Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 1

የመኪና ኪራይ ውል ቀን 28/02/2016 ዓ.

እኔ አከራይ ዘበነ ወርቁ ወ/ጊዮርጊስ በሕጋዊ ወኪሌ ዕፀገነት ገብረሀና ብርቄ በውክልና ቁጥር ቅ 3/3893/1/09 አድራሻ አዲስ አበባ
ከተማ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 የቤት ቁጥር 2886 ነዋሪ የሆንኩ የሻንሲ ቁጥር MBHCZF63500310416 የታርጋ ቁጥር
አአ-03-B57056 ሱዚኪ ዲዛየር መኪና በቀን ብር 1,500.00 (ብር አንድ ሺ አምስት መቶ ብቻ) በወር ብር 45,000.00 (ብር አርባ
አምስት ሺ ብቻ) ለማከራየት የተስማማው ሲሆን ለኪራይ የማቀርበው መኪና በቴክኒክ ብቁ ስለመሆኑ፤ አስፈላጊ የሆኑ የመንገድ
መድህን ሽፋን የሶስተኛ ወገን ኢንሹራንስ፣ ቦሎ እና ሊብሬ የታደሰና ወደፊትም በኪራይ ዘመኑ በወቅቱ ለማሳደስ፤ መኪናውን
ከማከራየቴ በፊት ማንኛውም የሶስተኛ ወገን እዳ እና እገዳ እንደሌለበት እና የሶስተኛ ወገን እዳና እገዳ ቢመጣ የኔ የአከራይ ሙሉ
ኃላፊነት መሆኑን እያረጋገጥኩ ከላይ የተጠቀሰውን መኪና ከዛሬ ጥቅምት 28 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለ 6 (ስድስት) ወር ያከራየሁ
መሆኑ እና ቅድመ ክፍያ የሁለት ወር ብር 90,000.00 (ብር ዘጠና ሺ ብቻ) በዚህ ውል መሰረት የተቀበልክ መሆኑን እያረጋገጥኩ፤
ወርሃዊ ክፍያውን ደግሞ በየወሩ ቅድሚያ ለመቀበል ተስማምቼ መኪናውን ከዛሬ ጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓ.ም አስረክቢያለሁ፡፡

ተከራይ ፊውቸር ኢንዱስትሪያል እና ጠቅላላ ንግድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በተወካይ ስራ አስኪያጅ አቶ አዳነ ተስፋዬ ሕጋዊ ውክልና
ቁጥር ቅ 1/0015243/1/2015 አድራሻ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 የቤት ቁጥር አዲስ ሰልክ ቁጥር 09-17-99-91-11 ወይም 09-
17-99-92-22 የአከራይ ንብረት የሆነውን የሻንሲ ቁጥር MBHCZF63500310416 የታርጋ ቁጥር አአ-03-B57056 ሱዚኪ ዲዛየር
የሆነውን መኪና በቀን ብር 1,500.00 (ብር አንድ ሺ አምስት መቶ ብቻ) በወር ብር 45,000.00 (ብር አርባ አምስት ሺ ብቻ)
ለመከራየት የተስማማን ሲሆን የተከራየነውን መኪና አግባብነት ያለው የመንጃ ፍቃድ ላላቸው የድርጅቱ አሽከርካሪ ለመስጠት፤
መኪናውን በአዲስ አበባ ከተማ እና በ 50 ኪ.ሜ ራዲየስ ዙሪያ ብቻ ለመጠቀም እና በተሸከርካሪው ላይ ለሚደርስ ማንኛውም ጉዳት
ወይም በሌላ ሶስተኛ ወገን ላይ ለሚያደርስ የንብረትም ሆነ የአካል ጉዳት ብናደርስ ሙሉ ኃላፊነት ለመውሰድ እና ለዚሁ ዋስትና
ይሆን ዘንድ ለመያዣ ዘመን ባንክ ሃያሁለት ቅርንጫፍ የቼክ ቁጥሩ C1025401 ብር 50,000.00 (ብር ሃምሳ ሺ ብቻ) ለመስጠት
የተስማማን ሲሆን ከላይ የተጠቀሰውን መኪና ከዛሬ ጥቅምት 28 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለ 6 (ስድስት) ወር የተከራየን መሆኑ እና
ቅድመ ክፍያ የሁለት ወር ብር 90,000.00 (ብር ዘጠና ሺ ብቻ) በዚህ ውል መሰረት የከፈልን መሆኑን እና ወርሃዊ ክፍያውን ደግሞ
በየወሩ ቅድሚያ ለክፈል ተስማምተን መኪናውን ከዛሬ ጥቅምት 28 ቀን 2016 ዓ.ም ተረክበናል፡፡

አከራይ እና ተከራይ የዚህን የመኪና ኪራይ ውል በማንኛውም ግዜ የማፍረስ መብት እንዳላቸው የተጠበቀ ሆኖ ውሉን ማፍረስ
የፈለገ በቅድሚያ የ 30 (ሰላሳ) ቀን ማስጠንቀቂያ የመስጠት ኃላፊነት እንዳለበት በመስማማት ይህንን ውል አግባብነት ባላቸው
የፍታብሔር ህጎች ተፈጻሚ እንደሚሆኑ እና ውል ያፈረሰ ብር 45,000.00 (ብር አርባ አምስት ሺ ብቻ) ውል ላከበረ ለመክፈል
ስለመስማማታችን በፊርማችን እና በምስክሮቻችን ፊት እናረጋግጣለን፡፡

ስለአከራይ፤ ስለተከራይ፤

ስም_________________________ ስም_______________________

ፊርማ _______________________ ፊርማ ____________________

ምስክሮች፡ ስም ____________ ስም ______________ ስም ________________

ፊርማ ___________ ፊርማ _____________ ፊርማ _______________

You might also like