Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 3

ክፍል አንድ

1. የፍርድ ቤት ሥልጣን
• በኢፌዴሪ ህገመንግስት አንቀጽ 79 (1) ላይ በግልጽ እንደተደነገገው በፌድራልም ሆነ በክልል የዳኝነት ሥልጣን
የፍርድ ቤቶች ነው፡፡
ይህ ማለት ግን ፍ/ቤቶች የሚቀርቡላቸውን ሁሉንም ጉዳዮች በማየት ውሳኔ ይሰጣሉ ማለት እንዳልሆነ ከዚሁ
ህገመንግስት አንቀጽ 37 )1) ምንምባብ መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
• በዚሁ ድንጋጌ መሰረት ፍ/ቤት ለመዳኘት ሥልጣን የሚኖረው ጉዳዩ በፍ/ቤት ሊወሰን የሚገባው ጉዳይ ሲሆን ብቻ
ነው፡፡ በመሆኑም ፍ/ቤቶች የሚቀርቡላቸውን ጉዳዮች ተመልክተው ከመወሰናቸው በፊት በቅድሚያ ጉዳዩ በፍ/ቤት
ታይቶ ውሳኔ ለማግኘት የሚገባው ጉዳይ መሆን አለመሆኑን መለየት ያስፈልጋቸዋል፡፡
• ለዳኝነት የቀረበው ጉዳይ በፍ/ቤት ሊወሰን የሚገባው ሆኖ ከተገኘ ቀጣዩ ፍ/ቤቶች ሊያጤኑት የሚገባው ነገር ይህንኑ
ጉዳይ ለመዳኘት ስልጣን ያላቸው መሆን አለመሆኑን መመርመር ይኖርባቸዋል፡፡
• ማንኛውም ፍ/ቤት አንድን ጉዳይ ተመልክቶ ዳኝነት ለመስጠት በህግ ስልጣን የተሰጠው ሊሆን ይገባል፡፡ የፍ/ቤት
ስልጣን ማለት አንድን ጉዳይ ሰምቶ ውሳኔ የመስጠትችሎታ ማለት ነው፡፡ ከላይ እንደተገለጸዉ፡፡
• የአንድ ፍ/ቤት ስልጣን በሶስት ክፍሎች የሚከፈል ሲሆን፣ እነዚህም፡ የብሄራዊ፣ የስረ ነገርና የአካባቢ የስልጣን
አይነቶች ናቸው፡፡
1.1 የቤሄራዊ የዳኝነት ስልጣን
• ብሄራዊ የዳኝነት ስልጣን ማለት የአንድ ሀገር ፍርድ ቤት አንድን ጉዳይ ሰምቶ ውሳኔ የመስጠት ችሎታ አለው? ወይስ
የለውም? የሚለውን የሚመልስ የስልጣን አይነት ነው፡፡
• የፍትሕብሔር ሥነ-ሥርዓት ህጋችን ይህንን አይነቱን የፍ/ቤት የዳኝነት ሥልጣንን በተመለከተ የደነገገው ነገር የለም፡፡
በመሆኑም ፍ/ቤቶች በተለይም የቤሄራዊ የዳኝነት ስልጣን የሚያስነሱ ጉዳዮች ምን አይነት ሁኔታዎች ናቸው፣ ይህንን
ሥልጣ መሰረት በማድረግ በተከራካሪ ወገኖች መቃወሚያ መቼ ሊነሳ ይገባል፣ መቃወሚያ ሳይቀርብ ውሳኔ ቢሰጥስ
የውሳኔው እጣ ፋንታ ምን ይሆናል የሚሉትና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች በአግባቡ ለመመለስ ችግር ሲፈጥርባቸው
ይስተዋላል፡፡
• አንድ ጉዳይ ለዳኝነት የቀረበለት የአንድ ሀገር ፍ/ቤት የብሄራዊ የዳኝነት ስልጣን የሚኖረው ከተከሳሹ ወይም የክርክሩ
ምክኒያት የሆነው ነገር ከተፈጸመበት ወይም የክርክሩ መነሻ የሆነው ንብረት የሚገኝበት ሀገር ጋር በቂ ግንኙነት ያለው
ሲሆን ወይም የተከራካሪ ወገኖች በአንድ ሀገር ፍ/ቤት ለመዳኘት ስምምነት ያደረጉ እንደሆነ ነው፡፡ እነዚህን አገናኝ
ምክኒያቶች መሰረት በማድረግ አንድ ሀገር የብሄራዊ የዳኝነት ስልጣን ይኖረዋል ማለት ሌላ ሀገር በዚያው ጉዳይ ይሄው
የዳኝነት ስልጣን አይኖረውም ማለት አይደለም፡፡
• የብሔራዊ የዳኝነት ስልጣ ክርክር የሚነሳውም የብሄራዊ የዳኝነት ስልጣን ላለው የአንድ ሀገር ፍ/ቤት የቀረበው ጉዳይ
ጉዳዩ ከቀረበለት ሀገር ፍ/ቤት በተጨማሪ የሌላ ሀገር/›ሀገራት ፍ/ቤት ለማየትና ውሳኔ ለመስጠት ስልጣን ሲኖረው ነው፡፡
እዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ የኢትዮጵያ ፍ/ቤቶች ብሄራዊ የዳኝነት ስልጣን ባላቸው አንድ ጉዳይ ላይ ተመሳሳይ ስልጣን
ያለው የሌላ ሐገር ፍ/ቤት ውሳኔ የሰጠበት ቢሆንና ይህንኑ ውሳኔ ወደ ጎን በማለት ከተከራካሪዎቹ አንዱ እንደአዲስ
በኢትዮጵያ ፍ/ቤት ክስ ቢያቀርብ፣ ሌላው ተከራካሪ ቀደም ሲል በሌላ ሀገር ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሳኔ በመጥቀስ
መቃወሚያውን ቢያቀርብ መቃወሚያ የቀረበለት ፍ/ቤት ምን ሊወስን ይችላል? የሚለው ነው፡፡
• ከዚህ አንጻር በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2 መሰረት በውሳኔዎቹ የሚሰጠው የህግ ትርጉም የአስገዳጅነት ውጤት
እንዲኖረው ስልጣን የተሰጠው የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በዚህ ጉዳይ ላይ በቅጽ 12 በሰ/መ/ቁ/
54632 እና በሰ/መ/ቁ/”59953 የሰጣቸውን ተቀራራቢነት ያላቸውን ሁለት ውሳኔዎች መመልከት ይቻላል፡፡ በነዚህ
ውሳኔዎችም ላይ እንደተመለከተው አንድ በውጪ ሀገር ባለ ፍ/ቤት
• የተሰጠን ውሳኔ በአንቀጽ 5 መሰረት በፍርድ ማለቅ መርህን በመጥቀስ መቃወሚያ ሲቀርብ በፍትሃ ብሄር ስነ ስርዐት
ህግ
ከአንቀጽ 456 እስከ 461 የተደነገጉት ድንጋጌዎች በሚያሳዩት መልኩ በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ተቀባይነትን ሊያገኝ
የሚችልበትን ሁኔታ በግልፅ መሟላቱ በመጀመሪያ መረጋገጥ ይኖርበታል በሚል ውሳኔ የሰጠ በመሆኑ በዚህ አይነት
ጉዳዮች ላይ በዚሁ አግባብ መስራት የሚያስፈልግ ይሆናል፡፡
• አንድ ጉዳይ የቀረበለት ፍ/ቤት ጉዳዩን አይቶ ውሳኔ ለመስጠት ምንም አይነት የብሄራዊ የዳኝነት ስልጣን የሌለው
መሆኑን የተረዳ እንደሆነ ፍ/ቤቱ በፍስስህ ቁጥር 231 መሰረት መዝገቡን መዝጋት ይኖርበታል፡፡ ይሁንና ፍ/ቤቱ ስልጣ
የሌለው መሆኑንባለመረዳት ወይም በሌላ በማንኛውም ምክኒያት መዝገቡን ያልዘጋ እንደሆነ ተከሳሹ በሚያቀርበው
የጽሁፍ መልስ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በማቅረብ ፍ/ቤቱ መዝገቡን እንዲዘጋለት ለማድረግ ይችላል፡፡ ነገር ግን
ተከሳሹ ቀርቦ ምንም አይነት መቃወሚያ ያላቀረበ እንደሆነ ጉዳዩ አንዲታይና ውሳኔ እንዲሰጥበት በተዘዋዋሪ የተስማማ
እንደሆነ ተቆጥሮ ፍ/ቤቱ የሚሰጠው ውሳኔ በተከራካሪዎች ላይ አስገዳጅነት ይኖረዋል፡፡
የመወያያ ጥያቄ
• የብሄራዊ የዳኝነት ስልጣን የሌለው ፍ/ቤት የላከለትን መጥሪያ ባለመቀበል ፍ/ቤት ያልቀረበ ተከሳሽ ላይ ፍ/ቤቱ
የሚሰጠው ውሳኔ አስገዳጅነት እንዴት ይታያል?
1.2 የፍ/ቤት የግዛት ክልል ስልጣን
• ሌላውና ሁለተኛው አይነት የፍ/ቤት የዳኝነት ስልጣን የፍ/ቤት የግዛት ክልል ስልጣን ነው፡፡ የፍ/ቤት የግዛት ነገር
ስልጣን
በፍትሕብሔር ሥነ-ሥርዓት ህጋችን ከአንቀጽ 19-30 ባሉት ድንጋጌዎች ተደንግጎ ይገኛል፡፡
• ይህ አይነቱ የፍ/ቤት የዳኝነት ሥልጣን አንድን ጉዳይ ተመልክቶ ውሳኔ ለመስጠት የስረ-ነገር ሥልጣን ካላቸው ፍ/ቤቶች
መካከል በየትኛው ፍ/ቤት ሊታይ እንደሚገባ የሚወስን የዳኝነት ሥልጣ አይነት ነው፡፡ የዚህም የዳኝነት ሥልጣ
አስፈላጊነት፣ ሌሎች ሁኔታዎች እንዳሉ ሆኖ፣ በመርህ ደረጃ ለተከራካሪ ወገኖች በተለይም ለተከሳሹ ማስረጃውን
ለማቅረብና ክርክሩንም በተመቼ ሁኔታ ለማከናወን እንዲያስችለው ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡
• በመርህ ደረጃ የፍ/ቤቶች የግዛት ክልል ስልጣን በፍትሃ ብሄር ስነስርዓት ህጋችን አንቀጽ 19 (1) እና (2) ላይ በግልጽ
የተደነገገ ሲሆን በዚህም መሰረት በህግ በሌላ መልኩ እስካልተደነገገ ድረስ ማናቸውም ክስ መቅረብ የሚገባው ተከሳሹ
ወይም ተከሳሾቹ ከአንድ በላይ በሚሆኑ ጊዜ ከተከሳሾቹ አንዱ በሚኖርበት ወይም ለግል ጥቅሙ በሚሰራበት ክፍል
በሚያስችለው ባለስልጣን ፍ/ቤት ነው፡፡
ከዚህ ድንጋጌ አቀራረጽ ለመረዳት እንደሚቻለው ሥነሥርዓት ህጋችን የግዛት ክልል ስልጣንን በመወሰን ረገድ ከላይ
ለማመልከት እንደተሞከረው በመርህ ደረጃ ተከሳሹን ማእከል ያደረገ መሆኑን ለመገንዘብ ይቻላል፡፡
• ይህም የሆነበት ምክኒያት የተለያየ ቢሆንም በዋናነት ግን
በአንድ በኩል ተከሳሹ የቀረበበትን ክስ ተገቢ የሚላቸውን
የሰውና የሰነድ ማስረጃ በማቅረብ በቀላሉ ለመከላከል
እንዲችል ሲሆን ሌላውና ዋናው ምክኒያት ሊሆን የሚችለው
ፍ/ቤቱ በቀረበው ክስ ላይ በተከሳሹ ላይ ፍርድ ቢሰጥ
ፍርዱን በቀላሉ ማስፈጸ እንዲቻል ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ
እንደሆነ ለመረዳት ይቻላል፡፡
• የመርሁ ልዩ ሁኔታዎች የክስ ምክኒያትን መነሻ በማድረግ ሊታዩ
የሚገባቸው በየትኛው ፍ/ቤት መሆን እንዳለበት በፍትሕብሔር ሥነሥርዓት
ህጉ አንቀጽ 20 እና ተከታዮቹ ተመልክተዋል፡፡ በመሆኑም
በልዩ ሁኔታ የተዘረዘሩትን ጉዳዮች ክሱን ለማየት በህጉ የግዛት ክልል
ሥልጣ ለተሰጠው ፍ/ቤት መቅረብ ያለበት መሆኑን እንዲሁም
ፍ/ቤቶች የቀረበላቸው በህጉ አግባብ መሆኑን የማረጋገጥ ሀላፊነት
ይኖርባቸዋል፡፡
• ይሁን እንጂ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 20 እና ተከታዩቹ ክሱ ተከሳሹ
ከሚኖርበት ወይም ለግል ጥቅሙ ከሚሰራበት ቦታ በተጨማሪ በሌላ
ቦታ ክስ ማቅረብ እንደሚቻል ተደንግጎ ከተገኘ (ቁጥር 24(1) እና 27)
ክሱ በከሳሹ ምርጫ ከሁለት በአንዱ ክስ የመመስረት መብት ያለው
መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡
የፍ/ቤቶች የግዛት ክልል ሥልጣን
• ሌላው እዚህ ጋር ሊነሳ የሚገባው ነጥብ በህጉ አንቀጽ 29 ላይ
የተመለከተው የልዩ ሁኔታዎቹ ልዩ ሁኔታ ነው፡፡
• በዚሁ ድንጋጌ እንደተመለከተው ከአንድ የክስ ምክኒያት በላይ የሆኑ
ክሶች ተጣምረው የሚቀርቡ እንደሆነና የክስ ምክኒያቶቹ ከአንድ በላይ
በሆኑ የፍ/ቤት የግዛት ሥልጣን ስር የሚወድቁ ከሆነ የአንዱን የክስ
ምክኒያት ለማየት በሚችለው ፍ/ቤት ቀርቦ ሊታይ የሚችል መሆኑን
ነው፡፡ ይህን በምሳሌ ለመግለጽ ያህል በተለያየ የፍ/ቤት የግዛት ሥልጣን
ስር የሚወድቁ የውልና ከውል ውጪ ሃላፊነት ክሶች ተጣምረው ቢቀርቡ
በህጉ አንቀጽ 24 ወይም 27 በተደነገገው በአንዱ የፍ/ቤት የግዛት ሥልጣ
መቅረብና መዳኘት የሚችሉበት አግባብ ነው፡

You might also like