Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 4

1

የሰርቪስ ቤት ኪራይ ውል ስምምነት

አከራይ፡ አቶ/ወ/ሮ አልማዝ ከበደ

• አድራሻ፡ (ከተማ) አዲስ አበባ (ክፍለ ከተማ) ኮ/ቀራኒዮ ወረዳ 03 ፣የቤት ቁጥር አዲስ ስልክ
ቁጥር፡0913278186

ተከራይ፡ አቶ/ወ/ሮ /ወ/ሪ___________________________________

• አድራሻ፡ (ከተማ) አዲስ አባባ (ክፍለ ከተማ) ኮ/ቀራኒዮ ወረዳ 03 የቤት ቁጥር ________ ስልክ
ቁጥር፡___________________
አንቀጽ አንድ
የውሉ አላማ

1. አከራይ የግላቸው የሆነውንና በስማቸው ተመዝግቦ በ አዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ
ከተማ ወረዳ 03 የሚገኘውን የቤት ቁጥር _________ በሆነው መኖሪያ ቤታቸው ቅጥር ግቢ
የሚገኘውን 1 ክፍል ሰርቪስ የጋራ ሽንት ቤትን ጨምሮ በዚህ ውል መሰረት ተከራይ ለሆነው
ለ_____________________________ ለመኖሪያ አገልግሎት ብቻ እንዲጠቀምበት በዚህ ውል መሰረት
አከራይተውታል፡፡

አንቀጽ ሁለት
የውሉ ዘመን

1. ይህ ውል ከ____________________ቀን ___________ ዓ.ም ጀምሮ ለ _______ ወር የፀና ነው፡፡


2. ውሉን ለማደስ የፈለገ ወገን ፍላጎቱን የውሉ ጊዜ ከማለቁ በፊት ባሉት ________ ቀናት ውስጥ
በጽሁፍ መግለጽ አለበት፡፡
አንቀጽ ሶስት
የኪራይ መጠን

1. ተከራይ ከላይ በአንቀፅ 1 ላይ የተገለፀውን ቤት በወር __________________ ብር መብራትና ውሀን


ሳይጨምር ለአከራይ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ ለመክፈል ተስማምቷል፡፡
2. ውሃን በተመለከተ ተከራይ እንደቆጠረ ለመክፈል ተስማምተዋል፨
3. አከራይ የውል ጊዜ ሲያበቃ እና አስፈላጊ ሲሆን የአካባቢን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት
ምክንያታዊ የሆነ የቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ ሊያደርግ ይችላል፡፡
2

አንቀጽ አራት
የኪራይ አከፋፈል

1. ተከራይ ይህ ውል በሁለቱ ወገኖች መካከል ሲፈረም ለአከራይ የ__________ ጊዜን የቤት ኪራይ
ማለትም ከቀን ______________ እስከ __________________________ዓ.ም ለአከራይ ከፍሏል፡፡
2. ተከራይ የሚቀጥለውን ወር የቤት ኪራይ ወር በገባ በ________________ ቅድሚያ መክፈል
ይኖርበታል ፨
አንቀጽ አምስት
የአከራይ መብትና ግዴታ

1. አከራይ አስፈላጊ ሲሆን ተከራይ ቤቱን በአግባቡ እየተጠቀመበት መሆኑን ለማረጋገጥ ወይም
በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት የሚፈጠሩ ብልሽቶችን እና ጉዳቶችን ለማስተካከል ወይም ለቤቱ
ደህንነት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ለተከራይ የ አንድ ቀን ማስታወቂያ ሰጥተው ቤቱ ውስጥ
የመግባት፣ቤቱን የመጎብኘትና አስፈላጊ ጥገናዎችን የማድረግ መብት አላቸው፡፡
አንቀጽ ስድስት
የተከራይ መብትና ግዴታዎች

1. ተከራይ በዚህ ውል ላይ የተገለጸውን ቤት በውሉ ጊዜ ውስጥ ለ መኖሪያ አገልግሎት የመጠቀም


መብት አለው፡፡
2. ተከራይ ቤቱን በአግባቡና በጥንቃቄ የመጠበቅና የመያዝ ግዴታ አለበት፡፡
3. ተከራይ በራሱ ጥፋት በቤቱ ላይም ሆነ በግቢው ውስጥ የሚያደርሰውን ጉዳት በራሱ ወጪ
ወዲያውኑ የማስተካከል ግዴታ አለበት፡፡
4. ተከራይ የቤት ኪራዩን ከላይ በአንቀጽ ሶስትና አራት መሰረት የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡
5. ተከራይ ያለ አከራይ የጽሁፍ ፈቃድ የተከራየውን ቤት ጣሪያና ግድግዳ መብሳት እና ማፍረስም
ወይም በቤቱ ላይ የማሻሻያ ለውጥ ማድረግ ወይም ቀለም መለወጥ አይችልም፡፡

አንቀጽ ሰባት
በቤቱ ላይ ያለን ጥቅም አሳልፎ መስጠት

1. ተከራይ በውሉ ላይ የተገለጸውን ቤት ለመጠቀም ያለውን ህጋዊ መብቱን የአከራይን በጽሁፍ


የተገለጸ ፍቃደኝነት ካላገኘ በስተቀር ለሶስተኛ ወገን ማስተላለፍ አይችልም፡፡

አንቀጽ ስምንት
ሕግን ማክበር
1. ተከራይ በውሉ ጊዜ ውስጥ ከቤቱ ጋር በተያያዘ ተግባራዊ የሆኑትን ህጎችና ደንቦች የማክበር ግዴታ
አለበት፡፡
3

አንቀጽ ዘጠኝ
ቤቱን ባለበት ሁኔታ ማስረከብ

1. ተከራይ የቤት ኪራዩ የውል ዘመን ሲያበቃ ቤቱን በተረከበበትና በጥሩ ሁኔታ ለአከራይ የማስረከብ
ግዴታ አለበት፡፡
2. ተከራይ በቤቱ ላይ የይዘት፣የቅርጽ፣የአቋም ወይም የውበት ለውጥ ሳያስከትል ሊንቀሳቀስ ወይም
ሊነሳ የሚችል ንብረት ካለው የውሉ ጊዜ ሲያበቃ አንስቶ የመውሰድ መብት አለው፡፡

አንቀጽ አስር
ውልን ማሻሻል
1. አከራይና ተከራይ ይህንን ውል ሊያሻሽሉ፣ሊለውጡ ወይም ሊቀይሩ የሚችሉት በጽሁፍ ከሆነ ብቻ
ነው፡፡
አንቀጽ አስራ አንድ
ውሉ ቀሪ የሚሆንባቸው ምክንያቶች

1. ተከራይና አከራይ በጽሁፍ ሲስማሙ ውሉ ቀሪ ይሆናል፡፡


2. የውሉ ዘመን በአከራይና በተከራይ የጽሁፍ ስምምነት ካልተራዘመ በስተቀር የውሉ ዘመን ሲያበቃ
ውሉ ቀሪ ይሆናል፡፡
አንቀጽ አስራ ሁለት
ግጭት መፍቻ
1. በአከራይና ተከራይ መካከል ከዚህ ውል አፈጻጸም ጋር በተያያዘ አለመግባባት፣ግጭት ወይም ቅራኔ
ቢፈጠር ሁለቱም ወገኞች በመመካከር ለመፍታት ተስማምተዋል፡፡ነገር ግን አለመግባባታቸውን
በመመካከር ለመፍታት ካልቻሉ ጉዳዩን ወደ ፍ/ቤት ይወስዳሉ፡፡

ይህ ውል በፍ/ብ/ሕ/ቁ/1731፣2005፣1889 እና 1890 መሰረት በህግ ፊት የጸና ነው፡፡

ይህ ውል ዛሬ___________ቀን _______ዓ.ም በ አዲስ አበባ ከተማ ተፈጸመ፡፡


4

አከራይ ተከራይ

——————— ———————

ስም ስም

——————– ———————-

ፊርማ ፊርማ

———————– ———————–

ቀን ቀን

ምስክሮች

ስም አድራሻ ፊርማ
___________________________ ____________________________ ______________

___________________________ ____________________________ ______________

___________________________ ____________________________ ______________

You might also like