Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 4

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ራስን መግዛት
አራት የድርም ጓዯኛማቾች የተሇያየ ፀባይን ተሊብሰው በአንዱቷ ድርማቸው ይኖራለ፡፡ ፈቃደ
ሇትምህርቱ ትሌቅ ትኩረት ከመስጠቱ የተነሣ ዘወትር በጥናት ይጠመዲሌ፡፡ ብርሃኑ ኳስ
በመጫወትና በማየት ከክፍሌና ከጥናት ውጪ ያሇውን ጊዜውን ያሳሌፋሌ፡፡ አንተነህ ዯግሞ
ቀሌዴ የሚያበዛና ፊሌምን ማየት የሚያዘወትር ነው፡፡ አስማማው የቤተ-ክርስቲያን አገሌጋይ
ሲሆን ሇትምህርቱም ጊዜውን በአግባቡ ያውሊሌ፡፡

ትእይንት 1
(ከንጋቱ 12 ሰዓት)

ፈቃደ፡- /አስማማው ከድርም ሲወጣ ተመሇከተና ፈቃደ ከአሌጋው ብዴግ ብል ተነሥቶ


ጥናቱን ጀመረ፡፡ እጆቹን እያወራጨና እያሰሊሰ ያጠናሌ፡፡ በመሀሌ ይቆምና ያጠናውን እየተናገረ
በድርሙ ይዘዋወራሌ፡፡/ . . . ‹‹Formoterol and Salmoterol for nocturnal asthma . . .
ኧ ኸ . . . epinephrine should not be given at nerve endings. . .

/የፈቃደ ዴምፅ የቀሰቀሰው ብርሃኑ ይነቃና/

- ብርሃኑ፡- ፍቄ ዛሬ ቀኑ ምንዴንነው?
- አንተነህ፡- /በአሌጋው ሊይ እንዯመንጎራዯዴ ይሌና/ እንዳት ይጠፋሻሌ! ሐሙስ የቀን
ቅደስ፤ ይሌሻሌ፡፡ ነይ እስቲ ብሬ መቀዯሱን እንጀምረው አንዴ ጌም እንጫወት፡፡
- ፈቃደ፡- ፈተና ዯርሷሌ፤ ማጥናት ይሻሇሀሌ፡፡ ፋርማ አይቸከሌም ጊዜ ይፈሌጋሌ፡፡
- አንተነህ፡- /የፈቃደን ንግግር ተቀብል/ ዯሞ ቢቸከሌም ነገዉ ይጠፋሌ፡፡
- ብርሃኑ፡- ከሰዓት የምቸክሇው ፋርማ ነው፤ ባይሆን ፍቄ ምንዴንነው ምታነቢው?
- ፈቃደ፡- ጉዴ ማን ተመችቶኛሌ፤ ስሊይደም አሪፍ ነው፡፡
- አንተነህ፡- ስሊይደን መቀሇም ነው ባክሽ፤ ላሊው እኮ አስተማሪዎቹም አያርፉትም፡፡
- ብርሃኑ፡- አንቺ ዯሞ ስሊይደ እንዱገባሽ መጽሐፍ ታነቢያሇሽ እንጂ በዚህ አጭር ጊዜ
አስተማሪዎቹን ሇመብሇጥ መሰሇሽ፡፡
- አንተነህ፡- ኤውሌሽ ብሬ ሜዱሲን ውስጥ የሚያስፈሌግሽ ውጤት እንጂ ዕውቀት
አይዯሇም፡፡ ስሊይዴ ዯሞ ፈተናውን ሇመሥራት በቂ ነው፡፡
- ፈቃደ፡- አንቴ ተፎግረሻሌ ነገ እኮ የምታክሚው በዕውቀትሽ ነው እንጂ በውጤት
አይዯሇም፡፡
- አንተነህ፡- ያኔማ ክሉኒካሌ ሲገባ ነው ነገሩ ፊጥ ሚዯረገው የአሁን ዕውቀት ምንም
አይጠቅምም፡፡
- ፈቃደ፡- አይ አንቴ አንቺ ገና አሌነቃሽም፤ መሽቶብሻሌ፤ የእውነት መሽቶብሻሌ፤ ዛሬ
የቋጠሩት ሇነገ ይሆናሌ ሲባሌ አሌሰማሽም፡፡
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

- ብርሃኑ፡- አይ ፍቄ ይህ አባባሌሽ እኮ ነው ብርቱ ያዯረገሽ፡፡ /ብርሃኑ ይህን ብል


የፈቃደን እጅ በአዴናቆት ሲመታ አስማማው ወዯ ድርም ይገባሌ፡፡/
- አስማማው፡- እንዳት አዯራችሁ?
- ፈቃደ፡- እግዚአብሔር ይመስገን
- አንተነህ፡- አስሜ አዴረናሌ እንዯ ጉዴ፣ እየተወንን በሙዴ፤
- አስማማው፡- ምን ማሇት ፈሌገሽ ነው?
- አንተነህ፡- ኧረ አሁን አይነገርም፤ ከፈተና በኋሊ ወይ ዯግሞ ጥናት ሲዯብረን
እነግርሻሇሁ፡፡
- አስማማው፡- ካሌክ ይሁን፤ ፈተና ግን መቼ ተወሰነ?
- ፈቃደ፡- Next week አርብ
- ብርሃኑ፡- በ ሇ ው. . . አንዴ ሳምንት ይጨመራሌ ተብል አሌነበር እንዳ?
- ፈቃደ፡- ዱኑ አይሆንም አሇ፤
- አንተነህ፡- ጉዴ መጣ አሇች ያሸብር እናት… ካፌ የሚሄዴ የሇም?
- ብርሃኑ፡- እንሂዴ ነይ…

/ብርሃኑና አንተነህ ይወጣለ፡፡ አስማማው ኮምፒዉተሩን እየከፈተ…/

- ፈቃደ፡- ክሊስ እስክንገባ ትንሽ እናዴማ፤ ምን ይመስሌሻሌ፤

- አስማማው፡- የኔም ዕቅዴ እሱ ነው፡፡

/አስማማውና ፈቃደ ጥናታቸውን ቀጠለ፡፡ … በመሀሌ ይጠያየቃለ አንደ አንደን


ያስረዲሌ፤… ከጥቂት ቆይታ በኋሊ ብርሃኑና አንተነህ ከላሊ ድርም ጓዯኛቸው ከእንዲሻው
ጋር ስሇኳስ እያወሩ ወዯ ድርም ይመጣለ፡፡/

- ብርሃኑ፡- ሩኒ የመታት ኳስ!... ሩኒ የመታት ኳስ!... በሕይወቴ እንዱህ ያሇ ጎሌ አይቼ


አሊውቅም! /በአንክሮ ይናገራሌ/
- እንዲሻው፡- በጣም ይገርማሌ! በረኛው ብቻ አይዯሇም አርሰን ቬንገር ከነ ተጫዋቾቹ
ፈዘዘ እኮ! በስመ አብ… /ይህን እያወሩ ወዯ ድርም ይገባለ፤/
- አንተንህ፡- አሁን ስንት ሰዓት ነው? /እያሇ የፈቃደን ሊፕቶፕ ጎንበስ ብል ተመሇከተና/
ሇክሊስ 20 ዯቂቃ ብቻ ነው የሚቀረን ብሬ እስከዛ አንዴ ጌም…
- ብርሃኑ፡- የማታው ሽንፈት አሌበቃህም? /ብል ከአንተነህ ጋር በኮምፒዉተር ጌም
ሉጫወቱ ጎን ሇጎን ይቀመጣለ/
- እንዲሻው፡- ዲኛ ነኝ /ብል ከጎናቸው ይቀመጣሌ/
/3 ሰዓት ሲሞሊ ሁለም ክፍሌ ሇመግባት ሲወጣ አንተነህ ‹‹ሊጥና ባክህ፤ ብዙ
ይቀረኛሌ/ ብል ጠረጴዛ ሊይ ሇማጥናት ይቀመጣሌ/
/ከድርም እየወጡና እየሄደ ሳሇ/
- አስማማው፡- በነገራችን ሊይ ዛሬ 12 ሰዓት ሊይ ጉባኤ እንዲሇ አሌረሳችሁም አይዯሌ?
- ብርሃኑ፡- 11 ሰዓት ኳስ እጫወታሇሁ፤ ከዚያ እስከ 12 ብጨርስም ስሇሚዯክመኝ
የምመጣ አይመስሇኝም፡
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

- ፈቃደ፡- ኦ ዛሬ መከሇስ አሇብኝ አስሜ አይመቸኝም፡፡


- አስማማው፡- ባትቀሩ ጥሩ ነው…

ትእይንት 2
(ከሳምንት በኋሊ ከፈተና መሌስ)

/ አስማማው ወንበር ሊይ ቁጭ ብል ከቀናት በፊት የጀመራትን መንፈሳዊ መጽሐፉን


ያነባሌ፡፡ ብርሃኑ ሇስፖርት የምትሆነውን ሌብስ እየሇበሰ ነው፤ አንተነህ ዯግሞ አሌጋው
ሊይ ተዘርሯሌ፡፡ ፈቃደ በሩን በርግድ ይገባና/
- ፈቃደ፡- ወይኔ ተመታሁ!
- አንተነህ፡- /ከአሌጋው እንዯመነሳት እያሇ/ ማን መታሽ ፍቄ? /ጓዯኞቹ ሲስቁ ተመሌክቶ/
ወይኔ ፈቃደ ፍቄ፣ ተመታሁ እሊሇሁ ባሇመነቅነቄ፤
- ፈቃደ፡- /እንዯ መበሳጨት ይሌና/ አንተ ዯሞ ሁላ ትቀሌዲሇህ፡፡ አጥንቼ እንዲሊጠናሁ፤
ጨፍጭፌዋሇሁ ስሌ ጨፍጨፎ ሇቀቀኝ…ኡህ…/ እያሇ በኃይሌ ሲተነፍስ/
- አስማማው፡- ፍቄ ተረጋጋ አንዲንዳ ይገጥማሌ፤ ፈተናው ዯግሞ ሇሁለም ከባዴ ስሇነበር
ሃሳብ አይግባህ፡፡
- ፈቃደ፡- እንዲንተ እኮ የሚያረጋጋ ነው የጠፋው፡፡ አስሜ ግን እንዳት ነው ይህ
መረጋጋት ካንተ ተርፎ ሇሰው የሚሆነው?!!! ካንተ በሊይ ነው ያጠናሁት፤ነገር ግን
ያንተን ያህሌ መዯሰትና መረጋጋት አሌቻሌሁም፡፡
- አስማማው፡- በራሴ የተረጋጋሁና ዯስተኛ አይዯሇሁም ፍቄ፤ ቤተ-ክርስቲያን የምትሇግሰኝ
የዘወትር ምግብና መጠጤ ይህ ነው፡፡ ቤተ-ክርስቲያን የምሄዯው ጊዜዬን ሇማጥፋት ወይ
ዯግም ሇመዝናናት አይዯሇም፤ በርግጥ ቤተ-ክርስቲያን ሲኬዴ አእምሮ ነፃ ይሆናሌ፤
ከከተማ ወጥተህ ብትዝናና እንኳን የማታገኘው ነፃነት ይከበሀሌ፡፡ ከዚህ ባሻገር ቤተ-
ክርስቲያን እንዯጠራ መስታዎት ማንነትህን አጉሌታ ታሳየሀሇች፤ የምታስተምርህ
ሇመንገዴህ ብርሃን ሇሰውነትህ ፀዲሌ ነው፤ ሇሕይወትህም ታሊቅ ስንቅ ትቋጥርሌሀሇች፡፡
እስቲ ከዚህ መጽሐፍ አሁን ያነበብኩትን የአቡነ ሺኖዲ ምክር ሊንተም ሊንብብሌህ፡፡…
(‹‹የሕይወት መዏዛ›› ገጽ 49 የመጨረሻው አንቀጽ ያነብሇታሌ)
/እያነበበ ሳሇ ብርሃኑ መውጣቱን ትቶ አንተነህም ከአሌጋው ተነሥቶ አስማማውን
መስማት ጀመሩ/
- ብርሃኑ፡- መ ን ፈ ሳ ዊ ሕ ይ ወ ት ባ ን ተ ዘ ን ዴ ዋ ጋ ው ን አጥቷሌ፡፡
/ብርሃኑ እንዯመተከዝ ብል ቃሊቱን እየረገጠ አንገቱን እየነቀነቀ ይናገራሌ፡፡/
- ፈቃደ፡- የምትፈሌገውን ሁለ አግኝተህ ነፍስህ ብትጎዲ ሇአንተ ምንዴን ነው ጥቅሙ?
/አቀርቅሮ ይህንኑ ይዯግማሌ/
- /አንተነህ አቀርቅሮ መሬቱን እያየ ይቆያሌ/
- አስማማው፡- አሁን ቁም ነገር የጨበጣችሁ ይመስሇኛሌ ጓድች፡፡ ቤተ-ክርስቲያን ጥሩ
ንጹሕ መስታዎት ናት ማንነትህን ታሳየሀሇች ማሇቴ ሇዚህ ነው፡፡ ሰው ማሇት የሥጋና
የነፍስ ጥምር ነው፡፡ ጠዋት ተነሥተን ካፌ፣ ሇምሳም ካፌ፣ ሇራትም ካፌ ተመሊሌሰን
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ሇሥጋ የሚሆነን ምግብ መጠጥ እንዯምንፈሌገው፤ ሇነፍሳችንም ምግብና መጠጥ


መስጠት አሇብን፡፡ ነፍስ እንዯ ሥጋ ባትገዝፍም፤ ትራባሇች ዯግሞም ትጠማሇች፡፡ ራቧና
ጥሟን ሇማስታገሥ ዯግሞ ቤተ-ክርስቲያን ሄዯን ምግብና መጠጥ ሌንሸምትሊት
ይገባሌ፡፡ ጉባኤ እንከታተሌ ቤተ-ክርስቲያን እንሂዴ የምሊችሁ ሇዚህ ነው፡፡ ያሌተረዲነው
ነገር ካሇ ቀስ ብሇን እናውቀዋሇን፤ ሇኛ ተብል የሚዯረገው ዝግጅት ዯግሞ እኛ አቴንሽን
አንሰጠውም እንጂ እኛን የሚያስዯስት ነው፡፡
- አንተነህ፡- ዛሬ ጉባኤ አሇ አስሜ?
- አስማማው፡- አዎ፤ Post exam ብዙ ሰው ይመጣሌ ተብል ተዘጋጅቷሌ፡፡
- አንተነህ፡- ኧረ Post exam የሇ Before exam ከዛሬ ጀምር ጉባኤ on time ከች ነው፡፡
- ፈቃደ፡- አስሜ በጣም ነው የማመሰግነው፡፡ የሕይወቴን መሠረት የነገርከኝ መሰሇኝ፡፡
እንኳን ጉባኤን መታዯም አይዯሇም አብሬህ ማገሌገሌ እፈሌጋሇሁ፡፡
- አስማማው፡- ዯስተኛ ነኝ፤ ሇኔም ትሌቅ እዴሌ ነው፡፡ /ሞቅ ያሇ ሰሊምታ ይሰጣጣለ፡፡/
/…እንዲሻው የስፖርት ሌብሱን ሇብሶ ወዯ ድርም በመግባት/
- እንዲሻው፡- ብሬ አረፈዴን እኮ እስካሁን አንተን ስጠብቅህ ነበር፣ ቀረህ፤
- ብርሃኑ፡- እንዳ እኔ ዛሬ አሌጫወትም ጉባኤ መሄዴ አሇብኝ፡፡
- እንዲሻው፡- ትንሽ ተጫውተህ እኮ ትዯርሳሇህ፡፡
- ብርሃኑ፡- አይ ከዯከመኝ በዯንብ መማር አሌችሌም፡፡ ተረጋግቼ ብማር ይሻሇኛሌ፡፡
- እንዲሻው፡- በይ እሺ ቸው፡፡ /ብል ከድርም ይወጣሌ፡፡/
- አንተነህ፡- አስሜ ያንን ሕሌም እኮ ከነገርኩህ በኋሊ ላሊ ተመሣሣይ ሕሌም አየሁ፡፡
- አስማማው፡- አንቴ አንዴ ነገር ሊስታውስህ፡፡ እዚህ ግቢ የመጣኸው ተምረህ ራስህንና
ቤተሰቦችህን እንዱሁም ርዲታህን የሚፈሌጉ ሰዎችን ሇመርዲት ነው፡፡ ፊሌምና ጌሞች
መዝናኛ እንጂ ቋሚ ሥራዎች ሉሆኑህ አይገቡም፡፡ በሕሌምህ ተዋናይ ሆነህ
የምትሠራባቸው ሆረሮች (Horrors) የዚህ ውጤት ናቸው፡፡ ስሇዚህ አንቴ ሇፊሌምና
ሇጌም የሰጠኸው ጊዜ ከፍሇህ ሇቤተ-ክርስቲያን አዴርገው፡፡ ላሉት የሚያስዯነግጡህንም
ነገሮች ከአንተ ይርቃለ፡፡
- አንተነህ፡- Thank you አስሜ!
- አስማማው፡- /የስሌኩን እስክሪን አየና/ የጉባኤ ሰዓት ዯርሷሌ በቃ እንሂዴ . . . /እንዲሇ
ሁለም ማስታወሻውን ይዞ ከድርም ይወጣሌ፡፡/

ወስብሐት ሇእግዚአብሔር

ወሇወሊዱቱ ዴንግሌ

ወሇመስቀለ ክቡር

ኀብተ ጊዮርጊስ

መጋቢት፣ 2007 ዓ.ም

You might also like