Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 2

ጊዜ

ጊዜ የምንለው ድርጊቱ የተፈፀመበትን ወይመ የሚፈፀምበትን ወቅት ነው፡፡ ይህም ድርጊቱ ንግግሩ
በሚፈፀምበት ወቅት ተፈፅሞ ያበቃ ከሆነ ሃላፊ ጊዜ እየተፈፀመ ያለ ከሆነ ያሁን ጊዜ ሲባል በንግግሩ ወቅት
ገና ያልተፈፀመ ከሆነ የትንቢት ጊዜ ይባላል፡፡ የሃላፊ ጊዜውን ከርቀት አንፃር ስናየው ድርጊቱ ንግግሩ
ለተፈፀመበት ጊዜ የሚርቅ ወይም የሚቀርብ ሊሆን ይችላል፡፡ የሚርቅ ሲሆን የሩቅ ሃላፊ ሲባል ሲቀርብ
ደግሞ የቅርብ ሃላፊ ይባላል፡፡

ለምሳሌ 1. እሱ ብርጭቆ ሰብር-ኦ ነበር፡፡

2. እሱ ብርጭቆ ሰብር-ኦ -አል፡፡

በሚሉት አረፍተነገሮች በመጀመሪያ የተገለፀው ድርጊት የቆየ ወይም ብዙ ጊዜ ያለፈው ሲሆን ሁለተኛ
የተገለፀው ግን ብዙ ጊዜ ያለፈው ላይሆን ይችላል፡፡ በሁለቱም አረፍተ ነገሮች ውስጥ የሚገኙት የግስ
አምዶችና የመደብ አመልካቾች አንድ አይነት ሲሆኑ ረዳት ግሳቸው ግን የተለየ ነው፡፡ በሩቅ ሃላፊ ጊዜ የገባዋ
ረዳት ግስ ነበር ሲሆን ለቅርብ ሀላፊው ግን /-አል/ ነው፡፡ በነዚህ የግስ አምዶች ላይ የሚጨመሩት መደብ
አመልካች ምዕላዶች እስካሁን ካየናቸው ለየት ያሉ ስለሆኑ በሚቀጥለው ምሳሌ እንመልከት

መደብ ነጠላ ብዙ

1 ኛ እኔ -ኤ (ኧ)ን

2 ኛ ተባዕታይ -ህ

አንስታይ -ሽ -ኣችሁ

3 ኛ ተባእታይ -ኦ

አንስታይ -ኣ (-ኧ)ው

ከዚህ ሌላ ድርጊቱ ተፈፅሞ ያበቃ ግን የተፈፀመበትን የጊዜ ርቀት የማይጠቁም ጊዜም አለ፡፡ ይህ አይነቱ ሃላፊ
ጊዜ የዋህ ሃላፊ ይባላል፡፡ በየዋህ ሃላፊ ጊዜ የግሱ አመድም መደብ አመልካቹ ምዕላድም ከፍ ብለን በቅርብና
በሩቅ ጊዜ ላይ ካየናቸው የተለዩ ናቸው፡፡ በሩቅና በቅርብ ጊዜ ሰብር- የነበረው አምድ በየዋህ ሃላፊ ጊዜ ሰበር-
ሲሆን መደብ አመልካች ምዕላዶቹም የሚከተሉት ናቸው፡፡

መደብ ነጠላ ብዙ

1 ኛ እኔ -ኩ/ሁ ን

2 ኛ ተባዕታይ -ህ

አንስታይ -ሽ -ኣችሁ

3 ኛ ተባእታይ -ኧ

አንስታይ -ኧች -ኡ
የአሁን ጊዜና የትንቢት ጊዜ ደግሞ በሩቅና በቅርብ ሃላፊ ጊዜ ባየነው አምድ ላይ ቅድመ አምድ መደብ
አመልካች ቅጥያና ረዳት ግስ/-ኣል/ን በመቀጠል ይገለፃል፡፡ በረዳት ግስ ላይም ድህረ አምድ መደብ አመልካች
ምዕላድ ይጨመርበታል፡፡

እኔ እ-ሰብር-አል-ኧሁ/አለሁ

አንተ ት-ሰብር-አል-ኧህ/አለህ

አንቺ ት-ሰብር-ኢ-አል-ኧሽ/አለሽ

እሱ ይ-ሰብር-አል/አል

እሷ ት-ሰብር-አል-ኧች/አለች

እኛ እን-ሰብር-አል-ኧን/አለን

እናንተ ት-ሰብር-አል-ኣችሁ/አላችሁ

እነሱ ይ-ሰብር-አል-ኡ/አሉ

You might also like