Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 1

የውስጥ ለውስጥ ማስታወሻ- ብ/ባ/ኳ/አ/ዳ

ለ: ሥራ አስኪያጅ-ደብረ ብረሀን አካባቢ ጽ/ቤት

ከ: ዳይሬክተር ብራንች ባንኪንግ እና ኳሊቲ አሹራንስ ዳይሬክቶሬት

ቁጥር: ብባኳአ/ውማ//16

ቀን: ጥር 29 ቀን 2016 ዓ.ም

ጉዳዩ: - የታገደ ገንዘብን ይመለከታል

በቀን 23/05/2016 ዓ.ም በማስታወሻ ቁጥር BB/DAO/018/2016 በተፃፈ ማሳታወሻ የሬማ ቅርንጫፍ
ደንበኛ የሆነው አቶ አማን አባወይ ጥላሁን ሂሳብ ቁጥር 5799527000009 የሚንቀሳቀሰውን ሂሳብ
አካባቢውን የተቆጣጠረው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ዕሁድ በቀን 19/05/2016 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ
እንዳይንቀሳቀስ በማገዱ ቅርንጫፍ በትዕዛዙ መሰረት ያገደ ቢሆንም የሀገር መከላከያ ሰራዊቱ ከሰኞ
ጀምሮ አካባው ላይ ባለመኖሩ ምክንያት አካባቢውን የተቆጣጠረው ሀይል የታገደውን ገንዘብ በሀይል
ያስለቀቀ ሲሆን በቀን 20/5/2016 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ ከላይ ከላይ የተገለጠው ደንበኛ ሂሳብ
እንዳይንቀሳቀስ በድጋሚ ለአለም ከተማ ቅርንጫፍ ደብዳቤ ትዕዛዝ የሰጠ መሆንን በመግለፅ በሀይል
የተለቀቀው ገንዘብ ወደቦታው በመመለስ የተሰጠውን የእግድ ትዕዛዝ ተፈፃሚ የሚሆንበት መፍትሄ
እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡

በመሆኑምአካባቢውን የተቆጣጠረው ሀይል በሀይል እንዲለቀቅ ያደረገውን ገንዘብ ወደቦታው በመመለስ


የተሰጠውን የዕግድ ትዕዛዝ ተፈፃሚ እንዲደረግ ስንል በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

ከሰላምታ ጋር

BANK OF THE VISIONARIES! የባለራዕዮች ባንክ!

You might also like