Professional Documents
Culture Documents
" "
" "
ከዚህ በኋላ፡ “አላህ ያለቦታ አለ” የሚለውን አመለካከት በርካታ ሰለፎች እንዳጸድቁት አንድ
አህባሽ አረጋግጦ ሲናገር አደመጥኩ፡፡ ይህም ከዓልይ ብን አቢጧሊብ ፣ ከዓልይ ብን አቢጧሊብ
የልጅ ልጅ ከሆነው ዘይኑል ዓቢዲን ዓልይ ብን አልሁሰይን ብን ዓልይ ብን አቢጧሊብ ፣ ከጀዕፈር
አስሷዲቅ -ጀዕፈር ብን ሙሐመድ ዓልይ ብን አልሁሰይን ብን ዓልይ ብን አቢጧሊብ ፣
ከአቡሀኒፋ ፣ ከሻፍዕይ ፣ ከአህመድ ፣ ከጦበሪ… እንደተገኘ ተናግሯል፡፡
➢ በዚህ ላይ አንድ ሰው ምላሽ ለመስጠት ቆሟል ፣ ይሁን እንጅ ምላሹ ደካማ ምላሽ ሆኖ ነው
ያገኘሁት፡፡ ምክያቱም አህባሹ ወዳወሳው ምንጭ በመመለስ አደገኛ የሆነውን ማምታቻ
ለማፍረስ ሙከራ አላደረገም፡፡ ይልቁንም እነዚህ የተወሱት -አቡሀኒፋ ፣ ሻፍዕይ ፣ አህመድ
፣ ጦበሪና ሌሎችም- ትክክለኛው እምነታቸው ከልቅናው ጋር በሚስማማ ሁኔታ የአላህን
ከዓርሽ በላይ መሆን ፣ እርሱ ከሁሉም በላይ መሆኑን የሚያጸድቁ መሆናቸውን
ከማባብራራት ጋር በሱና መሪዎች ላይ የቀጠፈው ቅጥፈቱ እንዲጋለጥ ፣ ማህይምነቱ ይፋ
እንዲሆን አህባሹ ወዳወሳው ምንጭ መመለስ የግድ ይላል፡፡
ማንቂያዎች
ማንቂያ አንድ፡- ስለነዚህ (የሙስሊም) መሪዎች አህባሹ ያወሳው “አላህ ያለቦታ አለ”
የሚለው ቃል በእውቀት ባለቤቶች መጽሐፎች ውስጥ አይታወቅም፡፡ በውስጧ ከሚገኙ
ማህይምነትና ቅጥፈቶች ማብራሪያ ጋር ወደነርሱ የተጠጉ ቃላቶች ለወደፊት ይወሳሉ፡፡
ማንቂያ ሁለት፡- ሐቅ ፈላጊ ሆይ! በአላህ ባህሪያት ዙሪያ ከቁርኣን እና ከሱና ያልጸደቀ ንግግር
ከመናገር ተጠንቀቅ፡፡
2/25
ኢማም ኢብኑ ተይሚያ የሚከተለውን ተናግሯል፡-“ሰለፎች ከአላህ ባህሪያቶች ፣ ከተግባራቶቹ
ከአላህ ይዘው በሚያጸድቁትና በሚያራቁቱት የቁርኣንን እና የሐዲስን ቃላቶች ይጠብቁ ነበር፡፡
በማጽደቅም ይሁን በማራቆት አዲስ የተፈጠረ ቃላትን አያመጡም፡፡ ይልቁንም ማንኛውም
ትክክለኛ ትርጉም በረሡል ﷺንግግር ውስጥ የተካተተ ነው፡፡ አዳዲስ የተፈጠሩ ቃላቶች ህግና
ስርዓት የላቸውም፡፡ ሁሉም ሰው በእርሷ የሚፈልገው ትርጉም ፣ ሌላው በሚፈልገው ትርጉም
ተቃራኒ ነው፡፡ “ጅስም” (አካል) ፣ “ጅሐት” (አቅጣጫ) ፣ “ሀይዝ” (ለእርሱ ብቻ
የተከለለ ቦታ) የሚሉት ቃላቶች… እንደምሳሌ ይጠቀሳሉ፡፡” መጅሙዕ አል ፈታዋ፡
የቢድዓ ባለቤቶች ይህን ጥቅል ቃል የሚናገሩት ፣ አላህን ከጉድለት እናጸዳለን በሚል በጃሂሉ
ማህበረሰብ ላይ ብዥታን ለመፍጠር ነው፡፡ አህለሱናዎች “ሙጀሲም” ፣ “ሙሸቢህ”
(አመሳሳዮች) ናቸው እያሉ ሰዎች ከእነርሱ እንዲርቁ ለማድረግ በአህለሱናዎች ላይ ይቀጥፋሉ፡፡
“እነርሱ መጽሐፉን ተቃራኒ ናቸው ፣ በመጽሐፉ ውስጥ እርስ በርስ ተወዛጋቢ ናቸው ፣
ከመጽሐፉ ለመለየት የተስማሙ ናቸው ፤ በአላህ ላይ ፣ ስለአላህ ፣ በአላህ ቁርኣን ያለእውቀት
ይናገራሉ፡፡ ከንግግር በሙተሻቢህ ይናገራሉ፡፡
4/25
በእነርሱ ላይ በማምታታት ጃሒሎችን ያታልላሉ፡፡ ከአጥማሚዎች ፈተና በአላህ እንጠበቃለን፡፡”
ኢብን ተይሚያህ ከዚህ በፊት የተወሳውን የአህመድን ንግግር ከወሰደ በኋላ የሚከተለውን
ተናገረ፡-
“ዲሷንያ” በመባል የሚጠሩት ቡድኖች “ሰነውያ” በመባልም ይጠራሉ፡፡ ዓለም በሁለት አምላክ የሚመራ ነው
ብለው ያምናሉ፡፡ የብርሃን አምላክ እና የጨለማ አምላክ፡፡ ማንኛውም መልካም ነገር ከብርሃን አምላክ የሚመጣ
ነው, ማንኛውም መጥፎ ነገር ደግሞ ከጨለማ አምላክ የሚመጣ ነው ብለው ያምናሉ፡፡
6/25
ወደፍልስፍና የዞረ ሰው ዋጋ ነው እንዲባል ነው” ኢብን ዓበዲልበር ፊ አልኢንቲቃእ፡ ገፅ ኸጢብ ፊ ሸረፊ
አስሃቢል ሐዲስ፡ ገፅ አል ፈታዋ አል ኩብራ ሊብን ተይሚያህ፡
َ ِاس َم َرب
﴾ك ْاْل َْعلَى ْ ﴿ َسبِ ِح
“ከሁሉ በላይ የሆነውን ጌታህን ስም አሞግስ” አል አዕላ፡
እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡
“ፈውቂያ” (የአላህ የበላይነት) በግልጽ የተወሳበት ቁርኣናዊ አንቀጾች የሚከተሉት ናቸው፡-
﴾ِ﴿فَ ْو َق ِعبَ ِاده
“እርሱም ከባሮቹ በላይ ሲሆን” አል አንዓም፡
አላህ ከሰማይ በላይ መሆኑ በግልጽ የተነገረበት ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለው ነው፡-
﴾ور ِ ِ ﴿أَأ َِمَتم همن ِِف ال هسماء أَن ََيْ ِسف بِ ُكم اْلَر
ُ ُض فَإذَا ه َي ََت
َ ْ ُ َ َ ُ
“በሰማይ ውስጥ ያለን በእናንተ ላይ ቢደረምስባችሁ ወዲያውም እርሷ የምታረገርግ
ብትሆን ትተማመናላችሁ” አል ሙልክ፡
ዘህብይ የሚከተለውን ተናገረ፡ “አላህ ለእርሷ በተለየ ፣ ከእርሷ በውሰጥ የገባ ሳይሆን ፣
እውቀቱ በሁሉም ቦታ ፣ ከዓርሽ በላይ ፣ ከፍጡሩ ሁሉ በላይ መሆኑን የሚገልጽ መረጃ ቁርኣን ፣
ሱና ፣ የሶሃባ ፣ የታብዕይ ፣ በቅን ጎዳና ላይ ያሉ መሪዎች ኢጅማዕ (ስምምነት) ነው፡፡” ኪታብ
አል ዓርሽ፡
➢ አስደናቂ ታሪክ፡ ኢብን ተይሚያ “ደርእ ተዓሩድ አልዓቅል ወንነቅል” በተባለው ኪታብ
(6/343) የሚከተለውን ተናግሯል ፡ -
“ከአራቋቾች መካከል አንዱ ብርቱ ነገር ካሳሰበው አላህን ሊማጸን ልቡ ወደላይ ያማትራል ፣
ከእኔ ዘንድ ይህን የሚያራቁት ከሸይኾቻቸው መካከል አንድ ሰው ነበር ፣ እርሱ ከእኔ የሆነ ጉዳይ
ፈለገ ፣ ይህን ጉዳይ የማልቃወም መስየ በዚህ መዝሐብ ዙሪያ አናግረው ነበር፡፡ ልቡ
እስከሚጨናነቅ ድረስ የሚፈልገውን ጉዳይ አዘገየሁበት ፣ እጁን እና ራሱን ወደሰማይ በማድረግ
“ያ አሏህ” አለ፡፡ አንተ ይገባሃል እንዴ? እጅህን እና ራስክን ወደላይ ያንጋጠጥክ ፣ አንተ ይህ
8/25
ጉዳይ ይገባሃል እንዴ? ከአንተ በላይ አንድ አካል አለን? አልኩት፡፡ እርሱም “አስተግፊሩሏህ”
አለ፡፡ ለእርሱ ግልጽ የሆነለት ጊዜ ፣ ተፈጥሮውንም የተቃረነ መሆኑ ግልጽ ሲሆንለት ወደዚያ
(ወደሚያስተባብለው ነገር) ተመለሰ፡፡ ይህ አነጋገሩ የተበላሸ መሆኑን ለእርሱ ግልጽ
አደረግኩለት፡፡ ተፈጥሯቸውን ወደሚያረጋግጡ ሙስሊሞች ንግግር ተጸጽቶ ተመለሰ፡፡”
“ዓርሽን ከማውሳት ተወን” ያለው ንግግር ፣ የአላህ ከዓርሽ በላይ መሆኑ በቁርኣን ፣ በሱና እና
በዑለሞች ስምምነት (በኢጅማእ) ተረጋግጧል ለማለት ነው፡፡ “ዑሉው” (ልቅ በሆነ ሁኔታ
ከአንድ ነገር በላይ መሆኑ) ግን በተፈጥሮ ግልጽ ነው፡፡ እምቢተኛ ካልሆነ በቀር እርሱን
የሚቃወም የለም፡፡ ኣሻዒራ ፣ አህባሽ ፣ ጀህምያ እና ሌሎች ቡድኖች ግን የሰው ልጅን ተፈጥሮ
ሊቀይሩ ይሞክራሉ፡፡ ከጥመት እና ከሐቅ ከመዘንበል በአላህ እንጠበቃለን፡፡
“አላህ የት ነው” በማለት ባሪያዋን ጠየቋት፡፡ እርሷም “ከሰማይ በላይ” በማለት ምላሽ ሰጠች፡፡
“እኔ ማን ነኝ” አሏት ፡፡ እርሷም “አንተ የአላህ መልክተኛ ነህ” በማለት ምላሽ ሰጠች፡፡
ረሡልም “ﷺእርሷ ሙእሚን ነችና ነጻ አድርጋት” በማለት ተናገሩ፡፡ ሙስሊም፡
አላህ ከዓርሽ በላይ ለመሆኑ አቡሁረይራ ከረሡል ﷺሰምቶ ያስተላለፈው የተረጋገጠ ትክክለኛ
ሐዲስ ሌላው ማስረጃ ነው፡፡
""لما قضى هللا الخلق كتب في كتابه فهو عنده فوق العرش إن رحمتي غلبت غضبي
“አላህ ፍጥረትን እንደፈጠረ ፣ ከዓርሽ በላይ ከእርሱ ዘንድ ከሚገኘው መጽሐፉ ውስጥ 'እዝነቴ
ቁጣየን አሸነፈች' በማለት ጻፈ፡፡” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡
የሚከተለውን ተናግሯል፡ “ፈጣሪ ከፍጥረቱ የተለየ ለመሆኑና አላህ ከፍጡራኑ ሁሉ በላይ ለመሆኑ
ማስረጃው ዓቅላዊ ፣ ተፈጥሯዊ ሲሆን ስለትርጉሙ አስፈላጊ እውቀት ግዴታ ነው፡፡ ከቁርኣን
10/25
ከሐዲስ የመጡ ማስረጃዎች ደግሞ ወደአንድ ሽ ይቃረባሉ፡፡” አሶዋዒቅ አል ሙርሰላ ፊር ረዲ ዓለል ጀህምየቲ
ወልሙዓጢላ ፡
አህባሹ “አላህ ያለ ቦታ አለ” የሚለውን ንግግር ዓልይ ተናግሮታል በማለት ወደርሱ አስጠግቶታል፡፡
እነዚያ የሌሊት እንጨት ለቃሚዎች ናቸው፡፡ ከእነርሱ ዘንድ የሐዲስ እውቀት ግንዛቤ የላቸውም፡፡
ያለምንም ሰነድ ከአኢማዎች የነቀሉትን ወሬ ፊት ሊዞርለት አይገባም በተለይም በአላህ ባህሪያት
ዙሪያ፡፡
እኔም የሚከተለውን እላለሁ፡ በሰነዱ ዙሪያ ሊታይ የሚገባው ነገር አለ፡፡ ነገር ግን በአህለሱና
ኪታቦች ታዋቂነት አለው፡፡ አህለሱናዎች ከሰዎች በጣም እውነተኛ ፣ ከፍጠራኖች ሁሉ በጣም
ታማኞች ናቸው፡፡ ያለምንም ልጓም እና ማሰሪያ ወሬን ነቅለው በሚያስተላልፉ የቢድዓ ባለቤቶች
ተቃራኒ የሚነቅሉትን ወሬ ከነሰነዷ ምንጩን ጨምረው ያወሳሉ- አላህ ይዘንላቸው፡፡
أخرجه مسلم في مقدمة صحيحة ."اإلسناد من الدين ولوال اإلسناد لقال من شاء ما شاء
“ሰነዶች ከዲን ናቸው፡፡ ሰነዶች ባይኖሩ ማንም ሰው የፈለገውን ይናገር ነበር፡፡” ሙስሊም በሶሂህ
ኪታባቸው መግቢያ ላይ ዘግበውታል
➢ አህባሹ “ኢትሀፍ ሳደቱል ሙትቂን” በሚባለው ኪታብ ውስጥ ዘይኑል ዓቢዲን ዓልይ ብን
አልሁሰይን ብን ዓልይ ብን አቢጧሊብ “አላህ ያለ ቦታ አለ” በማለት ተናግሯል የሚል
ንግግር ወደርሱ አስጠግቷል፡፡
12/25
እኔም እላለሁ፡- “ኢትሀፍ ሳደቱል ሙትቂን” በሚባለው ኪታብ የኪታቡ አዘጋጅ
ከዘይኑል ዓቢዲን ይዞ በሰነድ ረጅም ንግግር ተናገረ፡፡ በውስጡ የሚከተለው ንግግር ይገኝበታል ፡ -
ይህ የዙበይድይ መጽሐፍ “ኢህያኡ ኡሉሙ ዲን” የተባለው የገዛሊ ኪታብ ማብራሪያ ነው፡፡
“ኢህያኡ ኡሉሙ ዲን” የተባለው ኪታብ ደግሞ በሱፍያ ፣ በቢድዓ ፣ የአላህን ባህሪያት
በማራቆት የተሞላ ኪታብ ነው፡፡
“እንደዚህ አይነት ሲወረወር በጃሂልያ ምንድን ነበር የምትሉት?” በማለት ጠየቋቸው፡፡ “አላህና
መልእክተኛው ያውቃሉ በዚህ ሌሊት ታላቅ ሰው ተወለደ ፣ ታላቅ ሰው ሞተ እንል ነበር፡፡” አሉ፡፡
“እርሷ አንድ ሰው ስለሞተ ወይም ህያው ስለሆነ አትወረወርም ፤ ነገር ግን ስሙ የተባረከና ከፍ
ያለው ጌታችን አንድን ነገር የወሰነ ጊዜ የዓርሽ ተሸካሚዎች እርሱን ከጉድለት ያጠሩታል፡፡ ከዚያም
የሰማይ ባለቤቶች ተከትለው ያጠሩታል ፣ ከእነርሱ ለጥቀው ያሉትም ተስቢሁ ከቅርቢቱ ሰማይ
እስኪደርስ ያጠሩታል፡፡ ከዚያም ከዓርሽ ተሸካሚ ለጥቆ ያሉት ፣ ለዓርሽ ተሸካሚዎች “ጌታችሁ
ምን አለ” በማለት ይጠይቋቸዋል፡፡ ምን እንዳለ ይነግሯቸዋል፡፡ ወሬው ከቅርቢቱ ሰማይ እስኪደርስ
ድረስ ከፊሉ የሰማይ ባለቤት ለከፊሉ ወሬ ይጠይቃል፡፡ ወሬን ጅን ይነጥቃል፣ ይዘውት የመጡትን
ሐቅ በሆነው መልኩ ወደወዳጆቻቸው ይጥላሉ፡፡ ነገር ግን እነርሱ ይቀጥፋሉ ፣ ይጨምራሉ፡፡”
ሙስሊም፡
ዘይኑል ዓቢዲን ያወራው ሐዲስ የአላህን የበላይነት ከዓርሽ በላይ ከፍ ማለቱን ይጠቁማል፡፡
አላህ አንድ ነገር ለመወሰን ሲሻ ወደመላኢካዎች ወህይ ያወርዳል ፣ መጀመሪያ የሚሰሙት
14/25
የዓርሽ ተሸካሚ መላኢካዎች ናቸው፡፡ ከዚያም ተስቢሀቸው ዱንያ ሰማይ ወደሚገኙ መላኢካዎች
እስከሚደርስ የመላኢካዎች ተስቢህ ይከታተላል፡፡
ይህ አላህ የበላይ ለመሆኑ ፣ ከዓርሽ በላይ ከፍ ለማለቱ ግልጽ የሆነ ማስረጃ ነው፡፡ ይህን ሐዲስ
ለእኛ ሰምቶ ያስተላለፈልን ደግሞ የአልይ ብን አቢጧሊብ የልጅ ልጅ የሆነው ዘይኑል አቢዲን
ነው፡፡ ይህ ዘገባ በጣም ትክክለኛ በሚባለው ሶሂህ ሙስሊም ኪታብ ከአህለሱናዎች ዘንድ
ይታወቃል፡፡
“’አላህ በሆነ ነገር ውስጥ ነው ወይም የሆነ ነገር ነው ወይም በሆነ ነገር ላይ ነው፡፡’ ያለ
በእርግጥ አሻረከ፡፡ በሆነ ነገር ላይ ነው ከተባለ የሚሸከሙት ነገር ሆነ ፣ በሆነ ነገር ውስጥ ከሆነ
ተከበበ ማለት ነው ፣ አንድ ነገር ከሆነ አዲስ ነገር ሆነ፡፡” አሪሳለቱ አል ቁሸያህ፡
እኔም የሚከተለውን እላለሁ፡ ኢማም አቡሀኒፋ “ፊቅሁል አክበር” በሚባለው ኪታባቸው አላህ
ከዓርሽ በላይ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ እንዴውም አላህ ከዓርሽ በላይ መሆኑን የማያረጋግጥ
አካል ይከፍራል ብለዋል፡፡
በዚህ ከባልደረቦቻቸው ዘንድ በሚታወቀው የአቡሀኒፋ የታወቀ ንግግር፡ ጌታዬ በሰማይ ወይም
በምድር አላውቅም የሚል ዋቂፋ (አቋም የለሽ) የኩፍር ብይን ከተሰጠው ጌታውን በሰማይም
አይደለም ወይም በሰማይም በምድርም አይደለም የሚል አስተባባይ እና አራቋች እንዴት ሊሆን
ነው? አቡሀኒፋ ለክህደቱ ማስረጃ ያደረጉት “ረህማን በዓርሽ ላይ ነው” ፣ “ዓርሹ ከሰባት
ሰማያት በላይ ነው” የሚለውን አምላካዊ ቃል ነው፡፡
በዚህም “ረህማን ከዓርሽ በላይ ነው” የሚለው የአላህ ቃል አላህ ከሰማያት በላይ መሆኑን ፣
ከዓርሽ በላይ መሆኑን ፣ አላህ በነፍሱ ከዓርሽ በላይ መሆኑን ይጠቁማል፡፡ ከዚያም “በዓርሽ በ ላይ
ነው ነገር ግን ዓርሽ በሰማይ ይሁን በምድር መሆኑ ተወቁፍ ያደረገ ካፊር እንደሚሆን አያይዞ
ተናገረ፡፡ ምክንያቱም ከሰማይ ላይ መሆኑን ተቃወመ፡፡ ምክንያቱም አላህ ከኢልይን በላይ ነው፡፡
እርሱ የሚለመነው ከታች ሳይሆን ከላይ ሆኖ ነው፡፡ ይህ አቡሀኒፋ አላህ ከሰማይ መሆኑን
የተቃወመ አካል ካፊር መሆኑን በግልጽ የተናገሩበት ነው፡፡ በዚህ ላይ አላህ ከኢልይን በላይ
17/25
መሆኑን ፣ እንዲሁም እርሱ የሚለመነው ከታች ሳይሆን ከላይ እንደሆነ ማስረጃ አድርገዋል፡፡
እነዚህ ሁለት መረጃዎች ተፈጥሯዊ እና ዓቅላዊ ናቸው፡፡ ልቦች አላህ ከላይ እንደሆነ ፣ ከላይ
እንጅ ከታች እንደማይለመን በማረጋገጥ ላይ ተፈጥረዋል፡፡ በዚህ ላይ በሌላ ቃል በግልጽ
የተናገሩበት እንደሚከተለው መጧል፡፡
“ከሰማይ በላይ መሆኑን ከተቃወመ በእርግጥ ከፈረ” ይህን ቃል ከእርሱ ሰነድ ያወራው ሸይኹል
ኢስላም አቡ ኢስማኢል አልአንሷሪ አልሀረዊይ “ኪታቡል ፋሩቅ” በሚባለው መጽሐፍ ነው፡፡
መጅሙዕ አልፈታዋ ፡
➢ አህባሹ “ኢትሀፍ ሳደቱል ሙትቂን” በሚባለው ኪታብ “አላህ ያለቦታ አለ” የሚለውን
ንግግር ወደኢማም አሽሻፍዒይ አስጠግቷል፡፡
ይህ ከኢማም ሻፍዒይ ሲሆን ሰነዱ ሶሂህ ነው፡፡ ኢጅቲማኡል ጁዩሽ አልኢስላምይ ፡ ተመልከት
" وجمع عليه قلوب عباده،"خالفة أبي بكر رضي هللا عنه حق قضاها هللا في سمائه
19/25
አነስ ብን ማሊክ በትክክለኛ ሐዲስ የሙእሚኖች እናት ዘይነብ የሚከተለውን ንግግር በነብዩ
ﷺሚስቶች ላይ በኩራት ትናገር እንደነበር በሀዲሳቸው አስተላልፈዋል፡፡
(በሰማይ በላይ) በሚለው የሻፍዕይ ንግግር የአላህን የበላይነት ማጽደቅ ነው፡፡ ከልቅናው ጋር
በሚስማማ ሁኔታ የበላይነትን ፣ ከዓርሽ በላይ መሆንን የሚያጸድቅን አካል ዓሻኢራዎች
ያከፍራሉ፡፡ ከአላህ ሰላምን እንለምናለን
ኢማም ሻፍዕይ ካፊር ናቸው? በርካታዎች አሻዒራዎች በመዝሀብ ወደሻፍዒይ ይጠጋሉ፡፡ ነገር
ግን በዓቂዳው ይቃረኑታል፡፡ ከነርሱ መካከል የጥመት ሸይኽ የሆነው ዓብደላህ አልሀረሬ አንዱ
ነው፡፡ የሻፍዕይ መዝሀብ ተከታይ ነኝ ብሎ ይሞግታል፡፡
➢ ኢማም ሻፍዕይ በእርሱ ላይ ማስረጃ ለማድረግ (ነጻ የተደረገችውን) ባሪያ ሀዲስ በመጽሐፉ
ውስጥ አውስቷል፡፡ የአላህ መልእክተኛ “አላህ የት ነው” አሏት፡፡ እርሷም “ከሰማይ በላይ
ነው” አለች…
ሁለተኛው፡- አህባሹ ባወሳው ኪታብ ውስጥ እርሱ ካወሳው ጋር እርስ በበርሱ የሚጋጭ ንግግር
አለው፡፡ እርሱም፡ “አላህ ከተላቀው ዓርሽ በላይ ነው…” ብሎ ይናገር ነበር፡፡ ማለትም -ኢማም
አህመድ፡፡ እንዲሁም (ኢማም አህመድ) የ“ኢስቲዋእን” ትርጉም ዑሉው ፣ እርቲፋእ
“አለል ዓርሽ ኢስተዋ” የሚለውን ደግሞ በእርሱ ላይ የበላይ ሆነ በሚል ተርጉሞታል፡፡ ኢዕቲቃዱ
አልኢማም አልሙበጀል ኢብን ሀንበል፡ ገጽ
አህባሹ ባወሳው ኪታብ ውስጥ ፡ ኢማም አህመድ ለአላህ ሁለት እጆች እንዳሉት ያጸድቃሉ፡፡
እጅ የሚለውን ቃል ሀይል ብሎ የሚተረጉምን አካል አውግዘዋል፡፡ ኢእቲቃዱል አልኢማም አልሙበጀል ኢብን
ሀንበል፡ ገጽ
አሁንም በተወሳው ኪታብ ውስጥ አህመድ የአላህን ንግግር ያጸድቃል፡፡ አጣመው የሚተረጉሙ
አካላትንም ያወግዛል፡፡ ኢዕቲቃዱ ኢማም አልሙበጀል ኢብን ሀንበል፡ ገጽ
ሶሰተኛው፡- የኢማም አህመድ ዓቂዳ የሚወሰደው ከራሱ መጽሐፎች ፣ ከታማኝ ልጆቹ እና ታዋቂ
ሐፊዝ ከሆኑት በዓቂዳቸው ሰላማዊነት በከተማም ይሁን በሰፈር አብረውት ካልተለዩት ባልደረቦቹ
ነው፡፡
ከኢማም አህመድ ታላላቅ ኪታቦቹ መካከል (አርረድ አለል ጀህምያ ወዘናዲቃ) ይገኝበታል፡፡
በዚህ መጽሐፍ ውስጥ (አርረህማን ዓለል አርሽ ኢስተዋ) የሚለውን እና መሰል ቁርኣናዊ
አንቀጾች ጀህም አጣሞ በመተርጎሙ ምለሽ ሰጦታል፡፡ ኢማም አህመድ የአላህን የበላይነት
21/25
የሚጠቁሙ አንቀጾችን እንደሚከተለው አወሳ፡፡ ለምሳሌ፡
﴾ف نَ ِذي ِر ِ ِ ِ
َ ﴿أ َْم أَمَتُم همن ِِف ال هس َماء أَن يُْرس َل َعلَْي ُك ْم َحاصبًا فَ َستَ ْعلَ ُمو َن َكْي
“ወይም በሰማይ ውስጥ ያለን በእናንተ ላይ ጠጠርን ያዘለች ነፋስን ቢልክባችሁ
ትተማማናላችሁ?” አል ሙልክ፡
ِ ِ ِ
ْ َ﴿إِلَْيه ي
ُ ص َع ُد الْ َكل ُم الطهي
﴾ب
“መልካም ንግግር ወደርሱ ይወጣል” ፋጢር፡
ك إِ َه ِ ِ ِ
﴾ل َ يسى إِِّن ُمتَ َوف
َ ُيك َوَرافع ِ
َ ﴿إ ْذ قَ َال اَّللُ ََّي ع
“አላህም ባለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ዒሳ ሆይ! እኔ ወሳጂህ ወደ እኔም አንሺህ ነኝ፡፡”
አል ዒምራን፡
አህመድ የሚከተለውን ተናገረ፡ “እንሆ እርሱ ከሰባት ሰማያት በላይ እንደሆነ የእውቀት
ባለቤቶች ሁሉ አወቁ፡፡” አር ረድ ዓለል ጀህምያ ወዘናዲቃ፡ ገጽ
በአሽዓርይና በአህባሽ መዝሀብ ኢማም አህመድ ካፊር ናቸው፡፡ ምክንያቱም የቢድዓ ባለቤች
በጎደሎ ዓቅላቸው የሚያራቁቱትን ፣ በልብ ወለዳቸው የሚያጣምሙትን ፣ ከልቅናው ጋር
በሚስማማ ሁኔታ የአላህን የበላይነትና ከዓርሽ በላይ መሆን አጽድቋል ፤ ለአላህ ሁለት እጆችን
አጽድቋል ፤ የአላህን ተናጋሪነት አጽድቋል እንዲሁም ሌሎችንም ባህሪያቶች አጽድቋል፡፡
ኸላል የሚከተለውን ተናገረ፡ ዓብዱል መሊክ ብን አብዱል ሁመይድ አልመይሙኒ “አላህ ከዓርሽ
በላይ አይደለም” ስለሚሉ ሰዎች አባአብዲላህ አህመድን ጠየቅሁት፡፡ እርሱም “ንግግራቸው
በሙሉ የሚሽከረከረው በኩፍር ላይ ነው፡፡” አለ ብሎ ነገረኝ፡፡ የኢብን አልቀይም ኢጅቲማኡ አልጁዩሽ
አልኢስላምያ፡ ተመልከት፡፡
እንደዚሁ የሸይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያን ኪታቦች ተመልከት፡፡ ከእነርሱ መካከል “በያን
ተልቢስ አልጀህምያ” እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡
ኸላል ማለት አህመድ ብን ሙሀመድ ብን ሀሩን ብን የዚድ አልኸላል አቡበክር የሚባል ሲሆን የ
“ኪታቡ ሱና” ባለቤት ነው ፤ ሀፊዝ ፣ ፈቂህ ነው፡፡ የሀናቢላዎች ሸይኽ እና ዓሊማቸው ነው፡፡
እርሱ የኢማም አህመድ ብን ሀንበልን እውቀቶች በመሰብሰብ ላይ ትኩረት ከሰጡ ሰዎች
መካከል አንዱ ነበር፡፡ ለእርሷ ሲባል ወደየአገሮች ተጉዟል፡፡ በኢማም አህመድ እውቀቶች
ከሰዎች ሁሉ በጣም አዋቂ ነበር፡፡ ታሪክ አልኢስላም ሊዘህብይ፡ ተመልከት
23/25
(አስሱና ሊልኸላል) የሚባለውን ኪታብ ኢብን ተይሚያ ፣ ኢብን አልቀይም እና ሌሎችም
የኢስላም አኢማዎች ይደገፉበት ነበር፡፡
➢ አህባሹ “አላህ ያለቦታ አለ” የሚለውን ወደኢብን ጀሪር አጦበሪ አስጠግቷል፡፡
እኔም የሚከተለውን እላለሁ፡ ኢብን አልጀሪር አጦበሪ የቋንቋ እና የተፍሲር ኢማም ነው፡፡
ኢስቲዋእን በዑሉው (በበላይነት) እና በኢርቲፋእ (ከፍ በማለት) ተርጉሟል፡፡ ኢስተዋ
“አቅበለ” የሚል ትርጉም አለው ለሚሉ ሰዎች ምላሽ ሰጧል፡፡ የዚህን ሰለፍይ የሆነ ትርጓሜ
በተፍሲር ኪታቡ በተለያዩ ቦታዎች አውስቷል፡፡
አላህ ይዘንለትና (ሱምመ ኢስተዋ ዓለል ዓርሽ) የሚለውን የቁርኣን አንቀጽ “በእርሱ በላይ
ሆነ” በሚል ተርጉሞታል፡፡ ተፍሲር አጦበሪ፡
(አርረህማን ዓለል ዓርሽ ኢስተዋ) የሚለው ንግግሩን በተመለከተ፡ መወሳቱ የላቀው አላህ
የሚከተለውን ይላል፡ “ረህማን ዓለል አርሽ ኢርተፈዓ ፣ ዓላ”፡፡ ተፍሲሩ ጦበሪ፡
ጦበሪ የሚከተለውን ተናገረ፡ (ሁወ መዓኩም አይነማ ኩንቱም)፡ “እናንተ ሰዎች ሆይ!
እናንተን እርሱ በማንኛውም ቦታ ብትሆኑ ይመለከታችኋል፣ ያውቃችኋል፡፡ ስራችሁንም ያውቃል
፣ እንቅስቃሴያችሁንም ፣ መርጊያችሁንም ያውቃል፡፡ እርሱ ከሰባት ሰማያት በላይ ከዓርሽ በላይ
ነው፡፡” ተፍሲር ጦበሪ፡
“ሶሪሁ ሱና” በሚባለው ኪታቡ፡ ገጽ/ ላይ ልክ እንደዚሁ የአላህን ከዓርሽ በላይ መሆን
አጸደቀ፡፡ ይህ ስውር አምታቲታ አህባሽ በሙፈሲሩ ኢብን ጀሪር አጦበሪ ተፍሲር ይስማማል?
ኢብን ጀሪር ሁለት እጆች ለአላህ እንዳሉት ያጸድቃል፡፡ ከልቅናው ጋር በሚስማማ ሁኔታ
ሌሎችንም ባህሪዎች ያጸድቃል፡፡ እርሱ ሙጀሲም ካፊር ነውን?
አቡል ሀሰን አልአሻአርይ የሚከተለውን ተናገረ፡ “አላህ በእርሱ በሚስማማው መልኩ ከአርሽ
በላይ ነው” አልኢባና ዓን ኡሱሊ ዲያና አሽዓርይ ገጽ ፡
ወደኋላ የመጡ አሽዓርዮች በኢባና ኪታብ በአጠቃላይ ተቃራኒዎች ናቸው፡፡ የአላህ የበላይነት ፣
ከአርሽ በላይ መሆን ፣ የንግግር ባህሪ ፣ የእጅ እና ሌሎችም ባህሪያቶች ከአላሀ ጋር በሚስማማ
መልኩ ማጽደቅ በኢባና ኪታብ ውስጥ ይገኛል፡፡
ከኢማም አህመድ ሸይኾች ታላቁ እና አንዱ ሐፊዝ የሆነው የዚድ ብን ሀሩን “ጀህምያ
ማን ነው” የሚለው ጥያቄ ቀረበለት፡፡“ረህማን ከዓርሽ በላይ ነው የሚለውን ፣ ተራው ማህበረሰብ
25/25
በልቡ ከሚያረጋግጠው ተቃራኒ ያለ ሰው ጀህምይ ነው” በማለት ምላሽ ሰጧል፡፡ የቡኻሪ ኪታብ ኸልቁ