7 IV Completed

You might also like

Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 8

የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

I. አጠቃላይ መግለጫ

የመስሪያ ቤቱ ስም የሥራ መደቡ መጠሪያ የሥራ ዘርፍ/የሥራ ሂደት

ከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የከተማ አረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሠረተ የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት
ልማት ስታንዳርድ ዝግጅት ባለሙያ IV ስታንዳዳይዜሽን ዴስክ

የቅርብ ኃላፊ የሥራ መደብ /ተጠሪነት የሥራው ደረጃ የሥራው ኮድ

የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ


ልማት ስታንዳዳይዜሽን ዴስክ ኃላፊ

መስሪያ ቤቱ የሚገኝበት ቦታ

II. የሥራ መደቡ ዋና ዓላማ፣ ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት

2.1. የሥራ መደቡ ዓላማ፡-

የአረንጓዴና የአካባቢ ጥበቃ መሠረተ ልማት ዘርፍ የሚመራባቸውን ስታንዳርዶችን እንዲሁም የማስፈጸሚያ ሰነዶች በጥናት
በማዘጋጀት፣ በማሻሻል፣ ተግባራዊነታቸውን በመከታተል፣ ድጋፍ በማድረግ እና ሰነዶችን በማስተዋወቅ፣ በማስፋፋትና ስልጠናዎች
በመስጠት ዘላቂነት ያለውና ደረጃውን የጠበቀ የከተማ መሠረተ ልማት አገልግሎት እንዲሰጥ ማድረግ ነው፡፡
2.2.ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት

ውጤት 1፡ በአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማትና ስታንዳርድ ላይ የተለያዩ ጥናቶች ማድረግ፣

 የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማቶች አስመልክቶ በሚዘጋጁ የፖሊሲና የስትራቴጂ ሰነዶች ሲቀረጹ ሐሳብ ያመነጫል፣
መነሻ ሰነድ ያቀርባል፣ በዝግጅቱ ይሳተፋል፣
 የከተማ አረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት በተመለከተ የፖሊሲ ግብአትና የፖሊሲ አፈጻጸም ግምገማ ጥናትና ምርምሮች ያደርጋል፣
ለኃላፊ ያቀርባል፣
 የከተማ የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት ፖሊሲና ስትራቴጅና መተግበሪያ አማራጮች ለይቶ ያቀርባል፣ ለተግባራዊነታቸውም
ለክልሎች፤ ለከተሞችና ለግሉ ዘርፍ ድጋፍ ያደርጋል፡፡
 የተዘጋጁ የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማቶች ስታንዳዶችን ክፍተቶች በጥናት ይለያል፣
 የአዳዲስ ስታንዳርድ ፍላጎት ለማጥናት የሚያስችሉ ቼክሊስቶችና የዳሰሳ ጥናት ማንዋሎች ለዘርፉ ተዋንያንና ባለድርሻ አካላት
እንዲዳረሱ ያደርጋል፣

1
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

 የአዲስ ስታንዳርዶችን ወይም ማሻሻያ ፍላጎት ለመዳሰስና ግብዓቶች ለማሰባሰብ የሚውሉ መጠይቆችና ቼክሊስቶች ያዘጋጃል፣ በስራ ላይ
ያውላል፡፡

 በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎች ላይ ያለዉን የእዉቀት፣ ክህሎትና አመለካከት ክፍተት የመለየት ስራ ይሰራል፣

 በሰነዱ ላይ የተሰጡ ግብረ መልሶች እንዲሰባሰቡ እና ግብዓቶቹ እንዲደራጁ በማድረግ በመተንተንና በማጥናት ዘርፉ
የሚፈልጋቸውን ህግጋትን ይለያል፤
ውጤት 2፡- የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት ሰታንዳርድና ሌሎች ሰነዶች ያዘጋጃል፣

 የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት ስታንዳርድ ዝግጅት ለማካሄድ የሚያስችል የስታንዳርድ አዘገጃጃት አሰራር ይቀርጻል፣
ያዘጋጃል፣
 የሀገርና የዓለም አቀፍ የስታንዳርድ ስርዓትን በመፈተሸ ከሀገራዊ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ልምድ ይቀምራል፣
 የከተሞች ፈርጅ መሰረት በማድረግ የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት (ደረጃ ዘመናዊ ቄራ፣ የእሳት አደጋ መከላከያ
ጣቢያ፣ዘላቂ ማረፊያ፣ የተሸከርካሪ ማቆሚያ፣ ጋራዥ፣ መናኸሪያ፣ የገበያ ቦታዎች፣ፓርኮች፣መናፈሻዎች፣የመንገድ ዳርቻ፣
አካፋይና አደባባዮች፣ ተፋሰሶችና ሌሎች አረንጓዴ መሠረተ ልማቶች፣የቆሻሻ ማሰባሰቢያ፣መለያ፣ማቀነባበሪያ እና ማስወገጃ
ቦታዎች…) ስታንዳዶች ያዘጋጃል፣
 በተዘጋጁ የአረንጓዴና የአካባቢ መሰረተ ልማቶች ላይ ከባለድርሻ አካላት እና ከፈጻሚና አስፈጻሚ አካላት ጋር ይመክራል፣ ግብዓት
ያካትታል፣
 በውጭ አቅም ለሚዘጋጁ የስታንዳርድ ቴክኒካል ሰነዶች ዝግጅት አማካሪ ለመቅጠር የሚያስችል ቢጋር ያዘጋጃል፣
 በአማካሪ ተዘጋጅተው የሚቀርቡ የስታንዳርድ ሰነዶችን ይገመግማል፣ ውጤቱን ያቀርባል፣ ግብዓት ያካትታል፣
 የተዘጋጁና ትግበራ ላይ ያሉ የተለያዩ የአረንጓዴ መሰረተ ልማት ስታንዳዶች ክፍተት በመለየት ይከልሳል፣
 በአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ ዎርክሾች ላይ ይሳተፋል፣ የወርክሾፖችን ውጤት ሪፖርት አዘጋጅቶ ያቀርባል፣
ውጤት 3፡ የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሠረተ ልማት ስታንዳዶች አተገባበር መከታተልና መደገፍ፣

 የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሠረተ ልማት ስታንዳዶችን አተገባባር ለመከታተል የሚያችል የክትትልና ድጋፍ አሰራር ያዘጋጃል፣

 በከተሞች አረንጓዴ መሰረተ ልማቶች ላይ የተሰማሩ አልሚዎች በተቀመጠዉ ስታንዳርድ መሰረት እያለሙ መሆናቸዉን ናሙና በመውሰድ
ይከታተል፣ ይደግፋል፣
 የተዘጋጁ ስታንዳርዶች በከተሞች ተግባር ላይ ሲውሉ ያስገኙትን ፋይዳ ይገመግማል፣ ይደግፋል፣ ማሻሻያ ሲያስፈልግ ያስፈጽማል፣

 በክልሎችና ከተሞች የሚተገበሩ አረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማቶችን በመስክና በመድረክ በመገኘት አተገባበራቸውን ይከታተላል፣
ይደግፋል፣
ውጤት 4 ፡- የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማቶች ስታንዳርዶች ማስተዋወቅ፣ የማስረጽ ስልጠናዎች ይሰጣል፣

 የአረንጓዴና የአካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት ላይ የስልጠና ሰነዶች ያዘጋጃል፣


 አዲስ በሚዘጋጁና በተዘጋጁ የስታንዳድ ሰነዶች ላይ ስልጠና ይሰጣል፣
 አዳዲስ የወጡና የተሻሻሉ ስታንዳርዶችን ለማስረጽ እንዲቻል ለስልጠና የሚያስፈልጉ ሰነዶችና ፅሑፎች በማዘጋጀትና
በማሰባሰብ ለሚመለከታቸው የዘርፉ ባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ይሰጣል፤

2
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

 በዳሰሳ ጥናትና የመስክ አፈፃፀም ክትትል ወቅት የስታንዳርዶችን ሰነዶች አተገባበር በክልሎች፣ከተማ አስተዳደሮችና ሌሎች
ባለድርሻ አካላት ከታዩ ጉድለቶች በመነሳት ክፍተቶቹን የሚሞላ የግምገማ ስልጠና ሰነድ በማዘጋጀት በአገር አቀፍ ወጥነት ያለው
የስታንዳርዶችን ትግበራ እንዲኖር የሚያስችል ስልጠና ይሰጣል፤

III. የሥራው ባህሪ መግለጫዎች

3.1. የሥራ ውስብስብነት


 ሥራው የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማቶች አስመልክቶ ለሚዘጋጅ ፖሊሲና ስትራቴጂ በጥናት ላይ የተመሰረተ ሐሳብ
ማመንጨትና መነሻ ሰነድ አዘጋጅቶ ማቅረብ፣ የከተማ የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት ፖሊሲና ስትራቴጅና መተግበሪያ ዝርዘር
አማራጮች ተንትኖ ማቅረብ፣ የተዘጋጁ የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት ስታንዳዶችን ክፍተቶች በጥናት ፈትሾ መለየትና
ማቅረብ፣ የአዲስ ስታንዳርዶችን ወይም ማሻሻያ ፍላጎት ለመዳሰስና ግብዓቶች ለማሰባሰብ የሚውሉ መጠይቆችና ቼክሊስቶች አዘጋጅቶ
ማቅረብ፣ የሀገርና የዓለም አቀፍ የስታንዳርድ ስርዓትን በመፈተሸ ከሀገራዊ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ልምድ መቀመር፣
የከተሞች ፈርጅ መሰረት በማድረግ የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት (ደረጃ ዘመናዊ ቄራ፣ የእሳት አደጋ መከላከያ
ጣቢያ፣ዘላቂ ማረፊያ፣ የተሸከርካሪ ማቆሚያ፣ ጋራዥ፣ መናኸሪያ፣ የገበያ ቦታዎች፣ ፓርኮች፣ መናፈሻዎች፣የመንገድ ዳርቻ፣
አካፋይና አደባባዮች፣ ተፋሰሶችና ሌሎች አረንጓዴ መሠረተ ልማቶች፣ የቆሻሻ ማሰባሰቢያ፣ መለያ፣ ማቀነባበሪያ እና ማስወገጃ
ቦታዎች…) ስታንዳዶች ማዘጋጀት፣ አማካሪ ለመቅጠር የሚያስችል ደረጃው የጠበቀ ቢጋር ማዘጋጀትና በአማካሪ ተዘጋጅተው
የሚቀርቡ የስታንዳርድ ሰነዶችን መገምገም፣ ግብረመልስ መስጠትና መካተተቱን መከታተል፣ በከተሞች አረንጓዴ መሰረተ ልማቶች
ላይ የተሰማሩ አልሚዎች በተቀመጠዉ ስታንዳርድ መሰረት እያለሙ መሆናቸዉን ናሙና በመውሰድ መከታተል፣ክፍተቶችን ለይቶ መፍትሔ
መስጠት፣ የተዘጋጁ ስታንዳርዶች በከተሞች ተግባር ላይ ሲውሉ ያስገኙትን ፋይዳ መገምገም፣ በአረንጓዴና በአካባቢ መሰረተ ልማት ዙሪያ
ግንዛቤ ለመፍጠር የሚያስችል በስታንዳዶችና በተለዩ ክፍተቶችንና መልካም ተሞክሮዎችን በማካተት የስልጠና ሰነዶች
ማዘጋጀት የሚጠይቅ ነው፡፡

 ሥራው በሚከናወንበት ወቅት የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማቶች ስታንዳድ ዝግጅት አዲስ ከመሆኑ አንጻር
የሚፈለገውን ስታንዳርድ ለማዘጋጃት በቂ መነሻ መረጃዎች የማይገኝ መሆኑ፣ የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ
ልማቶች የተለያዩ የዘርፉን ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎና ግብዓት ማቀናጀት የሚፈልግ መሆኑ፣ የሌሎች ሀገሮች ሊገኙ
የሚችሉም ተሞክሮዎች ከተጨባጭ ሁኔታ ጋር ያለመጣጣም፣ በአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት ስታንዳዶችን
ክፍተቶች ላይ የሚደረጉ ጥናቶች ዘርፈ ብዙ ክህሎት ያላቸውን ባለሙያዎች ተሳትፎ የሚጠይቅ መሆን፣ የሚዘጋጁ (ደረጃ
ዘመናዊ ቄራ፣ የእሳት አደጋ መከላከያ ጣቢያ፣ዘላቂ ማረፊያ፣ የተሸከርካሪ ማቆሚያ፣ ጋራዥ፣ መናኸሪያ፣ የገበያ ቦታዎች፣
ፓርኮች፣ መናፈሻዎች፣የመንገድ ዳርቻ፣ አካፋይና አደባባዮች፣ ተፋሰሶችና ሌሎች አረንጓዴ መሠረተ ልማቶች፣ የቆሻሻ
ማሰባሰቢያ፣ መለያ፣ ማቀነባበሪያ እና ማስወገጃ ቦታዎች…) ስታንዳዶች ጥልቅ ትንተናና ትኩረት የሚጠይቅ መሆኑ፣
በአማካሪዎች የሚዘጋጁ ስታንዳርዶች የውል ጊዜ ማስጠበቅና ግብረ መልሶችን ተካታትሎ እንዲካተቱ ማድረግ የሚጠይቅ
መሆኑ፣ የተዘጋጁ ስታንዳርዶች በከተሞች ተግባር ላይ ሲውሉ ያስገኙትን ፋይዳ ተንትኖ በመገምገም በጥናት ላይ የተመሰረተ ስትራቴጂያዊ
መፍትሔ ማቅረብ የሚጠይቅ መሆኑ፣ የተዘጋጁ ስታንዳርዶች ላይ ከባለድርሻ አካላት በቂ ግብረመልስ አለማግኘት፣
3
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

የሚሰጡ ስጠናዎችና የግንዛቤ መፍጠሪያዎች እኩል ግንዛቤ አለመፈጠር በሥራው ሂደት የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች
ናቸው፡፡

 እነዚህን ችግሮች ለስታንዳድ ዝግጅት የሚያስፈልጉ መረጃዎችን የተለያዩ ባለድርሻ አካትን ዩንቨርሲቶችን፣ ተቋትን ወዘተ በሰፊው
እንዲሳተፉ በማድረግ ማሰባሰብና አደራጅቶ በመጠቀም፣ በአረንጓዴና አካባቢ መሰረተ ልማት ስንታንዳርድ ዝግጅት ወቅት
ባለድርሻ አካላትን አጥርቶ በመለየት በመድረኮች፣ በሰነድ ዝግጅት ወዘተ እንዲሳተፉና ግብዓት እንዲሰጡ በማድረግ፣ የተለያዩ
ሀገራትን ተሞክሮን የሚመለከቱ ወቅታዊ ጽሁፎችን በማፈላለግ ከሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ጋር እንዲጣጣም ጥናት
በማድረግና በመቀመር፤ በስታንዳድ ዝግጅ ወቅት ለተለያዩ መሰረተ ልማች የሚስፈልጉ ባለሙያዎች ከተለያ
አካባቢዎች ለይቶ በማሰባሰብ በንቃት እንዲሳተፉ በማድረግ፣በአማካሪ የሚዘጋጁ ስታንዳርዶችን በጥልቀት በመፈተሸና
ወቅታቸውን ጠብቀው እንዲቀርቡ የስምምነት ውል እንዲከበር በማድረግ፣ የሚሰጡ ስጠናዎችና የግንዛቤ
ማስጨበጫዎችን ብዛትና ጥራት በማሳደግ፣ በመስክ በመገኘት ተግባረዊ ስልጠና በመስጠትና ልምድ በማካፈል
የሚፈጠረው ግንዛቤ ተቀራራቢ እንዲሆን በማስቻል የሚያጋጥሙ ችግሮችን መፍታት ይጠይቃል፡፡

3.2. ራስን ችሎ መስራት


3.2.1 ሥራው የሚከናወንበት አግባብ
 ሥራው ሀገር አቀፍ ግቦችን፣ ተልእኮዎችን፣ አጠቃላይ ፖሊሲዎችን ስትራቴጂዎችን፤ ፕሮግራሞችን፣
ልዩ ልዩ አዋጆችን፣ የማስፈጸሚያ ደንቦችንና መመሪያዎችን፣ በሌሎች ዘርፎች የተዘጋጁ
ስታንዳርዶችን መነሻ በማድረግና የተለያዩ ሀገራት ልዶችን መሠረት በማድረግ ይከናወናል፡፡

3.2.2 ሥራው የሚጠይቀው የክትትልና ድጋፍ ደረጃ


 ሥራው ከአጠቃላይ ከሀገሪቱ ፖሊሲ፣ ከዘርፉ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች የተቋሙ ስትራቴጂያዊ
ዕቅድ እና የአሰራር ስርአቶች ግቦች ከማሳካት አንጻር ይገመገማል፡፡

3.3 ተጠያቂነት
3.3.1 ተጠያቂነት ለሥራ ውጤት /Responsibility for Impact/፣
 ሥራው የከተማ የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት ፖሊሲና ስትራቴጅና መተግበሪያ ዝርዘር አማራጮች ተንትኖ ማቅረብ፣
የተዘጋጁ የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት ስታንዳዶችን ክፍተቶች በጥናት ፈትሾ መለየትና ማቅረብ፣ የአዲስ
ስታንዳርዶችን ወይም ማሻሻያ ፍላጎት ለመዳሰስና ግብዓቶች ለማሰባሰብ የሚውሉ መጠይቆችና ቼክሊስቶች አዘጋጅቶ ማቅረብ፣ የሀገርና
የዓለም አቀፍ የስታንዳርድ ስርዓትን በመፈተሸ ከሀገራዊ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ልምድ መቀመር፣ የከተሞች ፈርጅ

4
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

መሰረት በማድረግ የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት (ደረጃ ዘመናዊ ቄራ፣ የእሳት አደጋ መከላከያ ጣቢያ፣ዘላቂ ማረፊያ፣
የተሸከርካሪ ማቆሚያ፣ ጋራዥ፣ መናኸሪያ፣ የገበያ ቦታዎች፣ ፓርኮች፣ መናፈሻዎች፣የመንገድ ዳርቻ፣ አካፋይና አደባባዮች፣
ተፋሰሶችና ሌሎች አረንጓዴ መሠረተ ልማቶች፣ የቆሻሻ ማሰባሰቢያ፣ መለያ፣ ማቀነባበሪያ እና ማስወገጃ ቦታዎች… ) ስታንዳዶች
ማዘጋጀት፣ አማካሪ ለመቅጠር የሚያስችል ደረጃው የጠበቀ ቢጋር ማዘጋጀትና በአማካሪ ተዘጋጅተው የሚቀርቡ የስታንዳርድ
ሰነዶችን መገምገም፣ ግብረመልስ መስጠትና መካተተቱን መከታተል፣ በከተሞች አረንጓዴ መሰረተ ልማቶች ላይ የተሰማሩ አልሚዎች
በተቀመጠዉ ስታንዳርድ መሰረት እያለሙ መሆናቸዉን ናሙና በመውሰድ መከታተል፣ክፍተቶችን ለይቶ መፍትሔ መስጠት፣ የተዘጋጁ
ስታንዳርዶች በከተሞች ተግባር ላይ ሲውሉ ያስገኙትን ፋይዳ መገምገም፣ በአረንጓዴና በአካባቢ መሰረተ ልማት ዙሪያ ግንዛቤ ለመፍጠር
የሚያስችል በስታንዳዶችና በተለዩ ክፍተቶችንና መልካም ተሞክሮዎችን በማካተት የስልጠና ሰነዶች ማዘጋጀት የሚጠይቅ ነው፡፡
 እነዚህ ተግባሮች በአግባቡ ባይከናወኑ የከተማ መሰረተ ልማት አቅርቦቱ ወጥ በሆነ ስታንዳርድ ስርዓት
እንዳይመራ ያደርጋል፣ ከፍተኛ የመሰረተ ልማት ሀብት ብክነት ያከትላል፣ የከተሞች ለአየር ብክለት
እንዲጋለጡ ያደርጋል፣ የመሰረተ ልማት አቅርቦት እጥረትን ያስከትላል እና የተቋሙ ግብ እንዳይሳካ
ያደርጋል፡፡

3.3.2 ተጠያቂነት ለሚስጥራዊ መረጃ፣

 ያልጸደቁና በረቂቅ ሂደት የሚገኙ የደረጃና ስታንዳርድ ዝግጅት በሚስጥር መያዝ ወይም መጠበቅ
ያለባቸው ሲሆን እነዚህን ሰነዶች በማይመለከታቸው እጅ ቢገቡ በተቋሙ ላይ ተአማኒነትን ያሳጣል፡፡

3.4 ፈጠራ
 ሥራው በዘርፉ ለሚዘጋጁ አዋጅና ደንቦች ዝግጅት የሚያስፈልጉ ሀሳቦችን ማመንጨት፣ የሚዘጋጁ
ስታንዳርዶች ሀገራዊ ተጨባጭን ያገናዘቡ እንዲሆኑ ማሰላሰልንና ሲተገበሩ በማህበረሰብ ላይ
የሚያሳድሩን ተጽዕኖ አሰላለስሎ ማሰራት፣ ተሞክሮዎችን በመቀመር እና ክፍተቶች ላይ ጥናት
በማድረግ አዳዲስ ወይም የተሻሻሉ የስታንዳርዶች የአሰራር ስርአትን ማዘጋጀትና ማሻሻል ይጠይቃል፣

3.5 የሥራ ግንኙነት /Work Communication/


3.5.1 የግንኙነት ደረጃ

 ሥራው ከውስጥ ከቅርብ ኃላፊውና ከክፍሉ ባለሙያዎች፣ ከሌሎች ሥራ ክፍሎች ባለሙያዎችና


ዴስኮች፣ ከተቋሙ የበላይ ኃላፊዎች፣ ከውጭ ደግሞ ከአማካሪዎች፣ ከሥራ ተቋራጮች ከሙያ
ማሕበራት፣ ከክልሎች፣ ከግሉ ዘርፍ፣ ከተማ አስተዳደሮች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላትና ተቋማት

5
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር ግንኙነት ማድረግን ይጠይቃል፡፡

3.5.2 የግንኙነቱ ዓላማ


 ሥራው መመሪያ ለመቀበል፣ ውሳኔ የሚጠይቁ ጉዳዮችን ለማማከርና ለመወያየት፤ በጋራ የሚሰሩ
ሥራዎችን ለመወሰን፣ የታቀዱ ስራዎችን በተያዘላቸዉ ጊዜ መፈጸማቸዉን ለመከታተል
ለመገምገም፣ በአሰራር ችግሮች ዙሪያ ለመወያየት፣ ለተዘጋጁ ረቂቅ ሰነዶች ግብዓት ለማሰባሰብና
ለማፀደቅ፣ በስራ ላይ በዋሉ ሰነዶች አፈጻጸም ዙሪያ ማብራሪያ ለመስጠትና ለማስረዳት፣ ስልጠናዎች
ለመስጠት ነው፡፡

3.5.3 የግንኙነቱ ድግግሞሽ


 ሥራው ከሥራ ጊዜው 35 በመቶ የሥራ ግንኙነት ማድረግን ይጠይቃል፡፡

3.6. ኃላፊነት
3.6.1 ኃላፊነት ለሰው ሀብት
3.6.1.1. በኃላፊነት የሚመራቸው ሠራተኞች ብዛት
 የለበትም፡፡

3.6.1.2. የኃላፊነት አይነትና ደረጃ


 የለበትም፡፡

3.6.2 ኃላፊነት ለንዋይ


 የለበትም፡፡

3.6.3 ኃላፊነት ለንብረት


 ሥራውን ለማከናወን ወንበር፣ ጠረጴዛ፣ ኮምፒዩተር(ዴስክ ቶፕና ላፕቶፕ)፣ ፕሪንተር፣ ፋክስ፣ የፋይል ካቢኔት እስከ ብር
150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ) የሚገመት ንብረት የመረከብ ኃላፊነት አለበት፡፡

3.7. ጥረት
3.7.1 የአዕምሮ ጥረት

 ሥራው የከተማ የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት ፖሊሲና ስትራቴጅና መተግበሪያ ዝርዘር አማራጮች ተንትኖ ማቅረብ፣ የተዘጋጁ
የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት ስታንዳዶችን ክፍተቶች በጥናት ፈትሾ መለየትና ማቅረብ፣ የአዲስ ስታንዳርዶችን ወይም

6
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

ማሻሻያ ፍላጎት ለመዳሰስና ግብዓቶች ለማሰባሰብ የሚውሉ መጠይቆችና ቼክሊስቶች አዘጋጅቶ ማቅረብ፣ የሀገርና የዓለም አቀፍ
የስታንዳርድ ስርዓትን በመፈተሸ ከሀገራዊ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ልምድ መቀመር፣ የከተሞች ፈርጅ መሰረት በማድረግ
የአረንጓዴና አካባቢ ጥበቃ መሰረተ ልማት (ደረጃ ዘመናዊ ቄራ፣ የእሳት አደጋ መከላከያ ጣቢያ፣ዘላቂ ማረፊያ፣ የተሸከርካሪ
ማቆሚያ፣ ጋራዥ፣ መናኸሪያ፣ የገበያ ቦታዎች፣ ፓርኮች፣ መናፈሻዎች፣የመንገድ ዳርቻ፣ አካፋይና አደባባዮች፣ ተፋሰሶችና ሌሎች
አረንጓዴ መሠረተ ልማቶች፣ የቆሻሻ ማሰባሰቢያ፣ መለያ፣ ማቀነባበሪያ እና ማስወገጃ ቦታዎች…) ስታንዳዶች ማዘጋጀት፣ አማካሪ
ለመቅጠር የሚያስችል ደረጃው የጠበቀ ቢጋር ማዘጋጀትና በአማካሪ ተዘጋጅተው የሚቀርቡ የስታንዳርድ ሰነዶችን መገምገም፣
ግብረመልስ መስጠትና መካተተቱን መከታተል፣ በከተሞች አረንጓዴ መሰረተ ልማቶች ላይ የተሰማሩ አልሚዎች በተቀመጠዉ ስታንዳርድ
መሰረት እያለሙ መሆናቸዉን ናሙና በመውሰድ መከታተል፣ክፍተቶችን ለይቶ መፍትሔ መስጠት፣ የተዘጋጁ ስታንዳርዶች በከተሞች ተግባር
ላይ ሲውሉ ያስገኙትን ፋይዳ መገምገም፣ በአረንጓዴና በአካባቢ መሰረተ ልማት ዙሪያ ግንዛቤ ለመፍጠር የሚያስችል በስታንዳዶችና

በተለዩ ክፍተቶችንና መልካም ተሞክሮዎችን በማካተት የስልጠና ሰነዶች ማዘጋጀት አዕምሮ የሚያደክሙ ሲሆኑ፣ ይህም ከቀን
የሥራ ጊዜው 75 በመቶ ይወስዳል፡፡

3.7.2 ስነልቦናዊ ጥረት

 ሥራው ከባለድርሻ እና አስፈጻሚ አካላት ጋር በመሰረተ ልማት ስታንዳርድ ዝግጅትና አፈጻጸም ስራዎች በምክክር መድረክ
በሚፈጠሩ ክርክሮች እና የሀሳብ አለመግባባቶች ስነልቦናን የሚፈታተኑ ሲሆኑ እነዚህን በትዕግስትና በተረጋጋ ስሜት ተቋቁሞ
ሥራዎችን ውጤታማ ማድረግ ይጠይቃል፡፡

3.7.3 የዕይታ ጥረት፣


 ሥራው የተለያዩ ጥናት ለማድረግ የሚስፈልጉ ግብዓቶችን ማንበብ እንዲሁም በዳሰሳ ላይ የተመሰረተ የፖሊሲ ሀሳብ
ማመንጨት፣ የጥናት ሰነዶችን አንብቦ ማረምና ማስተካከል፣ የመሰረተ ልማት ስታንዳርድ ሰነዶች በጥናት ላይ ተመስርቶ
የተለያ ሰነዶችን በማንብብና በማገናዘብ ማዘጋጀት፣ የተለያዩ ሰነዶችን በማንበብና በማገናዘብ የሀገራትን የስታንዳንድር
ዝግጅት ተሞክሮ መቀመር፣ የስልጠና ማንዋሎችን ዝግጅት፣ የክትትልና ድጋፍ ሪፖርቶች እና ሌሎች ሥራዎችን ኮምፕዩተር
ላይ ማዘጋጀት፣ የተለያዩ ማጣቀሻዎችን ማገናዘብ፣ የዋና ስራ አስፈጻሚውን የተጠቃለለ ሪፖርት ማዘጋጀትና በኮምፒዩተር
መጻፍ እይታን የሚያደክም ሲሆን ይህም ከሥራ ጊዜው 45 በመቶ ይሆናል፡፡

3.7.4 የአካል ጥረት


 ሥራው 70 % በመቀመጥ፣ 30 % በመንቀሳቀስ የሚከናወን ይሆናል፡፡

3.8 የሥራ ሁኔታ


3.8.1 ሥጋትና አደጋ
 የለበትም፡፡

3.8.2 የሥራ አካባቢ ሁኔታ


 የለበትም፡፡

7
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

3.9 እውቀትና ክህሎት፣

3.9.1 ትምህርት

የትምህርት ደረጃ የትምህርት አይነት

ከተማ ልማትና ኢንቫይሮንመንት፣ በተፈጥሮ ሀብት አያያዝና አስተዳድር፤ አግሪካልቸራል


ኢንጀር፣አካባቢ ሳይንስ፣ ኢንቫሮመንታል ኢንጂነር ወይም ስነ-ህይዎት ወይም ኢኮሎጅካል
የመጀመሪያ ዲግሪ ሳይንስ ወይም ደን ሳይንስ፣ በአርባን ፎርስትሪ ወይም በዕጽዋት ሳይንስ ወይም በከተማ ውበትና
አረንጓዴ ልማት፣

ሥራውን ለመጀመር የሚያስፈልግ የሥራ ልምድ

የሥራ ልምዱ ለማግኘት የሚጠይቀው ጊዜ ልምዱ የሚገኝበት የሥራ ዓይነት

6 ዓመት ቀጥታ አግበብነት ያለው የሥራ ልምድ

የሥራ ትንተና ባለሙያ ሥም ፊርማ ቀን

የሥራ ዝርዝሩን ያጸደቀው የኃላፊው ሥም የሥራ መደቡ መጠሪያ ፊርማ ቀን

You might also like