Professional Documents
Culture Documents
ራስን የማብቃት ሪፖርት
ራስን የማብቃት ሪፖርት
ራስን የማብቃት ሪፖርት
ነብዩ ገመዳ
(የተቀናጀ የመሰረተ ልማት ባለሞያ)
ጥር፣2016 ዓ.ም
1.መግቢያ
የወረዳ 3 ስራ ዕድል ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት በዚህ ዓመት በተሻለ መልኩ የአገልግሎት
አሰጣጥ ስርአትን በመዘርጋት ተግባራትን ስኬታማና እውን ለማድረግ በአመለካከት፣በእውቀትና በክህሎት የበቃ ፈጻሚ
በመሆን ህብረተሰቡን ማገልገል የሙያዬ ግዴታ መሆኑ የሚታወቅ ነዉ፡፡ ስለዚህ እኔም በል/ክ/ከተማ ወረዳ 3 ሥራ
ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት የመሰረተ ልማት ባለሞያ እንደመሆኔ መጠን በ 2015
በጀት አመት ለጽ/ቤቱ ብሎም ለወረዳዉ የበኩሌን ድርሻ በጽናትና በቁርጠኝነት በማበርከት ለ 2016 በጀት
ዓመት ያሉኝን ጠንካራ ጎኖች በማስቀጠል እና ያሉብኝን ክፍተቶች በመሙላት በሙያዬ ህብረተሰቡን
ለማገልገል ይህንን ራስ የማብቃት ሪፖርት እንደሚከተለዉ አቀርባለሁ፡፡
2.1.ጥንካሬዎች
ራስን ከሌላዉ ጋር በማለማመድ እና በመግባባት ከስራ ባልደረቦቼ ጋር ጥሩ የሆነ እና ዉጤታማ የሆነ ስራ
መስራት፣
በሃይል መድረኮችም ሆነ በንዑሳን መድረኮች ላይ ሃሳብን በነፃነት መግለፅ መቻል፣
ስራዎችን በራሴ በመተማመንና በተገቢው ሁኔታ ተረድቶ ለመስራት ያለኝ ተነሳሽነት
የተሰማራሁበትን ተግባር በጥራት መስራት ፣ ዕቅድ ማቀድና ሪፖርት ማዘጋጀት
የጽ/ቤት ንብረት በአግባቡ መያዝ፤መጠቀም፤፤
2.2. ክፍተቶች
በአንድ አንድ ስራዎች ላይ ባለመናበብ ስሜታዊነት መስተዋሉ
ሙሉ እቅምን አሟጥጦ አለመጠቀም
3- ዓላማ
4.3 ከስሜታዊነትና ከተስፋ ቆራጭነት በመላቀቅ በጽናት እና በቁርጠኝነት የሚሰራ ሰራተኛ መሆን
በየቀኑ የተከናወኑ ራስን ከማብቃት እና አጠቃላይ የተቋሙን ተልእኮ ከማሳካት አንጻር ተግባራትን
በየቀኑ በግል እየገመገሙና እያዩ መሄድ
የመጣውን ለውጥ በሳምንት አንድ ጊዜ ከቡድን አባላቶቼ ጋር በ 1 አቻ ለአቻ በጋራ መድረክ መገምገም፣
ሪፖርት በየወሩና በየሩብ ዓመቱ ለቅርብ ኃላፊ ማቅረብ፣
ከቅርብ ኃላፊ የሚሰጡ ግብረመልሶችን ተቀብሎ በቶሎ ምላሽ መስጠት፣
የመጣውን ለውጥ እያረጋገጡ መሄድና በመረጃ አጠናክሮ መያዝ፣
9.ማጠቃለያ
ይህ ሪፖርት ሲቀርብ ያሉኝን ጠንካራ ጎኖቼን የበለጠ አጠናክሬ ለመቀጠልና የሚታዩብኝን ክፍተቶች በመለየት
እና ለቀጣይ ሊሻሻል የሚችልበትን ስልቶች በማወቅ እና በመረዳት የታቀደ ነው ፡፡ስለሆነም በዚህ በጀት አመት
የጽ/ቤቱን እንቅስቃሴ ከዳር ለማድረስ የተጣለብኝን ሙያዊ ሀላፊነት በትክክል ለመወጣት ያስችለኝ ዘንድ
ያለብኝን የክህሎት ክፍተትና የአመለካከት ጉድለት ለመሙላት እንዲያግዘኝ ይህንን የ 2015 በጀት አመት የራስ
ማብቃት ሪፖርት አዘጋጅቻለሁ ፡፡