Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 101

በሶላት ዙሪያ ለቀረቡ ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች

እና
የሰጋጆች ስህተቶች

‫ الشيخ حممد بن صاحل العثيمني‬:‫تأليف‬


ትርጉም፡አቡ’ዓብዲልዓዚዝ/ ዩሱፍ አህመድ
1/99

ምስጋና ለሃያሉ አምላካችን አላህ ይድረሰው፡፡ እገዛን ከእርሱ ብቻ እንሻለን፡፡


እርሱ የመራውን ማንም አያጠመው፡፡ እርሱ ያጠመመውን ደግሞ ማንም አያቃናው፡፡
ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የሌለ መሆኑን እና ነብዩ ሙሐመድ ‫ﷺ‬

የአላህ አገልጋይ እና መልእክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-


﴾َ‫اّللا اح َّق تُ اقاتِِه اوالا اَتُوتُ َّن ِالَّ اوأاتُُ ُّم ِِْْ ُُو ا‬ ِ َّ
‫﴿ اَي أايُّ اها الذ ا‬
‫ين اآمنُواْ اتَّ ُقواْ ه‬
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገቢውን መጠንቀቅ ተጠንቀቁት እናንተም
ሙስሊሞች ኾናችሁ እንጅ አትሙቱ፡፡” አል ዒምራን ፡

َّ ‫اح ادةٍ او اخِا اق ِمْن اها ازْو اج اها اوبا‬ ِ َّ


‫ث ِمْن ُه اُا ِر اجاالا اكثِريا‬ ُ ‫﴿ اَي أايُّ اها الن‬
ِ‫سو‬ ِ
‫َّاس اتَّ ُقواْ اربَّ ُك ُ الذي اخِا اق ُك همن تَّ ْف ٍ ا‬
﴾‫اّللا اكا اَ اَِاْْ ُك ْ ارًِِْاا‬ ِ ِ
‫اّللا الَّذي تا اْاءلُو اَ بِه اواأل ْار اح اام ِ ََّ ه‬
ِ
‫اوت اْاء اواتَّ ُقواْ ه‬
“እናንተ ሰዎች ሆይ! ያንን ከአንዲት ነፍስ (ከአደም) የፈጠራችሁን ከእርሷም
መቀናጆዋን (ሀዋን) የፈጠረውን ከእነርሱም ብዙ ወንዶችን እና ሴቶችን
የበተነውን (ያባዛውን) ጌታችሁን ፍሩ፡፡ ያንንም በእርሱ የምትጠያየቁበትን
አላህን (ፍሩ) ዝምድናዎችንም (ከመቁረጥ) ተጠንቀቁ፡፡ አላህ በእናንተ ላይ
ተጠባባቂ ነውና፡፡” አን ኒሳእ፡

َّ‫صِِ ْح لا ُك ْ أ ْاَ اُالا ُك ْ اويا ْغ ِفْر لا ُك ْ ذُتُوبا ُك ْ اوامن يُ ِط ْع ا‬


‫اّلل‬ ‫اّللا اوُِولُوا ِا ْواال اس ِد ا‬
ْ ُ‫يدا۞ي‬ َّ ‫ين اآمنُوا اتَّ ُقوا‬
‫ا‬
ِ َّ‫﴿َي أايُّها ال‬
‫ذ‬ ‫ا ا‬
﴾‫ُْا‬ ِ
‫اوار ُسولاهُ فا اق ْد فا ااز فا ْوازا اَظ ا‬
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ ትክክለኛንም ንግግር ተናገሩ፡፡ስራዎቻችሁን
2/99
ለእናንተ ያበጅላችኋልና ሀጢያቶቻችሁንም ለእናንተ ይምርላችኋል፡፡ አላህን እና
መልእክተኛውን የሚታዘዝ ሰው በእርግጥ ታላቅን ዕድል አገኘ፡፡” አል አህዛብ፡
3/99

“አዛን”
ጥያቄ፡- ብቻውን የሚሰግድ ሰው አዛን እና ኢቃማ ማድረግ ይችላል?

መልስ፡- አብረውት እንዲሰግዱ ጥሪ የሚያደርግላቸው ሰዎች ባለመኖራቸው ፣


ብቻውን ለሚሰግድ ሰው አዛንም ይሁን ኢቃማ ማድረጉ ግዴታ ሳይሆን ሱና ነው፡፡ ነገር
ግን አላህን የሚያስታውስበትና የሚያልቅበት እንዲሁም እራሱን ወደሶላትና ወደስኬት
የሚጣራበት ከመሆኑ አኳያ አንድ ሰው ብቻውን ቢሰግድም እንኳ አዛን እና ኢቃማ
ማድረጉ ለእርሱ ሱና ነው፡፡ ለዚህ ማስረጃው ዑቅባ ብን ዓሚር 4 ያስተላለፈው
የሚከተለው የረሡል ‫ﷺ‬ ሐዲስ ነው፡-

‫ انظروا‬:‫"يعجب ربك من راعي غنم على رأس الشظية للجبل يؤذن للصالة فيقول هللا‬
"‫إلى عبدي هذا يؤذن ويقيم للصالة يخاف مني قد غفرت لعبدي وأدخلته الجنة‬

(ተራራው ጫፍ ላይ ሆኖ ለሶላት አዛን በሚያደርገው ፍየል ጠባቂ ጌታህ ይደነቃል፡፡ “እኔን


ፈርቶ ለሶላት አዛን እና ኢቃም የሚያርገውን ባሪያየን ተመልከቱ፡፡ ባሪያየን በእርግጥ
ምሬዋለሁ ፣ ጀነትም አስገብቸዋለሁ” ይላል አላህ፡፡) አህመድ፡ ነሳኢይ፡ አቡ ዳውድ፡
ሐዲሱን አልባኒ ሲሂህ ብለውታል ሶሂህ አል ጃሚዕ፡

ጥያቄ፡ የዙሁር እና የዓስርን ሶላት አጣምሮ የሚሰግድ ሰው ለሁለቱም ሶላቶች ኢቃማ


ይኖረዋል? ለሱና ሶላት ኢቃማ ይኖረዋል?

መልስ፡- ሁለት ሶላቶችን አጣምሮ የሚሰግድ ሰው ለእያንዳንዱ ሶላት ኢቃማ ማድረግ


ይኖርበታል፡፡ ለዚህ ማስረጃ የሚሆነው ነብዩ ‫ﷺ‬ ሐጅ ባደረጉበት ጊዜ ሙዝደሊፋ ላይ
ሁለት ሶላቶችን አጣምረው እንደሰገዱና ለሁለቱም ሶላቶች ኢቃማ እንዳደረጉ
የሚገልጸው የሚከተለው ሐዲስ ነው፡፡
4/99
"‫ ولم يسبح بينهما‬،‫ ثم أقام فصلى العشاء‬،‫"أقام فصلى المغرب‬

“ኢቃም አደረጉ ወዲያው መግሪብን ሰገዱ ፤ ከዚያም ኢቃም አደረጉና ወዲያው ኢሻን
ሰገዱ ፤ በመካከሉ ሱና አልሰገዱም፡፡” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

ሱና ሶላቶች ግን ኢቃማ የላቸውም፡፡

“አስ'ሶላቱ ኸይሩን ሚነን'ነውም” የሚለው ቃል መጀመሪያው አዛን ላይ ነው ወይስ


ሁለተኛው አዛን ላይ”

ጥያቄ፡-“አስ'ሶላቱ ኸይሩን ሚነን'ነውም” (ሶላት ከእንቅልፍ በላጭ ነው) የሚለው


ቃል በመጀመሪያው አዛን ላይ ነው የሚባለው ወይስ በሁለተኛው አዛን ላይ?

መልስ፡- “አስ'ሶላቱ ኸይሩን ሚነን'ነውም” የሚለው ቃል በመጀመሪያው አዛን ላይ


የሚባል ለመሆኑ በሐዲስ መጧል፡፡

የአላህ መልእክተኛ ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-

"‫ "الصالة خير من النوم‬:‫"فإذا أذنت لصالة الصبح األول فقل‬

“ለመጀመሪያው የሱብሒ ሶላት አዛን ስታደርግ “አስሶላቱ ኸይሩን ሚነንነውም”


የሚለውን ቃል በል፡፡” ነሳኢይ፡

ለሁለተኛው ሳይሆን ለመጀመሪያው አዛን እንደሆነ ይህ ሐዲስ በግልጽ ይናገራል፡፡

ነገር ግን በዚህ ሐዲስ የመጀመሪያው አዛን የተባለው የቱ እንደሆነ ማወቅ የግድ


ይላል፡፡ ኢቃማ አዛን የሚል ስያሜ ስለተሰጠው ወቅቱ ከገባ በኋላ የሚደረገው አዛን
የመጀመሪያ አዛን ሁለተኛ አዛን በመባል የተጠራው ደግሞ ኢቃማው ነው፡፡
ረሡል ‫ ﷺ‬የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-
5/99
"‫"بين كل أذانين صالة‬

“በሁለት አዛኖች መካከል ሶላት አለ፡፡” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

በዚህ መሰረት ቡኻሪ በትክክለኛ ሐዲስ እንደዘገቡት የሙእሚኖች ዓሚር ዑስማን


ብን ዓፋን 4 ለጁሙዓ ሶላት የጨመሩት ሶስተኛ አዛን ይሆናል ማለት ነው፡፡

ስለዚህ ቢላል “አስ'ሶላቱ ኸይሩን ሚነን'ነውም” እንዲል የታዘዘበት የፈጅር


ሶላት አዛን የመጀመሪያው አዛን ነው ማለት ነው፡፡

መጨረሻ ሌሊት ላይ ፈጅሩ ከመውጣቱ በፊት የሚደረገውን አዛን ሰዎች ለፈጅር


ሶላት የሚደረግ የመጀመሪያ አዛን አድርገው ቢቆጥሩትም በትክክል ከተመለከትነው
ግን ለፈጅር ሶላት የሚደረግ አዛን ሳይሆን የተኛው ከእንቅልፉ ነቅቶ ለሱሁር እንዲዘጋጅ
፣ የቆመውም ተመልሶ ለሱሁር እንዲዘጋጅ የሚደረግ የማንቂያ ጥሪ ነው፡፡

ምክንያቱም ነብዩ ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-

"‫"إن بالال يؤذن بليل ليوقظ نائمكم ويرجع قائمكم‬

“ቢላል ፣ የተኛውን ለማንቃት ፣ የቆመው ደግሞ እንዲመለስ በሌሊት አዛን ያደርጋል፡፡”


ነሳኢይ፡

ነብዩ ‫ﷺ‬ ለማሊክ ብን አል'ሁወይሪስ 4 የሚከተለውን ነግረውታል፡-

"‫"إذا حضرت الصالة فليؤذن لكم أحدكم‬

“ሶላት በደረሰች ጊዜ ከመካከላችሁ አንዱ አዛን ያድርግ” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

ፈጅሩ ካልወጣ የሱብሂ ሶላት እንደማይሰገድ ይታወቃል፡፡ ስለዚህ ፈጅር


ከመውጣቱ በፊት ያለው አዛን ለፈጅር የታሰበ አዛን አይደለም፡፡
6/99
በመሆኑም ሰዎች ፈጅሩ እንደወጣ አዛን ላይ “አስ'ሶላቱ ኸይሩን ሚነን'ነውም”
የሚለው ቃልን ቢጠቀሙ ትክክል ይሆናሉ ማለት ነው፡፡

የተቀረጸ አዛን ለሶላት ጥሪ መዋል ይችላል?

ጥያቄ፡ - የተቀረጸ አዛን ለሶላት መጥሪያ መሆን ይችላል?

መልስ፡- የተቀረጸ አዛን ለሶላት ጥሪ ማድረጊያ መጠቀም ትክክል አይደለም፡፡


ምክንያቱም አዛን አምልኮ ነው ፣ አምልኮ ደግሞ ኒያ (ሐሳብ) የግድ ሊኖረው
ይገባል፡፡

“በሶላት ዙሪያ ለቀረቡ ጥያቄዎች የተሰጡ ምላሾች”


“የሶላት ሸሪዓዊ ብይንና አንገብጋቢነት”

ጥያቄ፡- የሶላትን ሸሪኣዊ ብይን እና አንገብጋቢነት ማወቅ እንፈልጋለን?

መልስ፡- ሶላት ፣ በአካል ከሚተገበሩ አምልኮዎች ጠንካራው ፣ ረሡል ‫ﷺ‬

በሚከተለው ሐዲሳቸው እንደተናገሩት ከኢስላም ማዕዘናት መካከል ከሁለቱ


የምስክርነት ቃሎች ቀጥሎ የሚገኝ ሁለተኛው የዲን (የኢስላም) ምሰሶ ነው፡፡

‫"وعمود الدين" يعين الإسالم‬

“የዲን ምሰሶ ነው” ማለት የኢስላም ምሰሶ ማለት ነው፡፡ ቲርሚዘይ፡ አህመድ፡

በከፍተኛ ቦታ ፣ ለአላሀ መልእክተኛ ‫ﷺ‬ በላጭ በሆነች ሌሊት ፣ ያለምንም


ጣልቃ ገብ በቀንና በሌሊት የሚሰገድ አምሳ ሶላት አላህ - ሱብሃነሁ ወተዓላ - በነብዩ
‫ﷺ‬ ላይ ግዴታ አድርጓል፡፡
7/99
ነገር ግን በባሮች ላይ የደነገገውን ሶላት በተግባር አምስት ፣ በሚዛን ግን አምሳ
አድርጎታል፡፡ ይህ ፣ አላህ ሶላትን ከአምልኮዎች ሁሉ የበለጠ የሚወደውና አንገብጋቢ
መሆኑን ይጠቁማል፡፡

በዚህ ምክንያት የሶላት ግዴታነት መረጃዎቹ በአላህ ኪታብ ፣ በረሡል ‫ﷺ‬ ሱና


ግልጽ ሆነው የመጡ ፣ ሙስሊሞች የተስማሙበት ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

﴾‫وت‬
‫ني كُِا ااًب َّم ْوُِ ا‬ِِ َّ ََّ ِ ‫الصالاةا‬ ِِ‫﴿فاِإذاا اطُْأْتانُ فاأا‬
‫ت اَِاى الْ ُُ ْؤمن ا‬
ْ ‫الصالاةا اكاتا‬ َّ ْ‫ُْوا‬
ُ ُْ ‫ا‬
“በረጋችሁም ጊዜ ሶላትን (አሟልታችሁ) ስገዱ፡፡ ሶላት በምእመናን ላይ
በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናትና፡፡” አን ኒሳእ፡

ነብዩ ‫ﷺ‬ ለሙዓዝ 4 የሚከተለውን መልእክት አስይዘው ወደየመን ልከውታል፡-

"‫"أعلمهم أن هللا افترض عليهم خمس صلوات في كل يوم وليلة‬

“አላህ በእነርሱ ላይ በቀንና በሌሊት አምስት (ወቅት) ሶላቶችን ግዴታ እንዳደረገባቸው


አሳውቃቸው፡፡” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

የሶላት ግዴታነት በቁርኣን በሐዲስ የጸደቀ ፣ ሙስሊሞች ሁሉ የተስማሙበት በመሆኑ


እነዚህን ሶላቶች በሙሉ ወይም ከፊሏን ቢያስተባብል ወደአላህ ተጸጽቶ የተመለሰ
ካልሆነ ወይም ምክንያት የሚሰጠው ፣ ስለኢስላም ሸሪዓ ፍጹም የማያውቅ አዲስ
እስልምናን የተቀበለ ካልሆነ በቀር ከሀዲ ወይም ከኢስላም ያፈነገጠ፣ ገንዘቡም ደሙም
የተፈቀደ ይሆናል፡፡ ጃሂል ወይም ማህይም የሆነ ሰው የሶላት ግዴታነት ይብራራለታል ፣
እምቢ ብሎ የሶላትን ግዴታነት አልቀበልም ካለና በአቋሙ ከጸና ከሀዲ ይሆናል፡፡
8/99

“ሶላት በማን ላይ ነው ግዴታ የሆነው?”

ጥያቄ፡ - ሶላት በማን ላይ ነው ግዴታ የሆነው?

መልስ፡- ሶላት አዕምሯቸው ጤናማና ለአካለ መጠን በደረሱ ወንዶችና ሴቶች ላይ


ግዴታ ነው፡፡

ሙስሊም የከሐዲ ተቃራኒ ነው፡፡ ከሐዲ ከሆነ በእርሱ ላይ የሶላት ግዴታ የለበትም፡፡
ማለትም በክህደት ላይ ሆኖ እርሷን ተፈጻሚ አያደርግም፡፡ እስልምናን ከተቀበለ በኋላ
ቢሆንም ቀዷ አውጣ አይባልም፡፡ ነገር ግን ሶላትን በመተው የትንሳኤ ቀን ይቀጣል፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

ْ ‫﴿َِّال أ‬
‫ك ِم ان‬
ُ ‫ني۞ اما اسِا اك ُك ْ ِف اس اقار۞ِاالُوا اَلْ تا‬ ِ ٍ ِ ُِ ‫اب الْْا‬
‫ني۞ِف اجنَّات ياُا اْاءلُو اَ۞ اَ ِن الْ ُُ ْج ِرم ا‬ ‫اص اح ا‬
﴾‫ب بِْا ْوِم ال هِدي ِن‬ ِ
ُ ‫ني۞ اوُكنَّا تُ اك هذ‬
ِ ِ ْ ‫ك تُطْعِ الْ ُِْ ِكني۞وُكنَّا اَنُوض مع‬
‫اْلاائِض ا‬ ‫ُ اا‬ ‫ني۞ اواَلْ تا ُ ُ ْ ا ا‬
ِ ُْ‫ال‬
‫صِه ا‬
‫ُ ا‬
“የቀኝ ባለቤቶች ብቻ ሲቀሩ ፣ (እነርሱስ) በገነቶች ውስጥ ይጠያየቃሉ፡፡
ከአመጸኞቹ ሁኔታ፡፡ (ይሏቸዋልም) “በሰቀር ውስጥ ምን አገባችሁ?”
(እነርሱም) ይላሉ “ከሰጋጆቹ አልነበርንም፡፡ “ለድሆችም የምናበላ
አልነበርንም፡፡ “ከዘባራቂዎቹም ጋር እንዘባርቅ ነበርን፡፡ “በፍርዱ ቀንም
እናስተባብል ነበርን፡፡” አል ሙደሲር፡

በዚህ ቁርኣናዊ አንቀጽ ውስጥ “ከሰጋጆች አልነበርንም” የሚለው ቃላቸው ሶላትን


በመተዋቸው ምክንያት ቅጣት እንደሚደርስባቸው ነው የሚያመላክተው፡፡

ለአካለ መጠን የደረሰ ፡ ሲባል ወንድ ከሆነ ለአካለ መጠን መድረሱን የሚጠቁሙ
ከሶስት ምልክቶች አንዱ መታየት አለበት፡፡
9/99
ሴት ከሆነች ደግሞ ከአራት ምልክቶች አንዱ መታየት አለበት፡፡ ወንድ
ከሚያያቸው ምልክቶች በተጨማሪ ሴት አራተኛ ምልክት ታያለች፡፡ ከወንድም ይሁን
ከሴት ላይ የሚታዩ ሶስቱ ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው፡-

አንደኛ፡- እድሜያቸው አስራ አምስት አመት መሙላት፡፡

ሁለተኛ፡- ነቅቶም ይሁን በእንቅልፉ በእርካታ የፍትዎት ጠብታ ማፍሰስ፡፡

ሶስተኛ፡- በብልታቸው ዙሪያ ጸጉር ማብቀላቸው፡፡

ሴት ላይ ብቻ የሚስተዋለው አራተኛ ምልክት የወር አበባ መመልከቷ ነው፡፡

አቅለኛ መሆን፡ የዓቅለኛ ተቃራኒ አዓምሮው የተዛባ እብድ ነው፡፡ ወንድም ይሁን
ሴት ለአካለ መጠን ደርሰው ነገር ግን አዕምሯቸው የመለየት አቅም ከሌለው በእነርሱ
ላይ የሶላት ግዴታ የለባቸውም፡፡

የወር አበባ ወይም የወሊድ ደም መመልከት፡ እነዚህ ሁለት ምልክቶች ከሴቶች ላይ


ከተስተዋሉ በእነርሱ ላይ ሶላት የመስገድ ግዴታ የለባቸውም፡፡

“ሶላትን የተወ ሰው ሸሪዓዊ ብይን”

ጥያቄ፡- ሶላት በማን ላይ ግዴታ እንደሆነ ተገንዝበናል፡፡ ሶላትን የተው ሰዎች ሸሪዓዊ
ብይናቸው ደግሞ ምንድን ነው?

መልስ፡ - ሶላትን የተወ ሰው የክህደት ተግባር በመፈጸሙ ከኢስላም እንሚወጣ


የቁርኣን ፣ የሱና ፣ የሶሃቦች ንግግርና ትክክለኛ የሆኑ አመለካከቶች አረጋግጠውታል፡፡
የቀርኣን ማስረጃ፡-
﴾َ‫ت لِاق ْوٍم يا ْعِا ُُو ا‬
ِ ‫ص اَيَي‬
ِ ِ
ُ ‫﴿فاإَ اتبُواْ اوأاِا ُامواْ َّ ا‬
ِ َّ ْ‫الصالااة وآتاوا‬
‫الزاكا اة فاإ ْخ اواتُ ُك ْ ِف ال هدي ِن اوتُ اف ه ُ ا‬
ِ
10/99
“ቢጸጸቱም ፣ ሶላትንም ቢሰግዱ ፣ ዘካንም ቢሰጡ የሃይማኖት ወንድሞቻችሁ
ናቸው፡፡ ለማያውቁ ህዝቦችም አንቀጾችን እናብራራለን፡፡” አት ተውባህ፡

በሙሽሪኮችና በሙእሚኖች መካከል ወንድማማችነት ሊረጋገጥ የሚችለው ሶስት


መስፈርቶች ሲሟሉ እንደሆነ ይህ የተከበረ ቁርኣናዊ አንቀጽ ይጠቁማል፡፡ ከሽርክ
ተግባር ተጸጽቶ መመለስ ፣ ሶላትን ደንቡን ጠብቆ መስገድ እና ዘካ መስጠት ናቸው፡፡

ከእነዚህ ሶስቱ መስፈርቶች አንዱን ካጎደሉ የዲን ወንድሞቻችን አይደሉም፡፡


ወንድምነት የሚጠፋው ከኢስላም የሚያስወጣ የክህደት ተግባር ሲፈጸም ነው፡፡ ወንጀል
የፈለገው ቢገዝፍ ከክህደት ደረጃ እስካልደረሰ ድረስ ከዲን ወንድማማችነት
አያወጣም፡፡ አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

﴾َ‫ا‬ ِ ِِ ِ ِ
‫﴿فا اُ ْن َُف اي لاهُ م ْن أاخْه اش ْيءٌ فااتهًااعٌ ًبلْ اُ ْعُر ا ا ٌ ْ ْ ا‬
ٍ ْ‫وف وأاداء ِلاْ ِه ِبِِح‬ ِ ِ

“ለእርሱም (ለገዳዩ) ከወንድሙ (ደም) ትንሽ ነገር ምህረት የተደረገለት ሰው


(በመሃሪው ላይ ካሳውን) በመልካም መከታተል ወደርሱም (ወደመሃሪው)
ገዳዩ በመልካም አኳኋን መክፈል አለባቸው፡፡” አል በቀራህ፡

ሙእሚንን አውቆ መግደል ከባድ ወንጀል ከመሆኑ ጋር ገዳይና ተገዳይ


ወንድማማች እንደሆኑ አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ ገልጹዋል፡፡ አላህ
በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
ِ ‫اَ ِمن الُْؤِمنِني اِْ ُ ُ ُِوا فاأ‬
‫ُخارى فا اقاتُِِوا الَِِّت تاًْغِي‬
ْ ‫ت ِ ْح اد ُاُهاا اَِاى ْاأل‬
ْ ‫اصِ ُحوا باْْ نا ُه اُا فاِإَ باغا‬
ْ ‫﴿ اوَِ طاائِافُا ِ ا ُ ْ ا ا ا‬
‫ني۞ََِّّناا‬ ِِ
‫ب الْ ُُ ْقْط ا‬ َّ ََّ ِ ‫اصِِ ُحوا باْْ نا ُه اُا ًِبلْ اع ْد ِل اوأاِْ ِْطُوا‬
ُّ ‫اّللا ُُِي‬ ْ ‫اءت فاأ‬ْ ‫اّلل فاِإَ فا‬
َِّ ‫ح ََّّت تاِفيء ِ اَل أام ِر‬
ْ ‫ا‬ ‫ا‬
﴾َ‫اّللا لا اعَِّ ُك ْ تُْر اَحُو ا‬
َّ ‫اخ اويْ ُك ْ اواتَّ ُقوا‬ ِ ‫الُْؤِمنو اَ ِخوةٌ فاأ‬
‫ني أ ا‬
‫اصِ ُحوا باْ ا‬ْ ‫ُْ ُ ْا‬
“ከምዕምናንም የሆኑ ሁለት ጭፍሮች ቢጋደሉ በመካከላቸው አስታርቁ፡፡ ከሁለቱ
11/99
አንደኛይቱም በሌላይቱ ላይ ወሰን ብታልፍ ያችን ወሰን የምታልፈውን ወደ አላህ
ትዕዛዝ እስከምትመለስ ድረስ ተጋደሉ፡፡ ብትመለስም በመካከላቸው በትክክል
አስታርቁ ፡፡ በነገሩ ሁሉ አስተካክሉም፡፡ አላህ አስተካካዮችንም ይወዳልና፡፡
ምእመናኖች ወንድማማቾች ናቸው፡፡ በሁለት ወንድሞቻችሁም መካከል
አስታርቁ፡፡” አል ሑጁራት፡

ሙእሚንን መግደል ከባድ ወንጀል ከመሆኑ ጋር የተጋደሉት ሁለት ጭፍሮች


ለአስታራቂዎች ወንድሞች እንደሆኑ አላህ ተናገረ፡፡ ይህ የሚያመላክተው ክህደት
እስካልሆነ ድረስ በወንጀል የዲን ወንድማማችነት ሊጠፋ እንደማይችል ነው፡፡

ከላይ የተጠቀሰው ቁርኣናዊ አንቀጽ ትንታኔ፡- በሽርክ ላይ ከዘወተሩ ክህደታቸው


ግልጽ ለመሆኑ አሻሚ አይደለም፡፡ አምነው ደግሞ ሶላታቸውን ካልሰገዱም እንዲሁ፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

﴾‫الصالااة‬
َّ ْ‫﴿فاِإَ اتبُواْ اوأاِا ُاموا‬

“ቢጸጸቱም ፣ ሶላትንም ቢሰግዱ” አት ተውባህ፡

ከማጋራት ቢጸጸቱ ፣ ሶላታቸውን ደንቡን ጠብቀው ቢሰግዱ ፣ ዘካን ባይሰጡስ ይከፍራሉ


ወይስ አይከፍሩም በሚለው የዑለሞች ውዝግብ እንዳለ የሚታወቅ ሲሆን ከኢማም
አህመድ ዘንድ እንኳ ሁለት ዓይነት ዘገባዎች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን የረሡል
‫ﷺ‬ ሱና የሚጠቁመው ዘካን የተው ሰዎች እንደማይከፍሩ ነው፡፡ በዚህ ላይ
የሚጠቁመው አቡሁረይራ 4 ያስተላለፈው ረሡል ‫ﷺ‬ ያወሩት የሚከተለው ሐዲስ
ነው፡፡
‫ صفحت له‬،‫"ما من صاحب ذهب وال فضة ال يؤدي منها حقها إال كان يوم القيامة‬
12/99
‫ كلما‬،‫ فيكوى به جنبه وجبينه وظهره‬،‫ وأحمي عليها في نار جهنم‬،‫صفائح من نار‬
‫ ثم يرى‬،‫ حتى يقضى بين العباد‬،‫بردت أعيدت في يوم كان مقداره خمسين ألف سنة‬
"‫سبيله إما إلى جنة وإما إلى نار‬

“የብር ወይም የወርቅ ባለቤት ከእርሷ ሀቋን የማይሰጥ ከሆነ ፣ አንዱ ቀን የአምሳ ሽ
አመት ልክ በሚሆንበት የትንሳኤ ቀን በባሮች መካከል ፍርድ እስኪሰጥ ድረስ በእርሷ
የእሳት ሳህን ተዘጋጅቶ በጀሐነም እሳት ውስጥ ጎኑ ፣ ግንባሩ እና ጀርባው ይተኮሳል፡፡
(እሳቷ) በቀዘቀዘች ቁጥር እንደገና ይጨምራል ፤ ከዚያም መንገዱ ወደጀነት ወይም
ወደእሳት መሆኑን ይመለከታል፡፡” ሙስሊም፡ አህመድ፡

ይህ ሐዲስ ዘካን የከለከለ ሰው ከሐዲ እንደማይሆን ይጠቁማል፡፡ ምክንያቱም ከሀዲ


ቢሆን ኖሮ ወደጀነት የመግባት መንገድ አይኖረውም ነበር፡፡ ሶላትን የተወ ሰው ከሀዲ
እንደሚሆን ከሚጠቁሙ መረጃዎች መካከል የሚከተለው የረሡል ‫ﷺ‬ ሐዲስ
ይገኝበታል፡-

"‫"بين الرجل وبين الشرك والكفر ترك الصالة‬

“በሰውየውና በሽርክ መካከል ልዩነቱ ሶላትን መተው ነው፡፡” ሙስሊም፡

በኢማን እና በክህደት መካከል መለያው ሶላት ነው፡፡ ሶላትን የተወ ሰው ኢማን


የለውም፡፡ ከሶሃቦች ንግግር ማስረጃ፡ ዓብደሏህ ብን ሸቂቅ i የሚከተለውን ተናግሯል፡-

‫"كان أصحاب النبي صلى هللا عليه وسلم ال يرون شيئا من األعمال تركه كفر غير‬
"‫الصالة‬

“የነብዩ ‫ﷺ‬ ሶሃቦች ከሶላት ውጭ ክህደት ነው ብለው የሚመለከቱት አምልኮ


አልነበረም፡፡” ቲርሚዚይ፡
13/99
ኢስሀቅ ብን ራህዊያህ i ሶላትን መተው ክህደት እንደሆነ ዑለሞች ተስማምተዋል
ብሏል፡፡

ማንኛውም ሰው የሶላትን ክብር ፣ ሸሪዓው የሰጠውን ትኩረት አውቆና ተገንዝቦ


ከዚያም ያለምንም ምክንያት ሶላቱን የተዎ ከልቦናው ውስጥ ምንም አይነት ኢማን
የሌለው መሆኑን የሚያስረዳ ስለሆነ ከአላህ ፊት ምክንያት አይኖረውም፡፡ ትንሽ እንኳ
ኢማን በልቦናው ውስጥ ቢኖር ይህን ታላቅና ሸሪዓው ትኩረት የሰጠውን ሶላት
ባልተወው ነበር፡፡

ሶላትን የተወ ሰው ከኢስላም የሚያስወጣ ክህደት የፈጸመ ከሐዲ እንደሆነ


የቁርኣን፣ የሐዲስ እንዲሁም ንጹህ የሆነ ዓቅል ያስረዳል፡፡ ሶላትን መተው አስቀያሚ
ተግባር ነው፡፡ መጠንቀቅ ይኖርብናል፡፡ ምስጋና ለአላህ የተገባው ነው ምንም እንኳ
መዘናጋቱ ቢኖርም ወደአላህ ተጸጽቶ የመመለስ በሩ ክፍት በመሆኑ ፈጥነን
ልናስተካክል ይገባል፡፡ አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
ِِ
‫﴿فا اخِا ا‬
ِ ‫الص اال اة واتًَّ عوا الشَّهو‬
‫ف يا ِْ اق ْو اَ اغًّْا۞َِّال امن ات ا‬
‫ب او اآم ان‬ ‫ات فا اْ ْو ا‬ ‫اا‬ ُ ‫اضاَُوا َّ ا ا‬ ‫فأ ا‬ٌ ِْ ‫ف ِمن با ْعده ْ اخ‬
ِ ْْ‫الر َْحان ًَِا اادهُ ًِبلْغا‬ َّ ٍ ِ ِ
ُ‫ب ِتَّه‬ ُ َّ ‫اْلانَّةا اواال يُظِْا ُُو اَ اشْْ ئاا۞ اجنَّات اَ ْدَ ال ِِت او اَ اد‬ ‫صاِلاا فاأ ُْولائِ ا‬
ْ َ‫ك يا ْد ُخُِو ا‬ ِ
‫او اَُ ا ا‬
﴾‫اكا اَ او َْ ُدهُ امأْتًِّْا‬

“ከእነሱም በኋላ ሶላትን ያጓደሉ (የተው) ፍላጎቶችንም የተከተሉ መጥፎ


ምትኮች ተተኩ! የገሀነምንም ሸለቆ በእርግጥ ያገኛሉ፡፡ ግን የተጸጸተና ያመነም
በጎንም ስራ የሰራ ሰው እነዚህ ገነትን ይገባሉ፡፡ አንዳችንም አይበደሉም፡፡
የመኖሪያ ገነቶች ያችን አልረህማን ለባሮቹ በሩቅ ሆነው ሳሉ ተስፋ ቃል
የገባላቸውን (ይገባሉ)፡፡ እርሱ ተስፋው ተፈጻሚ ነውና፡፡” መርየም፡
15/99
እኛንም ሙስሊም ወንድሞቻችንንም ወደትክክለኛው ጎዳና እንዲመራ ፣ እርሱ
እንደሚወደው ትዕዛዙን ፈጻሚ እንዲያደርገን አላህን እንማጸነዋለን፡፡

“ሶላትን በመተው ተከትለው የሚመጡ ሸሪዓዊ ብይኖች”

ጥያቄ፡- ሶላትን (ሙሉ በሙሉ) የተወ ሰው ካፊር እንደሆነ ተገንዝበናል፡፡ ሶላትን


መተው የሚያስከትለው ሸሪዓዊ ብይን ምን ይሆን?

መልስ፡- ኩፍር ደረጃ የሚያደርስ ሶላትን መተው ፣ ከኢስላም በማፈንገጥ የሚመጡ


ሸሪዓዊ ብይኖች ሁሉ በእርሱ ላይ ይፈረዳሉ፡፡ እነዚህ ሸሪዓዊ ብይኖች ዱንያዊም
አኼራዊም ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ዱንያዊ ብይን

አንደኛ፡- ሙስሊም የሆነችን ሴት ማግባት አይችልም፡፡ ምክንያቱም ካፊር የሆነ ሰው


ሙስሊም ሴትን ሊያገባ አይፈቀድለትም፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-


ِ ِِ ِ ٍ ِ ِ ِ َّ‫﴿َي أايُّها ال‬
ُ ُُ ُُُْ َِ‫اّللُ أ ْاَِا ُ ِبِِميااِن َّن فاِإ َْ ا‬
‫وه َّن‬ َّ ‫وه َّن‬
ُ ُ‫ات ُم اهاجارات فا ْامُاحن‬ ُ ‫ين اآمنُوا ِذاا اجاء ُك ُ الْ ُُ ْؤمنا‬ ‫ا‬ ‫ذ‬ ‫ا ا‬
﴾ ُْ‫وه َّن ِ اَل الْ ُك َّفا ِر اال ُه َّن ِح ٌّ ََّّل‬ ِ ٍ ِ
ُ ُ‫ُم ْؤمناات فا اال تا ْرجع‬
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ምእምናት ስደተኞች ሆነው በመጧችሁ ጊዜ
(ለሃይማኖት መሰደዳቸውን) ፈትኑዋቸው፡፡ አላህ በእምነታቸው ይበልጥ ዐዋቂ
ነው፡፡ አማኞችም መሆናቸውን ብታውቁ ወደ ከሃዲዎቹ አትመልሱዋቸው፡፡
እነርሱ (ሴቶቹ) ለእነርሱ የተፈቀዱ አይደሉምና፡፡” አል ሙምተሒና፡

﴾ْ‫ني اح ََّّت يُ ْؤِمنُوا‬


‫﴿ اوالا تُنك ُحواْ الْ ُُش ِرك ا‬
ِِ ِ
15/99
“(በአላህ) አጋሪ የሆኑ ሴቶች እስከሚያምኑ ድረስ አታግቡዋቸው፡፡” አል በቀራህ፡

ለማይሰግድ ሰው ሴት ልጁን ከሰጠ ኒካሁ ውድቅ ይሆናል፡፡ እርሷም ለእርሱ ሀላል


(የተፈቀደች) ልትሆንለት አትችልም፡፡ አላህ ወደኢስላም እንደገና ከመራው እና
ተጸጽቶ ከተመለሰ ዓቅዱ (የጋብቻው ውል) እንደገና መደረግ አለበት፡፡

ሁለተኛው፡- “ወልይነቱ (ሀላፊነቱ) ውድቅ ይሆናል” ሴት ልጁን ለመዳር ወልይ


መሆን አይችልም፡፡ ምክንያቱም ካፊር በሙስሊም ላይ ወልይነት የለውም፡፡

ሶስተኛው፡- ለካፊሮች አላህ በሙእሚኖች ላይ መንገድ ባለማድረጉ ልጆቹን የማሳደግ


መብቱ ከእርሱ ላይ ይነሳል፡፡

አራተኛው፡- እርሱ ያረደው ሀራም (እርም) ነው፡፡ ምክንያቱም ከእርድ መስፈርቶቸ


አንዱ አራጁ ሙስሊም ወይም የመጽሐፍ ባለቤት አይሁድ ወይም ነሷራ መሆን
አለበት፡፡ ሙርተድ ደግሞ ከእነዚህ መካከል አይደለም፡፡ በመሆኑም እርሱ ያረደው
ሀራም ነው፡፡

አምስተኛው፡- በመካና በክልሏ መግባት አይፈቀድለትም፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

ْ ‫س فاالا يا ْقاربُواْ الْ اُ ْْ ِج اد‬


﴾‫اِلاار اام با ْع اد اَ ِام ِه ْ اه اذا‬ ِ َِّ ِ َّ
‫﴿ اَي أايُّ اها الذ ا‬
ٌ ‫ين اآمنُواْ َّناا الْ ُُ ْشرُكو اَ اَنا‬
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አጋሪዎች እርኩሶች ብቻ ናቸው፡፡ ከዚህም
ዓመታቸው በኋላ የተከበረውን መስጊድ አይቅረቡ፡፡” አት ተውባህ፡

ስለዚህ ሶላት የማይሰግዱ ሰዎችን በመካና በክልሏ ውስጥ እንዲገቡ ማመቻቸት


ተገቢ አይደለም፡፡
16/99
የአኼራ ሸሪዓዊ ብይን፡- ከሞተ አይታጠብም ፣ አይከፈንም ፣ በእርሱ ላይ አይሰገድም
፣ አላህ ይማረው ተብሎ ዱዓ አይደረግም ፣ ቦታ ተፈለጎ ለብቻው ይቀበራል እንጅ
ከእነርሱ ባለመሆኑ ከሙስሊሞች መቃብር አይቀበርም ፡፡ አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ
አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

ُْ ‫ني اَّلُْ أ َّاِن‬ ِ ِ ِ ِ ِ ِ َّ‫َّب وال‬ ِ‫﴿ما اكا اَ ل‬


‫ين اآمنُواْ أاَ يا ُْْا ْغفُرواْ ل ِْ ُُ ْش ِرك ا‬
‫ني اولا ْو اكاتُواْ أ ُْوِِل ُِ ْراَب من با ْعد اما تاًا َّ ا‬ ‫ذ‬
‫ها ا‬ ِ ِ‫ن‬ ِ ‫ا‬
﴾ ِ ْ‫اْلا ِح‬ْ ‫اب‬ ُ ‫اص اح‬ْ‫أ‬
“ለነብዩና ለነዚያ ላመኑት ለአጋሪዎቹ የዝምድና ባለቤቶች ቢሆኑም እንኳ እነሱ
(ከሓዲዎቹ) የእሳት ጓዶች መሆናቸው ከተገለጸላቸው በኋላ ምህረትን ሊለምኑ
የሚገባ አልነበረም፡፡” አት ተውባ፡

“አላህ ይቅርታ መጠየቅን የከለከለው ለሙሽሪኮች እንጅ ሶላትን ለተው ሰዎች


አይደለም፡፡” የሚል ጥያቄ ቢነሳ መልሱ ሶላት የተው ሰዎች አጋሪ ወይም ከሐዲ
እንደሆኑ ረሡል ‫ﷺ‬ በሚከተለው ሐዲሳቸው ግለጽ አድርገዋል የሚል ነው፡-

"‫"بين الرجل وبين الشرك والكفر ترك الصالة‬

“በሰውየው እና በሽርክ በክሀደት መካከል ሶላትን መተው ነው” ሙስሊም፡

ሶላትን መተው ከሽርክ ዓይነቶች አንዱ ነው፡፡

ሌላው አኼራዊ ብይን፡- በትንሳኤ ቀን ፊርዓውን ፣ ሃማን ፣ ቃሮን ፣ ኡበይ ብን ኸለፍ


ከተባሉና ፍጻሜያቸው እሳት ከሆኑ የክሀደት መሪዎች ጋር ይቀሰቀሳል፡፡ አህመድ፡

ዳሪሚይ፡

የሶላትን ግዴታነት ሲያስተባብል እንጅ በስንፍና ሶላትን የተወው ሰው ከኢስላም


የሚያስወጣው ክህደት ሳይሆን ከክህደት በታች ክህደት ነው የሚሉ ዓሊሞች አሉ የሚል
17/99

ጥያቄ ቢነሳ ለዚህ የምንሰጠው መልስ፡ - ልክ ነው ይህ ነጥብ የልዩነት ነጥብ በመሆኑ


ወደ ቁርኣንና ወደሐዲስ መመለስ አለብን፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

﴾‫ْب‬ِ ِ ِ ِْ ‫اّلل رِِ َِاْ ِه تاوَّك‬ ِ َِّ ‫﴿وما اخُ ِا ْفُ فِ ِْه ِمن شي ٍء فاح ْكُه ِ اَل‬
ُ ‫ت او لاْْه أُت‬
ُ ‫اّلل ذال ُك ُ َُّ ا ه ا ْ ا‬ ُُ ُ ْ ‫ا‬ ُْ ‫اا ْا‬
“ከምንም ነገር ያ በእርሱ የተለያዩበት ፍርዱ ወደ አላህ ነው፡፡ “እርሱ አላህ
ጌታዬ ነው፡፡ በእርሱ ላይ ተጠጋሁ ፣ ወደርሱም እመለሳለሁ”(በላቸው)፡፡ አሽ ሹራ፡

ِ ِ ‫ول َِ ُكنُ تُؤِمنو اَ ًِبّللِ والْْ وِم‬


ِ ‫الرس‬ ِ ‫﴿فاِإَ تانازَُ ِف شي ٍء فارُّدوه ِ اَل‬
‫اح اْ ُن‬ ‫اَيخ ِر اذل ا‬
ْ ‫ك اخ ْريٌ اوأ‬ ْ‫ُْ ْ ُ ه ا ا‬ ُ َّ ‫اّلل او‬
‫ا ا ُْ ْ ا ْ ُ ُ ه‬
﴾‫اَتْ ِويالا‬

“በማንኛውም ነገር ብትከራከሩ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ብትሆኑ


የተከራከራችሁበትን (ነገር) ወደ አላህና ወደ መልእክተኛው መልሱት፡፡ ይህ
የተሻለ መጨረሻውም ያማረ ነው፡፡” አን ኒሳእ፡

ይህን ጉዳይ ወደአላህና ወደረሡል ‫ﷺ‬ ከመለስነው ብይኑ የሚያርፈው የሶላትን


ግዴታነት በማስተባበል ሳይሆን በመተው ብቻ መሆኑ ግልጽ ይሆንልናል፡፡ በአላህ ህግጋት
ዙሪያ ከረሡል ‫ﷺ‬ የበለጠ ህጉን አውቃለሁ የሚል አለ? ለፍጥረታት ከረሡል ‫ﷺ‬

የበለጠ ታማኝ ነኝ ብሎ የሚሞግት አለ? በሚናገረው ንግግር ከረሡል ‫ﷺ‬ የበለጠ


ግልጽ አድርጌ እናገራለሁ ብሎ የሚሞግት አለ? ከረሡል ‫ﷺ‬ የበለጠ በአመለካከት
ቅን ወይም መልካምን የሚሻ አለ? በእነዚህ አራት ባህሪያት ላይ የተካንሁ ነኝ ብሎ
የሚሞግት አንድም ሰው አይኖርም፡፡ ስለዚህ ረሡል ‫ﷺ‬ በአላህ ሸሪዓ ከፍጡሮች ሁሉ
አዋቂ ፣ ለአላህ ባሮች ትክክለኛ መካሪ ፣ የተብራራ ንግግር የሚናገሩ ከሆኑ እርሳቸው
18/99
አንድ ሰው ከሀዲ የሚሆነው ሶላትን በማስተባበሉ ሳይሆን በመተው ብቻ እንደሆነ
በሚከተሉት ሐዲሶቻቸው ግልጽ አድርገው ተናግረዋል፡-

“በእኛ እና በእነርሱ (በከሐዲዎች) መካከል ያለው ልዩነት ሶላትን መተው ነው፡፡ እርሷን
የተወ በእርግጥ ካደ” አህመድ፡ ነሳኢይ፡ ቲርሚዚይ፡

ወይም “በግለሰቡ እና በሽርክ ወይም በክህደት መካከል ሶላትን መተው ነው” ሙስሊም፡

ከዚህ የበለጠ ማብራራት የት ይምጣ? ሸሪዓዊ ብይኑ የተቆራኘው በማስተባበሉ


ሳይሆን ሶላትን በመተው ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው ረሡል ‫“ﷺ‬ሶላትን የተወ”
በማለት የተናገሩትን “ሶላትን ያስተባበለ” በሚል ጽንሰ ሐሳብ ነው የምገነዘበው ካለ
ይህ ሰው የረሡልን ‫ﷺ‬ ግልጽ ማስረጃ ከሁለት ነገሮች አንጻር እንዳጣመመው ምላሽ
እንሰጠዋለን፡፡

አንደኛው፡- ረሡል ‫ﷺ‬ ሸሪዓዊ ብይን የሰጡበትን “ሶላትን የተወ” የሚለውን ጽንሰ
ሐሳብ ውድቅ አድርገኸዋል፡፡

ሁለተኛው፡- ሸሪዓዊ ብይን የተቆራኘበትን “ሶላትን የተወ” በሚለው ምትክ “ሶላትን


ያስተባበለ” የሚል ሌላ ሸሪዓዊ ብይን ተክተሀል፡፡ “የተዋት ሰው በእርግጥ ካደ”
ከሚለው የረሡል ‫ ﷺ‬ንግግር “ያስተባበላት በእርግጥ ካደ” የሚል የታለ?

አንድ ሰው የሶላትን ግዴታነት ካስተባበለ ሶላት ቢሰግድ እንኳ ከሀዲ ነው፡፡

“የሶላት መስፈርቶች”

ጥያቄ፡ - የሶላት መስፈርቶች እነማን ናቸው? እርሷን ተከትለው የሚመጡ ህጎችስ


ምን ምን ናቸው?
20/99
መልስ፡- የሶላት መስፈርቶች ፡ ሶላት ትክክል እንዲሆን የሚያደርጉ ነገሮች ናቸው፡፡

የሶላት መስፈርቶች በርካታ ናቸው፡፡ ከነዚህ መካከል ዋናው እና አንገብጋቢው


“ወቅት” ነው፡፡ አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

﴾‫وت‬
‫ني كُِا ااًب َّم ْوُِ ا‬ِِ
‫ت اَِاى الْ ُُ ْؤمن ا‬ َّ ََّ ِ﴿
ْ ‫الصالااة اكاتا‬
“ሶላት በምእምናን ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናትና፡፡” አን ኒሳእ፡

እያንዳንዱ ሙስሊም አላህ ያስቀመጠውን የሶላት ወቅት መጠበቅ ግዴታው ነው፡፡


እነዚህን የሶላትን ወቅቶች አላህ በቁርኣኑ በጥቅል የተናገረ ሲሆን ረሡል ‫ﷺ‬ ደግሞ
በሐዲሳቸው በዝርዝር አብራርተውታል፡፡

የቁርኣን ማስረጃው፡

﴾‫ودا‬ ِ ِ َّ ِِِ‫﴿أا‬
‫س ِ اَل اغ اْ ِق الَِّْْ ِ اوُِ ْرآ اَ الْ اف ْج ِر ِ ََّ ُِ ْرآ اَ الْ اف ْج ِر اكا اَ ام ْش ُه ا‬
ِ َُّ
ْ ‫الصالااة ل ُدلُوك الش‬
“ሶላትን ከጸሐይ መዘንበል እስከ ሌሊት ጨለማ ድረስ ስገድ፡፡ የጎህንም ሶላት
ስገድ፡፡ የጎህ ሶላት (መላእክት) የሚጣዱት ነው፡፡” አል ኢስራእ፡

“ሊዱሉኪ ሸምስ” ማለት የጸሐይ መዘንበልን ይጠቁማል፡፡

“ኢላ ገሰቂ ለይል” የሚለው ደግሞ እስከግማሽ ሌሊት ድረስ ያለውን ወቅት

ይጠቁማል፡፡ ምክንያቱም የጨለማው ጠንካራው ክፍል እስከሌሊቱ ግማሽ ድረስ ነው፡፡


በእነዚህ ሁለት የቁርኣን አንቀጾች ማለትም ጸሐይ ዘንበል ካለችበት ጊዜ አንስቶ እስከ
ሌሊት ጨለማ ድረስ አራት የሶላት ወቅቶችን አካቷል፡፡ እነርሱም ዙሁር ፣ ዓስር ፣
መግሪብ እና ዒሻእ ናቸው፡፡ እነዚህ የሶለት ወቅቶች በመካከላቸው መለያ ሳይኖራቸው
ተከታታይ ሆነው የተቀመጡ ናቸው፡፡
20/99
የዙሁር ወቅት፡ ከጸሐይ መዘንበል ጀምሮ የእያንዳንዱ ጥላ በቁመቱ ልክ እስኪሆን ድረስ
ነው፡፡

የዓስር ወቅት፡ ተመራጭ የሆነው ወቅት የእያንዳንዱ ሰው ጥላ በቁመቱ ከሆነበት ጊዜ


አንስቶ እስከ ጸሐይ ወደቢጫነት እስክትቀየር ድረስ ነው፡፡ ለተቸገሩ ሰዎች ደግሞ
ጸሐይ እስክትጠልቅ ድረስ ባለው የጊዜ ክፍተት ይሆናል ማለት ነው፡፡

የመግሪብ ወቅት፡ ከጸሐይ መጥለቅ ጀምሮ ሸፈቁ (ቀዩ) እስኪጠፋ ድረስ ነው፡፡

የዒሻ ወቅት፡ ሸፈቁ (ቀዩ) ከጠፋበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ሌሊቱ ግማሽ ድረስ ይቆያል፡፡

እነዚህ አራት ወቅቶች እርስ በርሳቸው የተያያዙ ናቸው፡፡ ከግማሽ ሌሊት ጀምሮ ፈጅር
እስኪወጣ ድረስ ፈርድ ሶላት ምንሰግድበት ጊዜ አይደለም፡፡

የፈጅር ወቅት፡ ከፈጅር (ወጋገኑ) መውጣት ጀምሮ እስከ ጸሐይ መውጣት ድረስ
ይዘልቃል፡፡

“ሶላትን ከጸሐይ መዘንበል እስከ ሌሊት ጨለማ ድረስ ስገድ፡፡” ከዚያም


በመቀጠል “የጎህ ሶላት (መላእክት) የሚጣዱት ነው፡፡” በማለት አላህ ተናግሯል፡፡

የረሡል ‫ﷺ‬ ሱና ደግሞ እነዚህን ወቅቶች የበለጠ ግልጽ አድርጎታል፡፡

አላህ በባሮች ላይ ግዴታ ያደረጋቸውን እነዚህን ወቅቶች ማንም ሰው መጦ ወደፊትም


ወደኋላም ማድረግ አይችልም፡፡ ተክቢረተል ኢህራም የሚያደርግባትን ወቅት ያክል
እንኳ ቢሆን ከወቅቷ ቢያስቀድም ሶላቱ ትክክል አይሆንም፡፡ ምክንያቱም ሶላት ግዴታ
የሚሆነው በወቅቱ ነው፡፡ በእንቅልፍ ፣ በመርሳት እና በመሳሰሉ ምክንያቶች ሶላቱን
በወቅቱ ባይሰግድ እንኳ ምክንያቶቹ እንደተወገዱ ወዲያውኑ የመስገድ ግዴታ አለበት፡፡
21/99
ነብዩ ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-

"‫ ال كفارة لها إال ذلك‬،‫"من نام عن صالة أو نسيها فليصلها إذا ذكرها‬

“ከሶላቱ የተኛ ወይም የረሳ ያስታወሰ ጊዜ ይስገዳት ፤ እርሱ ካልሆነ ሌላ ማካካሻ


የለውም፡፡” የሚከተለውን ቁርኣናዊ አንቀጽ በማስከተል አነበቡ፡-

﴾‫الص اال اة لِ ِذ ْك ِري‬


َّ ِِِ‫﴿ اوأا‬

“ሶላትንም (በእርሷ) እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡” ጦሃ፡ ሙስሊም፡

ሸሪዓዊ ምክንያት ሳይኖረው አላህ ከደነገገው ወቅት ውጭ አንድ ሽ ጊዜ እንኳ


ቢሰግድ ሶላቱ ትክክል አይሆንም፡፡ ሶላቷን በማሳለፉ ከተጠያቂነት ነጻ አይሆንም፡፡

ለዚህ ማስረጃው የሚከተለው የረሡል ‫ﷺ‬ ሐዲስ ነው፡-

"‫"من عمل عمال ليس عليه أمرنا فهو رد‬

“በእርሱ ላይ የእኛ ትእዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ እርሱ ተመላሽ ነው፡፡” (ሙስሊም፡ 1718, ቡኻሪ
“ኪታቡ አል’ኢዕቲሷም ቢልኪታቢ ወስ’ሱነቲ” ላይ በተዕሊቅ አውርተውታል)

ወቅቱ እስኪያልፍ ድረስ ቆይቶ ሶላቱን የሰገደ ሰው አላህ እና ረሡል ‫ﷺ‬

ባላዘዙት መልኩ በመስገዱ ስራው በእርሱ ላይ ተመላሽ ትሆንበታለች፡፡

ከሶላት መስፈርቶች መካከል፡ “አውረትን (ብልትን) መሸፈን ነው”

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

﴾ْ‫ند ُك ِه ام ْْ ِج ٍد وُكُِواْ اوا ْشاربُواْ اوالا تُ ْْ ِرفُوا‬ ‫﴿ اَي باِِن ا‬


‫آد ام ُخ ُذواْ ِزينا ُا ُك ْ َِ ا‬
“የአደም ልጆች ሆይ! ሃፍረተ ገላችሁን (የሚሸፍኑትን) ጌጦቻችሁን
በመስገጃው ሁሉ ዘንድ ያዙ፡፡ ብሉም ፣ ጠጡም ፤ አታባክኑም፡፡” አል አዕራፍ፡
22/99
ልብስን በተመለከተ ረሡል ‫ ﷺ‬ለጃቢር ብን ዓብዲላህ 4 የሚከተለውን ነግረውታል፡-

"‫ وإن كان واسعا فالتحف به‬،‫"إن كان ضيقا فائتزر به‬

“ጠባብ ከሆነ አሸርጠው ፤ ሰፊ ከሆነ ደግሞ በእርሱ ተጠቅለልበት” ቡኻሪ፡

ቡኻሪ በዘገቡት ደግሞ የአላህ መልእክተኛ ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፈዋል፡-

"‫"ال يصلي أحدكم في الثوب الواحد ليس على عاتقه منه شيء‬

“ከእናንተ መካከል ከጫንቃው ላይ አንዳች ነገር (ጨርቅ) ጣል ሳያደርግ በአንድ ልብስ


ብቻ አይስገድ፡፡” ሙስሊም፡

ይህ ሐዲስ የሚጠቁመን በሶላት ጊዜ ሰውነታችን መሸፈን እንደሚገባው ነው፡፡ በዚህ


ላይ የዑለሞች ስምምነት እንዳለበት ኢብን ዓብዱል በር -ረሂመሁሏህ- አረጋግጧል፡፡
ሰውነቱን በልብስ መሸፈን እየቻለ እርቃኑን የሰገደ ሰው ሶላቱ ትክክል አይሆንም፡፡

ከሶላት መስፈርቶች መካከል፡ “ንጽህና” ነው፡፡ ንጽህና ሲባል ሁለት አይነት ነው፡፡
ውዱእ ከሚያስፈቱ ነገሮች መጽዳትና ከነጃሳ (ከቆሻሻ) መጽዳት ናቸው፡፡

የመጀመሪያው፡ ውዱእ ከሚያስፈቱ ነገሮች መጽዳት ሲሆን እነርሱም ሁለት አይነቶች


ናቸው፡፡ ትጥበት ግዴታ የሚያስደርግ ትልቁ ውዱእ መፍታት ሲሆን ፣ ሁለተኛው ደግሞ
ውዱእ ግዴታ የሚያስደርግ ትንሹ ውዱእ መፍታት ነው፡፡

ከዚህ ቦታ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ነገር ውዱእ ፈቶ ውዱእ ማድረግ ወይም


ትጥበት ኖሮበት መታጠብ እንድንርቃቸው ሳይሆን በሸሪዓ መፈጸም ያለባቸው ነገሮች
ናቸው፡፡ ከእውቀት ባለቤቶች ዘንድ የታወቀው መርሆና ህግ ደግሞ እንድንርቀው ትዕዛዝ
የተላለፈበትን ነገር እንጅ እንዲተገበር የታዘዝነውን ነገር መተው ምክንያት አያሰጥም፡፡
23/99
በዚህ መሰረት አንድ ሰው ውዱእን ረስቶ ሶላት ቢሰግድ ፣ በመርሳቱ ምክንያት
ሐጢያት የለበትም ነገር ግን ውዱእ አድርጎ እንደገና ሶላቱን የመመለስ ግዴታ አለበት፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

﴾‫اخطاأْ اَن‬
ْ ‫﴿ اربَّناا الا تُ اؤاخ ْذ اَن َِ تَّْْناا أ ْاو أ‬
ِ ِ

“ጌታችን ሆይ! ብንረሳ ወይም ብንስት አትያዘን ፤ (አትቅጣን)” አል በቀራህ፡

በዚህ ህግ መሰረት ብቻውን የሰገደም ይሁን ኢማም ሆኖ ያሰገደ ምንም ልዩነት


የለውም፡፡ ስለዚህ ያለውዱእ የሰገደ ወይም ኢማም ሆኖ ያስሰገደ ሰው ሶላቱን እንደገና
መመለስ አለበት፡፡ ነገር ግን ኢማም ሆኖ እያሰገደ መሀል ላይ ውዱእ መፍታቱን
ካስታወሰ ከተከታዮች መካከል አንድ የሚያሰግድ ሰው ተክቶ መሄድ ይችላል፡፡
ኢማሙ ይህን ካላደረገ ተከታዮች ከመካከላቸው አንድ ሰው በመተካት ሶላታቸውን
መጨረስ ይችላሉ፡፡ ሶስተኛው አማራጭ ሁሉም ተከታይ ሶላታቸውን በአዲስ መልክ
ሳይሆን በነፍስ ወከፍ የራሳቸውን ሶላት ጨርሰው መውጣት ይችላሉ፡፡ ተከታዮች ሶላት
ሰግደው ሲጨርሱ የኢማሙን ውዱእ መፍታት ቢያውቁ ሶላታቸውን እንደአዲስ
የመመለስ ግዴታ የለባቸውም፡፡ ጃሂል ሆኖ ያለውዱእ ሶላቱን የሰገደ ወይም የግመል ስጋ
ውዱእ የሚያስፈርስ መሆኑን ያላወቀ የግመል ስጋ በልቶ ሶላቱን ቢሰግድ ባለማወቃቸው
ሐጢያት የለባቸውም እንጅ ካወቁ በኋላ ሶላታቸውን የመመለስ ግዴታ አለባቸው፡፡

“ረስቶ ያለውዱእ ሶላት ያሰገደ ኢማም ሸሪዓዊ ብይን”

ጥያቄ፡- ኢማሙ ውዱእ መፍታቱን ያወቀው ሶላት ካጠናቀቀ በኋላ ነው፡፡ ታዲያ
እርሱም ይሁን ተከታዮች ሶላታቸውን የመመለስ ግዴታ አለባቸው?
መልስ፡- ኢማሙ እንጅ ተከታዮች ሶላታቸውን የመመለስ ግዴታ የለባቸውም፡፡ እነርሱ
24/99
የሶላተል ጀማዓን ምንዳ ሙሉ በሙሉ ያገኛሉ፡፡
“ውዱእ ያደረገ ሰው ተየሙም ባደረገ ሰው ተከትሎ የመስገድ ሸሪኣዊ ብይን”
ጥያቄ፡ - ተየሙም ያደረገ ሰው ውዱዕ ያደረጉ ሰዎችን ኢማም ሆኖ ማሰገድ ይችላል?

መልስ፡- አዎ! ውዱእ ላደረገው ሰው ተየሙም ያደረገ ሰው ኢማም መሆን ይችላል፡፡


ምክንያቱም ሁሉም በተፈቀደ የጦሃራ መንገድ ነው እየሰገዱ ያሉት፡፡ በተለያየ ምክንያት
ውሃን ተጠቅሞ ውዱእ ማድረግ ያልቻለ ሰው ተየሙም አድርጎ መስገድ ይችላል፡፡ ውሃ
ማግኘት ያልቻለና ተየሙም አድርጎ የሰገደ ውሃ ሳያገኝ ወር እንኳ ቢቆይ የሰገደው
ሶላቱ ትክክል ነው፡፡ ወይም በሽተኛ ሆኖ በውሃ ምትክ ተየሙም እያደረገ ቢሰግድ
በተየሙም የሚሰገደው ሶላት ትክክል ነው፡፡

በሸሪዓዊ ምክንያት ውሃን መጠቀም ሳይችል ቀርቶ በተየሙም ሲሰግድ የቆየ ሰው


ችግሩ ሲወገድ በተየሙም የሰገድከው ሶላት ለሁለተኛ ጊዜ ይመለስ አይባልም፡፡
ምክንያቱም ተየሙም ውሃን ተክቶ እንዲሰራ በሸሪዓ የተደነገገ ነው፡፡ አላህ በተከበረው
ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

﴾َ‫يد لُِْطا َّهارُك ْ اولُُِِْ َّ تِ ْع اُُاهُ اَِاْْ ُك ْ لا اعَِّ ُك ْ تا ْش ُكُرو ا‬


ُ ‫اّللُ لِْا ْج اع ا اَِاْْ ُك ِهم ْن احارٍج اولا ِكن يُِر‬
‫يد ه‬ُ ‫﴿ اما يُِر‬
“አላህ በናንተ ላይ ምንም ችግር ሊያደርግ አይሻም፡፡ ግን ታመሰግኑ ዘንድ
ሊያጠራችሁና ጸጋውን በእናንተ ላይ ሊሞላ ይሻል፡፡” አል ማኢዳህ፡

ነብዩ ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-

"‫"جعلت لي األرض مسجدا وطهورا‬

“መሬት ለእኔ መስጊድ ተደርጋልኛለች ፤(አፈሯም በተየሙም) ንጽህናን መጠበቂያ


ተደርጎልኛል፡፡” ቡኻሪ፡
25/99
ሁለተኛው የሶላት መስፈርት ከነጃሳ (ከቆሻሻ) መጽዳት፡ ሶስት ቦታዎች ከነጃሳ
(ከቆሻሻ) መጽዳት አለባቸው፡፡

አንድ ሰው ከመስገዱ በፊት ከአካሉ ፣ ከልብሱና ከሚሰግድበት ቦታ ላይ ቆሻሻዎች


መወገድ አለባቸው፡፡ ከአካል ላይ ቆሻሻ መጽዳት እንዳለበት የሚጠቁመው የሚከተለው
የነብዩ ‫ﷺ‬ ሐዲስ ነው፡፡

የአላህ መልእክተኛ ‫ﷺ‬ በሁለት ቀብሮች በኩል አለፉ፡፡ ከዚያም የሚከተለውን


ተናግሩ፡-

"‫ أما أحدهما فكان ال يستبرئ من البول‬،‫"إنهما ليعذبان وما يعذبان في كبير‬

“እነዚህ ሁለቱ ይቀጣሉ በከባድ አይደለም የሚቀጡት ፤ ከሁለቱ አንደኛው ከሽንቱ


አይጸዳም ነበር፡፡” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

እንደዚሁ ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ ነብዩ ‫ﷺ‬ ሀይድ ያየች ሴት የሀይድ
ደም ከልብሷ ላይ ከነካ ትጠብና በእርሱው ትስገድ በማለት ትዕዛዝ አስተላልፈዋል፡፡

ልብስን ከነጃሳ (ከቆሻሻ) ማጽዳት ግዴታ እንደሆነ ከሚጠቁሙ መረጃዎች መካከል


የሚከተለው ሐዲስ ነው፡-

ከነብዩ ‫ﷺ‬ ዘንድ አንድ ምግብ ያልበላ ህጻን መጣላቸውና ከጭናቸው ላይ


አስቀመጡት፡፡ ወዲያውኑ ሽንቱን ሸና፡፡ ውሃ የያዘ እቃ አስመጡና ከሽንቱ ላይ
አፈሰሱበት፡፡

የሚሰገድበት ቦታ ከቆሻሻ መጽዳት አለበት፡ ለዚህ ማስረጃው አነስ ያስተላለፈው ሐዲስ


ነው፡፡
26/99
አንድ የገጠር ሰው ከመስጊዱ በአንድ በኩል ሸና፡፡ ነብዩም ‫ﷺ‬ ከሽንቱ ላይ ውሃ
እንዲደፋበት አዘዙ፡፡ ቡኻሪ፡

ስለዚህ ነጃሳን ከአካሉ ፣ ከልብሱ እና ከሚሰግድበት ቦታ ላይ ማራቅ የግድ ነው፡፡


ነገር ግን ከአካሉ ወይም ከልብሱ ወይንም ከሚሰግድበት ቦታ ቆሻሻ መኖሩን ሳያውቅ
ወይም አውቆ ነበር ነገር ግን ረስቶ ሰግዶ አበቃ፡፡ ካበቃ በኋላ ነጃሳ መኖሩን ቢያስታውስ
ሶላቱ ትክክል ነው፡፡ ድጋሚ የመስገድ ግዴታ የለበትም፡፡

ለዚህ ማስረጃ የሚሆነን አቡዳውድና አህመድ የዘገቡት የነብዩ ‫ﷺ‬ ሐዲስ ነው፡፡
ረሡል ‫ﷺ‬ ሶሃቦችን አንድ ቀን አሰገዱ፡፡ በመካከል ሁለቱንም ጫማዎቻቸውን
አውልቀው ጣሉ፡፡ ሶሃቦችም ረሡልን ‫ﷺ‬ ተከትለው ጫማቸውን አወለቁ፡፡ ሶላት ካበቁ
በኋላ ረሡል ‫ﷺ‬ ጫማዎቻቸውን ለምን እንዳወለቁ ሶሃቦችን ጠየቁ፡፡ “አንተ
ጫማዎችህን ስታወልቅ ስለተመለከትን ነው እኛም ያወለቅን” አሏቸው፡፡ ከዚያም
የሚከተለውን ተናገሩ፡-

"‫ فأخبرني أن فيهما قذرا‬،‫"إن جبريل أتاني‬

“ጅብሪል መጣ ፤ በሁለቱ ጫማዎች ቆሻሻ እንዳለ ነገረኝ” አህመድ፡ አቡዳውድ፡

ሳያውቅ ነጃሳ ስለነካ ሶላት ቢበላሽ ኖሮ ነብዩ ‫ﷺ‬ ሶላታቸውን እንደገና ይመልሱ
ነበር፡፡ አንድ ሙስሊም በሶላቱ መካከል ውዱእ አለማድረጉን ካስታወሰ ሶላቱን
አቋርጦ ውዱእ ማድረግ አለበት፡፡
ረስቶ ውዱእ ሳይኖረው ሰግዶ የጨረሰ ሰው ሶላቱን ይመልስ ፣ ረስቶ ነጃሳ ነክቶት
ሶላቱን የጨረሰ ሰው ደግሞ ሶላቱን መመለስ የለበትም፡፡ በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት
ምንድን ነው? የሚል ጥያቄ ቢነሳ፡፡
27/99
መልሱ ውዱእ ወይም ትጥበት እንድንፈጽመው የታዘዝነው ተግባር ነው፡፡
እንድንፈጽማቸው የታዘዝናቸው ነገሮችን ከረሳን ሶላታችንን የግድ መመለስ አለብን፡፡
ነጃሳን መራቅ ግን ተጠንቀቁት ነው የተባልነው፡፡ ተጠንቀቁት የተባልነውን ነገር
ፈጽመነው ብንገኝ የሰገድነው ሶላት ትክክል ነው የሚሆነው፡፡

ከሶላት መስፈርቶች መካከል “ወደቂብላ መዞር” አንዱ ነው

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

ْ ‫ك اشطْار الْ اُ ْْ ِج ِد‬


﴾‫اِلاارِام‬ ‫اها فا اوِهل او ْج اه ا‬
‫ضا‬
ِ ‫الُْاء فاِان ولهِْ ن‬
‫ك ِف َّ ا ُ ا ا ا‬
‫َّك ًِْ ِاةا تا ْر ا‬ ‫﴿ِا ْد تاارى تا اقُِّ ا‬
‫ب او ْج ِه ا‬
“የፊትህን ወደ ሰማይ መገላበጥ በእርግጥ እናያለን፡፡ ወደምትወዳትም ቂብላ
እናዞርሃለን፡፡ ስለዚህ ፊትህን ወደተከበረው መስጊድ (ወደካዕባ) አቅጣጫ
አዙር፡፡ የትም ስፍራ ብትሆኑም (ስትሰግዱ) ፊቶቻችሁን ወደርሱ አቅጣጫ
አዙሩ፡፡” አል በቀራህ፡

ወደቂብላ አቅጣጫ መዞር አንዱ የሶላት መስፈርት በመሆኑ ከአራት ምክንያቶች


ውጭ አቅጣጫውን ስቶ የሰገደ ሰው ሶላቱ ትክክል አይሆንም፡፡

አንደኛ፡-“ወደቂብላ አቅጣጫ መዞር ያቃተው ሰው” ለምሳሌ፡- በሽተኛ ሆኖ ከቂብላ


አቅጣጫ ውጭ ፊቱን ያዞረ፡፡ ይህ በሽተኛ በራሱም ይሁን በሌላ ሰው ወደቂብላ መዞር
ካልቻለ ባለበት አቅጣጫ ሆኖ ቢሰግድ ሶላቱ ትክክል ይሆናል፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

﴾ ْ ُُ‫اسُاطا ْع‬ َّ ‫﴿فااتَّ ُقوا‬


ْ ‫اّللا اما‬
“አላህንም የቻላችሁትን ያክል ፍሩት፡፡” አት ተጋቡን፡
28/99
ሁለተኛው፡-“አቅጣጫውን ከቂብላ ውጭ አድርጎ ከጠላት የሚሸሽ ሰው”አንድ
ሙስሊም በዚህ ሁኔታ ላይ ከሆነ ወደ ቂብላ አቅጣጫ መዞር ይቀርለታል፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

﴾‫اَن‬
‫﴿فاإ َْ ِخ ْفُُ ْ فا ِر اجاالا أ ْاو ُرْكًا ا‬
“ብትፈሩ እግረኞች ወይም ጋላቢዎች ሆናችሁ (ስገዱ)፡፡” አል በቀራህ፡

ይህ ቁርኣናዊ አንቀጽ ሙስሊሞች በፈረስም ይሁን በእግራቸው ከጠላት በሚሸሹ ጊዜ


ወደቂብላ ቢዞሩ ጠላት ሊያጠቃቸው ስለሚችል በዚያው ባሉበት ሁኔታ አላህን በሶላት
ማስታወስ እንዳለባቸው የሚጠቁም ነው፡፡ ከጠላት የሚሸሹ ሰዎች ወደቂብላ አቅጣጫ
ቢዞሩ ጠላት የሚያጠቃቸው ከሆነ ወደ ቂብላ አቅጣጫ መዞራቸው ይቀርላቸዋል፡፡

ሶስተኛ፡- “በጉዞ ላይ እያለ ትርፍ ሶላት መስገድ የፈለገ ሰው” ጉዞው በፈለገው
አቅጣጫ ቢሆንም ትርፍ ሶላቶችን መስገድ ይቻላል፡፡ ነብዩ ‫ ﷺ‬ሰፈር ሲወጡ ከፈርድ
ሶላቶች ውጭ ፊታቸውን በፈለገው አቅጣጫ አዙረው የሱና ሶላቶችን ይሰግዱ ነበር፡፡

አራተኛ፡- “ቂብላው በየት አቅጣጫ እንደሆነ ያላወቀ ሰው” ብዙ ጥናት አድርጎ


የቂብላውን አቅጣጫ ካላወቀው ቂብላ ነው ብሎ በገመተው አቅጣጫ ይስገድ፡፡ ከሰገደ
በኋላ ቂብላው ቢታወቅ ሶላቱን መመለስ የለበትም፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

﴾‫اخطاأْ اَن‬
ْ ‫﴿ اربَّناا الا تُ اؤاخ ْذ اَن َِ تَّْْناا أ ْاو أ‬
ِ ِ

“ጌታችን ሆይ! ብንረሳ ወይም ብንስት አትያዘን” አል በቀራህ፡

﴾ ْ ُُ‫اسُاطا ْع‬ َّ ‫﴿فااتَّ ُقوا‬


ْ ‫اّللا اما‬
29/99
“አላህንም የቻላችሁትን ያክል ፍሩት፡፡” አት ተጋቡን፡

“ቀሪ የሶላት መስፈርቶች”


ጥያቄ፡- ከዚህ ቀደም የሶላት መስፈርቶችን ወቅት ፣ ብልትን መሸፈን ፣ ንጽህና እና
ወደቂብላ አቅጣጫ መዞርን ተገንዝበናል፡፡ ቀሪ የሶላት መስፈርቶችን እንዲያሟሉልን
እንፈልጋለን?

መልስ፡- ከዚህ ቀደም ለሶላት ትክክለኛነት ከአራት ምክንያቶች በቀር ወደቂብላ


አቅጣጫ መዞር መስፈርት እንደሆነ ገልጸናል፡፡ ከላይ እንደጠቀስነው ወደቂብላ
የማይዞርበት ሁኔታዎች ቢኖሩም ከእያንዳንዱ ሰው የሚፈለገው አላህን መፍራት ፣
ትክክለኛውን ተጠባብቆ መፈጸም ነው፡፡ ነገር ግን ወደቂብላ አቅጣጫ መዞርን
አስመልክቶ የሚነሳ ጉዳይ አለ፡፡ ይህም አንድ ሰው ወደቂብላ አቅጣጫ ሲዞር ካዕባን
በትክክል ማግኘት አለበት ወይስ ወደርሷው አቅጣጫ መዞር ብቻ በቂ ነው፡፡ ለዚህ
መልሱ ለካዕባ ቅርብ ከሆነ እርሷ የቂብላችን መሰረት በመሆኗ ፊት ለፊት እርሷን
መቅጣጨት አለበት፡፡ ነገር ግን እርሷን ለመመልከት የማይችል ሩቅ ያለ ሰው ከሆነ
ግዴታው ወደእርሷ አቅጣጫ መዞር ብቻ ነው፡፡

የአላህ መልእክተኛ ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-

"‫"ما بين المشرق والمغرب قبلة‬

“በምስራቅና በምእራብ መካከል ቂብላ ነው፡፡” ቲርሚዚይ፡

ይህ ለመዲና ነዋሪዎች የተናገሩት ሐዲስ ነው፡፡ አንድ ሰው ከቂብላው የተወሰነ ቢዞር


ጉዳት እንደማያመጣ የእውቀት ባለቤቶች ተናግረዋል፡፡
30/99
የታወቁት የአለም አቅጣጫዎች አራት ናቸው፡፡ እነርሱም “ሰሜን ፣ ደቡብ ፣
ምስራቅ እና ምእራብ” ናቸው፡፡ አንድ ሰው በምስራቅም ይሁን በምእራብ ከካዕባ
እየራቀ በሄደ ቁጥር የእርሱ ቂብላ በሰሜን እና በደቡብ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ከሰሜን
እና ከደቡብ በራቀ ቁጥር ደግሞ ቂብላው በምስራቅና በምዕራብ አቅጣጫ ይሆናል፡፡
ግዴታው የቂብላን አቅጣጫ መከተል ብቻ ነው፡፡

አዎ! ለምሳሌ አንድ ሰው ከመካ በምስራቅ በኩል ቢሆንና ወደሰሜን አቅጣጫ


ቢዞር ትክክል አይሆንም፡፡ ምክንያቱም አቅጣጫውን ወደግራ አድርጓልና፡፡ እንደዚሁ
ወደደቡብ አቅጣጫውን ቢያዞር ትክክል አይሆንም፡፡ ምክንያቱም ቂብላውን ከቀኝ
በኩል አድርጓል ማለት ነው፡፡ እንደዚሁ የሰሜን ሰዎች ወደምእራብ ቢዞሩ ሶላቱ
ትክክል አይሆንም፡፡ ምክንያቱም ቂብላቸውን ከግራ በኩል አድርገዋል፡፡ ወደምስራቅ
አቅጣጫ ቢዞሩ አሁንም ትክክል ሊሆን አይችልም፡፡ ምክንያቱም ቂብላውን ከቀኝ በኩል
አድርገዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት አላህ b የቂብላን አቅጣጫ የምናውቅበት የተለያዩ ዘመናዊ


መሳሪያዎችን ሰጦናል፡፡ እነዚህን የአቅጣጫ ማወቂያ መሳሪያዎች ሰፈር ሲወጣም
ይሁን መስጅድ መስራት ሲፈልግ ይዞት መንቀሳቀስና መውጣት ይኖርበታል፡፡

ከሶላት መስፈርቶች መካከል “ኒያ” አንዱ ነው፡፡ የኒያ ቦታዋ ቀልብ ነች፡፡ ኒያ ለሶላት
መስፈርት የሆነበት ምክንያት እያንዳንዱን የምንሰራውን ስራ ለመለየት ሲባል ነው፡፡
በጥቅል ከተመለከትነው አንድ ሙስሊም ከቤቱ ውዱእ አድርጎ ወደመስጅድ
ሲንቀሳቀስ ሶላት ለመስገድ እንጅ ሌላ ኒያ ኖሮት አይደለም፡፡ ነገር ግን አንዱን አምልኮ
ከሌላው አምልኮ ለይቶ ለመፈጸም የግድ ኒያ ያስፈልጋል፡፡
31/99
ዙህርን ከዓስር ፣ ዓስርን ከመግሪብ ፣ መግሪብን ከዒሻ ፣ ዒሻን ከፈጅር ሶላት ለመለየት
የግድ ኒያ ያስፈልጋል፡፡ ሶላት መስገድ የሚለው ጥቅል ኒያ በቂ ሊሆን አይችልም፡፡ ጥቅል
የሆነው ኒያ ልዩ ከሆነው ኒያ ይለያል፡፡ አጠቃላይ ኒያ ልዩ የሆነውን ኒያ በውስጥ ሊያቅፍ
አይችልም፡፡ ጥቅል የሆነውን ኒያ የነያ ሰው ልዩ የሆነውን ኒያ አልነያም፡፡ ልዩ የሆነውን
ኒያ የነያም ሰው አጠቃላይ የሆነውን ኒያ አልነያም ፡፡

በዚህ ምክንያት አንድ ሰው ጥቅል ከሆነው ኒያ ልዩ ወደሆነው ኒያ ወይም ልዩ


ከሆነው ኒያ ልዩ ወዳልሆነው ኒያ ቢያሸጋግረው ትክክል አይሆንም፡፡ ከጥቅል ልዩ
ወደሆነው ኒያ ከተሸጋገረ ጥቅል የሆነው ኒያ ይበላሻል ፤ እንዲሁም ልዩ ከሆነው ኒያ ሌላ
ልዩ ወደሆነ ኒያ ቢሸጋገር የመጀመሪያውም የሁለተኛውም ይበላሻል፡፡ ይህ ጥቅል ንግግር
በምሳሌ ግልጽ ይሆናል፡፡

አንድ ሰው ትርፍ ሶላትን ነይቶ ወይም ሙጥለቅ (ልቅ) ሶላትን ይሰግዳል፡፡ ሶላት
እየሰገደ ባለበት መካከል ጥቅል የሆነውን የትርፍ ሶላት ኒያ ልዩ ወደሆነው የትርፍ ሶላት
ኒያ ለመቀየር ፈለገ ለምሳሌ ወደራቲባ ሊቀይር ፈለገ፡፡ ይህ ከሆነ ትክክል አይሆንም፡፡
ራቲባ (ረሡል ‫ﷺ‬ ትተዋቸው የማያውቁ ሱና ሶላቶች) እንደሚሰግድ ከተክቢረተል
ኢህራም በፊት መነያት አለበት፡፡ ካለበለዚያ ራቲባ ሊሆን አይችልም፡፡ ነገር ግን ራቲባ
ነበር እየሰገደ ያለው በመካከል ወደጥቅል ወይም ስድ ወደሆነ ትርፍ ሶላት ኒያውን
ለመቀየር ቢፈልግ ትክክል ይሆናል፡፡ ምክንያቱም ልዩ የሆነው ኒያ ልዩውንም ስድ
የሆነውንም ኒያ አጠቃሎ ይዟል፡፡ ልዩ ለሆነው ሶላት የነያውን ኒያ ሲተወው ስድ የሆነው
ኒያ ይቀራል ማለት ነው፡፡

ሌላው ምሳሌ፡- አንድ ሰው በዓስር ኒያ ሶላት ሊሰግድ ገባ፡፡ ከዚያ ከሶላቱ መካከል
32/99
ዙህርን አልሰገደም ነበርና ኒያውን ከአስር ወደዙህር ቢያዞር ዙሁር ሶላትም አስር
ሶላትም ሊሆንለት አይችልም፡፡ የዓስር ሶላት የማይሆነው በኒያ ስለቆረጠው ነው፡፡ ዙህር
ሶላት የማይሆነው ደግሞ ከመጀመሪያው ስላልነያው ነው፡፡ ነገር ግን የዚህን ሸሪዓዊ
ህግጋት የማያውቅ ጃሂል ከሆነ የሰገደው ሶላት ትርፍ ሶላት ሆኖ ይያዝለታል፡፡ ልዩ ሶላቱን
ውድቅ ሲያደርግ ስድ ወይም ጥቅል የሆነው ሶላት ቀረለት ማለት ነው፡፡

ማጠቃለያ፡-

በአምልኳችን ውስጥ ሙጥለቅ (ስድ) የሆነ ኒያ የማይነይት አለ ብየ አልልም፡፡


አንድም ሰው የሚነይት ቢሆን እንጅ ንግግርን አይናገርም ተግባርን አይፈጽምም፡፡ ነገር
ግን የግድ መኖር ያለበት አንዱን ስራ ከሌላው የሚለይ የሆነው ልዩ የሆነው ኒያ ነው፡፡

በኒያ ውስጥ ከሚካተቱ ነጥቦች መካከል ብቻውን ሲሰግድ የቆየ ሰው ሶላት ውስጥ
እያለ ኢማምነትን መነየቱ ወይም ብቻውን ሲሰግድ ከቆየ በኋላ የጀማዓ ሶላት ሲያገኝ
ተከታይነትን ነይቶ መግባት፡፡ በትክክለኛው የዑለሞች አመለካከት እንዲህ አይነቱ የኒያ
ሽግግር ችግር የለውም፡፡ ለመጀመሪያው ምሳሌ አንድ ሰው ብቻውን ሲሰግድ ከቆየ በኋላ
ሌላ ሰው መጦ አብሮት መስገድ ጀመረ ይህ ችግር የለውም፡፡ ለዚህ ማስረጃ የሚሆነው
ረሡል ‫ﷺ‬ የሌሊት ሶላት ብቻቸውን እየሰገዱ ዓብደሏህ ኢብን አባስ 4 ከእንቅልፉ
ተነስቶ ውዱእ አድርጎ ከነብዩ ‫ﷺ‬ ጋር ይሰግድ ነበር፡፡ ይህንንም ተግባር ነብዩ ‫ﷺ‬

አረጋግጠውታል፡፡ በመረጃ ካልሆነ በቀር በትርፍ ሶላት የጸደቀው ሸሪዓዊ ብይን ለፈርድ
ሶላቶችም ይጸድቃል፡፡

አንድ ሰው ብቻውን መስገድ ጀመረ ከኋላ ሌላ ሰው መጣና ተከተለው፡፡ በዚህ ጊዜ


የመጀመሪያው ሰው ኢማም ሁለተኛው ደግሞ ተከታይ ሆነ፡፡ ይህ ችግር የለውም፡፡
33/99
እንደዚሁ በተቃራኒው አንድ ሰው ብቻውን ሲሰግድ ከቆየ በኋላ በጀማዓ የሚሰግዱ
ሰዎችን ተመልክቶ ተከታይ መሆን ቢፈልግ ችግር የለውም፡፡ ይህ መሸጋገር ከአንድ
ባህሪ ወደሌላ ባህሪ እንጅ የመጀመሪያውን ኒያ የሚያበላሽ አይደለም፡፡

እነዚህ ከላይ የጠቀስናቸው መስፈርቶች አንገብጋቢ መስፈርቶችና ልንነጋገርበት የሚገባ


ስለሆኑ እንጅ ለሁሉም ዒባዳ የጋራ የሆኑ መስፈርቶችም አሉ፡፡ ለምሳሌ ፡- ኢስላም ፣
ተምይዝ (ሰባት አመት መሙላቱ) ፣ አቅል ጤናማ መሆን እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

“የሶላት መገለጫዎች”

ጥያቄ፡- የሶላትን ሸሪዓዊ ብይን ፣ ሶላትን የተው ሰዎች ብይን እና የሶላትን መስፈርቶች
ካወቅን በኋላ ስለሶላት መገለጫዎች ደግሞ ማወቅ እንፈልጋለን?

መልስ፡- ሶላትም ይሁን ሌሎች ዒባዳዎችን ማወቅና መገንዘብ በጣም አንገብጋቢ ነው፡፡
ምክንያቱም ከአምልኮ መስፈርቶች ሁለተኛው መስፈርት የሚረጋገጥበትና ረሡልን
‫ﷺ‬ የምንከተልበት ነው፡፡ ነብዩ ‫ﷺ‬ ሶላትን በአግባቡ ተግባራዊ ባደረጉበት አይነት
ሙስሊሞችም ተግባራዊ እንዲያደርጉ ለማድረግ የእርሳቸውን የሶላት ባሕሪያት
የሚያብራሩ የታወቁ ኪታቦችን መማር እንደሚያስፈልግ ነፍሴንም ሙስሊም
ወንድሞቸንም እመክራለሁ፡፡ እኛም አላህ ለትክክለኛው ጎዳና እንዲገጥመን እየተማጸን
የነብዩን ‫ ﷺ‬የሶላት ባህሪያቶች እንደሚከተለው እናወሳዋለን፡፡
አንድ ሰው ከዚህ ቀደም የጠቀስናቸውን የሶላት መስፈርቶች ማለትም - ንጽህና ፣
ብልትን መሸፈን ፣ ወደ ቂብላ መዞር እና መሰል መስፈርቶችን ካጠናቀቀ በኋላ እጆቹን
እስከትክሻው ወይም እስከ ልም ጀሮዎቹ ከፍ በማድረግ “አሏሁ አክበር” ይበል፡፡
ከዚያም የቀኝ እጁን ከግራ ክንዱ ላይ በማድረግ ደረቱ ላይ ያኑር፡፡
34/99
ከዚያም ከነብዩ ‫ﷺ‬ በመጣው ማንኛውም የዱዓ ዓይነት የመክፈቻ ዱዓ ያድርግ፡፡

ለምሳሌ፡ - የሚከተለውን ዱኣ ማድረግ ይችላል፡-

‫ اللهم نقني من‬،‫"اللهم باعد بيني وبين خطاياي كما باعدت بين المشرق والمغرب‬
‫ اللهم اغسلني من خطاياي بالماء والثلج‬،‫خطاياي كما ينقى الثوب األبيض من الدنس‬
"‫والبرد‬

“አሏሁምመ ባዒድ በይኒ ወበይነ ኸጧያየ ከማ ባዓድተ በይነል መሽሪቂ ወልመግሪቢ ፤


አሏሁምመ ነቂኒ ከማ ዩነቀ ሰውቡል አብየዲ ሚነደነሲ ፣ አሏሁምመ ኢግሲልኒ ሚን
ኸጧያየ ቢልማኢ ወስ'ሰልጅ ወልበረድ”

ትርጉሙ፡- “አላህ ሆይ! በእኔ እና በወንጀሌ መካከል ልክ ምስራቅን እና ምእራብን


እንዳራራቅህ አርቅልኝ ፤ አላህ ሆይ! ልክ ነጭ ልብስ ከቆሻሻ እንደሚጸዳው እኔን
አጥራኝ ፤ አላህ ሆይ በውሃ በበረዶ በቆራ ከሀጢያቴ አጥራኝ፡፡” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

ወይም የሚከተለውን የመክፈቻ ዱኣ ማድረግ ይችላል፡-

"‫"سبحانك اللهم وبحمدك وتبارك اسمك وتعالى جدك وال إله غيرك‬

“ሱብሃነከሏሁምመ ወቢሀምዲከ ወተባረከ ስሙከ ወተዓላ ጀዱከ ወላኢላሃ ገይሩከ”

ትርጉም፡-“አላህ ሆይ! ጥራት ይገባህ ስምህም ከሁሉም የላቀ ነው ልቅናህም ከፍ ያለ


ነው ከአንተ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም” አህመድ፡ ነሳኢይ፡ ቲርሚዚይ፡

ወይም ከዚህ ውጭ ባሉ ዱዓዎች ማለት ይችላል፡፡ ከዚያም “አዑዙ ቢላሂ ሚነሽይጧኒ


ረጅም ፤ ቢስሚላሂ ረህማኒ ረሂም” ይበል፡፡

ከዚያም “ፋቲሃን” እና የቻለውን የቁርኣን አንቀጽ ይቅራ፡፡ ፈጅር ሶላት ላይ በላጭ


35/99
የሚሆነው ከረጃጅም ምዕራፎች ፣ በመግሪብ ደግሞ በአብዛኛው ከአጫጭር ምዕራፎች
በሌሎች ሶላቶች ደግሞ መካከለኛ ከሚባሉ ምእራፎች መርጦ መቅራቱ ተመራጭነት
አለው፡፡

ከዚያም “አሏሁ አክበር” በማለት እጁን ከፍ በማድረግ የእጆቹን ጣቶቹ ነጣጥሎ


ከጉልበት ላይ ያድርግ፡፡ ጀርባውን ከቅንጭላቱ ጋር አስተካክሎና ዘርግቶ ፣ ቅንጭላቱን
ሳያንጋጥጥ እንዲሁም በጣም ሳያቀረቅር ይጎንበስ፡፡ “ሱብሃንረቢየል ዓዚም” የሚለውን
ዚክር ሶስት ጊዜ ደጋግሞ ይበል፡፡ ይህ አነስተኛውና የተሟላ የሚባለው ሲሆን ከሶስት
በላይ ቢጨምርም ችግር የለውም፡፡

ከዚያም “ሰሚዓሏሁ ሊመንሐሚደህ” በማለት ልክ በተክቢረተል ኢህራም እና


በሩኩዕ ጊዜ እጆቹን ከፍ እንዳደረገ አሁንም እጆቹን ከፍ አድርጎ ቀና ይበል፡፡ ከዚያም
ቀጥ ብሎ ከቆመ በኋላ የሚከተለውን ይበል፡-

"‫"اللهم ربنا ولك الحمد ملء السماوات وملء األرض وملء ما شئت من شيء بعد‬

“ረበና ወለከል ሀምድ ፤ ሀምደን ከሲረን ጦይበን ሙባረከን ፊህ ፤ ሚልኡሰማዋቲ


ወሚልኡል አርዲ ፣ ማበይነሁማ ወሚልኡ ማሽእተ ሚን ሸይኢን በእዱ” ሙስሊም፡

ከዚያም “አሏሁ አክበር” ብሎ ሱጁድ ያድርግ ፣ ወደሱጁድ ሲወርድ ሁለቱን እጆች


አያንሳ፡፡ ኢብን ዑመር 4 በሱጁድ ጊዜ እጅ እንደማይነሳ ገልጸዋል፡፡ ሱጁድ ሲያደርግ
በጉልበቱ ይውረድ ፤ ከዚያም እጆቹን ያኑር ፤ ከዚያም ግምባሩንና አፍንጫውን መሬት
ያኑር፡፡ በአጠቃላይ በሰባት ብልቶቹ ሱጁድ ያድርግ፡፡ ሰባት የሰውነት ብልቶች የሚባሉት
ግንባር ከአፍንጫ ጋር ፣ ሁለት መዳፎች ፣ ሁለት ጉልበቶች እና የጫማችን ጫፎች
(የእግር ጣቶች) ናቸው፡፡
36/99
ጀርባውን ሳይለጥጥ የክንዱን ጡንቻዎች በማራራቅ ሱጁድ ያድርግ፡፡ በትክሻው ትክክል
እጆቹን ወይም ጣቶቹን የተዘረጉ ፣ የተለጣጠቁና ወደቂብላ የዞሩ አድርጎ “ሱብሃነ
ረቢል አዕላ” የሚለውን ዚክር ሶስት ጊዜ ይበል፡፡ ይህ የተሟላው ሲሆን ከሶስት ጊዜ
በላይ ማድረግም ይችላል፡፡ ሱጁድ ላይ ዱዓን ያብዛ፡፡

ነብዩ ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

‫ وأما السجود فأكثروا فيه الدعاء فقمين أن يستجاب‬،‫"أما الركوع فعظموا فيه الرب‬
"‫لكم‬

“በሩኩዕ ላይ ጌታን አልቁ ፣ ሱጁድ ላይ ደግሞ ዱዓን አብዙ ለእናንተ ዱኣችሁን ለመቀበል
የተገባ ነው፡፡” ሙስሊም፡

ከዚያም ግራ እግሩን ያነጠፈ ቀኙን ደግሞ የተከለ ሆኖ “አሏሁ አክበር” በማለት


ከሱጁድ ይነሳ፡፡ ሁለት እጆቹን ከጭኑ ወይም ከጉልበቱ ላይ አድርጎ ይቀመጥ፡፡
“ረቢግፊር ሊ ወርሀምኒ ወጅቡርኒ ወዓፊኒ ወርዙቅኒ” የሚለውን ዱዓ ያድርግ፡፡
ከዚያም ሁለተኛውን ሱጁድ ያድርግ፡፡

ከዚያም “አሏሁ አክበር” በማለት ከሱጁድ ወደቂያም ይነሳ፡፡ ከዚያም “ፋቲሃን”


እና መጀመሪያው ረከዓ ላይ ካነበበው ቀነስ ያለ የቁርኣን አንቀጽ ይቅራ፡፡ ከዚያም
መጀመሪያ ረከዓ ላይ የሰራቸውን ስራዎች ይስራ፡፡ ከዚያም ግራ እግሩን አንጥፎ የቀኝ
እግሩን በመትከል ለተሸሁድ ይቀመጥ፡፡ አታህያቱንም ይቅራ፡፡ ከዚያም በነብዩ ላይ
ሶለዋት ያውርድ፡፡ ከዚያም የፈለገውን ዱዓ ያድርግ ፡፡ ከዚያም “አስሰላሙአለይኩም
ወረህመቱሏህ” በማለት ወደቀኝ ያሰላምት፡፡ በመቀጠልም “አስሰላሙአለይኩም
ወረህመቱሏህ” ወደግራ ያሰላምት፡፡
37/99
በባለሶስት እና አራት ረከዓ ላይ ለተሸሁድ ሲቀመጥ የአቀማመጡ ስርዓት ከሁለተኛው
ረከዓ ላይ ለተሸሁድ ከምንቀመጠው ይለያል፡፡ ይህ አቀማመጥ “ተወሩክ” የሚል ስያሜ
ያለው ሲሆን ሶስት አይነት የአቀማመጥ ስርዓቶች አሉት፡፡ የመጀመሪያው የቀኝ እግሩን
ይተክላል ፣ በቀኝ ባቱ ስር የግራ እግሩን ያሳልፋል፡፡ ሁለተኛው አይነት ደግሞ የቀኝ
እግሩን ያነጥፋል የግራ እግሩ በባቱ ስር ያልፋል፡፡ ሶስተኛው አይነት ደግሞ የቀኝ እግሩን
ያነጥፋል የግራ እግሩ በቀኝ ባቱና በጭኑ መካከል ያልፋል፡፡

አጠር ባለ ሁኔታ ከረሡል ‫ﷺ‬ የመጣው የአሰጋገድ ስርዓት ይህን ይመስላል፡፡ ስለዚህ
እያንዳንዱ ሙስሊም በቻለው አቅም የእርሳቸውን የአሰጋገድ ስርዓት ለመከተል ጥረት
ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ይህን ሲያሟላ ነው አምልኮቱ የተስተካከለ ፣ ኢማኑ ጠንካራ ፣
ረሡልንም ‫ﷺ‬ በመከተል ብርቱ ሰው የሚባለው፡፡

“በሶላት ውስጥ የእግሮች አቋቋም ስርዓት”

ጥያቄ፡- በሩኩዕ ፣ በሱጁድ ፣ በሁለቱ ሱጁዶች መካከል እንዲሁም ሰጋጁ ሲቆም


እጆችን የት ማስቀመጥ እንዳለበት ነገራችሁን፡፡ የእግሮችን የአቀማመጥ ስርኣት ግን
እስካሁን አልሰማንም፡፡ ሰዎች በአብዛኛው ሲቆሙ በሁለት እግሮቻቸው መካከል
ክፍተትን ያበዛሉ፡፡ ትክሻቸውን ያራርቃሉ፡፡ ይህን አስመልክቶ ትክክለኛው የቱ ነው?

መልስ፡- ስንቆም ተፈጥሯዊ በሆነው አቋቋማችን መቆም አለብን፡፡ ማለትም እግራችንን


በጣም ሳናራርቅ ወይም በጣም ሳናቀራርብ መቆም አለብን፡፡ የአላህ መልእክተኛ ‫ﷺ‬

በሚቆሙና ሩኩዕ በሚያደርጉ ጊዜ እግሮቻቸውን በጣም እንደማያቀራርቡና


እንደማያራርቁ ኢብን ዑመር 4 ተናግሯል፡፡ ይህም “ሸርሁ ሱና” በተባለው ኪታብ
ላይ ተዘግቦ ይገኛል፡፡
38/99
በመቀመጥ ጊዜ ያለውን ከዚህ ቀደም አውስተናል፡፡ በሱጁድ ጊዜ በላጩ ዓኢሻ 6
ባስተላለፈችው ኢብን ኹዘይማ ፣ ሙስሊም እና ነሳኢይ በዘገቡት ትክክለኛ ሐዲስ
መሰረት - ያለምንም ክፍተት አንዱን እግር ከሌላው እግር ጋር በማገናኘት መሬት ላይ
ተክሎ ሱጁድ ማድረግ ነው፡፡ የረሡልን ‫ ﷺ‬የሶላት ባህሪ ከማጠናቀቃችን በፊት ከሶላት
በኋላ አላህን መዝከር አስፈላጊ እንደሆነ ማስታዎስ እንወዳለን፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

﴾ ْ ‫ودا او اَِاى ُجنُوبِ ُك‬ ِ ْ‫الصالااة فااذْ ُكروا‬


‫اّللا ِْا ااما اوُِعُ ا‬
‫ُ ه‬ ‫﴿فاِإ اذا ِا ا‬
َّ ُ ُُ ْْ‫ِض‬

“ሶላትንም በፈጸማችሁ ጊዜ ቆማችሁም ተቀምጣችሁም በጎኖቻችሁም ላይ


ተጋድማችሁ አላህን አውሱ፡፡” አን ኒሳእ፡

ረሡል ‫ﷺ‬ ሶላታቸውን እንዳጠናቀቁ ሶስት ጊዜ ኢስቲግፋር ካደረጉ በኋላ


“አሏሁምመ አንተ ሰላም ወሚንከ ሰላም ተባረክተ ያ ዘልጀላሊ ወልኢክራም” ይሉ

ነበር፡፡ ሙስሊም፡ ከዚያም ሰላሳ ሶስት ጊዜ ሱብሃን አላህ ፣ ሰላሳ ሶስት ጊዜ አሏሁ
አክበር ፣ ሰላሳ ሶስት ጊዜ አልሐምዱ ሊላህ ይበል፡፡ ቡኻሪ፡

ይህን ዚክር ከፈለገ ሱብሃን አላህ ሰላሳሶስት ጊዜ ፣ አልሀምዱ ሊላህ ሰላሳ ሶስት ጊዜ ፣
አሏሁ አክበር ሰላሳ ሶስት ጊዜ ነጣጥሎ ማለት ይችላል፡፡ ወይም “ሱብሃን አላህ ፣
አልሀምዱ ሊላህ ፣ አሏሁ አክበር” በአንድ ላይ ሰላሳ ሶስት ጊዜ ማለት ይችላል፡፡ ሌላም
የዚክር አይነት አለ፡፡ አስር ጊዜ ሱብሃን አላህ ፣ አስር ጊዜ አልሀምዱ ሊላህ ፣ አስር
ጊዜ አሏሁ አክበር በጥቅሉ ሰላሳ ጊዜ መዝከር ይችላል፡፡ ሌላው የዚክር አይነት ደግሞ
“ሱብሃን አላህ ፣ አልሀምዱ ሊላህ ፣ ላኢላሃ ኢልለሏህ ፣ አሏሁ አክበር” የሚለውን
በአንድ ላይ ሀያአምስት ጊዜ መዝከር ይችላል፡፡ በድምሩ መቶ ማለት ነው፡፡
39/99
ዋናው ነገር ከነብያችን የመጣውን ዚክር ማለቱ ነው፡፡ እነዚህን ዚክሮች ከፈለገ አንዱን
በአንዱ በመተካት ከፈለገ ደግሞ ሁሉንም በአንድ ጊዜ ማለት ይችላል፡፡ ስለዚህ ሰዎች
በዚህ ላይ ፍላጎቱ እና መነሳሳቱ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ
የሚከተለውን ተናግሯል፡-

﴾‫اّللا‬
‫﴿فااذْ ُكُرواْ ه‬
“አላህን አውሱ” በቀራህ፡

ቡኻሪ በትክክለኛ ሐዲስ በዘገቡት መስጅድ ውስጥ ከሆነ እነዚህን ዚክሮች ድምጹን
የተወሰነ ከፍ አድርጎ ቢላቸው ተመራጭነት እንዳለው ኢብን አባስ 4 ተናግረዋል፡፡

‫"كان رفع الصوت بالذكر حين ينصرف الناس من المكتوبة على عهد النبي صلى هللا‬
"‫عليه وسلم‬

“በነብዩ ‫ﷺ‬ ዘመን ሰዎች ከፈርድ ሶለት ካበቁ በኋላ በዚክር ድምጻቸው ከፍ ይል
ነበር፡፡” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

በዚክር ድምጽን ከፍ ማድረግ የነብዩ ‫ﷺ‬ እንዲሁም የሶሃቦች ሱና ለመሆኑ


ዓብደሏህ ብን ዓባስ 4 እንደሚከተለው ይናገራሉ፡-

"‫"ما كنا نعرف اقضاء صالة النبي صلى هللا عليه وسلم إال بالتكبير‬

“የረሡልን ‫ ﷺ‬ሶላት ማብቃት የምናውቀው በተክቢራቸው ነበር” ይላል፡፡ ሙስሊም፡

እነዚህን ዚክሮች በፍጥነት ማለቱ ሱና ነው፡፡ ረሡል ድምጻቸውን ከፍ ያደረጉት ሰዎችን


ለማስተማር ነው የሚለው የአንዳንድ ዑለሞች ንግግር ችግር አለበት፡፡ የረሡል ‫ﷺ‬

ስራ መሰረቱ በሽሪዓ የተደነገገ መሆኑ ነው፡፡


40/99
ድምጽ ከፍ ማድረጉ የሸሪዓ ህግ ባይሆን ኖሮ ከዚህ በፊት ለኡመታቸው ድምጻቸውን
ከፍ ሳያደርጉ በንግግር ብቻ ያስተማሯቸው በቂ ይሆን ነበር፡፡ የተፈለገው ማስተማር
ቢሆን ኖሮ ከሶላት በኋላ ዘወትር ድምጻቸውን ከፍ ሳያደርጉ አንድ ጊዜ ወይም ሁለት
ጊዜ ዘክረው ዝም ይሉ ነበር፡፡

“የሶላት ማዕዘናቶች”

ጥያቄ፡- የሶላት ማዕዘናት እንዲብራራልን በጣም እንፈልጋለን?

መልስ፡- በሶላት ውስጥ የሚከሰቱ ነገሮች አርካን ፣ ዋጅባት እና ሱነን በሚል


እንደሚከፈል የእውቀት ባለቤቶች አውስተዋል፡፡ ማዕዘን እና ዋጅባት የሚባሉት
የሚስማሙበት አንዳንድ ሁኔታዎች ቢኖርም በመካከላቸው ግን የተወሰኑ ልዩነቶችም
አሏቸው፡፡

ከማእዘናቶች የተወሰኑትን እንደምሳሌ እናውሳ

የመጀመሪያው፡-“ችሎታ እያለው ቆሞ መስገድ” ይህ ለፈርድ ሶላት ብቻ ማዕዘን


ነው፡፡ አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

﴾‫ني‬ِِ ِ ِ ُِ‫الصالاةِ الْوسطاى و‬ ِ َّ ‫﴿حافِظُواْ َِاى‬


‫ومواْ هّلل ِااتُ ا‬
ُ ‫الصِا اوات و َّ ُ ْ ا‬ ‫ا‬ ‫ا‬
“በሶላቶች (በተለይ) በመካከለኛይቱም ሶላት ላይ ተጠባበቁ፡፡ ታዛዦች
ሆናችሁም ለአላህ ቁሙ፡፡” አል በቀራህ፡

ነብዩ ‫ﷺ‬ ለኢምራን ብን ሁሶይን 4 የሚከተለውን ነግረውታል፡-


"‫ فإن لم تستطع فعلى جنب‬،‫ فإن لم تستطع فقاعدا‬،‫"صل قائما‬

“ቆመህ ስገድ ፣ ካልቻልክ ተቀምጠህ ፣ ካልቻልህ በጎንህ” ቡኻሪ፡


41/99
ሁለተኛው፡- “ተክቢረቱል ኢህራም”

ነብዩ ‫ ﷺ‬ሶላቱን ላበላሸው ሰው የሚከተለውን አስተምረውታል፡-

"‫ ثم استقبل القبلة فكبر‬،‫"إذا قمت إلى الصالة فأسبغ الوضوء‬

“ወደሶላት ለመቆም (ባሰብክ)ጊዜ ውዱእህን በደንብ አዳርስ ፣ ከዚያም ወደቂብላ ዞረህ


አሏሁ አክበር በል” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

“አሏሁ አክበር” የሚለውን ቃል የግድ ማለት አለበት፡፡ “አሏሁ አክበር” በሚለው


ምትክ “አሏሁ አጀል” ወይም “አሏሁ አዕዞም” ማለት የተከለከለ ነው፡፡ ሀምዝን
በጣም በመሳብ “አአአሏሁ አክበር” ማለትም ክልክል ነው፡፡ ምክንያቱም
ወደኢስቲፍሃም (ወደጥያቄ) ተቀየረች ማለት ነው፡፡ ባእ’ን በመሳብ “አሏሁ
አክባር” ማለትም ትክክል አይሆንም፡፡ አክባር ያለው ከበረ ላለው ቃል ብዙ ቁጥርን
ጠቋሚ በመሆኑ አላህ ከሁሉ በላይ ላቀ የሚል ትርጉም ሳይሆን ከበሮ የሚል ትርጉም
ይይዛል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ሀምዝን ወደ ዋው በመቀየር “አሏሁ ወክበር” ይላሉ፡፡
ይህ በዓረብኛ ቋንቋ ትርጉሙን የሚያበላሽ ባለመሆኑ ሶለቱን አያበላሽበትም፡፡

ሶስተኛው ማዕዘን፡ “ፋቲሃን መቅራት”

ነብዩ ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

"‫"ال صالة لمن لم يقرأ بفاتحة الكتاب‬

“ፋቲሃን ያልቀራ ሰው ሶላት የለውም፡፡” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

ነገር ግን የማያውቅ ከሆነ የግድ መማር አለበት፡፡ መማር ካልተመቻቸለት ፤


በቁርኣን ቦታ ተተክቶ የሚሰራ ከሌላ የቁርኣን ምዕራፎች ካወቀ የሚያውቀውን ያንብብ ፣
42/99
ካለበለዚያ በቁርኣኑ ምትክ “ሱብሃን አላህ አልህምዱሊላህ ላኢላሃኢልለሏህ” የሚሉ
ዚክሮችን ይበል፡፡

አራተኛው ማዕዘን፡ “ማጎንበስ”

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

﴾‫اس ُج ُدوا‬ ِ َّ
‫﴿ اَي أايُّ اها الذ ا‬
ْ ‫ين اآمنُوا ْاراكعُوا او‬
“እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ! (በስግደታችሁ) አጎንብሱ፣ በግንባራችሁም
ተደፉ፤” አል ሐጅ፡

ነብዩ ‫ﷺ‬ ሶላቱን አሟልቶ ላልሰገደው ሶሃባ የሚከተለውን አስተምረውታል፡-

"‫"ثم اركع حتى تطمئن راكعا‬

“ከዚያም ፣ የተረጋጋህ አጎንባሽ እስከምትሆን ድረስ አጎንብስ ፣” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

አምስተኛ ማዕዘን፡-“ከማጎንበስ መነሳት” ሶላቱን ላከፋው ሶሃባ የሚከተለውን


አስተምረውታል፡-

"‫"ثم ارفع حتى تطمئن قائما‬

“ከዚያም ተረጋግተህ እስከምትቆም ድረስ (ከተጎነበስህ በኋላ) ተነሳ፡፡” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

ስድስተኛው ማዕዘን፡ - “ከመሬት መደፋት”


አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

﴾‫اس ُج ُدوا‬ ِ َّ
‫﴿ اَي أايُّ اها الذ ا‬
ْ ‫ين اآمنُوا ْاراكعُوا او‬
“እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ! (በስግደታችሁ) አጎንብሱ፣ በግንባራችሁም
ተደፉ፤” አል ሐጅ፡
43/99
ሰባተኛው ማዕዘን፡- “በሁለት ሱጁዶች መካከል መቀመጥ”

ረሡል ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-

"‫"ثم ارفع حتى تطمئن جالسا‬

“ከዚያም ተረጋግተህ የተቀመጥክ እስክትሆን (ከሱጁድ) ተነሳል” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

ስምንተኛው ማዕዘን፡- “ሁለተኛው ሱጁድ” በየረከዓው ሁሉ ሁለት ሱጁዶች አሉ፡፡

ነብዩ ‫ﷺ‬ ሶላቱን አበላሽቶ ለሰገደው ሰው የሚከተለውን አስተምረውታል፡-

"‫"ثم اسجد حتى تطمئن ساجدا‬

“ከዚያም ተረጋግተህ የሰገድክ እስክትሆን ድረስ መሬት ላይ ተደፋ” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

ይህን የተናገሩት የሚከተለውን ከተናገሩ በኋላ ነው፡፡

"‫"ثم ارفع حتى تطمئن جالسا‬

“ከዚያም ተረጋግተህ የተቀመጥክ እስከምትሆን ድረስ ከሱጁድ ተነሳ” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

ዘጠነኛው ማዕዘን ፡- “የመጨረሻው ተሸሁድ”

ኢብን መስዑድ 4 የሚከተለውን ተናግሯል፡-

"‫"كنا نقوم قبل أن يفرض علينا التشهد‬

“ተሸሁድ በእኛ ላይ ግዴታ ከመሆኑ በፊት እንል ነበር፡፡” ነሳኢይ፡

ይህ የሚጠቁመው ተሸሁድ ግዴታ መሆኑን ነው፡፡

አስረኛው ማዕዘን ፡- “በመጨረሻው አታህያቱ ላይ በነብዩ ‫ ﷺ‬ላይ ሶለዋት ማውረድ”


44/99

በመጨረሻው አታህያቱ ላይ ሶለዋት ማውረድ ግዴታ መሆኑ የሚታወቀው በኢማም


አህመድ መዝሐብ ነው፡፡

አስራ አንደኛው ማዕዘን፡- “በማእዘናቶች መካከል ተራን መጠበቅ”

በአንድ ረከዓ ውስጥ ያሉ የሶላት ተራዎች የሚከተሉት ናቸው፡ - መቆም ፣ ማጎንበስ ፣


አጎምብሶ ቆይቶ መነሳት ፣ ሱጁድ ማድረግ ፣ በሁለት ሱጁዶች መካከል መቀመጥ ፣
ሱጁድ ማድረግ ናቸው ፡፡

ከማጎንበሱ በፊት ሱጁድ ቢያደርግ ተራን ባለመጠበቁ ሶላቱ ትክክል አይሆንም፡፡

አስራ ሁለተኛው ማዕዘን፡- “በማእዘናቶች መካከል መረጋጋት”

ነብዩ ‫ﷺ‬ ሶላቱን አበላሽቶ ለሰገደው ሰው የሚከተለውን ምክር ለግሰውታል፡፡

“የተረጋጋህ እስከምትሆን ድረስ አጎንብስ” ፣ “ከዚያም የተረጋጋህ እስከምትሆን ድረስ


(ከተጎነበስክበት) ቀና በል” ፣ “ከዚያም የተረጋጋህ እስከምትሆን ድረስ ሱጁድ አድርግ”
ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

ሁሉም የሰውነት ክፍሎች በመገጣጠሚያ ክፍሎቻቸው ቦታ ቦታዎቻቸውን እስኪይዙ


ድረስ በማዕዘናቶች ሁሉ መረጋጋት አለበት፡፡

ዑለሞች የሚከተለውን ተናግረዋል፡-“አነስተኛ ቢሆንም እንኳ በሶላቱ ውስጥ


መረጋጋት ካልተገኘ አንድ ሽ ጊዜ ቢሰግድ ሶላቱ ተቀባይነት የለውም”

በአሁኑ ሰዓት በሶላት ውስጥ መረጋጋት የሚባለው ነገር ከበርካታ ሰጋጆች ዘንድ
የተረሳ ጉዳይ ሆኗል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ከሩኩዕ ወደቂያም ቀጥ ብለው መቆም ሲገባቸው
ወደሱጁድ የሚወርዱ ፣ እንዲሁም ሱጁድ አድርገው ቆይተው ሲነሱ ተረጋግተው
45/99
መቀመጥ ሲገባቸው ወዲያውኑ ወደሁለተኛው ሱጁድ የሚመለሱ ሰዎችን
ትመለከታለህ፡፡ ይህ በጣም ስህተት ነው፡፡ በዚህ ባህሪ አንድ ሰው አንድ ሽ ጊዜ ቢሰግድ
ከእርሱ ዘንድ ሶላቱ ተቀባይነት አያገኝም፡፡ ምክንያቱም ነብዩ ‫ﷺ‬ ሶለቱን አበላሽቶ
ለሰገደው ሶሃባ የሚከተለውን አስተምረውታል፡-

"‫"ارجع فصل فإنك لم تصل‬

“አልሰገድክም ፣ ተመለስና (እንደገና) ስገድ” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

ይህ ሐዲስ የሚጠቁመን ግለሰቡ ጃሂል እንኳ ቢሆን የሶላት ማዕዘን ካልተጠበቀ


ሶላት የሚባል ነገር እንደሌለ ነው፡፡

አስራ ሶስተኛው ማዕዘን ፡ “ማሰላመት”

የመጨረሻው የሶላት ማዕዘን “አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱሏሂ” ፣ “አስሰላሙ


አለይኩም ወረህመቱላሂ” በማለት ሶላቱን ማጠናቀቅ ነው፡፡

አንዳንድ ዓሊሞች በፈርድም ይሁን በሱና ሶላት የመጀመሪያው ሰላምታ እንጅ


ሁለተኛው ሰላምታ ማዕዘን አይደለም የሚሉ አሉ፡፡ በትክክለኛው የዑለማ ንግግር ግን
በፈርድም ይሁን በሱና ሶላቶች ሁለቱም ሰላምታዎች የሶላት ማዕዘን ናቸው የሚለው
ነው፡፡ በመሆኑም በፈርድም ይሁን በትርፍ ሶላት ከሁለቱ አንዱን ማጉደል ተገቢ
አይደለም፡፡

“ከሶላት ማዕዘናቶች የተወ ሰው ሸሪዓዊ ብይኑ ምንድን ነው”

ጥያቄ፡- ከሶላት ማዕዘናቶች መካከል አንዱን የተወ ሸሪኣዊ ብይኑ ምንድን ነው?

መልስ፡- ከሶላት ማዕዘናቶች መካከል አንዱን የተወ ሰው ሶላቱ ይበላሻል፡፡ ረስቶ ከሆነ
46/99
ወዲያውኑ ተመልሶ ያስተካክል፡፡ ሩኩዕ ማድረጉን ረስቶ ወደሱጁድ ከሄደና ትዝ ካለው
ተመልሶ በመቆም ሩኩዕ ያድርግ፡፡ መጀመሪያ ረከዓ ላይ የረሳው ማዕዘን ሁለተኛው
ረከዓ ላይ ሆኖ ትዝ ቢለው የመጀመሪያው ረከዓ እንደሌለ ቆጥሮ ሁለተኛውን ረከዓ
እንደአንደኛ ረከዓ ይቁጠረው፡፡

ለምሳሌ፡- ሩኩዕ አለማድረጉ በሁለቱ ሱጁዶች መካከል ትዝ ቢለው ወዲያው ተነስቶ


በመቆም ሩኩዕ ያድርግና ሶላቱን ይሙላ፡፡ ሁለተኛው ረከዓ ላይ እያለ የመጀመሪያው
ረከዓ ላይ ሩኩዑን መርሳቱ ትዝ ካለው የሁለተኛውን ረከዓ እንደአንደኛ ረከዓ
ይቁጠረው፡፡

አንድ ሰው ሁለተኛዋን ሱጁድና በሁለተኛው ሱጁድ መካከል መቀመጡን


መርሳቱን ፋቲሃ እየቀራ ትዝ ቢለው ተመልሶ ቁጭ በማለት ሱጁዷን ሰግዶ እንደገና
ወደነበረበት ፋቲሃ ይመለስ፡፡ ሁለተኛዋን ሱጁድና በሁለት ሱጁዶች መካከል
መቀመጡን መርሳቱ ከሁለተኛው ረከዓ ሩኩዕ ላይ ትዝ ቢለው የሁለተኛውን ረከዓ
እንደአንደኛ ረከዓ ይቁጠረው፡፡

አሁን ባልነው የማስተካከያ ስራ ሁሉ መጨረሻ ላይ ሰጀደተ ሰህው ይስገድ፡፡ ሰጀደተ


ሰህው ካሰላመተ በኋላ ቢሆን ይመረጣል፡፡
“የሶላት ማዕዘን (ሩክን) መተውን የተጠራጠረ ሰጋጅ”

ጥያቄ፡ - ከሶላት ማዕዘናት ውስጥ አንዱን መተውን የተጠራጠረ ሰው ምን ይስራ?

መልስ፡- አንድ ሰው ከሶላት ማዕዘናት ውስጥ ያጎደልኩት አለ ወይስ የለም ብሎ


ቢጠራጠር ከሶስት ሁኔታዎች የዘለለ አይሆንም፡፡
አንደኛው ጥርጣሬው እውነታነት የሌለው ብዥታ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ አይነቱ ጥርጣሬ
47/99
ሲከሰት ምንም አይነት ተጽእኖ እንደማያሳድር ወይም ምንም እንደሌለ ቆጥሮ ሶላቱን
ይቀጥል፡፡ ወይም አላህ ሰላም ያድርገንና ከአንዳንድ ሰዎች ላይ አብሯቸው የማይለይ
ዘውታሪ የሰይጣን ጉትጎታ ሊኖር ይችላል፡፡ በመሆኑም እንዲህ አይነቱ ጥርጣሬ ቦታ
ሊሰጠው የሚገባ አይደለም፡፡ ምንም ሳይጨናነቅና ሳያስብ ሶላቱን መጨረስ ነው
ያለበት፡፡

ወይም ጥርጣሬው ሶላት ከሰገደ በኋላ ተከትሎ የሚመጣ ጥርጣሬ ሊሆን ይችላል፡፡
እንዲህ አይነቱ ጥርጣሬም ምናልባት ከሶላት ማዕዘናቶች አንዱን በመተው እርግጠኛ
ካልሆነ በቀር ቦታ ሊሰጠው አይገባም፡፡

ጥርጣሬው እርግጠኛ ከሆነ ግን ለምሳሌ አንድ ሰው በሶላት መካከል ሱጁድ ላይ


እንደደረሰ ሩኩዕ አለማድረጉን በእርግጠኝነት ከተጠራጠረ መሰረቱ ሩኩዕ አለማድረግ
በመሆኑ ይቁምና ሩኩዕ አድርጎ ሶላቱን ይሙላ፡፡ ሩኩዕ የማድረጉ ጥርጣሬ ከፍ ካለ
ግን ጥርጣሬው ያዘነበለበትን ይዞ መጨረሻ ላይ ከሰላምታ በኋላ ሰጀደተ ሰህው ያድርግ፡፡

ሱጁደ ሰህው (የእርሳቻ ሱጁድ) በሀቂቃ አንገብጋቢ ጉዳይ በመሆኑ ሙስሊሞች


እርሱን ሊያውቁ ይገባል፡፡ በተለይም የመስጅድ ኢማሞች ብዙዎቹ የማያውቁ በመሆኑ
አለማወቃቸው ደግሞ ከእነርሱ አንጻር ተገቢ ባለመሆኑ ሊማሩ ይገባል፡፡ አላህ በረሡል
‫ﷺ‬ ላይ ያወረደውን ህግ እያንዳንዱ ሰው ሊያውቅ ይገባል፡፡
“ከኢማም ጋር ተከታይ የሆነ ሰው ስንት እንደሰገደ ቢረሳ”

ጥያቄ፡- አንዳንድ ሰዎች ሶላት ከተቆመ በኋላ መጠው ኢማምን ይከተላሉ፡፡


ያመለጣቸውን ሶላት ይረሳሉ ፤ ከዚያም በጎን በቆመው ሰው ይከተላሉ፡፡ ይህ ሸሪዓዊ
ብይኑ ምንድን ነው?
48/99
መልስ፡- ይህ ነገር ብዙ ጊዜ ይከሰታል፡፡ ከኢማሙ ጋር ሁለት ሰዎች ይገባሉ፡፡
አንድኛው ስንት እንደሰገደ ወይም ከኢማሙ ጋር ስንት ረከዓ እንዳገኘ ይረሳል፡፡
ከዚያም ከጎን የቆመውንና አብሮት ሶላት የጀመረውን ሰው እየተመለከተ ሶላቱን
ያጠናቅቃል፡፡ እርሱን የሚቃረን ጥርጣሬ ወይም እርሱን የሚቃረን እርግጠኝነት ካልኖረ
በቀር ይህን ቢፈጽም ችግር የለውም፡፡ ምክንያቱም በዒባዳችን ውስጥ አመዛኝ ወደሆነ
ጥርጣሬ መመለሱ ችግር የለውም፡፡

“የሶላት ዋጅባቶች”

ጥያቄ፡- የሶላትን ማዕዘን አውቀናል፡፡ አሁን ደግሞ የሶላት ዋጅባቶች ምን እንደሆኑ


ማወቅ እንፈልጋለን?

መልስ፡- የሶላት ዋጅባቶች ማለት ንግግሮች ወይም ተግባሮች ሆነው ሰዎች ሆን ብለው
ከተውት ሶላትን የሚያበላሽ ረስተው ከተውትና ትዝ ካላቸው ደግሞ በሰጀደተ ሰህው
የሚጠገኑ ናቸው፡፡

የመጀመሪያው፡-“ከተክቢረተል ኢህራም ውጭ ያሉ ተክቢራዎች” ነው፡፡ “ተክቢረተል


ኢህራም” ከሶላት ማዕዘናቶች መካከል አንዱ ነው፡፡ “ተክቢረተል ኢህራም” ሳያደርግ
ሶላት የጀመረ ሰው ወደሶላቱ እንደገባ አይቆጠርም፡፡ ዋጅባት ከሆኑት ተክቢራዎች
መካከል “የሩክዕ ተክቢራ” በአንድ ክስተት ብቻ ከዋጅባትነት ወጦ ሱና ይሆናል፡፡
ይህም ኢማሙ ተጎንብሶ የደረሰ ሰው ቆሞ “ተክቢረተል ኢህራም” ካደረገ በኋላ
ወደሩኩዕ ሲሄድ የሚያደርገው ተክቢራ ለእርሱ ዋጅብ ሳይሆን ሱና እንደሆነ ዓሊሞች
አጽድቀዋል፡፡
ሁለተኛው፡ በሩኩዕ ጊዜ “ሱብሃነ ረቢየል አዚም” በሱጁድ ጊዜ “ሱብሃን ረቢየል አዕላ”
49/99
ማለት ዋጅብ ነው፡፡

ሶስተኛው፡ የመጀመሪያው ተሸሁድ እና ለእርሱም መቀመጥ፡፡

አራተኛው፡ ኢማምና ብቻውን የሚሰግድ ሰው ከሩኩዕ ሲነሳ “ሰሚአላሁ ሊመን


ሀሚዳህ ፣ ረበና ወለከል ሀምድ” ማለት፡፡ ተከታይ ከሆነ ደግሞ ከሩኩዕ ሲነሳ “ረበና
ወለከል ሀምድ” ማለት ዋጅብ ነው፡፡

ከላይ የዘረዘርናቸው በሙሉ የሶላት ዋጅባቶች ሲሆኑ ሆን ብለን ከተውናቸው ሶላታችን


በቀጥታ ይበላሻል፡፡ ረስተን ከተውናቸውና ቆይተን ትዝ ካለን በሰጀደተ ሰህው ይጠገናሉ፡፡
ሶላታችንም ትክክል ይሆናል፡፡ ለዚህ መረጃችን ዓብደላህ ብን ቡሃይና 4 ያስተላለፈው
ሐዲስ ነው፡፡ ነብዩ ‫ﷺ‬ በዙሁር ሶላት ሁለተኛው ረከዓ ላይ ሳይቀመጡ እንዲሁ ተነሱ
ሶላታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ሁለት ሱጁዶችን ሰግደው አሰላመቱ፡፡ ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

“ሶላትን የሚያበላሹ ነገሮች”

ጥያቄ፡- በጥቅል እንኳ ቢሆን ሶላት የሚያበላሹትን ነገሮች ማወቅ እንፈልጋለን?

መልስ፡- ሶላትን የሚያበላሹ ነገሮች በሁለት ባህሪያት ላይ ይሽከረከራሉ፡፡ አንደኛው


የታዘዙ ነገሮችን ማለትም አርካኖችን ፣ ዋጅባቶችን ፣ ሸርጦችን መተው ሲሆን
ሁለተኛው ደግሞ ክልክል የሆኑ ነገሮችን በመፈጸም ነው፡፡

ማዕዘንን መተው፡ ማለት ሆን ብሎ ሩኩዕን መተው እንደምሳሌ መጥቀስ ይቻላል፡፡

ሸርጥ የሆኑ ነገሮችን መተው፡ ደግሞ ከሶላት መካከል ሆን ብሎ ከቂብላ አቅጣጫ


መዞር እንደምሳሌ መጥቀስ ይቻላል፡፡
ዋጅብን መተው ሲባል የመጀመሪያውን ተሸሁድ ሆን ብሎ መተው እንደምሳሌ
50/99
ይጠቀሳል፡፡ ማዕዘናት፣ ዋጅባቶችና ሸርጦችን ሆን ብሎ ከተዋቸው ሶላቱን ያበላሹበታል፡፡

ሁለተኛው የሶላት መበላሸት የሚሽከረከረው፡ ክልክል ነገሮችን በመፈጸም ነው፡፡


በሶላቱ ውስጥ ውዱእ መፍታት ወይም ወሬ ማውራት ወይም መሳቅ እና የመሳሰሉት
ናቸው፡፡ እነዚህን ነገሮች ሆን ብሎ ከሰራ ሶላቱ ይበላሻል፡፡

“የጀማዓ ሶላት ሸሪዓዊ ብይን”

ጥያቄ፡- ስለሶላት ሸሪዓዊ ብይን ፣ መስፈርቶቿ ፣ ማዕዘናቶቿ ፣ ዋጅባቶቿ እና ስለ


ሰጀደተ ሰህው ግንዛቤ ይዘናል አሁን ደግሞ ስለ ጀማዓ ሶላት ሸሪዓዊ ብይን
እንዲብራራልን እንፈልጋለን?

መልስ፡-የጀማዓ ሶላት ትኩረት ከሚሰጣቸውና በላጭ ከሚባሉ አላህን የምንታዘዝባቸው


ዒባዳዎች መሆኑ ዑለሞች ተስማምተዋል ፡፡ የጀማዓ ሶላት ጉዳይ በጀሐድ ጊዜ እንኳ
መቅረት እንደሌለበት አላህ በቁርኣኑ ተናግሯል፡፡

አላህ በሚከተለው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

ْ‫اسِِ احُا ُه ْ فاِإ اذا اس اج ُدواْ فا ِْْا ُكوتُوا‬ ‫الصالااة فا ُِْا ُق ْ طاآئِافةٌ ِهمْن ُه َّم اع ا‬
ْ ‫ك اولْْاأْ ُخ ُذواْ أ‬ َّ ُُ‫ت اَّل‬ ِ ‫﴿وِ اذا ُك‬
‫نت فْ ِه ْ فاأاِا ُْ ا‬
‫ا‬ ‫ا‬
﴾ ْ ‫اسِِ احُا ُه‬ ِ ‫صُِّواْ ام اع ا‬
ْ ‫ك اولْْاأْ ُخ ُذواْ ح ْذ ارُه ْ اوأ‬ ‫صُِّواْ فا ُِْْ ا‬
ِ ِ ِ ِ
ْ ‫من اوارآئ ُك ْ اولُْاأْت طاآئ افةٌ أ‬
‫ُخارى اَلْ يُ ا‬
“ከውስጣቸውም በሆንክና ሶላትን ለእነርሱ ባሰገድካቸው ጊዜ ከእነሱ አንዲት
ጭፍራ ካንተ ጋር ትቁም፡፡ መሳሪያዎቻቸውንም ይያዙ፡፡ በግንባራቸውም በተደፉ
ጊዜ ከስተኋላችሁ ይሁኑ፡፡ (እነዚህ ይሂዱና) ያልሰገዱትም ሌሎቹ ጭፍሮች
ይምጡ፡፡ ከአንተም ጋር ይስገዱ፡፡ ጥንቃቄያቸውንና መሳሪያዎቻቸውንም
ይያዙ፡፡” አን ኒሳእ፡

ከጀማዓ ጋር መስገድ ግዴታ እንደሆነ የሚጠቁሙ በርካታ ሐዲሶች መጠዋል፡፡


51/99
የአላህ መልእክተኛ ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

‫ ثم أنطلق برجال‬،‫ ثم آمر رجال فيصلي بالناس‬،‫"لقد هممت أن آمر بالصالة فتقام‬
"‫ فأحرق عليهم بيوتهم بالنار‬،‫معهم حزم من حطب إلى قوم ال يشهدون الصالة‬

“አንድ ሰው እንዲያሰግድና ሶላት እንድትቆም ከዚያም እንጨትን ከያዙ ሰዎች ጋር ሆኘ


ሶላትን የማይሰግዱ ወደሆኑ ሰዎች በመሄድ ቤቶቻቸውን በእሳት ለማቃጠል በእርግጥ
አሰብኩ፡፡” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

"‫"من يسمع النداء فلم يجب فال صالة له إال من عذر‬

“ምክንያት ለሚሰጠው ሰው ካልሆነ በቀር አዛን ሰምቶ ምንም ምላሽ ያልሰጠ ሶላት
የለውም” ኢብኑ ማጀህ፡

በቤቱ ለመስገድ ፈቃድ ፈልጎ ረሡልን ‫ﷺ‬ የጠየቀውን አይነስውር “አዛን


ትሰማለህ?” የሚል ጥያቄ ነበር ያቀረቡለት፡፡ እርሱም “አዎ!” በማለት ምላሽ ሰጠ፡፡

እርሳቸው “ለጥሪው አዎንታዊ ምላሽ ስጥ” በማለት መልስ ሰጠውታል፡፡ ሙስሊም፡

ኢብን መስዑድ 4 ደግሞ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

“የታወቀ ኒፋቅ ያለበት ሙናፊቅና በሽተኛ ካልሆነ በቀር ከሶላተል ጀማዓ - ወደኋላ
የሚል እንደሌለ በእርግጥ አይታችሁናል፡፡ ከሶፍ ለመቆም በሁለት ሰዎች መካከል
ተደግፎ የሚመጣም ነበር፡፡” ሙስሊም፡

ሶላት በጀማዓ መስገዱ ዋጅብ ነው የሚለው ትክክለኛው እይታ ነው፡፡ ኢስላማዊው


ማህበረሰብ አንድ ማህበረሰብ ነው፡፡ በአምልኮት በመሰባሰብ ካልሆነ በቀር አንድነት
በተሟላ ሁኔታ ሊረጋገጥ አይችልም፡፡ ከአምልኮዎች ሁሉ ላቅ ያለውና በላጩ እንዲሁም
ጠንካራው ደግሞ ሶላት ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ኢስላማዊው ማህበረሰብ በሶላት መሰባሰቡ
52/99
ግዴታ ሆነ ማለት ነው፡፡
ዑለሞች ከዒባዳዎች ሁሉ ጠንካራውና ታላቁ መሆኑን ከተስማሙ በኋላ በጀማዓ
መስገድ ለሶላት ትክክለኛነት መስፈርት ነች ወይስ በጀማዓ ባይሰገድ ወንጀል ከመሆኑ
ጋር ሶላቱ ትክክል ነው በሚል መወዛገባቸው ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጅ የተለያዩ
ውዝግቦች ቢኖሩም ትክክለኛው አመለካከት ለትክክለኛነቷ ሸርጥ ሳይሆን ሶላት በጀማዓ
መሰገዱ ዋጅብ ነው የሚለው ነው፡፡ ነገር ግን ሽሪዓዊ ምክንያት ካልሆነ በቀር ሶላትን
በጀማዓ ያልሰገደ ሐጢያተኛ ይሆናል፡፡ በጀማዓ መስገዱ ለሶላት ትክክለኛነት መስፈርት
አለመሆኑን ከሚጠቁሙ መረጃዎች መካከል በጀማዓ የሰገደውን እና ብቻውን
የሰገደውን ሰው በምንዳ ማበላለጡ ነው፡፡ ይህ የሚጠቁመው ብቻውን የሚሰግድ ሰው
ደረጃ እንዳለው ፣ ደረጃ አለው ማለት ደግሞ ያለጀማዓ የተሰገደው ሶላት ትክክል
መሆኑን ይጠቁማል ማለት ነው፡፡ ያም ሆነ ይህ ፣ ወንድ ሆኖ ለአቅመ አደም የደረሰ
ማንኛውም ሙስሊም ፣ በሰፈርም ይሁን በአገር ውስጥ ሶላትን በጀማዓ መስገድ
ይኖርበታል፡፡
“የተከታይና የኢማም ግንኙነት”

ጥያቄ፡- የጀማዓን ሶላት ብይን እስካወቅን ድረስ የኢማምና የተከታይን ግንኙነት ደግሞ
ማወቅ እንፈልጋለን?

መልስ፡-ተከታይ ከኢማም ጋር ያለው ግኑኙነት ፤ የመከተል ግንኙነት ነው፡፡ በዚህ


ምክንያት ነብዩ ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

‫ وإذا‬،‫ وإذا ركع فاركعوا‬،‫ فإذا كبر فكبروا‬،‫"إنما جعل اإلمام ليؤتم به فال تختلفوا عليه‬
‫ وإذا صلى‬،‫ ربنا ولك الحمد‬:‫ فقولوا‬،‫ وإذا قال سمع هللا لمن حمده‬،‫سجد فاسجدوا‬
“‫ وإذا صلى قاعدا فصلوا قعودا أجمعين‬،‫ فصلوا قياما‬،‫قائما‬
53/99
“ኢማም የተደረገው ሊከተሉት ነው፡፡ ስለዚህ ከእርሱ ተቃራኒ አትሁኑ ፤ አሏሁ አክበር!
ካለ እናንተም ወዲያውኑ አሏሁ አክበር በሉ ፤ ሲያጎነብስ ወዲያውኑ አጎንብሱ ፤ መሬት
ሲደፋ ወዲያውኑ ተደፉ ፤ ሰሚአላህ ሊመንሀሚዳህ ሲል ረበና ወለከል ሀምድ በሉ ፤ ቆሞ
ከሰገደ ቆማችሁ ስገዱ ፤ ቁጭ ብሎ ከሰገደ ሁላችሁም ቁጭ ብላችሁ ስገዱ፡፡” ቡኻሪ፡
ሙስሊም፡

አንድ ተከታይ ኢማምን ሲከተል በአራት ደረጃዎች ሊከተል ይችላል፡፡ እነርሱም


“ሙታበዓህ ፣ ሙዋፈቃህ ፣ ሙሳበቃህ እና ወተአኹር” በመባል ይጠራሉ፡፡

ሙታበዓህ፡ ማለት ኢማም የሚፈጽመውን ተግባር ያለምንም መዘግየት ተከታትሎ


መፈጸም ነው፡፡ ሩኩዕ ካደረገ ወዲያውኑ ሩኩዕ ሊያደርግ ፤ ሱጁድ ሲያደርግ
ወዲያውኑ ሱጁድ ሊያደርግ ነው፡፡

ሙዋፈቃህ፡ ማለት የሶላት ተግባራቶችን ኢማምና ተከታይ እኩል ሊፈጽሙ ነው፡፡


ያለምንም መዘግየትና መቅደም አብሮ ሩኩዕ ፣ ወይም ሱጁድ ማድረግ ፣ አብሮ
መቆምና አብሮ መቀመጥ ናቸው፡፡

ሙሳበቃህ፡ ማለት ደግሞ ተከታዩ በሶላት ተግባራት ኢማምን መቅደም ነው፡፡ ኢማሙ
ሩኩዕ ወይም ሱጁድ ከማድረጉ በፊት ተከታዩ ቀድሞ ሩኩዕና ሱጁድ ማድረጉ ፣
ኢማሙ ሳይቆም ተከታዩ መቆሙ ነው፡፡

ተአኹር፡ ማለት ደግሞ ኢማሙ ከፈጸመ በኋላ በጣም ዘግይቶ መፈጸም ነው፡፡ ኢማሙ
ሩኩዕ ሲያደርግ ቆሞ ይቀራል፡፡ ሱጁድ ሲደርግም ቆሞ “ሀምደን ከሲረን” ይላል፡፡

ከ “ሙታበዓ” ወይም መከተል በቀር ሌሎች ደረጃዎች ሁሉ የተወገዙ ናቸው፡፡


ከኢማም ጋር እኩል መፈጸም የሚከተለውን የረሡል ‫ﷺ‬ ቃል የሚቃረን ነው፡፡
54/99
“(ኢማሙ) አሏሁ አክበር እስከሚል አሏሁ አክበር አትበሉ ፤ ሩኩእ እስከሚያደርግ
ሩኩዕ አታድርጉ” አህመድ፡ አቡዳውድ፡

ኢማምን የሚቀድም ሰው ደግሞ በሚከተለው የረሡል ‫ﷺ‬ ቃል ብርቱ


ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶታል፡፡

‫ أو يجعل هللا‬،‫"أما يخشى الذي يرفع رأسه قبل اإلمام أن يحول هللا رأسه رأس حمار‬
"‫صورته صورة حمار‬

“ከኢማም በፊት ቅንጭላቱን ከፍ የሚያደርግ ሰው ራሱን የአህያ ራስ ወይም ቅርጹን ልክ


እንደአህያ ቅርጽ አድርጎ አላህ እንዳያዞረው አይፈራምን?” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

ከኢማም በጣም ዘግይቶ የሰገደ ሰው መከተልን አላረጋገጠም፡፡ የሚከተለውን


የረሡል ‫ﷺ‬ ሐዲስ ተግባራዊ አላደረገም፡፡

“ኢማሙ አሏሁ አክበር ሲል አሏሁ አክበር በሉ ፤ ሩኩእ ሲያደርግ ሩኩእ አድርጉ፡፡” ቡኻሪ፡
ሙስለም፡

ሙሳበቃ፡ ወይም ኢማምን መቅደም ሀራም ነው፡፡ ሙዋፈቃ ደግሞ አንዳንድ ዑለሞች
የተጠላ ተግባር ነው ሲሉት አንዳንዶች ደግሞ ሀራም ነው ብለውታል፡፡ አትተአኹር
(መዘግየት) አነስ ያለው ሸሪዓዊ ብይን የተጠላ መሆኑ ነው፡፡ ሙታበዓ (መከተል)
ደግሞ የታዘዝንበትና የረሡል ‫ﷺ‬ ተግባር ነው፡፡

“ኢማምን ከምንቃረንባቸው ብርቱው ሁኔታ የቱ ነው”

ጥያቄ፡- ከሶስቱ ሁኔታ ከሙሳበቃ ወይም ከሙዋፈቃህ ወይም ከተኸሉፍ ብርቱው


ተቃርኖ የቱ ነው?
መልስ፡እርሱን አስመልክቶ ማስጠንቀቂያ በመምጣቱ ብርቱው ሙሳበቃ ወይም መቅደም
55/99
ነው፡፡ አንድ ሰው ኢማምን ከቀደመ በሶላት ውስጥ ሀራም የሆነ ተግባር በመፈጸሙ
ሶላቱ ይበላሻል የሚለው ከዑለሞች አመዛኝ የሚባለው ንግግር ነው፡፡
“የሶላት ሱናዎች”

ጥያቄ፡-የሶላት ዋጅባቶችን ካወቅን በኋላ የሶላትን ሱናዎች ደግሞ ማወቅ


እንፈልጋለን?

መልስ፡- ከሶላት ማዕዘናቶችና ዋጅባቶች ውጭ ያሉት በሙሉ የሶላት ሱናዎች ናቸው፡፡


ለምሳሌ፡- በሩኩዕና በሱጁድ ከአንድ ጊዜ በላይ ተስቢህ ማድረግ ፣ በሱጁድ ጊዜ
“ኢፍቲራሽ” አድርጎ መቀመጥና የመሳሰሉት ሁሉ የሶላት ሱናዎች ናቸው፡፡

“ኢፍቲራሽ” ፡ ማለት በግራ እግሩ ተቀምጦ የቀኝ እግሩን መትከል ማለት ነው፡፡ ሁለት
ተሸሁዶች ባሉባቸው ሶላቶች ከሁለተኛው ተሸሁድ ውጭ “በተወሩክ” የአቀማመጥ
ስርዓት ይቀመጣል፡፡

“ተውሩክ” ፡ ማለት የግራ እግሩን በቀኝ ባቱ ስር በማውጣት ቀኝ እግሩን መትከል


ወይም ማንጠፍ ማለት ነው፡፡

በተክቢረተል ኢህራም እጅን ማንሳት, በሩኩዕ ፣ ከሩኩዕ ሲነሳ እና ከመጀመሪያው


ተሸሁድ ወይም ሁለተኛውን ረከዓ ጨርሶ ሲነሳ ፡ ሁለት እጆቹን በትክሻው ትክክል
ወይም በጆሮው ትክክል ማንሳት ከሶላት ሱናዎች መካከል አንዱ ነው፡፡

“የእርሳቻ ሱጁዶች”

ጥያቄ፡- “ሰጀደተ ሰህው” የእርሳቻ ሱጁዶች ግዴታ የሚሆኑበትን ቦታዎች ማወቅ


እንፈልጋለን?
56/99
መልስ፡- በጥቅሉ “ሰጀደተ ሰህው” የሚያስፈልግባቸው ምክንያቶች ሶስት ናቸው፡፡
ጭማሬ ፣ ቅነሳ እና ጥርጣሬ ናቸው፡፡

ጭማሬ፡ ማለት አንድ ሰው በሶላቱ ውስጥ ሩኩዕ ፣ ሱጁድ ፣ ቂያም እና መቀመጥን


መጨመሩ ነው፡፡

ቅነሳ፡ ማለት ደግሞ ከሶላት ማዕዘናቶች ወይም ዋጅባቶች መካከል አንዱን መቀነስ ነው፡፡

መጠራጠር ፡ ማለት ደግሞ አንድ ሰው ምን ያክል እንደሰገደ መጠራጠሩ ነው፡፡

ጭማሬ፡- አንድ ሰው በሶላት ውስጥ ሆን ብሎ ሩኩዕ ወይም ሱጁድ ወይም ቂያም ወይም
መቀመጥን ከጨመረ ረሡል ‫ﷺ‬ ካዘዙት ህግ ውጭ በመሆኑ ሶላቱ ይበላሻል፡፡

ለዚህ ማስረጃው የነብዩ ‫ﷺ‬ የሚከተለው ሐዲስ ነው፡-

"‫"من عمل عمال ليس عليه أمرنا فهو رد‬

“በእርሱ ላይ የእኛ ትእዛዝ የሌለበት ስራ የሰራ እርሱ ተመላሽ ነው፡፡” ሙስሊም፡

ረስቶ መጨመር ወይም መቀነስ ሶላትን አያበላሽም፡፡ ነገር ግን ከሰላምታ በኋላ


ሰጀደተ ሰህው (የእርሳቻ ሱጁድ) ማድረግ ይኖርበታል፡፡

ረስቶ መቀነስ ሶላት እንደማያበላሽ ማስረጃ የሚሆነን አቡሁረይራ 4 ያስተላለፉት


የሚከተለው ሐዲስ ነው፡፡

ነብዩ ‫ﷺ‬ ዙሁር ወይም አስር ሶላት ላይ ሁለት ረከዓ ሰግደው አሰላምተው ወጡ፡፡
ከዚያም ሶሃቦቹ ሁለት ረከዓ ያልሰገዱ መሆኑን አስታወሷቸው፡፡ ከዚያም ሁለት ረከዓ
ሰግደው ካሰላመቱ በኋላ ሁለት ሱጁዶች ሰገዱ፡፡ አህመድ፡

ኢብን መስዑድ 4 ባስተላለፉት ሐዲስ ደግሞ ነብዩ ‫ﷺ‬ ዙሁርን አምስት አድርገው
57/99
አሰገዱ፡፡ ከጨረሱ በኋላ “ሶላት ተጨምሯል እንዴ? በማለት ሶሃቦች ጠየቁ፡፡ ረሡልም
‫ﷺ‬ “ምንድን ነው?” ብለው ጠየቁ ከዚያም ሶሃቦች “አምስት ነው የሰገድክ”
አሏቸው፡፡ ረሡል ወደቂብላ በመዞር እግራቸውን አጥፈው በመቀመጥ ሁለት ሱጁዶችን
ሰገዱ፡፡ ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

ጉድለት፡ አንድ ሰው ከሁለተኛው ረከዓ ከተመሳሳይ ቦታ ሳይደርስ ያጎደለውን ማዕዘን


ካስታወሰ ወዲያው ተመልሶ ማስተካከል ይችላል፡፡ ወይም ያጎደለውን ማዕዘን
ሳያስታውስ ሁለተኛው ረከዓ ተመሳሳይ ማዕዘን ላይ ትዝ ቢለው የመጀመሪያውን ረከዓ
ውድቅ አድርጎ የሁለተኛውን ረከዓ እንደመጀመሪያ ቆጥሮ መጨረሻ ላይ አንድ ረከዓ
ያስገኝ (ይስገድ) ፡፡ በሁለቱም ሁኔታ ላይ “ሰጀደተ ሰህው” ይስገድ፡፡

ዋጅብን ማጉደል፡ ዋጅብ ረስቶ ቢነሳ ለምሳሌ “ሱብሃን ረቢየል አዕላ” ረስቶ ከተነሳ
በኋላ ቢያስታውስ ሶላቱን ይቀጥልና ከሰላምታ በፊት ሰጀደተ ሰህው ወይም የርሳቻ
ሱጁድ ይስገድ፡፡

ለዚህ ማስረጃ የሚሆነን ረሡል ‫ﷺ‬ የመጀመሪያውን ተሸሁድ ለእርሱም መቀመጥን


ረስተው ቆሙ ተመልሰው ሳይቀመጡ ሶላታቸውን ከጨረሱ በኋላ ከሰላምታ በፊት
ሰጀደተ ሰህው ወይም የርሳቻ ሱጁድ ሰገዱ፡፡ ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

ጥርጣሬ፡- በጭማሬ እና በመቀነስ መካከል መጠራጠር ነው፡፡ ሰጋጁ ሶስት ሰገድኩ


አራት ሰገድኩ ብሎ ከተጠራጠረ ሁለት አማራጮች አሉት፡፡ አንደኛው መጨመሩ
ወይም ማጉደሉ አመዝኖ መገኘቱ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ አመዛኝ የሆነውን ሰርቶ ከሰላምታ
በኋላ ሰጀደተ ሰህው ወይም የእርሳቻ ሱጁድ ይስገድ፡፡ ሁለተኛው አማራጭ ደግሞ
ከሁለት አንዱ ሳያመዝን መጨመሩም ማጉደሉም ከእርሱ ዘንድ እኩል መሆኑ ነው፡፡
58/99
በዚህ ጊዜ እርግጠኛ በሆነበት ውሳኔ ይስጥ፡፡ እርሱም አነስተኛው ነው፡፡ የጎደለውን
ይሙላና ከሰላምታ በፊት ሰጀደተ ሰህው ወይም የርሳቻ ሱጁድ ይስገድ፡፡

ለምሳሌ፡- አንድ ሰው ዙሁር እየሰገደ ሶስተኛው ረከዓ ላይ ነኝ ወይስ አራተኛው ረከዓ


ላይ ነኝ ብሎ ተጠራጠረ፡፡ ከእርሱ ዘንድ ሶስተኛው ረከዓ ላይ ነኝ የሚለው አመዘነበት፡፡
በዚህ ጊዜ አንድ ረከዓ ብቻ ያምጣና ያሰላምት፡፡ ከዚያም ሰጀደተ ሰህው ወይም የርሳቻ
ሱጁድ ይስገድ፡፡

ሁለቱ ነገሮች ከእርሱ ዘንድ እኩል ቢሆኑ ለምሳሌ አንድ ሰው ዙሁርን ይሰግዳል
ሶስት ረከዓ ነው ወይስ አራት ረከዓ ነው የሰገድኩ ብሎ ተጠራጠረ፡፡ ከእርሱ ዘንድ
አንዱ አመዛኝ ሊሆንለት አልቻለም፡፡ እርግጠኛውን ይዞ ይሂድ፡፡ እርሱም አነስተኛው
ቁጥር ነው፡፡ ሶስት በሚለው ይሂድና መጨረሻ አንድ ረከዓ ጨምሮ ከሰላምታ በፊት
ሰጀደተ ሰህው ወይም የርሳቻ ሱጁድ ይስገድ፡፡

ከዋጅባቶች አንዱን ዋጅብ ከተወ “ሰጀደተ ሰህው” ከሰላምታ በፊት እንደሚሆን


ግልጽ ሆነ፡፡ የረከዓዎችን ብዛት ተጠራጠረ ፣ ከሁለት አንዱ ሊያመዘንለት አልቻለም፡፡
በዚህ ጊዜ አነስተኛውን ይዞ አንድ ረከዓ ከጨመረ ወይም ተጠራጥሮ ከሁለቱ አንዱ
ካመዘነለት ከሰላምታ በኋላ ሰጀደተ ሰህው ወይም የርሳቻ ሱጁድ ይስገድ፡፡

“ከሰጀደተ ሰህው በኋላ የሰላምታ ሸሪዓዊ ብይኑ”

ጥያቄ፡-ከሰላምታ በኋላ ሰጀደተ ሰህው ካደረገ ድጋሜ ሰላምታ ማድረግ ይጠበቅበታል?

መልስ፡- ከሰላምታ በኋላ ሰጀደተ ሰህው ካደረገ ሰላምታ ማድረግ ግዴታ ነው፡፡

ጥያቄ፡ - ከሰላምታ በኋላ ሰጀደተ ሰህው ካደረገ ድጋሜ ተሸሑድ ማድረግ ይጠበቅበታል?
59/99
መልስ፡-በዚህ ዙሪያ ዑለሞች የተለያየ አመለካከት አላቸው፡፡ አመዛኙ የዑለሞች
ንግግር ግን ተሸሁድ (አታህያቱ) ግዴታ አይደለም የሚል ነው፡፡

“ትርፍ ሶላቶች ደረጃቸውና አይነታቸው”

ጥያቄ፡- የትርፍ ሶላቶችን ደረጃዎች እና ዓይነቶች ማወቅ እንፈልጋለን?

መልስ፡- አላህ b በምንዳ ወደርሱ እንዲቃረቡ እንዲሁም በፈርድ ላይ ያሉ ክፍተቶችን


በቂያማ ቀን ለመሙላትና ለመዝጋት ለባሮች ካደረገላቸው እዝነት መካከል
ለእያንዳንዱ ፈርድ እርሱን የመሰለ ትርፍ አምልኮቶችን ማድረጉ ነው፡፡ ለፈርድ ሶላት
እርሱን የመሰለ ትርፍ ሶላት አድርጓል፡፡ ለዘካም እንዲሁ እርሱን የሚመሰሉ
ሶደቃዎችን አድርጓል፡፡ ግዴታ ለሆነው ጾም እንዲሁ ትርፍ ጾሞችን አድርጓል፡፡ ለሀጅም
እንዲሁ፡፡

ከትርፍ ሶላቶች መካከል፡ ለፈርድ ሶላቶች ተከታይ የሆኑ ሱና ሶላቶች ናቸው፡፡


የዙሁር ወቅት ከገባ በኋላ ከዙሁር ፈርድ ሶላት በፊት በሰላምታ የሚለዩ አራት ትርፍ
ሶላቶች ይሰገዳሉ፡፡ ወቅት ከመግባቱ በፊት ትርፍ ሶላቶችን መስገድ ክልክል ነው፡፡
ከዙሁር በኋላ ሁለት ትርፍ ሶላቶች ይሰገዳሉ፡፡ በድምሩ ለዙሁር ሶላት ስድስት ራቲባ
የትርፍ ሶላቶች አሉት ማለት ነው፡፡ የዓስር ሶላት ራቲባ የሆነ ሱና ሶላት የለውም፡፡
ከመግሪብ ሶላት በኋላ ሁለት ረከዓ ፣ ከዒሻ በኋላ ሁለት ረከዓ፣ ከፈጅር ሶላት በፊት
ሁለት ረከዓ የራቲባ ሱና ሶላቶች ይሰገዳሉ፡፡
ከፈጅር በፊት ያለችው ሁለት ረከዓ ከሌሎች የሱና ሶላቶች የምትለይበት አንደኛ ቀለል
ተደርጋ መሰገዷ ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ የሚከተሉት ቁርአናዊ አንቀጾች ይቀሩባታል፡፡
መጀመሪያው ረከዓ ላይ “ቁል ያ አዩሀል ካፊሩን” ፤ ሁለተኛው ረከዓ ላይ ደግሞ “ቁል
60/99
ሁወሏሁ አሀድ” ወይም መጀመሪያው ረከዓ ላይ አል በቀራህ፡ “ቁሉ አመና ቢላህ ወማ
ኡንዚለ …” ሁለተኛው ረከዓ ላይ ደግሞ አል ኢምራን፡ “ቁል ያአህለል ኪታብ ተዓለው
ኢላ ከሊመቲን ሰዋኢን …” ይቀራባቸዋል፡፡

የፈጅር ሱና ትልቅ ደረጃ ያላት በመሆኑ በሰፈርም ይሁን በአገር ውስጥ ትሰገዳለች፡፡

ነብዩ ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

"‫"ركعتا الفجر خير من الدنيا وما فيها‬

“የፈጅር ሁለት ረከዓዎች ዱንያና በውስጡ ካለው ሁሉ በላጭ ናቸው” ሙስሊም፡

ከትርፍ ሶላቶች መካከል፡ “ዊትር” ይገኝበታል፡፡ ጠንካራ ከሚባሉ ትርፍ ሶላቶች


መካከል አንዱ ዊትር ነው፡፡ ከዑለሞች መካከል አንዳንዶች እስከ ዋጅብ ያደረሱታል፡፡

ኢማም አህመድ I የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

"‫"من ترك الوتر فهو رجل سوء ال ينبغي أن تقبل له شهادة‬

“ዊትርን የተወ ሰው ክፉ ሰው ነው ፣ ምስክርነቱን ሊቀበሉት አይገባም፡፡”

የሌሊት ሶላት የሚቋጨው በዊትር ነው፡፡ ሌሊት ላይ አልቆምም ብሎ ያሰበ ሰው


ከመተኛቱ በፊት ዊትርን ይስገድ፡፡ መጨረሻ ሌሊት ላይ እነሳለሁ ብሎ ተስፋ ያደረገ
ሰው ደግሞ የሌሊት ሶላቶችን በአንድ የዊትር ረከዓ ይቋጭ፡፡

ነብዩ ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

"‫"اجعلوا آخر صالتكم بالليل وترا‬

“በሌሊት የሶላታችሁን መጨረሻ ዊትርን አድርጉ” ቡኻሪ፡ ሙሰሊም፡


61/99
የዊትር አነስተኛዋ ረከዓ አንድ ነች፡፡ ብዛቱ ደግሞ አስራ አንድ ረከዓ ነው፡፡ የተሟላ
አነስተኛ የሚባለው ደግሞ ሶስት ረከዓ ነው፡፡ በሶስት ረከዓ ዊትር ቢሰግድ መልካም
ነው፡፡ ከፈለገ ሶስቱንም ረከዓ በአንድ ተሸሁድ ማጠናቀቅ ይችላል፡፡ ከፈለገ ደግሞ
በሁለት ረከዓ ላይ አሰላምቶ አንዷን ረከዓ ብቻዋን መስገድ ይችላል፡፡ አምስት ረከዓ ፣
ሰባት ረከዓ በአንድ ተሸሁድ ብቻ ሰግዶ ማሰላመትም ይችላል፡፡ ዘጠኝ ረከዓ ሲሰግድ
ግን ተራውን ሰግዶ ስምተኛው ላይ ተሸሁድ አድርጎ ለዘጠነኛው ረከዓ ይቁም፡፡ ከዚያም
ተሸሁድ አድርጎ ያሰላምት፡፡ ስለዚህ ዘጠኝ ረከዓ በሚሰግድ ጊዜ ሁለት ተሸሁድና አንድ
ሰላምታ አለው ማለት ነው፡፡ አስራ አንድ የሚሰግድ ከሆነ ደግሞ በየሁለት ረከዓው
እያሰላመተ መጨረሻ ላይ አስራ አንድኛዋን ረከዓ ብቻዋን ይስገዳት፡፡

ሌሊት ላይ ዊትርን ሳይሰግድ ቢቀር ቀን ላይ ቀዷ ማውጣት ይችላል፡፡ ነገር ግን


ረከዓዎችን ሙሉ ቁጥር (ሸፍዕ) አድርጎ መስገድ አለበት፡፡ ሶስት ረከዓ መስገድ
የለመደ ሰው ቀን ላይ ቀዷ ማውጣት ከፈለገ አራት ረከዓ አድርጎ ይስገድ፡፡ አምስት
ረከዓ መስገድ የለመደ ደግሞ ቀን ላይ ስድስት ረከዓ አድርጎ ይስገድ፡፡ ለዚህ ማስረጃችን
የሚከተለው ትክክለኛ ሐዲስ ነው፡፡
"‫إذا غلبه نوم أو وجع عن قيام الليل صلى من النهار ثنتي عشرة ركعة‬ ‫ﷺ‬ ‫"وكان‬

“ረሡል ‫ﷺ‬ እንቅልፍ ካሸነፋቸው ወይም ህመም (ከታመሙ) እና ሌሊት ሶላት


ሳይቆሙ ከቀሩ በቀን አስራ ሁለት ረከዓ አድርገው ይሰግዱ ነበር፡፡” ሙስሊም፡

“በፈርድ እና በሱና መካከል ያለው ብይን መለያየት”

ጥያቄ፡ - በፈርድ እና በሱና መካከል ልዩነቱ ምንድን ነው?

መልስ፡ አዎ!በፈርድ እና በሱና መካከል በርከታ ልዩነቶች አሉ፡፡ ግልጽ ከሆኑት ልዩነቶች
62/99
መካከል የሚከተሉት ይገኛሉ፡-

በሰፈር ላይ እያለን ትርፍ ሶላቶችን ወደፈለገው አቅጣጫ ቢሆንም በፈረስ ፣ በግመል ፣


በመኪና ፣ በአውሮፕላን ላይ ሆኖ መስገድ ይቻላል፡፡ ሩኩዕና ሱጁድ ላይ እየጠቀሰ
መስገድ ይችላል፡፡ ምክንያቱም ረሡል ‫ﷺ‬ ይህን ተግባር ሲፈጽሙ እንደነበር (ቡኻሪ
፣ ነሳኢይ እና አቡዳውድ) ላይ ተዘግቦ ይገኛል፡፡

በፈርድ እና በሱና መካከል ያለው ልዩነት፡ ወደ ፈርድ ሶላት አንዴ ከገባ ፣


አንገብጋቢ ሁኔታ ካልገጠመው በቀር መውጣት አይፈቀድም፡፡ ከወጣም ሐጢያተኛ
ይሆናል፡፡ ትርፍ ሶላት ግን ያለምንም ችግር መውጣት ይችላል፡፡ ዑለሞች በትርፍ ሶላት
መውጣቱ የተጠላ ተግባር ነው ቢሉም በመውጣቱ ግን ሐጢያተኛ አይሆንም፡፡

ሌላው መለያ፡- ፈርድ ሶላት በጀመዓ መስገድ ተደንግጓል፡፡ በተወሰኑ ሶላቶች ብቻ


ሲቀር - ማለትም በኢስቲስቃእ ፣ በኩሱፍ እና በተራዊህ - በትርፍ ሶላቶች በጀማዓ
መስገድ አልተደነገም፡፡ ነብዩ ‫ﷺ‬ በአንዳንድ ሌሊቶች ከሶሃቦች ጋር ለምሳሌ ከኢብን
ዓባስ ፣ ከሁዘይፋ እና ከብን መስዑድ ጋር በጀማዓ እንደሰገዱት አንዳንድ ጊዜ ሱና
ሶላቶችን በጀመዓ ቢሰገድ ግን ችግር የለውም፡፡

ረሡል ‫ﷺ‬ በረመዷን ለሶስት ቀናት ያክል በጀማዓ መስገዳቸው በሀዲስ ተረጋግጧል፡፡
ከዚያም በሰዎች ላይ ግዴታ ይደረጋል ብለው ስለፈሩ ከቤታቸው ቀርተዋል፡፡ ቡኻሪ፡

ሙስሊም፡

በረመዷን በጀማዓ መስገድ ሱና ነው፡፡ ረሡል ‫ﷺ‬ በጀማዓ መስገዱን የተውት


ፈርድ ይደረጋል ብለው በመስጋታቸው እንደሆነ ከዚህ ቀደም አይተናል፡፡ ከሞቱ በኋላ
ግን የሚያስፈራው ነገር በመወገዱ በጀማዓ መስገድ ችግር የለውም፡፡
63/99
“ሶላተል ጀናዛ”

ጥያቄ፡ - ትክክለኛ በሆነ የሙስሊም ዘገባ በጀናዛ ላይ አራት ተክቢራዎች እንዳሉ


ይታወቃል፡፡ ከዚህ ሌላ እንደመጣም እንሰማለን፡፡ ታዲያ ይህን ጉዳይ እንዴት ነው
የምናስማማው?

መልስ፡- ነብዩ ‫ﷺ‬ባብዛኛው ያደረጉት አራት ተክቢራዎችን ብቻ ነው፡፡

ነገር ግን ዘይድ ብን አል’አርቀም 4 ባስተላለፈው ሐዲስ ረሡል ‫ﷺ‬ አምስት


ተክቢያዎችን ማድረጋቸው ተዘግቧል፡፡ ረሡል ‫ﷺ‬ ከስድስት እስከ ሰባት ተክቢራ
ማድረጋቸውም ተወርቷል፡፡ በዚህ ምክንያት ከአራት እስከ ሰባት ቢጨመር ችግር
የለውም፡፡

ከነብያችን ‫ ﷺ‬በሶሂህ ሀዲስ በተረጋገጠው አንድ ጊዜ አንዱን ፣ በሌላ ጊዜ ሌላውን


መጠቀሙ ጥሩ ነው፡፡ ማለትም አንዳንድ ጊዜ አራት ፣ አንዳንድ ጊዜ አምስት ፣
አንዳንድ ጊዜ ስድስት ፣ አንዳንድ ጊዜ ሰባት መጠቀሙ በላጭ ነው፡፡ ነገር ግን
በአብዛኛው የተገኘው አራት ነው፡፡

በሱና የመጣ ማንኛውም ነገር በተለያየ መልኩ መጠቀሙ በላጭ መሆኑ መታወቅ
አለበት፡፡

“በሶላተል ጀናዛ በጀማዓ መስገድ ሸሪዓዊ ብይኑ ምንድን ነው?”

ጥያቄ፡- ልክ እንደ አምስት ወቅት ሶላት ሶላተል ጀናዛ በጀመዓ መስገድ ግዴታ ነው?

መልስ፡-በሟቹ ላይ ለመስገድ ጀማዓ ግዴታ አይደለም፡፡ ነገር ግን ከዚህ በፊት


እንዳሳለፍነው በላጩ በጀማዓ መስገዱ ነው፡፡ ምክንያቱም የሰጋጁ መጠን በበዛ ቁጥር
64/99
በሟቹ ላይ የሚሰግደው ዱዓውና ሸፈዓው ተቀባይነት ለማግኘት የቀረበ ነው፡፡
“ስለሟቹ ባህሪ መጠየቅ እንዴት ይታያል”
ጥያቄ፡- ወደኢማሙ አንድ ሟች እንዲሰገድበት ከመጣለት ስለሰውየው ማንነት እና
አንዳንድ ሁኔታዎች መጠየቅ ይቻላል? ለምሳሌ ፡- ይህ ሰው ይሰግድ ነበር? እና
የመሳሰሉ ጥያቄዎችን ማቅረብ ይቻላል?

መልስ፡- በዲን ላይ ድንበር ማለፍ በመሆኑ በዚህ ላይ ያለኝ አስተያየት ስለሟቹ ሁኔታ
መጠየቅ ተገቢ አይደለም የሚል ነው፡፡ ስለሟቹ ሁኔታ መጠየቅ ቢድዓ ከመሆኑ ባሻገር
ልክ የሙስሊሞችን ነውር እንደመከታተል ነው የሚቆጠረው፡፡ በነብዩ ‫ﷺ‬ ዘመን
ሙናፊቆች ነበሩ፡፡ ነገር ግን ይህ ሙናፊቅ ነው? ይህ ሙእሚን ነው? ብለው ጠይቀው
አያውቁም፡፡ ነገር ግን ረሡል ‫ﷺ‬ በርካታ ገንዘብና ሀብት ከማግኘታቸው በፊት ሟቹ
እዳ ነበረበት ወይስ አልነበረበትም? የሚል ጥያቄ ይጠይቁ ነበር፡፡ እዳ አለበት ካሏቸውና
የሚከፍለው ከሌለ የሚከተለውን ይናገራሉ፡-

"‫"صلوا على صاحبكم‬

“በጓደኛችሁ ላይ ስገዱበት” ረሡል ‫ﷺ‬ ብዙ ገንዘብና ሐብት ካገኙ በኋላ እዳ ከፋይ


ሆኑ፡፡ ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

“ሶላትን በተወ ሰው ላይ ሶላት መስገድ ሸሪዓዊ ብይኑ ምንድን ነው?”

ጥያቄ፡- እንደማይሰግድ እያወቁ ቅርብ ዘመዳቸውም ይሁን ሌላ ሶላተል ጀናዛ


እንዲሰገድበት ለሙስሊሞች የሚያቀርቡ ሰዎች ዙሪያ ምን አስተያየት አለወት? ሶላት
ሊሰገድበትስ ይገባል? ሙስሊሞች በመስገዳቸው ይመነዳሉ? የማይሰግድ ሰው
ከሙስሊሞች ጋር መቀበር አለበት ወይስ?
65/99
መልስ፡- ሶላት አለመስገዱን እያወቁ ሙስሊሞች እንዲሰግዱበት ማቅረብ አይገባም፡፡
ምክንያቱም ሙስሊሞች እንዲሰግዱበት እያቀረበ ያለው ካፊርን እንጅ ሙስሊምን
አይደለም፡፡ ቢሰግዱበትም ሶላታቸው ለእርሱ አይጠቅመውም፡፡ ከሙስሊም መቃብርም
መቀበር የለበትም፡፡

ስለርሱ የሚያውቁት ነገር ባለመኖሩ በእርሱ ላይ የሰገዱ ሙስሊሞች በመስገዳቸው


ሓጢያት የለባቸውም፡፡ ስለሁኔታው የሚያውቁ ሙስሊሞች ከሆኑ ግን በእነርሱ ላይ
ግዴታ ያለባቸው ሶላት በማይሰግድ ሰው ላይ አለመስገድ ነው፡፡

“ወንጀለኛ በሆኑ ሰዎች ላይ ሶላት መስገድን መተው እንዴት ይታያል?”

ጥያቄ፡- ሰዎችን ለማስጠንቀቅና ወንጀልን ከባድ ለማድረግ አስቦ ወንጀል በሚፈጽም


ሰው አልሰግድም ብሎ ወጦ ስለሚሄድ ሰው ምንድን ነው አስተያየትዎት?

መልስ፡ - አንድ ወንጀለኛ ወንጀሉ ከኢስላም የማያስወጣው ከሆነ በእርሱ ላይ ሶላት


መስገድ ተገቢ ነው፡፡ ሙስሊሞች ለእርሱ ዱዓ ማድረጋቸው ተገቢ ነው፡፡ መውጣትና
ሶላትን መተው አይገባም፡፡ ነገር ግን ሰጋጁ በአገሩ በጣም አንገብጋቢ ፣ ወንጀለኛው
ደግሞ ወንጀልን ሳያፍር በአደባባይ ፈጻሜ ከሆነና በእርሱ ላይ ባልሰግድበት ሸሪዓዊ
ጥቅሙ አመዛኝ ነው ብሎ ካሰበ አለመስገድ ይችላል፡፡
“ሴት በጀናዛ ላይ መስገዷ እንዴት ይታያል?”
ጥያቄ፡- አንዲት ሴት ወደመስጊድ በመሄድ በሟች ላይ መስገድ ትችላለች? በቤቷ
ውስጥ በእርሱ ላይ ብትሰግድ ይበቃላታል? ከሁለቱ የቱ ነው በላጩ?

መልስ፡- በቤቷ በእርሱ ላይ መስገዷ በላጭ ነው፡፡ ከቤቷ ወጣ ከሰዎች ጋር ብትሰግድም


ችግር የለውም፡፡ ነገር ግን ከእኛ ዘንድ ይህ ነገር የታወቀ አይደለም፡፡
66/99
በተለይም ሟች ቤተሰብ ከሆነ በላጭ የሚሆንላት ወደመስጊድ ወጣ መስገዷ ሳይሆን
ከቤት መስገዷ ነው፡፡ ሟቹ ከውጭ ከሆነ ሶለተል ጋኢብ (የርቀት ሶላት) መስገድ
አይገባትም፡፡

“በተቀበረ ጀናዛ እና በጋኢብ (በርቀት) መስገድ”

ጥያቄ፡- ለሶላቱል ጋኢብ (በርቀት መስገድ) እና በተቀበረ ሰው ላይ ለመስገድ የጊዜ


ገደብ ይኖረዋል?

መልስ፡- በእርሱ ላይ ያልተሰገደበት ካልሆነ በቀር ፣ በርቀት መስገድ ትክክለኛው


አመለካከት ሱና አይደለም የሚለው ነው፡፡ ለምሳሌ፡- አንድ ሙስሊም በበረሃ ወይም
በኩፍር አገር ሊሞት ይችላል፡፡ በእርሱ ላይ ይሰገድ አይሰገድ የሚታወቅ ነገር ከሌለ
በእርሱ ላይ ሶላቱል ጋኢብ መስገድ ዋጅብ ነው፡፡ ምክንያቱም ነብዩ ‫ ﷺ‬ነጃሽ i በሞተ
ጊዜ ወደመስገጃ ቦታ በመውጣት ሶላተል ጋኢብ (የርቀት ሶላት) ሰግደዋል፡፡ ቡኻሪ፡

በጋኢብ መስገድ በነጃሽ i ላይ ካልሆነ በቀር በሌላ ሰው ላይ አልተገኘም፡፡ ነጃሽ በሞተ


ጊዜ እርሱ በሚኖርበት አገር በእርሱ ጀናዛ ላይ ተሰገደበት የሚል መረጃም የለም፡፡

ሙስሊሞች በእርሱ ላይ መስገዳቸው የታወቀለት ሰው በሌላ አገር ያሉ ሙስሊሞች


በእርሱ ላይ መስገዳቸው ሱና አይደለም፡፡
በቀብር ላይ መስገድ ከነብዩ ‫ﷺ‬ የተገኘ ሱና ነው፡፡ ነገር ግን ዑለሞች የጊዜ ገደብ
አድርገዋል፡፡ አንዳንዶች ገደብ ያላደረጉም አሉ፡፡ ትክክለኛውም ገደብ አለመደረጉ
ነው፡፡ ነገር ግን መስፈርት አለው፡፡ እርሱም የሚሰገድበት ሰው በሰጋጆች እድሜ ውስጥ
የሞተ ማለትም ተወልደው ተምይዝ (ሰባት አመትና ከዚያ በላይ) እድሜ ከሞላቸው
በኋላ የሞተ መሆን አለበት፡፡
67/99
ነገር ግን ከዚያ በፊት ሞቶ ከሆነ በቀብር ላይ መስገድ ሱና አይሆንም፡፡

ለምሳሌ፡- አንድ ሰው በ አመተ ሒጅራ ቢሞትና በዚሁ አመት ደግሞ አንድ


ልጅ ቢወለድ ይህ ልጅ ትልቅ በሆነ ጊዜ እርሱ ሲወለድ በሞተው ሰው ቀብር ላይ
መስገድ አይችልም፡፡ ምክንያቱም ሟቹ ሲሞት የሶላት ባለቤት አልነበረም፡፡ ነገር ግን
አንድ ሰው በ አመተ ሂጅራ ቢሞትና ሌላው ሰው ደግሞ በ አመተ ሒጅራ
ቢወለድ ይህ ማለት በ አመተ ሂጅራ ግለሰቡ ሲሞት እርሱ የሀያ አመት ሰው
ነበር፡፡ ስለዚህ በሟቹ ላይ መስገድ ይችላል፡፡ ምክንያቱም ሲሞት ሰጋጁ የሶላት ባለቤት
ነበር፡፡

ይህን ያልንበት ምክንያት አንድ ሰው ቢድዓ መስርቶ ወደነብዩ ‫ﷺ‬ መቃብርም ይሁን
በቂእ ወደሚገኘው የሶሃቦች ቀብር በመሄድ ሶላት መስገድ አለብኝ እንዳይል ነው፡፡

“በጀናዛ ላይ ለመስገድ በሰጋጁ ላይ መስፈርት ይኖራል?”

ጥያቄ፡- በሞተው ሰው ላይ የሚሰግዱ አርባ ሰዎች ከትልቁም ይሁን ከትንሹ ሽርክ ነጻ


መሆናቸው መስፈርት ነው?

መልስ፡- ረሡል ‫ﷺ‬ በሚከተለው ሐዲሳቸው የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

‫"ما من رجل يموت فيقوم على جنازته أربعون رجال ال يشركون باهلل إال شفعهم هللا‬
"‫فيه‬

“አንድ ሰው ሞቶ በአላህ የማያጋሩ አርባ ሰዎች በጀናዛው ላይ አይቆሙበትም አላህ


ሸፈዓቸውን (ምልጃቸውን) የሚቀበላቸው ቢሆን እንጅ” ሙስሊም፡

“በአላህ ምንም የማያጋሩ” የሚለው ቃል ትንሹንም ትልቁንም ሽርክ ያካትታል፡፡


68/99
በዚህ አረፍተ ነገር ትልቁን ሽርክ ብቻ የማያጋሩ የሚል ትርጉምም ያስይዛል፡፡ ከእኔ
ዘንድ ግን ከሁለቱ አመለካከት አመዛኙ ግልጽ አልሆነልኝም፡፡ ምክንያቱም ትልቁን ሽርክ
የፈጸመ በጀናዛ ላይ ቢሰግድ ምልጃው ተቀባይነት እንደማያገኝ ምንም ጥርጥር
የለውም፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት ሶላት እየሰገዱ ሳያውቁ ትልቁን ማጋራት የሚፈጽሙ
፤ ከቀብር ውስጥ ያለን አካል የሚጣሩ እራሳቸውን ሙስሊም አድርገው የሚገምቱ
ሰዎች አሉ፡፡ ያም ሆነ አማላጁ ሰው ከትንሹም ይሁን ከትልቁ ሽርክ የጸዳ መሆን
እንዳለበት የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ ትልቁን ሽርክ የሚፈጽም ሰው አማላጅ
አይሆንም፡፡ ትንሹን ሽርክ የሚፈጽም ግን አሻሚ ነው፡፡

“በአደጋ ሰውነቱ በተቆራረጠ ሰው ላይ ሶላት በእርሱ ላይ መስገድ ሸሪዓዊ ብይኑ ምንድን


ነው”

ጥያቄ፡- አንዳንድ ጊዜ በመኪና አደጋ ፣ በእሳት ቃጠሎ ፣ በህንጻ መደርመስ እና


በመሳሰሉ አደጋዎች የሰው ልጅ አካል ተቆራርጦ ይጠፋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ትንሽ የሆነ
ቁራጭ ሊገኝ ይችላል፡፡ ለምሳሌ፡- እጅና እራስ ሊገኝ ይችላል? በእነዚህ የሰውነት አካል
ላይ ሶላተል ጀናዛ መስገድ ይቻላል? ልክ አካል እንደሚታጠበው ቁራጭ አካሉ
መታጠብ አለበት?

መልስ፡- እግሩ የተቆረጠ ጀናዛ ላይ ተሰግዶበት ሲያበቃ የእግሩ ቁራጭ ቢገኝ አብሮ
ይቀበራል እንጅ በቁራጭ አካሉ ላይ ሶላተል ጀናዛ አይሰገድም፡፡ ነገር ግን የሟቹ አካል
በአጠቃላይ አልተገኘም፡፡ የተገኘው ራሱ ወይም እግር ወይም እጅ ብቻ ነው፡፡ ይህ ቁራጭ
አካል ከታጠበ እና ከተከፈነ በኋላ ሶላተል ጀናዛ ይሰገድበታል፡፡ ከዚያም ልክ እንደሙሉ
አካሉ ይቀበራል፡፡
69/99
“በሟች ላይ ብቻን መስገድ”

ጥያቄ፡- አንድ ሰው ሙስሊም መሞቱን አወቀ ከዚያም ዛሬ በስራ ስለተጠመድኩ


በእርሱ ላይ ለመስገድ አልተመቸኝም ነገ ከተቀበረ በኋላ ብቻየን እሰግድበታለሁ ማለት
ይችላል?

መልስ፡- በዚህ ጉዳይ የማውቀው ነገር የለኝም፡፡ ነገር ግን አጅር ወይም ምንዳ የሚፈልግ
ከሆነ ፣ ከመቀበሩ በፊት መስገድ ይኖርበታለ፡፡ ምክንያቱም ይህ በረሡል ‫ﷺ‬ ሱና
የመጣ ነው፡፡ ረሡል ‫ﷺ‬ ከተቀበረ በኋላ የሰገዱት መቀበሩን ባላወቁና መረጃ
ባልደረሳቸው ሰው ላይ ነው፡፡

“በውስጡ መቃብር ያለበት መስጊድ ውስጥ ሶላት መስገድ ይቻላል?”

ጥያቄ፡- በጎረቤታችን የሚገኝ አንድ መስጅድ አለ፡፡ የመስጅዱ ባለቤት ከእርሱ ዘንድ
ተቀብሮበት ይገኛል፡፡ በውስጡ ሶላት መስገድ ይቻላል? ወይስ ረሡል ‫ﷺ‬ በሀዲሳቸው
ከከለከሉትና ካስጠነቀቁት ተግባር ይሆናል? በዚህ መስጅድ መስገዱ የማይበቃ ከሆነ
ከዚህ በፊት የሰገድነው ሶላት እንዴት ይታያል? ወደሌሎች መስጊዶች ብንሄድ ደግሞ
ሩቅ በመሆናቸው ሶላተል ጀማዓ ሊያመልጠን ነው፡፡ ታዲያ ምን ይሻላል?

መልስ፡- ይህ መስጊድ ከቀብር ላይ ተገንብቶ ከሆነ በውስጡ መስገድ ሀራም ነው፡፡


ማፍረስ ግዴታ ነው፡፡ ምክንያቱም ነብዩ ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-

“አይሁድና ነሷራ ተረገሙ የነብያቶቻቸውን መቃብር መስጅድ አድርገው በመያዛቸው”


ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

ነገር ግን መስጅዱ ከቀብሩ የቀደመ ከሆነ ፣ አስከሬኑን ከመስጅዱ አውጥቶ


ሙስሊሞች ከሚቀበሩበት ቦታ መቅበር ግድ ይላል፡፡
70/99
መቀበር ከማይገባው ቦታ በመቀበሩ አስከሬኑን ከመስጅድ አውጥተን ወደሙስሊሞች
መቃብር ብንቀብረው ይህ ለእኛ ችግር የለውም፡፡ መስጅዶች ሙታን ሊቀበርባቸው
አይገባም፡፡ ከቀብሩ በፊት የተሰራ መስጅድ ከሆነ ከዚህ ቀደም የተሰገደው ሶላት ሁሉ
ትክክል ነው፡፡ ታዲያ ከዚህ ላይ ሶላቱ ትክክል ሊሆን ዘንድ መስፈርቱ ቀብሩ ወደቂብላ
አቅጣጫ አለመሆኑ ነው፡፡ ምክንያቱም ነብዩ ‫ﷺ‬ ወደቀብር ሶላት መስገድ ክልክል
ነው ብለው በሐዲሳቸው አስጠንቅቀዋል፡፡

“ሶላተል ጀናዛ ሲሰገድ ከኢማም ጎን መቆም እንዴት ይታያል?”

ጥያቄ፡- የሟች ቤተሰቦች ሶላተል ጀናዛ ለመስገድ ሲፈልጉ ከኢማሙ ጎን ይቆማሉ ይህ


በሸሪዓ እንዴት ይታያል?

መልስ፡-ይህ በሸሪዓ ምንም ዓይነት መሰረት የለውም፡፡ በሱናም ይሁን በዚህ ዙሪያ
የሚፈቀድ መሆኑ ከእውቀት ባለቤቶች የተገኘ ንግግር የለም፡፡

ኢማም ይቀደማል ተከታዮች ደግሞ ከኋላ ሆነው ይሰግዳሉ፡፡ ይህ ነው ከነብዩ ‫ﷺ‬


ሱና የተገኘው፡፡ ነገር ግን የጀናዛው ባለቤቶች ጀናዛውን ሲያስቀድሙ ከመጀመሪያው
ሶፍ ለመሆን ቦታ ካጡ በጀናዛውና በመጀመሪያው ሶፍ መካከል ሶፍ ሰርተው መቆም
ይችላሉ፡፡ ቦታ የሚጠብ ከሆነ ደግሞ በኢማሙ ግራና ቀኝ መቆም ይችላሉ፡፡
“በሶላተል ጀናዛ ጊዜ ከኢማም ጀርባ ሶፉ መብዛቱ በሸሪዓ እንዴት ይታያል?”
ጥያቄ፡ የሰጋጆች ቁጥር ካነሰ ሶፉን ከሶስት መክፈል ሱና ነው?

መልስ፡- የሚከተለው ሐዲስ ከነብዩ ‫ﷺ‬ መነገሩ ተረጋግጧል፡-

‫ إال شفعهم‬،‫"ما من رجل يموت فيقوم على جنازته أربعون رجال ال يشركون باهلل شيئا‬
"‫هللا فيه‬
71/99
“በአላህ አንድም የማያጋሩ አርባ ሰዎች በጀናዛው ላይ የሚቆሙበት አንድም ሟች
አይኖርም ፤ አላህ ሸፈአቸውን (ዱዓቸውን) የሚቀበላቸው ቢሆን እንጅ” ሙስሊም፡

"‫"ما من مسلم يموت فيصلي عليه ثالثة صفوف من المسلمين إال غفر له‬

“ሙስሊሞች በጀናዛው ላይ ሶስት ሶፍ ሰርተው የሚሰግዱበት አንድም ሙስሊም


አይኖርም ፣ ለእርሱ ምህረት የሚደረግለት ቢሆን እንጅ፡፡” አቡዳውድ፡ ኢብኑ ማጀህ፡

በሁለት በሁለት ምድብ ሶስት ሶፍ ማድረጉ የተወደደ ነው ይላሉ ዑለሞች፡፡ ሌሎች


ዑለሞች ደግሞ “አርባ ሰው” በሚለው ሐዲስ መሰረት ረሡል ‫ ﷺ‬የፈለጉት የሰዎችን
መብዛት ነው ብለዋል፡፡ ለሀቁ የቀረበው አመለካከትም ይህ ነው፡፡ በዚህ መሰረት በርካታ
ሰው የሚገኝ ከሆነ ቅድሚያ የመጀመሪያው ሶፍ እንዲሞላ ማድረግ ፣ ከዚያም
የሚቀጥለው ፣ ከዚያም የሚቀጥለው እየሞላ ይሂድ፡፡

“በሶላተል ጀናዛ ጊዜ የመክፈቻ ዱዓ ማድረግ እንዴት ይታያል?”

ጥያቄ፡- በሶላተል ጀናዛ ጊዜ የመክፈቻ ዱዓ ማድረግ በሸሪዓ ተደንግጓል?

መልስ፡- ዑለሞች በሶላተል ጀናዛ የመክፈቻ ዱዓ ማድረግ የተወደደ ተግባር እንዳልሆነ


አውስተዋል፡፡ ያቀረቡት ምክንያት ሶላተል ጀናዛ ነገሮችን በማቃለል ላይ የተመሰረተ
ነው፡፡ ይህ ከሆነ ኢስቲፍታህ ወይም የመክፈቻ ዱዓ አያስፈልገውም ይላሉ፡፡

ነገር ግን ፋቲሃን ከመቅራቱ በፊት “ተዓውዝ” ወይም አኡዙቢላሂ ሚነሸይጧኒ


ረጅም ብሎ ቢጀምር ችግር የለውም፡፡

አላህ የሚከተለውን በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ ተናግሯል፡-

﴾ ِ ْ‫الرِج‬ ِ ‫﴿فاِإ اذا ِارأْت الْ ُقرآ اَ فااسُاعِ ْذ ًِبّللِ ِمن الشَّْطا‬
َّ َ‫ا‬ ْ ‫ه ا‬ ْ ْ ‫ا ا‬
72/99
“ቁርኣንንም ባነበብህ ጊዜ እርጉም ከሆነው ሰይጣን በአላህ ተጠበቅ፡፡” አን ነህል፡

“በወንድ ፣ በሴት ፣ በህጻናት ጀናዛ ላይ ሲሰገድ ኢማሙ እንዴት ነው መቆም


ያለበት?”
ጥያቄ ፡- በወንድ ፣ በሴት እና በህጻናት ጀናዛ ላይ የኢማሙ አቋቋሙ እንዴት ነው
መሆን ያለበት?

መልስ፡- ትልቅም ይሁን ትንሽ ወንድ ከሆነ በራሱ ትክክል ፣ ትልቅም ይሁን ትንሽ ሴት
ከሆነች ደግሞ በመካከሏ ይቁም፡፡
“(አሏሁምመ ላተህሪምና አጅረሁ) የሚል ዱዓ ለሟች እናደርጋለን ትርጉሙ ምንድን
ነው?”
ጥያቄ፡-“አሏሁምመ ላ ተህሪምና አጅረሁ” የሚለው የረሡል ‫ﷺ‬ ዱዓ ትርጉም
ምንድን ነው?

መልስ፡- በጀናዛ ላይ የሚሰግድ ሰው አጅር (ምንዳ) እንዳለው ይታወቃል፡፡ ረሡል


‫ﷺ‬ የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-

،"‫ ومن شهدها حتى تدفن فله قيراطان‬،‫"من شهد الجنازة حتى يصلى عليها فله قيراط‬
"‫ "مثل الجبلين العظيمين‬:‫قيل وما القيراطان؟ قال‬

“በጀናዛ ላይ እስከሚሰገድ ድረስ የተገኘ ለርሱ ቂራጥ አለው ፤ እስከሚቀበር ድረስ የተገኘ
ደግሞ ለርሱ ሁለት ቂራጥ አለው” “ቂራጣን” ማለት ምን ማለት ነው? የሚል ጥያቄ

ቀረበላቸው፡፡ እርሳቻም “ልክ ሁለት ታላላቅ ተራራ አይነት” በማለት ምላሽ ሰጡ፡፡ ቡኻሪ፡

ሙስሊም፡

“ላተህሪምና አጅረሁ” (ምንዳውን አትከልክለን) ማለት ፡ በእርሱ ላይ ሰግደን


የምናገኘውን ምንዳ አታሳጣን ማለት ነው፡፡
73/99
“በሰጋጆች ላይ የሚከሰቱ ስህተቶች”
“አቃመሀሏሁ ወአዳመህ” የሚለው ቃል”
ጥያቄ፡ - አንዳንድ ሰዎች ለሶላት ኢቃማ ከተደረገ በኋላ “አቃመሀሏሁ ወአዳመሀ”
ሲሉ ይደመጣል በሸሪዓ እንዴት ይታያል?

መልስ፡- ረሡል ‫ﷺ‬ ሙዓዚኑ “ቀድ ቃመቲ ሶላህ” ካለ በኋላ “አቃመሀሏሁ


ወአዳመሀ” እንደሚሉ በሐዲስ መጧል፡፡ ነገር ግን ሀዲሱ ደካማ በመሆኑ ማስረጃ
አይሆንም፡፡

“ተቀርጸ በተቀመጠ አዛን ሰዎችን ለሶላት ጥሪ ማድረግ እንዴት ይታያል?”

ጥያቄ፡- ተቀርጾ በተቀመጠ አዛን ሰዎችን ወደሶላት ጥሪ ማድረግ ትክክል ይሆናል?

መልስ፡- አዛን ዒባዳ ነው፡፡ ዒባዳ ደግሞ ለርሱ ኒያ ያስፈልገዋል፡፡ በመሆኑም በተቀረጸ
አዛን ሰዎች ወደሶላት እንዲመጡ ማድረግ ትክክለኛ ተግባር አይደለም፡፡

“የፈጅር ወቅት እስኪያልፍ ድረስ እንቅልፍ ሳይተኙ (እያወሩ) ማንጋት እንዴት ይታያል?”

ጥያቄ፡ - ሌሊትን (በወሬ) አንግቶ ሲያበቃ ጸሐይ ከወጣች በኋላ ሶላትን ቢሰግድ
ሶላቱ ተቀባይነት ይኖረዋል? ይህን የሚፈጽም ሰው ወቅቱን ጠብቆ የሚሰግዳቸው
ሶላቶችስ ሸሪዓዊ ብይን ምን ይሆን?

መልስ፡- በወቅቱ መስገድ እየቻለ ከወቅቱ ውጭ የሚሰግደው ሶላት ተቀባይነት


የለውም፡፡ ማስረጃችን የሚከተለው የነብዩ ‫ ﷺ‬ሀዲስ ነው፡-

"‫"من عمل عمال ليس عليه أمرنا فهو رد‬

“በእርሱ የእኛ ትእዛዝ የሌለበት ስራን የሰራ ሰው እርሱ ተመላሽ ነው፡፡” ሙስሊም፡
74/99
እያወቀ ያለምንም ምክንያት ሶላትን ከወቅቷ አዘግይቶ የሰገደ ሰው የአላህ እንዲሁም
የረሡል ‫ﷺ‬ ትዕዛዝ የሌለበትን ስራ ፈጸመ፡፡ ስራው በእርሱ ላይ ተመላሽ ይሆንበታል፡፡

ሶላቱን በእንቅልፍ ለማሳለፍ የሚከተለውን የረሡል ሐዲስ እንደምክንያት አቅርቦ


ቢሞግተን የሚከተለውን ምላሽ እንሰጠዋለን፡፡

"‫"من نام عن صالة أو نسيها فليصلها إذا ذكرها ال كفارة لها إال ذلك‬

“ከሶላት የተኛ ወይም የረሳት ሲያስታውስ ይስገዳት ፣ እርሱ እንጅ ለእርሷ ማካካሻ
የላትም” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

ቀደም ብሎ መንቃት ፣ ቀደም ብሎ መተኛት እየቻለ ወይም የማንቂያ ሰዓት


እያለው ወይም የሚያነቃ አካል እያለው በራሱ ችግር ከወቅቱ ውጭ ሶላትን የሚሰግድ
ሰው ሶላቱ ተቀባይነትን አያገኝም፡፡
በወቅቱ የሚሰግዳቸው ሌሎች ሶላቶች ግን ተቀባይነት አላቸው፡፡
በዚህ አጋጣሚ የተወሰኑ አቅጣጫዎችን መስጠት እፈልጋለሁ፡፡ በዚህ የዱንያ
ህይዎት የተፈጠርነው ለዒባዳ በመሆኑ ፣ ሞት መቼ እንደሚመጣ ስለማይታወቅና ዋጋ
ወደሚሰጥበት ፣ ስራ ወደሌለበት አኼራ መሸጋገራችን ስለማይቀር ዒባዳችንን አላህ
በሚወደው መልኩ መፈጸም ይኖርብናል፡፡
ረሡል ‫ ﷺ‬የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-

‫ أو ولد‬،‫ أو علم ينتفع به‬،‫ صدقة جارية‬:‫"إذا مات ابن آدم انقطع عمله إال من ثالث‬
"‫صالح يدعو له‬

“የአደም ልጅ ሲሞት ሶስት ነገሮች እንጅ ስራው በአጠቃላይ ይቋረጣል፡ ቋሚ ሶደቃ ፣


የሚጠቀሙበት እውቀት ፣ ለእርሱ ዱዓ የሚያደርግ ደግ ልጅ” ሙስሊም፡
75/99
“የፈጅርን (የሱብሂን) ሶላት ወቅቱ ከወጣ በኋላ መስገድ በሸሪዓ እንዴት ይታያል?”
ጥያቄ፡- ወቅት እስኪወጣ ድረስ ፈጅር ሶላት የሚያዘገይ ሰው ሸሪዓዊ ብይኑ ምንድን
ነው?
መልስ፡ - ወቅት ቢወጣም የፈጅርን ሶላት አዘግይቶ መስገድ ይበቃል የሚል እምነት
ኖሯቸው ከሆነ በአላህ ክህደት ነው፡፡ ያለምንም ሸሪዓዊ ምክንያት ወቅትን ማዘግየት
ይቻላል የሚል እምነት ያለው ሰው ለቁርኣን ፣ ለሐዲስ እና ለሙስሊሞች ስምምነት
ተቃራኒ በመሆኑ ካፊር ነው፡፡

ከወቅቱ ማዘግየት ይበቃል የሚል እምነት ሳይኖረው ፤ ነገር ግን ነፍሱ አሸንፋው


በማዘግየቱ ወንጀለኛ መሆኑን የሚያውቅ ከሆነ ይህ ሰው ጸጸት ሊያደርግ ይገባዋል፡፡
ክህደት ውስጥ የሚያስገባ ወንጀል እንኳ ቢፈጽም የተውበት በር ክፍት በመሆኑ ከዚህ
ተግባሩ ተጸጽቶ ወደትክክለኛው መስመር መምጣት አለበት፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-


ِ‫الذتُوب ا‬
‫ج اْعا ِتَّهُ ُه او‬ ِ َّ ََّ ِ ِ‫اّلل‬
َّ ‫اسارفُوا اَِاى أات ُف ِْ ِه ْ اال تا ْقناطُوا ِمن َّر َْحاِة‬ ِ َّ ‫﴿ُِ َي ًَِ ِاد‬
‫اّللا يا ْغفُر ُّ ا‬ ْ ‫ين أ‬
‫ي ال ذ ا‬
‫ْا ا ا‬
﴾ُ ْ‫الرِح‬
َّ ‫ور‬
ُ ‫الْغا ُف‬
“በላቸው “እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ
እዝነት ተስፋ አትቁረጡ ፡፡ አላህ ሃጢያቶችን በመላ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ
መሃሪው አዛኙ ነውና፡፡” አዝ ዙመር፡

ስለነርሱ ባህሪ የሚያውቅ ሰው ሊመክራቸው ወደትክክለኛው አቅጣጫ ሊመራቸው


ይገባል፡፡ ከተመለሱ መልካም ነው፡፡ ካለበለዚያ ግን ከተጠያቂነት ነጻ ይሆን ዘንድ
ለሚመለከታቸው አካላት ሁኔታውን ማድረስ ይገባዋል፡፡
76/99
“ስስ በሆነ ልብስ ሶላት መስገድ በሸሪዓ እንዴት ይታያል?”

ጥያቄ፡- በርካታ ሰዎች አካል የሚያሳይ ልብስ ከለበሱ በኋላ በስር ከጭን ግማሽ
የማይደርስ ሱሪ ያደርጋሉ፡፡ ከልብሱ ጀርባ ግማሹ ጭን ይታያል፡፡ የእነዚህ ሰዎች ሶላት
ሸሪዓዊ ብይን ምንድን ነው?

መልስ፡- የእነዚህ ሰዎች ሶላት ብይኑ አጭር ሱሪ ብቻ እንጅ ሌላ ልብስ ሳይለብሱ


እንደሚሰግዱ ሰዎች አይነት ናቸው፡፡ምክንያቱም አካልን የሚያሳይ ስስ ልብስ የለበሰ
ሰው ልክ እንዳለበሰ ነው የሚቆጠረው፡፡ በዚህ መሰረት ትክክለኛ በሆነው የዑለሞች
ንግግር ሶላታቸው ትክክል አይሆንም፡፡ ይህ በኢማም አህመድ መዝሀብ የታወቀ ጉደይ
ነው፡፡ ምክንያቱም የሚከተለውን የአላህ ቃል ተግባራዊ ለማድረግ ወንድ ሰጋጅ
ከእምብርቱ እስከ ጉልበቱ ያለው አካሉ መሸፈን አለበት፡፡

﴾‫ند ُك ِه ام ْْ ِج ٍد‬ ‫﴿ اَي باِِن ا‬


‫آد ام ُخ ُذواْ ِزينا ُا ُك ْ َِ ا‬
“የአደም ልጅ ሆይ! (ሐፍረተ ገላችሁን የሚሸፍኑትን) ጌጦቻችሁን
በመስገጃው ሁሉ ዘንድ ያዙ፡፡” አል አዕራፍ፡

በእነርሱ ላይ ግዴታ ያለበት ከሁለቱ አንዱ ነው፡-


አንደኛው አማራጭ ከእምብርት እስከ ጉልበት የሚሸፍን ሱሪ መልበስ ነው፡፡
ወይም ከዚህ አጭር ሱሪ ላይ አካል የማያሳይ ልብስ መደረብ ነው፡፡ ይህ በጥያቄው ላይ
የተጠቀሰው ተግባር ስህተት እና አደገኛ ነው፡፡ ይህን የሚፈጽሙ ሰዎች ወደአላህ
ተጸጽተው መመለስ አለባቸው፡፡ በሶላታቸው ውስጥ መሸፈን ያለበትን የሰውነት አካል
ለመሸፈን መነሳሳት አለባቸው፡፡
ለእኛም ለሙስሊም ወንድሞቻችን ቅኑን መንገድና ለሚወደውና ለሚቀበለው ተግባር
77/99
እንዲመራቸው አላህን እንጠይቃለን፡፡ እርሱ ለጋስና ቸር ነውና፡፡

“ወደሶላት እየፈጠኑ መሄድ በሸሪዓ እንዴት ይታያል?”

ጥያቄ፡- ወደሶላት እየፈጠኑ መሄድ ሸሪዓዊ ብይኑ ምንድን ነው?

መልስ፡- ወደመስጊድ ሲሄዱ መፍጠን ክልክል ነው፡፡ ምክንያቱም ነብዩ ‫ﷺ‬ አላህን
ፈርተን እና ተረጋግተን ወደመስጊድ እንድንሄድ አዘዋል፡፡ መፍጠንን ደግሞ
ከልክለዋል፡፡ ነገር ግን አንዳንድ የእውቀት ባለቤቶች የሶላት ረከዓ ያመልጠኛል ብሎ
ከፈራ የማያስቀይም በሆነ የፍጥነት አካሄድ ቢሄድ ችግር የለውም ብለዋል፡፡ ለምሳሌ፡-
ኢማሙ ተጎንብሶ እያለ አስቀያሚ ባልሆነ ፍጥነት ተጉዞ ቢገባ ችግር የለውም፡፡ የነብዩ
‫ﷺ‬ ሐዲስ የሚጠቁመው ግን አንድ ረከዓ ቢያመልጠውም እንኳ በጣም እየፈጠነ
መጓዝ እንደሌለበት ነው፡፡

“አንድ ረከዓ ለማግኘት መፍጠን እንዴት ይታያል?”

ጥያቄ፡ - ከኢማሙ አንድ ረከዓ ለማግኘት ብሎ መፍጠን ይቻላል?

መልስ፡-ኢማሙ ሩኩዕ አድርጎ ወደሶለት የገባ ሰው መቸኮል የለበትም፡፡


ከመጀመሪያው ሶፍ እስከምትደርስ ድረስ ወደሶላት አትግባ፡፡ ምክንያቱም አቢ በክረተ
4 ተጎንብሶ ወደሶላት በገባ ጊዜ ነብዩ ‫ﷺ‬ የሚከተለውን እርምት ሰጠውታል፡-

"‫"زادك هللا حرصا وال تعد‬

“ጉጉትህን አላህ ይጨምርልህ ፤ ነገር ግን (እንዲህ አይነት ተግባር) እንዳትደግም፡፡” (ቡኻሪ፡


783)

“የሚሰግድን ሰው በድምጽ መረበሽ በሸሪዓ እንዴት ይታያል?”


78/99
ጥያቄ፡- በመስጊድ ውስጥ ሰጋጆችን በሚረብሽ ሁኔታ እየጮኹ ቁርኣን መቅራት
እንዴት ይታያል?

መልስ፡ ተማሪዎችን ፣ ሰጋጆችን ፣ ቁርኣን ቀሪዎችን በሚረብሽ ሁኔታ ቁርኣን መቅራት


ረሡል ‫ﷺ‬ የከለከሉት ተግባር በመሆኑ ሀራም ነው፡፡ ማሊክ ሙወጦእ በሚባለው
ኪታባቸው ላይ ከፈርዋ ብን ዓምር 4 ይዘው የሚከተለውን አውርተዋል፡ - ሰዎች
ቁርኣንን በጣም ጮክ አድርገው እየቀሩ ሶላት እየሰገዱ ነብዩ ‫ﷺ‬ መጡ፡፡ ከዚያም
የሚከተለውን ተናገሩ፡-

‫ وال يجهر بعضكم على بعض‬،‫ فلينظر بما يناجيه به‬،‫"إن المصلى يناجي ربه‬
"‫بالقرآن‬

“ሰጋጅ የሆነ ሰው ከጌታው ጋር ነው የሚያወራው ፣ ምን እንደሚያወራ ያስተውል ፣


ከፊሉ በከፊሉ ላይ ቁርኣን በመቅራት አይጩህ” አህመድ፡ ሙወጦእ፡ አልባኒ ሶሂሁ አል ጃሚዕ፡

“ተህየተል መስጅድን ትቶ ኢማምን መጠባበቅ”

ጥያቄ፡- አንዳንድ ሰዎች ኢቃም በሚደረግበት ወቅት ተህየተል መስጊጅን ትተው


የኢማሙን መግባት የሚጠባበቁ አሉ፡፡ ይህ ተግባራቸው በሸሪዓ እንዴት ይታያል?

መልስ፡- ጊዜዋ አጭር ሆና በተህየተል መስጅድ ሶላት የሚያስመልጣቸው ከሆነ ቆመው


ቢጠብቁ ችግር የለውም፡፡ ኢማሙ መቸ እንደሚመጣ ካላወቁ ግን በላጩ ተህየተል
መስጅድን መስገድ ነው፡፡ ተህየተል መስጅድን ጀምረህ ኢማሙ ከመጣ መጀመሪያው
ረከዓ ላይ ከሆንህ ቆርጠህ ወደሶላት ግባ ፣ ሁለተኛው ረከዓ ላይ ከሆንህ ደግሞ ቀለል
አድርገህ በማጠናቀቅ ወደጀማዓ ሶላት ግባ፡፡
79/99
“ሀይድ (የወር አበባ) ያለባት ሴት ሶላት መስገዷ በሸሪዓ እንዴት ይታያል?”

ጥያቄ፡- አንዲት ሴት ሀይድ ወይም የወር አባባ ላይ ሆና ሶላትን ብትሰግድ በሸሪዓ ብይኑ
ምንድን ነው?

መልስ፡- ሴት ልጅ ሀይድ ወይም የወሊድ ደግም ላይ ሆና ሶላት መስገድ


አልተፈቀደላትም፡፡

ረሡል ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-

"‫"أليس إذا حاضت لم تصل ولم تصم‬

“ሀይድ ያየች ጊዜ የማትሰግድ የማትጾም አይደለችም እንዴ?” ቡኻሪ፡

የወር አበባ ያየች ሴት ጾም መጾም እንዲሁም ሶላት መስገድ እንደተከለከለች


ሙስሊሞች ተስማምተዋል፡፡ ይህች ሴት በሀይድ ሆና ሶላት ሰግዳ ከሆነ ወደአላህ
ተውበት አድርጋ መመለስ እና ከአላህ ይቅርታልን መጠየቅ አለባት፡፡

“በምሰሶዎች መካከል ሶላት መስገድ”

ጥያቄ፡ - በምሰሶዎች መካከል ሶላት መስገድ ሸሪዓዊ ብይኑ ምንድን ነው?

መልስ፡- የቦታ መጨናነቅ ካለ በምሰሶዎች መካከል ሶላት መስገድ ይፈቀዳል፡፡


መጨናነቅ ከሌለ እና ቦታው ሰፊ ከሆነ ግን ሶፎች ስለሚቆረጡ በምሰሶዎች መካከል
መስገድ አይገባም፡፡

“ኢን'ነሏሀ መዓ'ሷቢሪን” የሚለው ቃል


ጥያቄ፡-ኢማሙ ሩኩዕ እንዳደረገ የደረሰ ተከታይ ሁለት ተክቢራዎችን ማድረግ
አለበት?
80/99
መልስ፡-ኢማሙ ሩኩዕ እንዳደረገ የደረሰ ተከታይ ለኢህራም ተክቢራ ካደረገ በኋላ
ወዲያውኑ ሩኩዕ ያድርግ፡፡
በዚህ ሰዓት ለሩኩዕ የሚደረገው ተክቢራ ዋጅብ ሳይሆን ሱና ይሆናል፡፡ ነገር ግን
ለሩኩእ ተክቢራ ቢያደርግ በላጭ ነው፡፡ ቢተወው ግን ችግር የለበትም፡፡ ከዚያ በኋላ
ከሚከተሉት ሶስት ባህሪያት ያገለለ አይሆንም፡፡

የመጀመሪያው ባህሪ፡ ኢማሙ ከመውረዱ በፊት ሩኩዕ ላይ መድረሱን ማረጋገጡ ነው፡፡


ሩኩዕን ካገኘ ፋቲሃ ባይቀራም ረከዓን አግኝቷል፡፡

ሁለተኛው ባህሪ፡ እርሱ ሩኩዕ ሳያደርግ በፊት ኢማሙ ከሩኩዕ መነሳቱን ሊያረጋግጥ
ነው፡፡ በዚህ ሰዓት ረከዓ ያመለጠው በመሆኑ ቀዷ ማውጣት ይኖርበታል፡፡

ሶስተኛው ባህሪ፡ ኢማሙን ሩኩዕ ላይ ነው ያገኘሁት ወይስ ከሩኩዕ ተነስቶ የሚል


ጥርጣሬ ካደረበት ጥርጣሬው ያደፋውን ይውሰድና ሶላቱን ይጨርስ፡፡ ጥርጣሬው
ኢማሙን ሩኩዕ ላይ ነው ያገኘሁት የሚል ከሆነ ረከዓውን አግኝቷል፡፡ ጥርጣሬው
ኢማሙን ያገኘሁት ከሩኩዕ ተነስቶ ነው የሚለው ካመዘነ ደግሞ ረከዓ ስላመለጠው
ቀዷ ያውጣ፡፡ መጨረሻ ላይ ግን ሰጀደተ ሰህው ይስገድ፡፡

አንድ ተከታይ ኢማሙን በሩኩዕ ላይ ነው ያገኘሁት ወይስ አይደለም የሚል


ጥርጣሬ ውስጥ ከገባ መሰረቱን መያዝ ነው፡፡ መሰረቱ ሩኩዕ ላይ አለማግኘቱ ነው፡፡
አምልጦኛል ብሎ ረከዓውን ይሙላ፡፡ ከዚያም ሰጀደተ ሰህው ይስገድ፡፡

ሌላው ሳይነሳ መቅረት የሌለበት ነጥብ በርካታ ሰዎች ኢማሙ ሩኩዕ አድርጎ ከደረሱ
ኡህ ኡህ በማለት በተከታታይ ይስላሉ ወይም “ኢንነሏሃ መዓ ሷቢሪን” ይላሉ ወይም
በእግራቸው ይደበድባሉ፡፡ ይህ ሁሉ የሱና ተቃራኒ ሲሆን ሰጋጆችንም መረበሽ ነው፡፡
81/99
ኢማሙ ሩኩዕ አርጎ በአስቀያሚ ሁኔታ ፈጥኖ ወደሶላት መግባት የተከለከለ ነው፡፡

ይህን አስመልክቶ የአላህ መልእክተኛ ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-

‫ فما‬،‫ وال تسرعوا‬،‫ وعليكم بالسكينة والوقار‬،‫"إذا سمعتم اإلقامة فامشوا إلى الصالة‬
"‫ وما فاتكم فأتموا‬،‫أدركتم فصلوا‬

“ኢቃም በሰማችሁ ጊዜ ወዲያውኑ ወደሶላት ሂዱ ፤ እርጋታና አላህን መፍራትን አደራ ፤


አትቸኩሉ ፤ ያገኛችሁትን ስገዱ ፤ ያመለጣችሁን ሙሉ፡፡” ቡኻሪ፡

“ህጻንን ከሶፍ ማራቅ በሸሪዓ እንዴት ይታያል”

ጥያቄ፡ - አንድ ህጻን በሶፍ ውስጥ ተቀምጦ እያለ ከተቀመጠበት ቦታ ማራቅ ይቻላል?

መልስ፡- ህጻንን ከተቀመጠበት ሶፍ ማራቅ አይገባም፡፡

ለዚህ ማስረጃው የሚሆነው የሚከተለው የረሡል ‫ﷺ‬ ሐዲስ ነው፡-

"‫"ال يقيم الرجل الرجل من مقامه ثم يجلس فيه‬

“አንድ ሰው በዚያ ቦታ እርሱ ሊቀመጥ ዘንድ ሌላውን ከቦታው አያስነሳው፡፡” ቡኻሪ፡


ሙስሊም፡

የተከለከለበት ምክንያት በህጻኑ ላይ ድንበር መተላለፍ ፣ ቀልብን መስበር ፣


ከሶላት እንዲሸሽ ማድረግ እና ጥላቻን መዝራት በመሆኑ ነው፡፡ ሕጻናቶችን በአንድ ሶፍ
አድርገን ከኋላ ብናደርጋቸው እንኳ ጨዋታ ቀልድ በሶላት ውስጥ ይከሰት ነበር፡፡ ይህን
ስጋት ለማስወገድ በየሶፉ ጣልቃ አስገብተን ብናቆማቸው ችግር የለውም፡፡

“በሽንት የተወጠረ ሰው ሶላት ሸሪዓዊ ብይን”

ጥያቄ ፡- አንድ ሰው ሽንት ቤት ቢሄድና ቢጸዳዳ ጀማዓ ሶላት ያመልጠኛል ብሎ ቢሰጋ


82/99
ጀማዓን ለማግኘት ሲባል በሽንት ተወጥሮ መስገድ ይችላል? ወይስ ጀመዓ
ቢያመልጠውም ተጸዳድቶ ወደሶላት መምጣት ነው ያለበት?

መልስ፡- ይህ ምክንያት የሚያሰጥ ችግር ስለሆነ ቢዘገይም እንኳ ተጸዳድቶ ፣ ውዱእ


አድርጎ ነው መምጣት ያለበት፡፡
ነብዩ ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-

"‫"ال صالة بحضرة الطعام وال هو يدافعه األخبثان‬

“ምግብ ቀርቦ ወይም ሽንትና ሰገራ ወጥረውት ሶላት የለም” ሙስሊም፡

“በሱትራ (ሰው እንዳያቋርጠው የሚያደርግ ግርዶሽ) ላይ ቸልተኝነት”

ጥያቄ፡- ሱትራ ሸሪዓዊ ብይኑ ምንድን ነው? መጠኑስ ምን ያክል መሆን አለበት?

መልስ፡- ሶላትን በኢማም ከሚከተል ሰው ውጭ ሱትራ በሶላት ውስጥ ጠንከር ያለ ሱና


ነው፡፡ ተከታይ ከሆነ ግን ሱትራ አያስፈልገውም፡፡ የኢማሙ ሱትራ የተከታዮችም ሱትራ
ነው፡፡

የሱትራን መጠን በተመለከተ የአላህ መልእክተኛ ‫ﷺ‬ ተጠይቀው የሚከተለውን


መልስ ሰጠዋል፡-

"‫"مثل مؤخرة الرحل‬

“የፈረስ ኮርቻ መደገፊያን ያክል” ሙስሊም፡

ነገር ግን ይህ ከፍተኛው ነው ከዚህ በታችም ማድረግ የተፈቀደ ነው፡፡


ረሡል ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-
"‫"إذا صلى أحدكم فليستتر ولو بسهم‬
83/99
“አንድ ሰው በሰገደ ጊዜ በቀስቱ እንኳ ቢሆን ይጋረድ” አህመድ፡

አሁንም የሚከተለው ሀዲስ መጧል፡-


"‫"أن من لم يحد فليخط خط‬
“(ሱትራ) ያላገኘ ሰው መስመር ያስምር”(አህመድ፡ 7392, ኢብኑ ማጀህ፡ 943,አልባኒ ሐዲሱን ዶኢፍ ብለውታል)

ሀፊዝ ብን ሀጀር i “ቡሉግ አልመራም” በተባለው ኪታባቸው ይህን ሀዲስ


ሙድጦሪብ (የዋዥቀ) ነው የሚል ብይን የሰጠ ሰው ትክክሉን አላገኘም ይላሉ፡፡
በተጨማሪ ይህን ሀዲስ ውድቅ ለማድረግ የሚያበቃ ምክንያት የለም ይላሉ፡፡ በዚህ
መሰረት ለሱትራ ቀላሏ መስመር ስትሆን ፣ ከፍተኛው ደግሞ የፈረስ ኮረቻ መደገፊያ
ያክል ነው፡፡
“በሰጋጅ ፊት ለፊት ማለፍ”
ጥያቄ፡- ፈርድ ሰጋጅም ሆነ ተከታይ ወይም ብቻውን በተከበረው መስጊድ (ሀረም)
የሚሰግድ ሰው ፊት ለፊት ማለፍ ሸሪዓዊ ብይኑ ምንድን ነው?

መልስ፡ - በተከበረው መስጊድም ይሁን በሌላ በተከታዮች ፊት ለፊት ማለፍ ችግር


የለውም፡፡ ማስረጃው የኢብን ዓባስ 4 ሐዲስ ነው፡፡ ሚና ላይ ነብዩ ‫ﷺ‬ ሶሃቦችን
እያሰገዱ ዓብደሏ ኢብን ዓባስ 4 ሴት አህያ እየጋለበ በሶፉ መካከል አቋርጦ ሄደ፡፡
በዚህ ተግባሩ ረሡል ‫ﷺ‬ አልተቃወሙትም፡፡ ቡኻሪ፡

መረጃው አጠቃላይ በመሆኑ ሰጋጁ ኢማምም ይሁን ብቻውን የሚሰግድ ፣


በተከበረው መስጊድም ይሁን በሌላ በፊት ለፊቱ አቋርጦ ማለፍ አይፈቀድም፡፡
በተከበረው መስጊድ ወይም መካ በሰጋጅ ፊት ለፊት ማለፍ አይጎዳም ወይም ሐጢያት
የለውም የሚል ማስረጃ ፍጹም የለም፡፡
84/99
“በሶላተል ጀማዓ ላይ ቸልተኝነት”
ጥያቄ፡ - በአንድ አካባቢ ተሰባስበው የሚኖሩ በርካታ ሰዎች በመኖሪያ ቤታቸው
ተሰባስበው መስገድ ይችላሉ? ወይስ ወደመስጊድ ሄደው ነው መስገድ ያለባቸው?

መልስ፡-እነዚህ ሰዎች መስጅድ ሄደው የመስገድ ግዴታ አለባቸው፡፡ ሁሉም


በአካባቢው ቅርብ የሆነ መስጅድ ካለ መስጅድ በጀማዓ እንጅ ከቤቱ መስገድ
የለበትም፡፡ ቤቱ አዛን የማይሰማበት ሩቅ ከሆነ ግን ከቤቱ በጀማዓ ቢሰግድ ችግር
የለውም፡፡ የጀማዓ ሶላት አላማው መሰባሰብ ነው በመስጅድም ይሁን በሌላ ቦታ በሚል
የአንዳንድ ዑለሞች ንግግር መታለል የለብንም፡፡ እነዚህ ዑለሞች ሙስሊሞች በቤት
ውስጥ በጀመዓ ከሰገዱ ዋጅባቸውን አወረዱ ይላሉ፡፡ ነገር ግን ትክክለኛው ሐሳብ
በጀማዓ መስጅድ ውስጥ ነው መስገድ ያለባቸው፡፡
ረሡል ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-
‫ ثم أنطلق برجال معهم‬،‫"لقد هممت أن آمر بالصالة فتقام ثم آمر رجال فيصلي بالناس‬
"‫حزم من حطب إلى قوم ال يشهدون الصالة فأحرق عليهم بيوتهم بالنار‬
“አንድ ሰው እንዲያሰግድ በማዘዝ ሶላት እንድትቆምና ከዚያም እንጨት ከያዙ ሰዎች ጋር
ሆኘ ሶላት ወደማይገኙ ሰዎች በመሄድ ቤቶቻቸውን ለማቃጠል በእርግጥ አሰብኩ፡፡” ቡኻሪ፡
ሙስሊም፡

ስለዚህ እነዚህ በአንድ ቦታ የሚኖሩ ህብረተሰቦች መስጅዱ ሩቅ ሆኖ የሚቸገሩ


ካልሆነ በቀር መስጅድ ሄደው በጀማዓ ነው መስገድ ያለባቸው፡፡
“በቴሌቪዥን በሚሰራጭ ሶላት መስገድ ይቻላል?”
ጥያቄ፡- ኢማሙን ሳይመለከት በቴሌቪዥን ወይም በሬዲዮ በሚተላለፍ ሶላት መከተል
ይበቃል? በተለይም ለሴቶች?
85/99
መልስ፡- በሬዲዮ ወይም በቴሌቪዥን አማካኝነት በሚተላለፍ ሶላት ኢማምን መከተልና
መስገድ አይበቃም፡፡ ምክንያቱም የጀማዓ ሶላት አላማ የግድ በአንድ ቦታ ተሰባስቦና ሶፍ
ሰርቶ መሰገድ አለበት፡፡ በሬዲዮና በቴሌቪዥን በመስገድ የሚፈለገው አላማ
አልተገኘም፡፡ ይህን ብንፈቅድ ኖሮ አምስት ወቅት ሶላትንም ይሁን ጁሙዓን ሁሉም
ሰው በቤቱ ለመስገድ ያመቸው ነበር፡፡ ይህ የጀማዓን እና የጁሙዓም ሸሪዓዊ ህግ
የሚጣረስ ነው፡፡ ስለዚህ ሴቶችም ሆኑ ሌላው ሰው ከሬዲዮ ወይም ከቴሌቪዥን ጀርባ
ሆነው ሊሰግዱ አይገባም፡፡

“ከሶፉ ውጭ ብቻን መስገድ”

ጥያቄ፡- አንድ ሰው ዘግይቶ ወደመስጅድ ቢገባና ሙስሊሞቹ ያለምንም ክፍተት ሶፍ


ሰርተው እየሰገዱ ቢያገኝ ከሶፉ መካከል አንድ ሰው ጎትቶ አብሮት ይስገድ? ወይስ
ብቻውን ከሶፍ ጀርባ ቆሞ ይስገድ? ምን ይስራ?

መልስ፡- ይህ ጉዳይ ሶስት ሁኔታዎች አሉት፡፡ ዘግይቶ የመጣና ሶፉ ሞልቶ ያገኘ ሰው


አራት አማራጮች አሉት አንደኛ ከሶፍ ጀርባ ብቻውን መስገድ ፣ ሁለተኛ ከሶፍ
መካከል አንድ ሰው ጎትቶ ከእርሱ ጋር መስገድ ወይም ሶስተኛ ተቀድሞ ከኢማሙ ቀኝ
በኩል መስገድ ወይም አራተኛ ጀማዓውን ሙሉ በሙሉ መተው ነው፡፡ ከእነዚህ አራት
አማራጮች የትኛውን ይምረጥ?
አንደኛው አማራጭ፡ - ከሶፍ ጀርባ ብቻውን መስገድ
ከእነዚህ አራቱ አማራጮች ተመራጩ ብቻውን ከሶፍ ጀርባ ቆሞ ከኢማም ጋር
መስገድ ነው፡፡ ምክንያቱም ዋጅቡ በጀማዓ እና በሶፍ ውስጥ መስገዱ ነው፡፡ ሁለቱ
ዋጅቦች ናቸው፡፡ ስለዚህ የጀመዓን ደረጃ እንድታገኝ በሶፍ ውስጥ የምትገባበት ቀዳዳ
86/99
ካጣህ ብቻህን በኢማም እየተከተልክ ስገድ፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

﴾ ْ ُُ‫اسُاطا ْع‬ َّ ‫﴿فااتَّ ُقوا‬


ْ ‫اّللا اما‬
“አላህንም የቻላችሁትን ያክል ፍሩት” አት ተጋቡን፡

ለዚህ ማስረጃ የሚሆን አንዲት ሴት ከጎኗ የምትቆም ሴት ከሌለች ብቻዋን ነው ሶፍ


ሰርታ የምትቆመው፡፡ ይህች ሴት ከወንድ ጋር ሶፍ ሰርታ መቆም አትችልም፡፡ ሸሪዓው
ከልክሏታል፡፡ በመሆኑም በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ያላት አማራጭ ብቻዋን መስገድ ነው፡፡

ይህ ግለሰብ መስጅድ የመጣው በጀማዓ ሶላት ለመስገድ ነው፡፡ ነገር ግን ሶፍ


ሞልቶበታል ፣ ምንም ክፍተት የለም፡፡ በጀማዓ መስገድ ደግሞ ግዴታ ሆኖበታል፡፡ ስለዚህ
ሰው መጎተት ሳያስፈልገው ከሶፍ ጀርባ ብቻውን ይስገድ፡፡

ሁለተኛው አማራጭ፡- ከሶፍ መካከል ያለን አንድ ሰው ጎትቶ አብሮ መስገድ ነው

ሰውን መጎተት ሶስት አደጋዎች አሉት፡፡

አንደኛው አደጋ፡- የሶፍ ክፍተት መፍጠር ነው፡፡ ይህ ደግሞ በሶፍ መካከል ክፍተት ዝጉ
ከሚለው የረሡል ‫ﷺ‬ ትዕዛዝ ጋር መቃረን ነው፡፡

ሁለተኛው፡- ከፊት ያለን ሰው ስንጎትት ከበላጭ ወደተበላጭ ደረጃ ዝቅ እያደረግነው


ነው፡፡ ይህ ደግሞ አንዱ ድንበር የመተላለፊያ መንገድ ነው፡፡

ሶስተኛው፡- በሶላት ላይ ውስጥ ያለን አካል መረበሽ ነው፡፡ ይህ ሰጋጅ ሲጎተት በልቡ
ውስጥ እንቅስቃሴ ይኖራል፡፡ ይህም ድንበርና ወንጀል መፈጸም ነው፡፡
ሶስተኛው አማራጭ፡- ከኢማም ጋር መቆም ነው፡፡
87/99
ከኢማም ጎን መቆምም ተገቢ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ኢማም ከተከታዮች የግድ
መለየት አለበት፡፡ ኢማም በንግግር ፣ በተግባር ፣ አላሁ አክበር በማለት ፣ ሩኩዕ
በማድረግ በመቅደም እንደሚለየው ሁሉ በቦታም ከተከታዮች መለየት አለበት፡፡

ኢማም ከተከታዮች መቅደም የነብዩ ‫ﷺ‬ መመሪያ ነው፡፡ አንዳንድ ተከታዮች


ከኢማም ጋር ከቆሙ ኢማም ከተከታዮች የሚለይበት መለያ ተወገደ ማለት ነው፡፡

አራተኛው አማራጭ፡- ጀማዓውን መተው ነው

ይህ አመለካከት ቦታ የሚሰጠው አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሶፍ መስራት ፣ በጀማዓ


መስገድ ግዴታ ነው፡፡ ከሁለቱ አንዱ ካቃተው፡፡ አንዱን ስላቃተው ተብሎ ሌላው ይቅር
አይባልም፡፡
“ኒያውን በአንደበቱ መናገር”

ጥያቄ፡- ኒያን በአንደበት መናገር ሸሪዓዊ ብይኑ ምንድን ነው?

መልስ፡- ነብዩ ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

"‫"إنما األعمال بالنيات وإنما لكل امرئ ما نوى‬

“ስራዎች በኒያ (ይመዘናሉ) ለእያንዳንዱ ሰው (የሚመነዳው) በኒያው ነው፡፡” ቡኻሪ፡


ሙስሊም፡

የኒያ ቦታው ልብ ነው፡፡ መናገሩ አያስፈልግም፡፡ አንተ ውዱእ ለማድረግ ስትቆም


እየነያህ ነው፡፡ አንድ ዓቅለኛ የሆነ ሰው ሳይገደድ ይህን ተግባር ለመስራት ሲዘጋጅ ነይቶ
ነው፡፡ በዚህ ምክንያት አንዳንድ የእውቀት ባለቤቶች አላህ አንድን ስራ ያለኒያ ስሩት
ብሎ ቢያስገድደን ኖሮ በማይቻል ነገር ማስገደድ ይሆን ነበር ይላሉ፡፡

ከነብዩም ‫ ﷺ‬ይሁን ከሶሃቦች ኒያቸውን በአንደበታቸው ነው የተናገሩት የሚል አንድም


88/99
የመጣ ማስረጃ የለም፡፡ ኒያቸውን በድምጽ በማሰማት ሲናገሩ የምትሰሟቸው ጃሂሎችን
ነው፡፡ ወይም ኒያችንን በአንደበታችን ከተናገርን ከልባችን ጋር ይስማማል ብለው
የተናገሩ ዓሊሞችን በመከተል ነው፡፡

ለዚህ የምንሰጣቸው መልስ ይህ ንግግራችሁ ትክክል አይደለም፡፡ ይህ ጉዳይ ሸሪዓዊ


ቢሆን ኖሮ ረሡል ‫ ﷺ‬በንግግራቸው ወይም በተግባራቸው ለህዝባቸው ያብራሩት ነበር፡፡

“ሰጋጁ በሚቆምበት ጊዜ እጆችን ልብ በሚገኝበት የደረት ክፍል ላይ ማስቀመጥ”

ጥያቄ፡- ከግራ ደረት ላይ ወይም ቀልብ ከሚገኝበት ቦታ ላይ ቀኝ እጅን ማኖር ሸሪዓዊ


ፍርዱ ምንድን ነው? እጆችን ከእምብርት በታች ማኖር ብይኑ ምንድን ነው? በእጅ
አቀማመጥ ዙሪያ በወንድና በሴት መካከል ልዩነት ይኖር ይሆን?

መልስ፡- ቀኝን እጅ ከግራ እጅ ላይ ማኖር ሱና ነው፡፡

መረጃ የሚሆነው ሰህል ብን ሰእድ 4 ያወራው የሚከተለው ሐዲስ ነው፡-

"‫"كان الناس يؤمرون أن يضع الرجل يده اليمنى على ذراعه اليسرى في الصالة‬

“ቀኝ እጁን ከግራ ክንዱ ላይ በሶላት ውስጥ በማኖር ላይ ሰዎች ይታዘዙ ነበር፡፡” ቡኻሪ፡

ወደትክክለኛው የቀረበው ንግግር እጅን ደረት ላይ ማኖር ነው፡፡ ማሰረጃው ዋኢል


ብን ሁጅር 4 ያስተላለፈው ሐዲስ ነው፡፡

"‫"أن النبي صلى هللا عليه وسلم كان يضع يده اليمنى على اليسرى على صدره‬

“ነብዩ ‫ ﷺ‬ደረት ላይ ቀኝ እጃቸውን ከግራ እጃቸው ላይ ያኖሩ ነበር፡፡” አህመድ፡ አቡዳውድ፡

ይህ ሐዲስ የተወሰነ ድክመት ቢኖረውም ከሌሎች ሐዲሶች በትክክለኛነቱ የቀረበ ነው፡፡


89/99
በግራ በኩል ልብ ከሚገኝበት ቦታ እጅን ማኖር የሚለው ቢድዓና መሰረት የሌለው ነው፡፡

ከእምብርት ስር ማኖር የሚለው ደግሞ ከዓልይ 4 በኩል የተወራ ደካማ ወሬ ነው፡፡


በመሆኑም ዋኢል ብን ሁጅር 4 ያስተላለፈው ሀዲስ ከሌሎቹ ሁሉ ጠንካራው ነው፡፡

በዚህ ብይን ላይ በሴትም ይሁን በወንድ ምንም አይነት ልዩነት የለም፡፡ ምክንያቱም
ልዩነትን የሚገልጽ ነገር ከሌለ ሸሪዓዊ ብይንን በተመለከተ መሰረቱ በወንድና በሴት
መካከል ምንም አይነት ልዩነት አለመኖሩ ነው፡፡ እኔም በዚህ ዙሪያ በወንድና በሴት
መካከል ልዩነትን የሚያሳይ ማስረጃ እስካሁን የማውቀው የለኝም፡፡
“ጮክ ብሎ ቢስሚላህ ማለት”
ጥያቄ፡ - ቢስሚላህን ከፍ አድርጎ ማለት ሸሪዓዊ ብይኑ ምንድን ነው?

መልስ፡- ቢስሚላህን አስመልክቶ የፋቲሃ አካል ባለመሆኗ አመዛኙ ቢስሚላህን ከፍ


አለማድረግ ነው፡፡ ሱናውም ድምጽን ቀስ ማድረግ ነው፡፡ ነገር ግን አልፎ አልፎ ጮክ
ቢል ችግር የለውም፡፡ እንዴውም ነብዩ ‫ ﷺ‬ጮክ ብለው ቀርተዋል የሚልን ሙስተድረክ
ላይ የተዘገበ ሐዲስ ማስረጃ በማድረግ አንዳንድ ጊዜ ቢስሚላህን ጮክ አድርጎ ማለት
መልካም ነው የሚሉ የዒልም ባለቤቶች አሉ፡፡

ይሁን እንጅ ሙስሊም አህመድ እና አቡዳውድ በዘገቡት ትክክለኛ ሐዲስ ረሡል


‫ﷺ‬ እንደማይጮሁ ነው የሚያስረዳው፡፡
“ኢያከነዕ ቡዱ ወኢያከ ነስተዒን” ሲቀራ “ኢስተአና ቢላህ” የሚለውን ቃል ማለት
ጥያቄ፡- አንዳንድ ተከታዮች “ኢያከነዕቡዱ ወኢያከነስተዒን” የሚለው የቁርኣን
አንቀጽ ሲቀራ “ኢስተአና ቢላህ” (በአላህ ታግዘናል” የሚሉ ሰዎች አሉ፡፡ የዚህ
ሸሪዓዊ ብይኑ ምንድ ነው
90/99
መልስ፡ - ኢማሙ “ኢያከነዕቡዱ ወኢያከነስተዒን” በሚልበት ጊዜ ተከታዮች ዝም
ብለው ማድመጥ ነው ያለባቸው፡፡ ኢማሙ ፋቲሃን ቀርቶ ሲጨርስ ኢማሙም
ተከታዮም አሚን ይላሉ፡፡ ይህ ኢማሙም ተከታዩም “አሚን” ማለታቸው ኢማሙ
ፋቲሃን በሚቀራበት መካከል ሰዎች ከሚሉት ነገር ሁሉ የሚያብቃቃ ነው፡፡

“ረበና ወለከል ሀምድ” ከሚለው ቃል ላይ “ወሹክር” የሚል ቃል መጨመር

ጥያቄ፡- አንዳንድ ሰዎች “ረበና ወለከል ሀምድ” ካለው ቃል በኋላ “ወሹክር”


የሚለውን ቃል ይጨምራሉ፡፡ ሸሪዓዊ ብይኑ ምንድን ነው?

መልስ፡- በመጣው ዚክር ብቻ መወሰን በላጭ ለመሆኑ ምንም የሚያጠራጥር ነገር


የለውም፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው ከሩኩዕ በሚነሳ ጊዜ “ረበና ወለከል ሀምድ” የሚለውን
ዚክር ይበል፡፡ የሀዲስ ማስረጃ ስለሌለው “ወሹክር” የሚል መጨመር የለበትም፡፡

“ረበና ወለከል ሀምድ” የሚለውን ዚክር አስመልክቶ አራት አይነት አባባሎች


በሐዲስ መጠዋል፡፡ እነርሱም የሚከተሉት ናቸው፡-

1. ረበና ወለከል ሀምድ


2. ረበና ለከል ሀምድ
3. አሏሁመ ረበና ለከል ሀምድ
4. አሏሁመ ረበና ወለከል ሀምድ
እነዚህን አባባሎ በአንድ ላይ ሳይሆን አንዱን በአንድ ሶላት ሌላውን በሌላው ሶላት
እየቀያየርን ማለት እንችላለን፡፡
“ጀርባን ለጥጦ ሱጁድ ማድረግ”
ጥያቄ፡- ጀርባን ለጥጦ ሱጁድ ማድረግ ሸሪዓዊ ብይኑ ምንድን ነው?
91/99
መልስ፡- ጀርባን ለጥጦ ሱጁድ ማድረግ የሱና ተቃራኒ ነው፡፡ ከነብዩ ‫ﷺ‬ የሶላት
አሰጋገድ ሱጁድ ሲያደርጉ ጀርባቸውን ይለጥጡ ነበር የሚል አልተገኘም፡፡
ጀርባ የሚለጠጠው በሩኩዕ ጊዜ ነው፡፡ በሱጁድ ጊዜ ግን መለጠጥ ሳይሆን ሆድን
ከጭን ጋር እንዳይገናኝ ማንሳት ወይም ከፍ ማድረግ ነው፡፡
“በሶላት ውስጥ ሆኖ ሁለት አይኖችን መጨፈን”
ጥያቄ፡- በሶላት ውስጥ ሆኖ ሁለት አይኖችን መጨፈን ሸሪዓዊ ብይኑ ምንድን ነው?
መልስ፡- ያለምክንያት በሶላት ውስጥ ሁለት አይኖችን መጨፈን የተጠላ ተግባር ነው፡፡
ምክንያቱም ከነብዩ ‫ﷺ‬ ስራ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡ ምክንያት ያለው ሰው ግን መጨፈን
ይችላል፡፡ ለምሳሌ፡- ከግድግዳው ወይም ከምንጣፉ ላይ ከሶላት የሚያዘናጉ ውበት
ያላቸው ነገሮች ካሉ ወይም ፊት ለፊቱ ጠንካራ መብራት አይኑን የሚወጋው ከሆነ
መጨፈኑ ችግር የለውም፡፡ ተጨማሪ ማብራሪያ የፈለገ ሰው “ዛዱል መዓድ”
የሚባለው የኢብን አልቀይምን i መጽሐፍ ማንበብ ይችላል፡፡
“በተራዊህ ሶላትም ይሁን በሌላ ተከታዮች ኪታብ መያዛቸው እንዴት ይታያል?”
ጥያቄ፡ - ኢማሙን ለመከታተል በሚል በተራዊህ ሶላት ከኢማሙ ጀርባ ያሉ ተከታዮች
ኪታብ መያዛቸው በሸሪዓ እንዴት ይታያል?
መልስ፡- ለዚህ አላማ ተብሎ ኪታብ መያዙ ከብዙ ምክንያቶች አንጻር የሱና ተቃራኒ
ነው፡፡
የመጀመሪያው፡ በሚቆምበት ጊዜ ቀኝ እጁን ከግራው ላይ ማድረግ አይችልም፡፡ በዚህም
ሱናውን መተግበር አይችልም፡፡
ሁለተኛው፡ አስፈላጊ ላልሆነ እንቅስቃሴ ይዳረጋል፡፡ መጽሀፍ መግለጥ፣ መዝጋት፣
ማኖር፣ በኪሱ መክተትና የመሳሰሉ አላስፈላጊ እንቅስቃሴዎችን ያደርጋል፡፡
92/99
ሶስተኛው፡ በእርሱ እንቅስቃሴ ሰዎች ይረበሻሉ፡፡
አራተኛው፡ በሚሰግድ ጊዜ የሱጁድ ቦታን መመልከት አይችልም፡፡
አምስተኛው፡ በአጠቃላይ ልቦናው አላህን ከመፍራት ይዘነጋል፡፡
“በሶላት መካከል ጣቶችን ማንቀጫቀጭ”
ጥያቄ ፡ ረስቶ በሶላት መካከል ጣቶችን ማንቀጫቀጭ ሶላቱን ያበላሽበታል?
መልስ፡ ረስቶ እጣት ማንቀጫቀጭ ሶላትን አያበላሽም፡፡ ነገር ግን ጣትን ማንቀጫቀጭ
ጨዋታ ከመጫዎት የሚቆጠርና ሰጋጆችንም የሚረብሽ ተግባር ነው፡፡ ብቻውን እየሰገደ
ከሚያደርገው ደግሞ በጀማዓ ሶላት ውስጥ ይህን መፈጸሙ የበለጠ ጉዳቱ ከፍ ያለ
ይሆናል፡፡
በሶላት ውስጥ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በአምስት ይከፈላሉ፡፡ ዋጅብ የሆነ
እንቅስቃሴ ፣ ሱና የሆነ እንቅስቃሴ ፣ ከረሀ (የተጠላ) የሆነ እንቅስቃሴ ፣ ሀራም የሆነ
እንቅስቀሴ እና የተፈቀደ የሆነ እንቅስቃሴ ናቸው፡፡
1. ዋጅብ የሆነ እንቅስቃሴ፡ በሶላት ውስጥ ያሉ ዋጅቦች የተመሰረቱበት ነው፡፡
ለምሳሌ፡- አንድ ሰው እየሰገደ ከጥምጣሙ ላይ ነጃሳ መኖሩን ቢያስታውስ እና
ጥምጣሙን ለማውለቅ ቢንቀሳቀስ ይህ እንቅስቃሴ ዋጅብ ነው፡፡ ለዚህ ማስረጃ
የሚሆነው የነብዩ ሐዲስ ነው፡-ረሡል ‫ﷺ‬ ሶላት እየሰገዱ ጅብሪል d መጣ፡፡
ከሚሰግዱበት ጫማ ላይ ነጃሳ እንዳለ ነገራቸው፡፡ ሁለቱንም ጫማ ወዲያውኑ
አወለቁና ሶላታቸውን ቀጠሉ፡፡ ይህ ጫማን ለማውለቅ ያደረጉት እንቅስቃሴ ግዴታ
እንቅስቃሴ ነው ማለት ነው፡፡ በሶላት ውስጥ ይህ እንቅስቃሴ ግዴታ የሚሆነው
ዋጅብን ለመስራት ወይም ሀራምን ለመተው መሆን አለበት፡፡
2. ሱና የሆነ እንቅስቃሴ፡ ይህ ደግሞ ሶላት የሚሟላበት እንቅስቃሴ ነው፡፡ ለምሳሌ፡ -
93/99
በሶፍ ውስጥ ክፍተት ካለና ይህን ክፍተት ለመሙላት የሚደረገው እንቅስቃሴ ነው፡፡
3. የተጠላ እንቅስቃሴ ፡ ሶላትን ከማሟላት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌለው
እንቅስቃሴ ነው፡፡
4. ሀራም የሆነ እንቅስቃሴ ፡ ተከታታይ የሆነ እንቅስቃሴ ማድረግ ነው፡፡ ለምሳሌ፡
ሲቆም ፣ ሩኩእ ሲያደርግ ፣ ሱጁድ ሲያደርግ ፣ ሲቀመጥ በአጠቃላይ
እስከሚያሰላምት ድረስ መጫዎት፡፡ ይህ እንቅስቀሴ ሀራም ነው ምክንቱም ሶላቱን
ያበላሽበታል፡፡
5. የተፈቀደ እንቅስቃሴ፡ ከላይ ከጠቀስናቸው ውጭ ያሉ እንቅስቃሴዎች ናቸው፡፡
ሰውነቱን የሆነ ነገር ቢያሳክከው ማከክ ፣ ጥምጣሙ ፊቱን ቢሸፍነውና ጥምጣሙን
ገለጥ ቢያደርግ ይህ እንቅስቃሴው የሚበቃ ነው፡፡ ለምሳሌ እየሰገደ ከውጭ ያለ ሰው
መግባት ቢፈልግ በእጁ ጥቆማ አደረገ ይህ የሚበቃ እንቅስቃሴ ነው፡፡
ጥያቄ፡- ኢማሙ ተሸሁድ ላይ እያለ አንድ ሰው ለመስገድ ቢመጣ በቀጥታ
ወደተሸሁድ ይግባ ወይስ ሌላ አዲስ ጀማዓ ይጠብቅ?
መልስ፡ - የጀማዓ ሶላት በረከዓ እንጅ አትገኝም በሚለው የዑለሞች ንግግር መሰረት
ሌላ ጀማዓ አገኛለሁ ብሎ ተስፋ የሚያደርግ ከሆነ አይግባ፡፡
ረሱል ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ንግግር ተናግረዋል፡-
"‫"من أدرك ركعة من الصالة فقد أدرك الصالة‬
“ከሶላቱ አንድ ረከዓ ያገኘ በእርግጥ ሶላትን አገኘ፡፡” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

ጁሙዓም ያለአንድ ረከዓ እንደማይገኝ ሁሉ የጀማዓ ሶላትም በአንድ ረከዓ ካልሆነ


አይገኝም፡፡ ኢማሙን በመጨረሻው ተሸሁድ ካገኘው ጀማዓን አገኘ አይባልም፡፡ ከጀማዓ
ጋር እስኪሰግድ ይጠብቅ፡፡ ጀማዓን ተስፋ የማያደርግ ከሆነ ግን ብቻውን ከሚሰግድ
94/99
ከኢማም ጋር ገብቶ መስገዱ በላጭ ነው፡፡
“ተከታዩ ኢማሙ ከሱጁድ እስኪነሳ ድረስ መጠበቅ”
ጥያቄ፡ ተከታዩ ኢማሙ ሱጁድ ላይ ሆኖ አገኘው ይጠብቀው ወይስ ወደሱጁድ ይግባ?
መልስ፡- በላጩ ከኢማም ጋር መግባቱ ነው፡፡ በማንኛውም ባህሪ ላይ ቢያገኘው
መጠበቅ የለበትም፡፡
የአላህ መልእክተኛ ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
" ‫"فما أدركتم فصلوا‬
“ካገኛችሁት ስገዱ” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

“ኢማምን መቅደም”
ጥያቄ፡- ኢማምን መቅደም ሸሪዓዊ ብይኑ ምንድን ነው?
መልስ፡- ኢማምን መቅደም ሀራም ነው፡፡
ረሡል ‫ ﷺ‬የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-
‫ أو يجعل‬،‫"أما يخشى الذي يرفع رأسه قبل اإلمام أن يحول هللا رأسه رأس حمار‬
"‫صورته صورة حمار‬
“ከኢማም በፊት ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሰው አላህ ራሱን የአህያ ራስ አድርጎ እንዳያዞረው
፤ ወይም ቅርጹን የአህያ ቅርጽ እንዳያደርገው አይፈራምን?” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

ሀራምን በመተግበር ወይም ዋጅብን በመተወ ካልሆነ በቀር የአላህ መልእክተኛ ‫ﷺ‬

አያስጠነቅቁም፡፡ በመሆኑም ይህ ኢማምን ለሚቀድሙ ሰዎች የተሰጣቸው


ማስጠንቀቂያ ነው፡፡
ረሡል ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-

،‫ وإذا ركع فاركعوا‬،‫ وال تكبروا حتى يكبر‬،‫ فإذا كبر فكبروا‬،‫"إنما جعل اإلمام ليؤتم به‬
95/99

"‫وال تركعوا حتى يركع‬

“ኢማም የተደረገው ሊከተሉት ነው፡፡ አሏሁ አክበር ያለ ጊዜ አሏሁ አክበር በሉ ፤ አሏሁ


አክበር እስከሚል ድረስ አሏሁ አክበር አትበሉ ፤ እርሱ ሩኩእ እስኪያደርግ ድረስ ሩኩእ
አታድርጉ፡፡” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

ኢማምን የሚከተል ሰው አራት ባህሪያት አሉት፡፡

ሙሳበቃ, ሙዋፈቃ, ሙታበዓ, ተኸሉፍ


1. ሙሳበቃ፡ ማለት ከኢማሙ ቀድሞ መጀመር ነው፡፡ ይህ ሀራም የሆነ ተግባር ነው፡፡
በተለይም ተክቢረተል ኢህራም ላይ ከሆነ ሶላቱ እንደሶላት አይቆጠርም፡፡
በመሆኑም ይህን ተግባር የፈጸመ ሰው ሶላቱን በአዲስ መልኩ መጀመር አለበት፡፡
2. ሙዋፈቃ፡ ማለት ደግሞ ከኢማሙ ጋር እኩል መስራት ማለት ነው፡፡ ሩኩዕም ፣
ሱጁድም ሲያደርግ ከኢማሙ ጋር እኩል ሊፈጽም ነው፡፡ ግልጽ የሆነው መረጃ
የሚጠቁመው ይህ ተግባሩ ሀራም እንደሆነ ነው፡፡
ረሡል ‫ﷺ‬ የሚተከለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-
“እርሱ ሩኩዕ እስከሚያደርግ ሩኩዕ አታድርጉ፡፡” አህመድ፡ አቡዳውድ፡

አንዳንድ ዑለሞች ግን ይህ በተክቢረተል ኢህራም ካልሆነ ይህ ተግባሩ የተጠላ


ተግባር እንጅ ሀራም አይደለም ብለዋል፡፡
3. ሙታበዓ፡ ማለት ደግሞ ኢማም የሚፈጽመውን ተግባር እየተከተለ መፈጸም
ማለት ነው፡፡ ይህ ሸሪዓዊ አፈጻጸም እና ትክክለኛው ተግባር ነው፡፡
4. ተኸሉፍ፡ ማለት ደግሞ ኢማሙ ከፈጸመ በኋላ በጣም እየዘገየ መፈጸም ነው፡፡ ይህ
ተግባር ኢማምን ከመከተል የሚያወጣ የሱና ተቃራኒ የሆነ ተግባር ነው፡፡
96/99
“የጁሙዓ ሶላት”
“የጁሙዓ ሶላት ከቤት መስገድ”
ጥያቄ፡ - የኢማሙን ድምጽ የሚሰማ ከሆነ ጁሙዓን ከቤቱ መስገድ ይችላል?
መልስ፡- የጁሙዓን ሶላት በመስጂድ ውስጥ ከሙስሊሞች ጋር እንጅ ከቤት መሰገድ
አይቻልም፡፡ ነገር ግን መስጂዱ ከሞላና ሶፉ ተያይዞ ከሄደ መንገድ ላይ መስገድ
ይችላል፡፡ ከቤት ወይም ከሱቁ መስገድ ግን አይበቃለትም፡፡ ምክንያቱም የጁሙዓ አላማ
ሙስሊሞች በአንድ ላይ ተገናኝተው አንድ ማህበረሰብ እንዲሆኑ ፣ እርስ በርሳቸው
እንዲተሳሰሩ ፣ እንዲተዛዘኑ ፣ ጃሂሉ ከዓሊሙ እንዲማር ነው፡፡ ሶላተል ጀማዓን
ትታችሁ ሁላችሁም በሚሰማው ስፒከር ባላችሁበት ቦታ ስገዱ ብለን ለሁሉም በር
የምንከፍት ከሆነ መስጂድ መገንባቱ ሙስሊሞች በአንድ ላይ መሰብሰባቸው ምን
ትርጉም አለው፡፡ ይህ ደግሞ ጁሙዓ እንዲቀር ፣ ሶላተል ጀማዓ እንዲቀር በር
ይከፍታል፡፡
“ከጁሙዓ በኋላ የዙሁርን ሶላት መስገድ”
ጥያቄ፡- ጁሙዓን የሰገደ ሰው ዙሁርን መስገድ አለበት?
መልስ፡- ጁሙዓን ሰግዶ ዙሁርን መስገድ ቢድዓ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም በቁርኣንም
ይሁን በሐዲስ እንዲህ አይነት ተግባር አልመጣም፡፡ በመሆኑም እንዲህ አይነቱን ተግባር
መከልከል ግዴታ ነው፡፡
ጁሙዓ የሚሰገደው በበርካታ ቦታዎች እንኳ ቢሆን ከጁሙዓ ሶላት በኋላ ዙሁር
መስገድ አይቻልም፡፡ ይህን ተግባር መፈጸም ቢድዓና ሙንከር ነው፡፡ በአንድ ወቅት ላይ
አንድ ሶላትን እንጅ ተጨማሪ ሶላት ግዴታ አላደረገም፡፡ እርሱም የጁሙዓ ሶላት ነው፡፡
እርሱንም ፈጽሟል፡፡ አንዳንዶች ምክንያት የሚያደርጉት በብዙ ቦታ ጁሙዓን መስገድ
97/99
አይበቃም፡፡ በበርካታ ቦታ ጁሙዓ ከተሰገደ ዙሁርን ደግሞ መስገድ አለበት ይላሉ፡፡
ለዚህ የምንሰጣቸው መልስ በቅድሚያ ይህን ለማለት መረጃችሁ ምንድን ነው?
በሱና መረጃ የተመሰረተ ነው ወይስ በግል አስተያየት? አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በበርካታ
ቦታዎች ጁሙዓን መስገድ ይቻላል፡፡ ሁሉም ቦታ የሚሰገደው ጁሙዓ ትክክል ነው፡፡
አላህ በተከበረው ቁርዓናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
﴾ ْ ُُ‫اسُاطا ْع‬ َّ ‫﴿فااتَّ ُقوا‬
ْ ‫اّللا اما‬
“አላህንም በቻላችሁት ያክል ፍሩት” አት ተጋቡን፡

እርግጥ ነው ያለምንም ምክንያት ብዙ ቦታዎች ላይ ጁሙዓ መመስረት የሱና


ተቃራኒ መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ ነብዩ ‫ﷺ‬ እና ሶሃቦች ከነበሩበት ጋር
የሚቃረን ተግባር ነው፡፡
ሸሪዓዊ የሆነው መሰባሰብ፡ በየቀኑ መሰባሰብ የአምስት ወቅት ሶላቶች ስብስብ
ነው፡፡ ሳምንታዊ መሰባሰብ የጁሙዓ ቀን ሲሆን አመታዊ መሰባሰብ ደግሞ በዒድ
አልአድሃ ወይም በዒድ አልፊጥር መሰባሰብ ነው፡፡ አስቸጋሪና ሸሪዓዊ ምክንያቶች
ካልኖሩ በቀር የዒድ መሰባሰቢያዎች ልክ እንደ ጁሙዓ ሶላት በአንድ ቦታ ሊሆን
ይገባል፡፡
“የጁሙዓ ቀን ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ እጅን ማንሳት”
ጥያቄ፡- የጁሙዓ ቀን ኢማም ኹጥባ እያደረገ እጅን ማንሳት ሸሪዓዊ ብይኑ ምንድን
ነው?
መልስ፡- ከኢስቲስቃእ ዱዓ በቀር በጁሙዓ ቀን ኢማም ኹጥባ እያደረገ እጅን ማንሳት
ህጋዊ አይደለም፡፡ ቢሽር ብን መርዋን በጁሙዓ ቀን ኹጥባ ላይ እጁን ሲያነሳ ሶሃቦች
ተቃውመውታል፡፡ ሙስሊም፡
98/99
“በጁሙዓ ቀን ሶፍ እየረጋገጡ መግባት”
ጥያቄ፡ - የጁሙዓ ቀን ሶፎችን መረጋገጥ ሸሪዓዊ ብይኑ ምንድን ነው?
መልስ፡-ሰዎችን እየጠቀጠቁ የሚያልፉ ሰዎችን ያለምንም ንግግር በመጠቆም
ማስቀመጥ ግዴታ ነው፡፡ ነገር ግን ይህን ሀላፊነት መውሰድ ያለበት ኢማሙ ነው፡፡
ማስረጃችን የሚከተለው ሐዲስ ነው፡፡ ረሡል ‫ﷺ‬ ጁሙዓ ላይ ኹጥባ እያደረጉ
የሰዎችን ጫንቃ እየጠቀጠቀ የሚገባ ሰው ተመለከቱ፡፡ ከዚያም የሚከተለውን
ተናገሩ፡-
"‫"اجلس فقد آذيت‬
“ተቀመጥ በእርግጥ (ሰዎችን) አስቸገርክ” አህመድ፡ ነሳኢይ፡ አቡዳውድ፡

“ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ሰላም ማለትና በእርሱ ላይ መልስ መስጠት”


ጥያቄ፡ ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ሰላምታ መስጠት በእርሱ ላይ መመለስ ሸሪዓዊ ብይኑ
ምንድን ነው?
መልስ፡- ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ መስጊድ የገባ ሰው ቀለል አድርጎ ሁለት ረከዓ
ይስገድ፡፡ በማንም ሰው ላይ ሰላም ሳይል ይቀመጥ፡፡ በዚህ ሁኔታ ላይ ሰላምታ መስጠት
ሀራም ነው፡፡ ምክንያቱም ነብዩ ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
"‫"إذا قلت لصاحبك أنصت يوم الجمعة واإلمام يخطب فقد لغوت‬
“የጁሙአ ቀን ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ለጓደኛህ ዝም በል ካልህ በርግጥ ጥቅም የሌለው
ንግግር ተናገርህ” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

"‫ "من مس الحصى فقد لغا‬:‫وكذلك قال‬


በተጨማሪ የሚከተለውን ተናግረዋል-
“ጠጠር የነካ በርግጥ የማይጠቅም ተግባር ፈፀመ” ኢብኑ ማጀህ፡
99/99
በጁሙዓ የማይጠቅም ንግግር መናገር ምንዳን ሊያሳጣ ይችላል፡፡
ረሡል ‫ ﷺ‬የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-
"‫"من لغى فال جمعة له‬
“የማይጠቅም ንግግር የተናገረ ለእርሱ ጁሙዓ የለውም” አህመድ፡ አቡዳውድ፡

በአንተ ላይ ሰላምታ የሚሰጥ ሰው ካለ “ወአለይከ ሰላም” አትበል፡፡ በላጩ ሰላም


አለማለቱ ከመሆኑ ጋር ከንግግር ውጭ በእጅ መልስ መስጠቱ ችግር የለውም፡፡
አንዳንድ የእውቀት ባለቤቶች ሰላምታ ቢመልስ ችግር የለውም የሚሉ አሉ፡፡ ሰላምታ
መመለስም ይሁን ኹጥባን ማዳመጡ ዋጅብ ቢሆኑም ፣ ኹጥባ የማድመጥ ዋጅብ
መቀደም አለበት፡፡

‫وصلى الله على نبينا محمد وعلى آله وصحبه وسلم‬


ባህር ዳር በሚገኙ የአህለሱና
መሻይኾች የተቀሩ ጠቃሚ ኪታቦች፣ ከሀገር
ውስጥና ከውጭ በሚመጡ መሻይኾች የተሰጡ
ኮርሶች፣ ሙሓዶራዎች፣ የጁመዓ ኹጥባ፣
በትክክለኛ ማስረጃ የተደገፉ የተለያዩ ኢስላማዊ
መጣጥፎችን የሚከተለውን የቴሌግራም ሊንክ
ጆይን በማድረግ መከታተል ይችላሉ
http://t.me/alateriqilhaq

You might also like