ሽርክና ውል - አማረ ጌትነት ጎሹ

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 4

የሽርክና ውል ስምምነት

ውል ሰጪ ፡- አማረ ጌትነት ጎሹ
አድራሻ፡- ከተማ አዲስ አበባ ክ/ከተማ አራዳ ወረዳ 05 የቤት ቁጥር ------ ስልክ ቁጥር +251 930 001 331 (ከዚህ
በኋላ “ውል ሰጪ” እየተባለ በሚጠራው)

እና
ውል ተቀባይ ፡- ፊውቸር ኢንፖርት ኤክስፖርት እና ንግድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
(በተወካይ ሥራ አስኪያጅ አቶ አዳነ ተስፋዬ ቤኛ)
አድራሻ፡- ከተማ አዲስ አበባ ክ/ከተማ ንፋስ ስልክ ላፈቶ ወረዳ 12 የቤት ቁጥር አዲስ ለቡ መብራት ኃይል ሳሙኤል
ሕንፃ ምድር ቤት ስልክ ቁጥር +251 917 999 111 ወይም +251 917 999 222 ኢሜል
future.ind.gt.ada@gmail.com (ከዚህ በኋላ “ውል ተቀባይ” እየተባለ በሚጠራው)

1. አንቀፅ አንድ
የውሉ ዓላማ

1.1. ውል ሰጪ ለውል ተቀባይ በተለያየ ጊዜ ለሰራ ማስኬጂያ የሚሆን ገንዘብ ለማቅረብ አቅም ብቃት እና
ችሎታ ስላላቸው፤ ውል ተቀባይ ደግሞ የግብርና እና የምግብ ምርቶች አቅርቦት ጅምላ ንግድ ስራ
በተለይም መሰረታዊ የሸቀጣሸቀጥ አቅርቦት ላይ ለመስራት አቅም ችሎታ እና ብቃት ስላላቸው ውል
ሰጪና ውል ተቀባይ ከዚህ በታች በተዘረዘሩትን አንቀጾች ለመተዳደር ወድደው እና ፈቅደው ያለማንም
አስገዳጅነት ተስማምተው ተዋውለዋል፡፡

2. አንቀፅ ሁለት
የውል ሰጪ ኃላፊነትና ግዴታዎች

2.1. ውል ሰጪ ለውል ተቀባይ የሸቀጣሸቀጥ እና ሌሎች የግብርና ውጤቶች እና የኢንደስትሪ ምርቶች


አቅርቦት ንግድ ስራ የሚሆን በመጠን ያልተገደበ የስራ ማስኬጃ ገንዘብ ለማቅረብ/ለመስጠት
ተስማምቷል፡፡
2.2. ውል ሰጪ ለውል ተቀባይ የሚያቀርበው የገንዘብ መጠን እና የጊዜ ሁኔታ ውል ሰጪና ውል ተቀባይ
በመወያየት እና በመስማማት ለመወሰን ተስማምቷል፡፡
2.3. ውል ሰጪ ለውል ተቀባይ ገቢ ያደረገበትን ሰነድ መስጠትና በወቅቱ የማሳወቅ ኃላፊነት እንዳለበት
ተስማምቷለል፡፡
2.4. ውል ሰጪ በሚያቀርበው የገንዘብ መጠን የሚወሰን ሆኖ ቢያንስ በአንድ ሳምንት ግዜ ውስጥ እስከ ሶስት
ጊዜ ያቀረበውን የስራ ማስኬጃው ገንዘብ ውል ተቀባይ እንደሚንቀሳቀስ/ እንደሚያገላበጥ ተስማምቷል፡፡
2.5. ውል ሰጪ ከውል ተቀባይ ጋር እንደአስፈላጊነቱ የስራ ማስኬጃው ገንዘብ በምን አቅርቦት ንግድ ስራ ላይ
እንደሚውል በጋራ በቅድሚያ ለመነጋገር ተስማምቷል፡፡
2.6. ውል ሰጪ ባቀረበው የስራ ማስኬጃ ገንዘብ የግብርና ውጤቶች እና የኢንደስትሪ ምርቶች ዓይነት፣ መጠን፣
የመግዣ ዋጋና መሸጫ፤ የሚሸጥበት ቦታና ሀገር እና ሌሎች ዝርዝር ሁኔታዎችን የሚወሰነው በውል
ተቀባይ እንደሆነ ውል ሰጪ ተስማምቷል፡፡

3. አንቀፅ ሦስት
የውል ተቀባይ ኃላፊነትና ግዴታዎች

3.1. ውል ተቀባይ ከውል ሰጪ ለሸቀጣሸቀጥ እና ለሌሎች የግብርና ውጤቶች እና የኢንደስትሪ ምርቶች


አቅርቦት ንግድ ስራ የሚሆን በመጠን ያልተገደበ የስራ ማስኬጃ ገንዘብ ለመውሰድ ተስማምቷል፡፡
3.2. ውል ተቀባይ ከውል ሰጪ የሚቀበለውን የስራ ማስኬጃ የገንዘብ መጠን እና የጊዜ ሁኔታ ውል ሰጪና ውል
ተቀባይ በመወያየት እና በመስማማት ለመወሰን ተስማምቷል፡፡
3.3. ውል ተቀባይ ከውል ሰጪ ገቢ የተደረገለትን የስራ ማስኬጃ ገንዘብ ገቢ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ለውል ሰጪ
ለመስጠት ተስማምቷል፡፡
3.4. ውል ተቀባይ ከውል ሰጪ ያገኘውን የስራ ማስኬጃ ገንዘብ ቢያንስ በአንድ ሳምንት ግዜ ውስጥ እስከ ሶስት
ጊዜ ለማንቀሳቀስ/ለማገላበጥ ተስማምቷል፡፡
3.5. ውል ተቀባይ ከውል ሰጪ ያገኘውን የስራ ማስኬጃው ገንዘብ በምን የአቅርቦት ንግድ ስራ ላይ
እንደሚያውለው በቅድሚያ ለውል ሰጪ ለማሳወቅ ተስማምቷል፡፡
3.6. ውል ሰጪ ባቀረበው የስራ ማስኬጃ ገንዘብ የግብርና ውጤቶች እና የኢንደስትሪ ምርቶች ዓይነት፣ መጠን፣
የመግዣ ዋጋና መሸጫ፤ የሚሸጥበት ቦታና ሀገር እና ሌሎች ዝርዝር ሁኔታዎችን የሚወስነው ውል ተቀባይ
እንደሆነ ውል ሰጪ ተስማምቷል፡፡
3.7. ውል ተቀባይ በውል ሰጪ የስራ ማስኬጃ ገንዘብ የሰራውን ንግድ ስራ ዝርዝር መረጃ ለውል ሰጪ በወቅቱ
የማሳወቅ፤ ውል ሰጪ በማንኛውም ግዜ በሚጠይቅበት ወቅት አስፈላጊውን መረጃ ለራሱ ለውል ሰጪ
ወይም የውል ሰጪ ሕጋዊ ወኪል ለማሳወቅ ውል ተቀባይ ተስማምቷል፡፡
3.8. ውል ሰጪ በውል ተቀባይ መረጃ ቅር ከተሰኛ ሕጋዊ ውክልና ላለው የሂሳብ ባለሙያ ወይም ኦዲተር የውል
ተቀባይን የሂሳብ መዝገብ፣ መረጃ፣ የባንክ ሂሳብ ወይም ማንኛውንም ዓይነት ሰነድ ለማስመርመር ውል
ተቀባይ ተስማምቷል፡፡
3.9. ውል ተቀባይ በውል ሰጪ የመዋጮ ገንዘብ ማንኛውንም የንግድ እንቅስቃሴ የሚመነጭ ሕጋዊ ተጠያቂነት
ውል ተቀባይ ኃላፊነት እንዳለበት ውል ተቀባይ ተስማምቷል፡፡

4. አንቀጽ አራት
የትርፍ ክፍፍል መጠን እና የአከፋፈል ሁኔታ

4.1 ውል ሰጪ እና ውል ተቀባይ በውል ሰጪ የስራ ማስኬጃ ገንዘብ ብቻ ለሚገዙና ለሚሸጡ የግብረና ውጤቶች
እና የኢንደስትሪ ምርቶች ከሚገኝ የተጣራ ትርፍ ላይ 60% ለውል ሰጪ፤ 40% ለውል ተቀባይ የትርፍ ክፍፍል
ለማድረግ ተስማምተዋል፡፡
4.2 ውል ሰጪና ውል ተቀባይ የተጣራ ትርፍ ማለት በውል ሰጪ ስራ ማስኬጃ ገንዘብ በተገዙና በተሸጡ የግብረና
ውጤቶች እና የኢንደስትሪ ምርቶች ላይ የመግዣ ዋጋ፤ የሀገር ውስጥ ትራንስፖርት ዋጋ፣ የመጫኛና
የማውረጃ ዋጋ እና ሌሎች ቀጥተኛ የሆኑ ወጪዎች ተቀንሰው የሚገኝ ትርፍ ማለት እንደሆነ ውል ሰጪና
ውል ተቀባይ ተስማምቷል፡፡
4.3 ውል ተቀባይ እና ውል ሰጪ የትርፍ ድርሻቸውን የሚከፋፈሉት በየዙሩ ውል ተቀባይ በውል ሰጪ የስራ
ማስኬጃ ገንዘብ የገዛቸውን ከሸጠ በኋላ በየሳምንቱ ለመከፋፈል ተስማምተዋል፡፡
4.4 ውል ተቀባይ ለውል ሰጪ የመዋጮ ገንዘቡን እና የትርፍ ድርሻውን በአንድ ላይ ለመክፈል ተስማምቷል፡፡

5. አንቀጽ አምስት
ከአቅም በላይ ስለሚሆኑ ሁኔታዎች

5.1 በፍታብሔር ህግ ቁጥር 1792 እና 1793 የተመለከቱትን መሰረታዊ ሁኔታዎች ከተከሰቱ ከአቅም በላይተ ብለው
የሚታወቁ ሁኔታዎች እስከሚወገዱበት ቀን ድረስ ሁለቱም ወገኖች በውሉ ግዴታ አፈጻጸም ጉድለት/ቶች
የሚጠየቁ አይሆኑም፡፡
5.2 ከአቅም በላይ የሆኑ ሁኔታ የደረሰበት ወገን ሁኔታዉን እንዳወቀ በአስር ቀናት ውስጥ በጹሑፍ ለሌላኛው ወገን
በዝርዝር የማሳወቅ ኃላፊነት አለበት፡፡
5.3 ከአቅም በላይ ተብሎ የሚታወቀው ችግር እንደተወገደ የውሉ አፈጻጸም የጸና ይሆናል፡፡
5.4 ከአቅም በላይ ያጋጠመው ችግር ሁኔታ በአስር ቀናት ውስጥ መፍትሔ ካላገኘ አንደኛው ወገን ውሉን
ሊያቋርጥ ይችላል፡፡
6. አንቀጽ ስድስት
ውሉ የሚቋረጥበት ሁኔታ

6.1 ከሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች አንዱ ውሉን ያፈረሰ እንደሆነ፡፡


6.2 በውል ሰጪና በውል ተቀባይ መካከል አንደኛው በዚህ ውል ስምምነት መሰረት ሳይፈጽም ቢቀር፤
እንደስምምነቱ ውል ሳይፈጸምለት የቀረው ወገን በቅድሚያ የ 15 (አስራ አምስት) ቀን የጹሑፍ ማስጠንቀቂያ
በመስጠት ውሉን ሊያቋርጥ ይችላል፡፡
6.3 በስምምነቱ መቋረጥ ምክንያት ጉዳት የደረሰበት ወገን የጉዳቱን መጠን በሕግ የመጠየቅ መብት አለው፡፡
6.4 ውል ሰጪና ውል ተቀባይ በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ ለመተዳደር ተስማምተዋል፡፡

7. አንቀፅ ሰባት
ውሉን ስለማሸሻል
7.1 ውል ሰጪ እና ውል ተቀባይ በጋራ ሲስማሙ ውሉን በከፊልም ሆነ በሙሉ ለማሻሻል ተስማምተዋል፡፡
8. አንቀፅ ስምንት
ውሉ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ

8.1 ይህ ውል በሁለቱ የተዋዋይ ወገኖች ከተፈራረሙበት ከዛሬ መስከረም 9 ቀን 2016 ላልተወሰን ግዜ ድረስ የፀና
ይሆናል፡፡
8.2 ይህ ውል በፍ/ሕ/ቁ 1731/2005/2266 መሰረት የተደረገ ነው፡፡ ይህንን ውል ለማፍረስ ወይም ከውሉ ቃል ውጪ
ለማድረግ የሚሞክር ወገን ቢኖር ውሉን ላከበረ ወገን ኪሳራ 100,000.00 (አንድ መቶ ሺ ብር) ከፍሎ ውሉ በፍ/ሕ/ቁ
1889/1990 መሠረት የጸና ይሆናል፡፡

9. አንቀጽ ዘጠኝ
ስለ ማረጋገጫ እና ምስክሮች፤
ውል ሰጪ እና ውል ተቀባይ ከዚህ በላይ በሙሉ የተለገፁትን አንቀጾች ወድደን እና ፈቅደን ያለማንም አስገዳጅነት
የተስማማን መሆናችንን በፊርማችን እናረጋገግጣለን፡፡ እኛም ስማችን ከዚህ በታች የተዘረዘረው ምስክሮች ውል
ሰጪና ውል ተቀባይ ሲዋዋሉ ስለማየታችን በፊርማችን እናረጋግጣለን፡፡
ስለውል ሰጪ ስለውል ተቀባይ
ስም ………………………………. ስም …………………………….

ፊርማ …………………………….. ፊርማ …………………………..


ምስክሮች

1. ስም ---------------------------- ፊርማ -------------------

2. ስም ---------------------------- ፊርማ -------------------

3. ስም --------------------------- ፊርማ ------------------

You might also like