Professional Documents
Culture Documents
ስምዖን
ስምዖን
#እግዚአብሔርንም እየባረከ እንዲህ አለ:-'#ጌታ ሆይ! አሁን እንደ ቃልህ ባሪያህን በሰላም# ታሰናብተዋለህ:: ዓይኖቼ
በሰዎች ሁሉ ፊት #ያዘጋጀኸውን ማዳንህን አይተዋልና:: ይህም ለአሕዛብ ሁሉን የሚገልጥ ብርሃን: #ለሕዝብሕም
ለእስራኤል ክብር ነው::' #ዮሴፍና እናቱም ስለ እርሱ በተባለው #ነገር ይደነቁ ነበር:: "[ሉቃ. 2:27]
#እንኳን_አደረሳቹሁ_የእምየ_ተዋሕዶ_ልጆች
#በዓለ #ስምዖን🙏🕯
#ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደ በስምንተኛው ቀን (ጥር ፮ ቀን) በኦሪቱ ሕግ መሠረት ሥርዓተ
ግዝረትን ፈጽሟል በተወለደ በዐርባኛ ቀኑ (የካቲት ፰ ቀን) ደግሞ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቷል (ጌታችንመድኀኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ከተወለደበት ከታኅሣሥ ፳፱ቀን ጀምረን ስንቈጥር የካቲት ፰ /፵ቀን ነው ፡፡)
በኦሪቱ ሥርዓትም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና ጠባቂዋ ጻድቁ ዮሴፍ ለመሥዋዕት የሚቀርቡ
#እንስሳትን ይዘው ጌታችንን በዚህች ዕለት ወደ ቤተ #መቅደስ ወሰዱት ፡፡
በዚያም ክርስቶስ ኢየሱስን ሳያይ #እንደማይሞት የተነገረው ስምዖን የሚባል ሰው ነበር ይህስ እንደምንነው ? ቢሉ
የኦሪት መጻሕፍትን ከዕብራይስጥ ወደ ጽርዕ (ግሪክ) ቋንቋ እንዲተረጕሙ ከታዘዙ ሰብዓ ሰዎች (ሊቃናት) መካከል
አንዱ ነቢዩ ስምዖን ነበር ።
ይህ ነቢይ ትንቢተ ኢሳይያስ ደረሰውና እየተረጐመ ሳለ ‹‹እነሆ ድንግል #ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅንም ትወልዳለች
ስሙንም ዐማኑኤል ትለዋለች » ከሚለው ኀይለ ቃል በደረሰ ጊዜ በቀጥታ ቢተረጕመው ንጉሡ እንደማይቀበለው
በማሰቡ፤ እርሱም ‹‹ይህ እንዴት ሊኾን ይችላል?›› ብሎ በመጠራጠሩ #ድንግል›› የሚለውን ቃል ወለት›› (#ሴት
ልጅ) ብሎ ተረጐመው፡፡
ተኝቶ በነቃ ጊዜም #ወለት›› የሚለው ቃል ተፍቆ #ድንግል›› ተብሎ ተጽፎ አገኘና እርሱም ‹‹ድንግል››ን ፍቆ
‹‹ወለት›› ብሎ ይጽፋል ዳግመኛም ለሁለተኛና ጊዜ ተኝቶ ሲነቃ ቃሉ እንደ ነበረ ኾኖ ያገኘዋል ፡፡
ለሦስተኛ ጊዜ ቃሉን እፍቃለሁ ሲልም የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦ ‹‹የተጠራጠርኸውን፣ ከድንግል የሚወለደው
ክርስቶስን #እስከምታየውና እስከምትታቀፈው ድረስ #ሞትን_አትቀምስም፤ብሎታል፡፡
#መሲሑን ሳታይ አትሞት የተባለው ነቢዩ ስምዖን አርጅቶ ከአልጋ ተጣብቆ ለሦስት መቶ ዓመታት ያህል ከኖረ በኋላ
ትንቢቱ ተፈጽሞ፣ ዘመኑ ደርሶ ክርስቶስ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በተወለደ #በ፵ ቀን ወደ ቤተ
መቅደስ እስከ በገባበት ዕለት መንፈስ ቅዱስ አነሳሥቶ ወደ ምኵራብ ወሰደው፡፡
ነቢዩም #የእግዚአብሔርን #ማዳን በዓይኑ በማየቱ፣ ከደዌው በመፈወሱ እና ከእርጅናው በመታደሱ በአጠቃላይ
በተደረገለት ድንቅ #ተአምር ዅሉ በመደሰቱ እግዚአብሔርን አመስግኗል፡፡
አቤቱ ባሪያህን ዛሬ አሰናብተኝ፤ ዓይኖቼ ማዳንህን አይተዋልና ፤ በሚለው ትንቢታዊ መዝሙሩም #የእግዚአብሔርን
ማዳን በዓይኔ ስላየሁ #እንግዲህስ ልረፍ በማለት ሞቱን #ተማጽኗል፡፡
🥀ወስብሐት ለእግዚአብሔር ❤🍃
ተዋሕዶን እንወቅ።:
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖
✝አይሁድ ክፋተኞች መሆናቸውን ሰምቷልና 36 ድንኩዋን አዘጋጅቶ፥ ጥንድ ጥንድ ሆነው እንዲሠሩ፥ ሲተረጉሙ
እንዳይመካከሩ 36 ጠባቂዎችን ሾመባቸው። ይህ ነገር ለጊዜው ከንጉሡ ቢመስልም ጥበቡ ግን ከእግዚአብሔር ነው።
ምክንያቱም በጊዜ ሒደት መጻሕፍተ ብሉያት በአደጋ እንደሚጠፉ ያውቃልና ሳይበረዙ ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች
ለእኛ እንዲደርሱ ነው። ስለዚህም ከክርስቶስ ልደት 284 ዓመት በፊት 46 ቱም ሁሉም መጻሕፍት (ብሉያት)
ከእብራይስጥ ወደ ጽርዕ ልሳን በ 70 ው ሊቃናት አማካኝነት ተተረጐሙ። (በእርግጥ ከዚያ አስቀድሞ መጻሕፍት
(ብሉያት) ወደ ሃገራችን መምጣቸውና ወደ ግዕዝ ልሳን መተርጐማቸውን ሳንዘነጋ ማለት ነው) ወደ ዋናው ጉዳያችን
ስንመለስ ከ 70 ው ሊቃናት መካከል በእድሜው አረጋዊ የሆነ (እንደ ትውፊቱ ከሆነ 216 ዓመት የሆነው) ስምዖን
የሚሉት ምሑረ ኦሪት ነበር። በፈቃደ እግዚአብሔር ለእርሱ መጽሐፈ ትንቢተ ኢሳይያስ ደርሶት እየተረጐመ
ምዕራፍ 7 ላይ ደረሰ።
✝ቁጥር 7 ላይ ሲደርስ ግን "ናሁ ድንግል ትጸንስ፥ ወትወልድ ወልደ" የሚል አይቶ "አሁን እንኳን የአሕዛብ ንጉሥ
የእሥራኤልስ ቢሆን ድንግል በድንግልና ጸንሳ ትወልዳለች ብለው እንዴት ያምነኛል !" ሲል አሰበ። "በዚያውስ ላይ
ኢሳይያስ በምናሴ የተገደለው ስለዚህ አይደል!" ብሎ ቃሉን ሊለውጠው ወሰነ። አመሻሽ ላይም 'ድንግል' የሚለውን
'ወለት-ሴት ልጅ' ብሎ ቀየረው። እርሱ ሲያንቀላፋ ቅዱስ መልአክ ወርዶ 'ድንግል' ብሎ አስተካከለው። ከእንቅልፉ
ሲነቃ ግራ ተጋብቶ እንደ ገና ፍቆ ቀየረው። አሁንም መልአኩ 'ድንግል' ሲል ቀየረበት። 3 ጊዜ እንዲህ ከሆነ በኋላ ግን
መልአኩ ተገልጦ ገሰጸው። በዚያውም ላይ "ይህችን ድንግልና መሲሑን ልጇን ሳታየውና ሳትታቀፈው ሞትን
አታይም" ብሎት ተሰወረው። አረጋዊ ስምዖን ከዚያች ዕለት በኋላ የመድኅን ክርስቶስን መምጣት ሲጠብቅ ለ 284
ዓመታት የአልጋ ቁራኛ ሁኖ ኖረ። አካሉም አለቀ።
✝ለስም አጠራሩ ስግደት የሚገባው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው በሆነበት በዚያ ሰሞን እመቤታችን ቅድስት
ድንግል ማርያምና ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ ወደ ቤተ መቅደስ ወጡ። ሕግን የሠራ ጌታ እርሱ 'ፈጻሜ ሕግ' ይባል ዘንድ
የርግብ ግልገሎችን (ዋኖሶችን) ይዘው በተወለደ በ 40 ቀኑ ወደ ቤተ መቅደስ አስገቡት። በዚህች ቀንም ቅዱስ መልአክ
መጥቶ ቅዱስ ስምዖንን ከአልጋው ቀሰቀሰው። ተስፋ የሚያደርገው አዳኙ (መሲሑ) እንደ መጣም ነገረው። ይህን
ጊዜ አረጋዊው አካሉ ታድሶ እንደ 30 ዓመት ወጣት እመር ብሎ ከአልጋው ተነሳ። እንደ በቅሎ እየሠገረም ወደ
መቅደስ ወጣ። በዚያ መሲሑን (ፈጣሪውን) ሲመለከት እንደ እንቦሳ ዘለለ። ቀረብ ብሎም ሕጻን ጌታን ከድንግል እናቱ
እጅ ተቀበለው። ከደስታው ብዛት የተነሳም "ይእዜ ትስዕሮ ለገብርከ፥ በሰላም እግዚኦ በከመ አዘዝከ - አቤቱ ባሪያህን
እንደ ቃልህ በሰላም አሰናብተው" ሲል ጸለየ። ትንቢትንም ተናገረ። በዚያችው ዕለትም ዐርፎ ተቀበረ።
✝ዳግመኛ በዚህች ቀን አረጋዊቷን ነቢይት ቅድስት ሐናን እናስባለን። ይህች ቅድስት ትውልዷ ከነገደ አሴር ሲሆን
አባቷ ፋኑኤል ይባላል። በትውፊት ትምሕርት ሐና የተዳረችው በልጅነቷ (በ 12 /15/ ዓመቷ) ነው። ለ 7 ዓመታት
ከልጅነት ባሏ ጋር ኖራ ዕድሜዋ 19 (22) ሲደርስ ሞተባት። እንደ እሥራኤል ልማድ ሌላ እንድታገባ ብትጠየቅም
'እንቢ' ብላ መበለት ሆነች። ራሷንም ለእግዚአብሔር አሳልፋ ሰጠች። በቤተ መቅደስም ለ 84 ዓመታት ለፈጣሪዋ
ተገዛች። ፈጽማ ትጸልይና ትጾም ነበርና በእነዚህ ሁሉ ዓመታት ውጪውን አልተመለከተችም። ለእርሷ 103 (106)
ዓመት ሲሆን መድኃኒታችን ተወለደ። በዚህች ቀን ወደ ቤተ መቅደስ ሲገባ ተመልክታም ጌታን ባረከች። ደስ
እያላትም ትንቢትን ተናገረች። ወደ ቤቷ ገብታም ነፍሷን ሰጠች። (ሉቃ. 2፥ 36-38)
❖አረጋዊ ስምዖንን ከድካም አልጋ ያነሳ አምላከ ቅዱሳን እኛንም ድካመ ነፍስን ከሚያመጣ የበደል ምኝታ በቸርነቱ
ያንሳን። ቸሩ መድኃኒታችን ተርፎ ከሚቀረው ዘመን ዕድሜ ለንስሃ፥ ዘመን ለፍሥሐ አይንሳን። ከቅዱሳኑ በረከትም
አይለየን።
✝ ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
2.ኪሩቤል (አርባዕቱ እንስሳ)
3.አባ ብሶይ (ቢሾይ)
4.አቡነ ኪሮስ
5.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን
6.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ 12 ቱ ሐዋርያት)
✝✝"✝ እንደ ሕጉ ልማድ ያደርጉለት ዘንድ ሕጻኑን ጌታ ኢየሱስን በአስገቡት ጊዜ እርሱ ደግሞ ተቀብሎ አቀፈው።
እግዚአብሔርንም እየባረከ እንዲህ አለ፤ 'ጌታ ሆይ! አሁን እንደ ቃልህ ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ። ዓይኖቼ
በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን ማዳንህን አይተዋልና። ይህም ለአሕዛብ ሁሉን የሚገልጥ ብርሃን፥ ለሕዝብሕም
ለእስራኤል ክብር ነው። ' ዮሴፍና እናቱም ስለ እርሱ በተባለው ነገር ይደነቁ ነበር። ✝"✝ (ሉቃ. 2፥ 27)
. ዓ ይ ኖ ቼ፡ማ ዳ ን ህ ን፡አ ይ ተ ዋ ል ና
༺◉❖═───◉●◉◉●◉────═❖◉༻
በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ #የካቲት_8 ቀን ከሚከበሩ በዓላት መካከል የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ወደ ቤተ መቅደስ መግባት፣ የነቢዩ ስምዖን ልደት (መታደስ) እና የነቢዪት ሐና ዕረፍት በስፋት ይነገራል ፡፡
ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደ በስምንተኛው ቀን (ጥር 6 ቀን) በኦሪቱ ሕግ መሠረት ሥርዓተ
ግዝረትን ፈጽሟል በተወለደ በዐርባኛ ቀኑ (የካቲት 8 ቀን) ደግሞ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቷል (ጌታችንና መድኀኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ከተወለደበት ከታኅሣሥ 29 ቀን ጀምረን ስንቈጥር የካቲት 8 ዐርባኛው ቀን ነው፡፡)
በኦሪቱ ሥርዓትም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና ጠባቂዋ ጻድቁ ዮሴፍ ለመሥዋዕት የሚቀርቡ
እንስሳትን ይዘው ጌታችንን በዚህች ዕለት ወደ ቤተ መቅደስ ወሰዱት፡፡
በዚያም ክርስቶስ ኢየሱስን ሳያይ እንደማይሞት የተነገረው ስምዖን የሚባል ሰው ነበር ይህስ እንደምንነው ? ቢሉ
የኦሪት መጻሕፍትን ከዕብራይስጥ ወደ ጽርዕ (ግሪክ) ቋንቋ እንዲተረጕሙ ከታዘዙ ሰብዓ ሰዎች (ሊቃናት) መካከል
አንዱ ነቢዩ ስምዖን ነበር ።
ይህ ነቢይ ትንቢተ ኢሳይያስ ደረሰውና እየተረጐመ ሳለ ‹‹እነሆ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅንም ትወልዳለች
ስሙንም ዐማኑኤል ትለዋለች » ከሚለው ኀይለ ቃል በደረሰ ጊዜ በቀጥታ ቢተረጕመው ንጉሡ እንደማይቀበለው
በማሰቡ፤ እርሱም ‹‹ይህ እንዴት ሊኾን ይችላል?›› ብሎ በመጠራጠሩ ‹‹ድንግል›› የሚለውን ቃል ‹‹ወለት››
(ሴት ልጅ) ብሎ ተረጐመው፡፡
ተኝቶ በነቃ ጊዜም ‹‹ወለት›› የሚለው ቃል ተፍቆ ‹‹ድንግል›› ተብሎ ተጽፎ አገኘና እርሱም ‹‹ድንግል››ን ፍቆ
‹‹ወለት›› ብሎ ይጽፋል ዳግመኛም ለሁለተኛና ጊዜ ተኝቶ ሲነቃ ቃሉ እንደ ነበረ ኾኖ ያገኘዋል ፡፡
ለሦስተኛ ጊዜ ቃሉን እፍቃለሁ ሲልም የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦ ‹‹የተጠራጠርኸውን፣ ከድንግል የሚወለደው
ክርስቶስን እስከምታየውና እስከምትታቀፈው ድረስ ሞትን አትቀምስም፤›› ብሎታል፡፡
‹‹መሲሑን ሳታይ አትሞትም›› የተባለው ነቢዩ ስምዖን አርጅቶ ከአልጋ ተጣብቆ ለሦስት መቶ ዓመታት ያህል
ከኖረ በኋላ ትንቢቱ ተፈጽሞ፣ ዘመኑ ደርሶ ክርስቶስ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በተወለደ በዐርባኛው
ቀን ወደ ቤተ መቅደስ እስከ በገባበት ዕለት መንፈስ ቅዱስ አነሳሥቶ ወደ ምኵራብ ወሰደው፡፡
ነቢዩም የእግዚአብሔርን ማዳን በዓይኑ በማየቱ፣ ከደዌው በመፈወሱ እና ከእርጅናው በመታደሱ በአጠቃላይ
በተደረገለት ድንቅ ተአምር ዅሉ በመደሰቱ እግዚአብሔርን አመስግኗል፡፡
የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ለነቢዩ ስምዖን የተደረገለትን ታላቅ ሥራ ሲያደንቁ እንዲህ ይገልጹታል፤ ‹‹የማኅሌት
መዝሙርን በማዘጋጀት እያከበርሁትና እያደነቅሁት ከሱራፌል ክብር ለሚበልጠው ለስምዖን ክብር ሰላም እላለሁ፡፡
እርሱ መለኮትን በእጁ ታቅፏል፤ እሳቱንም ዳሷልና እቅፎቹን እጅ እነሳለሁ፤ እጆቹንም እስማለሁ።››
+ #እርቃንን_አለመሸፈን +
መልካም ስላልሆነው አለባበስ "ሊቁ ዲዲሞስ" ከአዳምና ሔዋን በቅጠል እርቃናቸውን ከመሸፈናቸው ጋር በማያያዝ
ጣፍጭ ፍቺ ይሰጠናል አንዲህ ይላል ፦ ‹‹ አዳምና ሔዋን የበለስን ቅጠል ማገልደማቸው ኃጢአታቸውን ቀላል
ለማድረግ ለመደበቅ የሚያደርጉትን ትግል የሚያሳይ ነው።›› አኹን ኹላችንም ለሰራነው ኃጢአት የምንሰጠው
ሽፍን ቀለል ያለ አይደለምን? በማለት ሊቁ ይጠይቃል። በእርግጥ አኹን ኹላችንም ብንኾን አእምሯችን
በኃጢአታችን ምክንያት ስለታወረብን ከፍ አድርገን ማልቀስ ንስሐ መግባት ሲገባን "ችግር የለውም ቀላል ነው"
በሚል በሸታ ሕሊናችን ቆስሎ ከገባንበት የኃጢአት ጉድጓድ መውጣት አቅቶን ስንቅበዘበዝ እንታያለን። ያልሰራነው
የኃጢአት ስራ የለም ኾኖም ነገሮችን በሙሉ ቅጣት እንደማይገባቸው ተራ ክስተት አድርገን ለራሳችን ራሳችንን
እያሳመንን እንገኛለን።
ድኅነት ተራ ነገር አይደለም፤ በብዙ መከራና ጭንቅ የሚገኝ የማያልቅ ፀጋ እንጂ። እኅቴ ሆይ! ለወንድምሽ መሰናክል
ምክንያት ትኾኚ ዘንድ እንዴት መረጥሽ? የራስሽን ፈቃድ ከምትወጂ የክርስቶስን ፍቃድ ብትወጂስ አይሻልሽምን ?
ስለወንድምሽ ብለሽ ብቻ ሳይኾን ስለ አምላክሽ ብለሽ ኃጢአትሽን ቀላል አድርገሽ አታስቢ፥ ይልቁንም ከልብሽ
በድርጊትሽ ተጸጽተሽ ክርስቶስን ይምርሽ ዘንድ ጠይቂ። (መጽሔተ ወራዙት ዘኦርቶዶክስ ዲያቆን ዮሐንስ ጌታቸው
ገጽ-86)
#ይህን_ቃል_አስታውሱ! “ከነዚህ ከታናናሾች አንዱን ከማሰናከል ይልቅ የወፍጮ ድንጋይ በዐንገቱ ታስሮ ወደባሕር
ቢጣል ይሻለው ነበር።” [ማቴ. 18፥6፤ ማር. 9፥42፤ ሉቃ. 17፥2]
##########
ተሰናባቹ ሽማግሌ
https://janderebaw.org/ተሰናባቹ-ሽማግሌ/
#######
ወበጽባህ አሌሊ ገይሰ ኀበ ቤተ ክርስቲያን
❤በጥዋት ተነስተህ ወደቤተ ክርስቲያን ሂድ
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የምታገኘው በቤተ መቅደስ ውስጥ ነውና በጧት ከመኝታህ ተነስተህ ወደቤተ ክርስቲያን
ገስግስ
✍የ 300 ዓመት እድሜ ባለጸገው ስምዖን ጌታችንን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመቅደሱ ውስጥ አግኝቶ
አቅፎታል
✍ካህኑ ዘካርያስ ያረጀችው ሚስቱ ኤልሳቤጥ ጸንሳ እንደምትዎልድ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል የነገረው በቤተ መቅደሱ
ውስጥ ነው
✍እመቤታችን ድንግል ማርያም ሰማያዊ ምግብ እና ሰማያዊ መጠጥ መልአኩ ያመጣላት በቤተ መቅደሱ ስትኖር ነው
✍ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ሐርና ወርቁን እያስማመች በቤተ መቅደሱ ስትፈትል አምላኳን እንድትዎልድ
መልአኩ አብስሯታል
✍እግሩ ሽባ ሁኖበት በቤተ መቅደሱ በር ወድቆ ሲለምን የነበረው ሰው ጴጥሮስና ዮሐንስ ለጸሎት ወደመቅደሱ
ሲሔዱ አግኝተው ፈውሰውታል
*ፈውስ ለማግኘት
*አዲስ ብስራት ለመስማት
*ሰማያዊ ምግብ ለማግኘት
*የጸለይከውን ጸሎት ለመሰማት
*ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለማግኘት
በጧት ተነስተህ ወደቤተ ክርስቲያን ሂድ
ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ እንዳለው ደዊት ወደቤተ ክርስቲያን በመሄድህ ደስ ይበልህ
መጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ