የሰለፎች ጎዳና ለሙስሊሙ ማህበረሰብ አስፈላጊነቱ

You might also like

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 45

‫حاجة األمة للمنهج السلفي‬

‫‪የሰለፎች ጎዳና‬‬
‫‪ለሙስሊሙ ማህበረሰብ‬‬
‫‪አስፈላጊነቱ‬‬

‫إعداد‪ :‬الشيخ صالح بن فوزان الفوزان‬


‫‪ትርጉም፡ አቡ’ዓብዲልዓዚዝ/ ዩሱፍ አህመድ‬‬
1/43

ምስጋና ለዓለማት ጌታ የተገባው ነው፡፡ ውዳሴና ሰላምታ በነብዩ ሙሐመድ ፣


በቤተሰቦቻቸው እና በአጠቃላይ በባልደረቦቻቸው ላይ ይስፈን፡፡

ከዚህ በመቀጠል፡

“የሰለፎች ጎዳና ለሙስሊሙ ማህበረሰብ አስፈላጊነቱ” የሚለው ርዕስ ፣ ወሳኝና


አንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡፡ ሰለፉነ ሷሊህ (ቀደምት ደጋጎች) የሚባሉት ለዚህ ኡመት
(ማህበረሰብ) የመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ሰዎች ናቸው፡፡ እነርሱም ሙሐጅርና
አንሷር በመባል የሚጠሩት የአላህ መልእክተኛ ‫ﷺ‬ ባልደረቦች (ሶሃቦች) ናቸው፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-


ِ ٍ ِ َّ ِ ‫اج ِرين واأل‬
ِ ِ َّ ‫﴿ َو‬
‫َع َّد‬
َ ‫ضواْ َعْنهُ َوأ‬ ‫وهم ِبِِ ْح َسان َّرض َي ه‬
ُ ‫اّللُ َعْن ُه ْم َوَر‬ ُ ُ‫ين اتَّبَ ع‬ َ َ َ ‫السابُِقو َن األ ََّولُو َن م َن الْ ُم َه‬
َ ‫َنصار َوالذ‬
﴾‫ك الْ َف ْوُز الْ َع ِظ ُيم‬ ِ ِ ‫َّات ََت ِري ََتت ها األ َْْنَار خالِ ِد‬
ٍ
َ ‫ين ف َيها أَبَ ًدا َذل‬
َ َ ُ َ َْ ْ ‫ََلُْم َجن‬
“ከስደተኞቹና ከረዳቶቹም ሲሆኑ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች እነዚያም በበጎ
ስራ የተከተሏቸው አላህ ከእነሱ ወዷል ከእርሱም ወደዋል፡፡ በስሮቻቸውም
ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ለዘላለም ነዋሪዎች ሲሆኑ
ለእነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ ይህ ታላቅ ዕድል ነው፡፡” አት ተውባህ፡

َِّ ‫ض ًًل ِمن‬ ِِ ِِ ِ ِ ِ َّ ‫اج ِر‬


ِ ِ
َ‫اّلل‬
َّ ‫نصُرو َن‬ ْ ‫اّلل َوِر‬
ُ َ‫ض َو ًاًن َوي‬ َ ‫ُخ ِر ُجوا من دايره ْم َوأ َْم َواَل ْم يَْب تَ غُو َن فَ ْ ه‬
ْ ‫ين أ‬
َ ‫ين الذ‬ َ ‫﴿ل ْل ُف َقَراء الْ ُم َه‬
﴾‫الص ِادقُو َن‬ َ ِ‫َوَر ُسولَهُ أ ُْولَئ‬
َّ ‫ك ُه ُم‬

“ለእነዚያ የአላህን ችሮታና ውዴታውን የሚፈልጉ ፣ አላህንና መልእክተኛውንም


2/43
የሚረዱ ሆነው ከአገሮቻቸውና ከገንዘቦቻቸው ለተወጡት ስደተኞች ድሆች
(ይስሰጣል)፡፡ እነዚያ እነርሱ እውነተኞቹ ናቸው፡፡” አል ሐሽር፡

ይህ ስለሙሐጅሮች አላህ የተናገረው ሲሆን ስለአንሷሮች የተናገረው ደግሞ


የሚከተለው ነው፡-

‫اجةً ِهمَّا أُوتُوا‬ ِ ِ


ُ ‫اجَر إِلَْي ِه ْم َوََل ََي ُدو َن ِِف‬
َ ‫ص ُدوِره ْم َح‬
ِ ِ ِ ِْ ‫﴿والَّ ِذين تَب َّوُؤوا الدَّار و‬
َ ‫اْلميَا َن من قَ ْبل ِه ْم ُُيبُّو َن َم ْن َه‬ ََ َ َ َ
﴾‫ك ُه ُم الْ ُم ْفلِ ُحو َن‬
َ ِ‫وق ُش َّح نَ ْف ِس ِه فَأ ُْولَئ‬
َ ُ‫اصةٌ َوَمن ي‬
َ ‫ص‬
ِِ ِ ِ
َ ‫َويُ ْؤثُرو َن َعلَى أَن ُفس ِه ْم َولَ ْو َكا َن ِب ْم َخ‬
“እነዚያም ከበፊታቸው አገሪቱን መኖሪያ ያደረጉት እምነትንም የለመዱት
ወደእነርሱ የተሰደዱትን ሰዎች ይወዳሉ፡፡ (ስደተኞቹ) ከተሰጡትም ነገር
በልቦቻቸው ውስጥ ቅሬታን አያገኙም፡፡ በእነርሱ ላይ ችግር ቢኖርባቸውም
በነፍሶቻቸው ላይ ሌላውን ይመርጣሉ፡፡ የነፍሱንም ንፍገት የሚጠበቅ ሰው
እነዚያ እነሱ ምኞታቸውን አግኚዎች ናቸው፡፡” አል ሐሽር፡

ከእነርሱ በኋላ ስለሚመጡት መልካም ትውልዶች ደግሞ የሚከተለውን ተናግሯል፡-


ِ َّ ِ ِ ِ ِِ ِ ِ َّ
‫ان َوََل ََْت َع ْل ِِف قُلُوبِنَا ِغ اًل‬ َ ‫﴿ َوالذ‬
ِ َ‫وًن ِِبِْْلمي‬
َ ‫ين َج ُاؤوا من بَ ْعده ْم يَ ُقولُو َن َربَّنَا ا ْغفْر لَنَا َوِْل ْخ َواننَا الذ‬
َ ‫ين َسبَ ُق‬
﴾‫وف َّرِح ٌيم‬ ِِ
َ َّ‫ين َآمنُوا َربَّنَا إِن‬
ٌ ‫ك َرُؤ‬ َ ‫لهلَّذ‬
“እነዚያም ከበኋላቸው የመጡት “ጌታችን ሆይ! ለእኛም ለእነዚያም በእምነት
ለቀደሙን ወንድሞቻችን ምህረት አድርግ ፤ በልቦቻችንም ውስጥ ለእነዚያ
ለአመኑት (ሰዎች) ጥላቻን አታድርግ፡፡ ጌታችን ሆይ! አንተ ርህሩህ አዛኝ ነህና”
ይላሉ፡፡ አል ሐሽር፡

ከዚያም ከሶሃቦች በኋላ የመጡት እና ከሶሃቦች የተማሩ የሆኑትን ታብዒዮች ፣


የታብዕዮች ተከታይ የሆኑት ምርጥ ክፍለ ዘመን ላይ የነበሩትን አስመልክቶ የአላህ
መልእክተኛ ‫ﷺ‬ እንደሚከተለው ተናግረዋል፡-
3/43
"‫ ثم الذين يلونهم‬،‫ ثم الذين يلونهم‬،‫"خيركم قرني‬

“ከእናንተ መልካማችሁ በእኔ ክፍለ ዘመን (ውስጥ የነበሩ ሰዎች) ናቸው ፤ ከዚያም
እነርሱን የሚቀጥሉት ፤ ከዚያም እነርሱን የሚቀጥሉት (ናቸው)” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

ሐዲሱን ያስተላለፈው ሶሃባ ፡ “ረሡል ‫ ﷺ‬ከእርሳቸው ክፍለ ዘመን በኋላ የተናገሩት


ሁለት ክፍለ ዘመን ይሁን ሶስት አላውቅም” በማለት ተናግሯል፡፡

ክፍለ ዘመናቸው “የተከበረ ክፍለ ዘመን” በመባል ይጠራል፡፡ ረሡል ‫ﷺ‬


በሚከተለው መልኩ ያወደሷቸውም እነርሱን ነው፡፡

“ከእናንተ መልካማችሁ በእኔ ክፍለ ዘመን (ውስጥ የነበሩ ሰዎች) ናቸው ፤ ከዚያም
እነርሱን የሚቀጥሉት ፤ ከዚያም እነርሱን የሚቀጥሉት (ናቸው)”

እነርሱ በዓቂዳቸው ፣ በስነ-ምግባራቸው ፣ በማህበራዊ ግንኙነታቸው እና


በአጠቃላይ እንቅስቃሴያቸው የሚከተሉት የቁርኣንና የሐዲስን ጎዳና በመሆኑ ፣
እንዲሁም ለረሡል ‫ﷺ‬ እና ቁርኣን ለወረደበት ዘመን ቅርብ በመሆናቸው
ለማህበረሰባችን መልካም ሞዴል ፣ ከክፍለ ዘመናቱ ሰዎች ሁሉ መልካሞቹ ሆኑ፡፡
ጎዳናቸው ከሁሉ ጎዳና በላጭ ሆነ፡፡ በዚህ ምክንያት ሙስሊሞች እነርሱ የተጓዙበትን
ጎዳና ለመከተል ፍላጎቱ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ በእነርሱ ጎዳና በትክክል ለመጓዝ ደግሞ
እውቀት ፣ ግንዛቤና ተግባር ያስፈልጋል፡፡
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
“ከስደተኞቹና ከረዳቶቹም ሲሆኑ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች እነዚያም በበጎ
ስራ የተከተሏቸው” አት ተውባህ የሚለው ቁርኣናዊ አንቀጽ በተጣራ እውቀትና
በመረጃ ላይ ተንተርሰው የተከተሏቸው ማለት ነው፡፡
4/43
እነርሱ የተጓዙበትን ጎዳና በደንብ ጠንቅቆ ካላወቀ መልካም ተከታይ አይባልም፡፡
ያለምንም እውቀት የሰለፍ ተከታይ ነኝ ማለት ብቻውን ጉዳት እንጅ ጥቅም አያስገኝም፡፡
የሰለፎችን ጎዳና የግድ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ሰለፎቹ እውቀታቸውን ከትውልድ ትውልድ
አስተላልፈዋል፡፡ ይሄው አሁንም የእነርሱ እውቀት በየመስጅዶች ፣ በየመድረሳዎች ፣
በየኮሌጆች እና በየዩኒቨርሲቲዎች እየተላለፈ ይገኛል፡፡ አማራጭ የሌለው የማወቂያ
መንገዱ ይህ ነው፡፡ ምንጩ ከቁርኣን እና ከሱና የሆነውን የሰለፎች ጎዳና ማወቅና
መገንዘብ ግን ይለናል፡፡

በዚህ ማህበረሰብ ውስጥ በርካታ ልዩነት ሊኖር እንደሚችል ረሡል ‫ﷺ‬


በሚከተለው ሐዲሳቸው ተናግረዋል፡-

‫ وتفترق أمتي على ثالث وسبعين‬،‫"إن بني إسرائيل تفرقت على ثنتين وسبعين ملة‬
‫ "ما‬: ‫ ؟ قال‬- ‫ ومن هي – يا رسول هللا‬: ‫ قالوا‬،‫ كلهم في النار إال ملة واحدة‬،‫ملة‬
‫أنا عليه وأصحابي‬

“በኒ ኢስራኢል ከሰባ ሁለት መንገድ ተከፋፈለች ፤ የእኔ ተከታዮች ደግሞ ከሰባ ሶስት
መንገድ ይከፋፈላሉ ፤ አንዷ መንገድ ስትቀር ሁሉም የእሳት ናቸው፡፡” - ማን ነች -

የአላህ መልእክተኛ ሆይ? “እኔና ሶሃቦቸ በነበርንበት (አይነት የተጓዙ) ናቸው” በማለት
ረሱል ምላሽ ሰጡ፡፡ ቲርሚዚይ፡

ይህ ረሡል ‫ﷺ‬፣ ሶሃቦች h እንዲሁም እነርሱን በመልካም የተከተሉት ሁሉ


የተጓዙበት መንገድ -የደጋግ ቀደምቶች መንገድ ነው፡፡ የቀደምት ደጋግ ባሮችን
መንገድ አጥብቆ ለመያዝ እውቀት የግድ ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም ከእሳት ነጻ ሆነን
ዘላለማዊ የሆነ የድሎት ህይዎትን የምናረጋግጥበት ጎዳና ነው፡፡
5/43

“አንዷ መንገድ ስትቀር ሁሉም የእሳት ናቸው፡፡” ይህች ብቸኛና አማራጭ የሌላት አንድ

መንገድ “ፊርቀቱ ናጅያ” በመባል ትጠራለች፡፡ ይህች መንገድ አህለሱና ወልጀማዓዎች


የሚጓዙባት መንገድ ነች፡፡ ህዝቦች በተለያዩ አንጃዎች ፣ አመለካከቶች እና
መስመሮች ሲጓዙ በቀደምት ደጋግ የአላህ ባሮች መንገድ የምትጸናው ፤ ጌታዋን
እስከምትገናኝ ድረስ የሰለፎችን ጎዳና አጥብቃ በትዕግስት የምትቀጥለው “ፊርቀቱ
ናጅያ” ብቻ ነች፡፡

ነብዩ ‫ﷺ‬ በመጨረሻ የህይዎት ዘመናቸው ጥልቅ የሆነ ፣ በሶሃቦች ላይ ተጽዕኖ


ያሳደረ ፣ አይኖችን ያስለቀሰ ፣ ልቦች በጣም የደነገጡበትን ምክር ለሶሃቦች መክረዋል፡፡
ሶሃቦችም “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ይህ ምክርዎት የመሳናበቻ ምክር ይመስላል ፤
አደራ የሚሉን ነገር ካለ ይንገሩን” አሏቸው፡፡ ረሡል ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ምክር
ለገሷቸው፡-

‫ فإنه من يعش منكم‬،- ‫"أوصيكم بتقوى هللا والسمع والطاعة – وإن عبدا حبشيا‬
،‫ وسنة الخلفاء المهديين الراشدين‬،‫ فعليكم بسنتي‬،‫بعدى فسيرى اختالفا كثيرا‬
‫ فإن كل محدثة‬،‫ وإياكم ومحدثات األمور‬،‫ وعضوا عليها بالنواجذ‬،‫تمسكوا بها‬
"‫ "وكل ضاللة في النار‬:‫ وكل بدعة ضاللة" وفي رواية‬،‫بدعة‬

“አላህን በመፍራት ፣ (መሪዎቻችሁን) - የሀበሻ ባሪያ እንኳ ቢሆን - በመስማትና


በመታዘዝ አደራ እላችኋለሁ ፤ እድሜ ሰጦት ከእኔ በኋላ የቆየ ሰው በርካታ ልዩነቶችን
ይመለከታል ፤ አደራ የእኔን ሱና የቅን መሪና ምክትሎቼን ሱና ፤ በእርሷ አጥብቃችሁ ያዙ
፣ በመንጋጋ ጥርሳችሁ ነክሳችሁ ያዙ ፤ አስጠነቅቃችኋለሁ አዳዲስ ፈሊጦችንም
(አስጠነቅቃችኋለሁ)፤ አዳዲስ ፈሊጦች ቢድዓ ናቸው ፤ ማንኛውም ቢድዓ ደግሞ ጥመት
6/43
ነው” አህመድ፡ አቡዳውድ፡ ኢብኑ ማጀህ፡ አድ ዳሪሚይ፡ ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል አስ ሲልሲለቱ አስ ሶሂህ፡

በሌላ ዘገባ ፡ “ማንኛውም ጥመት የእሳት ነው፡፡” ነሳኢይ፡ ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል

ተልኺሱ አህካም አል ጀናኢዝ፡

ይህ ፣ ረሡል ‫ﷺ‬ ህዝባቸው ከእሳት ነጻ የሚወጣበት የሆነውን የቀደምት ደጋግ


ባሮች ጎዳና አጥብቀው እንዲይዙ አደራ ያሉበት ምክር ነው፡፡
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
َّ ‫السبُ َل فَتَ َفَّر َق بِ ُك ْم َعن َسبِيلِ ِه َذلِ ُك ْم َو‬
‫صا ُكم بِِه لَ َعلَّ ُك ْم‬ ُّ ْ‫يما فَاتَّبِعُوهُ َوَلَ تَتَّبِعُوا‬ ِ ِ ِ َّ ‫﴿ َوأ‬
ً ‫َن َه َذا صَراطي ُم ْستَق‬
﴾‫تَتَّ ُقو َن‬

“ይህም ቀጥተኛ ሲሆን መንገዴ ነው ፤ ተከተሉትም፡፡ (የጥመት) መንገዶችንም


አትከተሉ፡፡ ከ (ቀጥተኛው) መንገዱ እናንተን ይለያዩዋችኋልና፡፡ እነሆ
ልትጠነቀቁ ዘንድ በርሱ አዘዛችሁ፡፡” አል አንዓም፡

“ልትጠነቀቁ ዘንድ” የሚለው የቁርኣን አንቀጽ እሳትንና ጥመትን ልትጠነቀቁ ፤

የጥመት ቡድኖችን ልትቃረኑ ፤ የነብያችሁንና የእርሳቸውን ባልደረቦች እንዲሁም


እነርሱን በመልካም የተከተሉት ሁሉ የተጓዙበትን ሰላማዊ መንገድ አጥብቃችሁ
ልትይዙ የሚል ትርጉም አለው፡፡

በመጨረሻው ዘመን ላይ በዚህ ትክክለኛ መንገድ ላይ የሚጓዙ ሰዎች ሰፊ የሆነ


መከራና ወቀሳ ከሰዎች በኩል ይደርስባቸዋል፡፡ ከዚህ ጎዳና ለማስጠንቀቅ ከጠላት በኩል
ውዥንብሮች ፣ ማስፈራሪያዎች ፣ ማባበያዎች ስለሚኖሩ በዚህ ጎዳና ላይ ጸንቶ ለመጓዝ
ትዕግስት ያስፈልጋል፡፡
የአላህ መልእክተኛ ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
"‫ فطوبى للغرباء‬،‫ وسيعود كما بدأ غريبا‬،‫"بدأ اإلسالم غريبا‬
7/43
“ኢስላም እንግዳ ሆኖ ጀመረ ፤ እንግዳ ሆኖ እንደጀመረ (እንደገና) ይመለሳል ፤
እንግድነቱን (ለተቀበለ) ጀነት (ተረጋገጠለት)” ሙስሊም፡

ረሡል ‫“ﷺ‬እንግዳው ማን ነው?” የሚል ጥያቄ ሲቀርብላቸው የሚከተለውን


ምላሽ ነበር የሰጡት፡-

"‫ "الذين يصلحون إذا فسد الناس‬:‫"الذين يصلحون ما أفسد الناس" وفي رواية‬

“ሰዎች ያበላሹትን የሚያስተካክሉ ናቸው” ቲርሚዚይ፡ የሐዲሱን ሰነድ አልባኒ ዶዒፍ አድርገውታል መሸካቱ

አል መሷቢህ፡ በሌላ ዘገባ ደግሞ፡ “ሰዎች የተበላሹ ጊዜ እራሳቸው የሚስተካከሉ ናቸው”


አህመድ፡ ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል፡ አስ ሲልሲለቱ አስ ሶሂህ፡

የቀደምት ደጋግ የአላህ ባሮችን መንገድ የተከተሉ ካልሆኑ በቀር በዱንያም


ከጥመት፤ በአኼራ ከእሳት ሰላም የሚሆን የለም፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-


ِ ِ ِ ‫ول فَأُولَئِك مع الَّ ِذين أَنْعم اّلل علَي ِهم ِمن النَّبِيِني و‬
‫﴿ َوَمن يُط ِع ه‬
‫ني‬ِِ َّ ‫لشه َداء و‬ ِ
َ ‫الصاِل‬ َ َ ُّ ‫ني َوا‬
َ ‫الص هديق‬
‫الر ُس َ ْ َ َ َ َ َ َ هُ َ ْ ه َ ه َ َ ه‬ َّ ‫اّللَ َو‬
﴾‫يما‬ ِ‫ضل ِمن اّللِ وَك َفى ِِبّللِ عل‬
ْ ‫ف‬
َ ‫ل‬
ْ ‫ا‬ ‫ك‬ ِ‫وحسن أُولَئِك رفِي ًقا۞ َذل‬
ً َ ‫ه‬ ‫ه‬
َ َ ُ َ َ َ َُ ََ
“አላህንና መልክተኛውንም የሚታዘዝ ሰው እነዚያ ከእነዚያ አላህ በእነርሱ ላይ
ከለገሰላቸው ከነብያት ፣ ከጻድቃንም ፣ ከሰማዕታትም ፣ ከመልካሞቹ ጋር
ይሆናሉ፡፡ የእነዚያም ጓደኛነት አማረ፡፡ ይህ ችሮታ ከአላህ ነው፡፡ አዋቂነትም
በአላህ በቃ፡፡” አን ኒሳእ፡

በዚህ ምክንያት በሁሉም የሶላት ረከዓዎች ላይ ፋቲሃን እንድንቀራ ግዴታ ሆኖብናል፡፡


በፋቲሃ መጨረሻ ላይ የሚገኘውን ዱዓ እስኪ እናስተውል፡፡ ጠማማ ከሆኑ መንገዶች
ነጻ ለመሆን “ቀጥተኛውን መንገድ ምራን” የሚል ዱዓ እንድናደርግ ታዘናል፡፡
8/43
ከነዚህ ጠማማ መንገዶች አርቆ ቀጥ ያለውን መንገድ እንዲመራን ፣ በእርሱም ላይ
እንዲያጸናን አላህን እንማጸናለን፡፡ “ቀጥተኛውን መንገድ ምራን” ብለን አላህን
እንማጸናለን፡፡ በዚህ ቀጥተኛ መንገድ ላይ የሚጓዘው ማን ነው? አላህ ጸጋውን
የዋለላቸው ነብያቶች ፣ እውነተኛዎች ፣ ሰማእታቶች እና ደጋግ የአላህ ባሮች ብቻ
ናቸው፡፡ ቀጥተኛ የሆነውን መንገድ እንዲመራህ አላህን እንደተማጸንከው ሁሉ
“በእነርሱ ላይ ከተቆጣህባቸው ሰዎች መንገድ ውጭ” በማለት ከጠማማ ጎዳናዎች

እንዲያርቅህ ትለምነዋለህ፡፡ አላህ የተቆጣባቸው ሐቅን ካወቁ በኋላ ባወቁት ያልሰሩት


አይሁዶች ናቸው፡፡ አውቆ በእውቀቱ የማይሰራ ማንኛውም ዓሊም አላህ ከተቆጣባቸው
አይሁዶች ጋር ይመሳሰላል፡፡

“ያልተሳሳቱት ሰዎችን መንገድ ምራን” የተሳሳቱት አላህን በስህተት ወይም

በማሕይምነት የሚግገዙ ሰዎች ናቸው፡፡ ከቁርኣንና ከሐዲስ መረጃ ውጭ ወደአላህ


ለመቃረብ ይሞክራሉ፡፡ አላህን የሚገዙት እራሳቸው በፈጠሩት ቢድዓ (ፈሊጥ) ነው፡፡
ማንኛውም ቢድዓ ደግሞ ጥመት ነው፡፡ ለዚህ ዋና ምሳሌ የሚሆኑት ክርስቲያኖች
ናቸው፡፡ እራሳቸው በመሰረቱት ትክክለኛ ያልሆነ መስመር አላህን እንገዛለን
በማለታቸው ጥመት ውስጥ ወደቁ፡፡ በዚህ ምክንያት የሚሰሩት ስራ ሁሉ ውድቅ
ተደረገባቸው፡፡

ይህ በየሶላቱ ሁሉ የምንደጋግመው አጠቃላይ የሆነ ዱዓ ነው፡፡ በመሆኑም አላህ


ከእኛ ዱዓችንን እንዲቀበለን ትርጉሙን አውቀን ከልባችን ልንለምነው ይገባል፡፡ ይህ
ዱዓ ላስተዋለው ትልቅ ዱዓ ነው፡፡ ለዚህ ነው ፋቲሃን ስንጨርስ “አሚን” የምንለው፡፡
አሚን የሚለው ቃል ትርጉም “አላህ ሆይ! ዱዓችንን ተቀበለን” ማለት ነው፡፡
9/43
ከዚህ በፊት እንደተናገርነው በዚህ መንገድ ላይ የሚጓዙ ሰዎች ከስድብ ከዘለፋ
ባሻገር በርካታ የሆኑ ፈተናዎች ስለሚደርስባቸው ከፍተኛ የሆነ ትዕግስት እና ጽናት
ያስፈልጋቸዋል፡፡

ረሡል ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-

"‫"يأتي على الناس زمان الصابر فيهم على دينه كالقابض على الجمر‬

“በዲኑ ላይ ትእግስተኛ የሆነ ሰው ልክ የእሳት ፍም እንደጨበጠ የሚሆንበት ዘመን


ይመጣል፡፡ አህመድ፡ ቲርሚዚይ፡ ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል አስ ሲልሲለቱ አስ ሶሂህ፡

ከሰዎች በኩል የከፋ ስቃይ ይገጥመዋል ፤ ልክ ፍም እሳት የጨበጠ ያክል


ይከብደዋል ፤ የሰለፎች መንገድ በአበባ የተነጠፈ ምቹ መንገድ አይደለም ፤ በርከታ
እንቅፋቶች ፊት ለፊቱ ይገጥሙታል፡፡ በመሆኑም በዚህ ጎዳና ላይ የሚጓዝ ሰው
ጌታውን እስኪገናኝ ድረስ ከፍተኛ የሆነ ትዕግስትና ጽናት ያስፈልገዋል፡፡ ያለምንም
ጥርጥር ፍጻሜው ያማረ ይሆናል ፤ በዱንያ ከጥመት በአኼራ ደግሞ ከእሳት ነጻ
ይሆናል፡፡ ከዚህ መንገድ ውጭ ሌላ መንገድ የለም፡፡ በዚህ መንገድ በመጓዝ ብቻ ነው
ሰላም የሚገኘው፡፡

በአሁኑ ሰዓት የሰለፎችን ጎዳና በመጽሄት ፣ በጋዜጣ እና በመጽሐፍ ሲያንቋሽሹ


እናስተውላለን፡፡ የሰለፍዮችን ክብር ሲያጓድሉ እናያለን፡፡ አክራሪ ፣ ተክፊር ወዘተ
የሚሉ ስም ሲለጥፉባቸው እንሰማለን፡፡ ይህ ፣ ትዕግስት በሌለው ሰው ላይ ካልሆነ በቀር
የሚያመጣው ጉዳት የለም፡፡ ምክንያቱም የኢስላም ጠላቶች ሶሃቦችን ተራግመዋል ፤
አቡበክርን ፣ ዑመርን ዑስማንን ፣ ሙዓውያን ተሳድበዋል ፣ በቀደምት ደጋጎች ፣
አኢማዎችና አሁን ባሉት ሰለፍዮች መካከል ያለውን ግንኙነት ለመቁረጥ የሶሃቦችን
10/43
ነውር እየፈለጉ አሰራጭተዋል ፣ ታሪካቸውን በመጥፎ አጠልሽተዋል፡፡

ከእነርሱ መካከል፡ “ሰለፎች እነማን ናቸው? ሰለፎች ማለት ልክ እንደሌሎች


ፊረቆች ናቸው ፤ ምንም መለያ የላቸውም” የሚሉ አሉ፡፡ ይህን የሚሉት የሰለፍ
መንሐጅ ከእጃችን እንዲያመልጥ መሆኑን ልብ ልንል ይገባል፡፡

ከእነርሱ መካከል ፡ “የሰለፎችን ፊቅህ እና እውቀት የመማርና የማወቅ ግዴታ


የለብንም” የሚሉ አሉ፡፡ “የሰለፎች ፊቅህ ለዚህ ዘመን የማይስማማ ፣ የቆየ ያረጀ
ያፈጀ በመሆኑ እኛ አዲስ ነገር ፣ አዲስ ብይን ፣ አዲስ ፊቅህ ያስፈልገናል” ይላሉ፡፡
“የሰለፎች መንገድ ለራሳቸው ዘመን ብቻ ተስማሚ ሆኖ የተዘጋጀ ነው” ይላሉ፡፡ ለዚሀ
ነው ሰዎች የሰለፎችን ፊቅህ እንዳያውቁ እንቅፋት የሚሆኑት፡፡ ጠማማ ጸሐፊዎች
አዲስ ፊቅህ እንደሚያስፈልግ ዘወትር በጋዜጣ ፣ በመጽሄት እና በመጽሐፍ እየፃፉ
ቅስቀሳ ያደርጋሉ፡፡ የእነርሱ ፍላጎት የሰለፎች መንሐጅ ከእጃችን አምልጦ እንዲሄድ ፣
የሰለፎችን መንሐጅ እንድንተውና ወደጥመት ጎዳና እንድንገባ ነው፡፡

ያለእውቀት ወደሰለፎች መዝሐብ መጠጋት በቂ ሊሆን አይችልም፡፡ እነርሱ


የሚፈልጉት የሰለፎችን መዝሐብ ፣ እውቀትና ግንዛቤ ትተን አዲስ ፊቅህ እንድንፈጥር
ነው፡፡ የሰለፎች መዝሐብ ከአላህ የመጣ ፣ ለሁሉም ቦታ ለሁሉም ዘመን የሚስማማ
ብርሃን በመሆኑ ጠማማ ሰዎች የሚያሰራጩት ውዥንብር ከሰለፎች ጎዳና ሊያዘናጋን
አይገባም፡፡
ኢማም ማሊክ I የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
"‫"ال يصلح آخر هذه األمة إال ما أصلح أولها‬
“የመጀመሪያውን (ትውልድ) ያስተካከለው ካልሆነ በቀር የመጨረሻው ማህበረሰብ
11/43
ሊስተካከል አይችልም፡፡” መጅሙዕ አል ፈታዋ ሊብን ተይሚያ፡

የመጀመሪያውን (ትውልድ) ያስተካከለው ማን ነው? ኪታብና ሱና ነው ፤


የረሡልን ‫ﷺ‬ ሱና መከተል ነው ፤ በቁርኣን መስራት ነው፡፡ ይህ ነው የመጀመሪያውን
ማህበረሰብ ያስተካከለው፡፡ ከእሳት ለመዳን የፈለገ ሰው የሰለፎችን መንሐጅ (ጎዳና)
ማወቅ ፣ እርሱን አጥብቆ መያዝ እና ወደርሱ ዳዕዋ ማድረግ አለበት፡፡ እርሱ ነው
ከእሳት የመዳኛው ብቸኛ መንገድ፡፡ እርሱ ልክ እንደኑህ d መርከብ ነው፡፡ እርሷን
የጋለበ ይድናል ፣ እርሷን ያልጋለበ ደግሞ ይጠፋል ፣ በጥመት ይሰምጣል፡፡ የሰለፎችን
ጎዳና ለማወቅ ዘወትር የሚከተለውን ዱዓ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ “ቀጥተኛውን
መንገድ ምራን ፡፡ የእነዚያን በነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን”

አላህ መልካሙን እንዲገጥመን ፣ በእርሱም ላይ እንዲያጸናን እንማጸነዋለን፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-


ٍ ‫﴿والَّ ِذين اتَّب عوهم ِبِِحس‬
﴾‫ان‬ َ ْ ُ َُ َ َ
“እነዚያ በመልካም የተከተሉ” አት ተውባህ፡

እውቀትን መሰረት አድርገው በትክክል የተከተሉ ማለት ነው፡፡ ካልተማርክ


የሰለፎችን መዝሀብ አጥርተህ ማወቅ አትችልም፡፡ ትዕግስት ከሌለህ ደግሞ የሰለፎችን
ጎዳና አጥብቀህ መያዝ አትችልም፡፡ ይህ ነው ትክክለኛውና ከእሳት መውጫው ብቸኛ
መንገድ፡፡ ረሡል ‫ﷺ‬ “አንዷ መንገድ እንጅ ሁሉም የእሳት ናቸው” በማለት
በሐዲሳቸው እንደተናገሩት የሰለፎችን ጎዳና የተቃረነ መንገድ ሁሉ የእሳት ነው፡፡
“እርሷ ማን ነች?” በማለት ሶሃቦች ጠየቁ “እኔ እና ሶሃቦች በነበርንበት (ጎዳና ላይ)
የተጓዙት ናቸው” በማለት የአላህ መልእክተኛ ‫ﷺ‬ ምላሽ ሰጠዋል፡፡
12/43
ይህ ነው የሰለፎች መንሐጅ ይህ ነው ወደጀነት የሚያደርሰው ከእሳት የምንድንበት
ብቸኛው መንገድ፡፡ ከእርሱ ውጭ ሌላ መንገድ የለም፡፡ ከእርሱ ውጭ የሆነው መንገድ
ሁሉ የጥመት መንገድ ነው፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

َّ ‫السبُ َل فَتَ َفَّر َق بِ ُك ْم َعن َسبِيلِ ِه ذَلِ ُك ْم َو‬


﴾‫صا ُكم بِِه لَ َعلَّ ُك ْم تَتَّ ُقو َن‬ ُّ ْ‫يما فَاتَّبِعُوهُ َوَلَ تَتَّبِعُوا‬ ِ ِ ِ َّ ‫﴿ َوأ‬
ً ‫َن َه َذا صَراطي ُم ْستَق‬
“መንገዶችንም አትከተሉ፡፡ ከ(ቀጥተኛው) መንገዱ እናንተን ይለያዩዋችኋልና፡፡
እነሆ ትጠነቀቁ ዘንድ በርሱ አዘዛችሁ፡፡” አል ንዓም፡

እርሱ የአላህ መንገድ ነው፡፡ ሌሎች መንገዶች አጥማሚ መንገዶች ናቸው፡፡


የተሳሳቱ መንገዶች ናቸው፡፡ ሰይጣን በእያንዳንዱ መንገድ ላይ ቆሞ ሰዎችን
ይቀሰቅሳል፡፡ ሰዎች ከሰለፎች መንገድ እንዲርቁ የሚያደርጉ የጥመት ተጣሪዎች አሉ፡፡
እነዚህ ሰዎች ከጀሀነም በር ላይ ቆመው ሰዎችን ወደጥመት እንደሚጣሩ የአላህ
መልእክተኛ ‫ ﷺ‬በሐዲሳቸው ተናግረዋል፡፡ እነዚህ የጥመት ተጣሪዎች ለኡመታቸው
ስጋት እንደሆኑም አስጠንቅቀዋል፡፡ እነዚህን የጥመት ተጣሪዎች አቤት ብሎ የታዘዘ
ጥመት ላይ ይወድቃል፡፡ አደጋው ከባድ ነው፡፡ ዘመን በዘገየ ቁጥር የኢስላም እንግድነቱ
ይበረታል ፤ ፊትና ይበዛል፡፡ ስለዚህ ሙስሊሞች በሰለፎች መንሐጅ ላይ ትኩረት
አድርገው ሊማሩ ይገባል፡፡
ከእነርሱ መካከል “ሁሉም ሙስሊም ነው” የሚሉ ናቸው፡፡ እኛም ሙስሊምነታቸው
በምን አይነት መንገድ እንደሆነ እንጠይቃቸዋለን፡፡

<ሸይኹ እያመላከቱ ያለው ሑዘይፋ 4 ረሡልን ‫ﷺ‬ ሰዎች ስለመልካም ሲጠይቁ እኔ ስለመጥፎ ነገር እጠይቃቸው
ነበር ብለው ያስተላለፉልንን ረዘም ካለው ሐዲስ ውስጥ የጠቆሙትን ቃል ነው፡፡> ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡
13/43
ሙስሊምነታቸው በረሡል ‫ﷺ‬ እና በሶሃቦች መንገድ ላይ ነው ወይስ ወደጀሀነም
የሚወስድ የተሳሳተ መዝሐብ በተከተሉት እነእከሌ የሚባሉ ሰዎች መንገድ ላይ? ልብ
በሉ! ጉዳዩ ወደኢስላም የመጠጋት ጉዳይ አይደለም፡፡ ጉዳዩ ትክክለኛ ሙስሊም ሆኖ
መገኘት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ጠቃሚ እውቀት ላይ ትኩረት በመስጠት ካልሆነ ሊገኝ
አይችልም፡፡ ለዚሀ ነው ዑለሞች ለዓቂዳና ለሰለፎች መንሐጅ ትኩረት ሰጠው በርዕስ
ከፋፍለው ረጃጅምና አጫጭር ኪታቦችን ያዘጋጁት፡፡ ስለዚህ ጉዳዩ ትኩረትን ይፈልጋል፡፡
በተለይም ጠማማ እና ጨለማ የሆነው መንገድ ከትክክለኛው ጎዳና በላይ ሆኖ ውሳኔ
ለመስጠት እንቅስቃሴ በሚያደርግበት ወቅት የግድ ሙስሊሞች ከጥመት ጨለማ እና
ከማህይምነት የሚወጡበት የብርሃን ጎዳና አቅጣጫ መስጠት ያስፈልጋቸዋል፡፡

እውቀትን ከምንጩ ሳይወስድ እውቀት አለኝ የሚለው ማህበረሰብ በአሁኑ ሰዓት


ቁጥሩ በዝቶ ይታያል፡፡ እውቀትን ከመሰሎቹ ወይም ከመጽሐፎች ወይም እነርሱ
“ሰቃፋ” ከሚሉት የዘመናዊ ትምህርት ነው የወሰደው፡፡ ይህ ደግሞ ወደመልካምና
ወደትክክለኛው መንገድ አያደርስም፡፡ እርሱን አጥብቆ ለመያዝና በእርሱም ላይ
ለመጓዝ ትክክለኛ የሆነውን የሰለፎች መንሐጅ ከእውቀት ባለቤቶች ማወቅ እና መማር
የግድ ነው፡፡ ለዚሁ ሲባል ነው በሚደርስብህ ወቀሳ የሰለፎችን መንሐጅ ዝቅ የማድረግና
የማዋረድ ስራ ትዕግስት ያስፈልጋል የምንለው፡፡

በአሁኑ ሰዓት በሰለፎች መንሐጅ ላይ የሚጓዙ ሰዎችን የሚንቁ የሚያዋርዱ ፤


የሰለፎችን ጎዳና “ኋላ ቀር” በማለት የሚዘልፉ ሰዎችን ትሰማለህ፡፡ ከእሳት ቅጣት
ሰላም ሆናችሁ ፍላጎታችሁን የምታገኙበት መንገድ እርሱ ብቻ በመሆኑ ይህ ንግግራቸው
የሰለፎችን መንሐጅ አጥብቃችሁ ከመያዝ ወደኋላ እንዳያደርጋችሁ፡፡
14/43
የአላህ መልእክተኛ ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

‫ وسنة الخلفاء‬،‫ فعليكم بسنتي‬،‫"فإنه من يعش منكم بعدى فسيرى اختالفا كثيرا‬
"‫المهديين الراشدين‬

“ከእኔ በኋላ ከእናንተ ለቆየ ሰው በርካታ ልዩነቶችን ይመለከታል፡፡ አደራ የእኔን ሱና የቅን
መሪ ምክትሎቸን ሱና ፤ በእርሷ አጥብቃችሁ ያዙ”

በልዩነት ጊዜ የረሡልን ‫ﷺ‬ ሱና ፣ የቅን ምክትሎችን ሱነ አጥብቆ የያዝ ካልሆነ


በቀር ከጥመት ሰላም የሚሆን የለም፡፡ ይህ ነው ከእሳት ሰላም መሆኛው መንገድ፡፡ ይህ
ነው ሰላማዊው የጀነት መንገድ፡፡

የዲን ጉዳዮችን እንደቀላል የሚመለከቱ ወይም ዲንን በመጥፎ የሚገልጹ ሰዎች


እንቅስቃሴ ለሰለፎች ጎዳና ትኩረት ከመስጠት እንዳያግደን፡፡ የሰለፎችን ጎዳና
በልቦቻችን ውስጥ ትልቅ ቦታ እንስጥ፡፡ ለእርሱ ፍላጎታችን ይጨምር፡፡ ምክንያቱም
እነርሱ የሚዋጉን የሰለፎች መንገድ የሐቅ መንገድ በመሆኑ ብቻ ነው፡፡ እነርሱ
የሚፈልጉት ጥመትን ነው፡፡ ከእነርሱ ተጠንቀቁ፡፡ የአላህ ባሮች ሆይ! ሰለፍይ ነኝ
በማለት ብቻ ወይም ሳይማሩ ተምሪያለሁ ማለቱ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ በትክክለኛው
ጎዳና ላይ ቀጥ ካሉ ታላላቅ አሊሞች ላይ እውቀትን ውሰዱ፡፡ አላህ ካስጠነቀቀን ጠማማ
ጎዳና ተጠንቀቁ፡፡ እርሱንም ራቁ፡፡
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
َّ ‫السبُ َل فَتَ َفَّر َق بِ ُك ْم َعن َسبِيلِ ِه َذلِ ُك ْم َو‬
﴾‫صا ُكم بِِه لَ َعلَّ ُك ْم تَتَّ ُقو َن‬ ُّ ْ‫﴿ َوَلَ تَتَّبِعُوا‬
“መንገዶችንም አትከተሉ፡፡ ከ(ቀጥተኛው) መንገዱ እናንተን ይለያዩዋችኋልና፡፡
እነሆ ትጠነቀቁ ዘንድ በርሱ አዘዛችሁ፡፡” አል አንዓም፡
15/43

ከቅጣት ነጻ የሚያወጣችሁ ብቸኛው መንገድ የአላህ መንገድ ነው፡፡ ይህ ቀጥተኛ


መንገድ ለእኛ በጣም አስፈልጎናል፡፡ በተለይም ፈተናው ፣ ተንኮሉ እና የጥመት
ተጣሪዎች በሰዎች መካከል በበዙበት ፤ የተንኮል ማሰራጫ መንገዱ በረቀቀበት ወቅት፡፡
ከቤታቸው ሳይወጡ ፣ ከፍራሻቸው ላይ ተደግፈው ተንኮል በቀላል መንገድ
ይደርሳቸዋል፡፡ ሀራሙን ሀላል ፣ ሀላሉን ሀራም የሚያደርግ የሹቡሃና የሸሀዋት ጥሪ
ይደርሳቸዋል፡፡ ይህን የጥመት ቅስቀሳ ልክ የአዕምሮ ስፋትና ስልጣኔ አድርገው
ይቆጥሩታል፡፡ ይህ የጥመት ጎዳና ከትክክለኛው የሰለፎች መዝሐብ ፣ እውቀትና ግንዛቤ
የሚያርቅ ፣ ቀልብን የሚያደርቅ አይደለምን?!

የሰለፎች መንገድ ከኸለፎች (ወደኋላ ከመጡት) በጣም ሰላማዊ ፣ በእውቀትና


በጥበብ የተሞላ ነው፡፡ የሰለፎች እውቀት ከቁርኣን እና ከሐዲስ በቀጥታ የተያዘ ነው፡፡
የኸለፎች እውቀት ያልጠሩ ነገሮች የተቀላቀሉበት እውቀት ነው፡፡ ለዚህ ነው በየጊዜው
የሰለፎችን እውቀት ከውስብስብ ነገሮች የጸዳ ሆኖ የምናገኘው፡፡

ኢብን ረጀብ I“ፈድሉ ዒልሚ አስለፍ አላ ኢልሚ አልኸለፍ” በሚለው ኪታቡ


የሚከተለውን ተናግሯል፡-

"‫ وعلمهم قليل‬،‫ الخلف كالمهم كثير‬،‫"السلف كالمهم قليل وعلمهم غزير‬

“ሰለፎች ንግግራቸው ቀላል እውቀታቸው ጥልቅ ነው፡፡ ኸለፎች (ወደኋላ የመጡት)


ደግሞ ንግግራቸው ብዙ እውቀታቸው ቀላል ነው፡፡”

ለዚህ ጉዳይ ነቃ እንበል፡ ፎርጅድ ያልሆነ ፣ ብዥታ የሌለበት ፣ አውቀን በጽናት


ከተገበርነው ሰላም የምንሆንበት ጎዳና የሰለፎች መንሐጅ ይህ ነው፡፡
16/43
በዚህ አጀንዳ ዙሪያ አጠር ያለው ማብራሪያየ ይህን ይመስላል፡፡ በእርግጥ ሁሉንም
ጎን እንዳላብራራሁ ይሰማኛል፡፡ ይሁን እንጅ አላማየ አላህ በሚከተለው ቁርኣን
እንደተናገረው መሆኑን ልትገነዘቡ ይገባል፡-

﴾‫ني‬ ِ
َ ‫﴿ َوذَ هكْر فَِإ َّن ال هذ ْكَرى تَن َف ُع الْ ُم ْؤمن‬
ِِ ِ

“ገስጽም ፤ ግሳጼ ምእመናንን ትጠቅማለችና፡፡” አዝ ዛሪያት ፡

﴾‫ت ال هِذ ْكَرى۞ َسيَ َّذ َّكُر َمن ََيْ َشى‬


ِ ‫﴿فَ َذ هكِر إِن نَّ َفع‬
َ ْ
“ግሳጼቱም ብትጠቅም (ሰዎችን) ገስጽም፡፡ (አላህን) የሚፈራ ሰው በእርግጥ
ይገሰጻል፡፡” አል አዕላ፡

ለመልካም ስራና ንግግር አላህን እዲገጥመን ፤ በሐቅ ላይ በትዕግስት እንዲያጸናን


እንማጸነዋለህ፡፡
‫وصىل هللا وسمل عىل نبينا محمد وعىل آهل وآحصابه آمجعني‬
17/43

ጥያቄ
ጥያቄ 1፡- እኔ በሽተኛ የሆንሁ የልጆች እናት ነኝ፡፡ ልጄ ጅሐድ ብሎ ከወጣ ቆይቷል፡፡
ጅሐድ ብሎ ሲወጣ እኔ ተስማምቸበት አይደለም፡፡ ልጀንም እርሱንም አነሳስቶ
እንዲሄድ ያደረገውንም አካል እስካሁን ድረስ እየተራገምኩ እገኛለሁ፡፡ በዚህ ተግባሬ
ሀጢያተኛ እሆናለሁ? ጀዛኩሙሏሁ ኸይረን

መልስ 1፡- አላህ እንዲመራው ፣ በሰላም እንዲመልሰው ፣ ትክክለኛውን ጎዳና


እንዲያሳየው ዱዓ አድርጊለት እንጅ አትርገሚው፡፡ ልጅሽ ያለምንም ጥርጥር
ተሳስቷል፡፡ ስለዚህ አደራ ቅኑን ጎዳና እንዲሰጠው ፣ አላህ እንዲያስተካክለውና ሰላም
እንዲያደርገው ዱዓ አድርጊለት፡፡ እርሱ ፣ ከቤታቸው ተቀምጠው ሙስሊም ወጣቶችን
ጅሐድ እያሉ በሚቀሰቅሱ የጥመት ተጣሪዎች ነው የተሸወደው፡፡ ይህ ተግባራቸው
ከሚከተለው ቀርኣናዊ አንቀጽ ጋር ይስማማል፡፡

﴾‫اّللِ أَن تَ ُقولُوا َما ََل تَ ْف َعلُو َن‬ ِ ِ َّ


َ ‫﴿ َاي أَيُّ َها الذ‬
َ ‫ين آَ َمنُوا ِلَ تَ ُقولُو َن َما ََل تَ ْف َعلُو َن۞ َك َُب َم ْقتًا ِع‬
َّ ‫ند‬

“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የማትሰሩትን ነገር ለምን ትናገራላችሁ ፤ የማትሰሩትን


ነገር መናገራችሁ አላህ ዘንድ መጠላቱ ተለቀ” አስ ሶፍ፡

ጥያቄ 2፡- አንድን ግለሰብ የተክፊር ባህሪ ስታገኝበት እንጅ “ኸዋሪጅ” ብሎ ለይቶ
መናገር አይገባም የሚሉ ሰዎች አሉ ይህ አባባላቸው ምን ያክል ትክክል ነው?

መልስ 2፡- የኸዋሪጅ መዝሀብ የተለያየ ነው፡፡

- አንደኛው በአንደበቱ ሳይናገር በልቡ ብቻ ማመን ነው፡፡ የኸዋሪጅ እምነት ትክክል


ነው ብሎ ካመነ በአንደበቱ ባይናገርም ኻሪጅይ ነው፡፡
18/43
- ሁለተኛው የኸዋሪጅ መዝሀብ (ጎዳና) በንግግር ሊሆን ይችላል፡፡ ለምሳሌ፡
በመሪዎች ላይ አመጽ እንዲያካሂዱ በአንደበቱ ማነሳሳት፡፡
- ሶስተኛው መሳሪያ ባይሸከሙም ከሽርክና ከኩፍር የራቁ ወንጀለኛ ሙስሊሞችን
ማክፈር፡፡ ይህ የኸዋሪጅ መዝሀብ ነው፡፡ በሙስሊሞች ላይ መሳሪያ ከመዘዘ ደግሞ
የበረታ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ኸዋሪጅነት ወይም ማፈንገጥ የተለያየ መሆኑን
ልንገነዘብ ይገባል፡፡
ጥያቄ 3፡- ሁከት ወዳለበትና ብጥብጥ ወዳለበት አገር ወጣቶች እንዲሄዱ ፈትዋ
የሚሰጡ ሰዎችን አስመልክቶ አቅጣጫ እንፈልጋለን?
መልስ 3፡- አጠቃላይ ፈትዋ የራሱ ባለቤት አለው፡፡ የፈትዋ ጉዳይ ለእውቀት እና
ለቀጥተኛነት ባቤቶች ነው ሊሰጥ የሚገባው፡፡ ፈትዋ በሚሰጥ ማንኛውም አካል ንግግር
አይሰራበትም፡፡
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
﴾‫اسأَلُواْ أ َْه َل ال هِذ ْك ِر إِن ُكنتُ ْم َلَ تَ ْعلَ ُمو َن‬
ْ َ‫﴿ف‬
“የማታውቁም ብትሆኑ የዕውቀት ባለቤቶችን ጠይቁ፡፡” አን ነሕል፡

ሁሉም አይጠየቅም ፤ ሁሉም ሙፍቲ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ይህ ለስርዓት


አልበኝነት በር ይከፍታል፡፡ የተናጠል ጥያቄ ከሆነ በአላህ ፍራቻው ለሚታወቅና
ለሚያምነው ሰው ይጠይቅ፡፡ እርሱ በሰጠው ፈትዋ ይስራ፡፡ የጅሀድ ጉዳይ ግን አጠቃላይ
የፈትዋ ጉዳይ ስለሆነ ወደዳረል ኢፍታእ (የፈትዋ ክፍል) መመለስ አለበት፡፡
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
﴾‫ين يَ ْستَنبِطُونَهُ ِمْن ُه ْم‬ ِ َّ ِ ِ ِ ِ َّ ‫﴿ولَو رُّدوهُ إِ ََل‬
َ ‫الر ُسول َوإ ََل أ ُْوِِل األ َْم ِر مْن ُه ْم لَ َعل َمهُ الذ‬ َ َْ
“ወደመልክተኛውና ወደ ትዕዛዙ ባለቤቶች ወደአዋቂዎች በመለሱት ኖሮ እነዚያ
19/43
ከእነርሱ (ነገሩን) የሚያውጣጡት ባወቁት ነበር፡፡” አን ኒሳእ፡

ከላይ ከተጠቀሱት ሰዎች ውጭ መጠየቅ ሰይጣንን መከተል ይሆናል፡፡


ጥያቄ 4፡- ጦርነት በአሁኑ ሰዓት የሚካሄድባቸው ለምሳሌ፡- ሶሪያና የመሳሰሉ
የሙስሊም አገሮች የሚኖሩ ሙስሊሞች እያንዳንዳቸው ጅሐድ የመውጣት ግዴታ
አለባቸው?

መልስ 4፡- ጅሐድ ዝግጅትና የመሪዎች ፈቃድ የግድ ያስፈልጋል፡፡ በመሪው ፕሮግራም
ነው ጅሐድ መካሄድ ያለበት፡፡ ለጅሐድ ጥሪ የሚያደርጉት መሪዎችና የጦር መሪዎች
ወይም እነርሱ የወከሏቸው ምክትሎች ናቸው፡፡ ጅሐድ የሚካሄደው በሙስሊም
መሪዎች ባንዲራ ስር ሊሆን ይገባል፡፡ ይህ ነው ጅሐድ የሚባለው፡፡ በጅሐድ ስርዓት
ሳይመራ ሁሉም በራሱ ተነስቶ ልታገል ማለት ጅሐድ አይባልም፡፡ ይህ ስርዓት አልበኝነት
ነው የሚባለው፡፡ ከሚጠቅመው የሚጎዳው ይበልጣል፡፡

ጥያቄ 5፡- የመን ላይ ደማጅ ውስጥ በጠላት ለሚንገላቱ ሰለፍይ ወንድሞችዎት አላህ
እንዲረዳቸው ዱዓ እንድታደርጉላቸው እንፈልጋለን?

መልስ 5፡- በሁሉም ቦታ ኢስላምና ሙስሊሞችን አላህ እንዲረዳ እማጸናለሁ፡፡ በደል


የደረሰባቸውን እንዲሁም ጭንቀት ውስጥ የገቡ የደማጅ ወንድሞቻችንን ከጭንቀት
እንዲገላግላቸውና በጠላቶቻቸው ላይ እንዲረዳቸው ፤ በሁሉም ቦታ ኢስላምና
ሙስሊሞችን እንዲያልቅ እለምናለሁ፡፡

ጥያቄ 6፡- ሰለፍዮች ተውሂድ እንጅ ሌላ የላቸውም ፤ ስለጅሐድ ስለፖለቲካ ጭራሽ


አይናገሩም ፤ በዓለም ስለሚገኙ ሙስሊሞች ችግር ጭንቀትና ሀሳብ የላቸውም የሚሉ
አንዳንድ ሰዎች አሉ ስለነዚሀ ሰዎች ምን ምላሽ አለዎት?
20/43
መልስ 6፡- ተውሒድ መሰረት ነው፡፡ ተውሂድና ዓቂዳ ከተስተካከለ ቀሪው ነገር ሁሉ
ይስተካከላል፡፡ ተውሂድ ከጎደለ ግን ሌሎች ነገሮች ፋይዳ አይኖራቸውም፡፡ ተውሂድ
መሰረት ነው፡፡ ተውሂድ ከቅጣት ነጻ የምንሆንበት መንገድ ነው፡፡ ነገር ግን ትምህርታችን
በተውሂድ ብቻ መወሰን የለበትም ፤ በእርሱ ይጀመራል ከዚያ ጎን በጎን ፊቅህን ፣
ሱናን እና ሌሎች ጠቃሚ የሆኑ እውቀቶች በዒልም ባለቤቶች አማካኝነት እንዲማሩ
ይደረጋል፡፡ እኛ ፣ ተውሂድ እንጅ ሌላ ሊማሩ አይገባም አላልንም፡፡ ለዚህ ነው
ትምህርት ቤት ብትገቡ ተውሂድ ፣ ፊቅህ ፣ ሐዲስ ፣ ጆግራፊ ፣ ሂሳብ እና
የመሳሰሉትን ተማሪዎች ሲማሩ የምታዩት፡፡ ሌላውን ትምህርት ማንም የከለከለ የለም፡፡
እኛ የምንለው ትምህርቱ ትኩረት ተሰጥቶ በተውሂድ ይጀመር ነው የምንለው፡፡ ሁሉን
የሚመለከት አጠቃላይ ጉዳይ ከሆነ ማንም ተነስቶ የሚመልሰው ሳይሆን ራሱን ችሎ
የሚመለከተው አካል ምላሽ የሚሰጥበት ይሆናል፡፡
ጥያቄ 7፡- አንዳንድ ሰዎች እውቀትን ከዓሻኢራ መውሰድ ይበቃል ይላሉ፡፡ ለምሳሌ ፡-
የዓሻኢራ ዓቂዳ ከነበራቸው ነወውይ እና ብን ሐጀር፡፡ ይህ ንግግር ምን ያህል ትክክል
ነው?
መልስ 7፡- ትክክለኛ እውቀት ይወሰዳል፡፡ ስህተቱ ደግሞ ይተዋል ወይም ይራቃል፡፡
አንድ ዓሊም ከእርሱ ዘንድ ዒልምና ስህተትም ካለበት ስህተቱን ትተን ጠቃሚ የሆነውን
እውቀት እንወስዳለን፡፡ ነወውይ I እና ኢብን ሐጀር I በተእዊል (በትርጉም
መዛባት) ምክንያት ስህተት ቢኖርባቸውም ዓሻኢራ ሳይሆኑ የሐዲስ ሰዎች ናቸው፡፡
ይህ የተከሰተው ስህተት ጁዝእይ (መሰረታዊ ያልሆነ) ነው፡፡

ጥያቄ 8፡- በሰለፍ መንሐጅ ላይ የተቃረነ አካል ከአህለል ቢድዓ ይቆጠራል ወይም
ከአህለሱና መጠሪያነት ይወጣል ወይስ አይወጣም?
21/43
መልስ 8፡- የሰለፎችን መዝሀብ የተቃረነ ከአህለሱና ወልጀማዓህ አይደለም፡፡ ይልቁንም
ከኸለፎች (ወደኋላ መጠው በዲኑ ላይ ከዘባረቁት) ነው፡፡ የሰለፎችን መዝሐብ
ከተቃረነ በሰለፍ መንሐጅ ሊሆን አይችልም፡፡ በእርግጥ ጥመቱ በተቃርኖው መጠን
ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም ሰዎች በተቃርኖ ይበላለጣሉ፡፡ በመሆኑም እንደተቃርኗቸው
የሚሰጣቸውም ብይን በዚያው መጠን ይለያያል፡፡

ጥያቄ 9፡- እኛ በአፍሪካ ነው የምንኖረው፡፡ ዳኛችን ሙስሊም ቢሆንም አገሪቱ የሸሪዓን


ህግ ተግባራዊ አታደርግም፡፡ እኛ ለመሪ ቃል ኪዳን መግባት ፣ መስማት እና መታዘዝ
እንዳለብን እናምናለን፡፡ ነገር ግን ወደሱና የተጠጉ እኛን “አህለል በይዓ” (የቃል
ኪዳን ባለቤት) ወይም “ጧኢፈቱ አልበይዓ” (የቃል ኪዳን ቡድን) በማለት
ይተቹናል፡፡ ስለነዚህ ሰዎች ምንድን ምክር ይሰጡናል?

መልስ 9፡- ሁለት ጉዳቶች ከተከሰቱ ከባድ የሆነውን ለመከላከል ሲባል ቀላሉን ሰርቶ
ማለፍ ይገባል፡፡ አንድ አገር በሁሉም ነገር የጠራ ይሆናል ማለት ትክክል አይደለም፡፡
ነገር ግን መልካም ነገሮችን እንይዛለን ፣ ጥሩ ያልሆኑ ነገሮችን ደግሞ እንርቃለን፡፡
ከሁለት ጉዳቶች ከፍተኛውን ለመከላከል ሲባል ቀላሉን መስራት አስፈላጊ ነው፡፡
ከእናንተ ለማሸሽ ከተቃራኒዎች የሚመጣውን አሜትና የስም ማጥፋት ቦታ ልትሰጡት
አይገባም፡፡ ከመሪዎቻችሁ ጋር ያላችሁ መመካከር ለእነርሱም የምታደርጉት ዳዕዋ
ይቀጥል፡፡

ጥያቄ 10፡- ሰለፍያ ጅሐድያ ፣ ኢልምያ እና ኡሱልያ የሚባሉ ክፍሎች እንዳሉት ብዙ


ጊዜ እንሰማለን፡፡ ይህ ምን ያህል ትክክል ነው?

መልስ 10፡- ይህ ፣ ስህተት ነው፡፡ ሰለፍያ አትከፋፈልም፡፡ ሰለፍያ በዓቂዳ ፣ በሙአመላ


22/43
(ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት) ፣ በስነምግባር እና በሌሎችም የዲን ጉዳዮች ረሡል
‫ﷺ‬ እና ሶሃቦች በተጓዙበት ጎዳና ላይ የተጓዙ ናቸው፡፡ ይህ ነው ሰለፍያ፡፡ ኡሱልያና
የመሳሰሉ ስያሜዎች ጥናት የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡ ከሰለፍ መዝሀብ
ከገጠመ ይያዛል ፣ ተቃራኒ ከሆነ ደግሞ ይተዋል፡፡ የሰለፍ መንሐጅ ሰዎች ለሚጓዙበት
እንቅስቃሴ ሁሉ ሚዛንና እና መቀየሻ ነው፡፡ የሰለፍን መንሐጅ እንድንከተል ፣
በእርሱም ተጎታች እንድንሆን እና በእርሱ ላይ እንድንጓዝ አላህ አዞናል፡፡ ከእርሱ
እንድርቅ ለሚያደርጉ ጉዳዮች ቦታ ልንሰጠው አይገባም፡፡ ከእንቅስቃሴያችን
ሊያግደንም አይገባም፡፡
ጥያቄ 11፡- ለሱና ተቃራኒ የሆኑትን አካላት ምላሽ መስጠት ለሰለፎች ጎዳና መሰረት
ነው? ዑለሞች በአህለል ቢድዓ ላይ ምላሽ በመስጠታቸው ሲተቹ እናስተውላለን?
መልስ 11፡- በአህለል ባጢል ላይ ምላሽ የሚሰጡ የእውቀት ባለቤቶች ከሆኑ ይህ
ሐቅ ነው፡፡ አላህ በሙሽሪኮች ፣ በሙናፊቆች ላይ መልስ ሰጧል፡፡ ረሡል ‫ﷺ‬

በአይሁድ ፣ በነሷራ ፣ በጠማማ ፊረቆች ላይ ምላሽ ሰጠዋል፡፡ በባጢል ላይ መልስ


ካልሰጠን ሐቅ ግልጽ ሊሆን አይችልም፡፡ ይህ አንገብጋቢ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡ ነገር ግን
ሁሉም እየተነሳ ምላሽ መስጠት የለበትም፡፡ መልስ መስጠት ያለባቸው የመልስ
አሰጣጥ ችሎታ ያላቸው የእውቀት ባለቤቶች መሆን አለባቸው፡፡ በአሁኑ ሰዓት
በወጣቶች እንዲሁም ወደእውቀት ተጠጋን የሚሉ ሰዎች እየተከሰተ ያለው አንዱ
አንዱን መተቸት ለሙስሊሞች የሚበጅ ጉዳይ አይደለም፡፡ ይህ ሙስሊሙን መበጥበጥ
እና መሳደብ በመሆኑ አይፈቀድም፡፡ እነዚህ ሰዎች የእውቀት ባለቤቶች እንዳልሆኑ
ሊታወቅ ይገባዋል፡፡ የእውቀት ባለቤት ይህን አይሰራም፡፡ በእውቀት ፈላጊዎች መካከል
የተከሰተውን ችግር ልዩነቱ በጣም ሳይሰፋ ማስማማት ያስፈልጋል፡፡
23/43
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

﴾‫ك ُه ُم الْ ُم ْفلِ ُحو َن‬ ِ ْ ‫﴿ َولْتَ ُكن ِهمن ُك ْم أ َُّمةٌ يَ ْدعُو َن إِ ََل‬
َ ِ‫اْلَِْْي َو ََيْ ُمُرو َن ِِبلْ َم ْعُروف َويَْن َه ْو َن َع ِن الْ ُمن َك ِر َوأ ُْولَئ‬
“እንደነዚያም ግልጽ ተዓምራት ከመጣላቸው በኋላ እንደተለያዩትና እንደ
ተጨቃጨቁት አትሁኑ፡፡ እነዚያም ለእነርሱ ታላቅ ቅጣት አላቸው፡፡” አል ዒምራን፡

ጥያቄ 12፡- በስራ መጠመድ ምክንያት ሶላትን ወቅቱ ከወጣ በኋላ ነው የምሰግደው፡፡
ይህ ሸሪዓዊ ብይኑ ምንድን ነው?

መልስ 12፡- ሶላትን በወቅቱ መስገድ የግድ ነው፡፡ በመርሳት ወይም በእንቅልፍ
ምክንያት ካልሰገድክ ተሸቀዳድመህ ቀዷ ማውጣት ይኖርብሃል፡፡

የአላህ መልእክተኛ ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

"‫"من نسي صالة فليصل إذا ذكرها ال كفارة لها إال ذلك‬

“ሶለትን የረሳ ሰው ያስታወሰ ጊዜ ይስገድ፡፡ እርሱ እንጅ ሌላ ከፋራ (ማካካሻ)


የለውም፡፡” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

ዋናው ገንዘብህ ሶላትህ ነው፡፡ ከእርሷ ፣ በሌላ ነገር አትጠመድ ወይም አትርሳ፡፡
ይልቁንም ከጀማዓ ጋር በወቅቱ ስገድ፡፡ ወቅቱ ሰፊ ነው ወይም የመሳሰሉ ንግግሮችን
በመናገር የስንፍና በር አትክፈት፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

﴾‫اهو َن‬ ِِ ‫﴿فَويل لهِْلمصلِهني۞الَّ ِذين هم عن‬


ُ ‫ص ًَلِت ْم َس‬
َ َ ُْ َ َ َ ُ ٌ َْ
“ወዩላቸው ለሰጋጆች ፡፡ ለእነዚያ እነርሱ ከስግደታቸው ዘንጊዎች ለሆኑት
(ሰጋጆች)” አል ማኡን ፡
24/43
ጥያቄ 13፡- “የሰለፎች (የቀደምቶች) ጎዳና ሰላማዊ ፤ የኸለፎች (ወደኋላ መጠው
በዲኑ ውስጥ አዳዲስ አመለካከቶችን የጨመሩ ሰዎች) ጎዳና ደግሞ በጣም ጥበበኛ
በጣም አዋቂ ነው” የሚለው አባባል ወደኢማም አንነወውይ ሲያስጠጉት እንሰማለን፡፡
ይህ ምን ያክል ትክክል ነው?

መልስ 13፡- ይህ የነወውይ ንግግር ነው ብየ አልልም፡፡ ይህን አባባል ብዙ ሰው


ይናገረዋል፡፡ አባባሉ ትክክል አይደለም፡፡ የሰለፍ መንሐጅ በጣም ሰላማዊ ፣ በዒልም እና
በጥበብ በጣም የተሞላ ነው፡፡ በእውቀትና በጥበብ የተሞላ ሳይሆን በጣም ሰላማዊ
ሊሆን እንዴት ይችላል? ሰላም የሚገኘው ከእውቀትና ከጥበብ ጋር ነው፡፡ የሰለፍ
መዝሐብ በእውቀት ፣ በጥበብና በሰላም የተሞላ ነው፡፡ ኢብን ረጀብ “ፈድሉ ኢልሚ
ሰለፍ አለል ኸለፍ” የሚባል መጽሐፍ ፤ ሸይኹል ኢስላም “ሀመውያ” በሚባለው
ኪታብ መግቢያ ላይ ይህን ጉዳይ በሰፊው አብራርተዋል፡፡ ሊነበቡ የሚገባቸው
መጽሐፎች ናቸው፡፡

ጥያቄ 14፡- ቡድን አቋቁሞ በእርሱ በኩል ብይን ለማግኘት ሙከራ ማድረግ
ከሰለፍያነት ነው?

መልስ 14፡- ይህ የኢስላም መንሐጅ (ጎዳና) አይደለም፡፡ ሸሪዓዊ ብይን ተግባራዊ


የሚደረገው በዑለሞች ወይም በአህሉል ሀል ወልዓቅድ (ነገሮችን መፍታት መቋጠር
በሚችሉ የሹራ አባሎች) አማካኝነት ቃል ኪዳን በተገባለት ኢማም አማካኝነት ነው፡፡
ህብረተሰቡ ለእውቀት ባለቤቶች ወይም ለአህለል ሀል ወልአቅድ ተከታይ ነው፡፡
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
ِ ‫اْلو‬
﴾‫ف أَ َذاعُواْ بِِه‬ ُ ‫﴿ َوإِ َذا َج‬
ِ
َْْ ‫اءه ْم أ َْمٌر هم َن األ َْم ِن أَ ِو‬
25/43
“ከጸጥታ ወይም ከፍርሃት አንዳች (ወሬ) በመጣላቸውም ጊዜ እርሱን
ያጋንናሉ፡፡” አን ኒሳእ፡

ሁሉም በየስብሰባው በምላሱ የፈለገውን ያመነዥካል ፤ ሁሉም መፍትሄ ነው ብሎ


የሚያስበውን ይሰነዝራል፡፡ ይህ መሆን የለበትም፡፡ ይህ መፍትሄ ሊያመጣ አይችልም፡፡
መፍትሔ የሚመጣው ነገሮች ወደባለቤታቸው ሲመለሱ ነው፡፡

﴾‫ول‬ ُ َّ ‫﴿ َولَ ْو َرُّدوهُ إ ََل‬


ِ ‫الرس‬ ِ

“ወደመልእክተኛው በመለሱት ኖሮ” አን ኒሳእ፡

ረሡል ‫ﷺ‬ በህይዎት ካሉ ወደርሳቸው በመሄድ መድዳኘት ያስፈልጋል፡፡ በህይዎት


ከሌሉ ደግሞ ጉዳያችንን ወደሱናቸው ወይም ሱናቸውን ወደወረሱት የእውቀት
ባለቤቶች መመለስ ይኖርብናል፡፡
ረሡል ‫ ﷺ‬የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

"‫"إن العلماء ورثة األنبياء‬

“ዑለሞች የነብያቶች ወራሽ ናቸው” ቡኻሪ ኪታቡ አል ዒልም ባቡ አልዒልሙ ቀብለል ቀውሊ ወልዓመል ላይ በተዕሊቅ
አስፍረውታል አህመድ፡ አቡዳውድ፡ ቲርሚዚይ፡ ሌሎችም ዘግበውታል

ጉዳዩ መመለስ ያለበት የፖለቲካውን ጉዳይ ወደሚያውቁት ዓሊሞች ነው፡፡ ሸሪዓዊ


ብይኖች ስርዓት አልበኛ ወደሆነ አካል ሳይሆን ወደእውቀት ባለቤቶች ነው መመለስ
ያለበት፡፡ አንገብጋቢ የሆኑ የማህበረሰብ ጉዳዮች መመለስ ያለባቸው ነገሮችን መፍታት
መቋጠር ወደሚችሉት የእውቀት ባለቤቶች ነው መመለስ ያለበት፡፡ ይህ በሁሉም ቦታና
በሁሉም ዘመን የሚሰራ ነው፡፡
ጥያቄ 15፡- እኔ የምሰራው የንግድ ማዕከል ውስጥ ነው፡፡ ጺሜን ማሳደግ እፈልጋለሁ፡፡
26/43
ነገር ግን የድርጅቱ ባለቤት አይስማማም፡፡ ምን ማድረግ አለብኝ?

መልስ 15፡- ስራውን ለባለቤቱ አስረክበህ ሌላ ስራ ፈልግ፡፡ አላሀ በተከበረው ቁርኣናዊ


አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
﴾ ُ ‫ث ََل َُْيتَ ِس‬ َّ ‫﴿ َوَمن يَت َِّق‬
ُ ‫اّللَ ََْي َعل لَّهُ َمََْر ًجا۞ َويَ ْرُزقْهُ ِم ْن َحْي‬
“አላህንም የሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጫን ያደርግለታል፡፡ ከማያስበውም በኩል
ሲሳይን ይሰጠዋል፡፡” አጥ ጦላቅ

ጥያቄ 16፡- የአላህ ወር በመባል የሚታወቀውን ሙሀረም መጾም ሱና ነው?


መልስ 16፡- ከወሩ አብዛኛውን ቀናቶች መጾም ሱና ነው፡፡ የአላህ መልእክተኛ ‫ﷺ‬

የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
"‫"أفضل الصيام بعد رمضان شهر هللا المحرم‬
“ከረመዷን ጾም በኋላ በላጩ የአላህ ወር ሙሀረም ነው፡፡” ሙስሊም፡

ጥያቄ 17፡- ሰለፍይ መንሐጅ የተመሰረተው በኢማም አህመድ ዘመን ከዚያም


በሸይኹል ኢስላም ብን ተይሚያ ፤ ከዚያም በሸይኽ ሙሀመድ ብን አብዱልወሃብ
እንደሆነ አንዳንድ ዓሊሞች ተናግረዋል የሚባለው ወሬ ምን ያክል ትክክል ነው?

መልስ 17፡- ይህ ውሸት ነው፡፡ ኢማም አህመድ I፣ ሸይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያ
I እና ሸይኽ ሙሀመድ ብን አብዱልወሃብ I በሰለፍ መንሐጅ ላይ የነበሩ ሰዎች
ናቸው፡፡ መንሐጅ አስሰለፍን ተከተሉ ፤ ወደመንሐጅ አስሰለፍ ሰዎችን ጥሪ አደረጉ ፤
መንሐጅ አስ’ሰለፍን አብራሩ እንጅ የሰለፎችን መንሐጅ እነርሱ አልመሰረቱትም፡፡
የሰለፍን መንሐጅ ያስቀመጡልን በቁርኣኑ አላህ ፤ በሱናቸው ደግሞ ረሡል ‫ﷺ‬
ናቸው፡፡
27/43
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
ِ ٍ ِ َّ ِ ‫اج ِرين واأل‬
ِ ِ َّ ‫﴿ َو‬
‫َع َّد‬
َ ‫ضواْ َعْنهُ َوأ‬ ‫وهم ِبِِ ْح َسان َّرض َي ه‬
ُ ‫اّللُ َعْن ُه ْم َوَر‬ ُ ُ‫ين اتَّبَ ع‬ َ َ َ ‫السابُِقو َن األ ََّولُو َن م َن الْ ُم َه‬
َ ‫َنصار َوالذ‬
﴾‫ك الْ َف ْوُز الْ َع ِظ ُيم‬ ِ ِ ‫َّات ََت ِري ََتت ها األ َْْنَار خالِ ِد‬
ٍ
َ ‫ين ف َيها أَبَ ًدا َذل‬
َ َ ُ َ َْ ْ ‫ََلُْم َجن‬
“ከስደተኞቹና ከረዳቶቹም ሲሆን የመጀመሪያዎቹ ተቀዳሚዎች እነዚያም በበጎ
ስራ የተከተሏቸው አላህ ከእነሱ ወዷል ከእርሱም ወደዋል ፤ በስሮቻቸውም
ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ነዋሪዎች ሲሆኑ
ለእነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ ይህ ታላቅ እድል ነው፡፡” አት ተውባ፡

ጥያቄ 18፡- የሰለፎችን መንሐጅ መከተል ለሚፈልግ አካል ምን ምክር ይመክራሉ?

መልስ 18፡- የቀደምት ሰለፎችን መንሐጅ (ጎዳና) መከተል የሚፈልግ አካል


የአህለሱና ወልጀማዓህን ዓቂዳ ከእውቀት ባለቤቶች መማር አለበት፡፡ የሰለፍ መንሐጅ
(ጎዳና) ምን እንደሆነ ሳያውቁ “እኔ ሰለፍይ ነኝ” ማለቱ ብቻ በቂ ሊሆን አይችልም፡፡

ጥያቄ 19፡- አንዳንድ ሰዎች ኸዋሪጆችን አስመልክቶ አልይ ባወሩት የሚከተለው ዘገባ
ላይ ተንተርሰው ኸዋሪጆችን ወዳጅ ማድረግ ችግር የለውም ብለው የሚሞግቱ አሉ፡፡
ለዚህ ብዥታ ምን መልስ እንስጣቸው?
"‫"إخواننا بغوا علينا‬
“(ኸዋሪጆች) በእኛ ላይ ወሰን ያለፉ ወንድሞቻችን ናቸው፡፡”

መልስ 19፡- የዓልይ 4 ንግግር ከሰነድ አኳያ ትክክል ከሆነ ፣ ትርጉሙ እነርሱን
ወዳጅ አድርጎ መያዝ ሳይሆን እነርሱ ከሀዲዎች ሳይሆኑ ወሰን ያለፉ አካሎች ናቸው
የሚል ነው፡፡ ኸዋሪጆችን አስመልክቶ ከፊሉ ዑለማ ካፊር ናቸው ይላል፡፡ ከፊሎቹ ደግሞ
ካፊር ሳይሆኑ የተሳሳቱ አመጸኞች ናቸው ይላሉ፡፡
28/43
ጥያቄ 20፡ - መቸ ነው አንድ ሰው የቢድዓ ባለቤት የሚባለው? ለመሆኑ በዘመናችን
ቢድዓ ይኖራልን? እነርሱን ሙብተዲዕ የማለት መብት ይኖረዋልን?

መልስ 20፡- ግለሰቡ በሱና ተቃራኒ ከሆነ ወይም ከሱና ተቃራኒ ከተገበረ ይህ ሰው
ሙብተዲዕ ይባላል፡፡
ረሡል ‫ ﷺ‬የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
"‫"من أحدث في أمرنا هذا ما ليس فيه فهو رد‬
“በዲናችን ውስጥ ከእርሱ የሌለን አዲስ ፈጠራ የፈጠረ እርሱ ተመላሽ ነው፡፡” ቡኻሪ፡
ሙስሊም፡

"‫"من عمل عمال ليس عليه أمرنا فهو رد‬


“የእኛ ትእዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ እርሱ ተመላሽ ነው፡፡” ሙስሊም፡

ቢድዓን ባይፈጥርም ቢድዓን ከተገበረ ሙብተዲዕ ይሆናል፡፡ ከአህለ ሱና መሆን እና


በሱና መስራት የፈለገ ሰው በቅድሚያ ሱና ምን እንደሆነ ማወቅ አለበት፡፡ ቁምነገሩ
“እኔ የሱና ሰው ነኝ” ማለቱ አይደለም፡፡ ሱናን ሳያውቅ ሱንይ መባሉ ትርጉም
የለውም፡፡ የሰለፍ መንሐጅ ሳያውቅ ሰለፍይ መባሉ ትርጉም የለውም፡፡ የግድ የሰለፍ
መንሐጅ ምን እንደሆነ መማር እና በእርሱ መጓዝ አለበት፡፡

ሙብተዲዖችና ጠማማ ቡድኖች በአሁኑ ሰዓት ቁጥራቸው በዝቷል፡፡ በመሆኑም


ሙስሊሞች ከቢድዓና ከተለያዩ አዳዲስ ፈሊጦች ነጻ ለመሆን እንዲሁም የሰለፍን
መንሐጅ አጥብቆ ለመያዝ መማር አለባቸው፡፡

ረሡል ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

‫ وسنة الخلفاء‬،‫ فعليكم بسنتي‬،‫"فإنه من يعش منكم بعدي فسيرى اختالفا كثيرا‬
"‫المهديين الراشدين‬
29/43
“ከእኔ በኋላ የቆየ ሰው በርካታ ልዩነቶችን ይመለከታል፡፡ ሱናየን እንዲሁም ቅን የሆኑ
የተመሩ ምክትሎቸን ሱናም አጥብቃችሁ ያዙ፡፡” አህመድ፡ አቡዳውድ፡ ኢብኑ ማጀህ፡
አድ ዳሪሚይ፡ ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል ሶሂህ አል ጃሚዕ፡

ጥያቄ 21፡- “ኢርሻዱ አጥጧሊቢን” የተባለ የፈኽሩ ዲን አርራዚ ኪታብ ሳነብ


የሚከተለውን አግኝቻለሁ፡፡ ስለዚህ በእርሱ ጉዳይ የሚሰጡን አስተያየት ካለ፡-

“ከሙብተዲዕ ፊቅህ የያዘ አይጎዳውም ፤ ምክንያቱም አቂዳን ከእነርሱ አልያዘምና”

መልስ 21፡- ከሙብተዲዕ ወይም ከጠማሞች እውቀትን እንዳንፈልግና እንዳንይዝ


ያደረገ ጌታ ምስጋና ይገባው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ቀጥ ያሉ የሱና ዑለሞች አሉ፡፡ ዘመናት
ከእነርሱ ባዶ ሆነው አያውቁም፡፡ በመሆኑም እውቀትን ከእነርሱ ልንይዝ ይገባል፡፡

ጥያቄ 22፡- “እኔ ሙስሊም ነኝ ፤ ሰለፍያም ይሁን ሌላ አንጃ መጠጋት አልፈልግም”


የሚል ሰው ንግግሩ ምን ያክል ትክክል ነው?

መልስ 22፡- “እኔ ሙስሊም ነኝ” ቢልም ወደሰለፍ ያልተጠጋ ፣ በሰለፎች ተቃራኒ
እንጅ በሰለፍ መንሐጅ ላይ ሊሆን አይችልም፡፡ ወደሰለፎች መንሐጅ ያለው ቅርበት እና
እርቀት ሊለያይ ይችላል፡፡ ይህን ንግግሩን ሊተው ይገባል፡፡ በቅድሚያ ጠቃሚ እውቀት
ይማር፡፡ የዚህ ማህበረሰብ ቀደምቶች የነበሩበትን አጥብቆ ይያዝ፡፡ ትክክለኛውን ኢስላም
ከሰለፎች መንሐጅ ካልሆነ ከማን ሊይዝ ነው? ያፈነገጠ አፈንግጦ እሳት ውስጥ ነው
የሚገባው፡፡

ጥያቄ 23፡- ከሸሪዓ አይደለም መረጃም የለውም በሚል መንግስት የሚያወጣቸውን


የትራፊክም ይሁን ሌላ ህጎች የሚቃረኑ ሰዎች አሉ፡፡ በዚህ ተግባራቸው በሌሎች ላይ
ብዥታ ስለሚፈጥሩ ህገወጥ ሰዎች የሚሰጡን ምክር ካለ?
30/43
መልስ 23፡- ወንድሜ ሆይ! መሪዎች ለህዝባቸው ጥቅም ሲሉ የሚያበጁት ህግና
ስርዓት ሊኖር እንደሚችል መገንዘብ አለብህ፡፡
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
﴾‫ول َوأ ُْوِِل األ َْم ِر ِمن ُك ْم‬ ِ َّ
َ ‫﴿ َاي أَيُّ َها الذ‬
َ ‫الر ُس‬ ِ ‫َطيعواْ اّلل وأ‬
َّ ْ‫َطيعُوا‬ ِ
َ َ‫ين َآمنُواْ أ ُ ه‬
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ መልእክተኛውንና ከእናንተም
የስልጣን ባለቤቶችን ታዘዙ፡፡” አን ኒሳእ፡

መሪዎች ለትራፊክም ይሁን ለሌላ አገልግሎት የሚውል ለህዝብ ጥቅም ብለው


በሚያወጡት ህግ መስራትና በዚያ ህግ ላይ መጓዝ ግዴታ ነው፡፡ እንዴውም መጠየቅ
ያለበት ራሱ ነው፡፡ “ይህን ስርዓት ለመከልከል ምንድን ነው ማስረጃህ” ሊባል
ይገባዋል፡፡
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ መልእክተኛውንና ከእናንተም
የስልጣን ባለቤቶችን ታዘዙ፡፡” አን ኒሳእ፡

መሪዎች ያወጡት ህግና ስርዓት በውስጡ ወንጀል የለበትም፡፡ እነርሱ ለህዝቡ


በሚያወጡት ህግ ላይ እነርሱን ለመታዘዝና ለእኛም ጥቅም እንዲሁም ከእኛ ላይ
ጉዳትን ለመከላከል ሲባል ተግባራዊ እናደርጋለን ፣ እንጓዝበታለን፡፡ ይህ ስርዓት አላህ
እንድንጠቀምበት ካዘዛቸው ጠቃሚ ሰበቦች መካከል አንዱ ነው፡፡

ጥያቄ 24፡- የምጠይቀው ከሶሪያ ነው በእኛ አገር በተከሰተው ሁከትና ግጭት ዙሪያ
ምን ይመክሩናል?
መልስ 24፡- በፈተና ወቅት ለሁሉም ሙስሊም የምንሰጠው ምክር፡
31/43
አንደኛ፡- በተቻለ አቅም ከሚከሰቱ ፈተናዎች መራቅ ነው፡፡ ሁዘይፋ ብን
አልየማን 4 ፈተና ሲገጥመው ምን ማድረግ እንዳለበት ረሡልን ‫ﷺ‬ ጠይቆ
የሚከተለውን መልስ አግኝቷል፡-

“የሙስሊምን ጀማዓ እና መሪዎቻቸውን አጥብቀህ ያዝ” በማለት ምላሽ

ሰጠውታል፡፡ ሁዘይፋም “ጀማዓና መሪ ባይኖራቸውስ” ብሎ ድጋሜ ጥያቄ


አቀረበላቸው፡፡ “ሁሉንም ቡድን እራቅ ፤ ሞት እስከሚመጣብህ ድረስ የዛፍ ስር
ነክሰህ እንኳ ቢሆን በዚያው (በሐቅ) ለይ ሁን” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

ሁለተኛ፡- በሙስሊሞች መካከል የሚከሰቱ አለመግባባቶችን ፈጥኖ መፍትሄ


መስጠት፡፡
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
﴾‫َصلِ ُحوا بَْي نَ ُه َما‬ َ ‫﴿ َوإِن طَائ َفتَان م َن الْ ُم ْؤمن‬
ْ ‫ني اقْ تَ تَ لُوا فَأ‬
ِِ ِِ ِ

“ከምእመናንም የሆኑ ሁለት ጭፍሮች ቢጋደሉ በመካከላቸው አስታርቁ፡፡”


አል ሑጁራት፡

ጥያቄ 25፡- በመሪዎች ላይ ማፈንገጥ ችግር የለውም የሚል አቋም ያለውና በተለያዩ
የጥመት አንጃዎች ዙሪያ የሚዘባርቅ ሙብተዲዕ ቢያጋጥመኝ ከእርሱ ላይ ዲናዊ
እውቀትን መውሰድ እችላለሁ?

መልስ 25፡- ቀጥ ካሉ ሚዛናዊ ዓሊሞች እንጅ ከእርሱ እውቀትን መቅሰም አይገባም፡፡


ምስጋና ለአላህ የተገባው ነው በአሁኑ ሰዓት ቁጥራቸው እንደቀላል የማይታዩ ቀጥ ያሉ
ዓሊሞች አሉ፡፡ ብትንቀሳቀስ የምትማርበት አታጣም፡፡ ስለዚህ ከእነርሱ እውቀትን
ውሰድ፡፡
32/43
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
ِ ‫﴿وما َكا َن الْمؤِمنو َن لِي ِنفرواْ َكآفَّةً فَلَوَلَ نَ َفر ِمن ُك ِل فِرقٍَة ِمْن هم طَآئَِفةٌ لهِي ت َف َّقهواْ ِِف ال هِدي ِن ولِي‬
‫نذ ُرواْ قَ ْوَم ُه ْم‬َُ ُ ََ ُْ ‫ه ْ ه‬ َ ْ ُ َ ُ ُْ ََ
﴾‫إِ َذا َر َجعُواْ إِلَْي ِه ْم لَ َعلَّ ُه ْم َُْي َذ ُرو َن‬

“ምእምናንም (ከነብዩ ጋር ካልሆነ) በሙሉ ሊወጡ አይገባም፡፡ ከእነሱ ውስጥ


ከየክፍሉ አንዲት ጭፍራ ለምን አትወጣም፡፡ (ሌሎች) ሐይማኖትን እንዲማሩና
ወገኖቻቸው ወደነርሱ በተመለሱ ጊዜ እንዲጠነቀቁ ይገስጹዋቸው ዘንድን (ለምን
አይቀሩም)፡፡ አት ተውባ፡

ጥያቄ 26፡-(በችግር ጊዜ) ወደታላላቆች መመለስ ከመንሐጀ ሰለፍ አንዱ ነው፡፡ ነገር
ግን ከአንዳንድ ታላላቆች ዘንድ ደረቅ የሆነ ባህሪ ይታያል፡፡ በመሆኑም ለመጠየቅ ፣
ከእነርሱ ዘንድ ለመቀመጥ እንፈራለን፡፡ በዚህ ዙሪያ ግዴታችን ምንድን ነው?

መልስ 26፡- ከእውቀት ባለቤቶች ዘንድ መቀመጥ የግድ ነው፡፡ በተለይም ከታላላቅ
የእውቀት ባለቤቶች ዘንድ፡፡ ከእነርሱ እውቀትን መያዝ አስፈላጊ ነው፡፡ ደረቅ ባህሪ
አላቸው በሚል ንግግር ከእነርሱ አትሽሽ፡፡ ይህ የሰይጣን ጉትጎታ ነው፡፡ እንዲህ አይነቱን
ባህሪ መተው አለብህ፡፡ ሐቅን ከፈለግህ አላህ ለአንተ ይገጥምሃል፡፡ ከዑለሞች
በምትይዘው እንድትጠቀም ያደርግሃል፡፡ በእነርሱ መጥፎን ከጠረጠርክ ፤ በአጥባቂነት
ባህሪ ከገለጽካቸው ከእውቀታቸው ትታገዳለህ፡፡ ስለዚህ ዒልማችን በመውሰድ ላይ
ትዕግስት ይኑርህ፡፡ አደብ ግዛ ፤ ከእነርሱ እንድትሸሽ በሚያደርግ ቃል አትግለጻቸው፡፡
ይህ የሰውና የጅን ሰይጣናት ተንኮልና ሴራ ነው፡፡

ጥያቄ 27፡- በመስማትና በመታዘዝ የሰለፎችን መንሐጅ የያዘች ቡድን ነች፡፡ ነገር ግን
ሰዎች ከዑለሞች ንግግር እንዳይሰሙ ታርቃለች፡፡ ከእነርሱ መካከል የዚህን ኡመት
33/43
ሰለፎች ልክ እንደነሸይኹል ኢስላም ብን ተይሚያ የመሳሰሉትን ይተቻሉ፡፡ ለዚህ ምን
አቅጣጫ ይሰጣሉ?

መልስ 27፡- ዑለሞች “ኡሉል ዓምር” በመባል ከሚጠሩት መካከል ናቸው፡፡


ዑለሞችና ዳኞች የሙስሊሞች መሪ ናቸው፡፡
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
﴾‫ول َوأ ُْوِِل األ َْم ِر ِمن ُك ْم‬ ِ َّ
َ ‫﴿ َاي أَيُّ َها الذ‬
َ ‫الر ُس‬ ِ ‫َطيعواْ اّلل وأ‬
َّ ْ‫َطيعُوا‬ ِ
َ َ‫ين َآمنُواْ أ ُ ه‬
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ መልክተኛውንና ከእናንተም የስልጣን
ባለቤቶችን ታዘዙ፡፡” አን ኒሳእ፡

ስለዚህ እነርሱ የሚያዙህን አጥብቀህ ያዝ ፤ እነርሱን አወድስ ፤ ለእነርሱ ዱዓ


አድርግ ፤ እነርሱን የሚተችን አካል ምክር ለግሰው ፤ ለእነርሱ ክብር ተከላከል፡፡
የአላህ መልእክተኛ ‫ﷺ‬ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
"‫"من رد عن عرض أخيه رد هللا عن وجهه النار يوم القيامة‬

“ከወንድሙ ክብር የተከላከለ የቂያማ ቀን ከፊቱ እሳትን አላህ ይከላከልለታል፡፡” አህመድ፡


ቲርሚዚይ፡ ሐዲሱን አልበኒ ሶሂህ ብለውታል ሶሂህ አጅ ጃሚዕ፡

ጥያቄ 28፡- በዓአቂዳ ዙሪያ የሰለፎች መዝሀብ (ጎዳና) የተለያየ ክፍል አለው፡፡
በውስጡ ከሌሎች - ወደኢስላም የተጠጉ - አንጃዎች መንሐጅ ጋር በማነጻጸር
ካልሆነ በቀር መብራራት የሚያስፈልጋቸው በርካታ መንሐጆች አሉት፡፡ በዚህ ዙሪያ ምን
አቅጣጫ ይሰጡናል?

መልስ 28፡- በቅድሚያ ሐቅን ፣ ቀጥሎ ደግሞ ከእርሱ ለመራቅ ያመችህ ዘንድ የሐቅን
ተቃራኒ ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ ሐቅን ማወቅ ብቻውን በቂ አይደለም፡፡አጥብቀህ ለመያዝ
34/43
ሐቅን እወቅ ፤ ከእርሱ ለመራቅ የሐቅን ተቃራኒ እወቅ፡፡ ምስጋና ለአላህ ይገባው ይህን
ሁሉ ከዓቂዳ ኪታቦች ማግኘት ይቻላል፡፡ የሰለፎችን መንሐጅ ታገኛለህ፡፡ ልትርቀው ዘንድ
የሙዕተዚላን ፣ የኸዋሪጅን እና በአጠቃላይ የጠማማ ፊረቆችን መንሐጅ ታገኛለህ፡፡
ተማሪዎች ደረጃ በደረጃ እንዲማሯቸው በዓቂዳ ዙሪያ የተዘጋጁ ትክክለኛ መጽሐፎች
በተለያየ መጠን ተዘጋጅተው ቀርበዋል፡፡ አሳሳቢው እነዚህን የዓቂዳ ኪታቦች ከማን ነው
የምትማረው? የሚለው ነው፡፡

ጥያቄ 29፡- በአሁኑ ሰዓት በሙብተዲዖች ወጥመድ ተጠልፈው ወደቢድዓ ለገቡ


ወጣቶች የሚሰጡት ምክር ካለ?

መልስ 29፡- ለእውቀት ፈላጊዎች የምሰጠው ምክር እውቀትን በቀጥተኛነታቸው ፣


በትክክለኛ ዓቂዳቸውና አላህን በመፍራት ከሚታወቁ ዓሊሞች እንዲቀስሙ ነው፡፡ ይህ
ከሙብተዲዕ እና ጠማማ ከሆኑ ዳዒዎች ነጻ የምትወጣበት የትክክለኛ እውቀት ምንጭ
ነው፡፡

ጥያቄ 30፡ - “ኡዝር ቢልጀህልን” (ባለማወቅ ምክንያት መስጠት) አስመልክቶ


አንዳንድ ዱዓቶች የዳዕዋ መሪዎች የጻፏቸውን ኪታቦች ቅጥፈት ፣ እርስ በርስ
የሚቃረንና የዒልም ድክመት ያለበት ፣ በጥናት ያልተዘጋጀ በማለት ሲተቹ ይደመጣል፡፡
በዚህ ዙሪያ ምን ምክር ይሰጡናል?

መልስ 30፡- “መን ጀሂለ ሸይአን አዳሁ” (አንድን ነገር ካላወቀው ጠላት
ያደርገዋል) እንደሚባለው እነዚህ ሰዎች ከእውቀት ባለቤቶች ስላልተማሩ የዳዕዋ
መሪዎች የጻፏቸውን ኪታቦች ጠንቅቀው ሊያውቁ አልቻሉም፡፡ በቃ በመጽሐፉ ውስጥ
ያለውን ፍሬ ነገር ስላልተገነዘቡት ፣ ከእውቀት ባለቤቶችም ስላልተማሩ መጽሐፎቹ
35/43
ስሜታቸውን ስለተቃረነ ብቻ መተቸት ጀመሩ፡፡

ስለዚህ እንደነዚህ አይነት ትችቶችን ከመናገር ቢቆጠቡ ጥሩ ነው፡፡ ከእውቀት


ባለቤቶች ቀረብ ብለው ይማሩ፡፡ ምስጋና ለአላህ ይገባው መጽሐፎቹ በሰለፎች መንሐጅ
ላይ የተጻፉ ናቸው፡፡ በሰለፎች ኪታቦች ውስጥ የተጣራ እና መልካም ነገር ታገኛለህ፡፡
ስለዚህ ፊታችንን ጥርጣሬን ወደሚነዙ ሰዎች ልናዞር አይገባም፡፡ ኡዝር ቢልጀህል
የሚገኘው ስውር በሆኑና ባልተብራሩ ዲናዊ ጉዳዮች ላይ ነው፡፡ ኡዝር የሚኖረው
እስኪብራራ ድረስ ነው፡፡ የኩፍርና የሽርክ ጉዳዮች በቁርኣን እና በሐዲስ በግልጽ
ተቀምጠዋል፡፡ ቁርኣንን ሱናን እንዲሁም የተለያዩ ሙሓዶራዎችን የሰማ ሰው ምክንያት
አይሰጠውም፡፡ ኡዝር የሚሰጠው ከእውቀት መንደር የተቋረጠ ፣ ጭራሽ ጀሮው
ያልሰማ ፣ እውቀት ያልደረሰው ፣ ከሰዎች ጋር ሳይቀላቀል በማይታወቅ ቦታ የሚኖር
ነው፡፡ በዘመናችን “ኡዝር ቢልጀህል” የሚለውን ንግግር ያለህግና ደንብ ጥቅል በሆነ
ሁኔታ የሚያሰራጩት ከእምነት ጋር ክህደት አይጎዳም የሚሉ የሙርጅዓ አንጃዎች
ናቸው፡፡

ጥያቄ 31፡- እኛ በሙስሊም አገሮች በሚካሄደው ግጭትና ሁከት ተሳታፊ


ባለመሆናችን ልክ መሪዎችን እንደምንደግፍ ፣ ለእነርሱም ዱዓ እንደምናደርግ
በመጠርጠር ከሰዎች ተገልለን የተቀመጥን ሰዎች ነን፡፡ በዚህ ዙሪያ ምን አቅጣጫ
ይሰጡናል?

መልስ 31፡- የምንሰጣችሁ ምክር ለነርሱ ንግግር ቦታ ሳትሰጡ በትክክለኛው መንገድ


ላይ ቀጥ ብላችሁ ተጓዙ የሚል ነው፡፡ እናንተን የተቃረነ አካል አይጎዳችሁም፡፡ “ፊርቀቱ
ናጅያ” ሐቅን አጥብቃ እስከያዘች ድረስ እርሷን የተቃረነ አካል አይጎዳትም፡፡
36/43
ለሰዎች ሀሜትና ትችት ብላችሁ ከያዛችሁት ሐቅ እንዳታፈገፍጉ፡፡ መሪዎችን ሸሪዓዊ
በሆነ መንገድ ከመምከር አላህ እንዲያስተካክላቸው ዱዓ ከማድረግ ወደኋላ አትበሉ፡፡
ምክንየቱም የእነርሱ መስተካከል የኢስላም እና የሙስሊሞች መስተካከል ነው፡፡ ይህ
በእኛ ላይ ያለው የእነርሱ ሐቅ ነው፡፡ እነርሱን መምከር የሰለፉነ ሷሊህ ተግባር ነው፡፡
ዱዓ አለማድረግ ፣ እነርሱን መቃወም ደግሞ የኸዋሪጅ መዝሀብ ነው፡፡

ጥያቄ 32፡- “ሰለፉነ ሷሊህ” የሚለው ግንዛቤ በሶሃቦች ብቻ የተለየ ነው ወይስ


ሶሃቦችን እና ከእነርሱ በኋላ በመልካም የተከተሉ ታብዕይና ታብዕዩ ታብዕይ ይካተታሉ?

መልስ 32፡- ምርጥ ክፍለ ዘመን ያሉ ሰዎችና ከእነርሱ በኋላ የእነርሱን መንገድ
የተከተሉት ሁሉ የሰለፉ ሷሊህ መንሀጅ ላይ ናቸው፡፡

ረሡል ‫ ﷺ‬የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-

"‫ ثم الذين يلونهم‬،‫ ثم الذين يلونهم‬،‫"خيركم قرني‬

“መልካማችሁ የእኔ ክፍለ ዘመን (ሰዎች) ናቸው፡፡ ከዚያም የሚቀጥሉት ፤ ከዚያም


የሚቀጥሉት” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

ጥያቄ 33፡- ሶስት ወር ያልሞላው ሽል በእናቱ ሆድ ውስጥ መቆየቱ ችግር የሚፈጥር


ከሆነ ማስወረድ ይቻላል?

መልስ 33፡- በቅድሚያ ችግር ላይ የሚጥላት መሆኑ በታወቁ ዶክተሮች መረጋገጥና


መፍፈረም ይኖርበታል፡፡ ከዚያ በኋላ ወደፈትዋ ኮሚቴ ይቀርባል፡፡ ከዚያም - አላህ ከሻ
- በእነርሱ በኩል ብይን ይሰጥበታል፡፡

ጥያቄ 34፡- አንዳንድ ጠማማ ቡድኖች የሰለፍ መንሐጅን አጥብቀው የያዙ ሰዎችን
37/43
“ጃሚያ” በሚል ቅጽል ሲጠሩ እንሰማለን፡፡ ለዚህ ምን ምላሽ አለዎት?
መልስ 34፡- በሐቅ ላይ መሆናችሁን ካረጋገጣችሁ የተለያየ ቅጽል ስም እያወጣ
ለሚለጥፍ እና ለሚቃረናችሁ ሰው ቦታ ባትሰጡ ጥሩ ነው፡፡ ቀደምት አህለሱና
ወልጀማዓዎች አስቀያሚ በሆኑ ቅጽል ስሞች ተጠርተዋል፡፡ ነገር ግን በእነርሱ ላይ
ምንም አልጎዳቸውም፡፡ ጉዳቱ የሚመለሰው አዲስ ስም ፈጥሮ በሚለጥፈው ሰው ላይ
ነው፡፡ የሐቅ ባለቤትን ምንም አይጎዳውም፡፡ ጃሚያ ብሎ የተናገረውን ሰው ጠይቁት
የጃሚያ መዝሀብ ምንድን ነው ብላችሁ ጠይቁት፡፡ ለማስበርገግ እና ለማነወር ካልሆነ
በቀር ከእርሱ ዘንድ መልስ አታገኙም፡፡
ጥያቄ 35፡- ሰለፎች በቢድዓ ከታወቀ ሰው እውቀትን ይፈልጉ ነበር?
መልስ 35፡- ሰለፎች እውቀትን ከቀጥተኛነት ባለቤቶች ወይም ከአህለሱና ወልጀማዓህ
እንጅ ከአህለል ቢድዓ አይፈልጉም፡፡ በአሁኑ ሰዓት ምንም አይነት ቢድዓ የሌላባቸውን
ሰዎች ሙብተዲዕ እና የመሳሰሉ ስያሜዎችን የሚለጥፉ ሰዎች በዝተዋል፡፡ ይህን
ድርጊት የሚፈጽሙ ሰዎች አንድም ስለቢድዓ ምንነት የማያውቁ ወይም ልብ ወለድ
ተከታይ ሆኖ ሰዎችን ከትክክለኛው ጎዳና ለማሸሽ የሚፈልግ ሰው ነው፡፡ ተገቢ የሆነ
ግንኙነት ለማድረግ ይመቸን ዘንድ የቢድዓን ምንነት እስከሚያብራሩ ድረስ ፊታችሁን
ወደነዚህ ሰዎች አታዙሩላቸው፡፡
አላሀ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
﴾‫ني‬ ِِ ٍ ِ ِ َّ
َ ‫﴿ َاي أَيُّ َها الذ‬
ٍ ِ ِ
ْ ُ‫ين َآمنُوا إِن َجاء ُك ْم فَاس ٌق بِنَ بَأ فَتَ بَ يَّنُوا أَن تُصيبُوا قَ ْوًما ِبَ َهالَة فَت‬
َ ‫صبِ ُحوا َعلَى َما فَ َع ْلتُ ْم ًَندم‬

“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነገረኛ ወሬን ቢያመጣላችሁ በስህተት ላይ ሆናችሁ


ህዝቦችን እንዳትጎዱና በሰራችሁት ነገር ላይ ተጸጻች እንዳትሆኑ አረጋግጡ፡፡”
አል ሑጁራት፡
38/43
ሳታረጋግጡ ንጹህ የሆኑ ሰዎችን እንዳትጎዱ ወሬው ትክክለኛ መሆኑን አረጋግጡ ማለት
ነው፡፡

ጥያቄ 36፡- አንዳንድ ሰዎች “እውቀትን ፈልግ እንጅ ዑለሞች ስለሙብተዲዕና


ስለተሳሰቱ ሰዎች የተናገሩትን አታስተላልፍ ምክንያቱም ይህ ከጀማሪ ተማሪዎች ጋር
የሚሄድ አይደለም” ይላሉ፡፡ ስለዚህ የእውቀት ባለቤቶች ስለሙብተዲዕ የተናገሩትን
ነቅሎ ማስተላለፍ ይቻላል?

መልስ 36፡-አዎ!የሐቅ ባለቤቶችን መንሐጅ በደንብ ጠንቅቀህ ካወቅህ የቀሰምከውን


እውቀት አሰራጨው ፤ ሰዎችን አስተምር፡፡ ነገር ግን መጀመሪያ መንገድ ላይ ሆነህ
እውቀትህ በደንብ የጠለቀ ካልሆነ በዚህ ጉዳይ አደራ አረጋግጥ ፍጥነት አይኑርህ፡፡

ጥያቄ 37፡- በሐቅ መንገድ ላይ ለመጽናት መንገዱ ምንድን ነው? እንዴት ነው


ተጸጽቶ በትክክለኛ ሁኔታ ወደአላህ መንገድ መመለስ የሚቻለው?
መልስ 37፡- በሐቅ ላይ ለመጽናት መንገዱ የሚከተለው ነው፡-
1. ሐቅን በማወቅ ነው፡፡ ሐቅ የሚታወቀው ደግሞ ጠቃሚ እውቀትን በመማር
ነው ፤
2. ወደቀጥተኛው መንገድ አላህ እንዲመራህና እንዲያጸናህ ዱዓ በማድረግ ፤
3. የሐቅ ባለቤቶችን አለመልቀቅ ፣ አብረሀቸው መቀመጥ እና ጓደኛ ማድረግ
፤ ከአህለል ባጢል ፣ ከአህለል ቢድዓና ከጥመት ባለቤቶች መራቅ ፤
4. ወደሐቅ ጎዳና ዳዕዋ ማድረግ ፤
5. በሚደረስው ችግር ትግስት ማድረግ ፤
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
39/43
﴾‫لص ِْب‬
َّ ‫اص ْوا ِِب‬ ِ ِ َّ ‫اْلنسا َن لَِفي خس ٍر۞إََِّل الَّ ِذين آمنُوا وع ِملُوا ال‬
ِ ِ ِ ْ ‫﴿والْ َع‬
َ ‫اص ْوا ِِب ِْلَِهق َوتَ َو‬
َ ‫صاِلَات َوتَ َو‬ ََ َ َ ُْ َ ْ ‫صر۞إ َّن‬ َ
“በጊዜያቱ እምላለህ ፡፡ ሰው ሁሉ በእርግጥ በከሳራ ውስጥ ነው፡፤ እነዚያ
ያመኑትና መልካሞችን የሰሩት ፣ በእውነትም አደራ የተባባሉት ፣ በመታገስም
አደራ የተባባሉት ብቻ ሲቀሩ፡፤” አል ዓስር፡
40/43
የሙፍቲ አሽ'ሽይኽ ዓብዱል ዓዚዝ ኢብን ዓብዲላህ አሊ'ሽይኽ በሸይኽ ፈውዛን
ትምህርት ላይ የሰጡት ተጨማሪ ማብራሪያ
ምስጋና ለዓለማት ጌታ ለአላህ የተገባው ነው፡፡ የተነባበረ ሶላትና ሰላምታ ደግሞ
በተላቁት ነብይና ሙርሰል ነብዩ ሙሐመድ ‫ﷺ‬ ላይ ይስፈን፡፡
ከዚህ በመቀጠል፡
ትክክለኛ ሰለፍይነት ፡ በአላህ ኪታብ ፣ በሙሐመድ ‫ﷺ‬ ሱና ፣ “የዚህ ማህበረሰብ
ቀደምቶች ሶሃቦችና እነርሱን በመልካም የተከተሉት የተጓዙበት ጎዳና ነው፡፡ ይህ
ሰለፍያነት እውነት መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ ምክንያቱም በቁርዓንና በሱና ላይ
የተመሰረተ ነው፡፡
አላህ የታብዕዮችን ደረጃ ሲገልጽ እንዲህ ይላል፡-
ٍ ‫اج ِرين واألَنصا ِر والَّ ِذين اتَّب عوهم ِبِِحس‬
﴾‫ان‬ ِ ِ ِ َّ ‫﴿و‬
َ ْ ُ ُ َ َ َ َ َ َ ‫الساب ُقو َن األ ََّولُو َن م َن الْ ُم َه‬ َ
“ከስደተኞቹና ከረዳቶችም ሲሆኑ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች እነዚያም በበጎ
ስራ የተከተሏቸው …” አትተውባ፡

እነዚህ በቅን ጎዳና ላይ የነበሩ ዲኑን የመሩ ደጋግ ቀደምቶች ናቸው፡፡


ይህን ሰለፍያ አጥብቆ የያዘ ፤ በእርሷም ላይ የጸና በታላቅና መልካም በሆነ ጎዳና
ላይ ነው፡፡ የተከበሩ ሸይኽ - ሸይኽ ፈውዛን - በዚህ ትምህርታቸው ሰለፍይነት
ዓቂዳንም ፣ ዒባዳንም ፣ ሙዓመላንም (ከሰዎች ጋር የምናደርገው ግንኙነት) ፣
ስነምግባርንም ፣ በአጠቃላይ የዲንና የዱንያ ጉዳዮችን የሚዳስስ መሆኑን ግልጽ
አድርገዋል፡፡ የደጋግ ሰለፎች ጎዳና የተሟላ እና ቀጥ ያለ ነው፡፡
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
﴾‫يت لَ ُك ُم ا ِْل ْسًلَ َم ِدينًا‬ ِ ِ
ُ ‫ت َعلَْي ُك ْم ن ْع َم ِِت َوَرض‬
ِ
ُ ‫﴿الْيَ ْوَم أَ ْك َم ْل‬
ُ ‫ت لَ ُك ْم دينَ ُك ْم َوأَْْتَ ْم‬
41/43
“ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለእናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡
ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ፡፡” አል ማኢዳ፡

ከዚህ ትክክለኛና ቀጥ ያለ ጎዳና ያፈነገጠ ሰው በሰይጣን ይነጠቃል፡፡


አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
َّ ‫السبُ َل فَتَ َفَّر َق بِ ُك ْم َعن َسبِيلِ ِه َذلِ ُك ْم َو‬
‫صا ُكم بِِه لَ َعلَّ ُك ْم‬ ُّ ْ‫يما فَاتَّبِعُوهُ َوَلَ تَتَّبِعُوا‬ ِ ِ ِ َّ ‫﴿ َوأ‬
ً ‫َن َه َذا صَراطي ُم ْستَق‬
﴾‫تَتَّ ُقو َن‬
“ይህም ቀጥተኛ ሲሆን መንገዴ ነው ፤ ተከተሉትም፡፡ (የጥመት) መንገዶችንም
አትከተሉ፡፡ ከ (ቀጥተኛው) መንገዱ እናንተን ይለያዩዋችኋልና፡፡ እነሆ ትጠነቀቁ
ዘንድ በርሱ አዘዛችሁ፡፡” አል አንዓም፡

የአላህ መንገድ ማለት ቁርኣን እና ሱና ፤ የአላህ መንገድ ማለት የዚህ ማህበረሰብ


ቀደምቶች የነበሩበት ማለት ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ያሉ መንገዶች ሁሉ የጥመት መንገዶች
ናቸው፡፡ ከእርሱ ላይ ቆሞ ወደራሱ መንገድ ጥሪ የሚያደርግ ወይም የሚቀሰቅስ ሰይጣን
አለ፡፡
እያንዳንዱ ሙስሊም ቁርኣንና ሐዲስን ፤ የዚህን ማህበረሰብ ደጋግ ቀደምቶች
መንገድ ፣ በደስታና በእምነት ፣ የጥመት ሹብሃዎች በመራቅ እና ይህ መንገድ ሐቅ
የሆነና ምንም አይነት ችግር የሌለበት እንደሆነ አምኖ አጥብቆ መያዝ አለበት፡፡
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
﴾‫ت ِمْن ُه ْم ِِف َش ْي ٍء‬ ِ ِ ِ َّ ِ
َ ‫﴿إ َّن الذ‬
َ ‫ين فَ َّرقُواْ دينَ ُه ْم َوَكانُواْ شيَ ًعا لَّ ْس‬
“እነዚያ ሃይማኖታቸውን የለያዩ አህዛብም የሆኑ በምንም ከእነሱ
አይደለህም፡፡” አል አንዓም፡

‫ين فَ َّرقُوا ِدينَ ُه ْم َوَكانُوا ِشيَ ًعا ُك ُّل‬ ِ َّ‫الص ًَل َة وََل تَ ُكونُوا ِمن الْم ْش ِركِني۞ ِمن ال‬
‫ذ‬ َّ ‫ا‬
‫و‬ ‫يم‬ِ‫﴿منِيبِني إِلَي ِه واتَّ ُقوه وأَق‬
َ َ َ ُ َ َ ُ َُ َ ْ َ ُ
﴾‫ب ِِبَا لَ َديْ ِه ْم فَ ِر ُحو َن‬
ٍ ‫ِحْز‬
42/43
“ወደእነርሱ ተመላሾች ሆናችሁ (የአላህን ሃይማኖት ያዙ)፡፡ ፍሩትም፡፡
ሶለትንም አስተካክላችሁ ስገዱ፡፡ ከአጋሪዎቹም አትሁኑ፡፡ ከእነዚያ
ሃይማኖታቸውን ከለያዩትና ክፍልፍሎችም ከሆኑት (አትሁኑ)፡፡ ህዝብ ሁሉ
እነሱ ዘንድ ባለው ነገር ተደሳቾች ናቸው፡፡” አር ሩም፡

ቁርኣንና ሱና የቅኑ ጎዳና መሰረቶች ናቸው፡፡


አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
ِ
َ ِ‫ض َعن ذ ْك ِري فَِإ َّن لَهُ َمع‬ َ ‫﴿فَإ َّما ََيْتيَ نَّ ُكم هم ِهّن ُه ًدى فَ َم ِن اتَّبَ َع ُه َد‬
ً‫يشة‬ ِ ِ ِ ِ
َ ‫اي فَ ًَل يَض ُّل َوََل يَ ْش َقى۞ َوَم ْن أ َْعَر‬
﴾‫ضن ًكا َوََْن ُشُرهُ يَ ْوَم الْ ِقيَ َام ِة أ َْع َمى‬ َ
“ከእኔም የሆነ መሪ ቢመጣላችሁ መሪየን የተከተለ አይሳሳትም አይቸገርምም፡፡
ከግሳጼየም የዞረ ሰው ለእርሱ ጠባብ ኑሮ አለው፡፡ በትንሳኤም ቀን ዕውር ሆኖ
እንቀሰቅሰዋለን፡፡” ጦሃ፡

እንደነዚህ አይነት አጀንዳዎችና መሰሎቻቸውን የእውቀት ፈላጊዎች ፣ የቅን


መሪዎች ፣ ሊከተሏቸው የሚገቡ አካላት ሲያወሩ በአላህ ፈቃድ ለሙስሊሙ
ህብረተሰብ ትጠቅማለች ፣ ህብረተሰብን ታስገነዝባለች ፣ ቀጥ ያለውን ጎዳና
ታብራራለች፡፡
ሸይኽ - አላህ ለመልካሙ ይግጠማቸውና - ይህ ሰለፍይነት ከተቃራኒዎች በኩል
በርካታ ተቃውሞዎች እንደገጠማት ፤ ደረቅ ፣ (ከጠቃሚ እውቀት) የታገደ እና
የመሳሰሉ መጥፎ ስሞች እንደተለጠፈባት ገልጸዋል፡፡ እንዲህ አይነት ስያሜዎች
ሙስሊሙን ህብረተሰብ ቁርኣንና ሐዲስን አጥብቀው እንዳይዙ ፣ በሰይጣን ጥሪ
እንዲታለል እና እምነቱ እንዲደክም አድርገውታል፡፡ በዚህ የጥመት አመለካከት የተነሳ
ነብዩ ‫ﷺ‬ ስንት ተተችተዋል፡፡
43/43
እብድ ፣ ድግምተኛ ፣ ገጣሚ እና የመሳሰሉት ስያሜዎች ተለጥፎባቸዋል፡፡ ከዚህ
በፊት የነበሩ ነብያቶች በመጥፎ ባህሪያት ተገልጸዋል፡፡ ይህ አልጎዳቸውም፡፡ ሙስሊሞች
በእነዚህ ሰዎች ስያሜ ሊሸወድ አይገባም፡፡ ሰለፉነ ሷሊህ ስንት ተተችተዋል ሀሸውያ
(ፋይዳ ቢስ) ፣ ሙሸቢሐ (አላህን በባህሪያት ከፍጡራን ጋር አመሳሳይ) ፣ ሙጀሲማ
(ለአላህ አካል አድራጊ) እና የመሳሰሉ መጥፎ ስያሜዎች ተለጥፎባቸዋል፡፡
ሙስሊም ፣ የዚህ ማህበረሰብ ቀደምቶች ቁርኣንና ሐዲስን መሰረት ባደረገና ቀጥ
ባለ እውነተኛ ጎዳና የተጓዙ መሆኑን ካረጋገጠ የሰለፎችን መንሐጅ ይወዳል ፣ ደረቱ
ይሰፋል እርካታ ይሰማዋል፡፡
ሼይኽ በመልካም በተናገሩት አላህ ጀዛቸውን ይክፈላቸው ፤ አላህ ለሚወደው
ይግጠማቸው፡፡

‫وصلى الله على نبينا محمد‬


ባህር ዳር በሚገኙ የአህለሱና
መሻይኾች የተቀሩ ጠቃሚ ኪታቦች፣ ከሀገር
ውስጥና ከውጭ በሚመጡ መሻይኾች የተሰጡ
ኮርሶች፣ ሙሓዶራዎች፣ የጁመዓ ኹጥባ፣
በትክክለኛ ማስረጃ የተደገፉ የተለያዩ ኢስላማዊ
መጣጥፎችን የሚከተለውን የቴሌግራም ሊንክ
ጆይን በማድረግ መከታተል ይችላሉ
http://t.me/alateriqilhaq

You might also like