በእንተ ቅዱስ ሉቃስ

You might also like

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 3

ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ

ቅዱስ ሉቃስ:-

† ሐዋርያ ነው
† ወንጌላዊ ነው
† ሰማዕት ነው
† ዓቃቤ ሥራይ (ዶክተር) ነው
† የጥበብ ሰው (ሰዓሊ) ነው
† ዘጋቢ (የሐዋርያትን ዜና ሕይወት የጻፈ) ነው።

ይሕስ እንደምን ነው ቢሉ:- በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን መነሻ አካባቢ በተወደደች የጌታ ዓመት ከእሥራኤላውያን
ወገኖቹ ቅዱስ ሉቃስ ተወልዷል። ያደገውም መቄዶንያ አካባቢ ነው። ጌታችን ተጠምቆ ማስተማር ሲጀምር ከተከተሉት የ5
ገበያ ሕዝብ መካከል 120ውን ለቤተሰብነት መምረጡ ይታወቃል። ይህም 12ቱ ሐዋርያትን፣ 72ቱ አርድእትንና 36ቱ ቅድሳት
አንስትን ያጠቃልላል።

ታዲያ ጌታችን ቅዱስ ሉቃስ እንዲጠቅም አውቆ ከ72ቱ አርድእት ደምሮታል። ቅዱስ ሉቃስ ጌታን ከተከተለ በኋላ ለ3 ዓመት
ከ3 ወር: ከዋለበት እየዋለ፣ ካደረበትም እያደረ የቃሉን ትምህርት፣ የእጆቹን ተአምራት በጥሞና ይከታተል ነበር።

ጌታችን ለዓለም ድኅነት ተሰቅሎ፣ ሙቶ ከተነሳ በኋላ ስለዚህ ቅዱስ የሚናገር አንድ የወንጌል ክፍል እናገኛለን። በሉቃስ
ወንጌል ምዕራፍ 24 ላይ ከምናያቸው የኤማሁስ መንገደኞች አንዱ ይህ ቅዱስ እንደ ሆነ አባቶች አስተምረውናል።

በእርግጥ 'ቀለዮዻ' የሚለው ስም በዘመኑ የብዙዎች መጠሪያ ቢሆንም እርሱም ጌታን ከመከተሉ በፊት በዚህ ስም ይጠራ እንደ
ነበር ይታመናል። በወቅቱ ታዲያ 2ቱ ደቀ መዛሙርት (ሉቃስና ኒቆዲሞስ) ወደ ኤማሁስ ሲሔዱ ጌታ መንገድ ላይ ተገልጦ
እያጫወታቸው አብሮ ተጉዟል። እነርሱም ማንነቱን አላወቁምና ስለ ራሱ ለራሱ እየሰበኩለት ተጉዘዋል። ከሐዘናቸው ብዛት
ማስተዋል ተስኗቸው፣ ቀቢጸ ተስፋም ወሯቸው ነበርና መድኃኒታችን ክርስቶስ የነቢያትን ትንቢት ተረጐመላቸው።

በዚህ ጊዜም ከነገሩ ማማር: ከምሥጢሩ መሥመር ጋር እየገረማቸው ልቦናቸው ይቃጠል (ይቀልጥባቸው) ነበር። "አኮኑ
ይነድደነ ልበነ" እንዲል። ወደ ኤማሁስ ሲደርሱ ግን ደጐች ናቸውና "በቤት ካላደርክ: ራት ካልበላህ" ብለው ግድ አሉት።

በማዕድ ሰዓት ግን ቡራኬውን ሰጥቷቸው: ቸር አምላክነቱን ገልጦላቸው ተሰወራቸው። እነርሱም በሐሴት ከኤማሁት
ተመልሰው እየሮጡ ኢየሩሳሌም ደርሰው ትንሳኤውን ሰበኩ። የመንገዱ ርዝመትም አልታወቃቸውም ነበር።

ከዚህ በኋላ ቅዱስ ሉቃስ እንደ ሐዋርያቱ መጽሐፈ ኪዳንን፣ ትምህርተ ኅቡዓትን ተምሮ: መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለስብከተ
ወንጌል ወጥቷል።

ቅዱሱ ዶክተር

በትውፊት ትምሕርት እንደ ተማርነው ቅዱስ ሉቃስ ጌታን ከመከተሉ በፊት ሥራው ሐኪምነት (ዶክተር) ነበር። በዚህም
አበው "አቃቤ ሥራይ / ባለ መድኃኒት" ይሉታል። በተሰጠው ሙያም ብዙዎችን አገልግሏል።
የጌታ ደቀ መዝሙር ከሆነ በኋላ ደግሞ "አቃቤ ሥራይ ዘነፍስ-የነፍስ ሐኪም" ተብሏል። እንዲያውም አባቶቻችን ሐዋርያትን
ያክማቸው ነበር ይባላል። ምክንያቱም ቅዱሳን ሐዋርያት አብዛኞቹ በሽተኞች ነበሩና ነው። ከደግነታቸው የተነሳም እልፍ
አእላፍ ድውያንን በተአምራት ሲፈውሱ እነርሱ ግን በስቃይ ይኖሩ ነበር።

ሕመማቸው ሲጠናባቸው ግን ቅዱሱ ዶክተር ሉቃስ ይራዳቸው ነበር። ይሕንንም ቅዱስ ዻውሎስ በቆላስይስ መልእክቱ ላይ
"የተወደደው ባለ መድኃኒቱ ሉቃስ: ዴማስም ሰላምታ ያቀርቡላቹሃል" ሲል ገልጾታል። (ቆላ. 4:14)

ዘጋቢው ሐዋርያ

ቅዱስ ሉቃስ እንደ ዛሬው ነገሮች ምቹ ባልነበሩበት ዘመን እጅግ አድካሚ የሆነ ጉዞ አድርጐ የሐዋርያትን ዜና ሕይወት
ዘግቦልናል። ልክ ወንጌሉን ለታኦፊላ (ቴዎፍሎስ) እንደ ጻፈለት ግብረ ሐዋርያትንም ለእርሱ በትረካ መልክ አቅርቦለታል።

ሲጽፍለትም "ሰማሁ" እያለ ሳይሆን አብሮ እያለ ያየውንና የተሳተፈበትን ነው። አተራረኩም በአንደኛና በ3ኛ መደብ አድርጐ
እያቀያየረ ነው። ማለትም አንዳንዴ "እኛ" እያለ ሌላ ጊዜ ደግሞ "እነርሱ" እያለ ነበር የሚተርክለት። መጽሐፉም 28 ምዕራፎች
ሲኖሩት በጌታ ዕርገት ጀምሮ በኢየሩሳሌምና በአሕዛብ የነበረውን ስብከተ ወንጌል ገልጦ: የቅዱስ ዻውሎስን ጉዞዎች በሰፊው
ዳስሶ ይጠናቀቃል።

ወንጌላዊው ሐዋርያ

ቅዱስ ሉቃስ ወንጌልን እንዲጽፉ ከተመረጡ (ከተፈቀደላቸው) ሐዋርያት አንዱ ነው። በቤተ ክርስቲያንም "ዘላሕም" እየተባለ
ይጠራል። ለዚህም ምክንያቱ:-

1. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በበረት: በላምና በአህያ መካከል መወለዱን በመጻፉ


2. ጌታችንን "መግዝአ ላሕም-የሚታረድ ሜልገች (ላም)" ብሎ በመግለጹ እና
3. ከ4ቱ እንስሳ (ኪሩቤል) አንዱ (ገጸ ላሕም) ይራዳው: ይጠብቀውም ስለ ነበር ነው።

ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጻፈው ጌታ ባረገ በ22ኛው ዓመት ሲሆን ይኼውም በ56 ዓ/ም አካባቢ ማለት ነው። ሲጽፍም ብቻውን
አልነበረም። ልክ ቅዱስ ማርቆስ ወንጌሉን የጻፈው ከሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስ ጋር እንደ ሆነው ሁሉ: ቅዱስ ሉቃስም
የጻፈው ከብርሃነ ዓለም ቅዱስ ዻውሎስ ጋር ነው። ምክንያቱም ለረዥም ዓመታት አብረው ለስብከተ ወንጌል ተጉዘዋልና።

ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን ሲጽፍ በነ ዘካርያስ ቤተሰብ ጀምሮ: ብሥራተ ገብርኤልን: ክብረ ድንግል ማርያምን: የጌታን ልደት:
እድገት: መጠመቅ: ማስተማር: መሰቀል: መሞት: መነሳትና ማረግ በቅደም ተከተል ይተርክልናል።

ጥበበኛው (ሰዓሊው) ሐዋርያ

ቅዱስ ሉቃስን ለየት ከሚያደርጉት ነገሮች ሌላኛው ደግሞ ጐበዝ ሰዓሊ የነበረ መሆኑ ነው። በሐዲስ ኪዳንም የመጀመሪያውን
የእመቤታችንን ስዕል (ምስለ ፍቁር ወልዳን) የሳለው እሱ ነው።

አንድ ቀን የአምላክ እናት ባለችበት ከጌታ አስፈቅዶ የሳላት ስዕለ አድኅኖ ሥጋን የለበሰች፣ ከፊቷ ወዝ የሚወጣ፣ የምታለቅስ፣
ስትወጋ የምትደማና ድውያንን የምትፈውስ ሆና ተገኝታለች። ይህች ስዕል ዛሬ ሃገራችን ኢትዮዽያ ውስጥ አለች ይባላል።

ሰማዕቱ ሐዋርያ
ቅዱስ ሉቃስ እንዲህ ባለ ሕይወት ሲመላለስ በትጋት (ያለ ዕረፍት) ወንጌልን እየሰበከ ነበር። በ66 እና በ67 ዓ/ም ብርሃናተ
ዓለም ዼጥሮስ ወዻውሎስ በኔሮን ቄሣር እጅ ሲገደሉ የሮም ግዛት ክርስቲያኖች ኃላፊነት በእርሱ ላይ ነበረ።

ከወንጌሉና ግብረ ሐዋርያቱ ባለፈ በመልእክታት: አንድም እየዞረ ክርስቲያኖችን አጸና: አሕዛብንም አሳመነ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ
ግን ዝናውን የሰማው ኔሮን ሊገድለው ፈለገ። በዚህ ጊዜ ቅዱስ ሉቃስ ከደቀ መዛሙርቱ መካከል ሲላስ የሚባለውን ሽማግሌ
መርጦ መጽሐፎቹን ሁሉ አስረከበው።

በድፍረትም ወደ ኔሮን ቄሣር ቀርቦ ተናገረው። ንጉሡም "ክርስቶስን አምልኩ የምትል ቀኝ እጅህ መቆረጥ አለባት" ብሎ እጁን
ከትክሻው በሰይፍ ለይቶ መሬት ላይ ጣለው። ሁሉ ሰው ሲደነግጥ ቅዱሱ ተጐንብሶ የወደቀች እጁን አነሳትና እንደ ነበረችው
አደረጋት።

በዚያ የነበሩ አሕዛብም "ግሩም" አሉ። መልሶ ግን "አሁን እጄ ሥራዋን ስለ ጨረሰች አልፈልጋትም" ብሎ እንደ ገና ለይቶ
ጣላት።

“ከመ ያርኢ ኃይለ ቅድመ ኔሮን ወተዓይኑ:


አስተላጸቃ ወሌለያ ለምትርት የማኑ:
እስመ ላዕሌሁ ተሰውጠ ለክርስቶስ ስልጣኑ።"

እንዲል ስንክሳር ዘ22ቱ ለጥቅምት። በዚህ ጊዜም ይህንን ድንቅ ያዩ 477 ያህል አሕዛብ በክርስቶስ አምነው አብረውት
ተሰይፈዋል። የስብከት ዘመኑም ከ36 ዓመታት በላይ ነው። ጸሎቱና የአምላኩ በረከት አይለየን።

አምላከ ቅዱስ ሉቃስ ምሥጢሩን: ፍቅሩን: ጥበቡን ይግለጽልን። ከሐዋርያው በረከት ያስድር

You might also like