Professional Documents
Culture Documents
8 Part 2
8 Part 2
ለምሳሌ፡-
ሩፋኖስና ሶቅራጥሰ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ወንጌል የሰበከ ቅዱስ ማቴዎስ እንደሆነ ገልጿል፡፡
ከ 317- 419 ዓ.ም. የነበረ የላቲን ቤተክርስቲያን አባት ጀሮም የኢትዮጵያ ሐዋርያ ቅዱስ እንድርያስ ነው ይላል፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ደግሞ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ሐዋርያ ቅዱስ ቶማስ ነው ይላል፡፡
ዜና ማርቆስ መጽሐፍ ላይ በርተሎሜዎስና እንድርያስ መጥተዋል፡፡
አውሳብዮስ በሁለተኛው መጽሐፍ እንደገለጸው የሐዋርያት ሥራ 8-26 መሠረት አድርጎ ጃንዳረባው ለወገኖቹ ሐዋርያ ሆነ
ብሏል፡፡
በርካታ ሐዋርያት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ቢያስተምሩም ተልእኳቸው ዓለምን ዞረው ለማስተማር ስለሆነ ኢትዮጵያም የዓለም
አንዷ አካል ስለሆነችና ለክርስትና መዲና ለኢየሩሳሌም ቅርብ ስለሆነች ኢትዮጵያ መጥተው ያስተማሩ ሐዋርያ ቁጥር በዛ ሊባል
አይችልም ነገር ግን እዚህ ላይ ልንገነዘብ የሚገባን የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ወንጌል ሰባኪ ጃንደረባው ባኮስ መሆኑን ነው፡፡ ኢትዮጵያ
በጃንደረባው አማካይነት ክርስትናን በ 34 ዓ.ም. የተቀበለች ብትሆንም በሲኖዶስ ሕግ የጵጵስና መንበር የተሰጣት ግን በ 328/330
ዓ.ም. ቅዱስ ፍሬምናጦስ የኤጲስ ቆጶስነት ሥልጣን በተሰጠው ጊዜ /በአራተኛው ምእተ ዓመት/ ነው፡፡
ምእራፍ አምስት
ምእራፍ ስድስት
ብሔረ ምላዳቸው ከውጪ ሆኖ ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ቅዱሳን
6.1 የሶርያው ፍሬምናጦስ
በ 300 ዓ.ም አካባቢ ሜሮጵስዮስ የተባለ ነጋዴ ፍሬምናጦስንና ኤዴስዮስ/ ሲደራኮስ/ ከተባሉ ወጣቶች ጋር በመሆን ከጢሮስ
ወደ ሕንድ በጀልባ ያመራል ሁሉም ክርስቲያኖች ነበሩ በጉዟቸው ወቅት በአፍሪካ ጠረፍ ቀይ ባሕር አካባቢ ሲደርሱም በአካባቢው
ለመናፈስ፤ ውሃ ለመጠጣት፤ አገር ለማየት ጀልባቸውን ከወደቡ አስጠግተው ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ሲሉ በአካባቢው ያሉ ሽፍቶች
በጀልባይቱና በተሳፋሪዎች ላይ አደጋ ጥለው እቃቸውን ዘረፏቸው፡፡ ሜሮጵዮስንና የጀልባይቱንም ቀዛፊዎች እዚያው ገደሉዋቸው እንደ
አጋጣሚ ሆኖ ሁለቱ ወጣቶች ብቻ ከመገደል አምልጠው በዛፍ ሥር ሲጸልዩ ሲያለቅሱ መጽሐፍ ሲያነቡ ተገኙ፡፡ ወጣቶቹንም ከማረኩ
በኋላ በዘመኑ ለነበረው ንጉሥ ኢዛና በጦር የማረክናቸው ናቸው ብለው ሰጡት፡፡ ቅዱስ ፍሬምናጦስ በአክሱም ቤተመንግሥት ለንጉሥ
ኢዛና (ታዜር) ልጆች ለአይዛናና ሳይዛና የሞግዚትነትና የአስተማሪነት ሥራ ተሰጠው ወንድሙ ኤዲስዮስን በአክሱም ቤተ መንግሥት
የግምጃ ቤት ኃላፊ አደረገው፡፡ ወጣቶቹ በአክሱም ቤተ መንግሥት ተወዳጅነትና ታማኝነት አገኙ፡፡ ንጉሡ ኢዛና ለሞት በተቃረበ ጊዜም
ልጆቹ አድገው ዙፋኑን ለመያዝ እስኪበቁ ድረስ መንግሥቱን በሞግዚትነት እንድትይዝ ለንግሥት ሶፍያ አደራ ሰጣት እናታቸው ንግሥት
ኦሕየዊ /ሶፍያ/ ሥልጣኑን በሞግዚትነት ተረከበች ፍሬምናጦስም ሁለቱን የንጉሥ ልጆች ወንጌል በማስተማር እናቲቱንም በአስተዳደር
እየረዷት ለ 3 ዓመታት ያህል ከንግሥት ኦሕየዊ ጋር በፍቅር ኑረዋል፡፡ የንግሥቲቱን ቃል በማክበርም በቤተመንግሥት ውስጥ
በአማካሪነት ሲያገለግሏት ቆይተዋል፡፡ ፍሬምናጦስ ለአይዛናና ሳይዛናን በተጨማሪም ለአክሱም ባለሥልጣናትና ለሀገሩ ተወላጆች
በይበልጥ ክርስትና በማስተማር አጠናከረ በወቅቱ ኢትዮጵያ ሃይማኖት ብቻ እንጂ ክህነት፣ ቁርባንና የመሳሰሉት የክርስቲያን ሥርዓት
አልነበራትም አይዛናና ሳይዛና አድገው ያባታቸውን ሥልጣን እንደተረከቡ፡፡ ኤዲስዮስ ወደ ሐገሩ ጢሮስ ተመለሰ በዚያም ካህን ሆነ፡፡
ይህንን በኢትዮጵያ ያሳለፈውን ጊዜ በጢሮስ ከሩፋኖስ ጋር ተገናኝተው እንደነገረውና ሩፋኖስም በመጽሐፉ መግቢያ ላይ ጽፎት ይገኛል፡፡
አይዛናና ሳይዛናም በትረ መንግሥቱን ከእናታቸው ተረክበው ከጨበጡ በኋላ ቀደም ብሎ በጃንደረባው የተሰበከውን ክርስትና
የሚጠናከርበትን መንገድ ያስተካክሉ ጀመር፡፡ በዚህ መሰረትም ጳጳስ ያመጣላቸው ዘንድ ፍሬምናጦስን ወደ እስክንድርያ ላኩት፡፡
ፍሬምናጦስ ስለ ጵጵስና ጉዳይ ለመነጋገር በቅርብ ወዳለች እስክንድርያ ቤተክርስቲያን ጋር እንዲወያይ ከአክሱም ነገሥታት ተልኮ ሄደ፡፡
ፍሬምናጦስም በእስክንድርያ ያሉትን፤ የእስክንድርያ የቤተክርስቲያን ባለሥልጣናት አላገኘም ምክንያቱም የደረሰበት ጊዜ በ 325 ዓ.ም.
ስለነበር የኒቅያ ጉባኤ የእስክንድርያ ሃይማኖት አባቶች አርዮስን ለማውገዝ ወደ ኒቅያ ተጉዘው ነበርና፡፡ ቅዱስ ፍሬምናጦስ እስኪመለሱ
ድረስ ለአንድ ዓመት በእስክንድርያ ቆይቷል፡፡ በዚህ ጊዜም የእስክንድርያ ቤተክርስቲያን ሃይማኖትንና የሃይማኖት ሥርአትን ጉዳዩ
የበለጠ እስኪጠናና እስኪሾም ድረስ ከ 2 ዓመት በላይ ሲቀመጥ የበለጠ አጥንቷል፡፡ ቅዱስ ፍሬምናጦስ እስክንድርያ ቤተክርስቲያን
ሹመቱን በመጠባበቅ ላይ እያለ በ 328 ዓ.ም. 19 ኛው የእስክንድርያ ፓትርያርክ እለ እስክንድሮስ አርፎ በምትኩ በእስክንድርያ መንበር
ቅዱስ አትናቴዎስ ተተካ፡፡
በዚህ ጊዜ ፍሬምናጦስ የተላከበትን ጉዳይ ለቅዱስ አትናቴዎስ አቀረበ ፓትርያርክ አትናቴዎስም በጉዳዩ ተደስቶ ለኢትዮጵያ
ክርስቲያኖች ቋንቋቸውንና ባህላቸውን የሚያውቅ ሌላ ባለመገኘቱ ራሱን ቅዱስ ፍሬምናጦስን ‹‹ጳጳስ ዘአክሱም ወዘኩሉ ኢትዮጵያ ብሎ
በቅብአትና በአንብሮተ እጅ ሹሞ ላከው አትናቴዎስም የእስክንድርያ 20 ኛው ሊቀ ጳጳስ ነው፡፡ ፍሬምናጦስ ጵጵስናውን ተቀብሎ
ከተመለሰ በኋላ በኢትዮጵያ የክርስትናን ሥርዓት አስፋፍቶ ሰበከ የክህነትና የቁርባንንም ሕግ አጠናከረ፡፡ በመላ ኢትዮጵያ ወንጌል
እንዲዳርስ ቀሳውስትና ዲያቆናትን ሾመ ከዘመዶቹ ጋር በደስታ ከመኖር ይልቅ ከመንፈሳዊ ልጆቹ ኢትዮጵያውያን መኖርንም መረጠ
በይበልጥ ስለተቀበለው ደስታ በኢትዮጵያ ሙሉ የክርስትና ትምህርት ሥርዓተ ቤተክርስቲንን ያለምንም ችግር አስተላልፎአል፡፡
አባ ሰላማ /ፍሬምናጦስ/ ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በዘመኑ ያከናወናቸው መንፈሳዊ ተግባራት
1. ስብከተ ወንጌልን ቀንና ሌሊት በትጋት ሰበከ
2. ካህናትና ዲያቆናትን ሾመ (ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ሾመ)
3. የክህነትና የቁርባን ሥርዓት እንዲጀመር አድርጓል
4. የመጀመሪያውን መንፈሳዊ ትምህርት ቤት አቋቁሟል፡፡
5. ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊ የምትባለውን የመጀመሪያ መንፈሳዊ የጽዮን ማኅበር በ 347 ዓ.ም. አቋቁሟል፡፡
6. በርካታ አብያተ ክርስቲያናት እንዲታነጹ አድርጓል፡፡
7. ቅዱሳት መጻሕፍትን ከሱርስት ከእብራይስጥና ከጽርእ ወደ ግእዝ ቋንቋ መልሶ ጽፏል
ቅዱስ ፍሬምናጦስ እነዚህን እና ሌሎችንም ዓበይት መንፈሳዊ ተግባራት በእግዚአብሔር አጋዥነት ከ 330 – 350 ዓ.ም. ድረስ
ቀንና ሌሊት የተደከመበትን የክርስትናን እምነትን በሀገሪቱ ብሔራዊ ሃይማኖት እንዲሆን በ 350 ዓ.ም. አሳውጇል። ብሔራዊ ሃይማኖት
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት እስከ 1966 ዓ.ም. ድረስ የመንግሥት ሃይማኖት ሆኗል፡፡ ፍሬምናጦስ የኢትዮጵያ
ቤተክርስቲያንን ከዚህ ያደረሰ ባለውለታ አባት ነው፡፡ በወቅቱም ይህ ሁሉ ድካሙ ታስቦለት በነገሥታቱ በአብርሃ አጽብሐ እና በአክሱም
ምሁራን /ከሣቴ ብርሃን የሚል/ የማእርግ ቅጽል ስም ተሰጥቶታል፡፡ ትርጓሜውም ብርሃንን የገለጠ ማለት ነው፡፡ ፍሬምናጦስ አባ ሠላማ
ይህንን የመሳሰለ ሐዋርያዊ ተጋድሎውን ፈጽሞ አርፏል ቅድስት ቤተክርስቲያንም የቅዱሳት ማእርግ ሰጥታ በዓለ እረፍቱን ሐምሌ 26
በየዓመቱ ታከብራለች፡፡
6.2 አባ ሊባኖስ
ከዘጠኙ ቅዱሳን መምጣት በፊት ጻድቃን በመባል የሚታወቁ አበው ወደ አገራችን መጥተው በሰሜን ኢትዮጵያ በኤርትራ
ክፍለ ሀገር ይኖሩ የነበሩ ናቸው፡፡ እነዚህ ጻድቃን በልዩ ልዩ ሥፍራ በተለይም በቡድን ተከፋፍለው በአምባዎች ላይ ከሚገኙ ዋሻዎች
ሥፍራ ተሠማርተው ሐዋርያዊ ተልእኮዋቸውን ይፈጽሙ ነበር፡፡ የሚበሉትም ቅጠልና ፍራፍሬ ነበር የሰፈሩባቸውም ቦታዎች ለመግለጽ
መጠራ፣ ሐረሳ፣ መንጉጢን፣ አውዓ፣ ከዲህ፣ ደብረሳህል ወዘተ ናቸው፡፡ ከእነዚህም መካከል አባ ሊባኖስ የተባሉትና ከደረቅ አለት ላይ
ጠበል በማፍለቅ የሚታወቁት በቀደምትነት የሚታወሱትና በስማቸው ገደማትና አብያተ ክርስቲያናት የተመሠረተላቸው ናቸው፡፡
በአጠቃላይ ጻድቃን ለ 30 ዓመታት ያህል ብዙ ገቢረ ተአምራት ሲሰሩ ወንጌልን ሲያስተምሩ ኖረዋል፡፡ በዓላቸውም የመታሰቢያ ቀናቸው
ጥቅምት 19 ቀን ይከበራል፡፡ ኣባ ሊባኖስ /መጣዐ/ ከዘጠኙ ቅዱሳን በቀደምትነት የሚታወቁ አባ ሊባኖስ ሌላ ስማቸው አባ መጣእ
በመባል ይታወቃል፡፡ የታናሽ እስያ ሰው ናቸው፡፡ በመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ጥሪ ወደ A ባ ጳኩሚስ ዘንድ ሄደው ምንኩስናን
ተቀብለዋል፡፡ ከዚያም ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በጾም ተጠምደው ገዳም ሠርተው ተአምራት እየፈጸሙ እስከ እለተ ሞታቸው
ቆይተዋል፡፡ የመሠረቱት ገዳም አካለ ጉዛይ ኤርትራ ክፍለ ሀገር ሕሞ ከሚባል ቦታ ነው፡፡ በላስታ ቅዱስ ላሊበላ ካሳነጿቸው አብያተ
ክርስቲያናት አንዱ በአባ ሊባኖስ ስም ነው፡፡ መታሰቢቸው ህዳር 3 ቀንና፣ ጥር 3 ቀን ይከበራል፡፡