Mofed - Gov.et/blog

You might also like

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 5

አንዳንድ ነጥቦች ስለ ታክስ

mofed.gov.et/blog/አንዳንድ-ነጥቦች-ስለ-ታክስ

Jan. 11, 2024

ለገንዘብ ሚኒስቴር ከተሠጡ ሥልጣንና ተግባሮች መካከል ለታክስና ለቀረጥ ሕጎች መሠረት የሚሆኑ ፖሊሲዎችን፣
ስትራቴጂዎችንና ሕጎችን ማመንጨት እንዲሁም በትክክል ሥራ ላይ መዋላቸውን መከተታል ይገኙበታል፡፡ በዚህም
መሰረት ገቢን አሰባስቦ የአገሪቱን የልማት ፕሮግራሞች ፋይናንስ በማድረግ ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ እንዲቻል ግልጽ
የሆኑ ታክስ ሕጎችን በማውጣትት ተግባራዊ ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በዚህ ጽሁፍ ለዜጎች ግንዛቤ የሚያስጨብጡ አንዳንድ መሰረታዊ የታክስ ጽንሰ ሀሳቦችን እናጋራለን፡፡ በመሆኑም ስለ
ታክስ ምንነትና አይነቶች በጥቂቱ እንደሚከተለው እናቀርባለን፡፡

ታክስ ማለት መንግሥት በሕግ ላይ ተመርኩዞ ለመንግስታዊ ተግባራት እና ለልማት ስራዎች ማከናወኛ
የሚያስፈልገውን ገቢ ለማግኘት የንግድ እንቅስቃሴ ከሚያከናውኑ ግለሰቦች፣ ድርጅቶች እንዲሁም ገቢ ከሚያገኙ
ማናቸውም ሰዎች ገንዘብ የሚያገኝበት ስልት ነው፡፡ ታክስ ለስልጣኔ የሚከፈል መዋጮ ሲሆን ታክስ የመጣልና
የማስከፈል ሥልጣን ያለው መንግስት ብቻ ነው፡፡ ታክስ ማስከፈልም ሆነ መክፈል ከሕግ የሚመነጭ ኃላፊነት
ሲሆን፣ ከኢትዮጵያ የታክስ ሥርዓት መረዳት እንደሚቻለው በሕግ ሳይፈቀድ ታክስ እንደማይሰበሰብ ነው፡፡ ለዚህም
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት ከአንቀጽ 95 እስከ 100 መሰረት ባሉት ድንጋጌዎች ታክስ የመጣል፣ የመሰብሰብ እና
የመጠቀም ሥልጣንን በፌደራሉ እና በክልል መንግሥታት መካከል አከፋፍሏል፡፡

1/5
የታክስ አይነቶች ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆኑ ተብለው በሁለት ይከፈላሉ፡፡ ለዚህ ክፍፍል መሰረቱ ታክሱን ሰብስቦ
ለመንግሥት የመክፈል ኃላፊነት እና ታክሱን የመክፈል የመጨረሻው ኃላፊነት የሚያርፍባቸውን አካላት መሰረት
በማድረግ ነው፡፡ ቀጥተኛ ታክስ የሚባለው ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በሚያገኘው ገቢ ላይ በቀጥታ
የሚከፍለው እና ታክስ የመክፈል የመጨረሻ ኃላፊነቱ በዚሁ ታክስ ከፋይ ላይ ሲሆን ነው፡፡ በሌላ በኩል ቀጥተኛ
ያልሆነ ታክስ እንደ ቀጥታ ታክስ ግለሰብ ወይም ድርጅት ከሚገኘው ገቢ በቀጥታ ግለሰቡ ወይም ድርጅቱ ራሱ
የሚከፍለው ሳይሆን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የተመረቱ ምርቶችና አገልግሎቶች ወደ አገር ሲገቡ ወይም በንግድ
ሠንሰለት ውስጥ ለግብይት ሲቀርቡ የሚሰበሰቡ እና ተጠቃሚዎች የመጨረሻውን ታክስ የመክፈል ኃላፊነት
የሚወስዱባቸው የታክስ አይነቶች ናቸው፡፡ የእንደዚህ አይነት ታክሶችን የመክፈል የመጨረሻው ኃላፊነት የዕቃዎቹ
እና አገልግሎቶቹ የመጨረሻ ተጠቃሚ ቢሆንም ታክሱን ሰብስቦ ለመንግሥት የመክፈል ኃላፊነት የተጣለበት
የዕቃዎቹ ወይም የአገልግሎቶቹ አቅራቢ ላይ ነው፡፡

ሀ/ ቀጥተኛየሆኑታክሶች

በኢትዮጵያ የታክስ ሥርዓት የቀጥተኛ ታክሶች አይነተኛ ምሳሌ የሚሆነው የገቢ ግብር ሲሆን የሚጣለው እና
የሚሰበሰበውም በፌደራል የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 እና እሱን ተከትሎ በወጣው የገቢ ግብር ደንብ ቁጥር
410/2009 (እንደተሻሻለ) እና በማሻሻያዎቹ እንዲሁም የገንዘብ ሚኒስቴር በተለያዩ ጊዜያት ባወጣቸው
መመሪያዎች መሰረት ነው፡፡ በመርሕ ደረጃ የገቢ ግብር የሚሰበሰበው በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆኑ ድርጅቶች እና
ግለሰቦች በየትኛውም የአለም ክፍል ከሚያገኙት ገቢ ላይ ሲሆን በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ግለሰቦች
በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚያገኙት ገቢ ግብር የመክፈል ኃላፊነት አለባቸው፡፡

የኢትዮጵያ የገቢ ግብር ሥርዓት ሰንጠረዣዊ ሲሆን የተለያዩ የገቢ አይነቶችን በተለያዩ ሰንጠረዥ በመከፋፈል ግብሩ
የሚጣልና የሚሰበሰብ ይሆናል፡፡ በዚህ መሰረት የኢትዮጵያ የገቢ ግብር ሕግ በሚከተሉት ላይ ተፈፃሚ ይደረጋል፡፡

ከመቀጠርየሚገኝገቢ

ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ የሚባሉት አንድ ሰራተኛ ከሥራው ቅጥር ጋር በተገናኘ የሚቀበለው ደመወዝ፣ ምንዳ፣ አበል፣
ጉርሻ፣ ኮሚሽን፣ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማበረታቻ፣ ሥጦታ፣ የዓይነት ጥቅማ ጥቅሞች፣ እና ሰራተኛው ከሥራ
ሲሰናበት ወይም ሲለቅ የሚከፈለውን የገንዘብ መጠን ያካትታል፡፡ ከመቀጠር ከሚገኝ ገቢ በየወሩ ከሰራተኛው ገቢ
ላይ የሚሰበሰብ ሆኖ ከ0% እስከ 35% የገቢ ግብር መጣኔ ተፈፃሚ ይሆንበታል፡፡

ከቤትኪራይየሚገኝገቢ

ማንኛውም ቤት በማከራየት ገቢ የሚያገኝ ሰው በግብር ዓመቱ ውስጥ ቤት በማከራየት ካገኘው ጠቅላላ ዓመታዊ
ገቢ ላይ አንዳንድ በሕጉ የተፈቀዱ ወጪዎች ተቀናሽ ተደርገው በሚቀረው ገቢ ላይ ታክሱን የመክፈል ግዴታ
አለበት፡፡ የዚህ አይነቱ ግብር ተፈፃሚ የሚሆነው በድርጅቶች የኪራይ ገቢ ላይ 30% ሲሆን ግለሰቦች በሚያገኙት
የኪራይ ገቢ ላይ እንደ ገቢ መጠኑ ልክ ከ0% እስከ 35% መጣኔ ተፈፃሚ ይደረግባቸዋል፣ ታክሱም በየግብር አመቱ
የሚከፈል ነው፡፡

ከንግድሥራየሚገኝገቢ

ማንኛውም ሰው ለአጭር ጊዜም ይሁን ለተከታታይ ለትርፍ ብሎ የኢንዱስትሪ፣ የንግድ፣ የሙያ፣ ወይም ቮኬሽናል
ሥራዎችን ሲያከናውን ወይም በንግድ ሕጉ መሰረት የንግድ ሥራ ናቸው ተብለው የተለዩትን ሥራዎች በማከናውን
የሚያገኛቸው የንግድ ሥራ ገቢዎች ታክስ ይከፈልባቸዋል፡፡ የዚህ አይነቱ ግብር ተፈፃሚ የሚሆነው በድርጅቶች

2/5
የኪራይ ገቢ ላይ 30% ሲሆን ግለሰቦች በሚያገኙት የኪራይ ገቢ ላይ እንደ ገቢ መጠኑ ልክ ከ0% እስከ 35% መጣኔ
ተፈፃሚ ይደረግባቸዋል፣ ታክሱም በየግብር አመቱ የሚከፈል ነው፡፡

ልዩልዩገቢዎች

ከላይ ከተዘረዘሩት ገቢዎች በተጨማሪ በሰንጠረዥ “መ” የተመደቡት የገቢ አይነቶች ልዩ ልዩ ገቢዎች በመባል
የሚታወቁ ሲሆን የትርፍ ድርሻ፣ ወለድ፣ ሮያሊቲ፣ የሥራ አመራር ክፍያ፣ የቴክኒክ አገልግሎት ክፍያ፣ የመድን
አረቦን፣ ከዕድል ሙከራ የሚገኝ ገቢ፣ ሀብትን አልፎ አልፎ ከማከራየት የሚገኝ ገቢ፣ የካፒታል ሐብቶችን
በማስተላለፍ የሚገኝ ጥቅም፣ ንፋስ አመጣሽ ትርፍ፣ እና ያልተከፋፈለ ትርፍ ላይ ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡ በዚህ
ሰንጠረዥ ታክስ የሚጣልባቸው ገቢዎች እንደ ገቢው አይነት የተለያዩ የታክስ መጣኔ ተግባራዊ የሚደረግባቸው
ሲሆኑ ታክሱ መከፈል ያለበትም በሚከፍለው ሰው ተቀንሶ ሲሆን የመክፈል ግዴታ ያለበት ሰውም ግብርን ቀንሶ
የመያዝ ኃላፊነት አለበት፡፡ ይሁን እንጂ ካፒታል ሐብቶችን በማስተላለፍ የሚገኝ ጥቅም እና ንፋስ አመጣሽ ትርፍ
ሊከፈሉ የሚገባው ገቢውን ባገኘው ሰው በቀጥታ ነው፡፡

ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ የኢትዮጵያ የገቢ ግብር ሕግ የቅድመ ግብር ክፍያዎች (Withholding Taxes)
የሚሰበሰቡበት ሁኔታን ይደነግጋል፡፡ ምንም እንኳን በገቢ ግብር አዋጁ የተለየ ሰንጠረዥ ውስጥ የተካተቱ ባይሆንም፣
በገቢ ግብር ሕጉ መሰረት ዕቃዎች ወደ አገር በሚገቡበት ጊዜ እና በሀገር ውስጥ ከሚፈፀሙ ክፍያዎች ላይ ግብር
እንዲቀነስ ይደረጋል፡፡ በዚህም መሰረት በንግድ ሥራ እንቅስቃሴ ላይ የተሰማራ እና የንግድ ሥራ ገቢ የሚያገኝ ግብር
ከፋይ ለንግድ የሚውሉ ዕቃዎችን ወደ አገር ሲያስገባ የዕቃዎቹን የጉምሩክ ዋጋ፣ የመድህን አረቦንና የመጓጓዣ ወጪ
ላይ 3% የሚሰላ የንግድ ሥራ ግብርን በቅድሚያ እንዲከፍል ይደረጋል፡፡ በሌላ በኩል ማናቸውም ድርጅቶች፣
የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ውስጥ የዕቃ እና አገልግሎት ግዥዎች
በሚፈጽሙበት ወቅት ከሚከፍሉት ጠቅላላ ክፍያ ላይ 2% ግብር ቀንሰው የማስቀረት ኃላፊነት አለባቸው፡፡ የዕቃ
እና አገልግሎት አቅራቢዎቹ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና የታክስ መክፈያ ቁጥርን ማቅረብ የማይችሉ በሚሆንበት ጊዜ
ከሚከፈሉት ጠቅላላ ክፍያ ላይ 30% ግብር ይቀነስባቸዋል፡፡

ለ/ ቀጥተኛያልሆኑየታክስአይነቶች፡

በኢትዮጵያ የታክስ ሥርዓት ቀጥተኛ ያልሆኑ ታክሶች በመባል የሚታወቁት የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ተርን ኦቨር
ታክስ፣ ኤክሳይዝ ታክስ፣ የጉምሩክ ቀረጥ፣ ሱር ታክስ እና የማህበራዊ ልማት ቀረጥ ናቸው፡፡

የተጨማሪእሴትታክስ

በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 (እንደተሻሻለ) የተጨማሪ እሴት ታክስ ቀደም ብሎ የነበረውን
የሽያጭ ታክስ የተካ ሲሆን በምርት፣ ዕቃዎችን ወደ አገር በማስገባትና በስርጭት ሂደት ውስጥ በተጨማሪው እሴት
ላይ ብቻ የሚታሰብ እና በዕቃዎች እና አገልግሎቶች አቅርቦት ላይ ተፈፃሚ የሚሆን ዘመናዊ የታክስ አይነት ነው::
ማንኛውም የንግድ ሥራ እንቅስቃሴን የሚያከናውን እና አመታዊ የሽያጭ መጠኑ ከአንድ ሚልዮን ብር በላይ የሆነ
ግብር ከፋይ የተጨማሪ እሴት ታክስን ከሚያቀርብላቸው ሰዎች በመሰብሰብ ለመንግሥት ገቢ የማድረግ ኃላፊነት
አለበት፡፡

የተጨማሪ እሴት ታክስ ሁለት አይነት መጣኔዎች አሉት:: እነሱም 15 ከመቶ መደበኛ መጣኔና ዜሮ ከመቶ መጣኔ
ሲሆኑ በዜሮ መጣኔ የሚስተናገዱት ኤክስፖርት የሚደረጉ እቃዎችና አገልግሎቶች እንዲሁም ለብሔራዊ ባንክ
የሚቀርብ የወርቅ ምርት ነው፡፡ እንደ ፋይናንስ አገልግሎት፣ በሐይማኖት ተቋማት የሚሰጡ ከአምልኮት ጋር

3/5
የተያያዙ አቅርቦቶች፣ የሕክምና አገልግሎት፣ ለሰብዓዊ እርዳታ የሚቀርቡ ዕቃዎች እና ሌሎች እቃዎች እና
አገልግሎቶች በአዋጁ መሰረት ከታክሱ ነፃ የተደረጉ ሲሆን የገንዘብ ሚኒስቴር ሌሎች ዕቃዎችን በመመሪያ ከታክሱ
ነፃ የማድረግ ሥልጣን አለው፡፡

ተርንኦቨርታክስ

ተርን ኦቨር ታክስ በአገር ውስጥ በሚከናወን የዕቃ ወይም የአገልግሎት ሽያጭ ወቅት በየደረጃው የሚጣል፤ በአዋጅ
ቁጥር 308/1995 (እንደተሻሻለ) የተደነገገ የታክስ አይነት ነው፡፡ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ያልተመዘገበ ወይም
ዓመታዊ የንግድ እንቅስቃሴ መጠኑ ከአንድ ሚሊዮን ብር በታች የሆነ ማንኛውም በንግድ ሥራ ላይ የተሰማራ ሰው
ወይም ድርጅት በአገር ውስጥ ከሚሸጣቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች ላይ የተርን ኦቨር ታክስ ሰብስቦ ለሚመለከተው
የታክስ ባለሥልጣን ገቢ ያደርጋል፡፡

ዕቃዎችን የሚያቀርብ ግብር ከፋይ 2% የታክስ መጣኔ ታክስ የማስከፈል ግዴታ ያለበት ሲሆን፣ በአገር ውስጥ የሥራ
ተቋራጭ፣ የእህል ወፍጮ ቤት፣ የትራክተር እና ኮምባይን ሀርቨስተር አገልግሎትን የሚሰጡ ግብር ከፋዮች 2% እና
ሌሎች አገልግሎቶችን በአገር ውስጥ የሚሰጡ ግብር ከፋዮች 10% ታክስ የመሰብሰብ እና ከገዥው የተሰበሰበውን
ታክስ ለመንግስት ገቢ የማድረግ ግዴታ አለባቸው፡፡ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የተደረጉ ሁሉም የዕቃ እና
አገልግሎት አቅርቦቶች ከተርን ኦቨር ታክስ ነፃ የተደረጉ ሲሆን የገንዘብ ሚኒስቴር ሌሎች ዕቃዎችን በመመሪያ
ከታክሱ ነፃ የማድረግ ሥልጣን አለው፡፡

የጉምሩክቀረጥ

በአዋጅ ቁጥር 859/2006 (እንደተሻሻለ) የጉምሩክ ቀረጥ ማለት በገቢና ወጪ ዕቃዎች ላይ የሚጣልና የሚሰበሰብ
ቀረጥ ነው፡፡ በሕግ ነፃ የተደረጉ ካልሆኑ በቀር ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ሁሉም እቃዎች የጉምሩክ ቀረጥ የመክፈል
ግዴታ አለባቸው፡፡ በኢትዮጵያ ያለው ከፍተኛ የጉምሩክ ቀረጥ መጣኔ 35% ሲሆን ዝቅተኛው 0% ነው፡፡ ከምስራቅ
እና ደቡብ አፍሪካ የጋራ ገበያ (COMESA) አባል ሐገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ዕቃዎች አነስተኛ የቀረጥ መጣኔ
ተፈፃሚ ይሆንባቸዋል፡፡

የኤክሳይዝታክስ

በአዋጅ ቁጥር 1186/2012 (እንደተሻሻለ) የኤክሳይዝ ታክስ በአገር ውስጥ በሚመረቱና ከውጭ ወደ አገር በሚገቡ
የተወሰኑ ምርቶች /ዕቃዎች/ ላይ የተጣለ የታክስ ዓይነት ነው፡፡ ታክሱ ተፈፃሚ የሚሆነው በዕቃዎችና አገልግሎቶች
ላይ ሲሆን ዋነኛ ትኩረቱም የቅንጦት ዕቃዎች፣ የሕብረተሰቡን ጤና የሚጎዱ እና የማህበራዊ ችግር የሚያስከትሉ
እንዲሁም መሠረታዊ በመሆናቸው ምክንያት የገበያ ተፈላጊነታቸው በማይቀንስ ዕቃዎች እና አገልግሎቶች ነው፡፡

በኢትዮጵያ አገር ውስጥ በሚመረቱ እና ከውጭ በሚገቡ የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው እቃዎች ላይ እንዲሁም
በቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎቶች ላይ የኤክሳይዝ ታክስ ተጥሏል፡፡ የታክስ መጣኔው ልክ እንደየእቃው/አገልግሎቱ
አይነት ከ5% እስከ 500% ይደርሳል፡፡

የሱርታክስ

ሱር ታክስ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ እቃዎች ላይ የሚጣል ተጨማሪ ቀረጥ ነው፡፡ በሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ
ቁጥር 133/1999 መሠረት ከመሬት ማዳበሪያዎች፤ ነዳጅ፤ የብረታ ብረት ቅባቶች፣ የጭነትና የሕዝብ ማመላለሻ
ተሽከርካሪዎች እና ለተለየ አገልግሎት የሚውሉ ተሽከርካሪዎች፣ አውሮፕላኖች፣ የአየር መንኮራኩሮችና የጠፈር

4/5
መንኮራኩሮች እና የእነዚህ ክፍሎች እንዲሁም የካፒታል (የኢንቨስትመንት) እቃዎች በስተቀር ወደ ኢትዮጵያ
በሚገቡ ሁሉም እቃዎች ላይ ሱር ታክስ ተጥሏል፡፡ በዚህም መሰረት ወደ አገር ውስጥ በሚገቡ እቃዎች ላይ 10%
ተጨማሪ ቀረጥ እየተጣለ ይሰበሰባል፡፡

የማህበራዊልማትቀረጥ

ወደ አገር በሚገቡ እቃዎች ላይ የማህበራዊ ልማት ቀረጥ ለማስከፈል የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር
519/2014 አንቀጽ 2 በሕጉ መሰረት ነፃ ከተደረጉ ዕቃዎች በስተቀር በጉምሩክ ታሪፍ ደንብ የተዘረዘሩት
ማናቸውም እቃዎች ወደ አገር በሚገቡበት ጊዜ የማህበራዊ ልማት ቀረጥ 3% ይከፈልባቸዋል፡፡ የቀረጡ አላማ
ለትምህርት፣ ለሥልጠና እና ለጤና ተቋማት መልሶ ማቋቋሚያ እና ግንባታ እና ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶችን
ማስፋፊያ የሚውል ነው፡፡ በዚህም መሰረት ማንኛውም ዕቃ ወደ አገር የሚያስገባ ሰው ቀረጡን መክፈል
ይጠበቅበታል፡፡ ከማህበራዊ ልማት ቀረጥ ነፃ የተደረጉትን ዕቃዎች በተመለከተ የዲፕሎማቲክ ልዩ መብት ያላቸው
ሰዎች እና ድርጅቶች እንዲሁም ወደ አገር በሚገቡ ዕቃዎች ላይ የተጣለው የተጨማሪ ቀረጥ የሚከፈልባቸው
እቃዎች ናቸው፡፡

5/5

You might also like