Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 70

"‫ال تفرقوا المسلمين باسم "السلفية" و "الصفية‬

‫و "األشاعرة" كلنا مسلمون‬


ሙስሊሞችን “ሰለፍያ” ፣ “ሱፍያ” ፣
“አሻዒራ” በሚሉ ስያሜዎች አትከፋፍሏቸው፡፡
ሁላችንም ሙስሊሞች ነን..

ትርጉሙ ፡ ዩሱፍ አሕመድ


1/68

ከዚህ በኋላ፡
በዚህ ዘመን “አላህ k አሸናፊ በሆነው መጽሐፉ ሙስሊሞች ብሎ ሰይሞናል
በመሆኑም ፣ መከፋፈልን እና መለያየትን በመጣል ሁላችንም ሙስሊሞች ነን
መሰባሰብ አለብን” ወደሚል ሙስሊሞችን ጥሪ ማድረግ ተበራክቷል፡፡ እርሷ ሐሰት
የተፈለገባት ፣ እውነተኛ ቃል ነች፡፡

እወቅ -አላህ ይዘንልህ- በትክክል ሙስሊም ማለት ሳያጋራ አላህን በብቸኛነት


የሚያመልክ ፣ ትክክለኛና የተረጋገጠ የሆነውን የነብዩ ‫ ﷺ‬ሱና የሚከተል ነው፡፡ ነብዩ
‫ ﷺ‬እና ሶሃቦች የነበሩበትን የሚከተል እንጅ በአሏህ k ዲን ላይ አዲስ የሚፈጥር
አይደለም፡፡

አቡ ሁረይራ e የሚከተለውን ተናግሯል፡-

“ነብዩ ‫ ﷺ‬አንድ ቀን በሰዎች መካከል ይፋ ሆኑ፡፡ ጅብሪል ወደርሳቸው መጣ፡፡ “ኢማን


ምንድን ነው?” አላቸው፡፡ “ኢማን፡ በአላህ ፣ በመላኢካዎች ፣ ከእርሱ ጋር በመገናኘት
፣ በመልእክተኞች ልታምን ነው ፤ ሙቶ በመቀስቀስም ልታምን ነው” በማለት ምላሽ
ሰጡ፡፡ “ኢስላም ምንድን ነው?” አላቸው፡፡ “ኢስላም ፡ በእርሱ ሳታጋራ አላህን ልትገዛ
ነው ፣ ሶላትን (ደንቡን ጠብቀህ) ልትሰግድ ነው …” በማለት ምላሽ ሰጡት፡፡ ቡኻሪ፡
ሙስሊም፡
2/68
ሙስሊም የሆነች ነፍስ እንጅ ጀነት እንደማትገባ ነብዩ ‫ ﷺ‬ተናግረዋል፡፡

‫متفق عليه‬ "‫"إنه ال يدخل الجنة إال نفس مسلمة‬


“እንሆ ፣ ሙስሊም ነፍስ እንጅ ጀነት አይገባም፡፡” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

ነብዩ ‫ ﷺ‬የሚከተለውን ለኡመታቸው እንዲናገሩ አላህ አዟል፡-


ِِ ِ ِ ِ ِ ِ ِ ‫﴿إِمَّنَا أ ُِمرت أَ ْن أَعب َد ر م‬
﴾‫ي‬ ُ ‫ب َهذه الْبَ ْل َدة المذي َحمرَم َها َولَهُ ُُ ُّ ََ ٍْْ َوأُمْر‬
َ ‫ت أَ ْن أَ ُُن َن م ََ الْ ُم ْسلم‬ َ ُْ ُْ
“የታዘዝኩት (በውስጧ ደም እንዳይፈስ) ያንን እርም ያደረጋትን የዚህችን
አገር ጌታ እንድግገዛ ብቻ ነው፡፡ ነገሩም ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ ከሙስሊሞችም
እንድሆን ታዝዣለሁ (በላቸው)፡፡” አን ነምል፡

አላህ b የሚከተለውን ተናግሯል፡-


ِ ‫اّلل وال أُ َْ ِرَك بِِه إِلَْي ِه أ َْدعُن وإِلَْي ِه م‬ ِ
ُ ‫﴿قُ ْ ُّ إِمَّنَا أُمْر‬
﴾‫آب‬ َ َ َ َ‫ت أَ ْن أ َْعبُ َد ه‬
“እኔ የታዘዝኩት አላህን ብቻ እንድግገዛ ፣ በእርሱም እንዳላጋራ ነው፡፡ ወደርሱ
እጠራለሁ ፤ መመለሻዬም ወደርሱ ነው” በላቸው፡፡ አር ረዕድ፡

በሁለት ታላላቅ መሰረቶች ካልሆነ በቀር ባሪያው ለአላህ ታዛዥ አይሆንም፡፡


አምልኮን ለአላህ በማጥራትና ረሡልን ‫ ﷺ‬በመከተል፡፡

አላህ b የሚከተለውን ተናግሯል፡-


ِ ‫اح ٌد فَمَ َُا َن ي رجن لَِقاٍ ربِِه فَ ْلي عم ُّ عم اًل ص‬
ِ ‫َل أَمَّنَا إِ ََل ُكم إِلَه و‬
‫نحى إِ َم‬ ِ ِ
‫اِلاا َوَال‬ َ َ َ ْ َ ْ َ ‫َه‬ ُ َْ َ ٌَ ْ ُ َ ُ‫﴿قُ ْ ُّ إمَّنَا أ َََن بَ َشٌر همثْ لُ ُك ْم ي‬
ِِ ِ ِ ِ
﴾‫َح ادا‬ َ ‫يُ ْش ِرْك بعبَ َادة َربهه أ‬
“እኔ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ማለት ወደኔ የሚወረድልኝ
ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ፡፡ የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው ፤ መልካም
ስራን ይስራ ፡፡ በጌታውም መገዛት አንድንም አያጋራ” በላቸው፡፡ አል ከህፍ፡
3/68

አንድነት ፣ መሰባሰብ በሸሪዓ ተፈላጊ ፣ ቁርኣን ፣ ሱና እንዲሁም የዑለሞች ስምምነት


የጠቆመው የኢስላማዊ ዓቂዳ መሰረታዊ ህግ መሆኑ ምንም የሚያጠራጥር አይደለም፡፡
አላህ b የሚከተለውን ቁርኣናዊ አንቀጽ ተናግሯል፡-
َِ ِ‫صمناْ ِِبب ِ ُّ اّلل‬
﴾‫َج ايعا‬ ِ
‫﴿ َو ْاعتَ ُ َْ ه‬
“የአላህንም (የማመን) ገመድ ሁላችሁም ያዙ፡፡” አል ዒምራን፡

ዓብዱላህ ብን መስዑድ e እንደተናገሩት የአላህ ገመድ ማለት የአላህ k ኪታብ


(ቁርኣን) ነው፡፡ ተፍሲር አጥ ጦበሪ ፡

አላህ b የሚከተለውን ቁርኣናዊ አንቀጽ ተናግሯል፡-


﴾‫اب َع ِظ ٌيم‬ ِ ِ ِ‫م‬
َ ِ‫ات َوأ ُْولَئ‬
ٌ ‫ك ََلُْم َع َذ‬ ُ َ‫اٍه ُم الْبَ يِهن‬
ُ ‫اختَ لَ ُفناْ مَ بَ ْعد َما َج‬
ْ ‫يَ تَ َفمرقُناْ َو‬
َ ‫﴿ َوالَ تَ ُكننُناْ َُالذ‬
“እንደነዚያም ግልጽ ተዓምራት ከመጣላቸው በኋላ እንደተለያዩትና እንደ
ተጨቃጨቁት አትሁኑ፡፡ እነዚያም ለእነርሱ ታላቅ ቅጣት አላቸው፡፡” አል ዒምራን፡

﴾‫اّللِ ُُم يُنَ بِهئُ ُهم ِِبَا َُانُناْ يَ ْف َعلُن َن‬ ِ ‫﴿إِ من الم ِذيَ فَ مرقُناْ ِدينَ هم وَُانُناْ َِي عا لمس‬
‫ت مْن ُه ْم ِِف ََ ٍْْ إِمَّنَا أ َْمُرُه ْم إِ ََ ه‬
َ ْ ‫َا‬ َ ُْ َ
“እነዚያ ሃይማኖታቸውን የለያዩ አህዛብም የሆኑ በምንም ከእነሱ አይደለህም፡፡
ነገራቸው ወደአላህ ብቻ ነው፡፡ ከዚያም ይሰሩት የነበሩትን ሁሉ ይነግራቸዋል፡፡”
አል አንዓም፡

ኢማም ኢብን ጀሪር አጥጦበሪ I የሚከተለውን ተናግሯል፡ -


“እንሆ እርሱ እውነተኛ ከሆነው ዲን በመልለየት እንዲሁም እርሱንም በመክፈል
የተለያዩ ቡድኖች ፣ ክፍልፍሎችና አህዛቦች ከሆኑ አካላት ንጹህ እንደሆነ አላህ b
ለነብዩ ‫ ﷺ‬ተናገረ፡፡ እርሱ ከእነርሱ አይደለም ፣ እነርሱም ከእርሱ አይደሉም፡፡
ምክንያቱም አላህ በእርሱ እርሱን የላከበት ዲን እስልምና ነው፡፡ ጌታው በእርሱ
እንደነገረውና እንዳዘዘው ወደእውነት አዘንባይ የሆነው ዲን የኢብራሂም ዲን ነው፡፡
4/68
ِ ِ ِ ِ ِ ِ ِ ِ ِ
َ ُ‫﴿قُ ْ ُّ إِنمِِن َه َد ِاِن َرِهّب إِ ََ صَراط م ْستَقيم ديناا قيَ اما هملمةَ إِبْ َراه َيم َحني افا َوَما َُا َن م ََ الْ ُم ْش ِر‬
﴾‫ي‬
“እኔ ጌታዬ ወደቀጥተኛው መንገድ ትክክለኛን ሃይማኖት ወደ እውነት አዘንባይ
ሲሆን የኢብራሒምን መንገድ መራኝ፡፡ እርሱም ከአጋሪዎቹ አልነበረም” በል፡፡
አል አንዓም ፡

ከሙሽሪክ ፣ ከወሰንይ (ጣዖት አምላኪ) ፣ ከየሁድይ ፣ ከነስራንይ


(ከክርስቲያን) ፣ ወደእውነት ካዘነበለው እና በእርሱ ረሡልን ‫ ﷺ‬የላከበት ከሆነው
ዲን የተለየ ፣ በዲን ውስጥ አዲስ የፈጠረ ፣ ቀጥ ካለው የኢብራሂም መንገድ
የጠመመ ሙብተዲዕ ነው፡፡ እርሱ ከሙሀመድ ሙሀመድም ‫ ﷺ‬ከእርሱ ንጹህ ናቸው፡፡
እርሱ በሚከተለው ጥቅል ንግግር ውስጥ ይካተታል፡-
“እነዚያ ሀይማኖታቸውን የለያዩ አህዛብም የሆኑ በምንም ከእነሱ
አይደለህም፡፡” አንዓም፡ ተፍሲር አጥጦበርይ፡ ጃሚዑል በያን

ሐፊዝ ብን ከሲር I የሚከተለውን ተናግሯል፡-


“ይህ አንቀጽ የአላህን ዲን የተለየ ፣ ለእርሱም ተቃራኒ የሆነ ሁሉ የሚመለከት
አጠቃላይ አንቀጽ ነው፡፡ አላህ b መልክተኛውን ከዲኑ ሁሉ የበላይ ሊያደርገው በቅን ፣
በእውነተኛ ዲን ልኳል፡፡ ሸሪዓቸው እርስ በርሱ የማይጋጭ መከፋፈል የሌለበት አንድ
ዓይነት ሸሪዓ ነው፡፡ በእርሱ ዙሪያ የተለያየ ፣ ጭፍራዎች የሆኑ ማለትም ልክ እንደ
መዝሐቦች ፣ ስሜት ተከታይ ጠማማ ጎዳናዎች ክፍልፍሎች የሆኑ ፣ እነርሱ ካሉበት
ጎዳና ሁሉ አላህ ረሡልን ‫ ﷺ‬ንጹህ አድርጓል፡፡”
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
‫يسى أَ ْن‬ ِ ‫صي نَا بِِه إِب ر ِاهيم ومنسى و‬
‫ع‬ ‫م‬ ‫و‬ ‫ا‬‫م‬ ‫و‬ ‫ك‬ ‫ي‬َ‫ل‬ِ‫صى بِِه نُنحا والم ِذي أَوحْي نَا إ‬
‫م‬ ‫و‬ ‫ا‬‫م‬ َِ ‫ي‬ ِ‫﴿َرع لَ ُكم ِمَ ال ه‬
‫د‬
َ َ َ ُ َ َ َ ْ ْ َ َ َ َ ْ َ ْ َ ‫ا‬ َ َ َ‫ه‬ َ ََ
﴾‫يَ َوَال تَتَ َفمرقُنا فِ ِيه‬
َ
ِ‫أَقِيمنا ال ه‬
‫د‬ ُ
5/68
“ለእናንተ ከሐይማኖት ያንን በእርሱ ኑሕን ያዘዘበትን ደነገገላችሁ፡፡ ያንንም
ወዳንተ ያወረድነውን ያንንም በእርሱ ኢብራሒምን ሙሳንና ዒሳንም
ያዘዝንበትን ሃይማኖትን በትክክል አቋቁሙ በእርሱም አትለያዩ ማለትን
(ደነገግን)፡፡” አሽ ሹራ፡

የአላህ መልእክተኛ ‫ ﷺ‬የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-


‫متفق عليه‬ "‫"أنا أولى الناس بابن مريم األنبياء أوالد عالت وليس بيني وبينه نبي‬
“ለመሬም ልጅ ከሰዎች ተገቢው እኔ ነኝ ፤ ነብያቶች በእናት የሚለያዩ የአንድ አባት ልጆች
ናቸው፡፡ በእኔ እና በእርሱ መካከል ነብይ የለም፡፡” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

ይህ ነው ቀጥተኛው መንገድ፡፡ እርሱም ሩሡሎች በአጠቃላይ የመጡበት አላህን


ምንም ሳያጋሩ በብቸኝነት ማምለክ ፣ መጨረሻ የመጣውን የረሡልን ‫ ﷺ‬ሸሪዓ አጥብቆ
መያዝ ነው፡፡ እርሱን የተቃረነ ጥመት ፣ ማህይምነት ፣ አስተያየትና ዝንባሌን መከተል
ነው፡፡ አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ እንደተናገረው ሩሡሎች ከእንዲህ ዓይነቱ
የጠሩ ንጹሆች ናቸው፡፡
﴾ٍْْ ََ ‫ت ِمْن ُه ْم ِِف‬
َ ‫﴿لم ْس‬
“በምንም ከእነርሱ አይደለህም” አል አንዓም ፡

ነብዩ ‫ ﷺ‬የሚከተለውን ተናግረዋል፡-


)667 ‫أخرجه أحمد وغيره وحسنه األلباني رحمه هللا (الصحيحة‬ "‫"الجماعة رحمة والفرقة عذاب‬
“ጀማዓ እዝነት ነው ፤ መከፋፈል ደግሞ ቅጣት ነው” አህመድ፡ ሐዲሱን አልባኒ ሐሰን
ብለውታል፡ አስ ሶሂህ፡

‫ وال يحل‬، ‫ وكونوا عباد هللا إخوانا‬، ‫ وال تدابروا‬، ‫ وال تحاسدوا‬، ‫"ال تباغضوا‬
‫متفق عليه‬ "‫لمسلم أن يهجر أخاه فوق ثالثة أيام‬
“አትጠላሉ ፣ አትመቀኛኙ ፣ አትዟዟሩ. እናንተ የአላህ ባሮች ሆይ! ወንድማማቾች ሁኑ፡፡
6/68
ለአንድ ሙስሊም ከሶስት ቀን በላይ ወንድሙን ሊያኮርፍ አይገባም፡፡” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

‫متفق عليه‬ "‫"المؤمن للمؤمن كالبنيان يشد بعضه بعضا‬


“ሙእሚን ለሙእሚን ልክ ከፊሉ ከፊሉን እንደሚያጠናክሩ ግንባታዎች ነው፡፡” ቡኻሪ፡
ሙስሊም፡

ሙስሊሞችን በመሰባሰብ ያዘዘ ፣ ከመከፋፈልና ከመለያየት የከለከለ የሆነው ሸሪዓ


ሊታወቅ ይገባዋል፡፡ በምን ላይ ነው መሰባሰቡ? ወደመሰባሰብ የሚያደርሱ ነገሮች
ምንድን ናቸው? የሚሉ ጥያቄዎች ሊዘነጉ አይገባቸውም፡፡ በሸሪዓ ተፈላጊ የሆነው
መሰባሰብ በአላህ ኪታብ ፣ በረሡል ‫ ﷺ‬ሱና እንዲሁም የዚህ ኡመት (ማህበረሰብ)
ቀደምቶች በነበሩበት ላይ መሰባሰብ መሆኑ ፍትሀዊና የሚያገናዝብ ለሆነ ሰው
የሚደበቅ አይደለም፡፡ ይህ ጎዳና ለሙስሊሞች ስብስብ መሰረቱ ፣ በመካከላቸው
የሚያስተሳስራቸው ጠንካራ ገመድና ከጥመት መንገዶች የሚከላከል ነው፡፡

ከእርሱ በቀር በእውነት የሚመለክ በሌለበት አላህ እምላለሁ - ወደአንድነት እና


መሰባሰብ ጥሪ የሚያደርጉ አካላት ቃልን ለመሰብሰብ ፣ በተለያዩ የዓቂዳዎችና
መንሐጆች መካከል ያለውን ክፍተት ለማስተካከል እንዴት እንደሚሞክሩ
ያስገርመኛል? ንቁ! አላህን በአምልኮ ብቸኛ በማድረግ ፣ ሽርክን አሽቀንጥሮ በመጣል
ሰዎችና ጅኖች ለእርሱ ሲባል የተፈጠሩለት ፣ መልእክተኞች የተላኩለት ፣ መጽሐፎች
የወረዱለት ፣ የጀነትና የእሳት ገበያ የተቋቋመለትን ትክክለኛ ተውሂድ -ማለትም
አላህን ሳያጋሩ በብቸኛነት ማምለክ- በማስተማር እና በማሳዎቅ ካልሆነ በቀር እነርሱ
የሚዘምሩለት ሰላም ሊረጋገጥ እንደማይችል ፣ በዱንያም ይሁን በአኼራ የሰዎች
እድለኛነት ሊገኝ እንደማይችል ማወቅ አለባቸው፡፡
7/68

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-


‫يَ ِمَ قَ ْبلِ ِه ْم‬
َ
ِ ‫ض َُما استخلَف الم‬
‫ذ‬ َ ْ َ ْ َ ِ ‫َر‬ْ ‫اْل‬ْ ‫ِف‬ ِ ‫م‬ ‫مه‬
ُ ‫ن‬ ‫ف‬
َ ِ‫ات لَيستخل‬
ْ َ َْ َ
ِ ‫اِل‬ ِ‫ص‬ ‫م‬ ‫ال‬ ‫ا‬
‫ن‬ ‫ل‬
ُ ِ ‫اّلل الم ِذيَ آمنُنا ِمن ُكم وع‬
‫م‬ ََ ْ َ َ ُ‫﴿ َو َع َد م‬
َ‫مهم ِهمَ بَ ْع ِد َخ ْنفِ ِه ْم أ َْمناا يَ ْعبُ ُدونَِِن َال يُ ْش ِرُُن َن ِّب ََْي ئاا َوَم‬ ِ
ُ ‫ضى ََلُْم َولَيُبَ هدلَن‬
ِ ِ ِ
َ َ‫َولَيُ َم هكنَ مَ ََلُْم دينَ ُه ُم المذي ْارت‬
ِ ‫ك هم الْ َف‬
﴾‫اس ُقن َن‬ ِ َ ِ‫َُ َفر ب ع َد َذل‬
ُ ُ َ ‫ك فَأ ُْولَئ‬ َْ َ
“አላህ እነዚያን ከእናንተ ያመኑትንና መልካም ስራዎችን የሰሩትን እነዚያን
ከነርሱ በፊት የነበሩትን እንደተካ በምድር ላይ በእርግጥ ሊተካቸው ፣ ለእነሱም
ያንን የወደደላቸውን ሃይማኖታቸውን ሊያደላድልላቸው ፣ ከፍርሃታቸውም
በኋላ ጸጥታን ሊለውጥላቸው ተስፋን ቃል ሰጥቷቸዋል፡፡ በእኔ ምንንም
የማያጋሩ ሆነው ይግገዙኛል፡፡ ከዚያም በኋላ የካደ ሰው እነዚያ እነርሱ
አመጸኞች ናቸው፡፡” አን ኑር፡

እኔም አልኩ፡ የሙስሊሞችን ቃል ለመሰብሰብ ይህን የቁርኣን አንቀጽ አርማ ያላደረገ


ሰው ወቅቱን ያባክናል ፤ ሊሳካ የማይችልን ምኞት ይመኛል፡፡ አላህን ሳያጋሩ በብቸኛነት
በማምለክ ላይ በመሰባሰብ ላይ ካልሆነ በቀር ጸጥታ ፣ በሁለት አገር ከውርደት ነጻ
ለመሆን ዋስትና የሚሆን ሰላም ሊረጋገጥ አይችልም፡፡
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
‫يسى أَ ْن‬ ِ ‫صي نَا بِِه إِب ر ِاهيم ومنسى و‬
‫ع‬ ‫م‬ ‫و‬ ‫ا‬‫م‬ ‫و‬ ‫ك‬ ‫ي‬َ‫ل‬ِ‫صى بِِه نُنحا والم ِذي أَوحْي نَا إ‬ ‫م‬ ‫و‬ ‫ا‬‫م‬ َِ ‫ي‬ ِ‫﴿َرع لَ ُكم ِمَ ال ه‬
‫د‬
َ َ َ ُ َ َ َ ْ ْ َ َ َ َ ْ َ ْ َ ‫ا‬ َ َ َ‫ه‬ َ ََ
َ‫اّللُ ََْيتَِِب إِلَْي ِه َمَ يَ َشاٍ َويَ ْه ِدي إِلَْي ِه َم‬
‫نه ْم إِلَْي ِه م‬
ُ ُ‫ي َما تَ ْدع‬
ِ ِِ
َ ُ‫يَ َوَال تَتَ َفمرقُنا فيه َُ َُُب َعلَى الْ ُم ْش ِر‬
َ
ِ‫أَقِيمنا ال ه‬
‫د‬ ُ
﴾‫يب‬ِ‫ين‬
ُ ُ
“ለእናንተ ከሃይማኖት ያንን በእርሱ ኑሕን ያዘዝንበትን ደነገገላችሁ፡፡ ያንንም
ወዳንተ ያወረድነውን ያንንም በእርሱ ኢብራሂምን ሙሳንና ዒሳንም
ያዘዝንበትን ሃይማኖትን በትክክል አቋቋሙ በእርሱም አትለያዩ ማለትን
8/68
(ደነገግን)፡፡ በአጋሪዎቹ ላይ ያ ወደርሱ የምትጠራቸው ነገር ከበዳቸው፡፡ አላህ
የሚሻውን ሰው ወደእርሱ (እምነት) ይመርጣል፡፡ የሚመለስንም ሰው ወደርሱ
ይመራል፡፡” አሽ ሹራ፡

ዲንን ቀጥ እንዲያደርጉና በእርሱ ዙሪያ እንዳይከፋፈሉ የመጀመሪያውንም


የመጨረሻዎችንም ትውልድ አላህ አዘዘ፡፡ ይህ ዲን አጠቃላይ መእክተኞችን የላከበት
ዲን ነው፡፡
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
ِ ‫﴿ولََق ْد ب عثْ نَا ِِف ُُ ِ ُّ أُمة مرسنالا أ َِن ْاعب ُدواْ اّلل و‬
َ ُ‫اجتَنبُناْ الطماغ‬
﴾‫نت‬ ْ َ َ‫ُ ه‬ ُ ‫ه‬ ََ َ
“በየህዝቡም ሁሉ ውስጥ “አላህን ተገዙ ፤ ጣዖትንም ራቁ” በማለት
መልክተኛን በእርግጥ ልከናል፡፡” አን ነሕል፡

ِ ‫اعب ُد‬ ِ ِ ِِ ِ ِ ِ َ ِ‫﴿وما أَرس ْلنَا ِمَ قَبل‬


﴾‫ون‬ ُ ْ َ‫ك مَ مر ُسنل إمال نُنحْ إلَْيه أَنمهُ َال إلَهَ إمال أ َََن ف‬ ْ َ ْ ََ
“ከአንተ በፊትም እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና ተገዙኝ በማለት ወደርሱ
የምናወርድለት ቢሆን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡” አል አንቢያ፡

﴾‫ون المر ْْحَ َِ ِآَلَةا يُ ْعبَ ُدو َن‬


ِ ‫ك ِمَ رسلِنَا أَجع ْلنَا ِمَ د‬
ُ ََ ُ
ِ
َ ‫اسأ َْل َم َْ أ َْر َس ْلنَا ِمَ قَ ْبل‬
ْ ‫﴿ َو‬
“ከመልክተኞቻችንም ካንተ በፊት የላክናቸውን (ተከታዮቻቸውን)
ከአልረህማን ሌላ የሚግገዟቸው የሆኑን አማልክት አድርገን እንደ ሆነ
ጠይቃቸው፡፡” አዝ ዙኽሩፍ፡

ከመወዛገብ ፣ ከመከፋፈል ከልክሎ እንድንሰባሰብ ያዘዘን ጌታችን k በመጽሐፉ


ከሸርክ ባለቤቶች ፣ ከቢድዓና ከጥመት ባለቤቶች አስጠንቅቆናል፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣን የሚከተለውን ተናግሯል፡-


‫يَ ِف قُلُنِِِ ْم‬ ِ‫م‬ ِ ِ َ‫ات ُه مَ أُم الْ ِكت‬ ِ َ‫ك الْ ِكت‬ ِ‫م‬
َ ‫ات فَأَما الذ‬
ٌ َِ‫ُخُر ُمتَ َشا‬
َ ‫اب َوأ‬ ٌ ‫ت ُّْم َك َم‬
ٌ ‫آَي‬
َ ُ‫اب مْنه‬
َ َ ‫َنزَل َعلَْي‬
َ‫يأ‬ َ ‫﴿ ُه َن الذ‬
9/68

‫اّللُ َوالمر ِاس ُخن َن ِِف الْعِْل ِم يَ ُقنلُن َن‬ ِِ ِ ِ ِ ِ ِ


‫َزيْ ٌغ فَيَ تمبِعُن َن َما تَ َشابَهَ مْنهُ ابْتغَاٍ الْفْت نَة َوابْتغَاٍ ََتْ ِويله َوَما يَ ْعلَ ُم ََتْ ِويلَهُ إِالم ه‬
﴾‫اب‬ِ ‫ند ربِنَا وما ي مذ مُر إِالم أُولُناْ اْللْب‬ ِ ‫آمنما بِِه ُُ ٌُّّ ِمَ ِع‬
َ ْ ُ َ َ َ ‫َه‬ ْ‫ه‬ َ
“እርሱ ያ በአንተ ላይ መጽሐፉን ያወረደ ነው ፤ ከእርሱ (ከመጽሐፉ) ግልጽ
የሆኑ አንቀጾች አልሉ፡፡ እነርሱ የመጽሐፉ መሰረቶች ናቸው፡፡ ሌሎችም
ተመሳሳዮች አልሉ፡፡ እነዚያማ በልቦቻቸው ውስጥ ጥመት ያለባቸው ሰዎች
ማሳሳትን ለመፈለግና ትችቱን ለመፈለግ ከእርሱ የተመሳሰለውን ይከታተላሉ፡፡
(ትክክለኛ) ትችቱንም አላህ ብቻ እንጅ ሌላ አያውቀውም፡፡ በዕውቀትም
የጠለቁት “በርሱ አምነናል ፤ ሁሉም ከጌታችን ዘንድ ነው” ይላሉ፡፡ የአእምሮ
ባለቤቶችም እንጅ (ሌላው) አይገሰጽም፡፡” አል ዒምራን፡

የአላህ መልእክተኛ ‫ ﷺ‬ይህንን የቁርኣን አንቀጽ ካነበቡ በኋላ የሚከተለውን ተናገሩ፡-


‫متفق عليه‬ "‫ فأولئك الذين سمى هللا فاحذروهم‬، ‫"إذا رأيتم الذين يتبعون ما تشابه منه‬
‫واللفظ لمسلم‬

“ከእርሱ ተመሳሳይ የሆኑትን የሚከተሉ (ሰዎችን) ያየህ ጊዜ እነዚያ እነርሱ አላህ


የሰየማቸው ናቸውና ተጠንቀቋቸው፡፡” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

ቢድዓና አዳዲስ ፈጠራዎች ለመከፋፈል እና ለመለያየት ሰበብ እንደሆነ አላህ


በተከበረው ቁርኣን ተናግሯል፡፡
﴾‫يما فَاتمبِعُنهُ َوالَ تَتمبِعُناْ السبُ َ ُّ فَتَ َفمر ََ بِ ُك ْم َعَ َسبِيلِ ِه‬ ِ ِ ِ
‫﴿ َوأَ من َه َذا صَراطْ ُم ْستَق ا‬
“ይህም ቀጥተኛ ሲሆን መንገዴ ነው ፤ ተከተሉትም፡፡ (የጥመት) መንገዶችንም
አትከተሉ፡፡ ከ(ቀጥተኛው) መንገዱ እናንተን ይለያዩዋችኋልና፡፡” አል አንዓም ፡

ነብዩ ‫ ﷺ‬ሙስሊሞችን በመሰባሰብ ላይ አዘዋል ፣ ከመከፋፈልና ከመለያየት ደግሞ


ከልክለዋል፡፡ በዚህ ላይ ንግግራዊና ተግባራዊ ሱናቸው እንዲሁም ተግባራዊ የሆነው
10/68

ታሪካቸው ይጠቁማል፡፡ የቢድዓ ባለቤቶች ለመከፋፈልና ለመለያየት ምክንያት


በመሆናቸው ከእነርሱ ያስጠነቀቁ እርሳቸው ናቸው፡፡

የአላህ መልእክተኛ ‫ ﷺ‬የሚከተለውን ተናግረዋል፡-


‫ ومن هي‬: ‫"وتفترق أمتي على ثالث وسبعين ملة كلها في النار إال ملة واحدة قالوا‬
)204 ‫حديث صحيح (الصحيحة‬ ) ‫ ما أنا عليه وأصحابي‬: ‫يا رسول هللا قال‬
“ኡመቶች ከሰባ ሶስት መንገድ ይከፋፈላሉ፡፡ አንዷ ብቻ ስትቀር ፣ ሁሏም መንገድ የእሳት
ነች፡፡ “የአላህ መልክተኛ ሆይ ማን ነች?” ብለው ጠየቋቸው፡፡ “በእርሱ ላይ እኔ እና

ሶሃቦቸ ያለንበት መንገድ ነው” በማለት ምላሽ ሰጡ፡፡ አህመድ፡ አቡዳውድ፡ ቲርሚዚይ፡
ኢብኑ ማጀህ፡ ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል፡ አስሶሂህ

ከኸዋሪጆች ቡድን የአላህ መልእክተኛ ‫ ﷺ‬እንደሚከተለው አስጠንቅቀውናል፡ -


“መጨረሻ ዘመን ላይ እድሜያቸው ወጣት ፣ አመለካከታቸው ለጋ ፣ የሰዎች (ሁሉ)
ምርጥ የሆነውን (የረሡልን) ንግግር የሚናገሩ ፣ ቀስት ከመወርወሪያ እንደሚወጣ
ከኢስላም የሚወጡ ሰዎች ይመጣሉ፡፡ እምነታቸው ከጉሮሮ አያልፍም፡፡ በማንኛውም ቦታ
ብታገኙዋቸው ግደሏቸው፡፡ ለሚገላቸው የትንሳኤ ቀን አጅር (ምንዳ) አለው፡፡” ቡኻሪ፡
ሙስሊም፡

አሁንም ስለኸዋሪጆች የሚከተለውን ተናግረዋል፡-


‫أخرجه مسلم‬ "‫"وهم شر الخلق والخليقة‬
“እነርሱ ክፉ አፈጣጠርና ስነምግባር አላቸው፡፡” ሙስሊም፡

አሁንም እነርሱን አስመልክቶ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-


‫أخرجه الترمذي وغيره وصححه‬ "‫"كالب النار شر قتلى تحت أديم السماء خير قتلى من قتلوه‬
)3554 ‫االلباني (المشكاة‬

“የእሳት ውሾች ከሰማይ በታች አሟሟታቸው በጣም የከፋ እነርሱ ናቸው፡፡ እነርሱን
11/68
የገደለ አሟሟቱ በጣም መልካም እርሱ ነው፡፡” አህመድ፡ ቲርሚዚይ፡ ሐዲሱን አልባኒ
ሶሂህ ብለውታል፡ አል ሚሽካት

ነብዩ ‫ ﷺ‬ሙብተዲዕ ሳይኖር በየኹጥባው ሁሉ ከቢድዓና ከጥመቶች ያስጠነቅቁ ነበር፡፡


የሚከተለውን ይናገሩ ነበር፡-
“ከዚህ በኋላ ፡ የንግግሩ ሁሉ መልካሙ የአላህ ኪታብ ነው፡፡ ከመመሪያው ሁሉ
መልካሙ የሙሐመድ መመሪያ ነው፡፡ ከነገሮች ሁሉ ክፉው ፈጠራዎቿ ነው፡፡ ማንኛውም
አዲስ ፈሊጥ ጥመት ነው፡፡” ሙስሊም፡

የክፍፍልና የቢድዓ ባለቤት ተቃራኒ የሆኑት ቀደምት ደጋግ አህለሱና ወልጀማዓዎች


በንግግራቸውም ይሁን በተግባራቸው ወደትስስር ፣ ወደመሰባሰብ ሰዎችን ጥሪ
አድርገዋል፡፡ ከቢድዓና ጥመት ባለቤቶች ደግሞ በማስጠንቀቅ ላይ ተስማምተዋል፡፡

በ449 ሒጅራ አቆጣጠር ላይ የሞቱት ሸይኹል ኢስላም አቡዑስማን አስሷቡኒ I


የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
“ይህ ከመሆኑ ጋር የቢድዓ ባለቤቶችን በንግግር ጫና በመፍጠር ፣ በማዋረድ ፣ ዝቅ
በማድረግ ፣ በማራቅ ፣ በማባረር ፣ ከእነርሱ በመራቅ እነርሱን ጓደኛ ከማድረግ አብሮ
ከመኗኗር በመራቅ እና እነርሱን በመራቅ እና በመተው ወደአላህ በመቃረብ ላይ
ተስማምተዋል፡፡” ሸርህ ዓቂደቲ ሰለፍ ፡

በ516 ሒጅራ አቆጣጠር ላይ የሞተው ሙህዩ ሱናህ አልበገውይ I የሚከተለውን


ተናግሯል፡ -
“ሶሃቦች ፣ ታብዒዮች ፣ የእነርሱም ተከታዮች የቢድዓ ሰዎችን ጠላት በማድረግና
በማኩረፍ ላይ ስምምነት አድርገው አልፈዋል፡፡” ሸርህ አስሱና ሊልበገውይ ፡

ሸይኹል ኢስላም ብን ተይሚያ I የሚከተለውን ተናግረዋል፡-


12/68

“ንግግሮቻቸው ፣ ዒባዳቸው ለኪታብና ለሱና ተቃራኒ የሆኑት የቢድዓ ባለቤቶችን ባህሪ


ግልጽ ማድረግ ፣ ማህበረሰቡን ከእነርሱ ማስጠንቀቅ ግዴታ እንደሆነ
ተስማምተውበታል፡፡ “ካንተ ዘንድ ተወዳጁ የሚጾም ፣ የሚሰግድ ፣ ኢዕቲካፍ
የሚያደርግ ሰው ነው ወይስ ስለቢድዓ ባለቤቶች የሚናገረው?” የሚል ጥያቄ ኢማም
አህመድ ብን ሀንበል I ተጠየቁ፡፡ “አንድ ሰው ቢቆም ፣ ቢሰግድ ፣ ኢእቲካፍ
ቢያደርግ (ጥቅሙ) ለራሱ ነው፡፡ ስለቢድዓ ባለቤት ቢናገር ግን (ጥቅሙ)
ለሙስሊሞች በመሆኑ በላጭ ነው፡፡” የዚህን አጠቃላይ የሆነ ጥቅም ሙስሊሞች
ለዲናቸው በአላህ መንገድ ከሚያደርጉት ትግል ጋር መመሳሰሉን ግልጽ አድርጓል፡፡
ዲንን ፣ መንሐጅን ፣ ሸሪዓን ማጥራት እንዲሁም በዲን ላይ ድንበር መተላለፍን
መከላከል ዋጅቡል ኪፋያ (የተወሰኑ ሰዎች ከሸፈኑት ሌላው የማይጠየቅበት) መሆኑን
ሙስሊሞች ተስማምተዋል፡፡ በኢስላም ላይ የሚመጣውን ጉዳት የሚከላከሉ ሰዎችን
አላህ ባያሰልፍ ኖሮ ዲኑ ይበላሽ ነበር፡፡ ብልሽቱ ጦረኞች (በሙስሊሙ) የበላይ ሆነው
ከሚያበላሹት የከፋ ይሆን ነበር፡፡ እነዚያ (ጦረኞች) ልቦናን በተከታይ ካልሆነ በቀር
ቀድመው አያበላሹም፡፡ እነዚያ ግን (ሙብተዲዖች) ቀልቦችን የሚያበላሹት ቀድመው
ነው፡፡” አልመጅሙዕ ፡

በአህለሱና ወልጀማዓ እና በቢድዓ ፣ በጥመትና በሸር ባለቤቶች መካከል ያለው


ልዩነት ቁርኣን ፣ ሱና እና የዑለሞች ስምምነት የሚጠቁመው በሸሪዓ ዓላማ የተደረገበት
ጉዳይ ነው፡፡ ቁርኣን ፉርቃን ተብሎ እንደሚጠራ አላህ ነግሮናል፡፡

﴾‫ي نَ ِذ ايرا‬ ِ ِ ِ ِِ ِ
َ ‫﴿تَبَ َارَك المذي نَمزَل الْ ُفْرقَا َن َعلَى َعْبده ليَ ُكن َن ل ْل َعالَم‬
“ያ ፉርቃንን በባሪያው ላይ ለዓለማት አስፈራሪ ይሆን ዘንድ ያወረደው
13/68
(አምላክ) ክብርና ጥራት ተገባው፡፡” አል ፉርቃን፡

ኢብን ከሲር I የሚከተለውን ተናግሯል፡-


“በዚህ ምክንያት ከዚህ ቦታ ፉርቃን ብሎ ጠራው ፤ ምክንያቱም ሀቅና ባጢልን ፤ ቅን
ጎዳና እና ጠማማውን ፣ ትክክለኛውን እና የተበላሸውን ፣ ሀላሉን እና ሀራሙን
ይለያል፡፡” ተፍሲር ብን ከሲር ፡

ነብዩ ‫( ﷺ‬በሰዎች መካከል ለይተዋል) ቡኻሪ፡

ረሡል ‫ ﷺ‬ተኝተው እያለ መላኢካ ወደርሳቸው መጦ (የሚከተለውን እንደነገራቸው)


በረጅሙ ሐዲስ ተወስቷል፡፡
‫ ومن عصى محمدا صلى هللا‬، ‫"فمن أطاع محمدا صلى هللا عليه وسلم فقد أطاع هللا‬
"‫ ومحمد صلى هللا عليه وسلم فرق بين الناس‬، ‫عليه وسلم فقد عصى هللا‬
“ሙሐመድን ‫ ﷺ‬የታዘዘ ፣ በእርግጥ አላህን ታዘዘ ፤ ሙሀመድን የነቀፈ ደግሞ አላህን
በእርግጥ ነቀፈ፡፡ ሙሐመድ ‫ ﷺ‬በሰዎች መካከል ከፋፈለ፡፡” ቡኻሪ፡

ሸይኽ አልባኒ I በዚህ ሐዲስ ላይ የሚከተለውን ማብራሪያ ሰጠዋል፡-


“መለያየት በራሱ የተወገዘ እንዳልሆነ ይህ ሐዲስ በግልጽ ይጠቁማል ፡፡ ወደኪታብና
ሱና ጥሪ ሲደረግ እንዲሁም ሁለቱን ከሚቃረኑ አዳዲስ ፈጠራዎች ማስጠንቀቂያ
ሲደረግ አንዳንድ ሰዎች መሸሻቸው ፣ ሰዎችን ትለያያላችሁ ትከፋፍላላችሁ በሚል
አጉል ሙግት ይህ አሁን ወቅቱ አይደለም የሚሉ አባባሎችን መናገሩ በትክክለኛው
ዳዕዋ ላይ ትልቅ ጅህልና ነው፡፡ በየዘመኑ እና በየቦታው የሚስተዋለው ከእርሷ ጋር
ተቆራኝቶ የሚከሰተው ውዝግብ ፣ በእርሷ ዙሪያ ድንበር ማለፍ አላህ በፍጡራኖች
ወስጥ ያደረገው ሱና ነው፡፡ ለአላህ ሱና ደግሞ ቅያር እና መለወጥ አታገኝም፡፡”
14/68

ِِ ِ
َ ‫ماس أُمةا َواح َدةا َوالَ يََزالُن َن مُْتَلف‬
﴾‫ي‬ َ ‫ك ََلََع َ ُّ الن‬
َ ‫﴿ َولَ ْن ََاٍ َرب‬
“ጌታህም ከተሞችን ባለቤቶቻቸው መልካም ሰሪዎች ሆነው ሳሉ በመበደል
የሚያጠፋቸው አልነበረም፡፡” ሁድ፡ አስ ሶሂህ፡

ከመከፋፈልና ከመለያየት ሰበቦች ትልቁ፡ ከዚህ በፊት እንዳሳለፍነው በአላህ ዲን


ላይ አዲስ ፈሊጥ መፍጠር ነው፡፡ እርሱም የመከራውና የተንኮሉ ሁሉ መሰረት ነው፡፡
በረሡል ‫ ﷺ‬ከዚያም በሁለቱ ሸይኾች -አቡበክር እና ዑመር- ዘመን ሙስሊሞች
በአንድ ዓቂዳ እና መንሐጅ ላይ ወንድማማቾች ፣ የሚዋደዱ ፣ የሚተሳሰሩ ነበሩ፡፡
ዑስማን e ከተገደሉ በኋላ ተከታታይ ፈተና ተከሰተ ፣ የዝንባሌ የቢድዓ ቡድኖች
አዳዲስ ፈጠራዎችን እና ሙስሊሙን መከፋፈል ጀመሩ…. የቢድዓ ባለቤቶች
የመከፋፈልና የመለያየት ባለቤቶች ናቸው፡፡ ወደአህለሱና ወልጀማዓህ መንሐጅ
የመመለስ ግዴታ አለባቸው፡፡

ሻጢቢይ I የሚከተለውን ተናግሯል፡-


‫(اإلعتصام‬ "‫"ونحن مأمورون بمعاداتهم وهم مأمورون بمواالتنا والرجوع إلى الجماعة‬
)1/159(

“እኛ እነርሱን ጠላት በማድረግ ላይ ታዘናል ፣ እነርሱ ደግሞ ወደጀማዓ በመመለስ


እኛን ወዳጅ አድርገው እንዲይዙ ታዘዋል፡፡” አል ኢዕቲሷም

ልዩነትና መከፋፈል ላይ ከሚጥሉ ነገሮች አንዱ ዝንባሌን መከተል ነው፡፡ ዝንባሌን


መከተል የዓቅልን ብርሃን ያጠፋል ፣ የልብን እይታ ያውራል ፣ ከቀጥተኛው መንገድ
ያጠማል፡፡ በዚህ ምክንያት ከእርሱ ማስጠንቀቅ በቁርኣን እና በሱና በበርካታ ቦታዎች
መጧል፡፡
15/68

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጾች የሚከተለውን ተናግሯል፡-


َ‫ص ِرهِ ِغ َش َاوةا فَ َم‬ ِ ِِ ِ
َ َ‫اّللُ َعلَى ع ْلم َو َختَ َم َعلَى ََسْعه َوقَ ْلبِه َو َج َع َ ُّ َعلَى ب‬ َ ‫ت َم َِ ماَّتَ َذ إِ ََلَهُ َه َناهُ َوأ‬
‫َضلمهُ م‬ َ ْ‫﴿أَفَ َرأَي‬
﴾‫اّللِ أَفَ ًَل تَ َذ مُُرو َن‬
‫يَ ْه ِد ِيه ِمَ بَ ْع ِد م‬
“ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ፣ አላህም ከዕውቀት ጋር ያጠመመውን
፣ በጆሮውና በልቡ ላይም ያተመበትን ፣ በዓይኑም ላይ ሺፋን ያደረገበትን ሰው
አየህን! ታዲያ ከአላህ በኋላ የሚያቀናው ማነው? አትገሰጹም?” አል ጃሲያ፡

ቀደምት ደጋግ የአላህ ባሮች የቢድዓ ባለቤቶችን፡ አህለል አህዋ (የዝንባሌ


ባለቤት) ብለው ይጠሯቸው ነበር፡፡
ኢብን ተይሚያ I የሚከተለውን ተናግሯል፡-
“… በዲን ምክንያት ከሸሪዓ ያፈነገጡትን ሁሉ ሰለፎች አህለል አህዋ (የዝንባሌ
ባለቤት) ብለው ይቆጥሯቸው ነበር፡፡ የቢድዓ ባለቤቶችን አህለል አህዋ (ዝንባሌ
ተከታይ) ያደርጓቸዋል፡፡” አል ኢስቲቃማ ፡

ኢብን አልቀይም I የሚከተለውን ተናግሯል፡-


“ዝንባሌን መከተል የልብን አይን ያውራል ፣ በሱና እና በቢድዓ መካከል ያለውን
ልዩነት መለየት አይችልም ወይም በተቃራኒው ቢድዓውን ሱና ሱናውን ቢድዓ አድርጎ
ይመለከታል፡፡ ይህ ዑለሞች ዱንያን በመረጡ ጊዜ ፣ መሪነትንና ስሜትን በተከተሉ ጊዜ
የሚከሰት አደጋ ነው ….” አልፈዋኢድ ሊብን አልቀይም፡ ገጽ

የሚከተለውን ተናገረ ፡ “አላህ b የዝንባሌ ባለቤቶችን በቅርጽም ይሁን በትርጉም


ወራዳ ከሆኑ እንስሳዎች ጋር አመሳስሏቸዋል፡፡
አንዳንድ ጊዜ ከውሻ ጋር ያመሳስላቸዋል፡፡ አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ
የሚከተውን ተናግሯል፡-
16/68

ْ ‫ب إِن ََْت ِم ْ ُّ َعلَْي ِه يَ ْل َه‬


﴾‫ث أَْو تَُُْْْهُ يَ ْل َهث‬ ِ ‫ض واتمبَ َع َهناهُ فَمثَلُهُ َُمثَ ِ ُّ الْ َك ْل‬
َ َ َ
ِ ْ ‫﴿ولَ ِكنمهُ أ‬
َ ِ ‫َخلَ َد إ ََ اْل َْر‬ َ
“እርሱ ግን ወደ ምድር ተዘነበለ፡፡ ፍላጎቱንም ተከተለ፡፡ ብጤውም ብታባርረው
ምላሱን አውጥቶ የሚያለከልክ ወይም ብትተወው ምላሱን አውጥቶ
የሚያለከልክ እንደሆነ ውሻ ነው፡፡” አል አዕራፍ፡

አንዳንድ ጊዜ በአህያ ያመሳስለዋል፡፡ አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን


ተናግሯል፡-
﴾‫ت ِمَ قَ ْس َنَرة‬ ِ
ْ ‫﴿ َُأَ مَّنُْم ُْحٌُر م ْستَنفَرةٌ۞فَ مر‬
“እነርሱ ልክ ደንባሪዎች የሜዳ አሕዮች ይመስላሉ፡፡ ከአንበሳ የሸሸ፡፡” ሙደሲር፡

ቅርጻቸውን አንዳንድ ጊዜ ወደዝንጀሮና ከርከሮ ይቀይራቸዋል፡፡


የሚከተለውን ተናገረ፡ “ዝንባሌውን የሚከተል ሰው ሊታዘዙት ፣ ኢማም ሊያደርጉት ፣
ሊከተሉት የሚገባ ሰው አይደለም፡፡ አላህ b ከኢማምነት አንስቶታል፡፡ የእርሱ ታዛዥ
ከመሆን ከልክሏል፡፡ ከስልጣን መወገዱን በተመለከተ አላህ ወዳጁ ለሆነው ኢብራሂም
d የሚከተለውን ተናግሯል፡-
ِِ ِ ُ ‫ال الَ ي ن‬
ََ َ َ‫ال َوِمَ ذُهِريمِِت ق‬ ِ ‫ك لِلن‬
َ َ‫ماس إِ َم ااما ق‬ ِ ‫ال إِِِن ج‬
َ ‫ال َع ْهدي الظمالم‬
﴾‫ي‬ َ ُ‫اعل‬ َ ‫﴿قَ َ ه‬
“እኔ ለሰዎች መሪ አድራጊህ ነኝ” አለው፡፡ “ከዘሮቼም (አድርግ) አለ፡፡ ቃል
ኪዳኔ በዳዮቹን አያገኝም አለው፡፡” አል በቀራ፡

በዳይ የሆነ ሰው በኢማምነት የእኔን ቃል ኪዳን አያገኝም፡፡ ዝንባሌውን የተከተለ ሁሉ


በዳይ ነው፡፡
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
﴾‫﴿ َوَال تُ ِط ْع َم َْ أَ ْغ َف ْلنَا قَ ْلبَهُ َعَ ِذ ُْ ِرََن َواتمبَ َع َه َناهُ َوَُا َن أ َْمُرهُ فُ ُرطاا‬
17/68

“ልቡንም እኛን ከማስታወስ ያዘነጋነውን ፍላጎቱንም የተከተለውን ነገሩንም ሁሉ


ወሰን ማለፍ የሆነውን ሰው አትታዘዝ፡፡” (አል’ከሕፍ፡ 28)
የሚከተለውን ተናገረ፡ “አላህ ዝንባሌ የሚከተሉትን ሰዎች በሁለት ቦታ ላይ ልክ
በጣዖት ተገዥ ደረጃ አድርጓቸዋል፡፡
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
﴾ُ‫ت َم َِ ماَّتَ َذ إِ ََلَهُ َه َناه‬
َ ْ‫﴿أ ََرأَي‬
“ፍላጎቱን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ሰው አየህን?” አል’ፉርቃን፡ 43)

የሚከተለውን ተናገረ፡- “ዝንባሌን መከተል ከባሪያው ላይ የተውፊቅን (ወደሀቅ


መመራትን) በሮች ዘግቶ የሹብሃ (የብዥታ) በሮችን ይከፍታል፡፡ “ለዚህ ነገር
ብግገጠም ኖሮ እንዲህ እንዲህ … ይሆን ነበር” ሲል ትመለከተዋለህ፡፡ ዝንባሌን
በመከተሉ የተውፊቅን (ወደሐቅ የመመራት) ጎዳናን በነፍሱ ላይ እርም አድርጓል፡፡”
ፉዶይል ብን ዒያድ I የሚከተለውን ተናግሯል፡-
"‫"من استحوذ عليه الهوى واتباع الشهوات انقطعت عنه موارد التوفيق‬
“ዝንባሌ እና ስሜቶችን መከተል የበላይ ሆኖ የተቆጣጠረው ሰው የተውፊቅ
መስመሮች ሁሉ ከእርሱ ላይ ይቋረጣሉ፡፡”
በስፋት ለመመልከት የፈለገ “ረውዶቱል ሙሂቢን ወኑዝሐቱል ሙሽታቂን” ገጽ 475
እና ከእርሱ በኋላ የሚገኙትን ገጾች ይመልከት፡፡

አንድ ሰው በዓቂዳ እንዲሁም በአላህ እምነት ዋና መሰረቶች ላይ ተቃራኒ ከሆነ


ሰው ጋር እንዴት በአንድ ላይ ሊሰባሰቡ ይችላሉ? አላህን በብቸኛነት ሳያጋራ የሚግገዛ
ሰው እና በአላህ የሚያሻርክ ፣ በወልዮች ፣ በሷሊሆች በመቃብር የሚማጸን ሰው
18/68

በአንድ ላይ እንዴት ሊሰባሰቡ ይችላሉ? በንግግራቸው ፣ በተግባራቸው እና አይተው


ባጸደቋቸው ነገሮች ሁሉ ረሡልን ‫ ﷺ‬የሚከተል ሰው እና በአላህ ዲን ላይ አዳዲስ
ፈጠራዎችን የሚፈጥር ሰው እንዴት በአንድ ላይ ሊሰባሰቡ ይችላሉ? የአላህን ባህሪያት
ከአላህ ጋር በሚስማማ ሁኔታ የሚያጸድቁ ሰለፍዮች እና የአላህን ባህሪያት የሚያራቁቱ
፣ የሚያጣምሙ ፣ የአላህን ባህሪያት በሚስማማ ሁኔታ የሚያጸድቁ ሰዎችን የሚያከፍሩ
ሰዎች ጋር እንዴት በአንድ ላይ ሊሰባሰቡ ይችላሉ? ሶሃቦችን የሚሳደብ እና ሶሃቦችን
የሚወዱ በሁሉም ሶሃቦች ላይ አላህ ይውደዳቸው ብለው ዱዓ የሚያደርጉ ሰዎች
እንዴት በአንድ ላይ ሊሰባሰቡ ይችላሉ? ይህ እብለት ነው፡፡ ከሰላማዊ ተፈጥሮ እና
ከተረጋገጡ የቁርኣንና የሐዲስ ማስረጃዎች ጋር የሚጋጭ ነው፡፡

ነብዩ ‫ ﷺ‬የሚከተለውን ሐዲስ ተናገረዋል፡-


"‫"األرواح جنود مجندة فما تعارف منها ائتلف وما تناكر منها اختلف‬
“ነፍሶች የተሰባሰቡ ጀማዓዎች ናቸው፡፡ ከእርሷ የተዋወቀ ይግባባል ፤ ከእርሷ የተኮራረፈ
ይወዛገባል፡፡” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

የኢኽዋነል ሙስሊሚን ዳዕዋ ግልጽ ነው፡፡ የተመሰረተው “ሰብስብ ከዚያም


አስተምር” በሚል መርሆ ላይ ነው፡፡ ለዚህ ነው በእነርሱ ሶፍ መካከል ራፊዲይ ፣ ሱፍይ
፣ ቁቡርይ እና ሌሎችም የዝንባሌ እና የጥመት ባለቤቶችን የምናገኘው፡፡

ኢማም አልባኒ I የሚከተለውን ተናግረዋል፡-


“ብዙ ጊዜ እናገረዋለሁ ፡ በረጅም ዘመን ልምዴ እንደተገነዘብኩት የኢኽዋን
አልሙስሊሙን ዳዕዋ በሁለት ቃላቶች ላይ የቆመ ነው፡፡ “ሰብስብ ከዚያም አስተምር”
ማለትም ሰዎችን ሰብስብና (በእውቀት) አንጻቸው የሚል ነው፡፡
19/68

የእኛ ዳዕዋ የረሡል ‫ ﷺ‬ዳዕዋ ነው፡፡ “አስተምር ከዚያ ሰብስብ” የሚል ነው፡፡
መጀመሪያ ዳዕዋ አድርግ ፤ ከዚያም በትክክለኛው ዳዕዋ ላይ ሰዎችን ሰብስብ፡፡
ሰዎችን እስከነውራቸው እራሳቸው በሚጓዙበት መመሪያና ጥመት ላይ ሰብስቦ
ከዚያም ለእነርሱ ቅኑን ጎዳና እንለይላቸው በሚል ሙከራ ማድረግ የሚከተሉት ችግሮች
አሉት፡-
አንደኛ ፡- ከረሡል ‫ ﷺ‬የዳዕዋ አጀማመር ጋር የሚቃረን ነው፡፡
ሁለተኛ፡- ፍሬ አልባ ነው፡፡ ምክንያቱም እኛ በሰለፍ መንሐጅ ላይ ከእኛ ጋር የነበሩ
ወንድሞቻችን ሰዎችን በመሰብሰብ ሲጠመዱ ፣ ከዚያም ዳዕዋቸውን ሲረሱ
ተመልክተናል፡፡ በዚህ ምክንያት ለበርካታ ዘመናት ፊት ለፊታቸው ሰፊ እድሎች
አምልጧቸዋል፡፡ ኢኽዋነል ሙስሊሙን የደረሰባቸው ደርሶባቸዋል፡፡ ኢኽዋን አንድ
ክፍለ ዘመን የሚቃረብ ዘመን አሳልፈዋል፡፡ አንድም (ኢስላማዊ) አገር
አላቋቋሙም፡፡ ከመሪያቸው አንዱ ያወጣላቸውን የሚከተለውን ህግና መርሆ እንኳ
ወደተግባር ሊቀይሩት አልቻሉም፡፡
"‫"أقيموا دولة اإلسالم في قلوبكم تقم لكم في أرضكم‬
“በልባችሁ ውስጥ የኢስላም ግዛት አቋቁሙ- በምድራችሁ ላይ ለእናንተ
ትቆማለችና፡፡”
የኢስላም ግዛት በልባቸው ውስጥ አላቋቋሙም ፣ የኢስላም ግዛት በምድራቸው
ላይ አላቋቋሙም፡፡ ምክንያቱ የሚከተለው ነው፡
"‫"من أحدث في أمرنا هذا ما ليس منه فهو رد‬
“በዚህ (በዲናችን) ከእርሱ ያልሆነ አዲስ ነገር የፈጠረ እርሱ ተመላሽ ነው” ቡኻሪ፡
ሙስሊም፡
20/68

በዚህ ምክንያት ሱናን የሚቃረን አካል ፍጻሜው ጥመትን መጨመር ፣ ልፋቱ ከንቱ
እንጅ ሌላ ሊሆን አይችልም፡፡
ስለዚህ በአሁኑ ሰዓት በኢስላማዊ ዳዕዋ ላይ ለሚንቀሳቀሱት ሁሉ እኔ የማስተላልፈው
መልዕክት፡- ኢስላማዊ ዳዕዋው በአንዳንድ አገሮች የወታደር ስርዓታቸውን
በሚገልጹበት አገላለጽ ዓይነት ነው ያለው፡፡ እርሱም “መካነከ ራዊህ” ባለህበት
እርገጥ፡፡ እነርሱ ይንቀሳቀሳሉ ፣ ይነቃቃሉ ፣ ይሰራሉ ፣ አሁንም ይሰራሉ ፣ ነገር ግን
ከዚያው ከቦታቸው ነቅነቅ አላሉም፡፡ ወደኋላ ካልሆነ በቀር ወደፊት ሊገሰግሱ
አልቻሉም፡፡ አልሀምዱ ሊላህ በአሁኑ ሰዓት የሰለፉነ ሷሊህ ዳዕዋ የሙስሊም አገሮችን
ሁሉ በአጠቃላይ ቀይሮታል፡፡ ከመንሀጅ ሰለፍ ጎዳና ውጭ ሲጓዙ የነበሩ አንዳንዶች
እንኳ ሳይቀር ዓቂዳቸው ተስተካክሏል፡፡ በሰለፍይ ዳዕዋ ምክንያት ከዚህ በፊት
የማያውቁትን ለአላህ ግዴታ የሆነውን ባህሪያት ፣ ትክክለኛውን ሱና ከደካማው
ለይተው አውቀዋል፡፡ በዚህ ምክንያት የሰለፍን ጀማዓ መንሀጅ እና የኸለፍዩን መንሐጅ
በአንድ ላይ ማዋሀድ አይቻልም፡፡” ሲልሲለቱል ሁዳ ወንኑር፡

እኔም አልኩ፡ ሸይኽ አልባኒ ኢኽዋነል ሙስሊሚን የደረሰባቸው አይነት የደረሰባቸው


ስለሆኑት በፖለቲካ ውስጥ በመጠመድ ከዚህ በፊት የሚያውቁትን እውነታ ያስተባበሉ
፣ ሰለፍዮችን ጠላት ያደረጉ ፣ በበደል እና በእብለት ሰለፍዮችን በመጥፎ ባህሪያት
የዘለፉ በሀበሻ ምድር ስለሚገኙ ሙመይዓዎች የሚያወሩ ይመስላሉ፡፡

በዚህ ድንበር ላይ ባቆሙ እመኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ተመዩዓቸውን ወደሰለፎች መንሐጅ


አስጠጉ ፣ ከቢድዓ ባለቤቶች ጋር መተጋገዝ ይበቃል ብለው አጸደቁ ፣ የሚከተለውን
የአላህ ቃል አጣመሙ ፡-
21/68

﴾‫﴿ َوتَ َع َاونُناْ َعلَى الْ ِهُب َوالتم ْق َنى َوالَ تَ َع َاونُناْ َعلَى ا ِل ُِْ َوالْعُ ْد َو ِان‬
“በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፡፡ ግን በሐጢያትና ወሰንን በማለፍ
አትረዳዱ፡፡ አል ማኢዳህ፡

የሚከተለውን የአላህ ቃል አጣመሙ፡-


ِ ‫﴿إِ من ه ِذهِ أُمتُ ُكم أُمةا و‬
﴾‫اح َد اة‬ َ ْ َ
“ይህች (ህግጋት) አንዲት መንገድ ስትሆን በእርግጥ ሐይማኖታችሁ ናት፡፡”
አል አንቢያ ፡

ለአንድነት ደረጃዎች አሉት አሉ… በዚህም የወላእና በራእን መሰረት አፈረሱት፡፡


የቢድዓ ባለቤትን መጥላትን ፣ ማባረርን ፣ ማኩረፍን የሚጠቁመውን የሰለፎችን
ንግግር አጣመሙ፡፡ ይህን የሰለፎች ህግና መርሆ የሚያረጋግጥን ሰው አጥባቂ ፣
ድንበር አላፊ እና ማህይም በሚሉ መገለጫዎች ገለጹ፡፡ ማንኛውንም የሚፈጽሙትን
የቢድዓና የጥመት ተግባር ከዳዕዋው መስለሀ (ጥቅም) አንዱ ክፍል እንደሆነ
ተመለከቱ፡፡ የሰለፍያ ዳዕዋ በሰለፎች ግንዛቤ በቁርኣን እና ሱና የተመሰረተ የሆነውን
የሰለፎችን መንሐጅ አፍራሽ ከሆነ መንሐጅ የጸዳ ነው፡፡ ይህ የራሳቸው መርከዝ ዳዕዋ
መስለሀ ነው፡፡ እንዴውም ከአላህ ውጭ የሚመለኩ አካላትን ስም በማውሳት ከሽርክ
የሚያስጠነቅቅን አካል ይዘልፋሉ ፣ በግልጽ መናገር ሙስሊሞችን ይከፋፍላል ከመስለሐ
አይደለም!! ከሚል ደረጃም ደርሰዋል፡፡ እነዚህ በውሸት የሰለፍይ ልብስ ለባሾች
ሰለፍያን አልረዱም ፣ አህለል ባጢልንም ሰባብረው አልጣሉም፡፡ የተውሂድን እና
የሱናን ዳዕዋ በመዋጋት በእኩል ደረጃ ከኢኽዋነል ሙስሊሚን ጋር ሆነዋል፡፡
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
‫ماس َوالَ تَ ْكتُ ُمننَهُ فَنَ بَ ُذوهُ َوَراٍ ظُ ُهنِرِه ْم َوا َْ ََْْواْ بِِه ََنا‬
ِ ‫اب لَتُبَ يِهنُنمهُ لِلن‬ ِ
َ َ‫يَ أُوتُناْ الْكت‬
ِ ‫﴿وإِ َذ أَخ َذ اّلل ِميث َ م‬
َ ‫اَ الذ‬ َ ُ‫َ َ ه‬
22/68

﴾‫س َما يَ ْش َُْو َن‬ ‫ئ‬


ِْ‫قَلِيًلا فَب‬
َ
“አላህ የእነዚያን መጽሐፉን የተሰጡትን ቃል ኪዳን ለሰዎች በእርግጥ
ታብራሩታላችሁ አትደብቁትምም በማለት የያዘባቸውን (አስታውሱ)፡፡
በጀርባዎቻቸውም ኋላ ጣሉት፡፡ በርሱም ጥቂትን ዋጋ ገዙ፡፡ የሚገዙትም ነገር
ከፋ!” አል ዒምራን፡

ከዚህ በመቀጠል፡ እኛ በሰለፎች አቂዳ ላይ ነን ፣ እኛ አህለሱና ወልጀማዓ ነን ብለው


የሚሞግቱ አንዳንድ አሻዒራዎችና አህባሾችን አቂዳ እጠቁማለሁ!!!

አሻዒራዎች ሙተቀዲም (የቀድሞ) እና ሙተአኺር (ወደኋላ የመጡ) በሚል


በሁለት እንደሚከፈሉ መታወቅ አለበት፡፡ ቀደምት አሻዒራ ከሚባሉት መካከል
ወደሰለፍ መዝሐብ የተመለሱ አቡልሐሰን አል’አሻዒራና ተማሪዎቹ ይገኙበታል፡፡
እነርሱ የአላህን የበላይነት ፣ ከዓርሽ በላይ መሆኑን ፣ ቁርኣን የአላህ ቃል መሆኑን ፣
አላህ በሚከተለው ቁርኣን እንደተናገረው
ለእርሱ ሁለት እጆች እንዳሉት ያለአኳኋን ያጸድቃሉ፡፡
‫ت بِيَ َد م‬
﴾‫ي‬ ِ
ُ ‫﴿ل َما َخلَ ْق‬
“በሁለት እጆቼ ለፈጠርኩት” ሷድ፡
﴾ٍ‫ف يَ َشا‬ ِ ِ
َ ‫﴿بَ ْ ُّ يَ َداهُ َمْب ُسنطَتَان يُنف ُق َُْي‬
“(የአላህ) እጆቹ የተዘረጉ ናቸው፡፡ እንደሚሻ ይለግሳል፡፡” አል ማኢዳህ፡

ሁለት አይን እንዳለው ያለአኳኋን ያጸድቃሉ፡


﴾‫﴿ ََْت ِري ِِب َْعيُنِنَا‬
“በአይናችን (ክትትል) ትንሻለላለች፡፡” (አል’ቀመር፡ 14)
“ኢባና ዓን ኡሱሊ አድዲያና” በሚባለው ኪታብ ገጽ 20 አቡልሀሰን አልአሽዓርይ I
መጀመሪያ ላይ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
23/68

“የምንናገረው ንግግር ፣ እምነት አድርገን የምናምንበት ፣ በጌታችን መጽሐፍ


በነብያችን ሙሐመድ ሱና ፣ አለቃ ከሆኑት ሶሃቦች ታብዒዮች እና የሀዲስ መሪዎች
የተወራውን አጥብቀን መያዝ ነው፡፡ አቡዓብዲላህ አህመድ ብን ሙሐመድ ብን ሀንበል
I ፊቱን አላህ ያብራለት ፣ ደረጃውን ይጨምርለት ምንዳውን የተነባበረ ያድርግለት፡፡
የተከበረ ኢማም ፣ የተሟላ መሪ በመሆኑ የእርሱን ንግግር ተቃራኒዎች ሲቃረኑ እኛ
የእርሱን ንግግር እንናገራለን፡፡
ሀቅን በእርሱ አማካኝነት ይፋ አድርጓል፡፡ ጥመትን በእርሱ አማካኝነት አስወግዷል፡፡
(ትክክለኛውን) ጎዳና ይፋ አድርጓል፡፡ የሙብተዲዖችን ቢድዓ ፣ የጠማሞችን ጥመት
፣ የተጠራጣሪዎችን ጥርጣሬ አስወግዷል፡፡ ከሁሉ ላቅ ያለ ተቀዳሚ ፣ ክብር
የሚሰጠው ፣ (ነገሮችን በደንብ ) አስገንዛቢ ለሆነው ኢማም አላህ ይዘንለት፡፡ ”

ወደኋላ ዘግይተው የመጡ አሻዒራዎች የቀድሞ አሻዒራዎችን ተቃራኒ ሆነዋል፡፡


የአላህን ባህሪያት አጣመው ተርጉመዋል ፤ የፍልስፍና ፣ የሱፍያ ህጎችን አስገብተዋል፡፡
ከእነርሱ መካከል ታዋቂ የሆኑት አቡልመዓሊ አልጁወይኒ ፣ ፈኽሩ ራዚ ፣ ገዛሊ እና
ሌሎችም ናቸው፡፡

በዘመናችን ያሉ አሻዒራዎችና አህባሾች ዓቂዳን ለማጽደቅ ድጋፍ የሚያደርጉት


ወደኋላ በመጡ (አሻዒራዎች) መጽሐፎች ነው፡፡ ይህ በጣም የሚገርም ነው፡፡
ምክንያቱም አቡል ሀሰን አልአሽዓርይ የአላህ ባህሪያት በሰለፎች መዝሐብ የሚያጸድቅ
፣ ከነበረው አቋም ተጸጽቶ የተመለሰ ፣ “አልኢባና ዓን ኡሱሊ አድዲያና” እና
ሌሎችንም ታዋቂ መጽሐፎችን ያዘጋጀ ሆኖ እያለ እንዴት ወደአቡል ሀሰን አልሻዒርይ
ይጠጋሉ?!
24/68

በዚህ ምክንያት አሽሸይኽ ሙሐመድ አማን አልጃሚ I የአላህን ንግግር በተመለከተ


ከአህለሱና ወልጀማዓ ጋር የሚስማማ የሆነውን የአቡል ሀሰን አልአሽዓርይ ንግግር
ከነቀሉ በኋላ- የሚከተለውን ተናግረዋል፡- “ኢማም አቡል ሀሰን አልአሽዓርይ
“ኢባና” ውስጥ ያሰፈረውን እና ወደኋላ የመጡ አሻዒራዎች የሚናገሩትን እና
የሚያምኑበትን ስናነጻጽረው ወደአቡል ሐሰን እራሳቸውን ማዛመዳቸው ትክክል
አይደለም ማለት እንችላለን፡፡ በዚህ ቦታ ግብጻዊው ሰለፍይ ሸይኽ ሙሂቡ ዲን
አልኸጢብ I የተናገረውን ንግግር ማስፈሩ ተዛማጅ ሆኖ እመለከታለሁ፡፡ “አሽዓርያ
በፍልስፍና እውቀት ወደአቡል ሀሰን አልአሽዓርይ የተዛመደ የመዝሐብ ስም ነው፡፡”
አሽዓርይ በኢዕቲዛል ዘመን ባለው እንደማይመሰለው ሁሉ በእርሷ ላይ አላህን
መገናኘት በሚፈልግባት ወደሆነችው የሰለፍ ዓቂዳ ከተመለሰ በኋላ አሽዓርይን ወደርሱ
ማስጠጋቱ ፍትህ አይደለም፡፡ ይልቁን አሽዓርይ የተዛመደው ተቅዩ ዲን “አልዓቅል
ወንነቅል” በተባለው ኪታቡ ግልጽ እንዳደረገው በ 240 ሒጅራ አቆጣጠር የሞተው
ኢብን ኩላብ አልበስርይ በነበረበት (አመለካከት) ላይ ነው፡፡ እንደምትመለከተው
ይህ ንግግር ማብራሪያ የማያስፈልገው በጣም ክብርና ግምት የሚሰጠው ንግግር ነው፡፡
(አስሲፋቱ አልኢላሂያ ፊል ኪታቢ ወስሱናህ ፡ 13/55-56)

ኢብን ተይሚያ I “ሸርህ አልዓቂደቱል አስፈሃኒያህ” በተባለው ኪታብ ገጽ 127


የሚከተለውን ተናግሯል፡-

“…ሀፊዝ አቡበክር አልበይሐቂይ እና መሰሎቹ ፣ ከበርካታ የእርሱ ንግግር ወጠው ወደ


ሙዕተዚላ ወይም ጀህምያ ወይም ፍልስፍና ንግግር የገቡ ከሆኑት ወደኋላ ከመጡ
በርካታ የአሽዓርይ ባልደረቦች ይልቅ ወደሱና የቀረቡ ናቸው፡፡”
25/68

ኢብን ተይሚያ I ስለሙዕተዚላና እነርሱ ወደሷቢእ ፈላስፎች የቀረቡ መሆናቸውን


በሚናገርበት ቦታ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
“ሩሡሎች በእርሱ የመጡበትን ፈጻሚ የሆነ ፣ መመልከቻን አላህ የለገሰው ፣
የእነዚያን ትክክለኛ ችግር ያወቀ ፣ የአላህን ስሞችና አንቀጾች የሚያጣምሙ ፣
በሩሡሎች በመጽሐፎች ፣ ሩሡሎች በእርሱ በተላኩበት ያስተባበሉ መሆናቸውን
በቁርጥ ያውቃል፡፡ በዚህ ምክንያት፡ “ቢድዓ ከክህደት የተወሰደ ፣ ወደክህደት
የሚወስድ ነው” ይሉ ነበር፡፡ “ሙዕተዚላ የፈላስፋ ድቅል ነው ፤ አሽዓርያ ደግሞ
የሙዕተዚላ ድቅል ነው” ይላሉ፡፡ የህያ ብን ዓማር የሚከተለውን ተናግሯል ፡-
“ሙዕተዚላ ወንዱ ጀህምያ ሲሆን አሽዓርያ ደግሞ ሴቷ ጀሕምያ ነች፡፡” አሽዓርያ
በማለት የተፈለገው ኸበርይ (ከአላህና ከረሡል የተነገረ) የሆነውን ባህሪያት አራቋች
የሆኑትን ነው፡፡ ተቃራኒ ንግግር ይፋ ሳያደርግ ፣ አሽዓርይ መጨረሻ እድሜው ላይ
ባዘጋጀው “ኢባና” ኪታብ የተናገረ ሰው ከአህለሱና ይቆጠራል፡፡ ነገር ግን እንዲሁ
ወደአሽዓርይ መጠጋቱ ቢድዓ ነው፡፡” (መጅሙዕ አልፈታዋ፡ 6/359)

➢ ወደ ኋላ የመጡት አሽዓርያዎች የአላህን ከፍጡሩ ሁሉ በላይ መሆኑን አያጸድቁም


ጀህምያዎች እንደሚሉት አላህ በአለም ውስጥ ፣ በአለም ውጭ ፣ በላይም በታችም
አይደለም ይላሉ፡፡
ሸይኽ ሙሐመድ አማን አልጃምሚ I የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
“አሽዓርይ በዚህ የጀህምያ ወይም ባጢንይ ህግና መርሆ ተማርከዋል፡፡ የአላህን
የበላይነት ፣ ኢስቲዋኡን ይህን በሚመስል አራቁተውታል፡፡ ይህ ይምናገረው ለወደፊት
ይገኛል ፤ የገለጽኩት ዓቂዳ ሸርሁ በይጁርይ በመባል በሚታወቀው ሰኑሲያ ኪታብ
26/68

ውስጥ ይገኛል፡፡ የሰኑሲያ መትን ባለቤት የሚከተለውን ተናግሯል፡-


‫"ليس هللا فوق العرش وال تحت العرش وال عن يمينه وال عن يساره وال خلفه وال‬
"‫أمامه‬
“አላህ ከዓርሽ በላይ ፣ በታች ፣ በቀኝም በግራም በኋላም በፊትም አይደለም፡፡”
አላህ ከዓርሽ በላይ ካልሆነ አሉታዊ ነገሮችን ሁሉ እንተውና እርሱ የት ሊሆን ነው?
እነዚህ ሰዎች በአላህ አምነዋልን?
አላመኑም ፣ በአላህ የበላይነት ካላመኑ በአላህ ላይ ያላቸው እምነት አይሟላም፡፡
የአላህ የበላይነትን ማመን በአላህ ከማመን የመጀመሪያው ነው፡፡ ለዚህ ማስረጃ
የሚሆነው ረሡል ‫( ﷺ‬ባሪያዋ) አማኝ መሆን አለመሆኗን ለማረጋገጥ እና ለማወቅ
በፈለጉ ጊዜ ይህን ጉዳይ ነው ለፈተና ያቀረቡላት፡፡ ከሌሎች የጌታ ባህሪያት በፊት
የአላህን የበላይነት የሚገልጸውን ባህሪ ነው ለፈተና ያቀረቡላት፡፡ ምክንያቱም የአላህ
የበላይነት አካላዊ የሆነ ባህሪ ነው ኡሉው ከኢስቲዋእ ጋር እንደሚለይ ለወደፊት
ይመጣል፡፡ አላህ ከፍጡራን ጋር ያልተቀላቀለና በአካሉ ከፍጡራን ሁሉ የበላይ መሆኑን
፣ ከአላህ ፍጡራኖች አንዳች ነገር በአላህ ዛት ላይ የሌለ መሆኑን ፣ ከአላህ ፍጡሮች
ውስጥ አንድም የአላህ ዛት የሌለ (ያልገባ) መሆኑን ይልቁንም ከፉጡራን ሁሉ በተለየ
ሁኔታ ከሁሉ የበላይ መሆኑ ያላመነ ሰው ጌታውን አላወቀም፡፡” ሸርህ ሪሳለቱ አትተድሙርያ
አልጃሚ ፡

ጀህምያ አላህ በሁሉም ቦታ ነው በማለታቸው ምክንያት ኢማም አህለሱና ወልጀማዓህ


አህመድ ብን ሀንበል I የሰጡት ምላሽ ፡-
“ሙስሊሞች የጌታ ልቅና በውስጡ የሌለበትን በርካታ ቦታዎች አውቀዋል፡፡”
እንላቸዋለን፡፡ “የትኛው ቦታ?” ይላሉ፡፡
27/68

“አካላችሁ ፣ ሆዶቻችሁ ፣ የከርከሮ እና እንስሳዎች ሆዶች ፣ የቆሻሻ ቦታዎች የጌታ


ክብር አንዳችም ነገር የለበትም፡፡” እንላቸዋለን፡፡
አላህ ከሰማይ በላይ እንዳለ ነግሮናል፡-
﴾‫نر‬ ِ ِ ‫﴿أَأ َِمنتم مَ ِِف ال مسماٍ أَن ََيْ ِسف بِ ُكم اْلَر‬
ُ ُ‫ض فَإ َذا ه َْ ََت‬
َ ْ ُ َ َ ُ
“በሰማይ ላይ ያለን በእናንተ ምድርን ቢደረምስባችሁ ወዲያውም እርሷ
የምታረገርግ ብትሆን ትተማመናላችሁ? (አትፈሩምን)? አል ሙልክ፡

﴾‫ف نَ ِذي ِر‬ ِ ِ ِ


َ ‫﴿أ َْم أَمنتُم مَ ِِف ال مس َماٍ أَن يُْرس َ ُّ َعلَْي ُك ْم َحاصباا فَ َستَ ْعلَ ُمن َن َُْي‬
“ወይም በሰማይ ላይ ያለን በእናንተ ላይ ጠጠርን ያዘለች ነፋስን ቢልክባችሁ
ትተማመናላችሁ? (አትፈሩምን)?” አል ሙልክ፡

﴾‫ب‬ ِ‫ص َع ُد الْ َكلِم الطمي‬


‫ه‬ ْ ‫ي‬
َ
ِ ‫﴿إِلَي‬
‫ه‬ ْ
ُ ُ
“መልካም ንግግር ወደርሱ ይወጣል” ፋጢር፡

‫ك إِ َم‬ ِ ِ
﴾‫َل‬ َ ‫﴿إِِهِن ُمتَ َنفه‬
َ ُ‫يك َوَرافع‬
“እኔ ወሳጅህ ወደ እኔም አንሺህ ነኝ፡፡” አል ዒምራን፡

﴾‫اّللُ إِلَْي ِه‬


‫﴿بَ ُّ مرفَ َعهُ ه‬
“ይልቁንስ አላህ (ኢሳን) ወደርሱ አነሳው” አን ኒሳእ፡

﴾‫ندهُ َال يَ ْستَ ْكُِبُو َن َع َْ ِعبَ َادتِِه َوَال يَ ْستَ ْح ِسُرو َن‬
َ ‫ض َوَم َْ ِع‬ ِ ‫﴿ولَه مَ ِِف ال مسماو‬
ِ ‫ات َو ْاْل َْر‬ ََ ََُ
“በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉም የእርሱ ነው፡፡ ከእርሱ ዘንድ
ያሉትም(መላእክት) እርሱን ከመገዛት አይኮሩም፡፡” አል አንቢያእ ፡

﴾‫﴿ ََيَافُن َن َرمُِم ِهمَ فَ ْنقِ ِه ْم‬


“ጌታቸውን ከበላያቸው ሲሆን ይፈሩታል፡” አን ነህል ፡

﴾‫اّللِ ِذي الْ َم َعارِِج‬


‫﴿ ِهم ََ م‬
28/68

“የ (ሰማያት)መሰላሎች ባለቤት ከሆነው አላህ (መላሽ የለውም)፡፡” አል መዓሪጅ ፡

ِ ‫﴿وهن الْ َق‬


﴾ِ‫اهُر فَ ْن ََ ِعبَ ِاده‬ ََُ
“እርሱም ከባሮቹ በላይ ሲሆን አሸናፊ ነው፡፡” አል አንዓም፡ አርረድ ዓለል ጀህምያ ወዝዘናዲቃ ፡
ገጽ ሊል ኢማም አህመድ

ኢብኑል ሙባረክ I የሚከተለውን ተናግሯል፡-


“ጀህምያዎች እርሱ (አላህ) ምድር ላይ ነው እንደሚሉት አንልም፡፡ ይልቁንም አላህ
ከአርሽ በላይ ነው፡፡ “ጌታችንን እንዴት ታውቀዋለህ? ተባለ፡፡ እርሱም “ከአርሽ ከፍ
ብሎ ከሰማያት በላይ ነው” በማለት ምላሽ ሰጠ፡፡ ኸልቁ አፍዓሊል ዒባድ ፡ ገጽ

ኢብን አልቀይም I የሚከተለውን ተናግሯል፡-


“ግልጽ ከሆነው የተፈጥሮ ፣ የአቅል እና የሸሪዓ ማስረጃ አላህ ከፍጡራኑ ሁሉ የበላይ
መሆኑ ነው፡፡ አላህ በማይናገሩ እንስሳት ላይ እንኳ ይህን አመለካከት ፈጥሯል፡፡ ይህን
የተቃወመ እርሱ በሌላ ጎን ሲሆን ሰላማዊ ተፈጥሮ ፣ የተስተካከሉ ዓቅሎች ፣ አጠቃላይ
ከሰማይ የወረዱ መጽሐፎችና በእርሱ የተላኩ (መልእክተኞች) ሁሉ በሌላ ጎን
ናቸው፡፡” አሶዋዒቂል ሙርሰላ ፊርረዲ ዓለል ጀህምየቲ ወልሙዓጢላህ፡

አሁንም የሚከተለውን ተናገሩ፡- “አላህ ከፍጥረታቱ የተለየ መሆኑ እንዲሁም


ከፍጡራኖች ሁሉ በላይ ለመሆኑ በገሀድ የሚታወቅ እውቀት ለመሆኑ በርካታ የዓቅልና
የተፈጥሮ ማስረጃዎች አሉ፡፡ ከቁርኣን እና ከሐዲስ የመጡ መረጃዎች አንድ ሽ
ይቃረባሉ፡፡” አሶዋኢቂል ሙርሰላ ፊርረዲ ዓለል ጀህምየቲ ወልሙዓጢላህ ፡

➢ አሻዒራ “ረህማን ከአርሽ በላይ ነው” የሚለውን የቁርኣን አንቀጽ አጣመዋል


ፈኽሩ ራዚ በተፍሲር ኪታቡ ላይ “ኢስተዋ” የሚለውን ቃል “ኢስተውላ”
29/68

በሚል ቃል አጣሞታል፡፡ “ለምኡል አዲለቲ ፊ ቀዋኢዲ ዓቃዒዲ አህሊ ሱነቲ


ወልጀማዓቲ” በተባለው የጁወይኒ ኪታብ ገጽ 108 ላይ ይህንን ቃል በተመሳሳይ
አጣመውታል፡፡
ጀህምያና ሙዕተዚላም እንደዚሁ “ኢስተዋ” ያለውን “ኢስተውላ” ብለው
ተርጉመውታል፡፡ “አርረድ ዓለል ጀህምየቲ” በሚባለው የዳሪምይ ኪታብ ገጽ 41
ላይ “አላህ በሁሉም ቦታ ነው፡፡ ከእርሱ ያገለለ አንድም ቦታ የለም” የሚል ንግግር
ተናግረዋል፡፡ መቃላቱል ኢስላምያ፡ ገጽ

ሰለፍዬች ከልቅናው ጋር በሚስማማ ሁኔታ አላህ ከዓርሽ በላይ ከፍ ያለ መሆኑን


ያምናሉ፡፡ ቁርኣን ፣ ሐዲስ እንዲሁም የቀደምት ደጋግ የአላህ ባሮች ስምምነት በዚህ
ላይ ይጠቁማል፡፡
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
ِِ ِ ِ
ْ ‫ض ِِف ستمة أ مََيم ُُم‬
﴾ ِ ‫استَ َنى َعلَى الْ َعْر‬ ‫﴿إِ من َربم ُك ُم ه‬
َ ‫اّللُ المذي َخلَ َق ال مس َم َاوات َواْل َْر‬
“ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናቶች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው፡፡
ከዚያም ከዓርሹ በላይ ከፍ አለ፡፡” አል አዕራፍ፡

ِِ ِ ِ
ْ ‫ض ِِف ستمة أ مََيم ُُم‬
﴾ ِ ‫استَ َنى َعلَى الْ َعْر‬ ‫﴿إِ من َربم ُك ُم ه‬
َ ‫اّللُ المذي َخلَ َق ال مس َم َاوات َواْل َْر‬
“ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው፡፡
ከዚያም ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብር ሲሆን ከአርሹ በላይ ከፍ አለ፡፡” ዩኑስ፡

ِ ِ ﴿
ْ ‫اّللُ المذي َرفَ َع ال مس َم َاوات بِغَ ِْْي َع َمد تََرْوََّنَا ُُم‬
﴾ ِ ‫استَ َنى َعلَى الْ َعْر‬ ‫ه‬
“አላህ ያ ሰማያትን የምታዮዋት አእማድ ሳትኖር ያነሳት ከዚያም ከአርሹ በላይ
ከፍ ያለ ጸሐይንም የገራ ነው፡፡” አር ረዕድ፡

ْ ِ ‫﴿المر ْْحَ َُ َعلَى الْ َعْر‬


﴾‫استَ َنى‬
30/68
“(እርሱ) አልረህማን ነው፡፡ በአርሹ በላይ ከፍ አለ፡፡” ጦሃ፡

ِِ ِ ِ
َ ‫﴿المذي َخلَ َق ال مس َم َاوات َو ْاْل َْر‬
ْ ‫ض َوَما بَْي نَ ُه َما ِِف ستمة أ مََيم ُُم‬
﴾ ِ ‫استَ َنى َعلَى الْ َعْر‬
“ያ ሰማያትና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀኖች ውስጥ
የፈጠረ ፣ ከዚያም ከዓርሹ በላይ ከፍ ያለ ነው፡፡” አል ፉርቃን፡

ِِ ِ ِ ‫﴿م‬
َ ‫اّللُ المذي َخلَ َق ال مس َم َاوات َو ْاْل َْر‬
ْ ‫ض َوَما بَْي نَ ُه َما ِِف ستمة أَ مَيم ُُم‬
﴾ ِ ‫استَ َنى َعلَى الْ َعْر‬
“አላህ ያ ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸውም ያለውን ሁሉ በስድስት ቀኖች
ውስጥ የፈጠረ ከዚያም ከዓርሹ በላይ ከፍ ያለ ነው፡፡” አስ ሰጅዳ፡

ِ ‫استَ َنى َعلَى الْ َعْر ِ يَ ْعلَ ُم َما يَلِ ُج ِِف ْاْل َْر‬
‫ض َوَما ََيُْر ُج‬ ِِ
ْ ‫ض ِِف ستمة أ مََيم ُُم‬
ِ ِ
َ ‫﴿ ُه َن المذي َخلَ َق ال مس َم َاوات َو ْاْل َْر‬
﴾‫ِمْن َها َوَما يَن ِزُل ِم ََ ال مس َماٍ َوَما يَ ْعُر ُج فِ َيها‬
“እርሱ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረ ፤ ከዚያም
ከዓርሹ በላይ ከፍ ያለ ነው፡፡ በምድር ውስጥ የሚገባውን ፣ ከእርሷም
የሚወጣውን ፣ ከሰማይም የሚወርደውን በእርሷም ውስጥ የሚያርገውን
ያውቃል፡፡” አል ሐዲድ፡

ከተረጋገጡ የሱና ማስረጃዎች መካከል የሚከተሉትን ይገኛሉ፡-


ነብዩ ‫ ﷺ‬ለባሪያዋ “አላህ የት ነው?” በማለት ጠየቋት፡፡ እርሷም “ከሰማይ በላይ”
በማለት መለሰች፡፡ “እኔ ማን ነኝ?” በማለት ጠየቋት፡፡ “አንተ የአላህ መልእክተኛ
ነህ” በማለት መለሰች፡፡ “እርሷ አማኝ ነችና ነጻ አድርጋት” በማለት ተናገሩ፡፡ ሙስሊም፡

የአላህ መልእክተኛ ‫ ﷺ‬የሚከተለውን ተናግረዋል፡-


"‫"ال تأمنوني وأنا أمين من في السماء يأتيني خبر السماء صباحا ومساء‬
“አታምኑኝምን ፣ እኔ ከሰማይ በላይ ካለው ታማኝ ነኝ፡፡ በጧትም በምሽትም የሰማይ
ዜና ይመጣልኛል፡፡” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡
31/68

አቡሁረይራ e የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፏል ረሡል ‫ ﷺ‬የሚከተለውን ሐዲስ


ተናግረዋል፡-
"‫"لما قضى هللا الخلق كتب في كتابه فهو عنده فوق العرش إن رحمتي غلبت غضبي‬
“አላህ ፍጥረትን ፈጥሮ ሲያበቃ ከእርሱ ዘንድ ከአርሽ በላይ ካለው መጽሐፉ “እዝነቴ
ቁጣየን አሸነፈች” የሚል ጻፈ” ቡኻሪ፡

አቡሁረይራ e የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፏል ረሡል ‫ ﷺ‬የሚከተለውን ሐዲስ


ተናገሩ፡-
“በሌሊትና በቀን መላኢካዎች ይፈራረቃሉ፡፡ በፈጅር ሶላትና በዓስር ሶላት ላይ ይሰባሰባሉ፡፡
ከዚያም ወደርሱ (ወደአላህ) ይወጣሉ፡፡ እርሱ አዋቂ ሆኖ እያለ (ሌሊት) ያደሩትን
(መላኢካዎች) “ባሮቸን እንዴት ተዋችኋቸው?” በማለት ይጠይቃቸዋል፡፡ “እየሰገዱ
ተውናቸው ፣ እየሰገዱ መጣን፡፡” በማለት ምላሽ ይሰጣሉ፡፡ (ቡኻሪ፡ 555, ሙስሊም፡ 210/632)

ታማኝና የሐዲስ ባለቤት የሆነው ጃዕፋር ብን ዓብዲላህ I የሚከተለውን ተናግሯል፡-


“አንድ ግለሰብ ወደ ማሊክ ብን አነስ መጣ፡፡ “አባ አብዲላህ ሆይ! “አርረህማን
አለል ዓርሽ ኢስተዋ” ጡሃ፡ (በማለት አላህ ተናግሯል)፡፡ እንዴት ነው ከዓርሸ በላይ
የሆነው?” በማለት ጠየቃቸው፡፡ እንደዚህ ሰው አነጋገር ማሊክን ያስተከዘው አይተን
አናውቅም፡፡ ብዙ ላበት በላዩ ላይ ፈሰሰ፡፡ ሳይናገር ዝም ብሎ አቀርቅሮ ቆየ፡፡ እርሱን
አስመልክቶ ምን እንደሚያዝ እንጠባበቅ ነበር፡፡ ከዚያም ሐሳብና ጭንቀት ከማሊክ ላይ
ተወገደ፡፡ የሚከተለውንም ተናገረ፡-
‫ والسؤال‬، ‫ واإليمان به واجب‬، ‫ واإلستواء منه غير مجهول‬، ‫"الكيف غير معقول‬
"‫ وإني ألخاف أن تكون ضاال‬، ‫عنه بدعة‬
“አኳኋኑ አይታወቅም ፤ ኢስቲዋኡ (ከፍ ማለቱ) የማይታወቅ አይደለም(ይታወቃል)
32/68

በእርሱ ማመን ግድ ነው ፤ ከእርሱ (አኳኋኑን) መጠየቅ ቢድዓ ነው ፤ ጠማማ


ትሆናለህ ብየ እፈራለሁ፡፡” ከዚያም እንዲወጣ አዘዙ፡፡” በይሐቂይ አል አስማእ ወስ ሲፋት፡

ሐፊዝ ብን ከሲር I የሚከተለውን ተናግረዋል ፡-


“ሱምመ ኢስተዋ ዓለል ዓርሽ” የሚለውን የአላህ ቃል ትርጉም አስመልክቶ ሰዎች
ብዙ ብለዋል፡፡ ነገር ግን ይህ በስፋት የምንናገርበት ቦታ አይደለም፡፡ በዚህ ቦታ የማሊክ
፣ የአውዛዒይ ፣ የሰውርይ ፣ የለይስ ብን ሰዕድ ፣ የሻፍዒይ ፣ የአህመድ ፣ የኢስሐቅ
ብን ራህዊየህ እና የሌሎችን የቀድሞም ይሁኑ አዲስ የደጋግ ቀደምት የሙስሊም
መሪዎችን ጎዳና ምን እንደሚመስል ለማቅረብ እንፈልጋለን፡፡ እርሱም፡-
"‫"إمرارها كما جاءت من غير تكييف وال تشبيه وال تعطيل‬
“ያለአኳኋን ፣ ያለማመሳሰል ፣ ያለማራቆት እንደመጣ ማስኬድ ነው፡፡”
በአመሳሳዮች አዕምሮ ፈጥኖ የሚመጣው ከአላህ ላይ የተራቆተ ነው፡፡ አላህ
ከፍጡሩ አንድም የሚመስለው የለም፡፡
“እርሱን የሚመስል አንድም ነገር የለም ፤ እርሱ ሰሚ ተመልካች ነው፡፡”
አሽ ሹራ፡ ነገሩ የሙስሊም መሪዎች እንደተናገሩት ነው፡፡ ከእነርሱ መካከል የቡኻሪ
ሸይኽ የሆኑት ይገኙበታል፡፡
የሚከተለውንም ተናግረዋል፡-“አላህን ከፍጡር ጋር ያመሳሰለ ከሀዲ ነው ፤ አላህ
በእርሱ ነፍሱን የገለጸበትን ያስተባበለ በእርግጥ ካደ ፤ አላህ ነፍሱን በእርሱ
የገለጸበትም ይሁን ረሡል ‫ ﷺ‬የገለጹት ተመሳሳይ የለበትም፡፡ ከአላህ ልቅና ጋር
በሚስማማ ሁኔታ በትክክለኛ ወሬ እና በትክክለኛ አንቀጾች በመጣው መሰረት ለአላህ
ያጸደቀ ፣ ጎደሎ ነገሮችን ከአላህ ላይ ያስወገደ ቅን የሆነውን ጎዳና በእርግጥ ተጓዘ፡፡”
ተፍሲር ኢብን ከሲር፡
33/68

አነስ ብን ማሊክ e የሚከተለውን ተናግሯል፡-


“ዘይነብ ቢንት ጀህሽ g በነብዩ ‫ ﷺ‬ሚስቶች ላይ የነበራትን የኩራት ስሜት
እንደሚከተለው ትገልጽ ነበር፡-
"‫"زوجكن أهاليكن وزوجني هللا من فوق سبع سموات‬
“እናንተን የዳሯችሁ ቤተሰቦቻችሁ ናቸው ፤ እኔን የዳረኝ ከሰባት ሰማያት በላይ ያለው
አላህ ነው፡፡” ቡኻሪ፡

ዓኢሻ g በምትሞት ጊዜ ዓብደላ ብን ዓባስ f ወደቤቷ ገባ፡፡ ከዚያም የሚከተለውን


አላት፡-
“ከረሡል ‫ ﷺ‬ሚስቶች ሁሉ ወደረሡል ተወዳጅ ሴት ነሽ ፣ ረሡል መልካም እንጅ
ሌላን አይወዱም፡፡ አላህ የአንችን (ከዝሙት) ነጻ መሆን የሚመለከት (አንቀጽ)
ከሰባት ሰማያት በላይ አወረደ፡፡” አድ ዳሪሚይ ፊርረዲ ዓለል ጀህሚየቲ፡ ገፅ

ዓኢሻ g የሚከተለውን ተናግራለች ፡-


“በአላህ እምላለሁ ፣ የእርሱን -ዑስማንን ማለቷ ነው - መገደሉን የምወድ ቢሆን
ኖሮ እገደላለሁ ብየ እፈራለሁ ፣ ነገር ግን የእርሱን መገደል እንደማልወድ ከዓርሽ
በላይ ያለው አላህ አውቋል፡፡” አድ ዳሪሚይ ፊርረዲ ዓለል ጀህሚየቲ፡ ገፅ

ኢብን ዑመር f በአንድ የፍየል ጠባቂ በኩል አለፈ፡ “ፍየል ጠባቂው ሆይ! ፍየል
አለ?” በማለት ጠየቀው፡፡ “ጌታዋ ከዚህ የለም” በማለት ፍየል ጠባቂው ምላሽ ሰጠ፡፡
“ተኩላ በላት እንዴ?” አለው ኢብን ዑመር፡፡ ጠባቂው እራሱን ወደሰማይ አደረገና
“አላህ የት ሆኖ?” አለ፡፡ (ከላይ ሆኖ ይመለከታል ማለቱ ነው) ኢብን ዑመር
ጠባቂውን ገዛና (ከባርነት) ነጻ አደረገው ፤ ፍየል ገዝቶም ሰጠው፡፡ ጦበራኒይ ፊልከቢር፡
አሰሩን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል፡ አስሶሂህ
34/68
ዓብዱረህማን ብን አቢ ሀቲም I “ሱና” ተብሎ በሰፊው በሚታወቀው “ኢዕቲቃድ”
ኪታብ ውስጥ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
“በዲን መሰረቶች ዙሪያ ፣ እንዲሁም በአጠቃላይ በየከተሞች የነበሩ ዓሊሞች
የነበሩበትን የአህለሱናን መዝሐብ እንዲሁም በዚህ ዙሪያ እምነታቸው ምን እንደሆነ
አባቴን እና አባዙርዓን ጠየቅኋቸው፡፡ የሚከተለውን ምላሽ ሰጡኝ፡- “በሁሉም
ከተሞች -ሂጃዝ ፣ ዒራቅ ፣ ግብጽ ፣ ሻም ፣ የመን- የሚገኙ ዑለሞችን አግኝተኛል፡፡
የሚከተሉት መንገድ የሚከተለው ነው፡- ኢማን በንግግር በተግባር የሚገለጽ ፣
የሚጨምር የሚቀንስ እንደሆነ ፣ በማንኛውም አቅጣጫ ቁርኣን ፍጡር ያልሆነ የአላህ
ንግግር መሆኑን ያምናሉ”… (ሸርሑ ኡሱል ኢዕቲቃዲ አህሊሱነቲ ወልጀማዓቲ ሊላለካኢይ፡ ገፅ; 176)
አሁንም በመቀጠል የሚከተለውን ተናገረ፡ “አላህ ከፍጡራኑ በተለየ ከዓርሽ በላይ ነው
፤ አላህ ነፍሱን በቁርኣኑ እንዲሁም በመልእክተኛው አንደበት እንደተገለጸው
ያለአኳኋን ይገልጻሉ፡፡ ሁሉንም ነገር በእውቀቱ ያካበበ መሆኑን ያምናሉ፡፡” (በያን ተልቢስ
አልጀህሚየቲ፡ 1/210)

ኢብን ተይሚያ I የሚከተለውን ተናግሯል፡-


“አንዳንዶች የሚናገሩት ምን ያማረ ሆነ! ፡ ጀህምይ (የሆነ ሰው) “እንዴት ነው አላህ
ከዓርሽ በላይ ያለው?” ወይም “እንዴት ነው ከሰማይ የሚወርደው?” ወይም “ሁለት
እጆቹ እንዴት ናቸው?” እና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች ከጠየቀህ፡፡ “አካሉ እንዴት
ነው?” ብለህ ጠይቀው፡፡ እርሱ እንደማያውቀው ፣ የጌታ አኳኋን ከሰዎች እውቀት
ውጭ እንደሆነ ከገለጸልህ፡፡ “የባህሪውን ሁኔታ ማወቅ የተገላጩን አኳኋን ከማወቅ ጋር
የተያያዘ ነው፡፡ የተገላጩን አኳኋን ሳታውቅ እንዴት የአንድን ነገር ባህሪ ልታውቅ
ትችላለህ? አካልን እና ባህሪያትን የምታውቀው ለአንተ በሚገባህ መልኩ ጥቅል በሆነ
35/68
መልኩ ነው፡፡” የሚል መልስ ስጠው፡፡
“በጀነት ውስጥ ስለሚገኙ ፍጡራኖች” በተመለከተ ኢብን አባስ የሚከተለውን
መናገሩ ተረጋግጧል፡፡
‫ليس في الدنيا مما في الجنة إال األسماء‬
“በጀነት ውስጥ ከሚገኙ ነገሮች ስማቸው እንጅ ዱንያ ላይ የሉም፡፡”
ምክንያቱም ነፍስ ለእነርሱ ከአይን ማረፊያ የተደበቀላትን ነገር እንደማታውቅ
አላህ ተናግሯል፡፡ ነብዩ ‫ ﷺ‬በጀነት ውስጥ አይን አይቶት የማያውቅ ፣ ጆሮም ሰምቶት
የማያውቅ ፣ የሰው ልጅ ልቦና ትዝ ብሎት የማያውቅ ነገር እንዳለ ተናግረዋል፡፡
የጀነት ጸጋ ከአላህ ፍጡራኖች አንዱ ፍጡር ከሆነ ፣ -ጥራት በተገባው ፈጣሪያችን ላይ
ምንድን ነው ጥርጣሬህ???
በሰው ልጆች አካል ውስጥ ስለምትገኘው “ሩህ” ሰዎች እንዴት እንደዋዥቁ ፤
አኳኋኗንም ግልጽ ከማድረግ መረጃዎች እንደተቆጠቡ አቅለኛ ያውቀዋል፡፡ ታዲያ
አቅለኛ የሆነ ሰው ስለአላህ አኳኋን ለመናገር በእርሷ ዙሪያ ያለውን አያስተነትንምን?
ይሁን እንጅ ሩህ ከአካል እንደምትወጣ ፣ ወደሰማይ እንደምትዘልቅ ፣ የሰው ልጅ
ሲሞት ፍስስ (ምዝዝ) ብላ እንደምትወጣ ትክክለኛ መረጃዎች መናገራቸውን በቁርጥ
እናምናለን፡፡” (መጅሙዕ አልፈታዋ ፡ 5/114)
➢ በእጃችን የሚገኘው ቁርኣን ፍጡር እንደሆነ አሻዒራዎች ያምናሉ
አሻዒራዎች “ቁርኣን የነፍስ ንግግር ከመሆኑ አኳያ ፍጡር አይደለም ፤
ከምንቀራው የቁርኣን ቃላት አኳያ ደግሞ ፍጡር ነው” ይላሉ፡፡ ጠቅለል ያለው
የአሻዒርያ እምነት፡ ቁርኣን የአላህ ንግግር አይደለም፡፡ ይልቁንም ሀርፍም ድምጽም
ያልሆነ ከአላህ ላይ ቋሚ የሆነ በነፍስ ውስጥ ያለውን ትርጉም ገላጭ ነው፡፡
36/68

ጁወይኒ የሚከተለውን ተናግሯል፡- “የንግግራቸው ትርጉም (የሙዕተዚላዎች) እነዚህ


መግለጫዎች የአላህ ንግግሮች ናቸው፡፡ እርሷን አላህ ፈጠራት፡፡ የአላህ ፍጡር
መሆኗንም እኛ አንቃወምም … አልኢርሻድ ገጽ

ፈኽሩ ራዚ የሚከተለውን ተናግሯል፡


“ቁርኣን (በሀርፍና በድምጽ በእጃችን ካለው ቁርኣን ጋር) በመጋራት በአላህ ዛት ላይ
ቋሚ ለሆነው ቀዳማዊ ባህሪ የተነገረበት ስም ነው፡፡ በዚህ መሰረት እነዚህ ሀርፎች እና
ድምጾች የተዋቀሩ ቃላቶች አዲስና ፍጡር መሆናቸው ምንም አይነት ጭቅጭቅ
የለበትም፡፡ ክርክሩ የተከሰተው ቀዳማዊ በሆነው መገለጫ ላይ አይደለም፡፡” ተፍሲር አርራዚ፡

በይጁሪ የሚከተለውን ተናግሯል ፡-


“(እንደነርሱ አባባል) የአህለሱና መዝሐብ (ማለትም አሻዒራ) ቁርኣን የነፍስ
ንግግር በሚል ትርጉም ከወሰድነው እርሱ ፍጡር አይደለም፡፡ ቁርኣን የምናነበው ቃላት
በሚል ከተረጎምነው ደግሞ እርሱ ፍጡር ነው፡፡ ነገር ግን ቁርኣን ፍጡር ነው ያልነው
ከምናነበው ቃላት አኳያ መሆኑን የምንገልጸው ትምህርት በምንሰጥበት ጊዜ እንጅ
(ከዚያ ውጭ) እንከለከላለን፡፡ ምክንያቱም ምናልባት የአላህ (በነፍሱ ላይ ቋሚ
የሆነው) የንግግሩ ትርጉም ፍጡር ነው የሚል ብዥታ ስለሚፈጥር፡፡” ቱህፈቱል ሙሪድ ሸርህ
ጀውሀረቱ አትተውሂድ ፡ ገጽ

አብዱረህማን ኢጅ የሚከተለውን ተናግሯል፡-“ድምጽ እና ሀርፎች ፍጡር ናቸው


በማለት ሙዕተዚላዎች የሚናገሩት እኛም በእርሱ የምንናገርበት መሆኑን እወቅ፡፡ በዚህ
ጉዳይ በእኛ እና በእነርሱ መካከል ጭቅጭቅ የለም፡፡ የነፍስ ንግግር መጽደቁን ግን እነርሱ
ይቃወማሉ… አልመዋቂፍ ሊልኢጅ ከአሻዒራ ዘንድ አንገብጋቢው ኪታብ ነው፡፡
37/68

ሐፊዝ ብን ሐጀር I የሚከተለውን ተናግረዋል፡-


“አሻዒራዎች የአላህ ንግግር ሀርፍም ድምጽም አይደለም ይላሉ፡፡ እነርሱ የነፍስን
ንግግር ነው የሚያጸድቁት፡፡ አገላለጹ ልክ እንደዓረብኛ እና አጀም (ከአረብኛ ውጭ)
የተለያየ ቢሆንም ሀቂቃው (እውነታው) በነፍስ ላይ ቋሚ የሆነው ትርጉም ነው፡፡
መለያየቱ ስለርሱ የሚገለጸው ነገር መለያየቱን አይጠቁምም፡፡ ስለርሱ የሚገለጸው
የነፍስ ንግግር ነው፡፡ አላህ በሀርፍ እና በድምጽ የሚናገር መሆኑን ሀንበልያዎች
አጽድቀዋል፡፡ ሀርፎች በቁርኣኑ ላይ በግልጽ ስለታዩ ነው፡፡ ድምጽን የከለከሉ ሰዎች
የሚከተለውን ምክንያት አቅርበዋል፡- ከጓዳ አየሩ ሲቆራረጥ የሚሰማ ድምጽ ነው፡፡
ለዚህ ምክንያት ድምጽን ያጸደቁ ሰዎች ደግሞ የሚከተለውን ምላሽ ሰጡ፡- የተገለጸው
ድምጽ ከሰው ልጆች ዘንድ ልክ እንደተለመደው መስማት እና መመልከት አይነት ነው፡፡
የጌታ ባህሪ ደግሞ በዚህ ተቃራኒ ነው፡፡ ማጥራትን አለመመሳሰልን አምኖ ከሆነ ግን
የተወሳው አደጋ (በውስጡ) አይዝም፡፡ ያለጉሮሮ ከሆነ ደግሞ ማመሳሰልን ፍጹም
አይዝም፡፡”
ዓብደሏህ ብን አህመድ ብን ሐንበል I ሱና በሚባለው ኪታቡ የሚከተለውን
ተናግሯል፡- አላህ ሙሳን በድምጽ አላናገረም ስለሚሉ ሰዎች አባቴን ጠየቅሁት፡፡
“አይደለም በድምጽ ነው የተናገረው” በማለት ምላሽ ሰጠኝ፡፡ እነዚህን ሐዲሶች
እንደመጡ አድርገን እናወራቸዋለን፡፡” ፈትሁል ባሪ ሊብን ሀጀር ጦብዓቱ አስሰለፍያ ዓብዱል ባቂ ወብኑ ባዝ

ሰለፍዮች ቁርኣን ፍጡር ያልሆነ የአላህ ንግግር እንደሆነ ያምናሉ፡፡ በሚሰማ


ድምጽና ሀርፍ እንደፈለገ በፈለገው ሰዓት ተናግሯል ብለው ያምናሉ፡፡ ወደጅብሪል
አስተላለፈው ፣ ጅብሪል ደግሞ በሙሐመድ ‫ﷺ‬ልቦና ላይ አወረደው ብለው ያምናሉ፡፡
38/68

በዚህ ላይ ቁርኣን ፣ ሱና እና የሰለፎች ስምምነት ጥቆማ ያደርጋል፡፡


ከቁርኣን ማስረጃዎች መካከል የሚከተሉት ይገኛሉ ፡-
﴾ُ‫نسى لِ ِمي َقاتِنَا َوَُلم َمهُ َربه‬
َ ‫﴿ َولَ مما َجاٍ ُم‬
“ሙሳም ለቀጠሯችን በመጣና ጌታውም ባነጋገረው ጊዜ” አል አዕራፍ፡

‫ك إِ َم‬ ِ ِ ِ
﴾‫َل‬ َ ‫يسى إِِهِن ُمتَ َنفه‬
َ ُ‫يك َوَرافع‬ َ ‫اّللُ ََي ع‬
‫ال ه‬َ َ‫﴿إِ ْذ ق‬
“አላህም ባለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ዒሳ ሆይ! እኔ ወሳጂህ ወደ እኔም አንሺህ
ነኝ፡፡” አል ዒምራን፡

﴾‫ب الطنِر ْاْلَْْيَ َِ َوقَ مربْنَاهُ ََِنيًّا‬


ِ ِ‫﴿و ََن َديْنَاهُ ِمَ َجان‬
َ
“ከጡር ቀኝ ጎን በኩልም ጠራነው፡፡ ያነጋገርነውም ሲሆን አቀረብነው፡፡” መርየም፡

﴾ِ‫اّلل‬ ِ
‫استَ َج َارَك فَأَجْرهُ َح مَّت يَ ْس َم َع ًَُلَ َم ه‬
ْ ‫ي‬
ِ ِ ‫﴿وإِ ْن أ‬
َ ُ‫َح ٌد هم ََ الْ ُم ْش ِر‬
َ َ
“ከአጋሪዎችም አንዱ ጥገኝነትን ቢጠይቅ የአላህን ቃል ይሰማ ዘንድ
አስጠጋው፡፡” አት ተውባ፡

َ‫اّللِ قُ ُّ لم‬
‫يدو َن أَن يُبَ هِدلُنا َُ ًَل َم م‬ ِ ِ
ُ ‫وَن نَتمبِ ْع ُك ْم يُِر‬ َ ‫نل الْ ُم َخلم ُفن َن إِ َذا انطَلَ ْقتُ ْم إِ ََ َمغَاِنَ لتَأْ ُخ ُذ‬
َ ‫وها َذ ُر‬ ُ ‫﴿ َسيَ ُق‬
﴾ُّ ُ ‫اّللُ ِمَ قَ ْب‬
‫ال م‬َ َ‫نَن َُ َذلِ ُك ْم ق‬
َ ُ‫تَتمبِع‬
“ወደዘረፋዎች ልትይዟት በሄዳችሁ ጊዜ እነዚያ ወደ ኋላ የቀሩት ሰዎች “ተውን
እንከተላችሁ” ይሏችኋል፡፡ (በዚህም) የአላህን ቃል ሊለውጡ ይፈልጋሉ፡፡
“ፈጽሞ አትከተሉንም ፡፡ ይህን (ቃል) ከዚህ በፊት አላህ ብሏል” አል ፈትህ፡

ቁርኣን ፍጡር ላለመሆኑ ማስረጃ


ْ ُ‫﴿أَالَ لَه‬
﴾‫اْلَْل ُق َواْل َْمُر‬
“ንቁ! መፍጠርና ማዘዝ የእርሱ ብቻ ነው፡፡” አል አዕራፍ፡
39/68

ትእዛዝን ከመፍጠር ሌላ አደረገው፡፡ ቁርኣን ደግሞ ከትዕዛዙ ነው፡፡


ማስረጃው የሚከተለው የቁርኣን አንቀጽ ነው፡-
﴾‫وحا ِهم َْ أ َْم ِرََن‬ ِ
َ ‫ك أ َْو َحْي نَا إِلَْي‬
‫ك ُر ا‬ َ ‫﴿ َوَُ َذل‬
“እንደዚሁም ወደ አንተ ከትእዛዛችን ሲሆን መንፈስን (ቁርአንን) አወረድን”
አሽ ሹራ፡

﴾‫َنزلَهُ إِلَْي ُك ْم‬ ِ‫﴿ذَلِك أَمر م‬


َ ‫اّلل أ‬ ُْ َ
“ይህ የአላህ ፍርድ ነው፡፡ ወደአንተ አወረድነው፡፡” አጥ ጦላቅ፡

የአላህ ንግግር ከባህሪያቶች አንዱ ባህሪ ነው፡፡ ባህሪው ደግሞ ፍጡር አይደለም፡፡
ከሱና ማስረጃዎች
ረሡል ‫ ﷺ‬በአስቸጋሪ ወቅት ላይ ነፍሳቸውን ወደ ሰዎች ባቀረቡ ጊዜ የተናገሩት
የሚከተለው ንግግር ነው፡-
‫ فإن قريشا قد منعوني أن أبلغ كالم‬، ‫"أال رجل يحملني إلى قومه ألبلغ كالم ربي‬
"‫ربي عز وجل‬
“ንቁ! (ከለላ ሆኖ) የጌታየን ንግግር እንዳደርስ ወደህዝቦቹ የሚወስደኝ የለም!
ቁረይሾች የጌታየን ንግግር ከማድረስ በእርግጥ ከለከሉኝ፡፡” አቡዳውድ፡ ቲርሚዚይ፡
ኢብኑ ማጀህ፡

የሚከተለው የረሡል ‫ ﷺ‬ንግግር ነው፡-


‫ إن هللا يأمرك أن‬:‫ فينادي بصوت‬. ‫ لبيك وسعديك‬: ‫ يا آدم ! فيقول‬: ‫"يقول هللا تعالى‬
"‫تخرج من ذريتك بعثا إلى النار‬
“አደም ሆይ! በማለት አላህ ይናገራል፡፡ “አቤት! አቤት! ጥሪህን አክባሪ ነኝ!”
“ከዘሮችህ ወደእሳት የሚሄዱ ጀማዓዎችን እንድታወጣ አላህ ያዝሐል፡፡” በማለት
በድምጽ ይጣራል፡፡” ቡኻሪ፡
40/68
የአላህ ንግግር ቃልም ትርጉምም በአንድ ላይ ተጣምሮ ነው፡፡ ቃል ብቻውን
አይደለም ወይም ትርጉም ብቻውን አይደለም፡፡ የአላህን ንግግር አስመልክቶ የአህለሱና
ወልጀማዓ ንግግር ይህ ነው፡፡
ዓድይ ብን ሃቲም e የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፏል የአላህ መልእክተኛ ‫ﷺ‬
የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-
“ከእናንተ አንድም አካል አይኖርም ፣ የቂያማ ቀን በአላህና በእርሱ መካከል ምንም
አስተርጓሚ ሳይኖር አላህ የሚያናግረው ቢሆን እንጅ፡፡ ከዚያም ይመለከታል፡፡ ፊት ለፊቱ
አንድም ነገር አይመለከትም፡፡ ፊት ለፊቱ ይመለከታል እሳት በፊት ለፊቱ አቅጣጫ
ትኖራለች፡፡ ከእናንተ መካከል ከእሳት መጠንቀቅ ለቻለ በተምር ስንጣቂ እንኳ ቢሆን
(እሳትን ይከላከል)” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

የአላህን ቃል በተመለከተ ከሰለፎችና ከሱና መሪዎች ንግግሮች


ማሊክ ብን አነስ I የሚከተለውን ተናግሯል፡-
"‫"من قال القرآن مخلوق يوجع ضربا ويحبس حتى يموت‬
“ቁርኣን ፍጡር ነው ያለ በግርፋት ማሳመም ፣ እስከሚሞት ማሰር” አስ ሱንና ሊዓብደላህ ብን
አህመድ፡

ሙሐመድ ብን አዕየን I ከነድር ብን ሙሐመድ I ይዞ የሚከተለውን ተናግሯል፡-


የሚከተለውን የቁርኣን አንቀጽ ፍጡር ነው ያለ ሰው ከሐዲ ነው፡፡
﴾‫ص ًَل َة لِ ِذ ُْ ِري‬
‫اعبُ ْدِِن َوأَقِِم ال م‬
ْ َ‫اّللُ َال إِلَهَ إِمال أ َََن ف‬
‫﴿إِنمِِن أ َََن م‬
“እኔ አላህ ነኝ፡፡ ከእኔ በቀር (በእውነት የሚመለክ) አምላክ የለምና (እኔን
ብቻ) ተገዛኝ” ጦሃ፡ ወደዓብደላህ ብን ሙባረክ I መጣሁ “አላህ ይቅር ይበለው
አቡሙሀመድ እውነት ተናገረ ፤ አላህ ፍጡርን እንድንገዛ አያዝም” የሚል ቃል
ተናገረ፡፡ አስ ሱንና ሊዓብደላህ ብን አህመድ፡
41/68
ዓምር ብን ዲናር I የሚከተለውን ተናገሩ ፡-
ከሰባ አመት ጀምሮ የነብዩን ‫ ﷺ‬ባልድረቦችና ከእነርሱ በታች የሆኑትንም አግኝቻለሁ፡፡
የሚከተለውንም ይናገሩ ነበር፡-
"‫ وإليه يعود‬، ‫ منه خرج‬، ‫ والقرآن كالم هللا‬، ‫ وما سواه مخلوق‬، ‫"هللا الخالق‬
“አላህ ፈጣሪ ነው ፤ ከእርሱ ውጭ ያለው ፍጡር ነው ፤ ቁርዓን የአላህ ንግግር ነው ፤
ከእርሱ ወጣ ፣ ወደርሱ ይመለሳል፡፡” ዳሪሚይ አር ረድ ዓለል ጀህሚያህ፡ ገፅ

ሱፍያን ብን ዑየይናህ I የሚከተለውን ተናግሯል፡-


ከሰባ አመት ጀምሮ ሽማግሌዎቻችንን አግኝቻለሁ፡፡ ከእነርሱ መካከል ዐምር ብን ዲናር
I ይገኝበታል፡፡ የሚከተለውን ይናገር ነበር፡-
"‫"القرآن كالم هللا وليس بمخلوق‬
“ቁርኣን የአላህ ንግግር ነው፡፡ ፍጡር አይደለም” ኸልቁ አፍዓሊል ዒባድ ሊል ቡኻሪ፡

ኢማም አህመድ I የሚከተለውን ተናግረዋል፡-


“ከቁርኣን በርካታ ቦታዎች ላይ አላህ ንግግሩን አውስቷል፡፡ ንግግር ብሎ ጠርቶታል፡፡
ፍጡር ብሎ አልጠራውም፡፡” አር ረዱ ዓለልህሚሚቲ ወዘናቀቲ፡ ገፅ ከዚያም ከቁርኣን ማስረጃ
አወሳ

አሁንም በተጨማሪ የሚከተለውን ተናገረ፡- “ቁርኣን ፍጡር ነው ያለ ሰው ከእኛ


ዘንድ ከሀዲ ነው፡፡ ምክንያቱም ቁርኣን ከአላህ እውቀት ነው፡፡” አላህ የሚከተለውን
ተናግሯል፡-
َ ‫ك فِ ِيه ِمَ بَ ْع ِد َما َج‬
﴾‫اٍك ِم ََ الْعِْل ِم‬ َ ‫﴿فَ َم َْ َحآ مج‬
“እውቀቱም ከመጣልህ በኋላ በርሱ (በኢሳ) የተከራከሩህን ሰዎች” አል ዒምራን ፡
42/68
ِ ِ ‫﴿ولََ تَرضى عنك الْي هند والَ النمصارى ح مَّت تَتمبِع ِملمت هم قُ ُّ إِ من ه َدى‬
‫اٍهم‬ َ ‫اّلل ُه َن ا َْلَُدى َولَئ َِ اتمبَ ْع‬
ُ ‫ت أ َْه َن‬ ‫ه‬ ُ ْ َُْ َ َ ََ َ ُ َُ َ َ َ ْ َ
ِ َ‫ك ِمَ اّللِ ِمَ وَِل والَ ن‬
﴾‫صْي‬ َ ‫ل‬
َ ‫ا‬‫م‬ ِ
‫م‬ ‫ل‬
ْ ِ‫اٍك ِمَ الْع‬
َ ‫ج‬ ‫ي‬‫ذ‬ِ ‫ب ع َد الم‬
َ‫َه‬ ‫ه‬ َ َ َ َ َْ
“አይሁዶችና ክርስቲያኖችም ሃይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ካንተ
ፈጽሞ አይወዱም፡፡ “የአላህ መምራት (ትክክለኛው) መምራት እርሱ ብቻ
ነው” በላቸው፡፡ ከዚያም እውቀቱ ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌያቸውን ብትከተል
ለአንተ ከአላህ (የሚከለክልልህ) ዘመድና ረዳት ምንም የለህም፡፡” አል በቀራህ፡

َ‫ض ُهم بِتَابِع قِْب لَة‬ ِ


ُ ‫َنت بِتَابِع قْب لَتَ ُه ْم َوَما بَ ْع‬
َ ‫ك َوَما أ‬
ِ
َ َ‫اب بِ ُك ِه ُّ آيَة ما تَبِعُناْ قْب لَت‬ ِ
َ َ‫يَ أ ُْوتُناْ الْكت‬
ِ ‫﴿ولَئَِ أَتَي م‬
َ ‫ت ال ذ‬ َْ ْ َ
ِِ ِ َ ‫اٍهم ِهمَ بَ ْع ِد َما َج‬
َ ‫اٍك ِم ََ الْعِْل ِم إِنم‬ ِ
﴾‫ي‬ َ ‫ك إِ َذا لمم ََ الظمالم‬ ُ ‫ت أ َْه َن‬ َ ‫بَ ْعض َولَئ َِ اتمبَ ْع‬
“እነዚያንም መጽሐፍን የተሰጡትን በአስረጅ ሁሉ ብትመጣቸው ቂብላህን
አይከተሉም፡፡ አንተም ቂብላቸውን ተከታይ አይደለህም፡፡ ከፊላቸውም የከፊሉን
ቂብላ ተከታይ አይደሉም፡፡ ከእውቀትም (ከራእይ) ከመጣልህ በኋላ
ዝንባሌያቸውን ብትከተል አንተ ያን ጊዜ ከበዳዮች ነህ፡፡” አል በቀራህ፡ አስ ሱንና
ሊዓብደላህ ብን አህመድ፡

ኢብን ተይሚያ I የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

“ከሙስሊም መሪዎችና ከሰለፎች አላህ በድምጽ አይናገርም ብሎ የሚናገር


አልነበረም፡፡ ይልቁንም ከበርካታ ሰለፎችና የሙስሊም መሪዎች የተረጋገጠው አላህ
በድምጽ ይናገራል የሚለው ነው፡፡ ከሰለፎችና ከሙስሊም መሪዎች በታወቀው
ንግግር የመጣው ይህ ነው፡፡ ሰለፎችና የሙስሊም መሪዎች አላህ በድምጽ መናገሩን
የሚገልጹ የቀደምቶችን ንግግር ያስታውሱ ነበር፡፡ ከእነርሱ መካከል እርሷን
የተቃወማት አንድም የለም፡፡
43/68

ዓብደላህ ብን አህመድ I የሚከተለውን ተናግረዋል፡- “ሰዎች አላህ በድምጽ


አይናገርም” ይላሉ በማለት ለአባቴ ነገርኩት፡፡ “ልጀ ሆይ! እነዚህ ሰዎች ጀህምያ
ናቸው፡፡ እነርሱ የሚሽከረከሩት የአላህን ባህሪ በማራቆት ላይ ነው” በማለት ምላሽ
ሰጠኝ፡፡ ከዚያም በዚህ ዙሪያ የተወሩትን የሰለፎችን ንግግር አወሳ፡፡ ከእነርሱ መካከል
“ኸልቂ አፍዓሊል ዒባድ” በሚባለው ኪታብ ቡኻሪ የተናገሩትን ጠቀሰ፡፡ “አላህ
በድምጽ መናገሩ ግልጽ ነው ፤ በአላህ ድምጽ እና በባሮች ድምጽ መካከል ልዩነት
አለው፡፡” በዚህ ዙሪያ ከነብዩ ‫ ﷺ‬ሐዲሶች በርካቶችን አወሳ ፣ እንደዚሁ በዚሁ
ጉዳይ በሶሂህ ኪታቡ ላይ ርእስ አብጅቷል … መጅሙዕ አልፈታዋ ፡

ኢብን ተይሚያ ‫ ﷺ‬እንደዚሁ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

“አላህ በድምጽ እንደሚጣራ የሚገልጹ ከነብዩ ‫ ﷺ‬ከሶሃቦች ከታብዕዮችና ከእነርሱ


በኋላ ከመጡ የሱና መሪዎች በርካታ ንግግሮች መጠዋል፡፡ አላህ ሙሳን ተጣርቷል ፣
የቂያማ ቀን ባሮችን በድምጽ ይጣራል፡፡ ወህይን (ራእይን) በድምጽ ይናገራል፡፡ አላህ
ያለድምጽና ያለ ሀርፍ ይናገራል የሚል ከሰለፎች አንድም የተገኘ ንግግር የለም፡፡ አላህ
በድምጽና በሀርፍ መናገሩን የተቃወመ አካል እንደሌለ ሁሉ ሙሳ የሰማው ድምጽ
ቀደምት ነው ወይም ጥሪው ቀደምት ነው ያለ አንድም የለም፡፡ ቁርኣን ከሚያነቡ ሰዎች
የሚሰማው ድምጽ በእርሱ አላህ የተናገረው መሆኑ በአላህ ንግግርና በባሮች ንግግር
መካከል ልዩነት እንዳለ በርካታ የሰለፎች ንግግር መጧል፡፡

አላህ በድምጽ መናገሩን የሚቃወምን ሰው የሱና መሪዎች እንደ ጀህምያ ይቆጥሩት


ነበር፡፡ ኢማም አህመድ I አላህ በድምጽ አይናገርም ብሎ ስለሚናገር ሰው ተጠየቁ፡፡
እነርሱ በተዕጢል (የአላህን ባህሪ በማራቆት) ዙሪያ የሚሽከረከሩ ጀህምይ ናቸው
44/68

በማለት ምላሽ ሰጠዋል፡፡

በዚህ ዙሪያ ከሰለፎች የተወሩ አንዳንድ ንግግሮችን እንዲሁም ይህን ጉዳይ


አስመልክቶ በሱና ኪታቦች ውስጥ ያዘጋጀ እንዳለ አወሳ፡፡ ከዚህ መካከል ቡኻሪ
በትንሹም ቢሆን በሶሂህ ኪታቡ የሚከተለውን ቁርኣን ርዕስ አድርጓል፡፡
﴾‫ع َعَ قُلُنِِِ ْم‬
َ ‫﴿ َح مَّت إِ َذا فُهِز‬
“ከልቦቻቸው ድንጋጤው በተገለጸም ጊዜ” አስ ሰበእ፡

“ኸልቂል አፍአል” በሚባለው ኪታቡም ሁለቱን - የአላህና የባሮቹን - ድምጾች


ልዩነት እንዳላቸው የበርካታ የሰለፎችን ንግግሮች ማስረጃ አድርጎ አቅርቧል፡፡ መጅሙዕ
አልፈታዋ ፡

“ቂዋሙ ሱናህ” በሚል ቅጽል ስም የሚታወቁት በ 535 ሒጅራ አቆጣጠር የሞቱት


ሀፊዝ አቡልቃሲም I የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

“ከሀርፎችና ከድምጾች ውጭ ያለ ትክክለኛ ንግግር እንደማይሆን የአረብኛ ባለቤቶች


ሁሉ ተስማምተዋል፡፡” አልሁጀቱ ፊ በያኒል መሀጃ ፡

ሰጅዝዩ I የሚከተለውን ተናግሯል፡-


“ከዓረቦች ዘንድ ጥሪ የሚባለው ድምጽ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ ከአላህ የሆነው ድምጽ
ላለመሆኑ ከአላህም ይሁን ከረሡል የመጣ (መረጃ) የለም፡፡” ሪሳለቱ አስጅዚይ ኢላ አህሊ
ዙበይድ ፊ ረድ ዓላ መን አንከረ አልሀርፈ ወስሶውት ፡ ገጽ

ኢማም አልቡኻሪ I የሚከተለውን ተናግረዋል፡-


“አላህ የቅርቡ እንደሚሰማው ሁሉ ለሩቁም በሚሰማው ድምጽ ይጣራል፡፡ ይህ
የተወሳው ከአላህ ውጭ ላለ አይደለም፡፡ አቡ አብዲላህ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
45/68

የአላህ ድምጽ የፍጡርን ድምጽ እንደማይመስል ይህ ማስረጃ ነው፡፡ ምክንያቱም


የአላህ ድምጽ ከቅርብ ያለ እንደሚሰማው ሁሉ የሩቁም ይሰማዋል፡፡ መላኢካ በአላህ
ድምጽ (ራሳቸውን ስተው) ይወድቃሉ፡፡ መላኢካዎች (እርስ በርሳቸው) ሲጠራሩ
ግን አይወድቁም፡፡ አላህ በተከበረው ቁርኣን የሚከተለውን ተናግሯል፡-
َ ‫﴿فًَلَ ََْت َعلُناْ ِهّللِ أ‬
﴾‫َندادا َوأَنتُ ْم تَ ْعلَ ُمن َن‬

“እናንተም (ፈጣሪነቱን) የምታውቁ ስትሆኑ ለአላህ ባላንጣዎችን አታድርጉ፡፡”


(አል’በቀራህ፡ 22)

ለአላህ ባህሪያት ቢጤ ፣ አቻ የለውም፡፡ ከባህሪያቶቹ አንዳች ከፍጡራን ላይ የሚገኝ


የለም፡፡” (ኸልቁ አፍዓሊል ኢባድ ሊል ቡኻሪ ገጽ፡ 98)

ኢብን ተይሚያ I የሚከተለውን ተናግረዋል፡- አላህ ሙሳን ማናገሩ ፣ ሙሳ ደግሞ


የአላህን ንግግር መስማቱን በኪታቡ መናገሩ የሚጠቁመው በድምጽ እንዳናገረው ነው፡፡
ድምጽ እንጅ አይሰማም፡፡ ሙሳን አስመልክቶ አላህ በኪታቡ ተናግሯል፡-
﴾‫نحى‬ ِ ِ َ‫﴿وأ َََن اخْتُك ف‬
َ ُ‫استَم ْع ل َما ي‬
ْ َ َْ ْ َ
“እኔም መረጥኩህ ፤ የሚወረድልህንም ነገር አዳምጥ” (ጡሃ ፡ 13) (መጅሙዕ አልፈታዋ ፡
6/531)

➢ ኸበርይ በሆነው (ከአላህና ከረሡል በተነገረን) ባህሪያት ለምሳሌ የአላህን ፊት ፣


ሁለት እጆች ፣ ሁለት አይኖች በተመለከተ ባህሪያትን ማራቆት ትርጉሙን ማጣመም
የአሽዓርይ ዓቂዳ (እምነት) ነው፡፡ ምክንያቱም(እነዚህን ባህሪያት እንዳሉ)
ማጽደቅ ከእነርሱ ዘንድ ለአላህ አካልን ያስይዛል ብለው ያስባሉ፡፡ በዚህ ምክንያት
አህለሱናዎችን ሙጀሲማ (አካል አድራጊ) ብለው ይጠሯቸዋል፡፡ (ተፍሲር ራዚ 12/395
ተመልከት)
46/68
ሰለፍዮች ያለምንም ማጣመም እና ማራቆት ባህሪያትን ከአላህ ልቅና ጋር በሚስማማ
ሁኔታ ያጸድቃሉ፡፡

አቡል መዓሊ አልጁወይኒ የሚከተለውን ተናግሯል፡- “መሪዎቻችን የተጓዙበት መንገድ


ሁለት እጆች ፣ ሁለት አይኖች እና ፊት የሚባሉ ባህሪያት ለጌታ የተረጋገጡ መሆኑን
ነው፡፡ እነዚህን ባህሪያት የማጽደቂያ መንገዱ የዓቅል ጉዳይ ሳይሆን ሰምዕይ (ቁርኣንና
ሐዲስ) ናቸው፡፡

አሁንም በተጨማሪ የሚከተለውን ተናገረ፡- ነገር ግን ከእኛ ዘንድ ትክክለኛ ሆኖ


ያገኘነው ሁለት እጆችን ችሎታ ፣ ሁለት አይኖችን መመልከት ፣ ፊትን ደግሞ መገኘት
ብለን መተርጎሙ ነው፡፡”

የጁወይኒይን ንግግር ካጣቀሰ በኋላ ኢብን ተይሚያህ I የሚከተለውን ተናግሯል፡-


“የኩላብያና የአሽዓርያ መሪዎች እነዚህን ባህሪያት እንደሚያጸድቁ ግልጽ ሆኗል፡፡
እርሱ (ጁወይኒ ግን) መሪዎቹን ተቃርኖ ከሙዕተዚላ ጋር ነው የተስማማ፡፡” አት ቲስዒንያ፡

ወደኋላ በመጡ አሻዒራዎች ተቃራኒ ከአሽዓርያ ቀደምቶች ጁወይኒይ ፣ ራዚ እና


ሌሎች ኸበርይ (ከአላህና ከረሡል ‫ ﷺ‬በኩል የሚታዎቁ) ባህሪያትን ያጸድቃሉ፡፡

ኢብን ዑሰይሚን I የሚከተለውን ተናግረዋል፡- “አህለሱና ወልጀማዓ ለአላህ በልቅና


እንዲሁም በክብር የተገለጸ የሆነ የፍጡራንን ያልመሰለ እውነተኛ ፊት አለው ይላሉ፡፡
ከአላህ በደረሰን መረጃ መሰረት እርሱ አካላዊ ከሆኑት ባህሪያት መካከል አንዱ ነው፡፡
ከአላህ በደረሰን መረጃ ያገኘናቸው አካላዊ መገለጫዎች የማይወገዱ ናቸው፡፡ በእርሷ
ከመገለጽም አይወገድም፡፡ ከእኛ አኳያ የሰውነት ክፍል በመባል የሚጠራው ነው፡፡
47/68

ትክክለኛ ፊት ለአላህ አለው መባልን ሙዓጢላዎች (አራቋቾች) ይቃወማሉ፡፡ “ፊት”


ማለት የተፈለገበት ምንዳ ወይም አቅጣጫ እና የመሳሰሉ ትርጉሞች አሉት ይላሉ፡፡ ይህ
ለግልጽ ቃሉ እንዲሁም ኡለሞች የተስማሙበትን ተቃራኒ የሆነ ማጣመም ነው፡፡ ምንዳ
የሚባለው በልቅና እና በልግስና አይገለጽም፡፡ አላህ ፊቱን በልቅና እና በልግስና ነው
የገለጸው፡፡
ِْ ‫اَلًََل ِل و‬
﴾‫ال َُْرِام‬ َ ‫﴿ َويَْب َقى َو ْجهُ َربِه‬
َ ْ ‫ك ذُو‬
“የልቅናና የልግስና ባለቤት የሆነው የጌታህ ፊትም ይቀራል፡፡” አር ረህማን ፡ ተፍሲሩ
አልፋቲሃ ወልበቀራህ ሊብን አል ዐሰይሚን፡

በተጨማሪ የሚከተለውን ተናገረ… አምስተኛው ህግ፡ “ሲፋቱ ሱቡትያ (የሚጸድቁ


ባህሪያት)” ለሁለት ይከፈላል፡፡ አካላዊ እና ተግባራዊ በመባል፡፡

አካላዊ የሚባለው ያልተወገደ በእርሷ በመገለጽ የማይወገድ ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ ፡


እውቀት ፣ ችሎታ ፣ መስማት ፣ መመልከት ፣ ልቅና ፣ ጥበብ ፣ የበላይነት ፣ ታላቅነት
፣ ከእርሷው የሆነ “ሲፋቱ ኸበርያ (ከአላህና ከረሡል በኩል የሚታወቁ የአላህ
ባህሪያቶች” ፊት ፣ ሁለት እጆች ፣ ሁለት አይኖች ናቸው፡፡

“ሲፋቱል ፊዕልያ (ተግባራዊ ባህሪያት)”፡ ከአላህ መሽኣ ጋር የተቆራኙ ናቸው፡፡


ከፈለገ የሚሰራቸው ካልፈለገ የሚተዋቸው፡፡ በዓርሽ ላይ መሆን ፣ ወደቅርቢቱ ሰማይ
መውረድ እንደምሳሌ ይጠቀሳሉ፡፡

አንድ ባህሪ ከሁለት ነገሮቸ አኳያ አካላዊም ተግባራዊም ሊሆን ይችላል፡፡ ንግግር
ለዚህ ምሳሌ ይሆናል፡፡ ከመሰረቱ አኳያ ሲታይ ሲፈተ ዛትያ (አካላዊ ባህሪ) ይሆናል፡፡
ምክንያቱም ተናጋሪ ከመሆን አላህ አልተወገደም አይወገድምም፡፡ (አልፎ አልፎ
48/68

የሚናገራቸውን) አንዳንድ ንግግሮች ከተመለከትን ደግሞ ሲፈተል ፊዕልያ (ተግባራዊ


ባህሪያት) ይሆናል፡፡ ምክንያቱም ንግግር ከመሽአ ጋር ተቆራኝቷል፡፡ በፈለገ ሰዓት
ይናገራል የፈለገውን ነገር ይናገራል፡፡

َ ‫﴿إِمَّنَا أ َْمُرهُ إِ َذا أ ََر َاد ََْي ئاا أَ ْن يَ ُق‬


﴾‫نل لَهُ ُُ َْ فَيَ ُكن ُن‬

“ነገሩም አንዳችን በሻ ጊዜ ሁን ማለት ነው፡፡ ወዲያው ይሆናልም፡፡” ያሲን፡

ማንኛውም ባህሪ ከመሽአ ጋር ከተቆራኘ ለእርሱ ጥበብ ተከታይ መሆኑ መታወቅ


አለበት፡፡

ጥበቡ ለእኛ ሊታወቅ ይችላል ፤ ማወቁም ሊሳነን ይችላል፡፡ ነገር ግን እኛ አላህ


የሚሻው ከጥበቡ ጋር የሚገጥም መሆኑን በእርግጠኛነት እናውቃለን፡፡ አንድ ነገር
አይሻም ለጥበቡ የሚገጥም ቢሆን እንጅ፡፡ ይህንንም የሚከተለው ቁርኣን ይጠቁማል፡፡
﴾‫يما‬ ِ ِ ‫اّللُ إِ من م‬
‫﴿ َوَما تَ َش ُاؤو َن إِمال أَن يَ َشاٍ م‬
‫يما َحك ا‬
‫اّللَ َُا َن َعل ا‬
“አላህም ካልሻ በስተቀር አትሹም፡፡ አላህ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና፡፡” አል ኢንሳን፡
መጅሙዕ አል ፈታዋ ወር ረሳኢል ሊል ዑሰይሚን፡

ኢብን ተይሚያህ I የሚከተለውን ተናግሯል፡- “እኔ በቻልኩት ያክል የሰለፎችን ንግግር


ከተሟላ ጥናትና ዳሰሳ በኋላ ከእነርሱ በነስም (አሻሚ ትርጉም የሌለው) ፣ በዟሂርም
(ከአንድ በላይ ትርጉም ሊኖረው በሚችል) ፣ በቀራኢንም (በአመላካች መረጃዎች)
ሲፋተል ኸበርያን (ከአላህና ከረሡል ‫ ﷺ‬በኩል የሚታወቁ ባህሪያቶች) የሚያራቁት
የአንድንም ንግግር አለማየቴን አላህ ያውቃል፡፡ ይልቁንም -በነስም ፣ በዟሂርም
የተመለከትኩት ከእነርሱ ንግግር ብዙው የሚጠቁመው የባህሪያትን አይነት የሚያጸድቅ
49/68

ይልቁንም የተመለከትኩት የባህሪ አይነቶችን በጥቅል እንደሚያጸድቁ ነው፡፡ ከእነርሱ


መካከል ሲያራቁቱ አንድም አላየሁም፡፡ እነርሱ የሚያራቁቱ ማመሳሰልን ነው፡፡ አላህን
ከፍጡር ጋር የሚያመሳስሉትን አመሳሳዮችንና ባህሪያትን የሚያራቁትን ጨምረው
ያወግዛሉ፡፡”

የቡኻሪ ሸይኽ የሆኑት ኑዓይም ብን ሀማድ አልኹዛዒይ I የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

‫"من شبه هللا بخلقه فقد كفر ومن جحد ما وصف هللا به نفسه فقد كفر وليس ما‬
"‫وصف هللا به نفسه وال رسوله تشبيها‬

“አላህን ከፍጡራን ጋር ያመሳሰለ በእርግጥ ካደ ፣ አላህ በእርሱ ነፍሱን የገለጸበትን


ያስተባበለ በእርግጥ ካደ ፣ አላህ በእርሱ ነፍሱን የገለጸበት እንዲሁም ረሱል የገለጹበት
መመሳሰል የለውም፡፡”

አንድን ግለሰብ ባህሪያትን ሳያጸድቅ ማመሳሰልን በማራቆት ላይ የሰመጠ መሆኑን


ካወቁ ይህ ሙዓጢል ጀህምይ ነው ይሉት ነበር፡፡ ይህ በንግግራቸው ብዙ ይገኛል፡፡
ጀህምያና ሙዕተዚላ እስካሁኗ ቀን ድረስ ከባህሪያት አንድ እንኳ ያጸደቀን አካል
ሙሸቢህ (አመሳሳይ) ይሉታል፡፡ ይህ ከእነርሱ የሆነ ቅጥፈትና ውሸት ነው፡፡ ከእነርሱ
መካከል ወሰን በማለፍ ነብያቶችን የሚዘልፍ አለ፡፡ ሱማማ ብን አሽረስ የሚባለው
የጀህምያ መሪ ከነብያት መካከል ሶስቱ ሙሸቢህ ናቸው ብሎ ተናግሯል፡፡ ሙሳ d
የሚከተለውን ተናግሯል፡-
ِ ِ
َ ُ‫﴿إِ ْن ه َْ إِالم فْت نَ ت‬
﴾‫ك‬

“እርሷ (ፈተናይቱ) ያንተ ፈተና እንጂ ሌላ አይደለችም” አል አዕራፍ፡


50/68

ኢሳ d የሚከተለውን ተናግሯል
َ ‫﴿تَ ْعلَ ُم َما ِِف نَ ْف ِسْ َوالَ أ َْعلَ ُم َما ِِف نَ ْف ِس‬
﴾‫ك‬
“በነፍሴ ውስጥ ያለውን ሁሉ ታውቃለህ፡፡ ግን በአንተ ነፍስ ያለውን
አላውቅም፡፡” አል ማኢዳህ፡

ሙሀመድ ‫ ﷺ‬የሚከተለውን ተናግሯል

“ጌታችን ይወርዳል …” ቡኻሪ፡ ፡ ሙስሊም፡

የሙዕተዚላ ታላላቅ የሚባሉት፡ የሙስሊም መሪዎችን -ማሊክ ፣ የእርሱ ባልደረባ ፣


ሰውሪይ ፣ የእርሱ ባልደረቦቹ ፣ አውዛዒይ ፣ የእርሱ ባልደረቦቹ ፣ ሻፍዕይ የእርሱ
ባልደረቦቹ ፣ አህመድ ፣ የእርሱ ባልደረቦቹ ፣ ኢስሐቅ ብን ራህዊያ ፣ አቡ ዑበይድ
እና ሌሎችም - ከሙሸቢሆች ይገባሉ ብለዋል፡፡” (መጅሙዕ አልፈታዋ 5/109-110)

➢ አሻዒራ የአህለሱና ወልጀማዓን ዓቂዳ የተቃረኑበት እጅግ በጣም ብዙ እንደሆነ ሌላ


ቦታ ላይ አውስቻለሁ

አሻዒራ አህለሱናን ከተቃረኑበት አንዱ የመረጃ ምንጫቸው ነው፡፡ የአህለሱና


ወልጀማዓ የመረጃ ምንጭ ሸሪዓ ሲሆን ከአሻዒራ -ምሳሌ፡ ሙዕተዚላና ጀህምያ- ዘንድ
የመረጃ ምንጫቸው ከቁርኣን ከሐዲስ ዓቅልን (አዕምሮን) ማስቀደም ነው፡፡

ተውሒድ ከአሻዒራ ዘንድ፡ አላህ አንድ ነው ፣ ለእርሱ አምሳያ የለውም የሚል


ትርጉም አለው፡፡ የኣላህን አብዛኛውን ባህሪያት ያራቁታሉ፡፡ በተለይም ከዚህ በፊት
እንዳሳለፍነው “ሲፋተል ኸበርያን” (በአላህና በረሡል ‫ ﷺ‬በኩል እንጅ የማይታወቁ
ባህሪያቶችን) ያራቁታሉ፡፡
51/68
ከእነርሱ ዘንድ “ላኢላሃ ኢልለሏህ” የሚለው ቃል ከአላህ በቀር በመፍጠር ችሎታ
ያለው አንድም አካል የለም የሚል ትርጉም አለው፡፡

ከሰለፍዮች ዘንድ ደግሞ፡ ተውሂድ ማለት አላህን በሩቡብያው ፣ በኡሉሑያው እና


በአስማእ ወስሲፋት ብቸኛ ማድረግ ነው፡፡

የ “ላኢላሃ ኢልለሏህ” ትርጉም ደግሞ ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም የሚል
ትርጉም አለው፡፡

አሽአሪያዎች ለአቂዳ በ “ኸበሩል አሀድ” (በአንድ ግለሰብ የተላለፈን ወሬ) ማስረጃ


አያደርጉም፡፡ ሰለፍዮች ግን በዓቂዳም ይሁን በሌላ ጉዳይ በ “ኸበሩል አሀድ” (በአንድ
ግለሰብ የተላለፈን ወሬ) ማስረጃ ያደርጋሉ፡፡ በዚህ መሰረት የቢድዓ ሰዎች ካልሆኑ
በቀር ከቀደምት ደጋግ የአላህ ባሮች አንድም የሚቃረን የለም፡፡

ኢማም አሽሻፍዒይ I የሚከተለውን ተናግረዋል፡- “የአንድን ሰው ወሬ በማጽደቅ ላይ


ከሙስሊም ፉቀሐዎች ዘንድ የተወዛገቡ አንድም አላሀፈዝኩም” አር ረሳኢል ሊሻፊዒይ፡

ኸጢብ አልበግዳዲ I የሚከተለውን ተናግሯል፡- “በኸበሩል ዋሂድ አጠቃላይ


ታብዒዮች ነበሩበት፡፡ ከእነርሱም በኋላ የመጡት ፉቀሀዎች እንዲሁም በሌሎች
ከተሞች የነበሩ ሙስሊሞች አሁን እስካለንበት ወቅት ድረስ የሰሩበት ነው፡፡ እርሱን
የተቃወመ ወይም ያወገዘ ከእነርሱ አንድም የደረሰን የተረጋገጠ ወሬ የለም፡፡ ለእኛ
የደረሰን ይህ ጉዳይ የሁሉም ዲን እንደሆነ እና ግዴታ እንደሆነ ነው፡፡ በእርሱ መስራቱ
ተገቢ እንዳልሆነ የሚመለከት ቢኖር ኖሮ ለእነርሱ መዝሐባቸው ሆኖ ወሬው ለእኛ
በደረሰን ነበር፡፡ ወሏሁ አዕ ለም” አል ካፊየቱ ፊ ዒልሚ አር ሪዋየቲ ሊኸጢብ አል ባግዳዲ፡ ገፅ
52/68

ኢማም ኢብን አብዱል በር I የሚከተለውን ተናግሯል፡- “እኔ እስከማውቀው ድረስ


በሁሉም ከተሞች የነበሩ የፊቅህና የአሰር (የሐዲስ) በአጠቃላይ የእውቀት ባለቤቶች
ሁሉ ኸበር አልዋሂድን (ፍትሀዊ የሆነ የአንድ ግለሰብ ወሬ) ትክክለኛ መሆኑ
ከተረጋገጠ በአሰር (በሐዲስ) ወይም በኢጅማዕ እስካልተሰረዘ ድረስ መቀበሉና
በእርሱ መስራቱ ግዴታ መሆኑን ነው፡፡ ልዩነታቸው ከቁጥር የማይገባ ኸዋሪጅና
ከአንዳንድ የቢድዓ ባለቤት ጭፍራዎች ካለሆኑ በቀር ከሶሃባ ጀምሮ አሁን እስካለንበት
ጊዜ ድረስ አጠቃላይ በየከተማው የሚገኙ ፉቀሀዎች ሁሉ በዚሁ መንገድ ላይ ናቸው፡፡”
(አት’ተምሂድ ሊማ ፊልሙወጠእ መነል ማዓኒ ወልአሳኒድ፡ 1/2)

➢ ከአሻዒራ ዘንድ (የአላህን መኖር ለማወቅ) የመጀመሪያው ዋጅብ (ግዴታ) ፡


መመራመር ወይም ወደምርምር ማሰብ ነው
➢ ከአሻዒራ ዘንድ የአላህ መኖር ሰዎችን በፈጠረበት ተፈጥሮ የሚታወቅ አይደለም
ከሰለፍዮች ዘንድ የመጀመሪያው ዋጅብ (ግዴታ) ፡ በአላህ ማመን ነው፡፡
የአሻዒራዎች ንግግር የቁርኣን ፣ የሱና ፣ የተፈጥሮን እና የዚህ ማህበረሰብ ቀደምቶች
የነበሩበትን ንግግር የሚቃረን በመሆኑ ውድቅ ነው፡፡
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
َ‫يَ الْ َقيِه ُم َولَ ِك م‬ ِ ِ‫اّللِ ذَل‬ ِ ‫اّللِ المِِت فَطَر النماس علَي ها َال تَب ِد‬ ِ‫﴿فَأَقِم وجهك لِل هِدي َِ حنِي افا ف‬
َ ‫ي ُّ ْلَْل ِق م‬
ُ ‫ك ال هد‬ َ ْ َ ْ َ َ َ ‫م‬ ‫ة‬
َ‫ر‬َْ‫ط‬ َ َ َْ َ ْ
ِ ‫أَ ُْثََر الن‬
﴾‫ماس َال يَ ْعلَ ُمن َن‬
“ወደ እውነት ተዘንባይ ሆነህም ፊትህን ለሃይማኖት ቀጥ አድርግ፡፡ የአላህን
ፍጥረት ያችን አላህ ሰዎችን በእርሷ ላይ የፈጠረባትን (ሃይማኖት ያዟት) ፡፡
የአላህን ፍጥረት መለወጥ የለም፡፡ ይህ ቀጥተኛ ሃይማኖት ነው፡፡ ግን አብዛኛዎቹ
ሰዎች አያውቁም፡፡” አር ሩም፡
53/68

አቡሁረይራ e የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፏል፡- የአላህ መልእክተኛ ‫ﷺ‬


የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-
“አንድም የሚወለድ የለም በተፈጥሮ (እምነቱ) የሚወለድ ቢሆን እንጅ ፣ ወላጆቹ
አይሁዳዊ ወይም ክርስቲያናዊ ወይም መጁሳዊ ያደርጉታል፡፡ አካሏ የተስተካከለ ሙሉ
እንስሳት እንደምትፈጠረው ከእርሷ ጀሮዋ ወይም ሌላው ብልቷ የተቆረጠ ታውቃላችሁ?”
ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

ከዚያም አቡሁረይራ e የሚከተለውን ይል ነበር ፡ ከፈለጋችሁ የሚከተለውን አንብቡ፡


َ‫يَ الْ َقيِه ُم َولَ ِك م‬ ِ ِ‫اّللِ ذَل‬ ِ ‫اّللِ المِِت فَطَر النماس علَي ها َال تَب ِد‬ ِ‫﴿فَأَقِم وجهك لِل هِدي َِ حنِي افا ف‬
َ ‫ي ُّ ْلَْل ِق م‬
ُ ‫ك ال هد‬ َ ْ َ ْ َ َ َ ‫م‬ ‫ة‬
َ‫ر‬َْ‫ط‬ َ َ َْ َ ْ
ِ ‫أَ ُْثََر الن‬
﴾‫ماس َال يَ ْعلَ ُمن َن‬
“የአላህን ፍጥረት ያችን አላህ ሰዎችን በእርሷ ላይ የፈጠረባትን (ሃይማኖት
ያዟት) ፡፡ የአላህን ፍጥረት መለወጥ የለም፡፡ ይህ ቀጥተኛ ሃይማኖት ነው፡፡ ግን
አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም፡፡” አር ሩም ፡

ነብዩ ‫ ﷺ‬ሙዓዝን e ወደየመን በላኩ ጊዜ የሚከተለውን አሉት፡ “አንተ ወደ መጽሐፍ


ባለቤቶች ትሄዳለህ ፤ የመጀመሪያው ጥሪህ ወደአላህ አምልኮ ይሁን፡፡” በሌላ ዘገባ
“የመጀመሪያው ጥሪህ አላህን (በአምልኮ) ብቸኛ ማድረግ ይሁን፡፡” ቡኻሪ፡

በሌላ ዘገባ፡ “ወደነርሱ እንደሄድክ ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለ


ሙሐመድ የአላህ መልእክተኛ እንደሆኑ ጥራቸው” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

ኢብን አቢል ዒዝ I የሚከተለውን ተናግሯል፡- “በዚህ ምክንያት ለአቅመ አደም


በደረሰ ሰው ላይ ትክክለኛውና የመጀመሪያው ግዴታ ምርምር ሳይሆን ፣ ወይም
ምርምርን ዓላማ ማድረግ ሳይሆን ወይም መጠራጠር ሳይሆን ላኢላሃ ኢልለሏህ ብሎ
መመስከር ነው፡፡ ይህ ውግዝ የሆነ የፍልስፍና ባለቤት ንግግር ነው፡፡ ይልቁንም ባሪያው
54/68
ለመጀመሪያ ጊዜ የሚታዘዘው በሁለቱ የምስክርነት ቃሎች እንደሆነ የሰለፍ
(የቀደምት) አኢማዎች ሁሉም ይስማማሉ፡፡ ለአቅመ አዳም ከመድረሱ በፊት ይህን
የሰራ ሰው ለአቅመ አዳም ሲደርስ እንደገና እድሳት እንደማያስፈልገው የሰለፍ
አኢማዎች ተስማምተዋል፡፡ ለአቅመ አደም የደረሰ ወይም (ይህን ከሚመለከቱ ሰዎች
ዘንድ) ለተምይዝ (የሰባት አመት እድሜ) በደረሰ ጊዜ በውዱዕና በሶላት ይታዘዛል፡፡
ለአቅመ አደም የደረሰ ጊዜ ወልዩ ሁለቱን የምስክርነት ቃሎች መታደስ አለባቸው ብሎ
ግዴታ ያደረገ የለም፡፡ ሁለቱ የምስክርነት ቃሎችን ማረጋገጥ ግዴታ መሆኑ ሙስሊሞች
የተስማሙበት ቢሆንም ፣ የእርሱ ዋጅብነት የሶላትን ዋጅብነት ይቀድማል፡፡ ነገር ግን
እርሱ ይህን ዋጅብ ቀድሞ ፈጽሞታል፡፡” ሸርሕ አጥ ጧሃዊያ፡ ገፅ

ኢብን ተይሚያህ I የሚከተለውን ተናግሯል፡- “ነብዩ ‫ ﷺ‬ሙዓዝን ወደየመን በላኩበት


ቡኻሪና ሙስሊም በትክክለኛነቱ ላይ ስምምነት ባደረጉበት ሐዲስ ሶሃቦችን መጀመሪያ
ያዘዙት ወደሁለቱ ምስክርነት ቃሎች ጥሪ ማድረግ እንጅ ወደ ምርምር ወይም የፈጣሪን
መገኘት ብቻ በማጽደቅ ላይ ለአንድም አካል ጥሪ አለማድረጋቸው ተረጋግጧል፡፡”
“አንተ ወደመጽሐፍ ባለቤቶች ትሄዳለህ ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የሌለ
መሆኑን ሙሐመድ የአላህ መልእክተኛ እንደሆኑ የመጀመሪያው ጥሪህ ይሁን፡”
ሌሎችም ከነብዩ ‫ ﷺ‬የተወሩ ሐዲሶች ከዚህ ጋር የሚስማሙ ናቸው፡፡
በቡኻሪና ሙስሊም በተዘገበ ሐዲስ አቡሁረይራ e እና ኢብን ዑመር f
የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፈዋል፡-
‫"أمرت أن أقاتل الناس حتى يشهدوا أن ال إله إال هللا وأني رسول هللا فإذا فعلوا ذلك‬
"‫عصموا مني دماءهم وأموالهم إال بحقها وحسابهم على هللا‬
55/68
“ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የሌለ መሆኑን እና እኔ የአላህ መልክተኛ መሆኔን
እስከሚመሰክሩ ድረስ ሰዎችን ልጋደል ታዝዣለሁ፡፡ ይህን ከሰሩ በሐቁ ሲቀር ከእኔ
ደማቸውን ፣ ገንዘባቸውን ጠበቁ (በልባቸው በደበቁት ነገር) ምርመራው በአላህ ላይ
ነው፡፡”
ኢብን ዑመር f ያስተላለፈው ሐዲስ ደግሞ የሚከተለው ነው፡-
"‫"حتى يشهدوا أن ال إله إال هللا وأن محمدا رسول هللا ويقيموا الصالة ويؤتوا الزكاة‬
“ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የሌለ መሆኑን ፣ ሙሀመድ የአላህ መልክተኛ
መሆናቸውን እስኪመሰክሩ ፣ ሶላታቸውን (ደንቡን ጠብቀው) እስከሚሰግዱ ዘካቸውን
እስከሚሰጡ ድረስ …” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡

ይህ ከመልእክተኞች ሐይማኖት በገሐድ የሚታወቅ መሆኑን የዲን መሪዎች ፣


የሙስሊም ልሒቃኖች የተስማሙበት ጉዳይ ነው፡፡ ማንኛውም ከሐዲ ምንም እምነት
የሌለውም ይሁን ወይም ሙሽሪክ ወይም የመጽሐፍ ባለቤት ወደ ሁለቱ የምስክርነት
ቃሎች ጥሪ ይደረግለታል፡፡ በዚህ ነው ከሀዲው ሙስሊም የሚሆነው፡፡ ከዚህ ውጭ
ሙስሊም መሆን አይችልም፡፡” ደርኡ ተዓሩድ አል ዓቅሉ ወን ነቅል፡

ኢማም ኢብን አልሙንዚር I የሚከተለውን ተናግሯል፡- “አንድ ከሐዲ እርሱ


ለአቅመ አዳም የደረሰ ጤናማ አዕምሮ ኖሮት ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የሌለ
መሆኑን ሙሐመድ የአላህ አገልጋይ እና መልእክተኛ መሆናቸውን ፣ ሙሀመድ
የመጡበት ሁሉ ሐቅ ነው ብሎ ከመሰከረ ፣ የኢስላም ሀይማኖትን ከሚቃረን ሁሉ
ከጠራ ሙስሊም ይሆናል፡፡ ከዚህ በኋላ ከተመለሰና ክህደትን ይፋ ካደረገ ሙርተድ
(ከኢስላም አፈንጋጭ) ይሆናል፡፡ ካልተጸጸተ ሸሪዓዊ ብይኑ መገደሉ ግዴታ ነው
በሚለው ሐሳብ የእውቀት ባለቤቶች ተስማምተዋል፡፡” አል ኢቅናእ ሊብን አል ሙንዚር፡
56/68
➢ ከአሻዒራ ዘንድ ኢማን የተሰጠው ትርጉም ፡ በልቡ እውነት ብሎ (ማረጋገጥ) ብቻ
ነው፡፡ አንዳንዶች በምላስ በመናገር ማረጋገጥን ይጨምሩበታል፡፡ እምነት
አይጨምርም አይቀንስም ይላሉ፡፡ ከእነርሱ ዘንድ ኢስቲስናእ (ኢንሻአላህ አማኝ ነኝ
ማለት) አይፈቀድም፡፡ ከአህባሽ ዘንድ ደግሞ ፡ ኢማን ማለት እውነት ብሎ ማረጋገጥ
ብቻ ነው፡፡
ኢማን ማለት ከሰለፍዮች ዘንድ፡ በምላስ መናገር ፣ በልብ ማረጋገጥ ፣ በአካል
መተግበር ማለት ነው፡፡ በመታዘዝ ይጨምራል ፣ ወንጀል በመፈጸም ይቀንሳል፡፡
ኢማም አልቡኻሪ I የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
የኢማንና ነብዩ ‫ ﷺ‬ኢስላም በአምስት መሰረቶቸ ላይ እንደተገነባ የተናገሩበት ክፍል፡፡
እርሱ (ኢማን) ንግግር እና ተግባር ነው፡፡ አላህ እንደተናገረው ይጨምራል ፣ ይቀንሳል
‫﴿لِيَ ْزَد ُادوا إِْيَ ا‬
﴾‫اَن‬
“እምነትን ይጨምሩ ዘንድ” አል ፈትህ፡
﴾‫﴿ َوِزْد ََن ُه ْم ُه ادى‬
“መመራትንም ጨመርንላቸው” አል ከህፍ፡
﴾‫يَ ْاهتَ َد ْوا ُه ادى‬ ِ ‫يد م م‬ ُ ‫﴿ َويَِز‬
َ ‫اّللُ الذ‬
“እነዚያንም የቀኑትን ሰዎች አላህ ቅንነትን ይጨምርላቸዋል፡፡ መርየም፡

﴾‫آَت ُه ْم تَ ْقن ُاه ْم‬


َ ‫يَ ْاهتَ َد ْوا َز َاد ُه ْم ُه ادى َو‬ ِ ‫﴿والم‬
‫ذ‬
َ َ
“እነዚያም የተመሩት (አላህ) መመራትን ጨመረላቸው፡፡ (ከእሳት)
መጥጠበቂያቸውንም ሰጣቸው፡፡” ሙሐመድ፡
﴾‫اَن َوُه ْم يَ ْستَ ْب ِشُرو َن‬
‫يَ َآمنُناْ فَ َز َاد ْْتُْم إِْيَ ا‬ ِ ‫﴿فَأَما الم‬
‫ذ‬
َ
“እነዚያ ያመኑትማ የሚደሰቱ ሲሆኑ እምነትን ጨመረላቸው፡፡” አት ተውባ፡

ِ ِ
﴾ُّ ‫ي‬ ‫﴿فَ َز َاد ُه ْم إِْيَاَنا َوقَالُناْ َح ْسبُنَا ه‬
ُ ُ‫اّللُ َون ْع َم الْ َن‬
57/68
“(ይህም) እምነትን የጨመረላቸው “በቂያችንም አላህ ነው ምን ያሚያምርም
መጠጊያ! “ያሉ ናቸው፡፡” አል ዒምራን፡

﴾‫يما‬ِ ‫﴿وما زادهم إِمال إِْي ا‬


‫اَن َوتَ ْسل ا‬َ ْ ُ َ َ ََ
“እምነትንና መታዘዝን እንጅ ሌላን አልጨመረላቸውም” አል አህዛብ፡

﴾‫ال بَلَى َولَ ِكَ لهِيَطْ َمئِ مَ قَ ْلِِب‬


َ َ‫ال أ ََوَلْ تُ ْمِمَ ق‬
َ َ‫ف َُْتيِ ْ الْ َم ْنتَى ق‬ ِ َ َ‫﴿وإِ ْذ ق‬
‫ال إِبْ َراه ُيم َر ِه‬
َ ‫ب أَِرِِن َُْي‬ َ
“ኢብራሂምም “ጌታዬ ሆይ! ሙታንን እንዴት ሕያው እንደምታደርግ አሳየኝ”
ባለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ አላህ፡- “አላመንክምን?” አለው፡፡ “አይደለም
(አምኛለሁ) ፤ ግን ልቤ እንዲረጋ” ነው አለ፡፡” አል በቀራህ፡

አቡሰዒድ አልኹድርይ e የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፈዋል፡-


የአላህ መልእክተኛ ‫ ﷺ‬ወደ (ዒድ) አልአድሃ ወይም (ዒድ) አልፊጥር መስገጃ ቦታ
ለስግደት ወጦ፡፡ በሴቶች በኩል አለፉ፡፡ “ሴቶች ሆይ! ሶደቃ ሶድቁ እሳት ውስጥ
ከሚገቡት ብዙዎች እናንተ እንደምትሆኑ እንድመለከት ተደርጌያለሁ፡፡” አሏቸው፡፡

“የአላህ መልእክተኛ ሆይ! በምን (ምክንያት) ነው? በማለት ሴቶች ጠየቁ፡፡


“እርግማን ታበዛላችሁ ፣ ውለታን ትክዳላችሁ ፣ ከዓቅልም ይሁን ከዲን ጎደሎ ሆኖ
የጠንካራ ወንድን ልቦና የሚሰልብ ከእናንተ የበለጠ አላየሁም” በማለት ተናገሩ፡፡

“የአላህ መልእክተኛ ሆይ! የዲንም የዓቅልም ጉድለቱ ምንድን ነው?” በማለት


ጠየቁ፡፡ የሴት ምስክር ከወንዱ ግማሽ አይደለምን?” በማለት ጠየቋቸው፡፡ “አዎ”
የሚል ምላሽ ሰጡ፡፡ “ይህ የዓቅል ጉድለት ነው፡፡” አሏቸው፡፡ “የወር አበባ የተመለከተች
ሴት ሶላት አትሰግድም አይደል?” በማለት ጠየቋቸው፡፡ “አዎ” አሉ፡፡ “ይህ ደግሞ የዲን
ጉድለት ነው፡፡” ቡኻሪ፡

ኢማም አልቡኻሪ I የሚከተለውን ተናግረዋል፡-


58/68

(የኢማን ባለቤቶች በተግባር ያላቸው መበላለጥ የሚል ክፍል)


ከዚያም የአቡ ሰዒድ አልኹድርይን e ሐዲስ ማስረጃ አቀረቡ፡፡ የአላህ መልክተኛ ‫ﷺ‬
የሚከተለውን ተናገሩ፡-
“የጀነት ሰዎች ጀነት ይገባሉ ፣ የእሳት ሰዎችም እሳት ይገባሉ፡፡ ከዚያም አላህ
የሚከተለውን ይናገራል ፡ ከልቡ ውስጥ የአንዲት ፍሬ ክብደት ያክል ኢማን ያለውን ሰው
አውጡ” በማለት ያዛል፡፡ ከእርሷ ከሰል መስለው ይወጣሉ ፡፡ ነሕረል ሀያት (የሒዎት
ወንዝ) ወይም (ማሊክ ተጠራጠረ) ሀያት ውስጥ ይጣላሉ ፤ ከወንዝ ዳር
እንደምትበቅል አትክልት ይበቅላሉ፡፡ ቀለሟ ቢጫ ፣ አቅመ ቢስ ሆና እንደምትበቅል
አላየህምን?” (ቡኻሪ፡ 22)
ከዚያም የአቡ ሰዒድ አልኹድርይን e ሐዲስ ማስረጃ አቀረቡ፡፡ የአላህ መልእክተኛ ‫ﷺ‬
የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፈዋል፡-
“በተኛሁበት ሰዓት ቀሚስ የለበሱ ሰዎቸ ወደእኔ ሲቀርቡ ተመለከትሁ፡፡ ከፊሎች
ጡታቸው ላይ የሚደርስ ፣ ከፊሎቹ ደግሞ ከእርሷ ዝቅ የሚል ቀሚስ ለብሰዋል፡፡ ዑመር
ብን አልኸጧብ e ወደ እኔ እንዲቀርብ ተደረገ፡፡ እርሱም ቀሚስ ለብሷል ይጎትተዋል፡፡
“የአላህ መልእክተኛ ሆይ! በምን ተረጎምከው” ተባሉ፡፡ “ዲን ነው” በማለት ምላሽ
ሰጡ፡፡ ቡኻሪ፡
ኢማን እንደሚጨምርና እንደሚቀንስ ሰለፎችና የሱና መሪዎች የተናገሩበት
ቡኻሪ በዘገቡት ሐዲስ ዓምማር e የሚከተለውን ተናግሯል፡- ሶስት ነገሮችን የሰበሰበ
ኢማንን በእርግጥ ሰበሰበ፡፡ “በነፍሱ ላይ ፍትሃዊ (ሐቀኛ) መሆን ፣ ሰላምታን ለሰዎች
ሁሉ ማቅረብ ፣ በችግር ተጨናንቆ እያለ መለገስ” ቡኻሪ በሶሂህ ኪታባቸው ባቡ ኢፍሻኡ አስሰላሚ ሚነል
ኢስላም ላይ አስፍረውታል

ፉዶይል ብን ዒያድ I የሚከተለውን ተናግረዋል፡- “በውስጥም ይሁን በውጭ ከእኛ


59/68

ዘንድ ኢማን ማለት ፡ በምላስ ማረጋገጥ ፣ በልቦና መቀበል ፣ በእርሱም መተግበር፡፡”


አስ ሱንና ሊዓብዲላህ ብን አህመድ፡

ማሊክ ብን አነስ I የሚከተለውን ተናግረዋል ፡-


“ኢማን ንግግርም ፣ ተግባርም ፤ የሚጨምርም የሚቀንስም ነው” አስ ሱንና ሊዓብዲላህ ብን
አህመድ፡

ዓብደላ ብን ሙባረክ I የሚከተለውን ተናግሯል፡-


"‫"اإليمان قول وعمل يزيد وينقص‬
“ኢማን ንግግርም ተግባርም ነው፡፡ ይጨምራል ይቀንሳል” አስ ሱንና ሊዓብዲላህ ብን አህመድ፡
ኢማም አህመድ I የሚከተለውን ተናግሯል፡- “እኛ ፣ ኢማን ንግግርም ተግባርም
ነው፡፡ ይጨምራል ይቀንሳል፡፡ ዝሙት በሰራ ጊዜ ፣ አስካሪ መጠጥ በጠጣ ጊዜ እምነቱ
ይጎድላል እንላለን፡፡” አስ ሱንና ሊዓብዲላህ ብን አህመድ፡

ቡኻሪ I የሚከተለውን ተናግራዋል፡- “ከአንድ ሽ በላይ የሚሆኑ -ከሂጃዝ ፣ ከመካ ፣


ከመዲና ፣ ከኩፋ ፣ ከበስራ ፣ ከዋሲጥ ፣ ከበግዳድ ፣ ከሻም ፣ ከግብጽ የሆኑ የእውቀት
ባለቤቶችን አንድ ዘመን አልፎ ሌላው ዘመን ሲተካ ደጋግሜ አግኝቻቸዋለሁ፡፡
ያገኘኋቸው እነርሱ ቁጥራቸው ብዙ ሆኖ ነው፡፡ ከአርባ ስድስት አመት በላይ ጀምሮ
ቁጥራቸው በርካታ ሆነው አግኝቻለሁ፡፡ በዚህ ጉዳይ፡- ዲን ንግግር ተግባር በመሆኑ
ከእነርሱ መካከል አንድም ሲቃረን አላየሁም” ሸርሕ ኡሱሉ አል ኢዕቲቃዲ አህሊስሱንነቲ ወልጀማዓቲ፡
ሰነዱን ሃፊዝ ብን ሐጀር በፈትሁል ባሪ ኪታብ ሶሂህ ብለውታል፡

አቡ ሙሐመድ ዓብዱረህማን ብን አቢ ሃቲም I የሚከተለውን ተናግሯል፡- “በዲን


መሰረቶች ዙሪያ የአህለሱና መዝሐብና በሁሉም ከተሞች ያገኙዋቸው ዑለሞች
ያሉበትንና ሁለቱም ዓቂዳ አድርገው ያመኑበት ምን እንደሆነ አባቴንና አቡዙርዓህን
ጠየቅኋቸው፡፡
60/68

“በሁሉም ከተሞች -በሂጃዝ ፣ በኢራቅ ፣ በሻም ፣ በየመን ፣ ዑለሞችን አግኝተናል፡፡


የሁሉም መዝሐብ ኢማን ንግግርና ተግባር እንደሆነ እንደሚጨምር እንደሚቀንስ …
በማለት ሁለቱም ተናገሩ፡፡” ሸርሕ ኡሱሉ አል ኢዕቲቃዲ አህሊስሱንነቲ ወልጀማዓቲ፡

ሀፊዝ ሙሐመድ ብን አልሁሰይን አልአጁሪ I የሚከተለውን ተናግረዋል፡- “እኛንም


እናንተንም አላህ ይዘንልንና ስሩ፡፡ ኢማን በፍጡራን ላይ ሁሉ ግዴታ መሆኑ ፣ በልብ
የሚታመን ፣ በምላስ የሚረጋገጥ ፣ በአካል የሚተገበር መሆኑ ሙስሊም ዑለሞች ሁሉ
ያሉበት ነው፡፡ በምላስ መናገር አብሮ ካልኖረ በቀልብ እና በእምነት ብቻ ማወቅ በቂ
አለመሆኑን እወቁ፡፡ በአካል መተግበር እስካልኖረ ድረስ የቀልብ እውቀት እንዲሁም
በምላስ መናገሩ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ እነዚህ ሶስት ክፍሎች ከተሟሉ ፡ ሙእሚን
ይሆናል፡፡ በዚህ ላይ ቁርኣን ፣ ሱና ፣ የሙስሊም ዑለሞች ንግግር መረጃዎች
ይጠቁማሉ፡፡” አሽ ሸሪዓ ሊል አጁሪ፡

ኢብን በጧእ I የሚከተለውን ተናግሯል፡- “ኢማን ንግግርና ተግባር ለመሆኑ ፣ ሶላት


እና ዘካ ከኢማን ለመሆኑ ከአላህ ኪታብ ፣ ከረሡል ሱና እንዲሁም እነርሱን
ከማውሳት ልቦና ብቸኛ የማይሆንባቸው ይልቁንም እነርሱን በመከተል የምትረካባቸው
የሙስሊም ኡለሞችና ፉቀሀዎች ስምምነት በጣም አመላካች ፣ የበለጠ ጠቋሚ ምን
አለ? አላህ ይዘንላቸው ፣ የእነርሱ ወንድሞችም ያድርገን!” አል ኢባነቱል ኩብራ፡

በተጨማሪ የሚከተለውን ተናገረ፡ “ይህ የሶሃባ ፣ የታብዒይ ፣ አላህ ለዲኑ መሪ


ያደረጋቸው የሙስሊም ፉቀሐዎች (ልሒቃኖች) መንገድ ነው፡፡ ይህ ከወረደው ግልጽ
መረጃና ከረሡል ‫ ﷺ‬ሱና ጋር ተስማሚ ነው፡፡ እነርሱን በመቃወም ፣ የአላህን ዲን ፣
ሸሪዓ ፣ የነብዩን ሱና ውድቅ አድርጎ አስተያየቱን ምርጫውን በመከተል የአላህን
61/68

ብርሀን ለማጥፋት በመፈለግ ክርክርን እና ድርቅናን በመጠቀም ከተፈተነ ባሪያ በአላህ


እንጠበቃለን፡፡ ከሐዲዎች ቢጠሉም አላህ ብርሀኑን ለመሙላት እንጅ እምቢ ብሏል፡፡”
(አል’ኢባነቱል ኩብራ፡ 2/827)

በርበሃሪይ I የሚከተለውን ተናግሯል፡ -


"‫"ومن قال اإليمان قول وعمل يزيد وينقص فقد خرج من اإلرجاء أوله وآخره‬
“ኢማን ንግግርም ተግባርም ነው ይጨምራል ፣ ይቀንሳል ያለ ለመጀመሪያና ለመጨረሻ
ጊዜ ከኢርጃእ ወጣ፡፡” (ሸርሑ አስሱንና፡ ገፅ/57)
➢ እኔም አልኩ፡ እስካሁን ያወሳኋቸው የአሽዓርያ ዓቂዳዎች አህባሽም ያረጋገጣቸው
መሆናቸውን የሚከተሉትን የአብደላህ አልሀረሪ አልሀበሽን መጽሐፎች ተመልከት፡፡
“ሶሪሁል በያን” (ገጽ ) ፣ “አድደሊሉል ቀዊም” (ገጽ ) ፣ “ሸርህ
ሲፋት” (ገጽ ፣ ) ፣ “ኢዝሀሩል አቂደቲ አስሱንያ” (ገጽ
) ተመልከት፡፡
- አብደላ አልሀበሺ (ሀረሪ) በባሪያው ላይ የመጀመሪያው ግዴታ መመራመር
እንደሆነ “ሸርህ ሲፋት” (ገጽ ) ፣ “ደሊሉ አልቀዊም” (ገጽ ) በተባሉ
ኪታቦች ያረጋገጠ መሆኑን ተመልከት፡፡
- በጣም የሚያስገርመው ዓብደላህ አልሀበሺ (ሀረሪ) በሻፍዒይ መዝሐብ ላይ
ተከታይ ነኝ ብሎ ይሞግታል፡፡ ነገር ግን እርሱ በእጃችን የሚገኘውን ቁርኣን
የአላህን ንግግር ነው አይልም፡፡ ዓልይ ብን ሰህል አረምሊዩ ስለሻፍዕይ
የሚከተለውን ተናግረዋል፡- “ስለቁርኣን ሻፍዒይን ጠየቅሁት ፤ “ፍጡር ያልሆነ ፣
የተወረደ የአላህ ንግግር ነው፡፡” የሚል ምላሽ ሰጠኝ፡፡ “ፍጡር ነው ያለ ሰው
ከአንተ ዘንድ ምንድን ነው” በማለት ጠየቅሁት፡፡ እርሱም “ከሀዲ ነው” አለኝ፡፡
62/68

ሻፍዕይ I የሚከተለውን ተናገረ፡- “ከመምህሮቸ አንድንም አላገኘሁም


ቁርኣንን ፍጡር ነው ያለ ሰው ከሐዲ የሚሉት ቢሆን እንጅ፡፡” አስማእ ወስሲፋት ሊል
በይሐቂይ

ብዙዎቹ ከአሽዓርይም ይሁን ከሌሎች የዝንባሌና የቢድዓ ባለቤት የሆኑት ሁሉ


በዓቂዳ ተቃራኒ ሆነው እያልለ ወደሻፍዕይ ይጠጋሉ!!!
➢ ዓብደላ አልሀበሺ (ሀረሪ) “ቡግየቱ አጥጧሊ” ከተባለው ኪታቡ ገጽ ላይ
ኡሉሁያ የሚለውን ቃል ፈጣሪ በሚል ተርጉሞታል፡፡
➢ ሀበሺ (ዓብደላ ሀረሪ) ከአላህ ውጭ የሚደረገው ጥሪ እርሱንም መለመን ዒባዳ
አይደለም በማለት አረጋግጧል፡፡ ዒባዳ ከእርሱ ዘንድ የመጨረሻ መተናነስ ማለት
ነው፡፡ ኢብን ተይሚያን እና ሙሐመድ ብን አብዱል ወሀብን በዒባዳ ላይ ጃሂሎች
ናቸው ብሏቸዋል፡፡ (አልመቃላቱ አስሱንያ ፡ ገጽ ) ተመልከት
➢ በተመሳሳይ ኢስቲዓና (እገዛን መፈለግ) ዒባዳ (አምልኮ) አይደለም ይላል
አብደላ አልሀበሺ (ሀረሪ)፡፡ ከአላህ ውጭ እርዳታን የጠየቀ ከአላህ ውጭ
አልተገዛም ፤ ሽርክ ላይ ወደቀ አይባልም ይላል፡፡ ከቋንቋ አዋቂዎች ዘንድ ከአላህ
ውጭ እርዳታ መጠየቅ የዒባዳ ትርጉም ተግባራዊ አይሆንበትም ይላል፡፡ (ሶሪሁል
በያን ወደሊሉል ቀዊም ፡ ገጽ ) ተመልከት
➢ በተመሳሳይ ዓብደላ አልሀበሽ (ሀረሪ) ኢስቲጋሳ (ተማጽኖ) ማድረግ ሽርክ
አይደለም ይላል፡፡ ከሞቱ በኋላም ይሁን በህይዎት እያሉ ነገር ግን በአካል ባይገኙም
በነብያቶች በወልዮች ኢስቲጋሳ ማድረግ (መማጸን) ለእነርሱ መገዛት
አይባልም.. (“መቃላቱ አስሰንያ” ገጽ ተመልከት)
➢ ዓብደላ አልሀበሽ (ሀረሪ) (ወደቅርቢቱ ሰማይ) መውረድ የሚለውን ባህሪ
63/68

“ሶሪሁል በያን” በሚባለው ኪታቡ ገጽ ላይ ፣ ወጅህ የሚለውን ባህሪ


“ደሊሉል ቀዊም” በተባለው ኪታቡ ገጽ ላይ ፣ ሁለት እጆች የሚለውን
ባህሪ “ሲራጦል ሙስተቂም” በሚባለው ኪታቡ ገጽ ፤ “ደሊሉል ቀዊም”
ገጽ ላይ እንዴት እንደተረጎማቸው ተመልከት፡፡ ውዴታ እና ቁጣ የሚባሉ
ከአላህ ጋር ተስማሚ የሆኑና የተረጋገጡ ባህሪያትን ዓብደላ አልሀበሽ እንዴት
እንደተረጎማቸው ተመልከት፡፡
➢ አልሀበሽይ (ዓበረደላ ሀረሪ) በአኼራ አላህ እንደሚታይ ያጸድቃል፡፡ ነገር ግን
የሚታየው በአቅጣጫ አይደለም ይላል፡፡ በእርግጥ ለዚህ አመለካከቱ ቀደምት
አለው፡፡ እነርሱም ወደኋላ የመጡ አሽዓሪዮችና ማቱሪዲያዎች ናቸው፡፡
“አልዒቅቲሷድ ሊልገዛሊ” ገጽ ፤ “አልመጧሊቡል ወፊያ” ገጽ
ተመልከት
በአኼራ አላህ ለመታየቱ ከአላህ ኪታብ ማስረጃ
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
﴾ٌ‫﴿ َوُو ُجنهٌ يَ ْنَمئِذ ََب ِسَرة‬
“ፊቶችም በዚያ ቀን ጨፍጋጊዎች ናቸው፡፡” አል ቂያማ ፡

ኢማም ብን ጀሪር አጥጦበሪ I የሚከተለውን ተናግረዋል፡-“ትክክለኛው የዚህ


ትርጉም ወደፈጣሪዋ ትመለከታለች የሚል ነው፡፡ በዚህ ላይ ከረሡል ‫ ﷺ‬የመጣው
ወሬም ይኸው ነው፡፡
ሱሐይብ e ከነብዩ ‫ ﷺ‬ይዞ የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፏል፡- “የጀነት ሰዎች ጀነት
በገቡ ጊዜ አላህ b “የምጨምራችሁ ነገር ትፈልጋላችሁ?” ይላቸዋል፡፡ ፊቶቻችንን
ብርሃን አላደረክምን? ፣ ከእሳት አድነህ ጀነት አላስገባህንምን?” የሚል ምላሽ ይሰጣሉ፡፡
64/68
ግርዶሹን ይገልጣል፡፡ ወደጌታቸው ከመመልከት የበለጠ ከእነርሱ ዘንድ በጣም ተወዳጅ
ነገር አልተሰጡም፡፡”
በሌላ ዘገባ፡ “ከዚያም የሚከተለውን ቁርኣን አንቀጽ አነበቡ፡- “ለእነዚያ መልካም

ለሰሩት መልካም ነገርና ጭማሪም አላቸው፡፡” ዩኑስ ፡ ሙስሊም፡

አላህ በትክክል እንደሚታይ የመጡ ሐዲሶች ሙተዋሪር ናቸው (ከነብዩ ሰምተው


ያስተላለፉ በርካታ ናቸው)፡፡ ወደትክክለኛው ጎዳና ለመመራት አላህ ለገጠመው ሰው
መረጃዎች በበቂ ሆኔታ ተወስተዋል፡፡
ሸይኹል ኢስላም ብን ተይሚያህ I የሚከተለውን ተናግረዋል፡- “በዚህ ምክንያት
ሙዕተዚላ በእነርሱ (በአሻዒራ ላይ) ያሾፋሉ፡፡ ከእነርሱ መካከል አንዱ ተናጋሪ
የሚከተለውን እስከመናገር ደርሷል “አላህ አቅጣጫ የለውም የሚል አመለካከት
ኖሮት ፣ (አላህ) ይታያል ብሎ የሞገተ ሰው በአዕምሮው ላይ ሰዎች እንዲስቁበት
ያደረገ ነው፡፡” በያኑ ተልቢሲል ጀህሚየቲ ፡

ሸይኽ ሙሐመድ አማን I የሚከተለውን ተናግረዋል፡- “አሻዒራዎች በአኼራ


(አላህ) በአይን እንደሚታይ ያጸድቃሉ፡፡ ይሁን እንጅ ፊት ለፊት አቅጣጫ መታየቱን
እና አላህ በሚከተለው ቁርዓን ያጸደቀውን የበላይነት አያጸድቁም፡፡
﴾‫﴿ ََيَافُن َن َرمُِم ِهمَ فَ ْنقِ ِه ْم‬
“ጌታቸውን ከበላያቸው ሲሆን ይፈሩታል፡፡” አን ነህል፡

አላህ ከዓርሽ በላይ መሆኑንና የአላህን አጠቃላይ የበላይነት ተቃውሞ አላህ (በትንሳኤ
ቀን) እንደሚታይ ማጽደቅ የመሸፋፈን አይነትና የግልጽነት ችግር እንደሆነ በመረጃ
የተደገፈ ጥናታዊ ጽሁፍ ከዚህ በፊት አሳልፈናል፡፡ በውጭ የተገኘን አካል በገሐድ
የሚታይ መሆኑን አጽድቆ ሲያበቃ እርሱ ከተናጋሪው በላይ ፣ በቀኝ ፣ በግራ ወይም በስር
65/68
አይደለም ብሎ መናገር የዓቅለኛ ንግግር አይደለም፡፡ ይህን ንግግር የሚሰማ ሰው ሁሉ
ወይም የሚሰማውን የሚገነዘብ ሰው ሁሉ ተቃውሞ የሚያቀርብበት ንግግር ነው፡፡”
አስ ሲፋቱል ኢላሂያ፡

➢ አብደላ አልሀበሽ (ሀረሪ) የሶሃቦችን ሐቀኛነት በአጠቃላይ አይመለከትም፡፡ ታላላቅ


ሶሃቦችን በግፍ ይተቻል፡፡ ለምሳሌ ፡ ሙአዊያ ብን አቢ ሱፍያን e “የእሳት ተጣሪ
ነው ፤ የዱንያ እና የስልጣን ፈላጊ ነው” በማለት ይኮንነዋል፡፡ (ሶሪሁል በያን ገጽ 225 ተመልከት)

ኢማም አንናቂድ አቡዙርዓህ አርራዚ I እውነት ተናገረ፡ “አንድ ሰው ከረሡል ‫ﷺ‬


ሶሃቦች መካከል የአንዱን ክብር ሲያጎድል ከተመለከትክ ይህ ሰው ዚንዲቅ (ሙናፊቅ)
መሆኑን እወቅ፡፡ ምክንያቱም ረሡል ‫ ﷺ‬ከእኛ ዘንድ ሐቅ ናቸው ፣ ቁርኣን ሐቅ ነው፡፡
ይህን ቁርኣንና ሱና ወደእኛ ያደረሱት የረሡል ‫ ﷺ‬ሶሃቦች ናቸው፡፡ ሸሂዶቻችንን
ለመተቸት ፍላጎት ያላቸው ሰዎች ቁርኣን እና ሱናን ለማበላሸት የሚፈልጉ ሰዎች
ናቸው፡፡ በዚንዲቅነት ሊተቹ የሚገባቸው እነርሱው ናቸው፡፡” አልኪፋየቱ ፊ ዒልሚ ሪዋያ ሊል ኸጢብ
አልበግዳዲ ገጽ

ከኸሊፋው መልክተኞች መካከል አንዱ ከሆነው የዕቁብ ለአቡ ዓብዲላህ ብን አህመድ


ብን ሐንበል I የሚከተለው ጥያቄ ቀረበለት፡- “አባ ዓብዲላህ ሆይ! በዓልይና
በሙዓዊያ -አላህ ይዘንላቸው- በነበረው ሁኔታ ምን ትላለህ?” በማለት ጠየቀው፡፡
“መልካም እንጅ ሌላ አልልም፡፡ ሁሉንም አላህ ይዘንላቸው፡፡” በማለት አቡዓብዲላህ
ምላሽ ሰጠ፡፡ አስሱና ሊል ኸላል

አህመድ ብን ሐንበል I የሚከተለውን ተናገረ፡- “ከረሡል ሶሃቦች መካከል የአንዱን


ክብር ያጓደለ ወይም ከእርሱ በተከሰተው የጠላ ወይም ስህተቶቹን ያወሳ ለሁሉም አላህ
ይዘንላቸው ብሎ ዱዓ እስካላደረገና ለእነርሱ ልቡ ሰላማዊ እስካልሆነ ድረስ ይህ ሰው
66/68
ሙብተዲዕ ነው፡፡” ኡሱሉ አስ ሱንና ኢብን ሐንበል፡ ገጽ

አውዋም ብን ሀውሸብ I የሚከተለውን ተናግሯል፡- “ከዚህ ኡመት (ማህበረሰብ)


የመጀመሪያ ትውልዶች መካከል “ልቦቻችሁ እንዲተሳሰሩ የረሱልን ሶሃቦች
መልካምነት አውሱ፡፡ በመካከላቸው የተፈጠረውን ችግር አታውሱ - ሰዎችን በእነርሱ
ላይ (ለጥላቻ) ታነሳሳላችና፡፡” በማለት ከፊላቸው ለከፊሉ እየተናገሩ አግኝቻለሁ፡፡”
አሽሸርህ ወልኢባና ዓላ ኡሱሊ አስሱናህ ወድዲያናህ ፡ ገጽ

ኢብን በጧ I የሚከተለውን ተናግሯል፡- “(ሶሃቦች) ረሡል ‫ﷺ‬በተገኙባቸው


መድረኮች ሁሉ ተገኝተዋል፡፡ (ሶሃቦች) በደረጃ ሌሎችን ሰዎች ቀድመዋል፡፡ አላህ
ለእነርሱ ምህረት አድርጓል፡፡ ለእነርሱ ኢስቲግፋር እንድታደርግ (አላህ) አዞሃል፡፡
ከእነርሱ የሚሆነውን ፣ እነርሱ እንደሚገዳደሉ እያወቀ ፣ እነርሱን በመውደድ ወደርሱ
እንድትቃረብ በነብዩ ‫ ﷺ‬ምላስ ግዴታ አድርጓል፡፡ ከሌላው ፍጡር እንዲበልጡ
የተደረገው ተሳስተውም ይሁን ሆን ብለው የሰሩት ከእነርሱ ዘንድ ውድቅ መደረጉ
(ምህረት መደረጉ) ነው፡፡ በእነርሱ መካከል የተከሰተው ውዝግብ ሁሉ ለእነርሱ
ይማራል፡፡ በሲፍፊን ፣ በጀመል ፣ በዳር እና በሌሎችም ቦታዎች የተከሰተውን
አለመግባባት የዘገቡ መጽሐፎችን መመልከት አይገባም፡፡ ለራስህም ይሁን ለሌላ
አትጻፈው፡፡ ለሌላም አታሳየው፡፡ በሌላም ላይ አታንበው፡፡ ከሚያወሩ ሰዎች አትስማው፡፡

ታላላቅ እና ዋና ዋና የሚባሉ ዑለሞች ከገለጽነው ሁሉ ከልክለዋል ፣ በዚህም


ተስማምተዋል፡፡ ከእነርሱ መካከል ሀማድ ብን ዘይድ ፣ ዩኑስ ብን ዑበይድ ፣ ሱፍያን
አስሰውርይ ፣ ሱፍያን ብን ዑየይና ፣ ዓብደላ ብን ኢድሪስ ፣ ማሊክ ብን አነስ ፣ ኢብን
አቢ ዚእብ ፣ ኢብን አልሙባረክ ፣ ሹዓይብ ብን ሀርብ ፣ አቡኢስሀቅ አልፈዛር ፣
67/68

ዩሱፍ ብን አስባጥ ፣ አህመድ ብን ሐንበል ፣ ቢሽር ብን ሀሪስ ፣ አብዱል ወሃብ


አልወራቅ ይገኙበታል፡፡ እነዚህ ዑለሞች ሁሉ ካሳለፍናቸው ነገሮች መከልከል
እንዳለብን ይመለከታሉ፡፡ ወደርሷ መመልከትም ወደርሷ መስማትም እርሷን
ከመፈለግም ፣ እርሷን በመሰብሰብ ላይ ትኩረት ከመስጠትም አስጠንቅቀዋል፡፡ በዚህ
ዙሪያ - ይህን ጉዳይ በመጥላት ፣ እርሷን በሚሰማና በሚያወራ ሰው ላይ በማውገዝ -
ከእነርሱ ትርጉሙ በሚስማማ ሁኔታ በተለያዩ ቃላቶች በብዛት ተወርቷል፡፡” ሸርህ ወልኢባና
ዓላ ኡሱሊ አስሱና ወዲያናህ፡ ገጽ

የአህለል ቢድዓ ምልክቶች


ኢብን ተይሚያ I የሚከተለውን ተናግሯል፡-“የዚህ ቡድን ምልክቶች ከቁርኣን ፣ ከሱና
እና ከዑለሞች ስምምነት መለየት ነው፡፡ በቁርኣን ፣ በሱና እንዲሁም ዑለሞች
በተስማሙበት የተናገረ ሰው እርሱ ከአህለሱና ወልጀማዓ ይሆናል፡፡” መጅሙዕ አል ፈታዋ ፡

- ከአህለል ቢድዓ ምልክቶች መካከል፡ ማደናገሪያዎችን መከታተል ፡፡


አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
﴾‫يَ ِف قُلُنِِِ ْم َزيْ ٌغ فَيَ تمبِعُن َن َما تَ َشابَهَ ِمْنهُ ابْتِغَاٍ الْ ِفْت نَ ِة َوابْتِغَاٍ ََتْ ِويلِ ِه‬
َ
ِ ‫﴿فَأَما الم‬
‫ذ‬
“በልቦቻቸው ውስጥ ጥመት ያለባቸው ሰዎች ማሳሳትን ለመፈለግና ትችቱን
ለመፈለግ ከርሱ የተመሳሰለውን ይከታተላሉ፡፡” አል ዒምራን፡

- ከአህለል ቢድዓ ምልክቶች መካከል ፡ አህለሱናዎችን ሙጀሲማ (ለአላህ አካል


አድራጊ) ፣ ሙሸቢሃ (አላህን ከፍጡራን ጋር አመሳሳይ) በማለት ተለጣፊ
ስሞችን ያወጡላቸዋል፡፡
ኢማም አቡ ሀቲም አርራዚ I የሚከተለውን ተናግሯል፡- “የአህለል ቢድዓ ምልክቶች
68/68
የሐዲስ ባለቤቶችን መተቸት ነው፡፡ የጀህምያ ምልክት አህለሱናዎችን ሙሸቢሀ ፣
ናቢተቱን በማለት መጥራት ነው፡፡ የቀደርያ ምልክት አህለሱናን ሙጅቢራ (አስገዳጅ)
ብሎ መጥራት ነው፡፡ የዘናዲቃ (የሙናፊቅ) ምልክት የሐዲስ ባለቤቶችን ሀሸውያ
(ውድቅ ፣ የማይረባ) ብሎ መጥራት ነው፡፡ ከረሡል ‫ﷺ‬ሐዲሶችን ውድቅ ማድረግ ነው
ፍላጎታቸው፡፡” ሸርህ ኡሱል ኢዕቲቃድ አህለሱና ወልጀማዓህ ሊላለካኢይ፡ ገጽ

ሸይኹል ኢስላም አስሷቡኒ I የሚከተለውን ተናግሯል፡- “የቢድዓ ምልክት በባለቤቶቿ


ላይ ግልጽ ነው፡፡ ከምልክቶቻቸው ግልጹና ይፋ የሆነው ፡ የረሡልን ‫ﷺ‬ሐዲስ ተሸካሚ
በሆኑት ላይ ያላቸው ከባድ ጠላትነትና እነርሱን ማቃለላቸው ፤ ሐሸውያ ፣ ጀሀላህ
(ማህይም) ፣ ዟሂሪያ ፣ ሙሸቢሃ ብሎ መጥራት ነው፡፡ ከእነርሱ ዘንድ ከረሡል
የተወራው ወሬ ሁሉ ከእውቀት የተራቆተ ነው፡፡ ከእነርሱ ዘንድ እውቀት ብሎ ማለት
ሸይጧን ወደነርሱ የሚያቀብላቸው ፣ ከተበላሹ አቅሎቻቸው ፣ ጨለማ ከሆኑት
ደረቶቻቸው የሚመነጨው ፣ ከመልካም እና ከማስረጃዎች የተራቆተው ልቦቻቸው
(አዕምሯቸው) ትዝ የሚያሰኛቸው እና የእርሱም ውጤት ነው፡፡ ይልቁንም የእነርሱ
ማደናገሪያ ባጢልና ውድቅ ነው፡፡ አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን
ተናግሯል፡-
﴾‫ص َارُه ْم‬ ِ ‫﴿أُولَئِك الم‬
َ ْ‫َص مم ُه ْم َوأ َْع َمى أَب‬
َ ‫اّللُ فَأ‬
‫يَ لَ َعنَ ُه ُم م‬ ‫ذ‬
َ َ ْ
“እነዚህ እነዚያ አላህ የረገማቸው ፣ ያደነቆራቸውም ፣ ዓይኖቻቸውንም
ያወራቸው ናቸው፡፡” ሙሐመድ፡

“አላህ የሚያዋርደውም ሰው ለእርሱ ምንም አክባሪ የለውም፡፡ አላህ የሻውን


ይሰራል፡፡” አልሐጅ ፡ ሸርህ ዓቂደቱ ሰለፍ ሊሷቡኒ ፡ ቢተርቂሚ አሽሻሚላህ አሊያ
ባህር ዳር በሚገኙ የአህለሱና መሻይኾች የተቀሩ ጠቃሚ ኪታቦች፣ ከሀገር
ውስጥና ከውጭ በሚመጡ መሻይኾች የተሰጡ ኮርሶች፣ ሙሓዶራዎች፣
የጁመዓ ኹጥባ፣ በትክክለኛ ማስረጃ የተደገፉ የተለያዩ ኢስላማዊ መጣጥፎችን
የሚከተለውን የቴሌግራም ሊንክ ጆይን በማድረግ መከታተል ይችላሉ
http://t.me/alateriqilhaq

You might also like