Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 3

በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት

ለልደታ ምድብ ------- ወንጀል ችሎት

አ/ አ

የፍ/ቤት መ/ቁ………

የዐ/ህግ መ/ቁ. 1664/15

የፌዴራል ፖ/ወ/ም ወ/መ/ቁ. 828/15

ከሳሽ ………….. በፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ

ተከሳሽ ………….. 1 ኛ/ ስጦታዉ በቀለ ገብሬ

ዕድሜ፡- 40

ስራ፡- ሹፌር

አድራሻ፡- ኦሮሚያ ክልል፣ ሸገር ከተማ፣ ዱከም ክ/ከ፣ ቀበሌ 01፣ የቤት ቁጥር…

2 ኛ/ ረ/ሳጅን መስከረም አበባየዉ ተሰማ

ዕድሜ፡- 26

ስራ፡- ረዳት

አድራሻ፡- ኦሮሚያ ክልል፣ ሻሻመኔ ከተማ፣ ኮንዶሚኒየም፣ የቤት ቁጥር…

1 ኛ ክስ በሁለቱም ተከሳሾች ላይ

ወንጀሉ
በ 1996 ዓ.ም የወጣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ፣ የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/06(በአዋጅ ቁጥር
1160/2011 እንደተሻሻለዉ) ፣ አንቀጽ 168/2 እና በ 2000 ዓ.ም የወጣ ሃርሞናይዝድ ሲስተም ላይ የተመሰረተ
የጉምሩክ ታሪፍ ቅጽ አንድ፣ ምዕራፍ 63፣ኤች ኤስ ኮድ 63.09 ፣ታሪፍ ቁጥር 6309.0000’ን በመተላለፍ፣

የወንጀሉ ዝርዝር

ተከሳሾቹ የተከለከለ ዕቃ መሆኑን እያወቁ ወይም ማወቅ ሲገባቸዉ ብዛቱ በኪ.ግ. 6,156 (ስድስት ሺህ አንድ
መቶ ሀምሳ ስድስት) የሆነ አሮጌ ልባሽ ጨርቅ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-34372 ኢት. የሆነ ኒሳን ሼልቶ ተሽከርካሪ
ላይ በተጫነዉ ሽንኩርት ስር ደብቀዉ በመጫን 1 ኛ ተከሳሽ አሽከርካሪ በመሆን 2 ኛ ተከሳሽ ደግሞ ረዳት
በመሆን ከአዳማ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ከተማ በሚወስደዉ የፍጥነት መንገድ ላይ ሲያጓጉዙ በቀን
30/06/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ በግምት 02፡30 ሰዓት ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ መግቢያ ቱሉ ዲምቱ የጉምሩክ
መቆጣጠሪያ ጣቢያ ተብሎ በሚጠራ ቦታ ላይ በተደረገዉ ፍተሻ እጅ ከፍንጅ ስለተያዙ በፈፀሙት
የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ማጓጓዝ ወንጀል ተከሰዋል፡፡

2 ኛ ክስ በ 2 ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ

ወንጀሉ

በ 1996 ዓ.ም የወጣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 340 እና 288/1’ን በመተላለፍ፣

የወንጀሉ ዝርዝር

ተከሳሽ በቀን 17/08/2007 ዓ.ም በመለያ ቁጥር 43248 በፌዴራል ፖሊስ አባል ሆኖ በመቀጠር በፌዴራል
ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የተጠርጣሪ ጥበቃ ስራ ላይ ተመድቦ ሲሰራ ቆይቶ ያለምንም ኃላፊ ፈቃድ ከቀን
01/01/2012 ዓ.ም ጀምሮ ከስራ ገበታዉ በመጥፋቱ ምክንያት ተፈልጎ ለህግ እንዲቀርብ ከተወሰነ በኃላ ከላይ
በ 1 ኛ ክስ ዉስጥ በተገለፀዉ ቀን፣ ቦታ እና ሁኔታ በቁጥጥር ስር የዋለ በመሆኑ በፈፀመዉ የኩብለላ ወንጀል
ተከሷል፡፡

የማስረጃዎች ዝርዝር

ሀ/ የሰዉ ምስክሮች፡-

1. አቶ ባንተአምላክ እጅጉ ተሻለ አድራሻ፡- አ/አ፣ አ/ቃሊቲ ክ/ከተማ፣ ወ/06፣የቤት ቁ….

2. ዋ/ሳጅን አማኑኤል ሽብሩ ያድና አድራሻ፡- አ/አ፣ አ/ቃሊቲ ክ/ከተማ፣ ወ/06፣ የቤ.ቁ….

3. ዋ/ሳጅን ደሳለኝ ሰጠኝ ቸኮል አድራሻ፡- አ/አበባ፣ ጉለሌ ክ/ከ፣ ወረዳ 09፣ ካምፕ

ለ/ የሰነድ ማስረጃዎች፡-

1. በጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በሞዴል ቁጥር 265፣በደረሰኝ ቁጥር
012342 በቀን 01/07/2015 ዓ.ም የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ገቢ ያደረገበት ሰነድ ኮፒዉን 01-ገጽ፡፡

2. በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ በቁጥር


ወምቢ/ሠ 1002/6523/15 በመጋቢት 20 ቀን 2015 ዓ.ም በፃፈዉ ደብዳቤ 2 ኛ ተከሳሽ የፌዴራል
ፖሊስ አባል ሆኖ ያለምንም ፈቃድ ከስራ ገበታዉ የኮበለለ መሆኑን የሚያስረዳ ደብዳቤ ከእነአባሪዉ
ኮፒዉን 05-ገጽ፡፡

ማስታወሻ፡-

 ሁለቱም ተከሳሾች ከ 30/06/2015 እስከ 12/07/2015 ዓ.ም እስር ላይ ቆይተዉ በቀን


12/07/2015 ዓ.ም በፍ/ቤት ዋስትና ተለቀዋል፡፡

 ክሱ በመደበኛ ስነ-ስርዓት የቀረበ ነዉ፡፡

You might also like