Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 3

የፍትህ ሚኒስቴር ዐቃብያነ ህግ ሆኘ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ (Master of Law in Criminal

Justice)ተማሪ መሆኔ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም የመመረቂያ ፅሁፌን እየሰራሁ ስለሆነ ከዚህ በታች
ዘርዝሬ ላቀረብካቸው መጠይቆች ምላሽ ለመስጠት እና ማስረጃ ለሚያስፈልጋቸው ተገቢ የሆኑ
ማስረጃዎችን ለመስጠት ፈቃደኛ ስለሆናችሁ ከልብ አመሰግናለሁ፡፡

1. የፌዴራል የወንጀል ጉዳዮችን በውክልና እንዲከታተሉ ለክልሎች መስጠት ያስፈለገበት ምክንያት


ምንድን ነው?

2. በ2010 ዓ.ም ጠ/ዐ/ሕግ(ፍትህ ሚኒስቴር) ክልሉ እንዲከታተለው የሰጠው የፌዴራል የወንጀል ጉዳዮች
ውክልና የወንጀል ዓይነቶችን በዝርዝር በለየ ሁኔታ ነው?
3. በተሰጠው ውክልና የክልሉ ዐ/ሕግ ምን እንዲሰራ ነው? (ምርመራ እንድታጣሩ? ክስ እንድትመሰርቱ
? የችሎት ክርክር እንድታደርጉ ነው?....) ወይስ ሁሉንም ተግባራት እንድታከናውኑ? ክስ ማቀረጥንስ
ያካተተ ነው? ስራዎችን ለማከናወን በሚያስችል ሁኔታ በግልፅ የተቀመጠ ነው?
4. ለክልሉ ውክልና ሲሰጥ ወንጀሎችን ለማከናወን የሚያስችል በጀት፤ ተቀማዊ
አደረጃጀት?የፈፃሚው አቅም፤ የትምህርት ዝግጅት እንዲሁም ልምድ ተለይቶ ነው? መረጃ ካለ?
5. የፌዴራል ጉዳዮችን ለሚከታተሉ ዐ/ሕጎች የፌዴራል ወንጀሎችን ለማከናወን የሚያስችላቸው ተገቢ
የሆነ ስልጠና ተሰጥተዋል(ይሰጣል?) መረጃ ካለ ቢሰጠን

6. በውክልና የተሰጡትን የፌዴራል ወንጀል ጉዳዮችን ብቻ የሚከታተል ፎካል ፐርሰን ወይም ሌላ


አደረጃጀት በክልሉ ተፈጥራል? ? መዝገቦችስ ራሳቸውን ችለው የሚያዙበት ሁኔታ አለ? ነው የክልሉ
ስራዎች የወንጀል ጉዳዮች ጋር ተቀላቅለው ነው?

7. ለክልሉ በውክልና የሰጠውን የፌዴራል የወንጀል ጉዳይ ፍትህ ሚኒስቴር በምን አግባብ ነው
የሚከታተለው?? ክትትል ተደርጎ ከሆነ ከመቼ ጀምሮ ነው? ክትትሉስ በምን አግባብ ተደረገ?

8. ውክልና ከተሰጠ ጊዜ ጀምሮ ለክልሉ በውክልና በተሰጡ የወንጀል ጉዳች ላይ ክልሉ ተከታትሎ ክስ
የመመስረት ሁኔታ ምን ያክል ነው? ክልሉ በራሱ ክስ ያቀረበባቸውን እና ክርክር ያካሄደባቸው የወንጀል
ጉዳዮች ለይቶ ማስረጃ ቢሰጠን? በጋራ የተመረመረሩ ካሉ ተለይተው ማስረጃ ቢሰጠን

9. በውክልና በተሰጡ የፌዴራል የወንጀል ጉዳዮች ላይ ምርመራ የሚያከናውኑት የክልሉ ፖሊስ ነው


ወይስ የፌዴራል ፖሊስ?
10. ፍትህ ሚኒስቴር ውክልና በሰጠበት የወንጀል ጉዳይ ምርመራውንም ሆነ ክስ እና ክርክሩን በራሱ
የሚያከናውንበት ሁኔታ/አሰራር/ አለ? ካለ በምን ምክንያት በየትኞቹ የወንጅል ጉዳዮች? በመዝገብ
የሚታወቅ ከሆነ ስምና የፈ/ዐ/ህግ/የፍርድቤት መዝገብ ቢገለፅልን
11. በራሱ የሚሰራበት ሁኔታ ካለ ለክልሉ አስቀድሞ የሰጠውን የውክልና ስልጣንስ ምን ያደርገዋል?

12. ለክልሎች ውክልና ከተሰጠበት ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በውክልናው መሰረት አልተከናወኑም ተብሎ
ከክልሉ ውክልናቸው የተነሳ የወንጀሎች ጉዳዮች አሉ? ካሉ ለማሳያ የሚሆን ጉዳይ ካለ ማስረጃ የተጠርጣሪ
ወይም የተከሳሽ ስም እና የዐ/ሕግ /የፍርድቤት መዝገብ ቁጥር ቢገለፅልን ቢሰጠን

13. ውክልና ተሰጥቶ የነበረ የፌዴራል የወንጀል ጉዳይ ውክልናው ከክልሉ የሚነሳበት ግልፅ የሆነ አሰራር
አለ?

14. በ2012 ዓ ም ከክልሎች ውክልናቸው የተነሳ የፌዴራል የወንጀል ጉዳዮች በግልፅ እና በዝርዝር
በክልሉ ይታወቃሉ? ለአሰራርስ ግልፅ ናቸው?

15. ውክልና ከክልሉ ሲነሳ የተነሳበት ምክንያት ለክልሉ ፍትሕ ቢሮ በደብዳቤ ይገለፃል?

16. በውክልና የተሰጡ የፌዴራል ወንጀሎች በክልሉ ተፈፅመው ምርመራ ሳይጣራባቸው፤ ክስ


ሳይቀርብባቸው ፤ ተገቢው ክርክር ሳይደረግባቸው እንዲሁም ወንጀል ፈፃሚዎች ተጠያቂ ሳይሆኑባቸው
የሚቀሩበት ሁኔታ አለ? ካለ አንደማሳያ በማስረጃ በተከሳሽ/ተጠርጣሪ ስም የወንጀሉ ዓይነት እንዲሁም
የፍ/ቤት መዝገብ ቁጥር ይዞ ከሆነ ቢገለፅልን?
17. እንደዚህ ዓይነት ችግር የሚፈጥሩ ፈፃሚዎች ከተገኙ ምን ዓይነት ተጠያቂነት (እርምጃ ) ይወሰዳል?
18. ክልሉ በውክልና ስለተሰጠው ተግባር የአፈፃፀም ሪፖርት ለፍትህ ሚኒስቴር የሚያቀርብበት ስርዓት
አለ? ካለ በምን ያህል ጊዜ ? የተላከ ሪፖርት ማስረጃ ቢሰጠን
19. በክልሉ የፌዴራል የወንጀል ጉዳዮች በውክልናው መሰረት እንዳይከናወኑ እና ውጤታማ እንዳይሆኑ
የሚያደርጉ ሁኔታዎች ምንድና ናቸው?
20. ክልሉ በተሰጠው ውክልና ግዴታውን ተወጥተል? እንዴት አልተወጣም ከሆነም ምክንያት ቢቀመጥ
21. ለክልሉ የተሰጠው ውክልና መቀጠል አለበት? አወ ከሆነ እንዴት? የለበትም ከሆነም ለምን?
22. የፌዴራል የወንጀል ጉዳዮችን በክልሉ ውጤታማ ለማድረግ ምን መሰራት አለበት?

Workie2016@yahoo.com /0912949764/

አመሰግናለሁ!!

You might also like