Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 2

የሀረሪ ክልል ስራ አመራርና ከያዘን ኢንስትቲዩት አመራርና ሰራተኞች በተገኙበት የ 2016 በጀት አመት የ 6 ት ወር

አፈጻጸም ግምገማን አስመልክቶ የተያዘ

ቃለጉባኤ

የስብሰባ ቦታ------------------ በተቋሙ መሰብሰቢያ አዳራሽ

የስብሰባ ቀን-----------------24/4/2016

የስብሰባው ሰአት------------ 3፡00

የመወያያ አጀንዳ፡- 1.የተቋሙን የ 2016 እቅድ የ 6 ት ወር አፈጻጸም ሂደቶች ላይ መወያየት

ሰብሳቢ ፡- 1. አቶ ፈትሂ አብዱልመጂድ

በእለቱ የተገኙ አባላት

1. ይትባረክ ታደሰ
2. ሺማ ሰለሀዲን
3. ካሊድ ዘይዳን
4. አመለወርቅ ወጋየሁ
5. ፉራድ አብዱላሂ
6. መቅደስ ተፈራ
7. ናዲያ አብዱላሂ
8. አሪፍ አሊዪ
9. አህመድ ረመዳን
10. ወሲላ ኑሮ
11. አይሻ አብዱሰላም
12. ተወዱዳ ካሚል
13. ገነት ጎንፋ
14. ደራርቱ ዳዊድ
15. ህይወት ፍሬው
16. ኩዳ ጃኒ
17. ዘይነባ አንሳር
18. ረመዳን አብዲ
19. ከዲር ኡስማን
20. አሚር አፈንዲ
21. ሱሄይብ ኡመር
22. ፋኑኤል ማትያስ
23. ማወርዲ አደም
24. የምስራች ካሱ
25. ኢፍራህ በክሪ

ከላይ በተጠቀሰው ቀንና የመሰብሰቢያ ቦታ የተቋሙ አመራርና ሰራተኞች በተገኙበት በእለቱ በተያዘው አጀንዳ ላይ ከዚህ
እንደሚከተለው ተወያይተንበታል ይኸውም፡-
የ 2016 በጀት አመት በ 1 ኛው መንፈቅ አመት የ 6 ት ወር እቅድ አፈጻጸም የተከናወኑ ቁልፍ ተግባራት ላይ በአፈጻጸም
ሂደት የታዩ ጠንካራ ጎኖች፣ጉድለቶች፣ እንዲሁም ያጋጠሙ ችግሮችን የገመገመ ሲሆን በእለቱ እንደድክመት ከተነሱት
አንኳር ነጥቦች ውስጥ

 የግብዓትና የበጀት ውስንነት ከፍተኛ መሆን፣


 ኢንስቲትዩቱ በሙሉ አቅሙ አደረጃጀትና አሠራሩን በማስተካከለ መንቀሳቀስ አለመቻል፣
 የጥናትና ሥልጠና ሥራዎች በክልል ደረጃ አቀናጅቶ መምራት አለመቻል፣
 የካይዘን አመራር ፍልስፍና ትግበራን ለሁሉም ተቋማት ተደራሽ አለማድረግ፣ የሚሉት በዋነኛነት ተጠቅሰዋል
የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል የተጠቀሱት ደግሞ
 የግብዓትና የበጀት ውስንነት ክፍተኛ ሆኖ ሳለ ስራውን ማከናወን መቻሉ፣
 በራስ አቅም የተለያዩ የስልጠና ማንዋሎች እና ቼክሊስቶችን ማዘጋጀት መቻሉ
 በተወሰኑ ተቋማት የካይዘን ትግበራ ማስጀመር መቻሉ፣
ያጋጠሙ ችግሮች በተመለከተም
 ለኢንስቲትዩቱ የሥልጠና በጀት አለመመድብ፣
 የፀደቀውን የኢንስቲትዩቱ ድርጅታዊ መዋቅር መሰረት በማድረግ የሰው ኃይል አለመመደ፣
 የሚመለከተው አካል ለኢንስቲትዩቱ ትኩረት አለመስጠት፣
 ምቹ የሥራ አካባቢ አለመኖር፣ የግብዓት ዕጥረት፣
 የኢንስቲትዩቱ ሥራ አመራር ቦርድ ሥራ አለመጀመር፣
በመጨረሻም ያጋጠሙ ችግሮች ሙሉ በሙሉ ቢወገዱ የመፍትሄ ሀሳብ ይሆናሉ በማለት በግምገማው ወቅት
የተወያየንባቸው ሲሆን በአፈጻጸም ሂደት የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል እንዲሁም የታዩ ደካማ ጎኖችን በማረም
የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ሁሉም የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች ተቀናጅተን መስራት እንዳለብን አቅጣጫ በማስቀመጥ
የእለቱን ስብሰባ አጠናቀናል፡፡

You might also like