Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 13

/ ///

የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ጥ አነ ኢ ል መምሪያ

የ 2016 በጀት የ 2 ኛ ሩብ ዓመት ሪፖርት

ታህሳስ /2016 ዓ.ም አሶሳ

መግቢያ

ሀገራችን ኢትዮጵያ ከድህነትና ኋላ ቀርነት በመላቀቅ ፈጣን ዕድገት ለማምጣት የቀየሰቻቸውን ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች
በብቃት ለማስፈፀም እንደክልል ብሎም በከተማ አስተዳደራችን የዘርፉን ተግባር የረጅም ጊዜ እና የአጭር ጊዜ ዕቅድ

በማቀድና በመተግበር ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛል። በመሆኑም ከወቅቱ አገራቀፍና አለም ዓቀፋዊ የስራ

ገበያ ፍላጎት ጋር ሊመጥን የሚችል በዕውቀት፣ክህሎትና አመለካት ተወዳዳሪ የሆነ የስራ ኃይል ማዘጋጀት

1
እና ከስራ ጋር ማስተሳሰሰር የሚያስችል የረጅም እና የመካከለኛ ጊዜ ዕቅድ አዘጋጅቶ መተግበር ያስፈልጋል፡፡

በዚህ ረገድ ከዚህ በፊት እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ክልል የስራ ዕድል ፈጠራ ተግባር ውጤታማ በሆነ መልኩ

ለመምራት የሚያስችል ተለዋዋጭ የሆነውን ሀገራዊና ዓለም ዓቀፋዊ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ሁኔታን

በጥልቀት ያገናዘበ ከመካከለኛ ጊዜ የዘለለ ዘርፉ የሚመራበት አካታችና የሚመለከታቸው አካላት

የተሳተፉበት ዕቅድ ወይም ፍኖተ ካርታ አልነበረም፡፡ ይሁንና ዓለም አቀፋዊ፣ ሀገራዊና ክልላዊ ሁኔታን ያገናዘበ

የከተማችን ነዋሪ ዜጎች ዘላቂና ጥራት ያለው ስራ መፍጠርን ዋና ዓላማ ያደረገ ዘርፉ የሚመራበት የ 10

ዓመት ፍኖተ ብልፅግና የእረጅም ጊዜ እቅድ እና የ 5 ዓመት የመካከለኛ ጊዜ እቅድ በማዘጋጀት እንድሁም

ለማስፈጸም የመች ዘንድ የ 2016 በጀት ዓመት እቅድን በማዘጋጀት ባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ በማድረግ ወደ

ትግበራ መገባቱ ይታወሳል፡፡

በዚህም መሰረት የ 2 ኛ ሩብ ዓመት የእቅድ ክንውን ሪፖርት እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል፡፡

ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ እሴቶች

የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ጥ/አነ/ኢ/ል/መምሪያ ሥልጣንና ኃላፊነት ፤ በሥሩ ካሉ የወረዳ መዋቅር እና ሌሎች
መንግስታዊ ተቋማት ጋር በመቀናጀት አጠቃላይ ተግባርና ኃላፊነትን ለመወጣት እንዲሁም ክልላዊና አገራዊ
ነባራዊ ሁኔታ መነሻነት የሚከተሉት ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ እሴቶች ተዘጋጅተዋል፡፡

1.1 ርዕይ /vision/

በ 2022 ብቃት ባለው የሰው ሀይል ጥራትና ቀጣይነት ያለውና ምቹ ስራ ለሁሉም ተደራሽ ሆኖ ማዬት፡፡

2
1.2. ተልዕኮ /Mission/
የአካባቢውን ፀጋ መሰረት በማድረግ በዘርፉ ጥራት እና ብቃት ያለው የክህሎት ስልጠና በመስጠት፣ የጥቃቅና አነስተኛ
ኢንተርፕራይዞች በስፋት እንዲቋቋሙ በማድረግ ፣ የተሟላ ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት በመስጠት፣ የስራ ዕድል
መፍጠር እና በምርት ጥራትና ብቃት በገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በማድረግ ዜጎች የዘላቂ ስራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ
ማስቻል፡፡

1.3. እሴቶች/Values/
በሚከተሉት እሴቶችና እምነቶች ላይ አተኩረን እንሰራለን፡-
• ውጤታማነት፣
 የቡድን ስራ ለጋራ ውጤት፣
 ጥራትና ተወዳዳሪነት፣
 ሁልጊዜ መማር፣
 አገልጋይነት፣
2. የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ጥ/አነ/ኢ/ል/መምሪያ ተግባርና ሀላፊነት

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት የከተሞች አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባራቸውን ለመወሰን በወጣ አዋጅ
ቁጥር 141/2008 ዓ.ም መሰረት የአሶሳ ከተማ አስተዳደር የተቋቋመ ሲሆን በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 6 ንዑስ ቁጥር
1 ለከተማ አስተዳደሩ የተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት የአስተዳደሩን ልማት የሚመለከቱ ፖሊሲዎችንና
አዋጆችን በሥራ ላይ የማዋል፣ መመሪያዎችን እንዲሁም የኢኮኖሚና የማህበራዊ ልማት ዕቅዶችን
የማውጣትና በሥራ ላይ የማዋል ሲሆን በአስተዳደሩ የልማት እቅድ በማውጣት የከተማውን ማህበረሰብ
ተጠቃሚ ከሚያደርጉ መምሪያዎች መካከል አንዱ የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ጥ/አነ/ኢ/ል/መምሪያ በመሆኑ
የሚያከናውናቸውን ተግባርና ኃላፊነት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

የዘርፉን ልማት ለማፋጠን የሚረዳ ከሀገራዊና ክልላዊ ሁኔታን ያገናዘበ የከተማ አስተዳደሩን የአጭርና የረጅም
ጊዜ ፊዚካልና ፋይናንስ ዕቅድ አዘጋጅቶ በማፀደቅ ይተገብራል፣ ለዘርፉ የወረዳ መዋቅሩም ያወርዳል፣
አፈጻጸሙንም ይገመግማል፣ ለፈጻሚዎች ግብረ-መልስ ይሰጣል፣ እንዲሁም ለሚመለከተው አካል ወቅታዊ
የአፈጻጸም ሪፖርት ያቀርባል፤

1. በከተማ አስተዳደሩ የሥራ ፈላጊ ዜጎች ምዝገባ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የሥራ ፈላጊዎች
ልየታ ያደርጋል፤መረጃውን አጠናክሮ በመያዝ ጥቅም ላይ ማዋል፡፡
2. በከተማ አስተዳደሩ ለዜጎች የሥራ ዕድል ሊፈጥሩ የሚችሉ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ፀጋዎች ልየታ በጥናት
እንዲለዩ በማድረግ ለስራ ፈላጊዎች ተደራሽ ይደረጋል፡፡
3. በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ ስራ ፈላጊዎችን አዳድስ ኢንተርፕራይዞችን በማቋቋም እና በሌሎች ቀጣሪ
አካላት የስራ እድል ተጠቃሚ ማድረግ፤
3
4. የሚፈጠረው የስራ እድል የሴቶችን፣የወጣቶችን፣የአካል ጉዳተኞችን፣የስደት ተመላሽ ዜጎችን፣የሀገር
ውስጥ ተፈናቃይዎችን፣መኖሪያቸው ጎዳና የሆኑ ዜጎችን፣የዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች እና የቴክኒክ እና ሙያ
ተመራቂዎችን አካታችነትን ባረጋገጠ መልኩ እንዲሆን ይሰራል፡፡
5. ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን በዘርፉ ልማት ስትራቴጂዎች መሠረት ያደራጃል፣ ሕጋዊ ሰውነት
ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፣ ያድሳል፣ እንዲሁም በሕግ አግባብ ይሰርዛል፤
6. በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ ነባርና አዲስ ኢንተርፕራይዞች የሂሳብ አያያዝ ምክርና የኦዲት አገልግሎት
እንዲያገኙ ያደርጋል፣
7. ሥራ ፈላጊዎች እና ኢንተርፕራይዞች የቁጠባ ባህል ለማዳበር በቅድመ እና ድህረ ቁጠባ እንዲሁም ብድር
አሰጣጥ እና አመላለስ ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ይሰራል፤
8. በከተማ አስተዳደሩ ለሚሰሩ አመራሮች እና ባለሙያዎች አቅም ግንባታ ሥልጠና ይሰጣል፤

9. የዘርፉን ውጤታማናት ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማስቀጠል በእሴት ሰንሰለት ጥናት ላይ መሠረት ያደረገ

የኢንተርፕራይዞች አደረጃጀት መፍጠርና ለአንቀሳቃሾች ክፍተት ላይ የተመሠረተ የሥልጠና፣ የፋይናንስ፣

የምክር አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ፤

10. ለሚደራጁ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ወደ ሥራ ከመግባታቸው በፊት እንዲሁም በሥራ ላይ ላሉ


የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ብቃታቸውን የሚያሻሽልና
ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችል የሙያ ስልጠና እንዲያገኙ ያደርጋል፤
11. የመምሪያውን እና የመምሪያው የታችኛውን መዋቅር የሰው ኃይልና ተቋማዊ አደረጃጀት የዘርፉን
የልማት ስራዎች ከማከናወን አኳያ ያለውን አስቻይና ተግዳሮት በመለየት በተግዳሮት የሚስተዋሉትን
እንዲፈተቱ ለከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ እና ለቢሮው ማቅረብና፣ አፈጻጸሙንም መከታተል፤
12. የዘርፉን የልማት ስትራቴጂ በተገቢው ሁኔታ መተግበር፣ በስትራቴጂው አፈፃፀም የሚከሰቱ ችግሮችን
ለይቶ እንዲፈታ ለቢሮው ማቅረብ፣

13. ለዘርፉ ልማት የተዘጋጁ የድጋፍ ማዕቀፎች፣የአቅም ግንባታ መርሀ-ግብሮችና ለእነዚህ የህግ ማዕቀፎች
የተዘጋጁ መመሪያዎችን መነሻ በማድረግ የከተማ አስተዳደሩን እቅድ በማዘጋጀት ተግባራዊ ማድረግ፡፡

14. በቴክኒክ ሙያ ትምርትና ሥልጠና ተቋማት የሚፈጠሩ አዳድስ ቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዞች ተጠቃሚ
እንዲሆኑ ከሚመለከተው አካላት ጋር በቅርበት፤

15. የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ለኢንተርፕራይዞች ተከታታይነት ያለው የኢንዱስትሪ


ኤክስቴንሽን ድጋፍ እንዲያደርጉ መስራት፤

4
16. በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞችን ተከታታይ ሁለንተናዊ ድጋፍ በማድረግ ከደረጃ ወደ ደረጃ
በመሸጋገር ደረጃቸውን እንዲያሻሽሉ እና ወደ መካከለኛ ባለሀብት የማብቃት ስራ ማከናወን፤እውቅናና
የምስክር ወረቀት መስጠት፤

17. የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች በስታንዳርድ መሰረት አገልግሎቱን ማቅረብ በሚችልበት
ሁኔታ ማጠናከር፣
18. በዘርፉ ለተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች የማምረቻና የመሸጫ ቦታዎች ተዘጋጅተው በፍትሃዊነት
ለኢንተርፕራይዞች እንዲተላለፉ ማድረግ፤ለተላለፈበት አላማ ብቻ እንዲውል ክትትል ማድረግ፤የውል
ጊዜ ሲጠናቀቅ መልሶ በመረከብ ለሌሎች ማስተላለፍ እና የአጠቃቀም ችግር ያለባቸውን
ኢንተርፕራይዞች እርምጃ መውሰድ፤
19. ለኢንተርፕራይዞች የገበያ አማራጮች የአካባቢ፣የሀገር አቀፍ እና አለም አቀፍ የገበያ ትስስር እንዲያገኙ
ከሚመለከተው አካል ጋር በሙሉ በቅንጅት መስራት፤ እንዲሁም የንግድ ትርዒትና ባዛሮችን በማዘጋጀት
የኢንተርፕራይዞችን የገበያ አማራጭ ማስፋት፣ በሌሎች አካላት የሚዘጋጁ ክልላዊና አገራዊ የንግድ
ትርዒትና ባዛሮች ላይ ኢንተርፕራይዞችን ማሳተፍ፤
20. በከተማ አስተዳደሩ ያለውን የሚዲያ አማራጭ በመጠቀም በየደረጃው ለሚገኙ ኢንተርፕራይዞች እና

ለስራ ፈላጊዎች የልማት ስትራቴጅ ማስፋትና በማስተዋወቅ እንዲሁም የግንዛቤ መፍጠር ሥራዎችን
በመሥራት የዘርፉን የንቅናቄ ሥራዎችን ያከናውናል፤
21. ዘርፉን በሚመለከት ከሚሰሩ ወይም ሊያግዙ ከሚችሉ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር
የጋራ መግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ይሰራል፤
3. የተቋሙ ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮችና ዉጤቶች
በመምሪያው በሚቀጥሉት ዓመታት ለመድረስ ያስቀመጠውን ራዕይ ከግቡ ለማድረስ የሚያስችሉ አምስት ስትራቴጂያዊ
የትኩረት መስኮችን አዘጋጅቷል። እነዚህ የተዘጋጁ ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች የተቋሙን ዉስንነቶች የዳሰሱ፤ ከዓላማ
አስፈጻሚ ቡድን መሪዎች ጋር የጠበቀ ቁርኝት እንዲኖራቸውና የተቋሙን ሠራተኞች ሙሉ ትኩረት ለመሳብ እንዲችሉ
ለማድረግ ተሞክሯል፡፡ እነሱም በሚከተለዉ መልኩ ተቀምጠዋል፡፡

የትኩረት መስክ 1- ተቋማዊ የማስፈጸም አቅም፣ የሀብት አጠቃቀም እና የአገልግሎት አሰጣጥ አሰራር
ማጎልበት፡- ይህ የትኩረት መስክ ግልፀኝነትና ተጠያቂነትን በማስፈን፣ ወቅታዊና ቀልጣፋ አገልግሎት
በመስጠት፣ የለውጥ ስራዎቸን አጠናክሮ በመቀጠል፣ ውጤታማና ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት፣
የአሰራር ሥርዓቶችን በማሻሻል፣የሀብት አስተዳደር ውጤታማነትን ማጎልበትን ያካትታል፡፡ ከትኩረቱ መስኩ
አፈፃፀም እርካታዉ ያደገ ተገልጋይ ማፍራት ይጠበቃል፡፡

የትኩረት መስክ 2- የተቋማዊ አቀወመወና ብቃት ማጎልበት፡- ይህ የትኩረት መስክ የዘርፉን ስራዎች
በስታንዳርድ መሠረት አገልግሎት መስጠት የሚችል ተቋምና የሰው ሀይል በመዘርጋትና አቅምን በመገንባት
5
የትኩረት መስክ 3- ዘላቂ የስራ እድል በመፍጠር የዜጎችን ተጠቃሚነት ማሳደግ፡-ይህ የትኩረት መስክ የስራ
ፈላጊ ዜጎችን በመለየት ከስራ ጠባቂነት መንፈስ በማላቀቅ ሥራ ፈጠሪ ሆነው ብቁና ተወዳዳሪ የሚሆን
ምርት በማምረት የሀገራቸውን ኢኮኖሚ በማሳደግ ረገድ የበኩላቸውን አስተዋጾ ሚያበረክቱ ማድረግ፡፡
የትኩረት መስክ 4- የላቀ መረጃ አያያዝ፡- ይህ የትኩረት መስክ በዘርፉ ያለውን መረጃ በዘመነ ቴክኖሎጅ
በማደራጀት የሚሰጡ አገልግሎቶችን በፍጠነትና በጥራት ለመስጠት ብሎም ከሚመለከተው መዋቅር ጋር
የመረጃ ፍሰቱ በተቀላጠፈና ወጥ በሆነ ፎርማት ለመለዋወጥ ብሎም የዘርፉን ስራ ለሪሰርች ሰሪዎች ክፍት
ለማድረግ ተቃሚ ነው፡፡
የትኩረት መስክ 5- የጥቃቅን አነስተኛና መካከለኛ ኢነተርፕራይዞችን ሚና ማሳደግ፡- ይህ የትኩረት መስክ
ኢንተርፕራዮዞች ከተደራጁ በኃላ የተጠናከረ መንግስታዊ ድጋፍና ክትትል በማድረግ፤ኢንተርፕራይዞች
ያሉባቸውን ችግርና ክፍተት በመለየት ሁለንተናዊ ድጋፍ በማድረግና ሲበቁም የደረጃ ሽግግር በመስጠት
ተወዳዳሪ አምራች ማድረግ፡፡
4. የመምሪያዉ ስትራቴጂያዊ እይታዎች

የተቋሙን አፈጻጸም ከተለያዩ አቅጣጫዎች አንጻር ለማየት የሚያስችሉ አራት ዕይታዎች ተመርጠዋል፡፡
እነሱም፡-
1.1. ተገልጋይ

ተገልጋይ ማለት በሴክተሩ አገልግሎት ተጠቃሚ የሚሆኑ ተገልጋዮችን የሚያመለክት ሲሆን ሴክተሩ
በከተማዉ የስራ ፈላጊውን ማህበረሰብ ዘላቂ የስራ እድል በመፍጠር የልማት ፍላጎት ለማሟላት ብሎም በዚህ
ሂደት ተገልጋዮችን ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት የተቀመጡት ግቦች የአፈጻጸም ስኬት ዕውን ለማድረግ
የሚያስችል እይታ ነው፡፡
1.2. ፋይናንስ

በዚህ ዕይታ የዘርፉን አገልግሎት ለመስጠት ሲባል ከከተማዉ ውስን ሀብት የሚበጀተውን ማለትም
የፋይናንስ፣ የንብረት፣ ወዘተ… በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋል የተቀመቱ ግቦችን የምንፈትሽበት እይታ ነው፡፡

1.3. የውስጥ አሠራር


የውስጥ አሰራር እይታ ማለት ሴክተሩ ለተገልጋዮች ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የተሳለጡ እንዲሆኑና እሴት
የሚጨምሩ የውስጥ አሰራሮች /Systems/ እርስ በእርሳቸው በመመጋገብ ስትራቴጂያዊ ውጤቱ እንዲረጋገጥ
የሚያደርጉ ናቸው፡፡

6
1.4. መማማርና ዕድገት
በዚህ እይታ ከላይ የተጠቀሱትን ሶስት እይታዎች ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመለወጥ የሚያስችሉ ረቂቅ የሆኑ
አዕምሮአዊ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና ተቋማዊ ሀብቶች የሚካተቱበት የእይታ መስክ ነው፡፡

5. የ 2016 በጀት ዓመት ዝርዝር የትኩረት አቅጣጫዎች

 በከተማው የሚገኘውን ስራ ፈላጊ መለየትና መረጃ ማተናከር፤


 በከተማው ሚገኙ የስራ ፈላጊዎች የዘርፉን ስትራቴጅ ግንዛቤ በመፍጠር ከስራ ጠባቂነት ወደ ስራ
ፈጣሪነት እንዲመጡ ማድረግ፤
 ዘላቂ የስራ እድል መፍጠር
 ለተደራጁ ኢንተርፕራይዞች መንግስታዊ ድጋፍ ማድረግ፤
 ከባለድርሻ የግልና የመንግስት ተቋማት ጋር በመቀናጀት ኢንተርፕራይዞች የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን
ድግፍ ተጠቃሚ ማድረግ
 በከተማው ያለው የዘርፉ መዋቅር አገልግሎቱን መስጠት በሚችልበት ቁመና እንዲቆም ማድረግ
 የመረጃ አያያዝ ማዘመን
 የኢንተርፕራይዞችን ሽግግር መስራት
 የኢንተርፕራይዞችን የገበያ ትስስር ማጠናከር

6. የመምሪያዉ ስትራቴጂያዊ ግቦች


በ 2016 ዓ.ም የሚከናወኑ ተግባራትን በውጤት ተኮር ስትራቴጅክ ዕቅድ ለመቅረጽ ከትኩረት መስኮችና
ከተለዩት ወሳኝ ጉዳዮች መነሻ ስትራቴጅክ ግቦችን መለየት ያስፈልጋል፡፡ በመሆኑም የመምሪያውን
ስትራቴጅያዊ ውጤቶች የሚያሳኩ ግቦችን ከተመረጡት የትኩረት መስኮችና እይታዎች አኳያ የተቀረጸ ሲሆን
ለዚህም በዋነኛነት በጥንካሬ፣ በዉስንነት፣ መልካም አጋጣሚ እና ስጋት /SWOT/ የተገኙ ውጤቶችን እንደ
ግብአት መውሰድ ተችሏል፡፡

7
ተ.ቁ እይታዎች የተቋሙ ስትራቴጅያዊ ግቦች

1. ተገልጋይ የተገልጋይ/ባለድርሻ አካላት እርካታ ማሳደግ፣


2. ፋይናንስ የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር አሰራርና ውጤታማነትን ማሻሻል

የዕቅድ ዝግጅት፣ የክትትልና ግምገማ እና የስታቲስቲክስ መረጃ አስተዳደር አሰራር ማሻሻል


የኢንፎርሜሽን፣ኮሙኒኬሽን እና ቴክኖሎጂ አሰራርና ውጤታማነትን ማሻሻል
የውስጥ የአጋርነት እና የህዝብ ግንኙነት አሰራርንና ውጤታማነትን ማሻሻል
3. አሰራር ለተጠሪ ተቋማት እና ለለታችኛው መዋቅር የሚደረገውን ድጋፍና ክትትል ማሻሻል
የሴቶችና ማሕበራዊ ተሳታፊነትንና ተጠቃሚነትን ማሻሻል ውጤታማነት ማሻሻል
የስራ ፈጣሪነት ክህሎት እና የሥራ ባህል ለማሳደግ የተሰጠ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና
መስጠት
የኢንተርፕራይዞችን ምርትና ምርታማነት ማሳደግ

ለኢንተርፕራይዞች ሁለንተናዊ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ

በማደራጀት የሚፈጠር የስራ ዕድል

በቅጥር የሚፈጠር የስራ ዕድል

የሥራ እድል ፈጠራ ስራው አካታችነት ማሳደግ

የመረጃ አያያዝ ስርዓት ግንባታና አጠቃቀም

ከኢንተርፕራይዞች ምርጥ ተሞክሮ ቀምሮ በማስፋት

ለኢንተርፕራይዞች የሚሰጡ መንግስታዊ ድጋፍችን ማጠናከር

የኢንተርፕራይዞችን ደረጃ ማሳደግ

4 የመማማር እና የሰው ሀብት ልማት እና አስተዳደር አሰራርና ውጤታማነት ማሻሻል


እድገት

መለኪያ ክብደት ግብ የአፈጻጸም ምርመራ


ተ.ቁ ስትራቴጂክ ግብ አፈፃፀም ደረጃ
በመቶኛ
1 የዕቅድ ዝግጅት፣ የክትትልና ግምገማ እና የስታቲስቲክስ በመቶኛ 3.2 100 በጣም
መረጃ አስተዳደር አሰራር ማሻሻል ከፍተኛ
2 የሰው ሀብት ልማት እና አስተዳደር አሰራርና ውጤታማነት በመቶኛ 1.4 100 በጣም
8
ማሻሻል ከፍተኛ
3 የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር አሰራርና ውጤታማነትን በመቶኛ 2.2 100 በጣም
ማሻሻል ከፍተኛ
4 የኢንፎርሜሽን፣ኮሙኒኬሽን እና ቴክኖሎጂ አሰራርና በመቶኛ 2.8 100 በጣም
ውጤታማነትን ማሻሻል ከፍተኛ
5 የአጋርነት እና የህዝብ ግንኙነት አሰራርንና ውጤታማነትን በመቶኛ 2 100 በጣም
ማሻሻል ከፍተኛ
6 ለተጠሪ ተቋማት እና ለወረዳዎች የሚደረገውን ድጋፍና ክትትል በመቶኛ 2 100 በጣም
ማሻሻል ከፍተኛ
7 የሴቶችና ማሕበራዊ ተሳታፊነትንና ተጠቃሚነትን ማሻሻል በመቶኛ 1.4 100 በጣም
ከፍተኛ
8 የስራ ፈጣሪነት ክህሎት እና የሥራ ባህል ለማሳደግ የተሰጠ የግንዛቤ በመቶኛ 9 100 በጣም
ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት ከፍተኛ
9 የኢንተርፕራይዞችን ምርትና ምርታማነት ማሳደግ በመቶኛ 11 100 በጣም
ከፍተኛ
10 ለኢንተርፕራይዞች ሁለንተናዊ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ በመቶኛ 8 100 በጣም
ከፍተኛ
11 በማደራጀት የሚፈጠር የስራ ዕድል በመቶኛ 4.3 94 በጣም
ከፍተኛ
12 በቅጥር የሚፈጠር የስራ ዕድል በመቶኛ 9.3 92 በጣም
ከፍተኛ
13 የሥራ እድል ፈጠራ ስራው አካታችነት ማሳደግ በመቶኛ 3.4 100 በጣም
ከፍተኛ
14 የመረጃ አያያዝ ስርዓት ግንባታና አጠቃቀም በመቶኛ 4 100 በጣም
ከፍተኛ
15 ከኢንተርፕራይዞች ምርጥ ተሞከሮ ቀምሮ ማስፋት በመቶኛ 8.7 100 በጣም
ከፍተኛ
16 ለኢንተርፕራይዞች የሚሰጡ መንግስታዊ ድጋፍችን በመቶኛ 24 67 መካከለኛ
ማጠናከር
17 የኢንተርፕራይዞችን ደረጃ ማሳደግ በመቶኛ 3.3 100 በጣም
ከፍተኛ
100 97 በጣም
ከፍተኛ

የ 2 ኛ ሩብ ዓመት ክንውን

1. የሥራ ፈላጊዎች ምዘገበና ግንዘቤ

በከተማችን 1500 ስራ ፈላጊ ዜጎችን ለመመዝገብ ታቅዶ ወንድ 976 ሴት 1001 በድምሩ 1977 ስራ ፈላጊ
ዜጎችን በመመዝገብ ከእቅድ አኳያ ከ 100% በላይ ተከናውኗል፡፡

ለተመዘገቡ 1500 ስራ ፈላጊ ዜጎች በስራ ዕድል ፈጠራ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለመስጠት ታቅዶ፤
በሁለቱ ወር ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ወንድ 976 ሴት 1001 በድምሩ 1977 ለሆኑ ስራ ፈላጊ
የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት ከእቅድ አኳያ ከመቶ ፐርሰንት በላይ ማከናወን ተችሏል፡፡

9
2. የስራ እድል ፈጠራ ስራዎች

በከተማ ግብርና ዘርፍ ፣በኢንዱስትሪ ዘርፍ እና በአገልግሎት ዘርፍ በማደራጀት የስራ እድል ከመፍጠር አንጻር
175 የነበረውን የኢንተርፕራይዝ ብዛት ወደ 223 ለማሳደግ ታቅዶ ወደ 207 ከፍ በማድረግ የእቅዱን 93%
ተከናውኗል፡፡

በአጠቃላይ በነባር ኢንተርፕራይዞች በከተማ ግብርና፣በማኑፋክቸሪንግ እና በአገልግሎት ዘርፍ ኢ/ዞች


ቢዝነሳቸውን በማስፋት በሚፈጠር የቅጥር ፍላጎት ከነበረበት 1506 ወደ 1793 ለማሳደግ ታቅዶ 1822
በማድረስ የእቅዱን 100% ተከናውኗል፡፡

በከተማችን የተሰማሩ የግል ባለሀብቶች በሚፈጥሩት የቅጥር እድል ከነበረበት 2180 ወደ 2705 ከፍ ለማድረግ
ታቅዶ 2317 በማሳደግ የእቅዱን 86% ተከናውኗል፡፡

በመንግስት ግዙፍ ፕሮጀክቶች ላይ የነበረው የስራ እድል ፈጠራ ከነበረበት 874 ወደ 1270 ለማሳደግ
ታቅዶ፤1144 በማሳደግ የእቅዱን 90 % ተከናውኗል፡፡

በመንግስት መስሪያቤት በከተማችን ከመምሪያ እስከ ቀበሌ ባለው መዋቅር፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ
አገልግሎት ሰጭ ተቋም፣በኢትዮ ቴሌ እና በመሰል መንግስታዊ ተቋም ከነበረበት 553 ወደ 593 ለማሳደግ
ታቅዶ፤689 በማድረስ የእቅዱን 100% ተከናውኗል፡፡

መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የሚፈጠረው የስራ እድለ ከነበረበት 450 ወደ 560 ለማሳደግ ታቅዶ 540
በማድረስ የእቅዱን 80% ተከናውኗል፡፡

በከተማችን በሚገኙ ህብረት ስራ ማህበራት የሚፈጠር የስራ እድል ከነበረበት 107 ወደ 116 ለማሳደግ ታቅዶ
154 ማሳደግ የእቅዱን 100% ተከናውኗል፡፡

አጠቃላይ በሩብ ዓመቱ የስራ እድል ፈጠራ ከነበረበት 5670 ወደ 7037 ለማድረስ ታቅዶ ወደ 6576 ከፍ
በማድረግ የእቅዱን 93.4 % ተከናውኗል፡፡

የአንድ ማዕከል ስራዎች

ኢንተርፕራይዞችን ሁለንተናዊ ድጋፍ በማድረግ ከደረጃ ወደ ደረጃ በማሸጋገር ረገድ ላይ ከደረሰበት 24 ወደ 53


ለማሳደግ ታቅዶ 53 ኢንተርፕራዞች ደረጃ ሽግግር የተከናወነላቸው ሲሆን የእቅዱን 100% ተከናውኗል፡፡

የገበያ ትስስር

 በሩብ ዓመቱ ለኢንተርፕራይዞች እርስበርስ፣ሰብኮንትራት እንዲሁም ከሌሎች መንግስታዊ እና


መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት የገበያ ትስስር ከመፍጠር አኳያ ቀደም ሲል ተጠቃሚ የነበሩት ኢዞች
10
ብዛት ከነበረበት 236 ወደ 260 ከፍ ላማድረግ ታቅዶ 258 ተጠቃሚ ኢንተርፕራይዞችን
የገበያትስስር የተፈጠረላቸው ሲሆን ከብር አኳያ ከነበረበት 147.4 ሚሊዮን ወደ 200 ከፍ
ለማድረግ ታቅዶ 161.2 ሚሊዮን ብር የገበያ ትስስር በመፍጠር የእቅዱን ከ 90%ተከናውኗል፡፡

ኢንተርፕራይዞችን የስራ ላይ እና የቅድመ ቁጠባ ባህላቸውን በማሳደግ የቆጣቢዎች ኢ/ዞች


ብዛት ቀደም ሲል ከነበረበት 151 ወደ 180 ኢ/ዞች ለማሳደግ ታቅዶ 182 ኢ/ዞ እንዲቆጥቡ
በማድረግና የተቆጠበው የገንዘብ መጠን ከነበረበት 10.9 ሚ ወደ 13.4 ሚ ለማድረስ ታቅዶ 13.5
ሚ ብር በመቆጠብ የእቅዱን 100% ተከናውኗል፡፡

 ውዝፍ ብድርን ከማስመለስ አንጻር ቀደም ሲል ከመለሱት 87 ኢንተርፕራይዞች ወደ 95


ለማሳደግ ታቅዶ 104 ኢንተርፕራይዞች ውዝፍ ብድር እንዲመለሱ በማድረግ ብሎም ቀደም ሲል
ከተመለሰው 1.5 ሚ ብር ወደ 1.6 ሚ ብር ለማሳደግ ታቅዶ ብር 1.78 ሚ ብር ውዝፍ ብድር
በማስመለስ የእቅዱን 100% ተከናውኗል፡፡

 በዘመኑ የሚመለስ ብድርን ከማስመለስ አንጻር ቀደም ሲል ከመለሱት 81 ኢንተርፕራይዞች ወደ


97 ለማሳደግ ታቅዶ 100 ኢንተርፕራይዞች በዘመኑ የሚመለስ እንዲመለሱ በማድረግ ብሎም
ቀደም ሲል ከተመለሰው 2 ሚ ብር ወደ 4 ሚ ብር ለማሳደግ ታቅዶ ብር 4.34 ሚ ብር ውዝፍ
ብድር በማስመለስ የእቅዱን 100% ተከናውኗል፡፡

 ለኢንተርፕራዞች የብድር አገልግሎት ከመስጠት አንጻር ለ 10 ኢንተርፕራይዞች ብር 3 ሚ ብር


ብድር ለማሰራጨት ታቅዶ ከለ 12 ኢ/ዞ 5.5 ሚ. ብር በማሰራጨት የእቅዱን 100%
ተከናውኗል፡፡

5. የኢንዱስትሪ ኤክስቴሽን ድጋፍ ስራዎች

ነባር ኢንተርፕራይዞችን በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ተጠቃሚ ለማድረግ በአሶሳ ከተማ የሚገኙ
የመንግስትና የግል ኮሌጆንን በማነጋገር ብሎም ስምምነት ላይ በመድረስ ኮሌጆቹ ስልጠና ለመስጠት
በተቋቋሙበት አላማ መሰረት ኢንተርፕራይዞችን በየዘርፋቸው ማለትም በከተማ ግብርና 22 ኢ/ዝ ወንድ 27
ሴት 31 ድምር 58፤ በአገልግሎት ዘርፍ በኢ/ዝ 14 ወንድ 24 ሴት 12 ድምር 36፤ በማኑፋክቸሪንግ በዚ/ዝ 16
ወንድ 42 ሴት 27 ድምር 69 በኮንስትራክሽን በኢ/ዝ 20 ወንድ 52 ሴት 47 ድምር 99 በመመልመል፤72

11
ኢንተርፕራይዞችን በአንቀሳቃሽ ወንድ 145 ሴት 117 ድምር 262 በማስረከብ በሂሳብ አያያዝ፤ በቴክኖሎጅ
ሽግግር፤ በሙያ ክህሎት፣ በኢንተርፕሪነርሽፕ፣ የካይዘን ልማት ስልጠና እና መሰል ድጋፎችን ተከታታይነት
ያለው ድግፍ በማግኘት ላይ ይገኛሉ፡፡

 በስደተኖች ተጽዕኖ ምልሽ ምዕራፍ 2 ፕሮጀክት በ 2015 የተመለመሉ 9 ኢንተርፕራይዞች


የመጀመሪያ ዙር የገንዘብ ድጋፍ እንዲለቀቅላቸው ወይም እንዲደርሳቸው ተደርጓል፡፡

 በተመሳሳይ በ DRIDP ፕሮጀክት የ 2016 ተጠቃሚዎችን ለመመልመል በክቡር ከንቲባ


ሰብሳቢነት ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጎ በተቀመጠው አቅጣጫ መደረት በምዝገባ ሂደት
ላይ እንገኛለን፡፡

6. ያጋጠሙ ችግሮች

 የኢንተርፕራይዞቻችን ጥያቄ የሆነው የመስሪያና የመሸጫ ቦታ ሲሆን ሊመቻችላቸው አለመቻሉ፤

 ከከተማው መስፋት እና ከኢንተርፕራይዞች መብዛት ባሻገር ለክትትልና ድጋፍ አገልግሎት የሚውል


ተሸከርካሪ በተቋሙ አለመኖር፤

 ለስራ ማስኬጃና ለቁሳቁስ ግዥ የሚውል የበጀት እጥረት መኖር፤

7. የተወሰዱ የመፍትሄ ሀሰቦች

 ባሉት ውስን የመምሪያው ባለሙያዎች በእግር እና በግል የባጃጅ ታክሲ ክፍያ አገልግሎት ክትትልና
ድጋፍ ማድረግ፤

8. የትኩረት አቅጣጫ

 ለነበር ኢ/ዞች የተጠናከረ ክትትልና ድጋፍ እንዲሁም ችግር ፈች የአቅም ግንባታ ስራ ማከናወን፡፡

 የስራ ፈላጊዎችን ልየታና ግንዛቤ በመፍጠር ማደራጀት ብሎም ወደ ስራ ማስገባት

 የመንግስትን ድጋፍ ማለትም የገበያ ትስስር፣ብድር የሸድና ሌሎችንም ድጋፎ ማጠናከር፡፡

የመምሪያው ማኔጅመት ውሳኔ

ከላይ የቀረበው የ 2 ኛ ሩብ ዓመት የመምሪያው ሪፖርት በ 024 /04/16 ዓ.ም የመምሪያው ማኔጅመት
ተሰብስቦ በመገምገም አጽድቆታል፡፡

የማኔጅመት አባላትም
12
1. አቶ ሰኢድ አብዱረሂም……………. ሰብሳቢ
2. አቶ ተስፋዬ ማናሎ ……………… አባል
3. አቶ አብዱልቃድር አብዱላሂ……… አባል
4. አቶ አብደላ ሀዲ…………………… አባል

13

You might also like