Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 4

ስርዓተ ነጥብ

በጽሁፍ ላይ የሰፈረ ሀሳብ መልዕክቱ ሳያሻማ ግልጽ ሆኖ እንዲተላለፍ ለማድረግ ሥርዓተ

ነጥቦች ትልቅ ድርሻ አላቸው፡፡ በጽሁፍ ውስጥ ሥርዓተ ነጥቦችን ባግባቡ አለመጠቀም

ሊተላለፍ የተፈለገው መልዕክት አሻሚ፣ የተዛባ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ ስለዚህ ሥረዓተ

ነጥቦችንና አገልግሎታቸውን ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ ከዚህ በታች በቋንቋው ውስጥ

የሚገኙት የሥርዓተ ነጥብ ዓይነቶችና ተግባራቸው ቀርቧል፡፡

፩. አንድ ነጥብ (.)፡- አንድ ነጥብ ይዘት ተብሎ ይጠራል፡፡ የተለያዩ አገልግሎቶች

አሉት፡፡ ከነዚህም ውስጥ ቃላትን አሳጥሮ ለመጻፍ፣ ብር እና ሳንቲሞችን

ለመለየት፣ እንዲሁም ክፍልፋይ እና ሙሉ ቁጥሮችን ለመለየት፣ መሉ ቁጥሮችን

ወይም ሆሄያትን ከዋናው ሀሳብ ለመለየት ያስችላል፡፡

ምሳሌ፡- ሀ. የተባበሩት መንግስታት ድርጅት …… ተ.መ.ድ.

ለ. ሶስት ብር ከሃምሳ ሳነቲም…………… 3.50

፪. ሁለት ነጥብ (፡)፡- ሰዓትን ከደቂቃ ለመለየት ያገለግላል፡፡

ምሳሌ፡- 4፡30 ሰዓት

ከዚህም በተጨማሪ በእጅ ጽሁፍ ውስጥ ቃልን ከቃል ለመለየት ያስችላል፡፡

አማርኛ (፱ኛ) ክፍል

(፱ኛ) ክፍል አማርኛ ቋንቋ

፫. ሁለት ነጥብ ከሰረዝ (፡-) መሪ ሃሳቡን ተከትለው የሚመጡ ዝርዝር ነገሮች

መኖራቸውን ለማመልክት ያገለግላል፡፡

ምሳሌ፡- ምግቦች ከሚሰጡት ጥቅም አንጻር በተለያዩ ክፍሎች ይመደባሉ፡፡

ከነዚህም ውስጥ፡- በሽታ ተከላካይ

ገምቢ

ኃይልና ሙቀት ሰጭ ናቸዉ፡፡

፬. ነጠላ ሰረዝ (፣)፡- የተለያዩ ተግባራት አሉት፡፡

ሀ. ተመሳሳይ ሙያ ያላቸውን ተከታታይ ቃላት ለመለየት ያገለግላል፡፡

ምሳሌ፡- ሆቴላችን የምግብ፣ የመጠጥ፣ የመኝታ እና የመዝናኛ አገልገሎቶች


ይሰጣል፡፡

ለ. በተከታታይ የሚመጡ ንዑሳን ሀረጎችን ለመለየት ያገለግላል፡፡

ምሳሌ፡- ባለፈው ክፍለ ጊዜ ትምህርት ስለውይይት መመሪያ፣ ስለዐረፍተ

ነገር ዓይነቶች፣ ስለአንቀፅ ምንነት እና ስለሥርዓተ ነጥቦች

አገልግሎት ተምራችኋል፡፡

ሐ. በዐረፍተ ነገር ውስጥ የባለቤት ተጣማሪን ለይቶ ለማመልከት ያገለገላል፡፡

ምሣሌ፡- አቶ ሙሃመድ፣ ጎበዙ ነጋዴ፣ ብዙ ትርፍ አገኘ፡፡

፭. ድርብ ሰረዝ (፤)፡- ተያያዥነት ያላቸውን፣ ራሳቸውን ችለው ሊነገሩ የሚችሉ

ሁለት እና በላይ ዐረፍተ ነገሮች አያይዞ ለማቅረብ ያገለግላል፡፡

ምሳሌ፡- ትምህረቷን በሚገባ ታጠናለች፤ የዕረፍት ጊዜዋን ባግባቡ

ትጠቀማለች፤ ወላጆቿንም በስራ ታግዛለች፡፡

፮. ነጠብጣብ /ሶስት ነጥብ/ (…)

አማርኛ (፱ኛ) ክፍል

(፱ኛ) ክፍል አማርኛ ቋንቋ

ሀ. በአንድ ጽሁፍ ወይም ጥቅስ ውስጥ የተወሰነ ሃሳብ ተቀንሶ መቅረቱን

ለማመልከት ያገለግላል፡፡

ምሳሌ፡- “…. ያለበት ዝላይ አይችልም፡፡”

ለ. ተመሰሳይ ነገሮች የሚቀጥሉ መሆናቸውን ለማመልከት (ወዘተ. ለማለት)

ያገለግላል፡፡

ምሳሌ፡- ከወር ደሞዙ ቀንሶ ለቤት አስቤዛ ምስር፣ ዘይት፣ ሽንኩርት፣

ቲማቲም… ገዛ፡፡

፯. ድርብ ትምህርተ ጥቅስ ( “ ”)፡- በጽሁፍ ውስጥ ሀሳቡ የሌላ ሰው መሆኑን

ለማሳየት፣ የተውሶ ቃላትን ለይቶ ለማመልከት፣ ጸሀፊው በትርጉማቸው

የማያምንባቸውን አባባሎች ለይቶ ለማሳየት፣ በጽሁፍ ውስጥ የሰዎችን ቃለ

ምልልስ ቀንብቦ ለማሳየት ያገለገላል፡፡

ለምሳሌ፡- ሀ. ምን አስቸኮለህ “ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ


ይፈታል” ሲባል አልሰማህም እንዴ!

ለ. ማንኛውም ነጋዴ “የቫት” ተጠቃሚ መሆን

አለበት፡፡

ሐ. ፈላስፋው “እብድ” ሲባል ኖሮ ከአካባቢው ተሰወረ፡፡

መ. ሰላም “ምነው ጠፋህ በሰላም ነው?”

“ባክሽ ሰሞኑን የሆነ ችግር ገጥሞኝ ነበር፡፡”

፰. አራት ነጥብ (፡፡)፡- ዐረፍተ ነገሩ ማለቁን ወይም መቋጨቱን ያሳያል፡፡

ምሳሌ፡- ልጆች ጨዋታ ይወዳሉ፡፡

፱. ትዕምርተ አንክሮ (!)፡- መገረምንና መደነቅን፣ ግዴታንና ትዕዛዝን፣ ማሞካሸትና

ማድነቅን፣ ለቅሶና ጩኸትን፣ ወዘተ. ለማመልከት ያገለግላል፡፡

ምሳሌ፡- “ይች ልጅ ተመረቀች እንዴ!” (መገረም እና መደነቅ)

ጎሽ! ደግ አደረጉ! (ማሞካሸትና ማድነቅ)

ሁሉም ተማሪ የቤት ስራውን መስራት አለበት! (ግዴታና ትዕዛዝ)

ኡኡ! እርዱኝ! እርዱኝ! (ለቅሶና ጩኸት)

፲. ጥያቄ ምልክት(?) ዐረፍተ ነገሩ በጥያቄ መልክ የቀረበ መሆኑን ያመለክታል፡፡

ምሳሌ፡- እዚህ ክፍል ስንት ተማሪዎች አሉ?

፲፩. ቅንፍ ( )፡- በዐረፍተ ነገር ውስጥ ወይም የሚለውን ቃል ተክቶ ይገባል፡፡

ምሳሌ፡- የበኩር ልጄ (የመጀመሪያ ልጄ) በህክምና ሙያ ተመረቀች፡፡

፲፪. ትዕምርተ ስላቅ (i)፡- ምፀትን፣ ቀልድንና ተሳልቆን ያመለክታል፡፡

ምሳሌ፡- ሀ. አቤት ውፍረት i በር አያስገባትም እኮ i (በጣም ቀጭን የሆነችን ልጅ -ምፀት)

ለ. ተያይዘን ወደማርስ ነዋ i ----› ቀልድ

ሐ. አጥንተህ ልብህ ውልቅ ብሏል i ----› ተሳልቆ

፲፫. እዝባር/አቆለቋይ (/ )፡- የተለያዩ አገልግሎቶች አሉት፡፡

ሀ. ቃልን አሳጥሮ ለመፃፍ

ምሳሌ፡- ትምህርት ቤት = ት/ቤት

ለ. ተራ ቁጥሮችን ወይም ቅደም ተከተሎችን የሚያሳዩትን ሆሂያትና ቁጥሮች


ለመለየት

ምሳሌ፡- ሀ/፣ 1/

ሐ. የመስሪያ ቤት ደብዳቤን መለያ ቁጥሮችንና ዓመተ ምህረትን ለመለየት

ምሳሌ፡- ቀን 12/12/2013 ዓ.ም.

፲፬. ሰረዝ/ጭረት ( _ )፡- ንዑስና ዓቢይ ተብሎ በሁለት ይከፈላል፡፡

፩. ንዑስ ሰረዝ (-)፡-

ሀ. ጥምር ቃላትን ለማመልከት ያገለግላል፡፡

ምሳሌ፡- ቃለ-ጉባኤ

ለ. ዝርዝር ነጥቦችን ለብቻ ለማሳየት

ምሳሌ፡- የቋንቋ ትምህርት ዋና ዋና ዓላማዎች ተማሪዎች፡--የማዳመጥ ክሂል

- የመናገር ክሂል

- የማንበብ ክሂል

- የመጻፍ ክሂል ማጎልበት እንዲሁም

- የስነ-ልሳንና የስነ-ጽሁፍ እዉቀትን ማዳበር ናቸው፡፡

፪. ዓቢይ ሰረዝ (–)፡- “እስከ” የሚለውን ቃል ለመተካት ያገለግላል፡፡

ምሳሌ፡- መንገዱ ከፒያሳ – ሜክሲኮ ተዘጋግቷል፡፡

፲፭. እሩይ (= )፡- እኩል ወይም ተመሳሳይ መሆንን ያመለክታል፡፡

ምሳሌ፡- ባላ = ተመገበ፣ 2+4=6

፲፮. እመጫት (^)፡- በእጅ ጽሁፍ ውስጥ አርትኦት ሲሰራ የተዘለለውን ፊደል፣ ቃል፣

ሐረግ ወይም ዐረፍተ ነገር ለማስገባት አቅጣጫ ተቋሚ በመሆን ያገለግላል፡፡

የማጣቀሻ መጻሕፍት

ደረጀ ገብሬ (1996) ተግባራ የጽሕፈት መማሪያ

You might also like