Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 9

ዘጠኙ ቅዱሳን

ዘጠኙ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ታሪክ ጥናት አከፋፈል


መሰረት “ ጥንታዊው የታሪክ ዘመን” ተብሎ
በሚጠራው ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ዘጠኝ የውጭ
ሀገር ታላላቅ የክርስትና ሃይማኖት አባቶች ናቸው ፡፡[1]
በየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን (h
ttp://www.ethiopianorthodox.org/) ታላቅ
የሆነ መንፈሳዊ አስተዋጽኦን ማለትም በመንፈሳዊ
ህይወት ፣ በስብከተ ወንጌል፣ ገዳማዊ እና
የምንኩስና ሕይወትን በማስፋፋት ፣ መጽሐፍትን
በመተርጎም፣ አበርክተዋል፡፡
ዘጠኙ ቅዱሳን

ከአቡነ አረጋዊ የሕይወት ታሪክ መጽሐፍ የተገኘ በ፲፯ኛው ክፍለ ዘመን የተሳለ የቅዱሳኑ ምስል

የክርስትና ሃይማኖት ሊቃውንት

-ስም ዝርዝር ፩ኛ - አቡነ አረጋዊ ሮም


-የትውልድ ሀገር ደብረ ዳሞ ጥቅምት ፲፬
-በኢትዮጵያ ፪ኛ - አቡነ ጰንጤሌዎን ሮም
የመሠረቱዋቸው አክሱም ጥቅምት ፮
ገዳማት ፫ኛ - አቡነ የማታ አቡነ
-ዓመታዊ ክብረ የማታ ጎህ ቆስይ ገርዓልታ
በዓላቸው ጥቅምት ፳፰
፬ኛ - አባ ገሪማ ሮም
መደራ/ዓድዋ ሰኔ ፲፯
፭ኛ - አባ ድሕማ አንጾኪያ
እንደ አባ ድሕማ/ይዲያ
ጥር ፲፮
፮ኛ - አባ አፍፄ ታናሽ እስያ
የሓ ግንቦት ፳፱
፯ኛ - አባ ሊቃኖስ
ቁስጥንጥንያ አክሱም
ህዳር ፳፰
፰ኛ - አባ አሌፍ ቂሳርያ
ደብረ ሃሌሉያ መጋቢት ፲፩

፱ኛ - አባ ጉባ ኪልቂያ ዓድዋ
አጠገብ ግንቦት ፳፱

የተገናኙበት ቦታ በቃልኬዶን በ፬፻፶፩


ዓ.ም.በተደረገው
የሃይማኖት አበው ጉባዔ
ወደ ኢትዮጵያ የገቡበት ፭ኛው ምዕተ ዓመት በንጉሥ
ዘመን ገብረ መስቀል ዘመነ
መንግሥት

ቅርጽ

በአባ ጰንጠሌዎን ገዳም አክሱም አጠገብ የሚገኝ የቅዱሳኑ ምስል

የሚከበሩት በየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ


ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን (htt
p://www.ethiopianort
hodox.org/)

ለአገራችን ሥነ-ፅሑፍ እድገት ጉልህ አስተዋፅኦ


አድርገዋል፡፡ ከደጋግ ነገስታት ጋር በመሆን ለትምህርት
፣ ለማህበራዊ ኑሮ ወዘተ መሠረት የሆኑ ገዳማትን
ከመመስረት ከቤት ክርስቲያን አልፎ ለአገራችን
ኢትዮጵያ አያሌ አበርክቶት አድርገው አልፈዋል፡፡
በአገራችን ለቅድስናና ምንኩስና ፣ ለመፈንሳዊነት ትልቅ
አብነት አላቸው፡፡ ከሮም ፣ ታናሽ እስያ፣ቁስጥንጥንያ ፣
ቂሳሪያ እና ሌሎች የእስያና ኤሮፓ አገሮች ቢመጡም
ግዕዝን አጥንተው የአገሩን ባህልና አኗኗር ለምደው
ክርስትናን በምድረ ኢትዮጵያ አስፋፍተዋል፡፡

ክርስትናን ወሰን አይገድበውምና ፣ ክርስቲያን


ሃይማኖት እንጂ የድንበር አገር የለውምና የመጡበትን
ቦታ ሳይሆን ህዝቡ መንፈሳዊ አባትነታቸውን ተቀብሎ!
ቤተክርስቲያንም ውለታቸውን ቆጥራ የቅድስና ማዕረግ
ሰጥታ ታከብራቸዋለች፡፡ ዕለት ተሰይሞላቸውም ክብር
ይደረግላቸዋል፡፡
ከተለያዩ አካባቢ መምጣታቸውም ከየመጡበት አገር
ወደ ግዕዝ መጽሐፍ ቅዱስን ጨምሮ አያሌ መንፈሳዊ
መጽሐፍትን እንዲተረጉሙ አስችሏቸዋል፡፡ በዚህች ትንሽ
ርዕስ ስለተሰዓቱ ቅዱሳን ይህን ያክል ካነሳን
በሚከተለው አንቀጽ ደግሞ ማንነታቸውን
እናስተዋውቃልኋለን፡፡ ስም የመጡበት አገር
የገደሙበት ቦታ የመታሰቢያቸው ቀን

፩- አቡነ አረጋዊ ሮም ደብረዳሞ ጥቅምት ፲፬

፪- አቡነ ጰንጤሌዎን ሮም አክሱም ጥቅምት ፮

፫- አቡነ የማታ ቆስይ ገርዓልታ ጥቅምት ፳፰


አቡነ የማታ ገዳም የሚገኝ ጥንታዊ የሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ስዕል

፬- ገሪማ ሮም መደራ/ዓድዋ/ ሰኔ ፲፯

፭- ድሕማ አንጾኪያ እንደ አባ ድሕማ/ይዲያ ጥር ፲፮

፮- አፍፄ ታናሽ እስያ የሓ ግንቦት ፳፱

፯- ሊቃኖስ ቁስጥንጥንያ አክሱም ህዳር ፳፰

፰- አሌፍ ቂሳርያ ደብረ ሃሌሉያ መጋቢት ፲፩

፱- አባ ጉባ ኪልቂያ አድዋ አጠገብ ግንቦት ፳፱


ምንጭ
1. ^ በ፬፻፵፫ ዓ.ም. የቃልኬዶን ጉባዔ
Monophysitism ስሕተት ነው ብሎ ወሰነ ።
በዚህም ምክኒያት ከቤዛንታይን መንግሥት
ለመሠወር ሊቃውንት ወደ ግብፅ ፣ አሬብያና ፣
ኢትዮጵያ ተሰደዱ (Ullendorff 1960;101)
እነዚህ የተሰደዱ ክርስቲያኖች "ፃድቃን" ተብለው
ይጠሩ ነበር ። በጣም ከታወቁት ውስጥ ወደ
ኢትዮጵያ ነበር የተሰደዱት እነሱም ዘጠኙ
ቅዱሳን በመባል ይታወቃሉ ።

ከ «https://am.wikipedia.org/w/index.php?
title=ዘጠኙ_ቅዱሳን&oldid=367428» የተወሰደ
ይህ ገጽ መጨረሻ የተቀየረው እ.ኣ.አ በ21:30፣ 11 ኖቬምበር
2021 ዓ.ም. ነበር። •
Content is available under CC BY-SA 3.0 unless
otherwise noted.

You might also like