Ref - No /date

You might also like

Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 2

ቁጥር/Ref.

No
ቀን/Date
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ

ለጉለሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ

አ/ አ

ጉዳዩ፡- እነ ማርታ ደመር የምርመራ መዝገብ በተመለከተ ተጨማሪ ምርመራ እንዲደረግ ስለመጠየቅ፡፡

በተጠርጣሪዎች እነ ማርታ ደመር ላይ በወ/መ/ቁ.516/16 ኮንትሮባንድ ወንጀል ምርመራ መዝገብ በቁጥር


42/8268/16 በቀን 12/06/2016 ዓ.ም በተጻፈዉ ሸኚ ደብዳቤ ተሟልቶ ተልኮልን ደርሶን ተመልክተናል፡፡

የመዝገቡ ፍሬ ነገርም ባጭሩ ተጠርጣሪዎች በቀን 01/05/2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጉለሌ
ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 08፣ጃንቦ ህንፃ አከባቢ በሚገኘዉ ኖክ ማደያ ዉስጥ የኮንትሮባንድ አሮጌ ልባሽ የሴት
ጫማዎችን የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 02-16234 አ/አ ከሆነ ተሸከርካሪ ወደ ሌላ ተሽከርካሪ ሰሌዳ ቁጥር ኮድ 01-
35443 አ/አ በመጫን ለመንቀሳቀስ በመዘጋጀት ላይ እያሉ ስለተያዙ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ይዞ የመገኘት
ወንጀል ፈጽመሟል የሚል ሲሆን በመዝገቡ ላይ ዉሳኔ ለመስጠት ተከታዮቹ ጉዳዮች ማለትም፡-

1. ተጠርጣሪ ማርታ ደመር የተባለችዉ የአልባሳት ሱቅ እንዳለት ስለገለፀች፡-

1.1 የንግድ ፈቃዷ ከመዝገቡ ጋር እንዲያያዝ በማድረግ ከሚመለከተዉ ንግድ ጽ/ቤት የንግድ ፈቃዱ
ትክክለኛነት ተረጋግጦ ማስረጃዉን ከመዝገቡ ጋር መያያዝ፣

1.2 ተጠርጣሪ ማርታ ደመር የተባለችዉ ግለሰብ የንግድ ፈቃድ ኖሯት በንግድ ስራ ላይ የተሰማራች
ከሆነ በንግድ ድርጅቷ ላይ የኢንቨስትጌሽን ኦዲት በሚመለከተዉ ገቢዎች ጽ/ቤት ተሰርቶ ዉጤቱ
ከመዝገቡ ጋር ማያያዝ፣

1.3 ተጠርጣሪ አሸናፊ እንድሪስ የተባለዉ ግለሰብ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 02-16234 አ/አ የሆነ ተሽከርካሪ
ሹፌር በመሆን ለትብብር አሁን ልክሱ ምክንያት የሆነዉን ዕቃ በትብብር ያለምንም ክፊያ ከአስኮ
ጨረታ ወደ ጉለሌ አዲሱ ገበያ የጫነ መሆኑን የገለፀ በመሆኑ፣ በተመሳሳይ መልኩ ተጠርጣሪ ጌቱ
አዱኛ ገላን የተባለዉ ግለሰብ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 01-35443 አ/አ የሆነ ተሽከርካሪ ሹፌር በመሆን
የራይድ አገልግሎት እንዲሰጥ በስልክ ትዕዛዝ ተቀብሎ ለተጠርጣሪ ማርታ ደመር ለተባለችዉ
ግለሰብ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ላይ እያለ የተያዘ መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን ይህ
ደግሞ ሁለቱም አሽከርካሪዎች የዕቃዉ በለንብረት የሆነችዉን ተጠርጣሪ ማርታ ደመር
የተባለችዉን ለመርዳት ወይም የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ያደረጉት ተግባር መሆኑን
ስለሚያሳይ ሁለቱም አሽከርካሪዎች ከተጠርጣሪነት ወደ ምስክርነት እንዲዞሩ በማድረግ
በተጠርጣሪ ማርታ ደመር ላይ የምስክርነት ቃላቸዉን በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 30 በዝርዝር
በማሰጠት ማስረጃዉን ከመዝገቡ ጋር ማያያዝ፣
1.4 ተጠርጣሪ አለማየሁ በላይ ዘመድኩን የተባለዉ ግለሰብ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 01-35443 አ/አ የሆነ
ተሽከርካሪ ባለንብረት መሆኑን በመግለጽ ተሽከርካሪዉን ለሹፌር ጌቱ አዱኛ ገላን የሰጠ መሆኑን
ስለገለፀ የኮንትሮባንድ ወንጀል ጋር ስላለዉ ግንኙነት የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ባለመኖሩ ግለሰቡ
ከተጠርጣሪነት ወደ ምስክርነት እንዲዞር በማድረግ በተጠርጣሪ ማርታ ደመር ላይ የምስክርነት
ቃሉን በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 30 በዝርዝር በማሰጠት ማስረጃዉን ከመዝገቡ ጋር ማያያዝ፣

1.5 የተጠርጣሪ ማርታ ደመር ማንነት የሚገልጽ መታወቂያ ከምርመራ መዝገቡ ጋር ማያያዝ፣

በአጠቃላይ ከላይ የተመለከቱትን ተጨማሪ ማስረጃዎችን በተቻለ ፍጥነት በማሟላት መዝገቡን


መልሳችሁ ትልኩልን ዘንድ የምርመራ መዝገቡን በወ/መ/ስ/ስ/ህግ ቀጥር 38/1/ሐ መሰረት ለተጨማሪ
ምርመራ በተላከልን ሁኔታ በዉስጡ 40-ገጽ እንደያዘ መልሰን የላክንላችሁ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

“ከሠላምታ ጋር”

ግልባጭ፡-

 ለጉምሩክ ወንጀል ጉዳዮች ዐ/ህግ ማስተባበሪያ

ኢኮ.ወ.ጉ.ዐ/ህ ዳይሬክቶሬት ጀነራል

You might also like