መሰግላን

You might also like

Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 3

ደብተራ ሁለት ትርጉም አለው

ኦሪት ወይም ድንኳን ማለት ነው ። በውዳሴ ማርያምም ፣ ደብተራ ድንኳን ፣ የእመቤታችን ምሳሌ እንደሆነ ተጽፏል

በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ፣ የቀኙንም ሆነ የግራውን ቁመት የሚመራ ፣ ሊቅ ፣ የመጽሃፍ አዋቂ የተማረ ..... ማለት
ነው ።

ኤላው ትርጉም ደግሞ ፣ መተተኛው ፣ አውደ ነገስት የሚገልጠው ፣ ልዩ ልዩ የጥንቆላ መጽሃፍትን ገልጦ የሚመትት ፣
ሲያዩት ካህን መሳይ ፣ ራሱ ላይ የጠመጠመ ፣ ነገር ግን ፣ ካህን ያልሆነ መሰሪ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሰርጎ የገባ የበግ
ለምድ የለበሰ ቀበሮ ማለት ነው ።

አንድ ካህን ፣ ትክክለኛ ካህን ወይም ደግሞ አስመሳይ ካህን ፣ ደብተራ መተተኛ ጠንቋይ ,,,.... መሆኑን የምናውቅበት
መንገድ የሚከተለው ነው ። ትክክለኛ ካህንን ከደብተራው የምንለይበት ችሎታ ካላዳበርን ፣ ለከፍተኛ ችግር
እንዳረጋለን ::

የንስሃ አባትም ስንመርጥ : ከዚህ የሚከተለውን መመሪያ ብንከተል : ከአደጋ እንድናለን :

1 በንግግራቸው

የሆነ ነገር ቸግሯችሁ ፣ ንግዳችሁ እየቀዘቀዘ ከተቸገራችሁ ፣ ልጆቻችሁ ዱርዬ ሆነው ፣ ወይም በትዳራችሁ ጭቅጭቅ
ገብቶ ከሆነ፣ ትዳር እምቢ ሊላችሁ ይችላል ፣ ህመም ጽንቶባችሁ ሊሆን ይችላል ........ በዚህ ጊዜ ፣ ወደ ካህን
ቀርባችሁ ፣ አባቴ ፣ አንድ ነገር ላናግርሆት ፈልጌ ነው ብላችህ ችግራችሁን ስትነግሯቸው ፣ ስታወያዩዋቸው ፣
“ይህማ ቀላል ነው ፣ መፍትሄ አለው ፣ ጥበብ አለው ከአባቶቻችን የመጣ ጥበብ አለ .....
መንገድ አለው ፣ ጥበብ አለው መፍትሄ አለው ..... ይላሉ ። ስገድ ፣ ጸልይ፣ ቅዱስ ቁርባን ተቀበል ...... የሚል መጽሃፍ
ቅዱሳዊ ምክር አይሰጡም ፣ አይሉም ። ይህንን ስራስር ተቀባ ብላ ተቀባ፣ ይህንን ገበያህ በር ላይ ድፋው ፣
ይህንን ነገር ሰውየው ላይ አስነካው ...... የሚል አጋንንታዊ ምክር ይመክራሉ ።

ይህ ከአባቶች የመጣ ነው ይላሉ ፣ ነገር ግ ን ከየትኞቹ አባቶች እንደመጣ አይናገሩም ። አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ፣
አቡነ ተክለሃይማኖት ..... አውደ ነገስት አልደገሙም ፣ ስራስር አልነቀሉም፣ መፍትሄ ሰራይ አልደገሙም ..... ።
ስለየትኞቹ ቅዱሳን አባቶች እንደሚናገሩ አይታወቅም ።

የቅዱሳን አባቶች ጥበባቸው ፣ ጸሎት ነው ፣ ስግደት ነው ...... ስለየትኞቹ ቅዱሳን አባቶች እንደሚያወሩ አይታወቅም

2 ቀለብትና ሃብል

ሁለተኛው የደብተራ መለያ መንገድ ደግሞ ፣ እጁ ላይ የብር ቀለበት ፣ አንገቱ ላይ ደግሞ ሃብል ያደርጋል ። ይህ ቀለበት
፣ ከጋብቻ ቀለበት ጋር ተመሳሳይ አይደለም ። ቀለበቱ መካከል ላይ ትልቅ ጥቁር ፈርጥ አለው ። የወርቅ ቀለበት ከሆነ
ደግሞ መካከሉ ላይ ትልቅ ፈርጥ አለው ። ይህ ቀለበት ፣ ድግምት ያለበት ቀለበት ነው ። ሃብል ደግሞ ፣ መስቀል
ያለው ሃብል ሳይሆን ፣ ወይም ማህተም ሳይሆን ፣ ከዚህ የተለየ ልዩ ልዩ አይነት ሃብል ነው ።

3 ስግደት

ቀረብ ብላችሁ ፣ ስለ ስግደት ፣ ጸሎት .... ህይወታችሁ ስትነግሯቸው ፣ መስገድ ጥሩ ነው አይሏችሁም ፣ በሰምበት
አይሰገድም ፣ ስግደት አታብዛ ፣ ያስመታሃል ..... የሚል ስግደትን የሚያጥላላ ከላይ መልካም የሚመስል ፣ ነገር ግን
ስግደትን የሚያጣጥል መልስ ይሰጣሉ ።
የጸሎት ቤት ሰርቻለሁ ፣ ስትሏቸው፣ ቤት ውስጥ የጸሎት ቤት አያስፈልግም ፣ ብዙ ሃጢያት የሚሰራበት ነው ፣ .....
የሚል መልስ ይሰጣሉ ።
ቤት በእጣን አይታጠንም ቤታችሁን በተቀደሰ እጣን አትጠኑ ፣ ካጠናችሁም ከገበያ በተገዛ እንጂ ከቤተ ክርስቲያን
በመጣ እጣን አትጠኑ ፣ ቅባ ቅዱስ አትቀቡ ፣ ...... ይሏችኋል ። እንደዚህ የሚሏችሁ ፣ ለቅባ ቅዱሱና ለእጣኑ
አስበው ሳይሆን ፣ እናንተ ላይ የመተቱት መተታቸው እንዳይከሽባቸው ፣ እላያቸው ላይ ያለውን እርኩስ መንፈስ
እንዳይቃወም ,,,, ነው ።

4 ስለ ዛር ፣ ስለ ድግምት ፣ ስለመሳሰሉት አያወሩም

እነዚህ ደብተራዎች ፣ ስለ ድግምት ፣ዛር ፣ አዳልሞቴ ፣ ወሰንገላ ፣ መተት ፣ ቡዳ ፣ ጠቋር ፣ ግርማሞገስ ፣ ጨሌ .......
ስለመሳሰሉት በጭራሽ አያወሩም ። ለስሙ የቤተ ክርስቲያን አባት ናቸው ፣ ጨሌ በየቤቱ እየተመለከ እንደሆነ
ያውቃሉ ፣ ነገር ግን ፣ ጨሌያችሁን ከቤታችሁ አውጡና ጣሉ ፣ በፍጹም አይሉም ። ስለ ዛር በደምብ ያውቃሉ
አያወሩም ።
በቤቴ የሚመለክ ጨሌ ፣ ዛር አለ .... ስትሏቸው ፣ እዚያው ኮተታችሁን ያዙ ያላሉ ወይም ወሬውን ወደሌላ
ያስቀይሳሉ ፣ እንጂ ፣ አውጥታችሁ ጣሉና ወደ እግዚአብሄር ተመለሱ በፍጹም አይሉም ።

5 መተት የሚባል የለም

አንድ ካህን ፣ ደብተራ መሆኑን ማወቂያው አንዱ መንገድ ፣ ስለ መተት ስትጠይቋቸው ፣ መተት የሚባል ነገር የለም
ይሏችኋል ። እነሱ ራሳቸው ፣ መተት እየመተቱ ስለሆነ ፣ ሌላው ህዝብ እንዳይነቃባቸው ፣ መተት የለም እያሉ
ህዝቡን ያደነዝዙታል ። መተት የለም ማለትኮ ፣ መንፈስ የለም ፣ ሰይጣን የለም ..... እንደማለት ነው ። ይህ አደገኛ
የሆነ ትምህርት ነው ።

ወይም ደግሞ ፣ መተት እንዴት ባንተ ህይወት ላይ ይሰራል ፣ ቤተ ክርስቲያን ትሄድ የለ እንዴ ፣ ክርስቲያን አይደለህም
እንዴ፣ ትጸልይ የለ እንዴ ፣ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ብለህ ስታማትብ ካንተ ይሄዳል ..... የሚል ንግግር
ይናገራሉ

6 ጸበል

ደበተራዎች በፍጹም ጸበል አይጠመቁም ። አንዳንዶች ቢጠመቁም ፣ሳያምኑበት ነው ። የጸበል ቦታዎችን


አይደግፉም ። እንደ በርሜል ጊዮርጎስ ፣ ጻድቃኔ ማርያም የመሳሰሉ አንዳንድ ታዋቂ የጸበል ቦታዎችን ያጥላላሉ
ይቃወማሉ ፣ ምእመኑ ወደ እነዚህ ቦታዎች እንዲሄዱ አያበረታቱም ። ወይም ስለጸበል ቦታዎች ማውራት
አይፈልጉም ፣ ስለ ጸበል ቦታዎች አያስተምሩም ።
ለምሳሌ፣ በርሜል ጊዮርጎስ ይሰውራል ,,, ተብሎ ሲነገራቸው ይስቃሉ ያጥላላሉ። አጥማቂዎችን ይቃወማሉ ፣
ትምህታቸውን ይነቅፋሉ ያጥላላሉ ።

7 የድግምት መጽሃፎች

መፍትሄ ሰራይ ፣ አውደ ነገስት ፣ ድርሳነ ሰለሞን ፣ ጸሎተ ጴጥሮስ ...... እነዚህ መጽሃፎችን ፣ የአባቶች ጥበብ ነው
ብለው ይናገራሉ ። በየቤቱ ሲሄዱ ፣ እነዚህን መጻህፍት ይደግማሉ ።

እነዚህ መጻህፍት ፣ አጋንንትና ፣ሰይጣንን ..... ፣ የመጎተቻ መጻህፍት ናቸው ። እነዚህ መጻህፍት ፣ በሚያሳዝን ሁኔታ
፣ ከቅዱሳን መጻህፍት ጋር ተደባልቀው ፣ በቤተ ክርስቲያን በሮች አካባቢ ለምእመናኑ እየተሸጡ ናቸው ። ሰምበት
ተማሪዎችም ፣ ካህናትም ሆኑ የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪዎች ፣ ደብተራዎችን ስለሚፈሩ ፣ ሽያጩን ለማስቆም ፣
ምንም አይነት እርምጃ አይወስዱም ። እነዚህን መጽሃፎች ሰብስቦ የሚያቃጥል የቤተ ክርስቲያን መሪ ወደፊት
እስኪመጣ ድረስ ፣ እንደዚህ አይነት ነገሮች ይቀጥላሉ

8 በእጅ የሚያዝ ነገር

ደብተራዎች ጠንቋዮችና ድግምተኞች ፣ ሁልጊዜ በእጃቸው የሚይዙት አንድ አይነት እቃ ይኖራል ። ልብ ብላችሁ
ሁሌ አስተውሏቸው

9 ወንጌል ትምህርት

ደብተራዎች የወንጌል ትምህርት ሲያስተምሩ ፣ ቀልድ ያበዛሉ ። ምእመናኑ ፣ በቁም ነገር ወንጌል ተምሮ እንዳይሄድ
፣ የትምህርት ጊዜውን በቀልድና በሳቅ ያሳልፉታል ። የወንጌል ትምህርታቸው ፣ በቀልድና አለማዊ ወሬ በማብዛት ፣
የአሮጊቶች ተርታ ተረት በማውራት ፣የክርስቶስ ትምህርት እንዳይነገር የትምህርቱን ጊዜ በዋዛ በፈዛዛ ያሳልፉታል
። ለትምህርት የመጣው ምእመን ፣ ምንም ሳይማር አደንዝዘውት ይመልሱታል

10 እውነተኛ አባቶችን ይነቅፋሉ

በትምህርታቸው ላይ ፣ እውነተኛ አባቶችን ይሳደባሉ ያጥላላሉ ይራገማሉ ። መቁጠሪያ ለገዳም ብቻ ነው ፣


መቁጠሪያ አትጠቀሙ ፣ ከቤታችሁ አውጡ ፣ ..... ይላሉ ።

ደብተራዎች ፣ በማህበራዊ ሚዲያ ፣ "የባህል ህክምና" በማለት ስራስርና ቅጠላቅጠል .... በግልጽ መሸጥ ጀምረዋል።
በአደባባዩ ፣ስለ ኮከብ ቆጠራ በግልጽ ማስተማር ጀምረዋል ።

ቤተ ክርስቲያን ኮከብ ቆጣሪ አይደለችም ። በኮከብ አትቆጥርም ። መጽሃፈ ሄኖክ ምእራፍ 2 ላይ እንደተገለጸው ፣
ኮከብ መቁጠር ከሰይጣን ነው ።

የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሄርን መፍራት ነው ፣ መጽሃፈ ምሳሌ ምእራፍ 1

ቀሲስ ሄኖክ (ዘሚካኤል ) ካስተማሩት የተወሰደ

ማይክ ከ DC

You might also like