Professional Documents
Culture Documents
2006
2006
ጥር 2006 ዓ/ም
ባሕር-ዳር
በከተሞች የህዝብ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱ ምክንያት በመሬት አቅርቦት እና ፍላጎት
መካከል ያለው ያለመጣጣም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ በመምጣቱ ቀጣይነት ያለው መሰረተ ልማት የተሟላለት
የመሬት አቅርቦትን ማረጋገጥ በማስፈለጉ፤
በከተሞች የመሬት ሊዝና ኪራይ መነሻ ዋጋ የመሬት ዝግጅት ወጪ በሊዝ ዘመኑ ውስጥ መመለስ በሚያስችል ታሳቢ በስራ
ላይ ያለውን የመሬት የሊዝና ኪራይ መነሻ ዋጋ በማሻሻል የመሬት አቅርቦቱን ማሳደግ ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ፤
0
የመሰረተ ልማት መዘርጊያ እና ሌሎች የመሬት ዝግጅት ወጭዎች ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመር ምክንያት
የመሬት ዋጋ/land value /የጨመረ ሲሆን ከተሞች ይህን መሬትን ለማዘጋጀት የሚወጣ ወጭ ከመሬት ሀብት
በሚገኝ ገቢ መሸፈን እንዳለባቸው ስለታመነበት፤
አሁን በስራ ላይ ያለው የከተሞች የሊዝ ወይም የቦታ ኪራይ መነሻ ዋጋ በ 2005 እና 2006 ዓ.ም ለተለያዩ አገልግሎቶች
በጨረታ በቀረቡ ቦታዎች ላይ ለካሬሜትር ከቀረበው ዝቅተኛና ከፍተኛ ዋጋ ጋር ሲነፃፀር እና ከሌሎች አቻ ክልሎች ሊዝ
ወይም ኪራይ ዋጋ ጋር ሲገናዘብ በጣም አነስተኛ ሆኖ በመገኘቱ፤
በስራ ላይ የነበረው የሊዝ ወይም ኪራይ መነሻ ዋጋ መወሰኛ የአፈፃፀም መመሪያ ለረጅም ጊዜ ሳይከለስ
በመቆየቱ እና የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ ተሻሽሎ በወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 14
ንዑስ አንቀጽ 3 እንዲሁም አዋጁን ለማስፈፀም በወጣው ደንብ ቁጥር 103/2004 አንቀጽ 30
ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት የሊዝ ወይም ኪራይ መነሻ ዋጋ ወቅታዊነቱን እንዲጠብቅ ቢያንስ
በየሁለት አመቱ መከለስ እንዳለበት በመደንገጉ፤
የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ ተሻሽሎ በወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 33 ንዑስ አንቀጽ
2፣ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አስፈጻሚ አካላት እንደገና ማቋቋሚያና ስልጣንና ተግባራት መወሰኛ አዋጅ ቁጥር
176/2003 አንቀጽ 11 ንዑስ አንቀጽ 1 ፊደል ሠ እና የከተማ ቦታን በሊዝ ለማስተዳደር በወጣዉ የክልሉ
ደንብ ቁጥር 103/2004 አንቀጽ 57 ንዑስ አንቀጽ 2 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት የኢንዱስትሪና ከተማ
ልማት ቢሮ ይህንን መመሪያ አዉጥቷል፡፡
ክፍል አንድ
ጠቅላላ
1. አጭር ርዕስ
ይህ መመሪያ “የተሻሻለው የሊዝ እና የኪራይ መነሻ ዋጋ መወሰኛ የአፈፃፀም መመሪያ
ቁጥር--------/2006” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
2. ትርጓሜ
1
3. “ሊዝ” ማለት በጊዜ በተገደበ ውል መሰረት የከተማ ቦታ የመጠቀም መብት የሚገኝበት የመሬት
ይዞታ ስሪት ነው፣፡
4. “የሊዝ ዘመን” ማለት በአዋጁ አንቀጽ 18 በተደነገገው መሰረት ለየአገልግሎት አይነቱ የተወሰነው
የይዞታ መጠቀሚያ የጊዜ ጣሪያ ነው፡፡
5. “ኪራይ” ማለት በጊዜ ባልተወሰነ ወይም ባልተገደበ ውል መሰረት የከተማ ቦታ የመጠቀም መብት
የሚገኝበት የመሬት ይዞታ ስሪት ነው፣፡
6. “ከተማ” ማለት ማዘጋጃ ቤት የተቋቋመበት ወይም ሁለት ሺህ ወይም ከዚያ በላይ የህዝብ ቁጥር
ያለውና ከዚህ ውስጥ ሃምሳ በመቶ በላይ የሚሆነው ነዋሪ ከግብርና ውጭ በሆነ ሥራ ላይ
የተሰማራ ሆኖ የሚገኝበት አካባቢ ነው፡፡
7. “የከተሞች ፈርጅ” ማለት በክልሉ ደንብ ቁጥር 65/2001 በተደነገገው መሰረት የክልሉ ከተሞች
ሜትሮፖሊታን፣ መካከለኛ፣ አነስተኛ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም የማዘጋጃ ቤት ከተማ መሪ
ማዘጋጃ ቤት፣ ንዑስ ማዘጋጃ ቤትና ታዳጊ ከተማ በሚል የተከፋፈሉበትና የተሰየሙበት ነው፡፡
8. “የከተሞች ደረጃ” ማለት ለክልሉ ከተሞች የቦታ ደረጃ ምደባ አሰጣጥ ብቻ ሲባል በስድስት የከተማ
ደረጃ የተመደቡበት ነው፡፡
9. “የቦታ ደረጃ” ማለት የክልሉ ከተሞች እንደ ከተሞቹ የልማትና እድገት ስትራቴጅካዊ ጠቀሜታ
አንፃር ከአምስት እስከ ሁለት የቦታ ደረጃ የተከፋፈሉበት ነው፡፡
10. “መሰረተ ልማት” ማለት ኢኮኖሚያዊ መሰረተ ልማት (መንገድ፣ ዉሀ፣ መብራት፣ ስልክ፣ ዲች
ድልድይ፤ ግድብ፤ የገበያ ማዕከል፤ ወዘተ) እና አካባቢያዊ መሰረተ ልማት (የደረቅ እና ፈሳሽ ቆሻሻ
ማስወገጃ፤ የብክለት ማከሚያ ስትራክቸሮችን እና ወዘተ) የሚያጠቃልል ነው፡፡
11. "ካሳ" ማለት ለሕዝብ ጥቅም ሲባል እንዲለቀቅ በተፈለገው መሬት ላይ በህጋዊ መንገድ ለሰፈረ ንብረት በዓይነት፣
በገንዘብ ወይም በሁለቱም በካሳ መመሪያ ቁጥር 35/2000 መሰረት የሚፈፀም ክፍያ ነው፡፡
12. “የሊዝ መነሻ ዋጋ” ማለት ዋና ዋና የመሠረተ ልማት አውታሮችን ለመዘርጋት የሚያስፈልጉ
ወጪዎችን ፣ነባር ግንባታዎች ባሉበት አካባቢ የሚነሱ ግንባታዎችንና ንብረቶችን ለማንሳት
የሚያስፈልጉ ወጪዎችን፣ ለተነሺዎች የሚከፈል ካሣን እና ሌሎች አግባብነት ያላቸዉ
መስፈርቶችን መሰረት በማድረግ ለአንድ የሊዝ ዘመን በካሬ ሜትር የሚተመን የመሬት ሊዝ
የጨረታ መነሻ ዋጋ ነው፡፡
13. “በጨረታ መሰረት የተላለፈ ይዞታ ጠቅላላ የሊዝ ክፍያ” ማለት ጠቅላላ የቦታው ስፋት(ካ.ሜ) ሲባዛ
ቦታው ለካሬ ሜትር የተላለፈበት ዋጋ ነው፡፡
14. “በጨረታ መሰረት የተላለፈ የሊዝ ይዞታ ዓመታዊ ክፍያ” ማለት ቅድሚያ የሊዝ ክፍያ
መጠን ከጠቅላላ የሊዝ ክፍያ መጠን ላይ ተቀንሶ የሚገኘው ጠቅላላ ቀሪ ክፍያ በሊዝ ውሉ
ላይ ለተቀመጠው የክፍያ ማጠናቀቂያ ጊዜ ተካፍሎ የሚገኘው የገንዘብ መጠን ነው፡፡
2
15. “በሊዝ ምደባ መሰረት የተላለፈ ይዞታ ጠቅላላ ክፍያ” ማለት ለአገልግሎት ዓይነቱ ለካሬ ሜትር
የተቀመጠው የሊዝ መነሻ ዋጋ ሲባዛ በቦታው ጠቅላላ ስፋት ይሆናል፡፡
16. “በሊዝ ምደባ መሰረት የተላለፈ የሊዝ ይዞታ ዓመታዊ ክፍያ” ማለት ለአገልግሎት ዓይነቱ ለካሬ
ሜትር የተቀመጠው የሊዝ መነሻ ዋጋ ሲባዛ በቦታው ጠቅላላ ስፋት የሚገኘው ውጤት
ሲካፈል በሊዝ ውሉ ላይ ለተቀመጠው የክፍያ ማጠናቀቂያ ጊዜ የሚገኘው የገንዘብ መጠን
ነው፡፡
17. “የሊዝ ወይም የኪራይ ጨረታ ዋጋ” ማለት የነጻ ገበያ ስርዓትን በመከተል መሬትን ለልማት
የሚፈልግ ተጫራች በነጻ ዉድድር የሊዝ መነሻ ዋጋዉን መሰረት በማድረግ በጨረታ ላይ ለቀረበ
አንድ ካሬ ሜትር ቦታ የሰጠዉ እና ጨረታዉን ያሸነፈበት ከፍተኛ የሊዝ ወይም ኪራይ ዋጋ ነዉ፡፡
18. “የጨረታ ከፍተኛ ዋጋ” ማለት በአንድ የጨረታ ሂደት ለአንድ ቦታ ከተወዳዳሪዎች ለቦታዉ የተሰጠ
ከፍተኛ የመሬት ሊዝ ወይም ኪራይ ዋጋ ሆኖ አሸናፊው መሬቱን ተረክቦ ውል የተፈራረመበት ዋጋ
ነው፡፡
19. “የኪራይ መነሻ ዋጋ” ማለት በሊዝ ከተሞች በሚገኙ ነባር ይዞታዎች እና ወደ ሊዝ ስርዓት ባልገቡ
ከተሞች ላይ ለአንድ ዓመት ተነጥሎ የሚተመን በካሬ ሜትር የቦታ ስፋት ታሳቢ የሚደረግ የኪራይ
ጨረታ መነሻ ዋጋ ነው፡፡
20. “በምደባ የተላለፈ ይዞታ ዓመታዊ የቦታ ኪራይ ዋጋ” ማለት ለአገልግሎት ዓይነቱ ለካሬ ሜትር
የተቀመጠው የኪራይ መነሻ ዋጋ ሲባዛ በቦታው ጠቅላላ ስፋት ይሆናል፡፡
21. “በጨረታ መሰረት የተላለፈ ይዞታ ዓመታዊ የኪራይ ክፍያ ” ማለት የቦታው ጠቅላላ ስፋት
(ካ.ሜ) ሲባዛ ቦታው በጨረታ ለካሬ ሜትር የተላለፈበት ዋጋ ነው፡፡
22. ማንኛውም በወንድ ጾታ የተገለጸው የሴትንም ይጨምራል፡፡
3. የተፈጻሚነት ወሰን
ይህ መመሪያ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ የሊዝ ወይም ኪራይ መነሻ ዋጋና የቦታ ደረጃ
በተወሰነላቸው እና በቀጣይም በሚወሰንላቸው ሁሉም የክልሉ ከተሞች ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
3
ክፍል ሁለት
1. የከተሞች ፈርጅ አወሳሰንና ደረጃ ሽግግር በደንብ ቁጥር 65/2001 መሰረት የሚወሰን
ይሆናል፡፡
2. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 አገላለጽ እንደተጠበቀ ሆኖ ለከተማ ቦታ ደረጃ አሰጣጥና
ለሊዝ መነሻ ዋጋ ሲባል የክልሉ ከተሞች ከደረጃ 1 እስከ 6 ድረስ ተለይተው
ተመድበዋል፡፡ዝርዝሩን በዚህ መመሪያ አባሪ-3 ላይ መመልከት ይቻላል፡፡
3. የከተማ ፈርጅ ደረጃ ወይም ስያሜ ሽግግር የሚያደርጉ ከተሞች ሽግግር ላደረጉበት የከተማ ፈርጅ
የተቀመጠውን የከተማና ቦታ ደረጃ እንዲሁም የሊዝ ወይም ኪራይ መነሻ ዋጋ በመጠቀም
ተግባራዊ ያደርጋሉ፡፡
6. የሊዝ ዘመን
4
7. የከተሞች የሊዝ ሽግግር
1. የክልሉ ሁሉም ከተሞች የሊዝ ሽግግር መርሀ ግብር በክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት በሚጸድቀው የድርጊት
መርሀ ግብር መሰረት በአዋጁ አንቀጽ 5 ንዑስ አንቀጽ 4 ላይ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ተፈጻሚ
የሚያደርጉ ይሆናል፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ወደ ሊዝ ስርዓት ያልገቡ ከተሞች ወደ ሊዝ
እስከሚሸጋገሩ ድረስ በዚህ መመሪያ ላይ በቦታ ደረጃና በአገልግሎት ዓይነት የተቀመጠውን የቦታ ኪራይ
ዋጋ የሚጠቀሙ ይሆናል፡፡
3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 የተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ ከተሞቹ ወደሊዝ ስርዓት ሲሸጋገሩ በዚህ
መመሪያ በከተማና ቦታ ደረጃ የተቀመጠውን የሊዝ መነሻ ዋጋ ተግባራዊ የሚያደርጉ ይሆናል፡፡
5
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የማይሻሻልበት ሁኔታ ሲያጋጥም ወይም
አስፈላጊና አሳማኝ ባልሆነበት ጊዜ በስራ ላይ ያለው መመሪያ አግባብ ያለው አካል ቀርቦ የመመሪያው
ተፈፃሚነት እንዲቀጥል ውሳኔ ማግኘት ይኖርበታል፡፡
3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ የቦታ ኪራይ ዋጋ ማሻሻያ ጥናት ከአራት ዓመት
መብለጥ የለበትም፡፡
4. ሁሉም የከተማ አስተዳደሮች የሊዝና ቦታ ኪራይ መነሻ ዋጋ የማሻሻያ ጥናት በማጥናት ወይም በማስጠናት ጥናቱ
ለቢሮው ቀርቦ ከተገመገመ በኋላ በምክር ቤታቸው በኩል አስጸድቀው ተግባራዊ ማድረግ ይችላሉ፡፡
5. ለሁሉም ማዘጋጃ ቤትና ታዳጊ ከተሞች በዞን ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት መምሪያዎች በኩል የሊዝና ቦታ ኪራይ
መነሻ ዋጋ ማሻሻያ እየተጠና በቢሮው የሚፀድቅ ይሆናል፡፡
ክፍል ሶስት
የአስፈጻሚ አካላት ማንነት፣ ተግባር እና ኃላፊነት
10. የአስፈጻሚ አካላት ማንነት
የከተሞች የተሻሻለ የሊዝ እና የኪራይ መነሻ ዋጋ መመሪያን በተሟላ አኳኋን ተፈጻሚ ለማድረግ ከዚህ
6
ረ. የከተማ ቦታ ዋጋ ወቅታዊነት እንዲረጋገጥ ተገቢውን የአሰራርና የአቅም ግንባታ ስራ የማከናወን
ተግባርና ኃላፊነቶች ይኖርበታል፡፡
2. የኢንዱስትሪና ከተማ ልማት መምሪያዎች፡-
ክፍል አራት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
12. ወደ ሶስተኛ ወገን የሚተላለፉ ይዞታዎችን በተመለከተ
1. ይዞታው ቀደም ሲል የሊዝ ይዞታ ከሆነ ወደ ሶስተኛ ወገን ሲተላለፍ ሁለተኛ ወደሊዝ ስለማይገባ ይዞታው
የተላለፈለት ሰው የአገልግሎት እና ሌሎች የሚጠበቅበትን ክፍያ የሚከፍል ሆኖ የአገልግሎት ለውጥ እስካልተደረገ
ድረስ ቀደም ሲል ይዞታው ወደ ሶስተኛ ወገን ከመተላለፉ በፊት ሲከፈል የነበረውን አመታዊ የሊዝ ክፍያ የሚከፍል
ይሆናል፡፡
7
2. በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1 ላይ የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ የሊዝ ይዞታው ወደ ሶስተኛ ወገን
ሲተላለፍ የአገልግሎት ለውጥ ካለ አመታዊ የሊዝ ክፍያው የቦታው ስፋት ሲባዛ የአገልግሎቱ አካባቢያዊ
የጨረታ ዋጋ ሲካፈል በሊዝ ውሉ ላይ የተቀመጠው ቀሪ የሊዝ ክፍያ ማጠናቀቂያ ጊዜ ይሆናል፡፡
3. በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1 የተጠቀሰው ቢኖርም ነባር ይዞታ ከውርስ በስተቀር ወደ ሶስተኛ ወገን ሲተላለፍ
ቀደም ሲል ሲከፈል የነበረው ዓመታዊ የቦታ ኪራይ ቀሪ ሆኖ ወቅታዊ የቦታው የሊዝ መነሻ ዋጋ በቦታዉ ጠቅላላ
ስፋት ከተባዛ በኋላ የሚገኘዉ የገንዘብ መጠን በሊዝ ውሉ ላይ በተቀመጠው የመክፈያ ጊዜ ተካፍሎ የሚገኘው
ውጤት በየዓመቱ ሚከፈል ይሆናል፡፡
4. በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 3 መሰረት የሊዝ ውል የፈፀመው ባለይዞታ የሊዝ ቅድሚያ ክፍያ እንዲፈጽም
ባይገደድም ይህንኑ የመክፈል ፍላጎት ካለው ከጠቅላላው የሊዝ ክፍያ የሚታሰብ ቅድሚያ ክፍያ አግባብ ላለው አካል
የመፈጸም መብት ይኖረዋል፡፡
5. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 4 መሰረት ባለመብቱ የቅድሚያ ክፍያ በመፈጸም የችሮታ ጊዜ እንዲሰጠው ጥያቄውን
በጽሁፍ ካቀረበ እንደ አገልግሎቱ አይነት የችሮታ ጊዜ የሚፈቀድለት ይሆናል፡፡
በሊዝ ውሉ ላይ የሊዝ ክፍያ ማጠናቀቂያ ጊዜው ያልተቀመጠበት ሁኔታ ሲያጋጥም በደንቡ አንቀጽ 32 ንዑስ
አንቀጽ 3 ላይ ለአገልግሎቱ የተቀመጠው የክፍያ ማጠናቀቂያ ጊዜ ተፈፃሚ የሚደረግ ይሆናል፡፡
8
16. የተሻሩና ተፈጻሚነት የማይኖራቸው ህጎች
1. የሊዝ መነሻ ዋጋ መወሰኛ መመሪያ ቁጥር 23/1998 እና ነባር የከተማ ቦታ የኪራይ
ተመን መወሰኛ መመሪያ ቁጥር 24/1998 በዚህ መመሪያ ተሽረዋል፣
2. ከዚህ መመሪያ ጋር የሚቃረን ማናቸውም ሌላ መመሪያ ወይም የተለመደ አሰራር በዚህ መመሪያ ውስጥ
በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡
9
አባሪ-1 የተሻሻለው የክልሉ ከተሞች የሊዝ መነሻ ዋጋ፡-
ሰንጠረዥ 4፡- የከተማ ቦታ የሊዝ መነሻ ዋጋ በ አ ገ ል ግ ሎ ት አ ይ ነ ት ፣ በከተማና በቦታ ደረጃ፣
( ብር/ካሬ ሜትር)
0
5 160 605 275 188 65 150
3 3 1 222 758 351 384 204 180
2 189 665 298 327 138 170
3 161 614 253 270 84 160
4 138 605 208 213 65 150
5 120 590 163 156 45 140
4 4 1 189 665 298 327 115 160
2 161 614 253 270 95 150
3 138 605 208 213 61 140
4 120 590 163 156 50 130
5 5 1 161 614 253 270 95 140
2 138 605 208 213 61 130
3 120 590 163 156 50 120
6 6 1 138 605 208 213 61 130
2 120 590 163 156 50 100
ማሳሰቢያ፡-ለኢንዱስትሪ የቦታ አገልግሎት የተቀመጠው የሊዝ መነሻ ዋጋ በኢንዱስትሪ መንደርነት ለተከለለ/ለሚከለሉ/ አገልግሎት ውጭ ላሉ ዘርፎች
የሚያገለግል ነው፡፡
1
ሰንጠረዥ 5፡- የከተማ ቦታ የኪራይ ተመን መነሻ ዋጋ በ አ ገ ል ግ ሎ ት አ ይ ነ ት ፣ በከተማና በቦታ ደረጃ
( ብር/ካሬ ሜትር)
2
2 0.79 1.7 1.2 1.29
3 0.67 1.2 0.7 1.09
4 0.55 0.95 0.45 0.89
5 0.49 0.825 0.325 0.69
4 4 1 0.79 1.7 1.2 1.29
2 0.67 1.2 0.7 1.09
3 0.55 0.95 0.45 0.89
4 0.49 0.825 0.325 0.69
5 5 1 0.67 1.2 0.7 1.09
3
አባሪ-3. የክልሉ ከተሞች ዝርዝር በዞንና በከተሞች ደረጃ
ተ.ቁ የከተማው ስም ከተማው ለቦታ ምደባ የተሰጠ የከተማ ደረጃ ከተማው ምርመራ
የሚገኝበት ዞን የሚኖረው ቦታ
ስም ደረጃ ፈርጅ ደረጃ ብዛት
15 ሞጣ 3 አነስተኛ ከተማ 5
18 ቡሬ 3 አነስተኛ ከተማ 5
4
19 ቆቦ 3 አነስተኛ ከተማ 5
23 ባቲ 3 አነስተኛ ከተማ 5
5
40 መካነ ብርሃን “ 3 መሪ ማ/ቤት 4
41 ዳባት “ 3 መሪ ማ/ቤት 4
42 አብርሀ ጃራ “ 3 መሪ ማ/ቤት 4
43 አብደራፊ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
44 ትክልድንጋይ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
46 ማክሰኝት “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
47 ቆላ ድባ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
48 መተ/ዩሀንስ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
49 ሻሁራ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
50 አርባያ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
51 ዙሀሙሲት “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
52 ሳንጃ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
53 ደልጊ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4 15
57 ወገዳ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
58 ሀሙሲት “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
59 አንበሳሜ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
60 አንዳ ቤት “ 4 መሪ ማ/ቤት 4 7
6
61 ሙጃ ሰ/ወሎ 4 መሪ ማ/ቤት 4
63 ኮን “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
64 ሃራ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
65 ኩርባ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
66 አይና “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
67 ጋሸና “ 4 መሪ ማ/ቤት 4 7
68 ሳልመኔ ደ/ ወሎ 4 መሪ ማ/ቤት 4
69 ሃርቡ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
70 ኩታበር “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
71 ውጫሌ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
72 ቢስቲማ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
73 ደጎሎ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
74 ወረኢሉ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
75 መዲና “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
76 አቀስታ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
77 አጅባር “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
78 ማሻ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
79 ማህደረ ሰላም “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
(ወግዲ)
80 ከላላ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
81 ሳይንት አጅባር “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
82 ወገል ጤና “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
83 ወይንአምባ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
84 ደንሳ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4 17
7
85 ጫጫ ሰ/ሸዋ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
86 ጊና አገር “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
87 ጎረቤላ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
88 ሾላ ገበያ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
89 መተህብላ 4 መሪ ማ/ቤት 4
90 መኮይ 4 መሪ ማ/ቤት 4
91 ማጀቴ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
92 ራቤል “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
93 ሞላሌ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
94 እነዋሪ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
95 አረርቲ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
96 መራኛ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
97 ደነባ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
98 ደብረ ሲና “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
99 ሰላድንጋይ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
100 ለሚ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
8
105 ዲጐጽዮን “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
108 ቁይ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
118 ቁጭ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
120 ጅጋ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
9
126 ፅፅቃ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4
138 ቦራ “ 4 መሪ ማ/ቤት 4 3
10
147 ገለጉ “ 5 ንኡስ ማዘጋጃ ቤት 3
11
168 አዳዳ “ 5 ንኡስ ማዘጋጃ ቤት 3
12
190 ወይን ውሃ ምስ/ ጎጃም 5 ንኡስ ማዘጋጃ ቤት 3
13
211 እሁዲት “ 5 ንኡስ ማዘጋጃ ቤት 3
14
232 ጭን ድባ “ 6 ታዳጊ ከተማ
15
253 ገላማጠቢያ “ 6 ታዳጊ ከተማ 2
16
274 ጦሳ ፈላና “ 6 ታዳጊ ከተማ 2
17
295 ፍጅ “ 6 ታዳጊ ከተማ 2
18
316 አቤት ውሃ “ 6 ታዳጊ ከተማ 2
19
337 ጃቢ ገነት “ 6 ታዳጊ ከተማ 2
20
358 ዲቦ “ 6 ታዳጊ ከተማ 2
21
379 አጉት “ 6 ታዳጊ ከተማ 2
22
400 “ 6 ታዳጊ ከተማ 2
መሰላ
401 “ 6 ታዳጊ ከተማ 2
ችጓሊ
402 ደቅ “ 6 ታዳጊ ከተማ 2
23