5

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 7

'ቅኔ'፡ማለት፡'ቀነየ'፡ገዛ፡ካለው፡ግስ፡የተገኘ፡ጥሬ፡ዘር፡ነው።ወይም፡'ቀነየ'፡ገዛ፡የሚለውን፡አንቀጽ፡ያስገኘ፡ጥሬ፡ዘር፡

ነው።ፍችውም፡'መገዛት'፡ማለት፡ነው።'ቁሙ፡እንከ፡ወኢትሑሩ፡ዳግመ፡ውስተ፡አርዑተ፡ቅኔ'፡እንዲል፡

(ገላ.፥5፥1)፥ቅኔ፡ማለት፡መገዛት፡ማለት፡ከኾነ፥ይህ፡ከያንዳንዱ፡ሰው፡በየጊዜው፡የሚመነጨው፡እ ንግዳ፡ድርሰት፡

ስለ፡ምን፡ቅኔ፡ተባለ፡ቢሉ፥ፍጡር፡ዐዲስ፡ዐዲስ፡ምስጋና፡እየደረሰ፡በማቅረብ፥ለፈጣሪው፡መገዛቱን፡የሚገልጥበት፡

ስለ፡ኾነ፡ነው።ለፍጡራን፡የሚደረሰውም፡ቅኔ፥ቅኔው፡የሚደረስለት፡ፍጡር፡ከቅኔ፡ደራሲው፡በላይ፡ክብር፡ያለው፡

መኾኑን፡የሚገልጽ፡ድርሰት፡ስለ፡ኾነ፥መገዛትን፡ከማመልከት፡የራቀ፡አይደለም።አንድም፥ሕዋሳተ፡

አፍኣን፣ሕዋሳተ፡ውስጥን፡ለኅሊና፡አስገዝቶ፥በተወሰነ፡ቍርጥ፡ሐሳብ፡የሚታሰብ፡ስለ፡ኾነ፥ቅኔ፡

ተብሏል።ይኸውም፡ሊታወቅ፥በቅኔ፡ምስጢር፡ልቡ፡የተነካ፡ሰው፥ቅኔ፡በሚያስብበት፡ጊዜ፥እፊቱ፡የሚደረገውን፡

ነገር፡እያየ፣እየሰማ፥አይሰማም።ከዚህም፡የተነሣ፥በጎንደሮች፡መንግሥት፥የቍስቋሙ፡አለቃ፡በእልፍኙ፡ውስጥ፡

ምንጣፉን፡አስነጥፎ፥መጻሕፍቱን፡እፊቱ፡ደርድሮ፥ለበዓለ፡ቍስቋም፡የሚቀኘውን፡ቅኔ፡ሲያወጣና፡

ሲያወርድ፥ንጉሡ፡ዘው፡ብለው፡ቢገቡ፥ልቡ፡ተመሥጦ፥ሊያያቸው፡ባለመቻሉ፥ቀና፡ብሎ፡ሳያያቸው፡ቁጭ፡እንዳለ፡

ቀረ።ንጉሡም፥ነገሩ፡ደንቋቸው፥ፍጻሜውን፡ለማየት፥ርሱን፡ዐልፈው፡ዐል ጋ፡ላይ፡ተቀምጠው፥ኹኔታውን፡

ይመለከቱ፡ዠመር።ብዙ፡ሰዓት፡ካሳለፈ፡በዃላ፥አእምሮው፡ሲመለስ፥ንጉሡ፡ተቀምጠው፡ቢያይ፥ደንግጦ፡ተነሥቶ፡

እጅ፡ነሣ።ንጉሡም፦ምነው፧ምን፡ኾነኽ፡ነው፧ቢሉት፦ጃንሆይ፥ቍስቋምን፡ያኽል፡ደብር፡አምነው፡

ሾመውኛል፤ለበዓል፡የተሰበሰበው፡ሰው፡አለቃው፡ምን፡ይናገር፡ይኾን፧እያለ፡ ዐይን፡ ዐይኔን፡ ሲያየኝ፥ ያልኾነ፡ ነገር፡

ቢሰማ፡ ደብሩን፡ አዋርዳለኹ፥ ጃንሆይንም፡ አሳማ ለኹ፥እኔም፡አፍራለኹ፡ብዬ፥ቅኔ፡እቈጥር፡ነበር፡አለ፡

ይባላል።አንድም፥ቅኔ፡ማለት፥'ተቀንየ'፡ሙሾ፡አወጣ፥ግጥም፡ገጠመ፥አራቆ፡

ተናገረ፥አዜመ፥አንጐራጐረ፥መራ፥ዘፈነ፡ካለው፡የወጣ፡ጥሬ፡ዘር፡ነው።ስለዚህ፥ቅኔ፡ማለት፥ባጪሩ፥ጠቅላላ፡

ሎ ፥ም ስጢ ር፡
ትርጕሙ፥ሰው፡ከራሱ፡አንቅቶ፡ለእግዚአብሔር፡ዐዲስ፡ምስጋና፡ላቅርብ፡ባለ፡ጊዜ፥ምሳሌ፡መስ፟ሎ፥ምስጢር፡ስ፟

ት፡የሚ ገልጽ በት፥የዕው ቀቱን፡ደረጃ፡


አሻሽሎ፡ግጥም፡በመግጠም፥የልቡናውን፡ዕውቀት፣የአእምሮውን፡ርቀ፟ት፡የሚገልጽበት፥የዕውቀቱን፡ደረጃ፡ቀ፟

የሚያስታውቅበት፥የሰሚንም፡ልቡና፡የሚያነቃቃበትና፡የሚያራቅቅበት፡ድርሰት፡ማለት፡ነው።ከዚህም፡

የተነሣ፥መጋቢ፡መርሻ፡ኀይሉ፡የተባሉ፡የዲማው፡ባለ፡ቅኔ፦የሰውን፡ዕውቀቱን፡መጠን፡የማውቀው፡በቅኔው፡ነው፡

ይሉ፡ነበር፡ይባላል።

አለቃ፡አፈ፡ወርቅ፡ዘውዴ
የቅኔ፡ጥበብ፡አዠማመርና፡አረማመድ

("የግእዝ፡ቅኔያት፤የሥነ፡ጥበብ፡ቅርስ"፥ብርሃንና፡ሰላም፡ማተሚያ፡ቤት፥ዐዲስ፡አበባ፥፲፱፻፹፡ዓ.፡ም.፥ገጽ፡15-29።)

በስድስተኛው፡ምእት፡ዓመት፥ባፄ፡ገብረ፡መስቀል፡ዘመነ፡መንግሥት፡የተነሣው፡ያሬድ፥በግእዝ፡መጻ ሕፍት፡

ምስጢር፡የተራቀቀ፡ሊቅ፡በመኾኑ፥ከመጻሕፍት፡ጠቅሶ፥ከራሱም፡አነቅቶ፡ዐያሌ፡መዝሙራትን፡ ከነዜማቸው፡

ደርሷል።እንዚህም፡ምዝሙራት፡ፆመ፡ድጓ፥ምዕራፍ፥ድጓ፥በተባሉ፡መጻሕፍት፡ሰፍረው፥ከ ትውልድ፡ወደ፡

ትውልድ፡ሲተላለፉ፡እስካኹን፡ደርሰዋል።

የያሬድ፡መዝሙር፡ድርሰት፡በግጥም፡ረገድ፥አብዛኛውን፡ቤት፡አልባ፡ቢኾንም፥ዐልፎ፡ዐልፎ፡ቤት፡እ የመታ፡

ከስድ፡ንባብነት፡ወደ፡ጕትነት፡ያመራ፥በሰምና፡በወርቅ፡የተመሰጠረ፥በኹለትም፡በሦስትም፡ ዐምስት፡ቤት፡

የተወሰነ፡ኾነ።ቢኾንም፥ኺደቱ፡የቅኔን፡መንገድ፡የተከተለ፡ነው።

ባት ፡አልባ፡ቅ ኔዎ ች ና፡ቤተ ኛ ፡ቅ ኔዎ ች ፥ ኹለቱ ም ፥ በያ ሬድ፡ድርሰት ፡ው ስጥ ፡ይገኛ ሉ ።ለቤት ፡አልባው ፡ ቅኔ፡ምሳሌ፡

የሚከተለውን፡ጥቅስ፡ከድጓ፡ይመለከቷል።

1.፡

ወብዙኃን፡ኖሎት፡መጽኡ

ወሰእኑ፡ከሢቶታ፡ለእብን፡እምአፈ፡ዐዘቅት

እስከ፡ይመጽእ፡ያዕቆብ።

ወከማሁመ፡መጽኡ፡ብዙኃን፡ነቢያት

ወስእኑ፡ከሢቶታ፡ለጥምቀት

እስከ፡ይመጽእ፡ዐቢይ፡ኖላዊ።

የዚህና፡የሚለጥቁት፡የግእዝ፡ጥቅሶች፥ያማርኛ፡ትርጕማቸው፥በዚህ፡ጽሑፍ፡መጨረሻ፡በየተራ፡ቍጥ

ራቸው፡ለብቻው፡ሰፍሯል።
በቤተኛው፡የያሬድ፡ቅኔ፡ምሳሌ፥አኹንም፡ከጾመ፡ድጓ፡እንጠቅሳለን።

2.

ሀገረ፡ክርስቶስ፡ሐዳስ፡ንድቅ፡

ዘበውስቴታ፡የኀድር፡ጽድቅ፡

ጻድቃን፡ኪያሃ፡አብደሩ፡እምወርቅ።

እንዲሁም፥አርያም፡ከተባለው፡ክፍል፡የሚከተለው፡ሊጠቀስ፡ይችላል፤

3.

እምፈልፈለ፡ብዕል፡ገነተ፡ንጉሥ፡ሠቀዩ

እምነቅዐ፡ወንጌል፡ገራህተ፡አርወዩ።

4.

በፄወ፡መለኮት፡ቀሰሙ፡ዓለመ፡

ውስተ፡ቤተ፡መርዐ፡አውኀዙ፡ሰላመ፡

ሐዋርያት፡እምሕዝብ፡አእተቱ፡ፀራዌ፡ርጉመ።
5.

በቅድስና፡ወበንጽሕ፡ምኵራበ፡ሥጋሁ፡ነደቀ፡

በሠረገላ፡ሉዓሌ፡ተመጥቀ፡

ኤልያስ፡ክቡር፡እምዓለም፡ዘርኅቀ።

ከዚህ፡በላይ፡ላይነት፡ያኽል፡የተጠቀሰው፡የያሬድ፡ቅኔ፥ቤተኛም፡ቢኾን፥ቤት፡አልባም፡ቢኾን፥ጕት ፡ግጥም፡

ነው።(ጕት፡ማለት፡ጐታታ፥ያልተጠቃለለ፥በመደበኛ፡የቅኔ፡ሐረግ፡አሰካክ፡ያልተቀናበረ፡ማለት፡ነው።)፡ኾኖም፥በዚህ፡

በታላቅ፡ሥራው፡በዜማው፡ድርሰት፡ውስጥ፡ቅኔን፡በማስገባቱና፡በማዋሐዱ፡የቅኔን ፡ሟያ፡

አጐላው።ርግጥ፥ከርሱ፡በኋላ፡የተነሡ፡ሊቃውንት፡የያሬድን፡ፈለግ፡ተከትለው፥ርሱ፡የዠመረ ውን፡ሥራ፡

አስፋፍተዋል።ይህ፡ግን፡ያሬድን፡ከቅኔ፡ቀደምት፡መሥራቾች፡ዋነኛው፡ከመኾን፡አያግደው ም።

አንድ፡የድሮ፡ሊቅ፡ስለ፡ያሬድ፡የደረሱት፡ዐጪር፡ዘይእዜ፡ቅኔ፡አለ፤

ተትሕተ፡ያሬድ፡ዘኢተትሕተ፡

ለቅኔያቲሁ፡ደቂቅ፡እስመ፡ኢሐነጸ፡ቤተ።

ሊቁ፡በዚህ፡ቅኔያቸው፥ያሬድ፡ከርሱ፡በኋላ፡እንደተነሡት፡እንደ፡ደቀ፡እስጢፋና፡እንደ፡ተ ዋነይ፡

ቅኔዎች፡ያለ፡ቅኔ፡ባለመድረሱ፡ብቻ፥"የያሬድ፡ቅኔዎች፡ቤት፡አልባ፡ናቸው"፡ለማለት ፡ሞክረዋል።ነገር፡

ግን፥የነደቀ፡እስጢፋና፡የነተዋነይ፡ቅኔያትም፡ቢኾኑ፥ከነርሱ፡በኋላ፡ ከተነሡት፡ሊቃውንት፡ቅኔያት፡

የተለዩ፡መኾናቸው፡አይዘነጋም።ስለዚህ፥"ያሬድ፡ለቅኔያቱ፡ቤ ት፡አልሠራም"፡

አያሠኝም።ባይኾን፥ያሬድ፡ከዜማ፡ደን፡ገብቶ፡ለቅኔ፡ቤት፡መሥሪያ፡የመዘዘው ፡ሐረግ፡ረዥምና፡

ቀጥተኛ፡አይደለም፥በሐረጉም፡የተሠራው፡ቤት፡ጠባብ፡ነው፡ቢባል፡እንኳ፡ ያስኼዳል።

ቅኔ፡ከጕት፡ግጥምነት፡ወደ፡ሙሉ፡ቤት፡ግጥምነት፡በመሸጋገር፡አስፈላጊው፡የተሟላለት፥ትም ህርት፡

ቤት፡የተቋቋመለት፥ጉባኤው፡የተስፋፋለት፡በዮሐንስ፡ገብላዊ፡መሪነት፡ነው።ዮሐንስ ፡ገብላዊ፡
በዋድላ፥ገብሎን፡ወይም፡ገብላት፡በተባለች፡ቀበሌ፡የተወለደ፡ታላቅ፡ሊቅ፡በመኾ ኑ፥በትውልድ፡

ቦታው፡"ዮሐንስ፡ገብላዊ፡ተብሏል፤በፈላስፋነቱ፡"ዮሐንስ፡ዘፍልሱፍ"፡ተብሏል ።ባፄ፡ዘርዐ፡ያዕቆብ፡

ዘመነ፡መንግሥት፡(፲፬፻፳፯-፲፬፻፷)፡የነበረ፡ነው።

ዮሐንስ፡ገብላዊ፡የያሬድን፡ቅኔዎች፡መርምሮ፡የያሬድን፡ፈለግ፡ተከትሎ፥ቅኔን፡በሰምና፡ወ ርቅ፡

ለማጕላት፥ምስጢሩን፡ለማርቀቅ፥መንገዱን፡ለማስፋት፥ቤቶቹን፡ለመሙላት፡በቅቷል።በዚ ያን፡

ዘመን፥ያፄ፡ይኩኖ፡አምላክ፡ከተማ፡ክልሏን፡በሚዋሰኑ፡ታቦርና፡አርሞንኤም፡በተባሉ፡ ያማራ፡

ሳይንትና፡የቦረና፡ኹለት፡ተራሮች፡መካከል፡ነበር፡አቀማመጧ።ዮሐንስ፡ገብላዊ፡እዚ ያች፡

ተቀምጦ፥የቅኔን፡ምስጢር፡አፍታታ፥አራቀቀ፤ዕውቀቱን፡አደላደለ፤የቅኔ፡ትምህርቱን፡ ለነወልደ፡

ገብርኤል፡አስተማረ።

ባፄ ፡ዘርዐ፡ያ ዕቆ ብ፡ዘመ ን፥ በዮሐ ንስ፡ገብላዊ ፡ጊ ዜ፡የተ ደረሱ ፡ቅ ኔያ ት ፡እኒህን፡የመ ሰሉ ፡ ነበሩ፦

በመዝሙር፡እቀኒ፡በዘዐሠርቱ፡አውታር፡

ለዘርዐ፡ያዕቆብ፡ኄር፡ዕበዮ፡በከመ፡ያሬድ፡መምህር።

ይህ፡ጉባኤ፡ቃና፥በስንኙ፡አቀነባበርና፡በሐረጉ፡አሰካክ፡እንዳኹኑ፡ጊዜ፡ጉባኤ፡ቃና፡ነው ።የሚከተለው፡

ዕጣነ፡ሞገር፡ግን፡ካኹኑ፡ዘመን፡ዕጣነ፡ሞገር፡ጋራ፡አንድ፡አይደለም፦

ሃሌ፡ሉያ፥ሃሌ፡ሉያ፥ሃሌ፡ሉያ፥

ቃየል፡አበሰ፡እንበይነ፡ሉድ፡በላዕለ፡አኁሁ፡ቀኒኦ፤

ሶምሶን፡ተሠግረ፡በደሊላ፡ምስጢረ፡ነገሩ፡ኅቡአ፡ኅቢኦ።

ምስለ፡ጸጕረ፡ርእሱ፡ላጸየት፡ጽንዖ፡

ብፁዕ፡እምአንስት፡ዘጐየ፡ተንሢኦ፡
ለንጉሥነ፡ዘርዐ፡ያዕቆብ፡ከመ፡ይርድኦ።

ይህ፡የዱሮ፡ዕጣነ፡ሞገር፥ቤቱ፡ዐምስት፡በመኾኑ፥ካኹኑ፡ዘመን፡ባለሰባት፡ቤት፡ዕጣነ፡ሞገር፡በኹ ለት፡ቤት፡

ያንሳል።ይህ፡የሚያመለክተው፡የቅኔ፡ጥበብ፡ከዘመን፡ወደ፡ዘመን፡ለውጥ፡እያገኘና፡እያ ደገ፡የኼደ፡እንጂ፥ባንድ፡

ጊዜ፡ተስተካክሎ፡የተገኘ፡አለመኾኑን፡ነው።

የዮሐንስ፡ገብላዊ፡ደቀ፡መዝሙር፡የኾነው፡አባ፡ወልደ፡ገብርኤል፡ለሰምረ፡አብ፡(ሰምረ፡ክርስቶስ)፡

አስተማረ።በዐፄ፡በእደ፡ማርያም፡ዘመነ፡መንግሥት፡(ካ፲፬፻፷፡ዓ.፡ም.፡እስካ፲፬፻፸፡ዓ.፡ም.)፡ሰምረ፡አብ፡ቅኔ፡

ሲያስተምር፥ርሱና፡ንጉሥ፡በእደ፡ማርያም፡በቅኔ፡ጥበብ፡የተነሣ፡ተጣሉ።የቅ ኔው፡መንገድ፡ለንጉሡ፡እንግዳ፡

ስለ፡ኾነበት፥ንጉሡ፡የቅኔውን፡አነጋገር፡ከድንፋታ፡ቈጥሮ፥ቅኔው ን፡አቃለለው፤እንደ፡መቀባጠር፡አድርጎ፡

ተመልክቶት፡የሰመረ፡አብን፡ሟያ፡አኰሰሰበት፤የመምሩንም ፡ያባ፡ወለድ፡ግብርኤልን፡ቅኔ፡ዘራፊነት፡

ነቀፈበት።«አንተ፡ከነመምህርኽ፡እንዲያው፡ትቀባጥራለ ኽ፡እንጂ፥ከሌላ፡ከማን፡ዘንድ፡አግኝተኸዋል፧»፡

አለው።

ሰምረ፡አብ፡ግን፡ለንጉሡ፡በጎ፡ቃል፡መልሶ፥«እንዲህ፡ካልኽ፥ኹለታችንም፡ሱባኤ፡እንግባ፤ያን፡ጊ ዜ፥ቅኔ፡ደገኛ፡

ትምህርት፡ስለ፡መኾኑ፥ምስጢር፡ይገለጥልናል።»፡አለው።ኹለቱም፡ለየብቻቸው፡ሱባ ኤ፡ገቡ።በሱባኤ፡

ሳሉ፥ለንጉሡ፡ምስጢር፡ተገለጠለትና፥እንደ፡ቅኔ፡መምህሩ፡እንደ፡ሰምረ፡አብ፡ኹ ለት፡ቤት፡ቅኔ፡ዘረፈና፡ተቀኘ፡

ይባላል።ቅኔውም፡የሚከተለው፡ነው፤

ድኅረ፡ተሰብረ፡አጽንኦ፡ለሰብእናነ፡ልሕኵት፡

ለብሓዊ፡ክርስቶስ፡በማየ፡ሐዲስ፡ጥምቀት።

ንጉሥ፡በእደ፡ማርያም፡ይህን፡ቅኔ፡የዘረፈበት፡ቀን፡የቃና፡ዘገሊላ፡ዕለት፡ነበርና፥በዚህ ፡ሳቢያ፥የቅኔው፡

ስም፡"ጉባኤ፡ቃና"፡ተባለ፡ይባላል።

"ዘረፋ"፡ማለት፥አልቃሾችና፡ዘፋኞች፡ሳያወጡና፡ሳያወርዱ፡በቱማታ፡(በፍጥነት)፡እንደሚገጥሙት፡

ግጥም፡ቅኔን፡ለተቀባይ፡(ከፍ፡ባለ፡ድምፅ፡ለሚያሰማ)፡መንገር፡ነው።አፍጣኝ፡ዘራፊ፡ኹለትም፡
ሦስትም፡አራትም፡ተማሪዎች፡(አዚያሚዎች)፡አቁሞ፥ለዅሉም፡በተራ፡ልዩ፡ልዩ፡ቅኔያትን፡

ያቀብላል።እንደ፡መምህር፡ሰረገላ፡ብርሃን፥ ዳተኛ፡ዘራፊ፡ግን፡ሐሳብ፡ማውጣትና፡ማውረድ፡

ስላለበት፥ካንድ፡ተቀባይ፡አያልፍም።

ሰመረ፡አብ፡ለልሄብ፥ልሄብ፡ለኤልያብ፥ኤልያብ፡ለተዋናይና፡ለደቀ፡ወልደ፡ማርያም፡አስተማ ረ።ከዚህ፡

በኋላ፥መንግሥት፡ታወከና፡ግራኝ፡ተነሣ።ድድቅ፡ወልደ፡ማርያም፡በዳውንት፡(ጎንደር)፡የጨረቃ፡

እሚባል፡ቀበሌ፡ገባ፤ተዋነይ፡በጣና፡ባሕር፡ውስጥ፥ደቀ፡እስጢፋ፡እሚባል፡ደሴት ፡ገብቶ፡ተቀመጠ።

You might also like