Professional Documents
Culture Documents
2727
2727
27፡44====
======በነጋም ጊዜ ምድሩን አላወቁትም። =======
የቀጠለ……..
መግቢያ
ወንጌላዊ ቅዱስ ሉቃስ ስለ ወንጌል እስረኛ የሆነዉን የቅዱስ ጳዉሎስን ጉዞ በደንብ ገልጿል። ያሳያል።
በጉዞው ምን እንደገጠማቸው፦
• የጳዉሎስን ምንነት
• የእሰረኞቹን
• የመሪዎቹን ሁኔታ በደንብ ገልጿል።
• እስረኖቹ በመቶ አለቃ በሚመሩ ወታደሮች ይጠበቁ ነበር።
• ቅዱስ ጳዉሎስ እንደ እስረኛ ሳይሆን እንደ የክርስቶስ ወንጌል ሰባኪ ነበር
• ጉዞው በመከራ የተመላ ቢሆንም፣ ወንጌልን ለማስተማር ጥሩ አጋጣሚ ነበር
ጉዞው ፦
ከቂሳርያ ወደ ማይራ 1-5
ከማይራ/ ሙራ/ ወደ መልካም ወደብ 6-8
ከመልካም ወደብ ወደ ማልታ 9-44
ዳግመኛም እንደ ፍርዱ እንዴት እንደ ፈረዱ ተመልከት፤ “አንተ ከራስህ ጋር ነህ” ካሉ በኋላ ለሞት
ብቻ ሳይሆን ለእስራትም ያልተገባ ነው ብለው ነጻ አወጡት፤ በእርግጥም ሊፈቱት ይወዱ ነበር።
ቅዱስ ጳዉሎስም ከእነዚያ ጋር / ከእስረኞቹ ጋር/ አብሮ ታሰረ/ አብሮ ለፍርድ ወደ ሮም ሄደ/ ተባበረ
እንጂ በክፉ ድርጊታቸው አልተባበረም።
በዚህም ድንቅ ነገር ይታያል።
የጳዉሎስ ጉዞ ወደ ሮም
የቀጠለ………….
ጉዞው ተወሰነ፦
"ወደ ኢጣሊያም በመርከብ እንድንሄድ በተቈረጠ ጊዜ፥ ጳውሎስንና ሌሎች እስረኞችን ከአውግስጦስ
ጭፍራ ለነበረው ዩልዮስ ለሚሉት ለአንድ የመቶ አለቃ አሳልፈው ሰጧቸው።
የጳውሎስ ጉደኞች፦
ቅዱስ ሉቃስ፡
ጳዉሎስ ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ አብሮት ነበር።
በቂሳርያ ጳዉሎስ ሲታሰርም በቂሳርያ ይኖር ነበር
ቅዱስ ጳዉሎስ ወደ ሮም ለፍርድ ሲስሄድ አብሮት ነው የተጓዘው።
አርስጥሮኮስ፦ ተሰሎንቄያውም አብሮቸው ነበር። ከቅዱስ ጳዉሎስ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም አብሮ መጥቷል። የሐዋ.ሥ
19፡29 ወደ ሮም አብሯቸው ተጉዘ።
=====ሁለቱም በጳዉሎስ መታሰር አላፈሩም። የታሰረው ስለ ወንጌል ነውና። ነገር ግን አብረው እርሱ የሚቀበልዉን መከራ፣ በጉዞው
የሚመጣዉን ፈተና ለመቀበል የወሰኑ እዉነተኛ ጉደኛ፣ ደቀመዝሙር ናቸው። ህይወታቸዉን ለእሱ፣ ለስብከት አገልግሎት፣ ክርስቶስን
በአህዛብ ፊት ለመመስከር አሳልፈው የሰጡ ናቸው።=========
አርስጥሮኮስ ከጳውሎስ ጋር ምን ያህል ርቀት እንደሄደ ተመልከት። አርስጥሮኮስ በዚህ ጉዞ መኖሩ/መገኘቱ ለመልካም ነገር
እና ለአላማ ነው። ምክነያቱም የጳዉሎስን የሌሎችንም ስለ ክርስቶስ መከራ መቀበላቸዉን የሁሉንም ዘገባ ወደ መቄዶንያ ሰዎች
ይወስዳልና።
ጉዞው የጀመረው፦ ከቂሳርያ ነው። ከደቡብ ጠርሴስ ወደብ ማለት ነው። ወደ አድራሚጢስ መርከብ ገብተን በእስያ ዳር
ለመጓዝ ተነሳን።
የቀጠለ………….
ነፋሱ ትክክለኛ ነፋስ ቢሆን ኖሮ፣ በቀጥታ ይጓዙ ነበር። ቆጵሮስን በስተቀኝ አድርገው ይሄዱ
ነበር።
ነገር ግን ነፋሱ ትክክለኛ ነፋስ አይደለምና በነፋሱ ተጽዕኖ/ አስገዳጅነት ወደ ተለያየ አቅጣጫ ተጓዙ።
በዚህም ቆጵሮስን በስተግራ አለፏት።
የመርከቡ ሰራተኞች ቀጥታ በባህሩ ለመሄድ አልቻሉም። ነገር ግን በምዕራብ ነፋስ ተጽዕኖ
በኪልቅያና በጵንፍልያ አጠግብ ከተሻገሩ በኋላ በሉቅያ ወደ አለ ወደ ሙራ ደርሱ።
ማጠቃልያ፦
የቅዱሳን ሕይወት በጠቅላላው እንዴት መከራ የበዛበት ህይወት እንደሆን ተመልከት:፡
ከእስር ቤት ወደ ሌላ ፈተና ገቡ።
ግን በመርከብ እና በማዕበል ዉስጥ ወደቁ።
ሙራ፦ በግሪክ የሉቅያ ከተማ ናት። ትልቅ/ ዝነኛ የወደብ ከተማ ናት። ትላልቅ መርከቦችን
የምትስተናግድ ናት። በተለይ ከእስክንድርያ ወደ ሮም ስንዴ የሚያጓጉዙ መርከቦች
ይበዙባታል።
የቀጠለ…………
ጉዞ ከሙራ ወደ መልካም ወደብ
በዚያም የመቶ አለቃው ወደ ኢጣሊያ የሚሄድ የእስክንድርያ መርከብ አገኘ። በውስጧም አኖረን። (ቁ. 5፣6።)
ከከባዱ ነፍስ ለማምለጥ
ለመርከቧም ደህንነት
ቆጵሮስን ተገን አድርገው ተጉዙ። ይህዉም አደገኛዉን ነፋስ ለመሸሽ ነው።
ቀኒዶስ ከሙራ 130 ማይል ይርቃል። በምዕራብ ሙራ የሚገኝ ወደብ ነው። ጉዟቸውም ጥግ
ጥጉን ነው። ሲጓዙም በጭንቅ በዝግታ ነብር።
በዝግታ የሚጉዙበት ምክነያት በሰሜን ምዕራብ ነፋስ ምክነያት ነው። ይህ ነፍስ ጉዞው
በጭንቅ እንዲሆን አድርጓል።
ስለዚህም የቀርጤስን ከተማ ተገን አድርገው በሰልሙና አንጻር ሄዱ።
ለልስያ ከተማ ወደቀረበች ወደ መልካም ወደብ ደርሱ።
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ይህ ጾም የአይሁድ ጾም ሲሆን፣ ታላቁ ‘የሥርየት ቀን’ እንደሆነ ያምናል (ዘሌ.
23፡27)።
በሰባተኛው ወር በአሥረኛው ቀን (በመስከረም መጨረሻ አካባቢ) የበልግ ወራትን ተከትሎ፣ ያለው ወር ለመርከብ
ጉዞ አደገኛ በሚሆንበት ጊዜ ነው።
ከዚህ በተጨማሪ ሐዋርያው መንፈስ ቅዱስ እንዳናገረው ማንም ሊክደው አይችልም። በመርከቡ ጉዞ ላይ ምን
እንደሚገጥማቸው ማለት ነው።
ስንዴዉንም ሮም ትፈልገዋለች።
የመቶ አለቃው ግን ጳውሎስ ከተናገረው ይልቅ የመርከቡን ባለቤትና የመርከቡን መሪ አመነ። ቁ.11
ምክነያቱም፦
ብዙ ልምድ አላቸው በማለት ነው።
ከጳዉሎስ ይልቅ ለመርከባቸው እና ለደህነታቸው ያስባሉ ያዉቃሉ ብሎ ነው።
በዚህ ምክነያት መቶ አለቃው አመነ። ምንም እንኳ ለጳዉሎስ ርህራሄ እና አድናቆት፣ ክብር ቢኖረውም።
ነገር ግን ምክሩን አልተቀበለም።
"እኛም በዐውሎ ነፋስ ስለ ተናወጥን በማግስቱ መርከቡ ጭነት ወደ ባህር ይጥሉ ነበር።" (የሐዋ. ሥራ 27:18)
በማግስቱ እቃውን በተለይም እህሉን ወደ ባህር መጣል ጀመሩ።
ሀብት እንደማያድናቸው ተረድተዋል።
ነገር ግን ይህ በህይወታችን መርከብ ላይ ያለዉን ከባድ ሸክም ያሳያል።
ይህም ሸክም በዚህ ዓለም ውኃ ውስጥ ልንጥለው የሚገባ ነው።
የቀጠለ…………
ጠቢቡ ሰሎሞን “ሀብት ለባለቤቱ የተቆጠበች መከራው ናት።” ሀብት ጉዳት ነው። (መክ. 5፡13)።
የዚህ ዓለም ሰዎች ጊዜያዊ ሕይወታቸውን ለማዳን ያገኙትን/ያጠራቀሙትን/ በዉድ ዋጋ የገዙትን ሁሉ በቀላሉ እንዴት
እንደሚጥሉ አስገራሚ ነው።
ለዘለአለማዊ ሕይወታቸው ሲሉ ከሱ ትንሽ ክፍል ለድሆች እና ለችግረኛ ወንድሞቻቸው ለመስጠት በጣም ይከብዳቸዋል።
ዘላለማዊነትን ከክብ የሚጠባበቅ ሁሉ በዓለማዊ ጉዳዮች አይጠመድም።
የሚበልጥና ለዘወትር የሚኖር ገንዘብ በሰማይ ለራሳችሁ እንዳላችሁ አውቃችኋል” (ዕብ. 10፡34)።
የዚያች መርከብ መርከበኞች እንዳደረጉት፦ እኛም በዚህ ዓለም ማዕበል መካከል ሆነን ከባድ ሸክማችንን
ለማቅለል፣ በአየር ላይ እንደምትበር ወፍ ቀላል ለመሆን ቆርጠን መነሳት አለብን።
እንደ ፈርዖንና ወታደሮቹ እንዳንሆን። “ በግዙፍ በዉቅያኖስ/ ባህር ውስጥ እንደ እርሳስ ሰመጠን እንዳንቀር ማለት
ነው። " (ዘፀ. 15.10)
በእነዚያ አስጨናቂ ሁኔታዎች ውስጥ የኃይለኛውን ንፋስ ተፅእኖ ለመገደብ ሸራዎቹን ወደ ታች አወረዱ እና የ
1000 ቶን ጭነት መርከቧን ማቅለል ጀመሩ ።
ይኸዉም መርከቧ በኃይለኛ ማዕበል ግርፋት እንዳትፈርስ ነው።
በሦስተኛው ቀን የመርከቧን መያዣ በገዛ እጃቸው ወደ ባህሩ ላይ ጣሉት።
መርከቧ ውሃ መሞላት ስትጀምር፣ በብስጭት በየቦታው እየሮጡ እርስ በእርሳቸው እየተጣደፉ በከፍተኛ ድምፅ ጮሁ።
በዚህ ላይም ደግሞ ፦
ቀዝቃዛው ንፋስ፣
ከባድ ዝናብ
ድቅድቅ ጨለማ መከራቸውን ከፍ አደረገው።
================በዚያም አስፈሪ ድባብ ውስጥ ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ አምላኩ እየጾመ እየጸለየ ከእርሱ
ጋር በመርከብ ለሚሄዱት ሁሉ ሊፈጽምለት የገባውን አምላካዊ ቃል ኪዳን እውን ለማድረግ በቄሳር ፊት ቆሞ
ለጌታውና ለአዳኙ ይመሰክር ዘንድ ተልእኮውን ይፈጽም ዘንድ በመካከላቸው ነው ።
=====================
አንዳንዶች በዚህ ጾም ውስጥ ሁሉም ተሳትፈዋል ብለው ያምናሉ። ግን የጾሙት በአምልኮ ሥርዓት
ሳይሆን ከመከራና ከመራራነት የተነሣ ነው። እራሳቸውን እና መርከቧን ለማዳን አድካሚ ችግር ዉስጥ
ስለሆኑ ነው።
በዚህ ምክነያት በመብልና በመጠጥ አልጠመዱም።
ነገር ግን፣ ሁሉን ሰጠህ የሚለው ይህ በትዕቢት አይደለም ነገር ግን በታንኳ የሚሄዱትን ሊረዳቸው
ፈልጎ ነው እንጂ፤ ከእርሱ ጋር እንደ ታሰሩ እንዲሰማቸው አይደለምና።
ነገር ግን የተናገረውን ያምኑ ዘንድ ነው።
"እግዚአብሔር ሰጠህ" እነርሱ አልሰሙህምና በእውነት ሞት ይገባቸዋል፤ ነገር ግን ይህ የተደረገው
ለአንተ ከቸርነቱ የተነሣ ነው።
“ነገር ግን አሥራ አራተኛው ሌሊት በአድርያ ወደ ላይና ወደ ታች ስንነዳ፥ መርከበኞች በመንፈቀ ሌሊት
ጊዜ ወደ አገር የቀረቡ መሰላቸው። ልኩ፥ ሀያ ጫማም አገኘው። ጥቂትም ወደ ፊት ሄዱ፥
ደግመውም ለኩ፥ አሥራ አምስትም ስብ ሆኖ አገኙት።
የቀጠለ…………
“ቀኑም ሲደርስ ጳውሎስ ምግብ ይበሉ ዘንድ ሁሉን ለመነአቸው እንዲህም አላቸው፡- “እናንተ ከቀራችሁበት ምንም
ሳትቀምሱ በጾማችሁ ዛሬ አሥራ አራተኛው ቀን ነው። (ቁጥር 33)
(ለ) አንተስ ትላለህ፣ ምንም ሳይበሉ እንዴት ሄዱ?
እንዴትስ ተሸከሙት? ፍርሃታቸው ያዛቸው፣ እና የምግብ ፍላጎት ውስጥ እንዲወድቁ አልፈቀደላቸውም ፣ እነሱ
፣ በጣም ከባድ አደጋ ላይ ስለሆኑ ነው።
Note.
==============እየዬም ሲዳላ ነው።
እንዲሉ።
(=========በዛ ሰኣት ከመከራው ከሞት
እንዴት እንዳን እንጂ ምግብ ትዝ አላላቸውም።)
በዚያን ጊዜ ሁሉም ደስ አላቸው ሥጋንም ያዙ፤” (ቁ. 34-36) ሕይወታቸው ስለመዳኑ ምንም ጥያቄ እንደሌለው በማየቱ።
መልሕቆቹንም በወሰዱ ጊዜ፣ ራሳቸውን ወደ ባሕሩ አሳልፈው ሰጡ፣ እናም የመሪዎቹን ማሰሪያ ፈቱ፣ እናም ዋናውን ሸራውን
ለነፋስ አንስተው ወደ ባሕሩ ዳርቻ ሄዱ። ( ቁ. 37–41 )
የቀጠለ…………
መሪዎቹን ለነፋስ ሰጥተው "ወደ ባሕሩ ዳርቻ ሄዱ" ብዙ ጊዜ እንደዚህ አያደርጉትምና።
ኃይለኛ ነፋስ በሚኖርበት ጊዜ, ይህ መዘዝ ነው, የኋለኛው ክፍል (የማዕበሉን) ይሸከማል።
(ሀ) “ወታደሮቹም እስረኞቹን አንዳቸውም ዋኝተው እንዳያመልጡ ይገድሏቸው ነበር። (ቁጥር 42)
ዳግመኛም ዲያቢሎስ ትንቢቱን ሊያደናቅፍ ሞከረ፣ እና አንዳንዶቹን ሊገድሉ አሰቡ፣ ነገር ግን የመቶ
አለቃው አልፈቀደላቸውም፣ ምናልባትም ጳዉሎስ ያድነው እንደሆን ስላመነ።
የመቶ አለቃው ከጳዉሎስ ጋር ይህን ያክል ይወደው ነበር።
=================ጳውሎስም “ይህ ጉዞ ከጉዳትና ከመጥፋት ጋር እንደሚሆን
አይቻለሁ” ብሏል። (ቁጥር 10)==================
የቅዱስ ጳውሎስ አገላለጽ ምን ያህል የማይታሰብ/የማይገመት መሆኑን ተመልከት።
ትንቢት የሚናገር እንዳይመስል፥ ነገር ግን እንደ ግምት ይናገር ዘንድ፥ "አለሁ" ይላል።
ሲጀምር ይህን ተናግሮ ቢሆን ኖሮ አይቀበሉትም ነበርና።
እንዲያውም በዚህ በቀደመው አጋጣሚ ትንቢት ተናግሯል።
በኋላ እንዳደረገው እና (እዚያ) እንዳለው“የማመልከውን አምላክ” እየመራቸው ነው ይላል።
ከዉስጥ “ጠብ፣ ክርክር አለ”፣ ከውጭም ፍርሃት አለ። (2ቆሮ7፡5) ስለዚህ እርሱ/ጳውሎስ/ እውነተኛ
አብራሪ ነበር።
መላ ሕይወታችንን ተመልከት፡-
የእኛም ሕይወት ልክ እንደዚህ ነው። (እንዲህ ዓይነት ጉዞ ነበረ)።
በአንድ ወቅት በደግነት፣ በሌላ ጊዜ በዐውሎ ነፋስ እንናወጣለን።
አንዳንድ ጊዜ ከራሳችን ምክር፣ አንዳንዴ ከሥራ ፈትነት፣ ቁጥር ወደሌለው ክፋት ውስጥ
እንወድቃለን።
ጳውሎስን ባለመስማት፣ እርሱ ወደ አልመራን ወደ ሌላ መሄድ ስንፈልግ ይህ ይከሰታል።
ጳውሎስ ያን ጊዜ እንደ ታሰረ ሳይሆን አሁን ከእኛ ጋር በመርከብ እየተጓዘ ነው።
አሁንም በዚህ ባህር ላይ ለሚጓዙ/ በዚህ ዓለም/ ሁሉ “ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። እያለ ይመክረናል።
ልማድ/experience፦
በልምድ አንማር (በእኛ ወጪ) ነገር ግን ከተሞክሮ በፊት “ጉዳት እና
ኪሳራን እናስወግድ”።
የመቶ አለቃው ግን ጳውሎስ ከተናገረው ይልቅ የመርከብ መሪውንና
የመርከቡን ባለቤት ያምን ነበር። ሐዋ.ሥ. 27፡11
የመርከቡ መሪ እና የመርከቡ ባለቤት የቅዱስ ጳዉሎስን ምክር
አልሰማ ብለው በራሳቸው ተሞክሮ እና ልምድ ተጉዘው ትልቅ ኪሳራ ዉስጥ
ገቡ።
የራሳቸዉንም ህይወት እስከ ማጣት ደረሰ።
“ሀብታሞች ሊሆኑ የሚወዱ ወደ ፈተና ይወድቃሉ” የሚለውን ስሙ። (1 ጢሞ.6፡9.)
የቀጠለ…………
================እንግዲህ እንታዘዘው፣ ያለበለዚያ ምክሩን ስላልተቀበሉ
የደረሰባቸውን ተመልከት።===============
ዳግመኛም በሌላ ቦታ የመርከብ መሰበር መንስኤ የሆነውን ተናገረ።
“በእምነት ረገድ መርከብ /ዓለምን/ የሰበረ (ያሸነፈ) ማን ነው?” ብሏል።
አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር። (1ኛ ጢሞ. 19.)
ለጳውሎስ እንታዘዝዉ፡ በዐውሎ ነፋስ መካከል ብንሆንም ከአደጋው በእርግጥ ነፃ እንወጣለን።
በድጋሜ ፣ አንድ ሰው ራሱን ለፍትህ አሳልፎ ሲሰጥ፣ እርሱ ደግሞ በሌላ እስራት የታሰረ
አይደለምን?
ራሱን ለእይታዎች (ጊዜዎች) ሲሰጥስ?
ረሃቡ፣
አውሎ ነፋሱ፣
የተሳፈሩ ሰዎች ክፋት፣
የወቅቱ አለመመጣጠን፣ ተፈጥሮዊ ወቅት፣ ዝናቡ፣ ብርዱ፣
ማዕበሉ፣ ጨለማው?
ነገር ግን ከዚህ በተጻራሪ፣ የቅዱስ ጳውሎስ ክብረ ተገለጠ።
የቀጠለ…………
አሁን/ ዛሬም እንደዚያህ ነው፡-
ቅዱሳንን በአጠገባችን እንዲቆሙ እንለምን፣ የዚህ ዓለም ማዕበልም አይመጣም፣ አያሸንፈንም።
ይልቁንም አውሎ ነፋሱ ቢመጣም፣ ታላቅ መረጋጋት፣ ጸጥታ እና ነጻነት ከመከራ ዉስጥ ይሆናል።
ምሳሌ፦ ያች መበለት ቅዱስ ወዳጅ ነበራት።
ቅዱስ ወዳጅ ስለ ነበራት ልጅዋ ከሞት ዳነ።
ልጇን ደግሞ በሕይወት ተቀበለችው። (1ኛ ነገሥት 17:17.)...
የቅዱሳን ባሉበት ቦታ መከራ፣ ህመም አይኖርም፥ መከራ፣ ስቃይ ከመጣብን እኛን ለመፈተሽ
እና ለታላቁ የእግዚአብሔር ክብር ለመብቃት ነው።
አትፍራ፥ ቀበሮዎች አንበሶችን እንደሚፈሩ። (ክፉ ሰው) የቅዱሳንን መንገድ ይፈራል። “ጻድቅ
እንደ አንበሳ ደፋር ነው” ይላልና። (ምሳ. 28፡1
1) እነዚያን አንበሶች ወደ ቤታችን እናምጣቸው፥ አራዊትም ሁሉ ይሸሻሉ።
አንበሶች ማገሳት አያስፈልጋቸውም፣ ነገር ግን በቀላሉ ድምፃቸውን ሲያሰሙ ሌላው አራዊት
ይሸሻል።
አራዊትን ለማባረር አንበሳ ያን ያህል ጩኸት ማሰማት አይጠበቅበትም፤ ትንሽ ድምጽ ሲያሰማ/
ሲያጉረመርም ይፈራሉ።
ልክ እንደዚሁ የጻድቅ ጸሎት ክፉ መናፍስት እንዲሸሹ ያደርጋል።
ወደ ቤትህ መጥተው መቀበል ባትችል እንኳ። አንተ ወደ እነሱ ሂድ። ከእነሱ ጋር ኑር። በማደሪያቸውም እደር።
በዚያዉም ትደሰታለህ፣ በረከትም ታገኛለህ።
ታላቁ ነገር ከቅዱሳን በረከት ማግኘት ነውና። በቅዱሳን መባረክ ነዉና።
የቅዱሳን ጸሎታቸው ከእግዚአብሔር ምህረት ያስገኝልናል።