Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 9

የሪፖርት አቀራረብ እና የሽያጭ ግጭት አፈታት

መመሪያ

ዓላማ

1. የሽያጭ ሰራተኞች አማካኝነት የሚሰበሰብ የደምበኞች መረጃ በአንድ ማዕከል እንዲቀመጥ እና ለድርጅት
ጥቅም መዋል እንዲችል ለማድረግ፣(ሪፖርት አቀራረብ)

2. በሽያጭ ሰራተኞች መካከል የሽያጭ ይገባኛል ጥያቄ ቢነሳ በትክክለኛ መረጃ መሰረት ባደረገ መልኩ የሽያጩን
ባለቤት ለመወሰን እንዲያስችል

3. የሽያጭ ሰራተኞች ጀምሮ እስከ ሽያጭ መምሪያ ያለውን የስራ ሂደት ጊዜን በሚቆጥብ መልኩ ለመምራት እና
ለመመራት እንዲያስችል

4. የማህበራዊ ትስስር ድህረ-ገፅ ማስታወቂያ ስራ መምርያ

አንቀጽ -1
ሪፖርት አቀራረብ በተመለከተ

1.1. የሽያጭ ወኪሎች በየዕለቱ መረጃ የሚሰጧቸው ደምበኞች ለሽያጭ ሱፐርቫይዘር በድርጅቱ እለታዊ የደንበኛ
መመዝገቢያ ፎርም በመሙላት ለሱፐርቫይዘራቸው ሪፖርት ማቅረብ አለባቸው ሱፐርቫይዘሩም የሪፖርቱን
ትክክለኛነት ተመልክቶ በፊርማው ያረጋግጣል፡፡

1.2. የሽያጭ ወኪሉ የደንበኞች ዝርዝር ሪፖርት በስልኩ ፎቶግራፍ በማንሳት ለሽያጭ ሱፐርቫይዘር በቴሌግራም በየዕለቱ
መለክ ይኖርበታል፡፡

1.3. የሽያጭ ወኪሉ በየዕለቱ የደንበኞች ክትትል ሪፖርት (Follow Report) ቢሮ የመጡ እና ሳይት የጎበኙ ደንበኞች
ሪፖርት በስልኩ ፎቶግራፍ በማንሳት ለሽያጭ ሱፐርቫይዘር በቴሌግራም በየዕለቱ መላክ ይኖበታል፡፡

1.4. በየዕለቱ የሽያጭ ወኪሎች ተዘጋጅቶ በሱፐርቫይዘሮች የተፈረመበት ከሰኞ እስከ እሁድ የተጠቃለለ ሪፖርት ከሰኞ
ጠዋት ለሽያጭ ስራ አስኪያጆች ማቅረብ ይኖበታል፡፡

Page | 1
1.5. የሽያጭ ሱፐርቫይዘር ዕለታዊ ሪፖርቱን ትክክለኛነቱን አረጋግጦ ሳምንታዊ ሪፖርት እና ወርሀዊ ሪፖርት ለሽያጭ
ምክትል መምሪያ ሪፖርት ያደርጋል፡፡

1.6. የአፓርተመንት ሽያጭ መምርያው ወርሀዊ ሪፖርት ለአፓርትመንት ሽያጭና ማርኬቲንግ መምርያ ማቅረብ
ይኖርበታል፡፡

1.7. የሚቀርበው ሪፖርት ትክክለኛነት በሚቀበለው አካል ሳምፕል ተወሰዶ መረጋገጥ አለበት ነገር ግን በተደጋጋሚ
ሀሰተኛ ሪፖርቶች አቅርበው በተገኙ ጊዜ የሽያጭ ሀላፊዎች ግዴታቸውን ባልተወጡ አካላት ላይ ከመለስተኛ እስከ
ከፍተኛ ቅጣት ሊጣል ይችላል፡፡

1.8. የሽያጭ ሱፐርቫይዘር እንዲሁም የሽያጭ ምክትል መምርያ ወርሀዊ ዕቅድ እና ወርሀዊ የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት
ማድረግ ይኖርበታል፡፡

1.9. የኢንተርኔት አገልግሎት በሚቋረጥበት ጊዜ በየዕለቱ የተፈረመበትን የደምበኞች ዝርዝር በ SMS ለሽያጭ
ሱፐርቫይዘር መላክ ይኖርበታል፡፡

1.10. ጥናትና ፕሮሞሽን ባለሙያ በ Social Media የሚመጡትን ስልክ ቁጥሮች በመመዝገብ እለታዊ ሪፖርት ለሽያጭ
ስራ አስኪያጅ እና ለሸያጭ መምሪያ መላክ ይኖርበታል፡፡

1.11. ጥናትና ፕሮሞሽን ባለሞያ በ Social Media የድርጅቱ ስም እና ገፅታ በማይመጥን መልኩ ማስታወቂያ እንዳይሰራ
ይከታተላል፡፡ ነገር ግን ድርጅቱን በማይመጥን መልኩ የተሰሩ ማስታወቂያዎችን ከነማስረጃው ባገኘ ሰዓት የሸያጭ
ወኪሉ ወይም ማስታወቂያውን የተጠቀመም አካል ላይ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ለሸያጭ ሀላፊዎች ሪፖርት
ማድረግ አለበት፡፡

1.12. የሸያጭ ሀላፊዎች እና የውስጥ ሰራተኞች የአፖርትመንት ሽያጭ ሲኖራቸው በግል ጥረት ብቻ የተገኙ ደንበኞች
መሆናቸውን ለቅርብ አለቆች ከማስረጃ ጋር ሪፖርት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን

- ወደ ቢሮ የሚመጣን ደንበኛ
- በድርጅቱ ማስታወቂያ ድረ ገፅ የመጣ ደንበኛ
- በሽያጭ ወኪሉ በኩል የመጣን ደንበኛ
- የሽያጭ ቢሮ አካባቢ የመጣን ደንበኛ
- በሽያጭ ቢሮ ስልክ ቁጥሮች በሚደውል ደንበኛ

Page | 2
እንደ የግል ደንበኛ አድርጐ የሚያስመዘግብ የሽያጭ ሀይል እና የሽያጭ ሀላፊዎች በመረጃ ከተገኘ የዲሲፒሊን ቅጣት
እንዲሁም ያቀረበው የደንበኛው የይገባኛል ጥያቄ ውድቅ ይኖንበታል፡፡

1.13. የአልሳም ኃ/የተ/የግ/ማ ውስጥ በሌላ ዘርፍ ላይ ተሰማርተው የሚሰሩ የድርጅቱ ሠራተኞች ተመድበው ከሚሰሩበት
አላማ ውጪ ሽያጭ ላይ ማሳተፍ አይችሉም፡፡ ይህም (conflict of interest) እንዳይፈጥር እና ተቀጥረው
የሚሰሩበትን ስራ እንዳይበድል ይረዳል፡፡

አንቀጽ 2
የሽያጭ ግጭት አፈታት
ዓላማ

2/ በሽያጭ ሰራተኞች መካከል የሽያጭ ይገባኛል ጥያቄ ሲነሳ በትክክለኛ መረጃ መሰረት ባደረገ መልኩ የሽያጭ
ባለቤትነትን ለመወሰን እንዲያስችል

የሽያጭ ግጭት መፍቻ መስፈርቶች በፐርሰንት (%)

2.1. ደንበኛውን ቀድሞ ሪፖርት ያደረገ (Prospect) - - - - - - - - 30%


2.2. ቢሮ ያስመጣ ወይም ሳይት ያስጐበኘች (Office Visit and presentation) - - - 20%
2.3. ደንበኛ ክትትል ያደረገ (Flow up) - - - - - - - - - 20%
2.4. ሽያጩን ያካሄደ (Closing) - - - - - - - - - 30%
ጠቅላላ ድምር 100%

ሌሎች አስፈላጊ ነጥቦች

- አንድ የሽያጭ ወኪል የሽያጭ ግጭት እንዲታይለት መጠየቅ የሚችለው ሽያጭ ከተከናወነ በ 15 ቀን ውስጥ
ብቻ ይሆናል፡፡
- አንድ የሽያጭ ሰራተኛ አንድ ደንበኛን ሪፖርት አስቀድሞ ካቀረበ በኃላ ለ 1 ወር ደንበኛው የሽያጭ ወኪሉ
ተደርጐ ይቆጠራል፡፡ ነገር ግን ካለ ምንም ክትትል (Flow Up) 1 ወር ካለፈው በሌላ የሽያጭ ሰራተኛ ክትትል
ማድረግ ይችላል፡፡

Page | 3
- ግዢ በፈፀመው ደንበኛ በኩል RIFER ተደረገው የሚመጡ ደንበኞች መጀመሪያ ሽያጭ ወኪል የይገባኛል ጥያቄ
ማቅረብ የሚችለው መመዝገቢያ ገፅ ላይ ወይም Telegram ላይ 1 ወር ሪፖርት ካቀረበ ብቻ ነው፡፡
- በግጭት አፈታት ወቅት የሚታየው ሪፖርት በዋናነት በሽያጭ ሀላፊዎች በተከፈተው ቴሌግራም ግሩፕ ላይ
ይሆናል፡፡
- በሁለት የሽያጭ ወኪሎች የይገባኛል ጥያቄ ሪፖርት ላይ ተመሳሳይ ቀን ሆኖ ከተገኘ በሰዓታት ልዩነት የሚወሰድ
ይሆናል፡፡
- የቢሮ የሽያጭ ወኪሎች በድርጅቱ ለማስታወቂያ በሚደውሉት ተንቀሳቃሽ ስልክ በሚመጣው ቅደም ተከተል
መሰረት በመያዝ በዕለቱ መረጃ ፈልገው የሚደውሉ ደንበኞች ስልኩን የያዘው አካል ተደርጐ ይወሰዳል፡፡ ነገር ግን
በተንቀሳቃሽ ስልክ የሚደውሉ ደንበኞች ስልክ ሳይነሳላቸው እና መረጃ በስልክ ሳያገኝ ወደ ቢሮ የሚመጡትን
ደንበኞች ካሉ ለቢሮ ተረኛ (Walkin) ይሰጣል፡፡
- በሽያጭ ቢሮዎች መረጃ ለማግኘት የሚመጡ ደንበኞች በዕለቱ ደንበኛ ለማስተናገድ ተረኛ በሆነ የቢሮ ሽያጭ
ወኪል ይስተናገዳል፡፡
- በመመሪያው ላይ የተቀመጠው የሽያጭ ግጭት መፍቻ ፐርሰንት (%) ውጤት እኩል ከሆነ እና ለሸያጩ ወኪሉ
እኩል የሆነ ጥረት ማድረጋቸውን በሀላፊዎች ከታመነበት ሽያጩን የሚካፈሉ ይሆናል፡፡

- አንድ የሽያጭ ወኪል አንድ ደንበኛን በሪፖርቱ አስቀድሞ ካቀረበ በኋላ ለ 1 ወር ደንበኛው የሸያጭ ወኪሉ ተደርጎ
ይቆጠራል፡፡ ከ 1 ወር በኃላ ደንበኛው አብሮ ሊቀጥል የሚችለው ክትትል መኖሩ በሪፖርት ከተደገፈ ብቻ ነው፡፡
- ማንኛውም የሚቀርቡ መረጃዎች በሽያጭ ኃላፊዎቻቸው ቴሌግራም ላይ በሚታይ መልኩ ግጭት ከመከሰቱ
በፊት የተቀመጡ ዳታዎች መሆን አለባቸው፡፡
- ኮምሽን የተከፈለባቸው ሽያጮች የሽያጭ ግጭት ቢቀርብም የመታየት እድል የላቸውም፡፡
- ከዚህ በፊት የገዛን ደንበኛ ማንኛውም የሽያጭ ሠራተኛ በአዲስ መልኩ ፍላጎት በመፍጠር ለደንበኛውም ሆነ
ለቅርብ ጓደኞቹ መሸጥ ይችላል፡፡ ሆኖም ነባሩ የሽያጭ ሠራተኛ ከደንበኛው ጋር አዲስ የሽያጭ ሂደት አለመኖሩ
መረጋገጥ አለበት፡፡
- ከቴሌግራም የሪፖርት ልውውጥ ውጭ የድምፅ ቅጂ ወይንም የደንበኞች ምስክርነት ለግጭት መፍቻ መዋል
አይችልም፡፡
- የሸያጭ ወኪሉ ወይንም ፍሪላንሠር የደንበኞችን ሪፖርት ፎቶግራም በማንሣት ወይንም ቀጥታ በቴሌግራም
በየቀኑ ለሚመለከተው ሥራ አስኪያጅ መላክ ይኖርበታል፡፡
- የደንበኞችን ክትትል ሪፖርት (Follw up) የደንበኛውን አስተያየት ያካተተ ወቅቱን ጠብቆ ለሚመለከተው ሃላፊ
በፎቶ ወይንም በቀጥታ በቴሌግራም ላይ ማስቀመጥ ይኖርበታል፡፡
- ሐሰተኛነታቸው የተረጋገጡ ሪፖርቶች የሚገኙ ከሆነ መረጃውን የሠጠውም አካል ሆነ እያወቀ የተቀበለው አካል
በየደረጃው ቅጣት የሚጣልበት ይሆናል፡፡
- የኢንተርኔት አገልግሎት በማይኖርበት ግዜ በ SMS መላክ እና ኢንተርኔት በማይኖርበት ሰዓት በስክሪን ሹት
በማድረግ ቴሌግራም ላይ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡

Page | 4
አንቀጽ 3

የአልሳም ፕሮጀክት 1 ላይ የገዙትን ደንበኞች በተመለከተ

3.1. የአልሳም ፕሮጀክት ላይ የገዙት ደንበኞች በአሁኑ ሰዓት ደንበኝነታቸው የድርጅቱ ስለሆነ በሽያጭ መምሪያው
አደረጃጀት ብቻ የሚሸጡ ይሆናል፡፡
3.2. የአልሳም የሽያጭ ቢሮ ሽያጩ ከመጀመሩ በፊት ደንበኞቹ ጋር በመደወል ሙሉ መረጃ በመስጠት አዲስ
በተከፈተው የቴሌግራም ፔጅ ላይ ሪፖርት ማድረግ አለበት፡፡
3.3. የአልሳም የሽያጭ ቢሮ ደንበኞቹን እንደራሱ የቢሮ ደንበኛ አድርጐ መያዝ የሚችለው ለ 3 ወር ብቻ ነው፡፡
3.4. የአልሳም ቁጥር 1 ላይ ያሉ ደንበኞች የሽያጭ ቢሮው በ 3 ወር ውስጥ ክትትል አድርጐ ሽያጭ ያላስመዘገበ
ከአልሳም የሽያጭ ቢሮ ውጪ ይሆናል፡፡
3.5. የአልሳም የሽያጭ ቢሮ ከዚህ በፊት አልሳም ቁጥር 1 ላይ በተገዛ በባል እና ሚስት እንደሁም በተወካይ የተመዘገቡ
ሽያጮች ላይ ብቻ የሽያጩ ባለቤት ይሆናል፡፡
3.6. የአልሳም የሽያጭ ቢሮ ለደንበኞች መረጀ ከሰጠ በኃላ በየ 15 ቀኑ ክትትል (FOLLOW UP) ማድረጉን በየ 15 ቀኑ
ሪፖርት ያቀርባል
3.7. አልሳም ቁጥር 1 ላይ የነበሩ የሽያጭ ሰራተኞች ከአልሳም ቁጥር 2 ላይ የድርጅቱ ደሞዝተኛ ቅጥር ከሆኑ ከዚህ
በፊት በሽያጭ ወኪሉ ከተመዘገበ ደንበኞቹን አሳምኖ አልሳም ቁጥር 2 ላይ እንዲገዙ የማድረግ እድል ይሰጠዋል፡፡
3.8. አልሳም አፓርትመንት ቁጥር 2 ላይ የሚገዙ የቀድሞ ደንበኞች በቢሮ ያመጣ(Walkin) ደንበኛ የሚመዘገቡ
ይሆናሉ፡፡
3.9. ከአልሳም ቁጥር አንድ ላይ የገዙ ደንበኞች ስልክ ቁጥራቸው በብዙ አካላት በስራ ጉዳይ የሚኖር ሲሆን በዋናነት ስለ
አልሳም ቁጥር 2 መረጃ በመስጠት እና ሽያጭ በማካሄድ የአልሳም አፓርትመንት ሽያጭ ቢሮ ሀላፊነት ወስዶ
ይሰራል፡፡
3.10. በአልሳም ቁጥር አንድ ላይ የገዙትን ደንበኞች በተለያየ መንገድ በመደወል እና ምቾት መንሳት ፈፅሞ የተከለከለ
ነው፡፡
3.11. ከሶስት ወር በኃላ የሚመጡ የይገባኛል ጥያቄ በአንቀፅ 2 ላይ ባለው የሽያጭ ግጭት አፈታት ላይ መሰረት
ያደርጋል፡፡

አንቀፅ 4
የሽያጭ ግጭቶችን የመዳኘት ስልጣን

4.1. በአንድ የሸያጭ ሱፐርቫይዘር ቡድን ለሚፈጠር የሸያጭ ግጭቶች የሽያጭ ሱፐርቫይዘር ዳኝነት የመስጠት መብት
አለው፡፡
4.2. በሁለት የሽያጭ ሱፐርቫይዘር ቡድን ለሚፈጠር የሸያጭ ግጭቶች የሽያጭ ስራ አስኪያጅ ዳኝነት የመስጠት
መብት አለው

Page | 5
4.3. ከዚህ መመሪያ ያልተዳሰሰ ጉዳይ ሲጋጥም የሽያጭ መምሪያው እና የሽያጭ ስራ አስኪያጅ በጋር በመሆን ውሳኔ
ይሰጣሉ፡፡
4.4. በሚሰጡ ውሳኔዎች ላይ ቅሬታ ያለው ማንኛውም አካል ቅሬታውን ለሽያጭ መምሪያ በማመልከቻ በድጋሚ
እንዲታይለት ማቅረብ ይችላል፡፡ ይህም ውሳኔ የመጨረሻው ውሳኔ ይሆናል፡፡
4.5. የሽያጭ ግጭቶች በሚፈጠሩ ጊዜ ውሳኔ የሚሰጠው በተቀመጠው የሪፖርት አቀራረብ መመሪያ መሰረት ብቻ
ሲሆን በማንኛውም ሁኔታ ደንበኛው ጋር መደወል ግጭቱን በተመለከተ ደንበኛው ጋር መነጋገር ምስክርነት
መጠየቅ በፍፁም ክልክል ነው፡፡
4.6. እንደ አስፈላጊነቱ በመመሪያው መሰረት ባደረገ መልኩ የሽያጭ ግጭቶችን የሚፈታ በሽያጭ መምሪያው ቢሮ ስር
ሶስት አባላት ያሉት ኮሚቴ ይቋቋማል፡፡

አንቀጽ 5
1. የማህበራዊ ትስስር ድህረ ገጽ ማስታወቂያ ሥራ መምርያ

ይህ የማህበራዊ ትስስር ድረ-ገጽ ማስታወቂያ ስራ (Social Media Promotion) መመሪያ የተዘጋጀው ከአልሳም
ፕሮፐርቲስ ጋር የሽያጭ ስራ የሚሰሩ አካላት የአልሳም ፕሮፐርቲስ ንብረቶችን በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ድረ-ገጾች ላይ
ሲያስተዋወቁ ሊከተሉዋቸው የሚገቡ ህጎችን ለማሳወቅ ነው።

2. የማህበራዊ ትስስር ገጾች

ማህበራዊ ትስስር ድረ-ገጽ ሰዎች የሚገናኙበት የኦንላይን መድረክ ሲሆን የተለያዩ ግለሰቦችና ድርጅቶች ምርትና
አገልግሎታቸውን ያስተዋውቁበታል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እነዚህ የማህበራዊ ትስስር ድህረ ገጾች ለማስታወቂያ ምቹ እና
ለመገበያየት ተመራጭ እየሆኑ መተዋል።

አልሳም ፕሮፐርቲስ በፌስቡክ፣ በኢንስታግራም፣ ቴሌግራም እንዲሁም በዩቲዩብ ምርቶቹን ያስተዋውቃል። የቤት
ዲዛይኖችን በምስል እና በተንቀሳቃሽ ምስል በእነዚሁ በማህበራዊ ትስስር ድረ-ገጽ ላይ ይለቃል።

ከአልሳም ፕሮፐርቲስ ጋር አብረው የሚሰሩ የሽያጭ ቢሮዎች እና የሽያጭ ባለሙያዎች በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ድረ-
ገጾች ላይ ምርቶቹን እንዲያስተዋውቁ ይፈቅዳል።

3.አልሳም ፕሮፐርቲስ እና የማህበራዊ ትስስር ገጾችን አጠቃቀም የተመለከቱ መመሪያዎች

3.1. የማህበራዊ ትስስር ገጽ ስያሜ

Page | 6
 አልሳም ፕሮፐርቲስ የሚለው ስያሜ ድርጅቱ በመንግስት እውቅና አግኝቶ የተሰጠው ህጋዊ የንግድ ስያሜ
ሲሆን ይህንን ስም ከድርጅቱ በስተቀር እንደ ማህበራዊ ትስስር ድህረገጽ ስያሜ አድርጎ መጠቀም በጥብቅ
የተከለከለ ነው።
 በአልሳም ፕሮፐርቲስ ስር የሚሰሩ የሽያጭ ባለሙያዎች ስማቸውንና አልሳም ፕሮፐርቲስ ውስጥ በሽያጭ
ባለሙያነት እንደሚሰሩ የሚያሳይ የማህበራዊ ትስስር ድረ-ገጽ ስያሜ የመጠቀም መብት አላቸው። ይህም
የሚሆነው ስማቸውን አስቀድመው የድርጅቱን ስም በማስከተል ነው። ነገር ግን የማህበራዊ ትስስር ድህረ ገጽ
ስያሜ የድርጅቱን ስም በማስቀደም መክፈት በጥብቅ የተከለከለ ነው።
 ከአልሳም ፕሮፐርቲስ ጋር አብረው የሚሰሩ የሽያጭ ቢሮዎች የድርጅቱን ስም የማህበራዊ ትስስር ድረ-ገጽ
ስያሜ አድርገው መጠቀም አይችሉም።

3.1.1. መሆን ያለባቸው እና የሌለባቸው የስያሜ አጠቃቀም ምሳሌዎች

✔ Jane Doe, Sales Consultant

✔ Jane Doe, Sales Officer

✘ AL-SAM Properties Sales Office

✘ AL-SAM Real Estate Sales Office

✘ AL-SAM Properties, Jane Doe

✘ AL-SAM Sales & Marketing

✘ AL-SAM Apartments

✘ AL-SAM Commercial Buildings

3.2. የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ የሚለጠፉ የፕሮፋይል እና ከቨር ምስሎች

በአልሳም ፕሮፐርቲስ ስር የሚሰሩ የሽያጭ ባለሙያዎች እንዲሁም ከድርጅቱ ጋር አብረው የሚሰሩ የሽያጭ ቢሮዎች
የማህበራዊ ትስስር ድረ-ገጾቻቸው ላይ የአልሳም ፕሮፐርቲስ አርማ ወይም ሎጎ እንዲሁም አልሳም ፕሮፐርቲስ
የሚያጋራቸውን የቤት ወይም የህንጻ ሞዴሎች እና ፎቶዎችን ፕሮፋይል ምስል እና ከቨር ምስል አድርገው መጠቀም
አይችሉም።ይህንን አድርገው ቢገኙ ግን ድርጅቱ ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል።

3.3. የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ የሚለጠፉ ግራፊክሶች እና የድርጅቱ ስራዎች

Page | 7
አልሳም ፕሮፐርቲስ በተለያዩ ጊዜያት ለሽያጭ ቀርበው የነበሩ ቤቶች/ህንጻዎች፣ በአሁን ላይ እየተሸጡ ያሉ
ቤቶች/ህንጻዎች እንዲሁም ወደፊት የሚሸጡ ቤቶች/ህንጻዎችን የሚገልጹ ሞዴሎችን የውጪ እና የውስጥ ዲዛይን ምስሎች
እና ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለሽያጭ ባለሙያዎቹ በቴሌግራም ግሩፕ ላይ እንዲሁም ለደንበኞቹ በሁሉም የድርጅቱ የማህበራዊ
ትስስር ድረ-ገጽ ላይ ይለቃል።

 በአልሳም ፕሮፐርቲስ ስር የሚሰሩ የሽያጭ ባለሙያዎች እንዲሁም ከድርጅቱ ጋር አብረው የሚሰሩ የሽያጭ
ቢሮዎች እነዚህን ምስሎች እና ተንቀሳቃሽ ምስሎች ለማስታወቂያነት ሲጠቀሙ፤ ምስሎቹ የአልሳም ፕሮፐርቲስ
ንብረቶች እንደሆኑ የሚገልጽ ጸሁፍ የመጠቀም ግዴታ አለባቸው።
 በምስሎቹ ላይ የአልሳም ፕሮፐርቲስን ሎጎ እንዲሁም አልሳም ፕሮፐርቲስ የሚል ጸሁፍ ወተር ማርክ
(watermark) ማድረግ
 የምስሉን ገላጭ ጸሁፍ የሚጽፉበት ቦታ (caption)ላይ የአልሳም ፕሮፐርቲስ ንብረቶች መሆናቸውን ማሳወቅ
አለባቸው።
 በማንኛቸውም በማህበራዊ ትስስር ድረ-ገጾች ላይ የሚለጠፉ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ላይም እንዲሁ የአልሳም
ፕሮፐርቲስ ሎጎ እና ስያሜ መግባት አለበት። ተንቀሳቃሽ ምስሉ የገባበት ፖስት መግለጫ (caption)
ላይምየአልሳም ፕሮፐርቲስ ስም መጠቀስ ይኖርበታል።
ይህንን ሳያደርጉ ቢገኙ ግን አልሳም ፕሮፐርቲስ የቅጂ መብት (Copyright)፣ የአዕምሮአዊ ንብረት መብት(Intellectual
Property Right) እንዲሁም የፈጠራ ባለቤትነት መብቱን(Patent Right)የማስከበር ተግባሩን በህጋዊ መንገድይወጣል።
ከእነዚህ አካላት ጋር ያለውን ውል ለማቋረጥም ይገደዳል።

3.4. ጠቅላላ መመሪያዎች

 ድርጅቱ የሚያስተዋውቅበትን የቴሌቪዥን እንዲሁም የሬዲዮ ማስታወቂያዎችን መጠቀም በጥብቅ የተከለከለ


ነው።
 የድርጅቱን ቤቶች ለማስተዋወቅ የአልሳም ፕሮፐርቲስ የሽያጭ ባለሙያው በከፈተው የማህበራዊ ድረ-ገጽ ላይ
ከአልሳም ፕሮፐርቲስ ውጪ የሌላ ሪል ስቴትም ሆነ ፖለቲካዊ እንዲሁም ሌሎች ይዘት ያላቸውን ነገሮች
ማስተዋወቅ አይችልም።
 ወቅታዊ የሆኑ በድርጅቱ የሚሰጡ መረጃዎችን ማክበር እና ማሻሻል (update)ማድረግ ይኖርበታል።
 ማንኛውም ማስታወቂያ የድርጅቱን በጎ ስም እና ብራንድ የሚጠብቅ መሆን አለበት።
3.5. የሃሰት መረጃ

አልሳም ፕሮፐርቲስ በተለያዩ ጊዜያት ስለሚሸጡት ቤቶች የሽያጭ ባለሙያዎች እና ከድርጅቱ ጋር አብረው ለሚሰሩ የሽያጭ
ቢሮዎች ትክክለኛ መረጃ እና ስልጠና ይሰጣል። በየጊዜውም የዋጋ ዝርዝሮችን በቴሌግራም ግሩፖች ላይ ያሳውቃል። ሆኖም
ግን ከእነዚህ መረጃዎች ውጪ የተሳሳቱ መረጃዎችን በማህበራዊ ትስስር ድህረገጽ ላይ መስጠት በጥብቅ የተከለከለ ነው። ይህ
ተግባር የድርጅቱን ስም የሚያጎድፍ በመሆኑ ውሉን ሊያቋረጥ ይገደዳል።

Page | 8
አንቀጽ 6
5.1. ይህ የደንበኛ ዝርዝር ሪፖርት አቀራረብ እና የሽያጭ ግጭት አፈታት መመሪያ ከጥቅምት 1 ቀን 2016 ዓ.ም
ተፈፃማ ይሆናል፡፡
5.2. ከዚህ በፊት ስራ ላይ የነበረው የግጭት አፈታት መመሪያ ተሽሯል፡፡

መመሪያውን ተወያይቶ ያፀደቀው የስራ ክፍል አባላት


ስም ስም

መመሪያውን የተወያዩበት አባላት


ስም

ስም

ስም

አልሳም ፕሮፐርቲስ

Page | 9

You might also like