው
የግንባታ ግብዓቶች ዋጋ መናርን ተከትሎ ግንባታዎቹን ለማጠናቀቅ ቀድሞ ከተያዘላቸው ተጨማሪ በጀት
የሚጠይቁ መሆናቸው ነው
6. የግንባታው ስራ ከመቆሙ በፊት መደረግ የነበረበት ቅድመ ጥንቃቄ ብለው የሚያስቡት ካለ
ቢገልፁልን?
 ግንባታዎቹ ከመቆማቸው በፊት በዩኒቨርሲቲው በኩል ያላደረግናቸው ቅድመ ጥንቃቄዎች እና አሁን
ላይ እንዲህ ቢደረግ ወይም ቀረ ብየ የማስበው የለም፡፡ እንደውም የግንባታዎቹ አፈፃፀም ዝቅተኛ
ከመሆኑ በፊት የተለያዩ ድጋፎችንና ክትትሎችን ለማድረግ ተሞክሯል፡፡ለምሳሌ፦ ከውጭ ሊገዙ
የሚችሉ የማጠናቀቂያ ምርቶችን በአገር ውስጥ ባሉና ጥራቻቸው በአማካሪ ድርጅቶች እየተረጋገጥ
እንዲሰሩ፣ የጥሬ ገንዘብ እጥረት ቢኖርም ክፍያዎችን በተቻለ መጠን በቀቅቱ ለመክፈል ጥረት ተደርጓል፣
አፈፃፀማቸውን ለማሻሻል ተደጋጋሚ የሶስትዮሽ ውይይትና የማሳሰቢያ ደብዳቤዎች በመፃፍ ግንባታዎቹ
 ሁሉም ፕሮጀክቶች በፌደራል መንግስት በጀት የሚሰሩና የሚተዳደሩ እንደመሆናቸው መጠን ከላይ
እንደችግር ያነሳናቸው ምክንያቶች ከመከሰታቸው በፊት ሊደረጉ የሚገቡ ቅድመ ሁኔታዎች ነበሩ፡፡
ከነዚህም መካከል በ 2010 ዓ.ም መንግስት የገንዘብን የመግዛት አቅም በ 15% በመቀነሱ ምክንያት
ክልሎች የውል ዋጋ ማሻሻያ ቢያደርጉም የፌደራል ፕሮጀክቶች የውል ዋጋ ላይ ማሻሻያ አለመደረጉ
በግንባታ ፕሮጀክቶች ውል ላይ ሊያሳድር የሚችለውን ጫና ከግምት ውስጥ ሳይገባ መታለፉ አንዱ
ነው፡፡ ሁለተኛው የግንባታ ግብዓቶች ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ ባልተገመተ ሁኔታ መጨመሩን ተከትሎ
ቀድሞ በተገባ የግንባታ ውል ሊጠናቀቁ የማይችሉ ፕሮጀክቶችን ከማቋረጥ ይልቅ የዋጋ ማካካሻ ማድረግ
የተሻለ አማራጭ መሆኑ ቢታወቅም የዋጋ ማካካሻ ለማድረግ በሂደት ላይ ከአንድ አመት በላይ ፈጅቷል፡፡
ከላይ የተገለጹት ምክንያቶች ቀጥተኛ ከመስሪያ ዋጋ ጋር የተያያዙ በመሆናቸው ወቅቱን የጠበቀ ምላሽ
መሰጠት የነበረባቸው ናቸው ብዩ አምናለሁ፡፡ የሰላም አለመረጋጋቱ ከባለድርሻ አካላቶች ቁጥጥር ውጭ
በመሆኑ በመሆኑ ለዚህ ችግር ቀድሞ ሊታሰብ የሚገባ ጥንቃቄ ያለ አይመስለኝም፡፡
7. በክፍላችሁ የሚታዩ ተግዳሮቶች ካሉ በዝርዝር ቢነግሩንና ዩኒቨርሲቲው ማድረግ የሚገባቸውን
የትኩረት አቅጣጫዎች ቢጠቁሙን?
 በዋናነት በክፍሉ ውስጥ ከሚታዩ ተግዳሮቶች መካከል አንዱ የጥሬ ገንዘብ እጥረት ነው፡፡ ይህም
ዩኒቨርሲቲውን በመሰረተ ልማት አቅርቦት ተወዳዳሪና ተመራጭ ዩኒቨርሲቲ ለማድረግ የሚያስችሉ
አዳዲስ ግንባታዎችን ለማስጀመርና የተጀመሩትን በወቅቱ ለማስጨረስ ተግዳሮት እየሆነ ያለበት ሁኔታ
ተፈጥሯል ፡፡
 ሌላኛው ከስራው ስፋት አንፃር በክፍሉ ውስጥ በቂና ቋሚ የሆነ የሰው ኃይል የሌለው መሆኑ ነው፡፡
ይህም በተወሰነ መልኩ የስራ ጫና ፈጥሯል፡፡
8. ከእናንተ የስራ ዘርፍ ሌሎች መማር ቢፈልጉ አስተማሪ የሆኑ ልዩ ተሞክሮዎችና ልምዶች ካሉ
ወይም ቢሆን/ቢደረግ ብለው የሚያልሙት የአሰራር ስልት ካለ ቢነግሩን?
 ይህን ጥያቄ ከእኛ ጋር ለሚሰሩ ተገልጋዮች ቀርቦ ምላሽ ቢሰጡበት ምላሹ በጣም አሳማኝ
ይሆን ነበር፡፡ ቢሆንም ከጠየቅሽን በእኛ የስራ ዘርፍ ለሌሎች አስተማሪ ተሞክሮዎች አሉን ብየ
አስባለሁ፡፡ ከእነዚህም መካከል አንዱ ለተቋራጮች የሚፈፀሙ ክፍያዎችን በጋራ አካውንት
ማስተዳደር ነው፡፡ ይህም የሚፈፀሙ ክፍያዎች ለፕሮጀክቱ አገልግሎት ብቻ እንዲውል
ያደርጋል፡፡ ሁለተኛው ዩኒቨርሲቲውን ወክለው በየፕሮጀክቶቹ ላይ በተለያየ ሙያ የተመደቡ
መምህራን አሉን፡፡ ይህም ግንባታው ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ጥራት ባለው መልኩ
እንዲከናወን፣ ክፍያዎችም ለተሰራ ስራና ለፕሮጀክቱ እንዲውል ለማስቻል፣ በግንባታው ሂደት
ወቅት የሚከሰቱ ለውጦችን በአጭር ጊዜ መፍትሔ ለመስጠት እና መማር ማስተማሩ በተግባር
የተደገፈ እንዲሆን አስችሏልና
9. በመጨረሻ የሚያስተላልፉት መልዕክት እና በኛ በኩል ያልተነሳ ጥያቄ ካለ ከነማብራሪያው ቢገልፁልን?
 የግንባታ ዘርፉ ብዙ ተዋናዮች ያሉበት እና የስራ ሂደቱም ውስብስብ በመሆኑ ምክንያት ብዙ ያልተነሱ
ርእሰ ጉዳዮች ያሉ በመሆኑ ቀጣይነት ባለው መልኩ እንዲቀጥል እያልኩ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን፡፡
10. የስራ ጊዜዎትን አጣበዉ ለቃለ መጠይቁ ፈቃደኛ ስለሆኑ ከልብ እናመሰግናለን፡፡
 ይህ ርእሰ ጉዳይ ቢነሳ ለአንባቢዎች መረጃ ወይም እውቀት ይሰጣል ብለሽ ይህን ቃለመጠይቅ
በማዘጋጀትሽ እኔም አመሰግናለሁ፡፡

ስለነበረን ቆይታ በዝግጅት ክፍላችን ስም እናመሰግናለን !!

You might also like