Professional Documents
Culture Documents
Microsoft Excel Student Handout
Microsoft Excel Student Handout
Microsoft Excel Student Handout
1
ክፍለ ጊዜ 1፡ ትምህርት 1
የትምህርት 1 ርእሶች፡
Microsoft Word ን መክፈት
1. Excel ን መክፈት
2. በExcel ዊንዶው መስራት
3. ሪበን አጠቃቀም
4. የExcel ን እይታ መቀየር
5. የተሰራ ወርክቡክ ላይ መስራት
6. የExcel Help System አጠቃቀም
7. ወርክቡክ መፍጠር
8. ስፕሬድሺት ሴቭ ማድረግ
9. ሴል ሪፈረንስ መረዳት
10. በወርክሺት ውስጥ ውሂብ ማስገባት እና ማስተካከል
11. ወርክሺትን ለመሙላት የውሂብ አይነቶችን መጠቀም
የክፍለ ጊዜ ማስታወሻዎች፡
1. ከአንዱ ርዕስ ወደሌላ ያሉ ክህሎቶችን ለማከናወን
ፕረዘንቴሽኖችን ክፍት ያድርጉ፣ ካልታዘዙ በስተቀር አይዝጉ።
2. በሚታዘዙበት ጊዜ ሁሉ ሴቭ ያድርጉ።
2
Microsoft Excel ን መክፈት
1. በፍለጋ ሳጥኑ ውስጥ ጠቅ ያድርጉ እና “Excel” ብለው ይፃፉ እና Enter የሚለውን ጠቅ ያድርጉ።
2. Blank workbook የሚለውን ጠቅ ያድርጉ። (ባዶ ወርክቡክ በራስ ሰር ካልተከፈተ)
ወይም
1. Microsoft Excel 2016ን ለማስጀመር በዴስክቶፕ ወይም በታስክባር ላይ ባለው የExcel ምልክት ላይ ጠቅ ያድርጉ።
2. ባዶ ስፕሬድሺት ይከፈታል።
እያንዳንዱ አዲስ ወርክቡክ አንድ Sheet1 የተባለ ስፕሬድሺት አለው።
ተጨማሪ ስፕሬድሺቶችን በወርክቡክ ውስጥ እንዴት ማስገባት እንደሚችሉ ይማራሉ።
3
በExcel ዊንዶው መስራት
መቆጣጠሪያ ቁልፎች
Quick Access Toolbar የወርክቡኩ ስም
Minimize ( ) ቁልፍ ስፕሬድሺትዎን
በማያ ገጽዎ የታችኛው ክፍል ታስክባር
ሴቭ የአምዶች ርእስ ላይ በማስቀመጥ ከእይታ ለመደበቅ
ያገለግላል።
Restore Down ( ) ወይም Maximize
( ) ቁልፎች መስኮቱን ማንቀሳቀስ
ሪበን እንዲችሉ የመስኮትዎን መጠን ለመለወጥ
ያገለግላሉ።
Close ( ) ቁልፍ አሁን የተከፈተ
ስፕሬድሺትዎን ለመዝጋት ያገለግላል።
ምድብ ሥራዎን ከመዝጋትዎ በፊት ሴቭ
ማድረግዎን ያረጋግጡ፣ አለበለዚያ
ሁሉንም ሴቭ ያልተደረጉ ሥራዎችን
የረድፍ ርእስ የቀመር ያጣሉ።
ሴል ሳጥን(ባር)
ስፕሬድሺት ቦታ
የታብ ስም
ማንሸራተቻ
ስታተስ ባር ባር
4
ሪበን አጠቃቀም
ስፕሬድሺት ላይ በሚሰሩበት ጊዜ፣ ስፕሬድሺትዎ የሚታይበትን መንገድ መቀየር ይችላሉ። ይህን በማድረግ ገፁ የሚጀምርበትን እና
የሚኧልቅበትን ቦታ ማየት ይችላሉ እንዲሁም ስፕሬድሺትዎ በሚታተምበት ጊዜ ምን እንደሚመስል ማየት ይችላሉ።
1. Yearly Report የሚለውን ስፕሬድሺት ይክፈቱ።
2. ሪበኑ ላይ View ላይ ጠቅ ያድርጉ።
3. መደበኛ እይታ (Normal View)፡ ይህ የExcel ነባር እይታ ነው።
4. የገጽ ዕረፍት ቅድመ -እይታ (Page Break Preview): የቱ የስፕሬድሺት ክፍል በ1 ወረቀት ላይ ምን እንደሚታተም ለማየት ያገለግላል።
5. Page Layout View: በወረቀት ላይ ሲታተም እንደሚታየው ስፕሬድሺትዎን ያሳያል።
6. ለሚቀጥለው ርዕስ ይህንን ስራ ክፍት እንደሆነ ያቆዩ።
6
ቀድሞ የተከፈተ ስፕሬድሺትን ይክፈቱ
1. ማንኛውንም ሴቭ የተደረገ ወርክቡክ ለመክፈት፣ ባክስቴጅ እይታን ለመጠቀም
በFile ቁልፍ ላይ ጠቅ ያድርጉ።
2. Open የሚለው ላይ ጠቅ ያድርጉ።
3. ከዝርዝሩ ታች Browse ቁልፍ ላይ ጠቅ ያድርጉ።
4. Open ሳጥን ይከፈታል።
5. በData Files አቃፊ ውስጥ ያስሱ።
6. የExcel ሁሉንም የምንሰራባቸውን ፋይሎች ዝርዝር ለማየት በMicrosoft
Excel አቃፊ ላይ ሁለቴ ጠቅ ያድርጉ።
በዚህ ጊዜ ምንም ወርክቡክ አይክፈቱ።
7
Help እና Support
Microsoft Office በስፕሬድሺትዎ ላይ ሲሰሩ እርዳታ ከፈለጉ የሚያመለክቱበት አጠቃላይ Help and Support ላይብረሪ
ያቀርብልዎታል።
8
ወርክቡኮችን መፍጠር
1. File ከዚያ New ላይ ጠቅ ያድርጉ።
2. አዲስ ባዶ የወርክቡክ ለመፍጠር እንዲሁም የተለያዩ ቴምፕሌቶችን ለመጠቀም የሚያገለግል አዲስ ዊንዶው ይከፈታል።
3. Blank workbook የሚለውን ጠቅ ያድርጉ።
9
ስፕሬድሺት ሴቭ ማድረግ
Backstage View ስፕሬድሺትዎን ለማስቀመጥ ያገለግላል።
1. File ከዚያም Save As የሚለው ላይ ጠቅ ያድርጉ።
2. Browse የሚለው ላይ ጠቅ ያድርጉ።
3. Save As የሚለው ሳጥን ይከፈታል። ይህ ሳጥን የፋይሉን ስም እንዲሁም
ፋይሉ የሚቀመጥበትን ቦታ ለመለየት ይጠቅማል።
4. ወደሚቀጥለው ርእስ ከማለፋችን በፊት ወርክቡክዎን My Plannerብለው
ሴቭ ያድርጉ።
10
ሴል ሪፈረንስ መረዳት
• በስፕሬድ ሺት ውስጥ በሚሰሩበት ጊዜ ሴል ሪፈረንስ (Cell Reference) ማለት አምድ እና ረድፍዎ የሚገናኙበት ቦታ ነው።
• በምስሉ ውስጥ፣ Cell Reference የሚለው ፅሁፍ አምድ C፣ ረድፍ ቁጥር 3 ላይ ይገናኛል።
• Excel ውስጥ ይህ C3 ተብሎ ተቀምጧል።
• ይህ የሴል አድራሻ በስም ሳጥን (Name box) ውስጥ ይታያል።
1. ሴቭ ያደረጉት My Planner የሚል ስፕሬድ ሺት ክፍት መሆኑን እርግጠኛ ይሁኑ።
2. ሴል E10 ይምረጡ።
3. ሴል A3 ይምረጡ።
4. ሴል D8 ይምረጡ።
5. ወርክቡኩን ክፍት እንደሆነ ያቆዩ።
የስም ሳጥን
11
መሠረታዊ ውሂብ ማስገባት
ወደ ስፕሬድሺት ውሂብ በሚያስገቡበት ጊዜ ሴል ለመምረጥ የማውስዎን የግራ ቁልፍ ይጠቀሙ። እንዲሁም ስፕሬድሺትዎ ላይ ለመንቀሳቀስ
በኪቦርድዎ ላይ የቀስት ቁልፎችን ወይም tab መጠቀም ይችላሉ። በሴል ውስጥ ከፃፉ በኋላ Enter የሚለውን ይጫኑ።
1. የሚቀጥለውን ውሂብ ያስገቡ።
B1 ውስጥ ያለው ጽሑፍ፣ ብዙ ቁርስ መብላት ለሴሉ በጣም ረጅም ነው እና በአምድ C ላይ ተደርቧል።
2. ይህንን ለማስተካከል ማውስዎን በ B እና C አምድ ርዕሶች መካከል ወዳለው መስመር ይውሰዱት እና ባለ 2 ራስ ጥቁር ቀስት ሲያዩ ሁለቴ
ጠቅ የድርጉ።
ይሄ የአምዱ መጠን በራሱ እንዲስተካከል ያደርገዋል። ጽሑፉ በአምዱ ውስጥ እንዲገባ Excel ዓምዱን ያስተካክላል።
13
የውሂብ አይነቶችን መጠቀም
በExcel ውስጥ፣ በስፕሬድሺት ውስጥ ውሂብን የሚያዩበት መንገድ፣ እና Excel ውሂቡን የሚተረጉምበት መንገድ ሁል ጊዜ አንድ አይደለም።
ለምሳሌ፣ ወጭዎችን ለመመዝገብ ስፕሬድሺት እየፈጠሩ ከሆነ፣ Excel የወጪ ዋጋዎችን እንደ ምንዛሬ ሳይሆን እንደ ቁጥር ይተረጉመዋል።
14
የውሂብ አይነቶችን መጠቀም
1. Staff Wages የሚለውን ወርክቡክ ይክፈቱ።
2. ሴል A3 ይምረጡ።
15
ክፍለ ጊዜ 1፡ ትምህርት 2
የትምህርት 2 ርእሶች፡
Microsoft Word ን መክፈት
1. ውሂብን መቁረጥ፣ መቅዳት እና ፔስት ማድረግ
2. የወርክቡክ ባህሪዎችን ማስተካከል
3. የሚታተመውን ቦታ ማስተካከል
4. እያንዳንዱን ወርክሺት በተናጠል ማተም
5. የህትመት ልኬት ማስተካከል
6. ወርክቡኮችን ለህትመት ማዋቀር
7. Quick Access ቱልባር ማዋቀር
8. ሪበን ማዋቀር
9. ቴምፕሌቶችን በመጠቀም አዲስ ወርክቡክ መፍጠር
የክፍለ ጊዜ ማስታወሻዎች፡
1. ከአንዱ ርዕስ ወደሌላ ያሉ ክህሎቶችን ለማከናወን
ፕረዘንቴሽኖችን ክፍት ያድርጉ፣ ካልታዘዙ በስተቀር አይዝጉ።
2. በሚታዘዙበት ጊዜ ሁሉ ሴቭ ያድርጉ።
16
ፅሁፍ መቁረጥ
1. Cut and Copy የሚለውን ወርክቡክ ይክፈቱ።
2. የዚህን ስፕሬድሺት ከታች በስተግራ በኩል ይመልከቱ። ሁለት የተለያዩ ሺቶች አሉ፡ Original እና Paste።
3. ከA1 ወደ B6 ጠቅ በማድረግ እና በመጎተት A1: B6ን ይምረጡ ወይም የሺፍት ዘዴን ይጠቀሙ።
5. ፅሁፉን አንዴ ከቆረጡ በኋላ፣ ከስፕሬድሺቱ ይጠፋል። ይህ የሆነበት ምክንያት የተመረጠውን ጽሑፍ ከስፕሬድሺቱ ውስጥ ወስደው
በኮምፒተርዎ ማህደረ ትውስታ ውስጥ ስላስገቡ ነው።
17
ፅሁፍ ፔስት ማድረግ
1. ሺቱን ይምረጡ እና እሱ ላይ ጠቅ በማድረግ ፔስት ያድርጉ።
2. A1 ሴል መመረጡን ያረጋግጡ።
3. Home ታብ ውስጥ በClipboard ምድብ Paste የሚለው ቁልፍ ላይ ጠቅ ያድርጉ።
(ቃሉ ላይ ሳይሆን ምልክቱ ላይ ጠቅ ማድረግዎን ያረጋግጡ)።
4. ከዚህ በታች ምስሉ ላይ እንደሚታየው ጽሑፉ ከሴል A1 ጀምሮ ስፕሬድሺቱ ውስጥ ፔስት ይደረጋል።
18
ፅሁፍ መቅዳት
• ጽሑፍን ለመቅዳት እና ፔስት ለማድረግ የሚያገለግል ዘዴ ጽሑፍን ከመቁረጥ እና ፔስት ከማድረግ ጋር ተመሳሳይ ነው።
• የሚለወጠው ብቸኛው ነገር እርስዎ እየቀዱት ያለው ጽሑፍ ከስፕሬድሺትዎ ውስጥ አይጠፋም፣ ይልቁንም ቅጂ ወደ ኮምፒተርዎ
ማህደረ ትውስታ ውስጥ ይቀመጣል።
1. ወደ Original ሺት ይመለሱ።
2. A8:B13 የሚለውን ይምረጡ።
3. Home ታብ ውስጥ በClipboard ምድብ Copy የሚለው ቁልፍ ላይ ጠቅ ያድርጉ።
4. ወደ Paste ሺት ይቀይሩ።
5. ሴል E1 ይምረጡ።
6. Home ታብ ውስጥ በClipboard ምድብ Paste የሚለው ቁልፍ ላይ ጠቅ ያድርጉ።
7. በምስሉ ላይ እንደሚታየው ጽሑፍዎ ከሴል E1 ጀምሮ ወደ ስፕሬድሺትዎ ፔስት ይሆናል።
19
የወርክቡክ ባህሪያትን ማስተካከል
የስፕሬድሺት ባህሪዎች ስለ ወርክቡክ ለመግለጽ የሚረዳ መረጃ ነው። ምሳሌ፡ Author, Title, Subject
20
የሚታተመውን አካባቢ ማዘጋጀት
ወርክሺት በመደበኛነት በሚያትሙበት ጊዜ፣ የትኛውን ስፕሬድሺት ማተም እንደሚፈልጉ መግለፅ ይችላሉ።
1. Yearly Report የሚለውን ወርክቡክ ይክፈቱ።
2. A1:E4 የሴል ክልሉን ያድምቁ።
3. Page Layout, Print Area, Set Print Area የሚለው ላይ ጠቅ ያድርጉ።
4. File, Print ላይ ጠቅ ያድርጉ።
5. በቅድመ -እይታ መስኮት ውስጥ እርስዎ የመረጧቸው ሴሎች ብቻ ይታያሉ።
6. ለውጦችን ሴቭ ሳያደርጉ ወርክቡኩን ይዝጉ።
21
እያንዳንዱን ወርክሺት በተናጠል ማተም
ስፕሬድሺት በሚያትሙበት ጊዜ እያንዳንዱን ወርክሺት ወይም ሙሉውን ወርክቡክ የማተም አማራጭ አለዎት።
22
የህትመት ልኬት ማስተካከል
አንዳንድ ጊዜ ሺት በሚያትሙበት ጊዜ በ1 ገጽ ላይ ለመግባት በጣም ትልቅ ይሆናል። በሚያትሙበት ጊዜ በአንድ ወይም በብዙ ገጾች ላይ
ለማተም አንድ ሺት ለማስተካከል የህትመት ልኬትን (Print Scaling) መጠቀም ይችላሉ።
1. Flower Sales የሚለውን ወርክቡክ ይክፈቱ።
2. File, Print ላይ ጠቅ ያድርጉ። ይህ ስፕሬድሺት በአንድ ገጽ ላይ
የሚገቡ በጣም ብዙ ረድፎችን እና ዓምዶችን ይዟል።
3. አሁንም የህትመት ስክሪን ላይ ሆነው Scaling ዝርዝር ውስጥ ጠቅ
ያድርጉ እና Fit on One Page የሚለውን ይምረጡ።
4. የቅድመ እይታ መስኮትዎን በቀኝ በኩል ይመልከቱ። ጠቅላላው
ስፕሬድሺት በአንድ ገጽ ላይ እንዲገባ መጠኑ ተቀንሷል።
5. Print ላይ ጠቅ ያድርጉ።
6. ምንም አይነት ለውጦችን ሳያስቀምጡ ወርክቡኩን ይዝጉ።
23
ወርክቡኮችን ለህትመት ማዋቀር
በExcel ውስጥ፣ ወርክቡክ ከአንድ በላይ የውሂብ ሺት ከያዘ፣ ከዚያ Excel በማያ ገጽዎ ላይ የተከፈተውን ሺት ብቻ ያትማል።
24
የQuick Access Toolbar
Quick Access Toolbar በመስኮቱ በላይኛው ግራ ጥግ ላይ ይገኛል። በዚህ ቱልባር ላይ በመደበኛነት የሚጠቀሙባቸውን
ማንኛውም መሣሪያዎች ማከል ወይም ማስወገድ ይችላሉ።
መሳሪያ ማከል።
1. ወደ Formulas ታብ ይቀይሩ።
2. Show Formulas መሳሪያ ላይ የማውስዎን የቀኝ ቁልፍ ጠቅ ያድርጉ እና Add to Quick Access Toolbar
ይምረጡ።
መሳሪያ ማስወገድ
1. Show Formulas መሳሪያ ላይ የማውስዎን የቀኝ ቁልፍ ጠቅ ያድርጉ እና Remove From Quick Access
Toolbar የሚለውን ይምረጡ።
25
ሪበን ማዋቀር
Microsoft Excel ውስጥ መሣሪያዎችን በማከል ወይም በማስወገድ ሪባን ማበጀት ይችላሉ።
26
በቴምፕሌቶች መስራት
• ቴምፕሌት ከተለያዩ በቅድሚያ ከተዘጋጁ ቅንብሮች ጋር፣ ለምሳሌ የፅሁፍ መጠን እና የፅሁፍ ቀለም ጋር አብሮ የሚዘጋጅ ሰነድ ነው።
• ኮምፒተርዎ ከኢንተርኔት ጋር ከተገናኘ፣ የመስመር ላይ ቴምፕሌቶችን ማግኘት ይችላሉ።
27
ክፍለጊዜ 2: ትምህርት 3
የትምህርት 3 ርእሶች፡
Microsoft Word ን መክፈት
1. ቀመሮችን መረዳት እና ማሳየት
2. የአሰራሮችን ቅደም ተከተል መረዳት
3. መሠረታዊ ቀመሮችን መስራት
4. ቀመሮች ውስጥ ሴል ሪፈረንስ መጠቀም
5. ቀመሮችን በራስ እንዲሞላ ማድረግ
6. SUM አሰራር መተግበር
7. COUNT አሰራር መተግበር
8. AVERAGE አሰራር መተግበር
9. MIN እና MAX አሰራር መተግበር
የክፍለ ጊዜ ማስታወሻዎች፡
1. ከአንዱ ርዕስ ወደሌላ ያሉ ክህሎቶችን ለማከናወን ፕረዘንቴሽኖችን
ክፍት ያድርጉ፣ ካልታዘዙ በስተቀር አይዝጉ።
2. በሚታዘዙበት ጊዜ ሁሉ ሴቭ ያድርጉ።
28
ቀመሮችን መረዳት
በExcel ውስጥ አንድ ቀመር የተወሰኑ የሂሳብ ስሌቶችን ለማከናወን እና ውጤትን ለማግኘት ቁጥሮችን እና ሴል ሪፈረንሶችን የሚጠቀም
የሂሳብ መግለጫ ነው፣ ለምሳሌ የቁጥሮችን ቡድን በአንድ ላይ መደመር ለምሳሌ =A1+A2+A3
በሴል ወይም በቀመር ሳጥን ውስጥ ቀመር መፃፍ መሠረታዊ የExcel ቀመሮችን ለማስገባት በጣም ቀላሉ ዘዴ ነው። ብዙ ጊዜ ሂደቱ የእኩል
ይሆናል ምልክቶችን በመፃፍ ይጀምራል።
1. Basic Formulas የሚለውን ወርክቡክ ይክፈቱ።
2. ሴል E4 ላይ = ያስገቡ
3. A4 ላይ ጠቅ ያድርጉ፣ የመደመር ምልክት ይፃፉ።
4. B4 ላይ ጠቅ ያድርጉ፣ የመደመር ምልክት ይፃፉ።
5. C4 ላይ ጠቅ ያድርጉ እና Enter ጠቅ ያድርጉ።
29
ቀመሮችን ማሳየት
ቀመሮችን በሚያሳዩበት ጊዜ፣ ከቀመር መልስ ይልቅ ትክክለኛውን ቀመር ራሱን ማየት ይችላሉ።
1. በሴል ክልል B2:B5 ውስጥ፣ A2:A5 የሴል ክልል ውስጥ ለእያንዳንዱ ቁጥር 33 ቁጥርን
የሚጨምር መሠረታዊ ቀመር አለ።
2. Formulas ታብ ላይ ጠቅ ያድርጉ እና Formula Auditing ምድብ ውስጥ
Show Formulas ላይ ጠቅ ያድርጉ።
3. B2:B5 የሴሉን ክልል ይመልከቱ፣ እነዚህ ሴሎች አሁን ከመልሱ ይልቅ ቀመሩን ያሳያሉ።
4. በዚህ ስፕሬድሺት ቀመሩን ለመደበቅ Show Formula ቁልፍ ላይ በድጋሚ ጠቅ የድርጉ።
5. ወርክቡኩን My Formulas ብለው ሴቭ ያድርጉ።
30
የአሰራሮችን ቅደም ተከተል
Excel በሂሳብ ውስጥ የአሠራር ቅደም ተከተል ደንብ ላይ የተመሠረተ ቀመር መልሱን ያሰላል።
31
መሠረታዊ ቀመሮችን መስራት
መሠረታዊ ቀመር በቀመር ውስጥ መደመርን፣ መቀነስን፣ ማባዛት እና ማካፈል ሲሰሩ ነው።
32
ቀመሮች ውስጥ ሴል ሪፈረንስ መጠቀም
ቀመሮችን በሚጠቀሙበት ጊዜ ከቁጥር ይልቅ የሴል አድራሻን መጠቀም የተሻለ ነው። በዚህ መንገድ፣ በሴል አድራሻው ውስጥ ያለው
ቁጥር ከተለወጠ መልሱ በራስ -ሰር ይዘምናል።
1. Sales and Expenses የሚለውን ወርክቡክ ይክፈቱ።
2. ሴሉን ለማንቃት ሴል E4 ላይ ጠቅ የድርጉ።
3. የD4 ይዘት ከC4 ይቀንሱ። Excelውስጥ፣ =C4-D4 ተብሎ ተገልጿል።
4. ይህንን ቀመር ለማስገባት:
1. ኪቦርድዎ ላይ = ይጫኑ።
2. ሴል C4 ላይ ጠቅ ያድርጉ።
3. ኪቦርድ ላይ – ይጫኑ።
4. ሴል D4 ላይ ጠቅ ያድርጉ።
5. ኪቦርድ ላይ Enter ይጫኑ
5. ወርክቡኩን My Sales ብለው ሴቭ ያድርጉ።
33
ቀመሮችን በራስ እንዲሞላ ማድረግ
በቀድሞው ስላይድ ውስጥ የሴል ሪፈረንስን በመጠቀም ቀመር እንዴት እንደሚየስገቡ ተምረዋል። ቀጥሎ የምንማረው ቀመሮችን እንዴት
በራስ መሙላት (መቅዳት) እንደምንችል ነው።
1. ሴል E4 ላይ ጠቅ ያድርጉ (ያስገቡትን ቀመሮች የያዘ)
2. የዚህ ሴል የታችኛው ቀኝ ጥግ አንድ ትንሽ ካሬ ያመለክታል።
3. የማውስዎን ጠቋሚ በዚህ ካሬ ላይ ያንቀሳቅሱት እና ወደ መስቀል ይለወጣል። É
4. መስቀሉ በሚታይበት ጊዜ በካሬው ላይ ጠቅ ያድርጉ እና ማውስዎን ወደ E15 ይጎትቱ። ይህ ቀመሩን ከታች ይገለብጣል።
5. ወርክቡኩን ያዘምኑ (ሴቭ) ያድርጉ።
34
SUM አሰራር መተግበር
Functions በExcel ውስጥ ቀመሩን እራስዎ መፃፍ ሳያስፈልፍዎ በፍጥነት ቁጥሮች ማስገባት የሚያስችሉ ቀድመው የተሰሩ ቀመሮች
ናቸው። አንዳንድ ቀመሮች ከአንድ ሴል ይልቅ የሴል ክልል ይጠቀማሉ።
SUM የሴል ክልልን አንድ ላይ ለመደመር ያገለግላል። ምሳሌ፡ (5+5+5)= 15
1. My Sales የሚለው ወርክቡክ ክፍት መሆኑን ያረጋግጡ።
2. ሴል C16 የሚለውን ይምረጡ።
3. በC16 ውስጥ ያለውን ቁጥር ለማስላት ሁሉንም ቁጥሮች ከC4 እስከ C14 ያለውን ይደምሩ።
Excelውስጥ፣ ይህ =SUM(C4:C16) ተብሎ ይገለፃል።
4. ይህንን ቀመር ለማስገባት:
1. ኪቦርድዎ ላይ = ይጫኑ።
2. SUM( ብለው ይፃፉ
3. ከC4 እስከ C14 ጠቅ እድርገው ይጎትቱ።
4. ኪቦርድዎ ላይ ) ይጫኑ።
5. ኪቦርድ ላይ Enter ይጫኑ
5. ይህንን ቀመር በራስ-ሙላ ይሙሉ።
6. ወርክቡኩን ያዘምኑ (ሴቭ) ያድርጉ።
35
COUNT አሰራር መተግበር
COUNT በሴል ክልል ውስጥ ስንት ቁጥሮች እንደሆኑ ለመቁጠር ይጠቅማል። ምሳሌ፡ (5+5+5)= 3 ቁጥር
1. My Sales የሚለው ወርክቡክ ክፍት መሆኑን ያረጋግጡ።
2. ሴል B17 የሚለውን ይምረጡ።
3. =COUNT(B4:B14) የሚለውን ቀመር ያስገቡ እና enter
ይጫኑ።
4. Excel ከሴል ክልል B4 እስከ B14 ውስጥ ስንት ዓመት እንደሆነ
ይቆጥራል።
5. ወርክቡኩን ያዘምኑ (ሴቭ) ያድርጉ።
36
AVERAGE አሰራር መተግበር
AVERAGE ጥቅም ላይ የሚውለው ከሴል ክልል ውስጥ ያለውን አማካይ ለማስላት ነው። ምሳሌ፡ (5+5+5)/3=5
37
MIN Function መተግበር
MIN ከሴል ክልል ዝቅተኛው ቁጥር ያሳያል። ምሳሌ፡ (15, 13, 8, 25) = ዝቅተኛው ቁጥር 8 ነው።
38
MAX Function መተግበር
MAX በሴል ክልል ውስጥ ከፍተኛውን ቁጥር ያሳያል። ምሳሌ፡ (15, 13, 8, 25) = ከፍተኘው ቁጥር 25 ነው።
39
ክፍለጊዜ 2: ትምህርት 4
የትምህርት 4 ርእሶች፡
Microsoft Word ን መክፈት
1. ሴሎችን ማስገባት እና ማጥፋት
2. የሴል ይዘቶችን በእጅ ማስተካከል
3. የሴል ቅርፀቶችን በፎርማት ፔይንተር መቅዳት
4. የፔስት ልዩ ምርጫዎችን መረዳት
5. ሴሎችን በስታይልስ ማስተካከል
6. በሀይፐርሊንክድ ውሂብ መስራት
7. ሴሎች ላይ ሁኔታዊ ቅርፀት መተግበር
8. የሴል ቅርፀቶችን ማጥፋት
የክፍለ ጊዜ ማስታወሻዎች፡
1. ከአንዱ ርዕስ ወደሌላ ያሉ ክህሎቶችን ለማከናወን ፕረዘንቴሽኖችን
ክፍት ያድርጉ፣ ካልታዘዙ በስተቀር አይዝጉ።
2. በሚታዘዙበት ጊዜ ሁሉ ሴቭ ያድርጉ።
40
ሴሎችን ማስገባት
Excel ውስጥ 1 ወይም ከዚያ በላይ ሴሎችን ወደ ሴል ክልል ማስገባት ይችላሉ። ይህንን በሚያደርጉበት ጊዜ ነባሮቹ ሴሎች ወደ ላይ ወይም
ወደ ታች ይንቀሳቀሳሉ።
1. Flower Sales የሚለውን ወርክቡክ ይክፈቱ።
2. የሴል ክልል B4:C10 ያድምቁ።
3. Home ታብ ላይ Insert፣ Insert Cells ላይ ጠቅ ያድርጉ።
4. Insert ሳጥን ይከፈታል። የShift ሴሎች የቀኝ አማራጭ ተመርጧል። OK ላይ ጠቅ ያድርጉ ይህ በሴል ክልል B4:I10
ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ሴሎች ወደ ፊት ያንቀሳቅሳል።
42
የሴል ይዘቶችን በእጅ ማስተካከል
በExcel ውስጥ፣ ቅርጸት የሚለው ቃል በስፕሬድሺትዎ ውስጥ አንድ ነገር የሚታይበትን መንገድ መለወጥ ማለት ነው። ምሳሌ፡ የፅሁፍ
መጠን፣ ቀለም
43
ፎርማት ፔይንተር መጠቀም
ፎርማት ፔይንተር በአንድ የጽሑፍ ክፍል ላይ የተተገበሩትን ሁሉንም የቅርፀት ቅንብሮችን ለመቅዳት እና ሁሉንም ቅንብሮች በሰነድዎ
ውስጥ በሌላ ጽሑፍ ላይ ፔስት ለማድረግ ያገለግላል።
1. Formatting የሚለውን ወርክቡክ ይክፈቱ።
2. A1 ሴል መመረጡን ያረጋግጡ።
የሴል A1 ቅርጸት ለመቅዳት
3. Home ታብ ሪበን ውስጥ Clipboard ምድብ ላይ Format Painter ላይ ጠቅ ያድርጉ።
4. A3:A10 ሴል ክልል ይምረጡ።
5. በ A1 ውስጥ ያለው ቅርጸት በተመረጠው ክልል ላይ ይተገበራል።
6. ወርክቡኩን My Painter ብለው ሴቭ ያድርጉ እና ይዝጉ።
44
የፔስት ልዩ ምርጫዎችን መረዳት
አንድን ይዘት ወደ ስፕሬድሺትዎ ፔስት ሲያደርጉ፣ ይዘቱ እንዴት ፔስት እንዲደረግ እንደሚፈልጉ መምረጥ ይችላሉ። ምሳሌ፡ ቁጥሮች፣
ቀመሮች፣ አገናኞች
46
በሀይፐርሊንክድ ውሂብ መስራት
በExcel ውስጥ፣ አሁን ባለው ስፕሬድሺት፣ ወይም የድር አድራሻ ወይም በስፕሬድሺትዎ ላይ ወዳለው ነባር ሴል hyperlink ማስገባት
ይችላሉ
1. Links የሚለውን ወርክቡክ ይክፈቱ።
2. B1 የሚለውን ይምረጡ።
3. ኪቦርድዎ ላይ = ይጫኑ።
4. Sales ሺት ላይ ጠቅ ያድርጉ።
5. D9 የሚለው ላይ ጠቅ ያድርጉ። Enter የሚለውን ይጫኑ።
6. በሁለቱ ሺቶች መካከል አገናኝ ይደረጋል። ከሽያጭ ሺት D9 ውስጥ የሆነ ነገር ቢቀየር የB3 ይዘቶች በራስ -ሰር ይለወጣሉ።
7. ወርክቡኩን ለሚቀጥለው ርእስ ክፍት እንዲሆን ያድርጉ።
47
ወደ ውጪ ሚዲያ አገናኝ
በExcel ውስጥ፣ አሁን ባለው ስፕሬድሺት፣ ወይም የድር አድራሻ ወይም በስፕሬድሺትዎ ላይ ወዳለው ነባር ሴል hyperlink ማስገባት
ይችላሉ።
1. A1 የሚለውን ይምረጡ።
2. Insert ታብ Link ቁልፍ ላይ ጠቅ ያድርጉ።
3. ወደ ታች ይውረዱ እና Movies ላይ ጠቅ ያድርጉ።
4. OK ላይ ጠቅ ያድርጉ።
5. ወርክቡክ ውስጥ Movies ለመክፈት አገናኙ ላይ ጠቅ ያድርጉ።
6. ወርክቡኩን My Links ብለው ሴቭ ያድርጉ።
48
ሁኔታዊ ቅርጸት
ሁኔታዊ ቅርጸት በመመዘኛዎች ላይ በመመርኮዝ ወደ ሴል ክልል ቅርጸት ሲተገበሩ ነው። ምሳሌ፡ ከ 5500 የሚበልጠው በቀይ ተለይቷል።
49
የሕዋስ ቅርጸት ማጥፋት
በስፕሬድሺት ውስጥ ሲሰሩ፣ በእሱ ላይ የተተገበረውን ሁሉንም ቅርጸት ማስወገድ አንዳንድ ጊዜ አስፈላጊ ነው።
1. More Formatting የሚለውን ወርክቡክ ይክፈቱ።
2. A3:F7 የሴል ክልሉን ያድምቁ።
3. Home ታብ ላይ Editing ምድብ ውስጥ Clear፣ Clear Formats ላይ ጠቅ ያድርጉ።
4. ወርክቡኩን My Clear ብለው ሴቭ ያድርጉ እና ይዝጉት።
50
ክፍለጊዜ 3፡ ትምህርት 5
የትምህርት 5 ርእሶች፡
Microsoft Word ን መክፈት
1. በአምድ እና ረድፍ መስራት
2. ገፅታዎችን መጠቀም
3. ሄደር እና ፉተር ማስገባት
4. ስፕሬድሺትን ለህትመት ማዘጋጀት
5. ወርክሺትን መቅዳት እና ቦታ መቀየር
6. የወርክሺትን ቅደም ተከተል ማስተካከል
7. የወርክሺት ታብ ቀለም መቀየር
8. ወርክሺት መደበቅ
9. አዲስ ወርክሺት ማስገባት
የክፍለ ጊዜ ማስታወሻዎች፡
1. ከአንዱ ርዕስ ወደሌላ ያሉ ክህሎቶችን ለማከናወን ፕረዘንቴሽኖችን ክፍት
ያድርጉ፣ ካልታዘዙ በስተቀር አይዝጉ።
2. በሚታዘዙበት ጊዜ ሁሉ ሴቭ ያድርጉ።
51
አምዶች ውስጥ መስራት
በExcel ውስጥ አሁን ባለው ስፕሬድሺት ውስጥ ረድፎችን እና ዓምዶችን ማስገባት እና መሰረዝ ይችላሉ።
52
ረድፍ ውስጥ መስራት
1. በረድፍ ርዕስ ላይ ጠቅ በማድረግ ረድፍ 6ን ይምረጡ።
2. Home ታብ ላይ Insert፣ Insert Sheet Row ላይ ጠቅ ያድርጉ።
3. ባዶ ረድፍ በ6ኛ ረድፍ ውስጥ ይገባል።
4. ረድፍ 3ን ይምረጡ።
5. Home ታብ ላይ Delete፣ Delete Sheet Rows የሚለው ላይ ጠቅ ያድርጉ።
6. ረድፍ 3 ይጠፋል።
7. ወርክቡኩን My Movies ብለው ሴቭ ያድርጉ እና ይዝጉት።
53
ገፅታን መጠቀም
አንድ ገጽታ በጠቅላላው ስፕሬድሺትዎ ላይ የሚተገበር የፅሁፎች፣ ቀለሞች ወዘተ ስብስብ ነው።
54
ሄደር ማስገባት
ሄደር እና ፉተር በእርስዎ ስፕሬድ ሺት የላይኛው እና የታችኛው ጠርዝ ላይ ይታያል እና ጽሑፍ፣ ትናንሽ ሥዕሎች እና አገናኞችን ሊይዝ
ይችላል።
1. Insert፣ Text፣ Header & Footer ላይ ጠቅ ያድርጉ።
2. ስፕሬድሺትዎ ወደ የገጽ አቀማመጥ (Page Layout) እይታ ይለወጣል፣ እና ጠቋሚዎ በገጹ አናት ላይ ወዳለው ራስጌ ሄደር
ይንቀሳቀሳል።
3. ሄድረ እና ፉተር ሁለቱም በ3 ክፍሎች ተከፍለዋል፣ ግራ፣ መሀከል እና ቀኝ Header & Footer Tools፣ Design ታብ
በእርስዎ ሪበን ላይ ይታያል።
4. በሄደሩ የመሀል ክፍል ላይ your name ይፃፉ።
5. ሪበኑ ላይ፣ Design ታብ ላይ Go to Footer ላይ ጠቅ ያድርጉ።
3. በቀኝ በኩል ባለው ክፍል፣ የአሁኑን ገጽ ቁጥር በሺቱ በቀኝ በኩል ለማስገባት Page Number ያስገቡ።
4. የHeader & Footer እይታን ለመዝጋት በመጀመሪያ በዋናው ስፕሬድሺትዎ ውስጥ አንድ ቦታ ላይ ጠቅ
ያድርጉ፤ እና View፣ Normal ላይ ጠቅ ያድርጉ።
5. በቀኝ በኩል ባለው የቅድመ-እይታ መስኮት ውስጥ ሁሉንም ለውጦች ለማየት File፣ Print ላይ ጠቅ ያድርጉ።
6. ወርክቡኩን My Header ብለው ሴቭ ያድርጉ እና ይዝጉት።
56
ስፕሬድሺት ማስተካከል
የስፕሬድሺት አዘጋጅተው ከጨረሱ በኋላ መጀመሪያ የስፕሬድሺትዎ ውሂብ ትክክል መሆኑን ማረጋገጥ አለብዎት፣ ከዚያ ከማተምዎ በፊት
የፊደል ስህተቶች አለመኖራቸውን ያረጋግጡ። (የህትመት ዘዴዎች ከዚህ በፊት ባሉት ርዕሶች ተሸፍነዋል)
57
ወርክሺትን መቅዳት እና ቦታ መቀየር
በExcel ውስጥ ሳጥን በመጠቀም ነባር ወርክሺት ወደ ሌላ ወርክቡክ መገልበጥ ወይም ማንቀሳቀስ ይችላሉ።
59
የወርክሺትን ቅደም ተከተል ማስተካከል
• ከዚህ በፊት በነበረው ርዕስ ውስጥ የ 2025ን ሺት በMy Spelling ወርክቡክ ውስጥ ቀድተው ወደ Yearly Sales ወርክቡክ ፔስት
አድርገዋል።
• ይህ አዲስ ሺት በተሳሳተ ቦታ ላይ ነው፣ ከሁሉም ሺቶች መጨረሻ መወሰድ አለበት።
60
የወርክሺት ታብ ቀለም መቀየር
ለማንበብ ቀላል እንዲሆኑ ለማድረግ በማያ ገጹ ታችኛው ክፍል ላይ የሺት ታቦች ላይ ቀለም ማድረግ ይችላሉ።
61
ወርክሺቶችን መደበቅ
በExcel ውስጥ ሌሎች ሰዎች እንዲያዩ የማይፈልጉትን ወርክሺት መደበቅ ይችላሉ።
ሺት እንዲታይ ማድረግ፡
1. Format፣ Hide & Unhide፣ Unhide Sheet ላይ ጠቅ ያድርጉ።
2. Unhide ሳጥን ይከፈታል። ሺትዎ እንዲታይ ለማድረግ OK በሚለው ላይ ጠቅ ያድርጉ።
ማስታወሻ፡ እንዲሁም አንድን ሺት ለመደበቅ እና ለማሳየት የማውስዎን የቀኝ ቁልፍ ጠቅ የማድረግ ዘዴን
መጠቀም ይችላሉ።
3. ወርክቡኩን ያዘምኑ (ሴቭ) ያድርጉ። ለሚቀጥለው ርዕስ ስራውን ክፍት ያድርጉት።
62
አዲስ ወርክሺት ማስገባት
በExcel ውስጥ፣ አሁን ባለው ወርክ ቡክ ውስጥ ባዶ ሺት ማስገባት ይችላሉ። ይህንን በማድረግ አንድን የተወሳሰበ ስፕሬድሺት ሽያጮች
በአንድ ሺት ላይ እንዲመዘገቡ እና ወጪዎች በሌላ ላይ እንዲመዘገቡ መከፋፈል ይችላሉ።
63
ክፍለጊዜ 3፡ ትምህርት 6
የትምህርት 6 ርእሶች፡
Microsoft Word ን መክፈት
1. አጉሊ መጠቀም
2. ፓን እንዳይንቀሳቀስ(እንዳይቀየር) ማድረግ
3. ወርክቡክ ውስጥ ውሂብ መፈለግ
4. ውሂብ መገለግ እና መተካት
5. Go To መጠቀም
6. አስፈላጊ ውሂብ
7. የውሂብዎን መጠበቅ ያረጋግጡ
8. ውሂብ (Sort) ማስተካከል
9. ውሂብ ማጥራት (Filter)
10. ረቂቅ እና ንዑስ ድምር ውሂብ
11. ውሂብን በሠንጠረዥ መልክ ማስቀመጥ
12. አንድን ስራ እንደ ማክሮስ ማስቀመጥ
የክፍለ ጊዜ ማስታወሻዎች፡
1. ከአንዱ ርዕስ ወደሌላ ያሉ ክህሎቶችን ለማከናወን
ፕረዘንቴሽኖችን ክፍት ያድርጉ፣ ካልታዘዙ በስተቀር አይዝጉ።
2. በሚታዘዙበት ጊዜ ሁሉ ሴቭ ያድርጉ።
64
አጉሊ መጠቀም
አንዳንድ ጊዜ በስፕሬድሺት ውስጥ ያለው ጽሑፍ በትክክል ለማንበብ በጣም ትንሽ ይሆናል። በስፕሬድሺት ውስጥ ያለውን የጽሑፍ
መጠን መለወጥ ይችላሉ፣ ግን ያ በስፕሬድሺትዎ ውስጥ ሌላ ቅርጸት ሊያበላሽ፣ እንዲሁም በስፕሬድሺት ውስጥ ያሉ ገጾችዎን
ሊቀያይረው ይችላል። ይህን ለማስተካከል ቀላሉ መንገድ Zoom ባህሪን በመጠቀም ስፕሬድሺትዎን የሚታይበትን መጠን ብቻ
መለወጥ ነው።
65
ፓን እንዳይንቀሳቀስ(እንዳይቀየር) ማድረግ
• ፓን እንዳይንቀሳቀስ(እንዳይቀየር) በሚያደርጉበት ጊዜ በማያ ገጹ ላይ አንዴ ለመግባት በጣም ብዙ ውሂብ ባላቸው ትላልቅ
ስፕሬድሺቶች ውስጥ በሚሰሩበት ጊዜ ወደታች ሲወርዱ ወይም ወደላይ ሲሄዱ ረድፍ እና አምድዎን ርእሶች ሁል ጊዜ እንዲታዩ
ያደርጋሉ።
• Flower Sales የሚለው ወርክቡክ ክፍት መሆኑን እና የማጉላት ደረጃው 100% መሆኑን ያረጋግጡ።
• ፓነሎችን በሚያቆሙበት ጊዜ፣ እንዳይንቀሳቀስ በሚፈልጉት ከማንኛውም ረድፎች በታች እንዲሁም ለማሰር ከሚፈልጉት ከማንኛውም
ዓምዶች በስተቀኝ ይምረጡ።
1. ሴል B2 ላይ ጠቅ ያድርጉ።
2. View፣ Freeze Panes፣ Freeze Panes ላይ ጠቅ ያድርጉ።
3. ወደታች ይውረዱ እንዲሁም ወደቀኝ ይሂዱ። የላይኛው ረድፍ አሁን እንደቆመ ይመለከታሉ እና በሚወርዱበት ጊዜ ርዕሶቹን ማየት
ይችላሉ።
4. ወርክቡኩን ለሚቀጥለው ርእስ ክፍት እንዲሆን ያድርጉ።
66
አንድ ቃል ወይም ሀረግ መፈለግ
1. Home ታብ ላይ Editing ምድብ ውስጥ Find & Select፣ Find… ላይ ጠቅ ያድርጉ።
2. Find and Replace ሳጥን ይከፈታል።
3. Find What የፅሁፍ ሳጥን ውስጥ አርሜኒያ ብለው ይፃፉ እና Find Next ላይ ጠቅ ያድርጉ።
4. Excel በስፕሬድሺቱ መጨረሻ አንድ ፅሁፍ ያገኛል።
5. Find and Replace ሳጥኑን ይዝጉ።
6. ወርክቡኩን ለሚቀጥለው ርእስ ክፍት እንዲሆን ያድርጉ።
67
ፅሁፍን
1. Home ታብ ላይ Editing ምድብ ውስጥ ባለው Find & Select፣ Replace ላይ ጠቅ ያድርጉ።
2. Find and Replace ሳጥን ይከፈታል።
3. Find What የሚለው ሳጥን ውስጥ ጠቅ ያድርጉ እና ቤጎኒያ ብለው ይፃፉ።
4. Replace With የሚለው ሳጥን ውስጥ ጠቅ ያድርጉ እና ስኖውድሮፕሰ ብለው ይፃፉ።
5. ሁሉንም ቤጎኒያ የሚለውን ቃል ስኖውድሮፕሰ በሚለው ቃል በራስ -ሰር ለማግኘት እና ለመተካት
Replace All የሚለው ቁልፍ ላይ ጠቅ ያድርጉ።
6. OK የሚለው ላይ ጠቅ ያድርጉ።
7. ወርክቡኩን My Flowers Sales ብለው ሴቭ ያድርጉ እና ይዝጉት።
68
Go To መጠቀም
Go To ወደ አንድ የስፕሬድሺትዎ የተወሰነ ክፍል በፍጥነት ለመሄድ ጥቅም ላይ ይውላል፣ ለምሳሌ ቀመር የያዘ ማንኛውም ሴል።
69
ውሂብ ያስገቡ
ውሂብ ማስገባት ማለት ኸስፕሬድሺትዎ ውጪ ያለን ውሂብ ማስገባት ማለት ነው።
70
የውሂብዎን መጠበቅ ያረጋግጡ
• አንዴ ውሂብ ወደ ስፕሬድሺት ካስገቡ በኋላ ትክክል መሆኑን ለማረጋገጥ ውሂቡን መመልከት ያስፈልግዎታል።
• ውሂብዎን ለመፈተሽ መጠቀም የሚችሏቸው የተለያዩ ዘዴዎች አሉ። ለዚህ ምሳሌ፣ የተደገሙ የቀን ቁጥሮችን ለመፈለግ
Conditional Formatting ደንብ እንጠቀማለን።
71
ውሂብ ማስተካከል
Excel ውስጥ ውሂብ በአንድ ወይም ተጨማሪ አምድ ሊስተካከል ይችላል።
1. Flower Sales የሚለውን ወርክቡክ ይክፈቱ።
2. በሺት ውስጥ ያለውን ውሂብ በሙሉ ለማድመቅ CTRL + A ይጫኑ።
3. Data ታብ ላይ Sort ቁልፍ ላይ ጠቅ ያድርጉ።
4. Sort ሳጥን ይከፈታል።
5. Sort By በዝርዝር ውስጥ፣ ውሂብዎን በየትኛው የExcel አምድ ማስተካከል
እንደሚፈልጉ መምረጥ ይችላሉ። ምርጫው Type ላይ እንዲቆይ ያድርጉ። ውሂቡ
በType አምድ መሰረት ለማስተካከል OK ላይ ጠቅ ያድርጉ።
6. ወርክቡኩን My Data ብለው ሴቭ ያድርጉ እና ለሚቀጥለው ርእስ ክፍት እንደሆነ
ይተዉት።
72
ውሂብ ማጥራት (Filter)
በExcel ውስጥ፣ መረጃን በሚያጣሩበት ጊዜ፣ በአንድ ወይም በብዙ መመዘኛዎች ላይ በመመስረት አንድን ውሂብ ከአንድ ትልቅ የውሂብ
ምንጭ ማውጣት ይችላሉ። ምሳሌ፡ ተመሳሳይ የቤተሰብ ስም የያዘ ውሂብ ሁሉ።
ማጥሪያ መተግበር፡
1. Data ታብ ላይ Sort & Filter ምድብ ውስጥ Filter ላይ ጠቅ ያድርጉ።
2. Excel ስፕሬድሺትዎ ውስጥ ከእያንዳንዱ አምድ ርዕስ ቀጥሎ ወደታች የሚታዩ ዝርዝር ቁልፎችን
ያክላል።
3. የጅምላ ሻጭ ዝርዝር ቁልፍ ላይ ጠቅ ያድርጉ።
4. ፍሎራል ጊፍትስን ለማጥራት:
1. ሁሉንም ምልክቶች ያጥፉ፡ ሁሉንም የጅምላ ሻጭ ላለመምረጥ ከላይ Select All
የሚለው ሳጥን ውስጥ ጠቅ ያድርጉ።
2. የምልክት ሳጥን ውስጥ ምልክት በማድረግ ፍሎራል ጊፍትስን ይምረጡ።
5. ለሚቀጥለው ርእስ ፋይሉን ክፍት እንደሆነ ያቆዩ።
ማጥሪያን ማስወገድ፡
1. Data ታብ ላይ Sort & Filter ምድብ ውስጥ ባለው Filter ላይ ጠቅ ያድርጉ።
2. ይህ ማንኛውንም የተተገበሩ ማጣሪያዎችን ያጠፋል እና ወደታች መዘርዘሪያ ቁልፎችን ያስወግዳል።
3. ወርክቡኩን ያዘምኑ (ሴቭ ያድርጉ) እና ይዝጉ።
74
ንዑስ ድምር መረጃ ረቂቅ
አንድ ረቂቅ ቀመር ጥቅም ላይ በሚውልበት ሺት ውስጥ ካለው ነባር ውሂብ ማጠቃለያ ጋር ተመሳሳይ ነው።
75
ንዑስ ድምር መረጃ ረቂቅ
1. በሺቱ በግራ በኩል፣ በስም ሳጥኑ ስር፣ በግራጫ ብሎኮች ውስጥ 3
ቁጥሮች አሉ።
2. ሁሉንም የጅምላ ሻጮች ገቢ አጠቃላይ ድምር ለማየት ቁልፍን ጠቅ
ያድርጉ። (ሁሉም ሌሎች ረድፎች ከእይታ ይደበቃሉ)
3. የእያንዳንዱን አከፋፋይ ጠቅላላ ገቢ ለማየት ቁልፍን ጠቅ ያድርጉ።
4. ስፕሬድሺት ውስጥ ያለውን ሁሉንም ውሂብ ለማየት ቁልፍ ላይ
ጠቅ ያድርጉ።
5. ይህን ወርክቡክ My Outline ብለው ሴቭ ያድርጉ እና ለሚቀትለው
ርእስ ክፍት እንደሆነ ያቆዩ።
6. ወርክቡክዎን ያዘምኑ (ሴቭ ያድርጉ)።
76
ውሂብን በሠንጠረዥ መልክ ማስቀመጥ
በExcel ውስጥ ሠንጠረዥ የስፕሬድሺት ውሂብዎን ወደ ረድፎች እና ቡድኖች ለመሰብሰብ እና የበለጠ አቀራረቡን ለማስተካከል የተለያዩ
የቅርፀት ስታይሎችን ለመተግበር ሊያገለግል ይችላል።
1. Flower Sales የሚለውን ስፕሬድሺት ይክፈቱ።
2. Home ታብ ላይ Styles ምድብ ውስጥ Format As Table ቁልፍ ላይ ጠቅ
ያድርጉ።
3. ከቀለም ስብስቡ ፈካ ያለ አረንጓዴ ስታይል ይምረጡ።
4. Excel በእርስዎ ስፕረድሺት ውስጥ ያለውን ሁሉንም ውሂብ በራስ -ሰር ይመርጣል
እና Create Table ሳጥን ይከፍታል።
5. My Table Has Headers ቀጥሎ ያለው አመልካች ሳጥን ላይ ምልክት
መደረጉን ያረጋግጡ እና OK ጠቅ ያድርጉ።
6. ስፕሬድሺትዎ Table Style ውስጥ ከተቀመጡት ሁሉም ቅንብሮች ጋር
ይስተካከላል።
7. ሠንጠረዥ ውስጥ ሲሰሩ፣ ውሂብዎን ለማጣራት Filters መጠቀም ይችላሉ።
8. ወርክቡኩን My Table ብለው ሴቭ ያድርጉ እና ይዝጉት።
77
አንድን ስራ እንደ ማክሮስ ማስቀመጥ
ማክሮ በመደበኛነት የሚያከናውኗቸውን የሥራዎች ስብስብ ለመመዝገብ ያገለግላል። ለምሳሌ፡ ወርክቡክ አንድ ቦታ ላይ ሴቭ ማድረግ።
መመዝገብ ለማቆም፡
7. View፣ Macros፣ Stop Recording ጠቅ ያድርጉ ።
8. አዲስ ወርክቡክ ይክፈቱ።
ማክሮ ለመጠቀም፡
7. View፣ Macros፣ View Macros ላይ ጠቅ ያድርጉ።
8. SaveAs ይምረጡ እና Run ላይ ጠቅ ያድርጉ።
9. ሁለቱንም ወርክቡኮች My Macros 1 እና My Macros 2 ብለው ሴቭ ያድርጉ።
78
ክፍለ ጊዜ 4፡ ትምህርት 7
የትምህርት 7 ርእሶች፡
Microsoft Word ን መክፈት
1. SUMIF አሰራር መተግበር
2. COUNTIF አሰራር መተግበር
3. SUMIFS አሰራር መተግበር
4. COUNTIFS አሰራር መተግበር
5. VLOOKUP አሰራር መተግበር
6. NOW, TODAY, YEARFRAC, DATEDIF አሰራር መተግበር
የክፍለ ጊዜ ማስታወሻዎች፡
1. ከአንዱ ርዕስ ወደሌላ ያሉ ክህሎቶችን ለማከናወን ፕረዘንቴሽኖችን ክፍት
ያድርጉ፣ ካልታዘዙ በስተቀር አይዝጉ።
2. በሚታዘዙበት ጊዜ ሁሉ ሴቭ ያድርጉ።
79
SUM አሰራር መጠቀም
SUMIF የተወሰኑ መስፈርቶችን የሚያሟሉ የሴሎችን ቡድን በአንድ ላይ ለመደመር ያገለግላል።
ሁኔታ፡ ቀመር በመጠቀም የክሌማቲስ አበባ ምን ያህል እንደሚያስወጣ ይወቁ።
1. Adv Functions የሚለውን ወርክቡክ ይክፈቱ።
2. SUMIF ሺት ክፍት መሆኑን ያረጋግጡ።
3. ሴል F28 ይምረጡ እና ከዚያ ከ Formula Bar አጠገብ በሚገኘው FX
ቁልፍ ላይ ጠቅ ያድርጉ።
4. በInsert Function ሳጥን ውስጥ መጠቀም የሚፈልጉትን አሰራር ስም ይፃፉ፣
በዚህ ሁኔታ SUMIF እና ከዚያ በGo ቁልፍ ላይ ጠቅ ያድርጉ።
5. የSUMIF አሰራር ከታች እንደተመረጠ ያረጋግጡ እና OK የሚለውን ቁልፍ ጠቅ
ያድርጉ።
80
SUM አሰራር መጠቀም
በFunction Arguments ሳጥን ውስጥ የሚከተሉትን መስኮች
ይሙሉ።
1. Range: ይህ በቀመርዎ ውስጥ ለመጠቀም የሚፈልጉት ሙሉ
የሴል ክልል ነው። A2:F26 ብለው ይፃፉ።
2. Criteria: Excel እንዲደምር የፈለጉትን አበባ የሚሞሉት እዚህ
ነው። ክሌማቲስ ብለው ይፃፉ።
3. Sum_range: Excel ለመደመር የሚጠቀመውን የሴል ክልል
የሚገልጹት እዚህ ነው። F2:F26 ብለው ይፃፉ።
4. ቀመሩን ለመጨረስ እና ወደ ስፕሬድሺቱ ለመመለስ OK የሚለውን
ቁልፍ ጠቅ ያድርጉ።
5. Excel የሁሉንም ክለማቲስ አበባዎችን ጠቅላላ ወጪ 36050
ያሰላል።
6. ወርክቡኩን My Functions ብለው ሴቭ ያድርጉ እና ለሚቀጥለው
ርእስ ክፍት እንደሆነ ይተዉት።
81
COUNTIF አሰራር መጠቀም
COUNTIF በተወሰኑ መመዘኛዎች ላይ በመመስረት በሴል ክልል ውስጥ ስንት
ቁጥሮች እንዳሉ ለመቁጠር ይጠቅማል።
ሁኔታ፡ ፍላወርወርልድ ስንት ጊዜ ግዢ እንዳደረገ ይወቁ።
1. ወደ COUNTIF ሺት ይቀይሩ።
2. ሴል E28 ይምረጡ እና FX ሳጥን ይክፈቱ።
3. COUNTIF ይፈልጉ። ከዝርዝሩ ውስጥ ትክክለኛውን ተግባር ይምረጡ
እና OK ላይ ጠቅ ያድርጉ።
በFunction Arguments ሳጥን ውስጥ የሚከተሉትን መስኮች ይሙሉ።
4. Range: ይህ በቀመርዎ ውስጥ ለመጠቀም የሚፈልጉት ሙሉ የሴል
ክልል ነው። E2:E26 ብለው ይፃፉ።
5. Criteria: Excel እንዲደመር የፈለጉትን በአከፋፋዩ ውስጥ የሚሞሉት
እዚህ ነው። FlowerWorld ብለው ይፃፉ።
6. ቀመሩን ለመጨረስ እና ወደ ስፕሬድሺቱ ለመመለስ OK የሚለውን ቁልፍ
ጠቅ ያድርጉ።
7. Excel ፍላወርወርልድ ስንት ጊዜ ግዢ እንዳደረገ (4) ያሰላል።
82
SUMIFS አሰራር መጠቀም
ከአንድ በላይ መመዘኛዎችን መጠቀም ከመቻልዎ በስተቀር SUMIFS ከSUMIF በተመሳሳይ መንገድ ይሠራል።
ሁኔታ፡ በበጋ የተገዛው የሁሉም ቤጎኒያ አጠቃላይ ዋጋ ምን ያህል እንደሆነ ይወቁ።
1. ወደ SUMIFS ሺት ይቀይሩ።
2. ሴል F28 ይምረጡ እና FX ሳጥን ያስጀምሩ።
3. SUMIFS ይፈልጉ። ከዝርዝሩ ውስጥ ትክክለኛውን አሰራር ይምረጡ እና OK ላይ ጠቅ
ያድርጉ።
በFunction Arguments ሳጥን ውስጥ የሚከተሉትን መስኮች ይሙሉ።
4. SUM Range: አንድ ወይም ከዚያ በላይ መመዘኛዎችን በመጠቀም መደመር
የሚፈልጓቸውን ሁሉንም ቁጥሮች የያዘ የሴል ክልል ነው። F2:F26 ብለው ይፃፉ።
5. Criteria_Range1: ይህ 1ኛ መስፈርትዎን የያዘ የሴል ክልል ነው። A2:A26 ብለው
ይፃፉ።
6. Criteria1: ይህ በቀመርዎ ውስጥ መጠቀም የሚፈልጉትን 1ኛ መስፈርት የሚፅፉበት
የሴል ክልል ነው። ቤጎኒያ ብለው ይፃፉ።
7. አንዴ መስፈርት ለCriteria_Range1 ከሞሉ በኋላ Excel በሚቀጥለው Criteria
Range ውስጥ ያክላል። Criteria_Range2.
የሚቀጥለው ስላይድ ላይ ይቀጥሉ …
83
SUMIFS አሰራር መጠቀም
8. Criteria_Range2: ይህ 2ኛ መስፈርትዎን የያዘ የሴል ክልል ነው። E2:E26 ብለው ይፃፉ።
9. Criteria2: ይህ በቀመርዎ ውስጥ መጠቀም የሚፈልጉትን 2ኛ መስፈርት የሚፅፉበት የሴል ክልል ነው። በጋ ብለው ይፃፉ።
10. OK ቁልፍ ላይ ጠቅ ያድርጉ።
11. Excel በበጋ የተገዛው የሁሉም የቤጎኒያ ጠቅላላ ወጪ ምን ያህል እንደሆነ ያሰላል። (15000)
12. ወርክቡኩን ያዘምኑ (ሴቭ) ያድርጉ። ለሚቀጥለው ርዕስ ክፍት ያድርጉት።
84
COUNTIFS አሰራር መጠቀም
ከአንድ በላይ መመዘኛዎችን መጠቀም ከመቻልዎ በስተቀር COUNTIFS ከCOUNTIF ጋር በተመሳሳይ መንገድ ይሠራል።
ሁኔታ፡ ፍላወርወርልድ ስንት ጊዜ ቤጎኒያ እንደገዛ ይወቁ።
1. ወደ COUNTIFS ሺት ይቀይሩ።
2. ሴል D28 ይምረጡ እና FX ሳጥን ያስጀምሩ።
3. COUNTIFS ይፈልጉ። ከዝርዝሩ ውስጥ ትክክለኛውን አሰራር
ይምረጡ እና OK ላይ ጠቅ ያድርጉ።
• በFunction Arguments ሳጥን ውስጥ የሚከተሉትን መስኮች
ይሙሉ።
4. Criteria_Range1: ይህ 1ኛ መስፈርትዎን የያዘ የሴል ክልል ነው።
A2:A26 ብለው ይፃፉ።
5. Criteria1: ይህ በቀመርዎ ውስጥ መጠቀም የሚፈልጉትን 1ኛ
መስፈርት የሚፅፉበት የሴል ክልል ነው። ቤጎኒያ ብለው ይፃፉ።
86
VLOOKUP አሰራር መጠቀም
VLOOKUP በሌላ ሴል ቁጥሮች ላይ በመመስረት በቁም ሰንጠረዥ ውስጥ የሴሎችን ቁጥር ለመፈለግ ያገለግላል።
ሁኔታ፡ ለጅምላ አከፋፋይ ቤኒስ የግንኙነት ሰው ማነው?
1. ወደ VLOOKUP ሺት ይቀይሩ።
2. ሴል B10 ይምረጡ እና የFX ሳጥኑን ያስጀምሩ።
3. VLOOKUP ይፈልጉ። ከዝርዝሩ ውስጥ ትክክለኛውን አሰራር ይምረጡ እና OK
ላይ ጠቅ ያድርጉ።
በFunction Arguments ሳጥን ውስጥ የሚከተሉትን መስኮች ይሙሉ።
4. Lookup_Value: ይህ በቤኒስ ውስጥ የዓይነትን የግንኙነት ዝርዝሮችን
ለማግኘት የሚፈልጉት ጅምላ አከፋፋይ ነው።
5. Table_array: ይህ የጅምላ አከፋፋዮችን ስም እንዲሁም የግንኙነት ሰዎችን
የያዘ የሴል ክልል ነው። A1:B8 ብለው ይፃፉ።
የሚቀጥለው ስላይድ ላይ ይቀጥሉ …
87
VLOOKUP አሰራር መጠቀም
6. Col_index_num: ይህ የግንኙነት ሰዎች ስም የያዘ ዓምድ ነው።
7. OK ቁልፍ ላይ ጠቅ ያድርጉ።
8. Excel በመጀመሪያ በጅምላ አከፋፋይ ቤኒስ በአምድ A ውስጥ ይመለከታል፣ ከዚያ በአምድ B ውስጥ የትኛው የግንኙነት ሰው
በተመሳሳይ ረድፍ ውስጥ ከጅምላ አከፋፋዩ ጋር እንደሚዛመድ ይመልከታል።
9. ወርክቡኩን ያዘምኑ (ሴቭ) ያድርጉ።
88
NOW & TODAY አሰራር መጠቀም
የNOW አሰራር በስርዓት ቅንብሮችዎ መሠረት የአሁኑን ቀን እና ሰዓት ይመልሳል።
1. Dates ሺት ይቀይሩ።
2. ሴል B2 ይምረጡ እና =NOW() ብለው ይፃፉ።
89
YEARFRAC አሰራር መጠቀም
YEARFRAC በመጀመሪያ እና በማብቂያ ቀን መካከል በሚወከልበት ጊዜ የዓመቱን ክፍልፋይ ለማስላት ያገለግላል።
90
DATEDIF አሰራር መጠቀም
• መልሱን በቀናት፣ በወራት ወይም በዓመታት ለማሳየት ከመምረጥ በስተቀር የDATEDIF አሰራር ከYEARFRAC አሰራር ጋር ተመሳሳይ
ነው።
• ሴል C13ን ይምረጡ እና =DATEDIF(A13;B13;"D") ይፃፉ። ማስታወሻ፡ Excel ከሎተስ 1-2-3 የቆዩ
ወርክቡኮችን ለመክፈት የDATEDIF አሰራርን
ይሰጣል። የDATEDIF አሰራር በአንዳንድ
የቀመር ማብራሪያ ሁኔታዎች ውስጥ ትክክል ያልሆኑ ውጤቶችን
1. =DATEDIF እየተጠቀሙ ያሉት አሰራር ስም ነው። ሊያሰላ ይችላል። ለተጨማሪ ዝርዝሮች እባክዎን
የዚህ ጽሑፍ የሚታወቁ ጉዳዮች ክፍልን
2. A13 የመጀመሪያ ቀን ነው። ይመልከቱ።
3. B13 የመጨረሻ ቀን ነው።
4. “D” ለExcel የቀኖች ውስጥ መጀመሪያ እና በማብቂያ ቀን መካከል ያለውን የጊዜ መጠን እንዲገልጽ ይነግረዋል።
1. ይህንን አሰራር ሲጠቀሙ ለቀናት “D” ብለው ይፃፉ።
2. “M” ለወራት
3. “Y” ለአመታት።
5. ወርክቡኩን ያዘምኑ (ሴቭ ያድርጉ) እና ይዝጉ።
91
ክፍለ ጊዜ 4፡ ትምህርት 8
የትምህርት 8 ርእሶች፡
Microsoft Word ን መክፈት
1. ቻርቶችን መስራት
2. የቻርት ቅርፀት
3. ቻርት ማስተካከል
4. ምስል ማስገባት
5. ቅርፆችን፣ መስመሮችን፣የፅሁፍ ሳጥኖችን እና ወርድአርት ማከል
6. የግራፊኮችን መሰረዝ፣ መቅዳት እና ቦታ መቀየር
7. የግራፊክ ማስተካከያ ማከል
8. ስማርትአርት ግራፊክ መጠቀም
የክፍለ ጊዜ ማስታወሻዎች፡
1. ከአንዱ ርዕስ ወደሌላ ያሉ ክህሎቶችን ለማከናወን ፕረዘንቴሽኖችን ክፍት
ያድርጉ፣ ካልታዘዙ በስተቀር አይዝጉ።
2. በሚታዘዙበት ጊዜ ሁሉ ሴቭ ያድርጉ።
92
ቻርት ማስገባት
አንድ ቻርት መረጃን በስዕላዊ መንገድ ለማስተላለፍ ያገለግላል። ምሳሌ፡ በዚህ ያህል አመታት ውስጥ የሽያጭ ውሂብ።
93
የቻርት ቅርፀት
ለእይታ የበለጠ ማራኪ ለማድረግ አንድ ቻርት በግራፊክ ሊሻሻል ይችላል። ምሳሌ፡ ቀለሞች፣ ርእሶች
95
ምስል ማስገባት
በኮምፒተርዎ ላይ ያስቀመጡትን ማንኛውንም ምስል፣ ለምሳሌ የኩባንያ አርማ ማስገባት ይችላሉ።
1. Insert ታብ ላይ Illustrations ቁልፍ ላይ ጠቅ ያድርጉ እና Picture፣ This Device ይምረጡ። ይህ ባህሪ ምን ማድረግ
እንደሚችል የሚያብራራ ጠቃሚ መረጃ በማያ ገፅዎ ላይ ይታያል።
2. ምስሉን ወደ ቻርቱ በስተቀኝ ያንቀሳቅሱት እና መጠኑን ይለውጡ።
96
ቅርፆች ማስገባት
ቅርፅ ወደ ስፕሬድሺት ውስጥ ማስገባት የሚችሉት ቀለል ያለ ግራፊክ ኦብጀክት ነው፣ ለምሳሌ አራት ማዕዘን።
97
የፅሁፍ ሳጥን
የጽሑፍ ሳጥን ጽሑፍ መፃፍ የሚችሉበት ትንሽ ሳጥን ነው።
1. ኪቦርዱ ላይ Ctrl + End ይጫኑ።
2. Insert ታብ ላይ።
3. Text ፅሁፍ ላይ ጠቅ ያድርጉ። Text Box ይምረጡ።
4. በኮከቡ ቅርፅ አጠገብ የፅሁፍ ሳጥን ያስቀምጡ።
5. 2015 የእኛ ኮከብ አመት ነበር! ብለው ይፃፉ።
98
ወርድአርት ማስገባት እና ማስተካከል
ወርድአርት እንደ ጥላ ወይም የሚያንጸባርቅ ጽሑፍን የማስጌጥ ውጤቶችን ለመፍጠር ወደ ስፕሬድሺትዎ ማከል የሚችሉት የጽሑፍ ስታይሎች
ማዕከለ -ስዕላት ነው። በስፕሬድሺት ላይ ልዩ የጽሑፍ ውጤቶችን ለማከል ወርድአርት መጠቀም ይችላሉ።
1. Insert, Text, WordArt ላይ ጠቅ ያድርጉ።
2. የመጨረሻውን አማራጭ ይምረጡ።
3. ቻርቱ ላይ እንዳይደረብ ወርድአርቱ ላይ ጠቅ ያድርጉ እና ይጎትቱ።
4. የወርድአርት ፅሁፍን ይምረጡ እና Annual Sales ብለው ይፃፉ።
99
የግራፊኮችን መሰረዝ፣ መቅዳት እና ቦታ መቀየር
1. ኮከቡን ይምረጡ እና ኪቦርድዎ ላይ Ctrl + D ይጫኑ። D ማባዛትን ይጠቁማል፣ የኮከቡ
ቅጂ ይፈጠራል።
2. ይህንን ድርጊት ይድገሙ።
100
የግራፊክ ማስተካከያ ማከል
ስዕልን በስዕላዊ ሁኔታ ለማስተካከል Picture Tools፣ Format ታብን መጠቀም ይችላሉ።
101
ስማርትአርት ማስገባት እና ማስተካከል
ስማርትአርት አንድ ጽሑፍ ከመጻፍ ይልቅ አንድን ሀሳብ በስዕላዊ መንገድ ለማስተላለፍ ያገለግላል። ምሳሌ፡ ዝርዝር፣ ግንኙነት
1. አዲስ ስፕሬድሺት ያክሉ።
2. SmartArt፣ Insert ታብ ላይ ከIllustrations ቁልፍ ይምረጡ።
3. Process የሚለው ላይ ጠቅ ያድርጉ እና Continuous Block Process ይምረጡ።
4. በCreate Graphic ምድብ SmartArt Tools, Design ታብ ላይ ሌላ ቅርፅ ያክሉ።
5. በምስሉ ውስጥ እንደሚታየው ፅሁፍ ይፃፉ።
6. ወርክቡክዎን ያዘምኑ (ሴቭ ያድርጉ)።
102