Professional Documents
Culture Documents
መራሕያን
መራሕያን
ክፍል ፩
- እሉኒ (እነሱም)፦
🔸ቀዳማይ መደብ
፩ . አነ = እኔ | I
፪ . ንሕነ = እኛ | We
🔸ካልዓይ መደብ
🔸ሣልሳይ መደብ
፯ . ውእቱ = እሱ | He
፰ . ይእቲ = እሷ | She
፱ . ውእቶሙ = እነሱ | They
፲ . ውእቶን = እነሱ (ለሴቶች) | They
##😂😂#
🌀 መራሕያን (ተውላጠ ስም)
ክፍል ፪
➩ ዘተባዕታይ ጾታ (ወንድ)
• አንተ
• አንትሙ
• ውእቱ
• ውእቶሙ
➩ ዘአንስታይ ጾታ (ሴት)
• አንቲ
• አንትን
• ይእቲ
• ውእቶን
➩ ዘዋሕድ (ነጠላ)
• አነ
• አንቲ
• አንተ
• ውእቱ
• ይእቲ
➩ ዘብዙኅ (የብዙ)
• ንሕነ
• አንትሙ
• አንትን
• ውእቶሙ
• ውእቶን
➩ ዘቅሩብ (የቅርብ)
• አንተ
• አንቲ
• አንትሙ
• አንትን
➩ ዘርሑቅ (የሩቅ)
• ውእቱ
• ይእቲ
• ውእቶሙ
• ውእቶን
➩ ዘክልዔቱ (የወል)
• አነ
• ንሕነ
######
🌀 መራሕያን (ተውላጠ ስም)
ክፍል ፫
➩ አነ ▹ ( -ኩ)
ንሕነ ▹ ( -ነ)
ይእቲ ▹ ( -ት)
➩ አንተ ▸ ( -ከ)
አንቲ ▸ ( -ኪ)
➩ አንትሙ ▹ ( -ክሙ)
አንትን ▹ ( -ክን)
፩ - አነ ዘመርኩ
እኔ አመሰገንኩ።
፪ - ንሕነ ዘመርነ
እኛ አመሰገንን።
፫ - ይእቲ ዘመረት
እሷ አመሰገነች።
፬ - አንተ ዘመርከ
አንተ አመሰገንክ።
፭ - አንቲ ዘመርኪ
አንቺ አመሰገንሽ።
፮ - አንትሙ ዘመርክሙ
እናንተ አመሰገናችሁ።
፯ - አንትን ዘመርክን
እናንተ አመሰገናችሁ።
ክፍል ፬
ግስ፦ ሖረ ➛ ሄደ
◍ አነ ኀበ ቤተ ትምህርት ሖርኩ
እኔ ወደ ትምህርት ቤት ሄድኩ።
◍ ውእቱ ኀበ ቤተ ትምህርት ሖረ
እሱ ወደ ትምህርት ቤት ሄደ።
◍ ውእቶሙ ኀበ ቤተ ትምህርት ሖሩ
አነሱ ወደ ትምህርት ቤት ሄዱ።
◍ ውእቶን ኀበ ቤተ ትምህርት ሖራ (ለሴቶች)
እነሱ ወደ ትምህርት ቤት ሄዱ።
########
መጠይቃዊ ቃላት ( WH-words )
ክፍል ፩
መጠይቃን ቃላት የምንላቸው ነገሮችን በፈለግነው መንገድ እንድንጠይቅ የሚያረጉን ናቸው። እነሱም (እሉኒ)
የሚከተሉት ናቸው።
• መኑ ➾ ማን | Who
• ምንት ➾ ምን | What
• ማእዜ ➾ መቼ | When
• አይቴ ➾ የት | Where
• አይ ➾ የቱ | Which
• እፎ ➾ እንዴት | How
ክፍል ፫
፪ . ለጠይቆተ ነገራት
(What - Asking things)
• ምንት ➾ ምን
• ምንተ ➾ ምንን
ምሳሌ
➛ ምንተ ታፈቅር ?
(ምንን ትወዳለህ?).
• አነ አፈቅር ግብር።
(እኔ ሥራ እወዳለሁ። )
➛ ምንት ገበርከ ናሁ ?
(አሁን ምን ሠራኸ?)
• ግብረ ቤት ገበርኩ።
(የቤት ሥራ ሠራሁ። )
➛ ምንት ገበርኪ ትማልም ?
(ትናንት ምን ሰራሽ?)
• አንበብኩ መጽሐፍ ትማልም።
(ትናንት መጽሐፍ አነበብኩ። )
➛ ምንት ተመሀርክሙ ትማልም?
(ትናንት ምን ተማራችሁ?)
• በእንተ አድዋ ተማሀርነ ትማልም።
(ትናንት ስለ አድዋ ተማርን። )
➛ ምንተ ታፈቅሩ አርድእት ?
(ተማሪዎች ምንን ትወዳላችሁ?)
• ንሕነ ናፈቅር ተውኔት።
(እኛ ጨዋታ እንወዳለን። )
ክፍል ፮
፭ . ለጠይቆተ ኲነት
(How - Asking process)
• እፎ ➾ እንዴት
ምሳሌ
➛ እፎ ኃደርከ ?
(እንዴት አደርክ)
• እግዚአብሔር ይሰባሕ።
(እግዚአብሔር ይመስገን፡)
➛ እፎ ወአልክሙ አርድእት ?
(እንዴት ዋላችሁ ተማሪዎች)
• እግዚአብሔር ይሰባሕ መምህር።
(እግዚአብሔር ይመስገን መምህር፡)
➛ እፎ ኀደርኪ ኦ እምየ ?
(እናቴ ሆይ እንዴት አደርሽ)
➛ ትምህርት እፎ ውእቱ ?
(ትምህርት እንዴት ነው)
• ሠናይ ውእቱ።
(ጥሩ ነው)
➛ ግብር እፎ ውእቱ ?
(ሥራ እንዴት ነው)
• ጥቀ ሠናይ ውእቱ።
(በጣም ጥሩ ነው፡)
➛ እፎ አንተ ?
(እንዴት ነኽ)
• ዳኅና አነ።
(ደኅና ነኝ)
➛ ሕይወት እፎ ውእቱ ወልድየ ?
(ሕይወት እንዴት ነው ልጄ)
• አኮ ሠናይ አቡየ።
(መልካም አይደለም አባቴ)
፮ . ለጠይቆተ ኁልቁ
(How Many - asking quantity)
• ስፍን ➾ ስንት
• እስፍንቱ ➾ ስንት
• እስፍንተ ➾ ስንትን
ምሳሌ
➛ እስፍንቱ ውእቱ ዕድሜኪ ?
(ዕድሜሽ ስንት ነው)
• እስራ ውእቱ ዕድሜየ።
(ዕድሜዬ ሃያ ነው)
➛ እስፍንቱ ውእቶሙ አኀዊከ ?
(ወንድሞችህ ስንት ናቸው ?)
• ክልዔቱ ውእቶሙ።
(ሁለት ናቸው። )
➛ እስፍንቱ ሰዓት ውእቱ ናሁ ?
(አሁን ስንት ሰዓት ነው ?)
• ተስዓቱ ሰዓት ውእቱ ናሁ።
(አሁን ዘጠኝ ሰዓት ነው። )
➛ ስፍን ውእቱ ዝንቱ ?
(ይኸ ስንተ ነው ?)
• ዐሠርቱ ብር ውእቱ።
(ዐሥር ብር ነው። )
➛ እስፍንቱ አርድእት መጽኡ ዮም ?
(ዛሬ ስንቱ ተማሪዎች መጡ)
• ብዙኀኑ መጽኡ።
(ብዙዎቹ መጡ)
➛ እስፍንተ ሐዋርያተ ኀረየ ክርስቶስ ?
(ክርስቶስ ስንት ሐዋርያትን መረጠ)
• ዐሠርተ ወክልዔተ ሐዋርያተ።
(አሥራ ሁለት ሐዋርያትን፡)
ግስ ( Verb )
ክፍል ፫
✝ አርእስተ ግስ (Root Verbs)
፪. ቀደሰ ➾ አመሰገነ
- በመሀከል ያለው ፊደል ጠብቆ ይነበባል።
- ሦስት እና አራት ፈደላት አሉት።
- መነሻው ፊደል ግዕዝ ነው።
- መሀከል ላይ ያለው ፊደል ግዕዝም ሳድስም ይሆናል።
ቀ = ግዕዝ
ደ = ግዕዝ
ሰ = ግዕዝ
➜ የቀደሰ ቤት ለምሳሌ
• ➾ ፈጸመ = ጨረሰ
• ➾ ሐወጸ = ጎበኘ
• ➾ ሰብሐ = አመሰገነ
• ➾ ነጸረ = አየ
• ➾ አደመ = አማረ
• ➾ ዘሠረ = አመሰገነ
• ➾ ፈወሰ = አዳነ
• ➾ ኀለየ = አሰበ
• ➾ ተነበየ = ተናገረ
• ➾ ተመነየ = ተመኘ
• ➾ ተመገበ = በላ
• ➾ ተመክሐ = ተመካ
• ➾ ወለጠ = ለወጠ
• ➾ ወደሰ = አመሰገነ
• ➾ ከለለ = ጋረደ
• ➾ ጸውዐ = ጠራ
ግስ ( Verb )
ክፍል ፬
፫. ገብረ ➾ ሠራ
- ላልቶ ይነበባል።
- ሦስት ፈደላት ብቻ አሉት።
- መነሻው ፊደል ግእዝ ነው።
- መሀከል ያለው ፊደል ሳድስ ነው።
ገ = ግእዝ
ብ = ሳድስ
ረ = ግእዝ
➜ የገብረ ቤት ለምሳሌ
• ➾ ከብረ = ከበረ
• ➾ አምነ = አመነ
• ➾ መጽአ = መጣ
• ➾ ሰምዐ = ሰማ
• ➾ ወድቀ = ወደቀ
• ➾ ሰክረ = ሰከረ
• ➾ ለብሰ = ለበሰ
• ➾ መስየ = መሸ
• ➾ ከርመ = ከረመ
• ➾ ደክመ = ደከመ
• ➾ ቀርበ = ቀረበ
• ➾ ቀድሐ = ቀዳ
• ➾ ነግሠ = ነገሠ
• ➾ ሰፍሐ = ሰፋ
ተዋሕዶን እንወቅ።:
ግስ ( Verb )
ክፍል ፭
፬. ተንበለ ➾ ለመነ
- ላልቶ ይነበባል።
- አራትና ከዚያ በላይ ፈደላት አሉት።
- መነሻው ፊደል ግእዝ ነው።
- መኸከለኛው ፊደሉ ሳድስ ና ግእዝ አሉት።
ተ = ግእዝ
ን = ሳድስ
በ = ግእዝ
ለ = ግእዝ
➜ የተንበለ ቤት ለምሳሌ
• ➾ ሐንከሰ = አከማቸ
• ➾ አድለወ = አደላ
• ➾ ሰንበተ = አከበረ
• ➾ አመድበለ = አከማቸ
• ➾ አመስጠረ = አራቀቀ
• ➾ ገልገለ = ገላገለ
• ➾ ደምሰሰ = አጠፋ
፭. ባረከ ➾ ባረከ
ባ = ራብዕ
ረ = ግእዝ
ከ = ግእዝ
የባረከ ቤት ለምሳሌ
• ➾ ሣረረ = ሠራ
• ➾ ፃመወ = ደከመ
• ➾ ማህረከ = ማረከ
• ➾ ባረወ = ቆፈረ
• ➾ ቃነየ = ደረደረ
• ➾ ሣቀየ = አናወጠ
፮. ክህለ ➾ ቻለ
የክህለ ቤት ለምሳሌ
• ➾ ርእየ = አየ
• ➾ ልህቀ = አደገ
• ➾ ብህለ = አለ
• ➾ ርሕቀ = ራቀ
• ➾ ጥዕመ = ቀመሰ
• ➾ ንዕደ = አማረ
ግስ ( Verb )
ክፍል ፮
፯. ዴገነ ➾ ተከተለ
- ላልቶ ይነበባል።
- ሦስትና ከዚያ በላይ ፈደላት አሉት።
- መነሻው ፊደል ኃምስ ነው።
ዴ = ኃምስ
ገ = ሳድስ
ነ = ግእዝ
➜ የዴገነ ቤት ለምሳሌ
• ➾ ዜነወ = ነገረ
• ➾ ጼነወ = ሸተተ
• ➾ ሌወወ = ጠመጠመ
• ➾ ጤገነ = ጣደ
• ➾ ፄወወ = ማረከ
• ➾ ቴፈነ = ገረፈ
፰. ጦመረ ➾ ጻፈ
- ላልቶ ይነበባል።
- ሦስትና ከዚያ በላይ ፈደላት አሉት።
- መነሻው ፊደል (ሳብዕ) መጨረሻ ፊደል ነው።
ጦ = ሳብዕ
መ = ግእዝ
ረ = ግእዝ
➜ የጦመረ ቤት ለምሳሌ
• ➾ ሞጥሐ = ለበሰ
• ➾ ሞቅሐ = አሰረ
• ➾ ሎለወ = ጠበሰ
• ➾ ኖተወ = ዋጠ
• ➾ ሞፈደ = ጫረ
• ➾ ሞገደ = አወከ
📜 የግስ ጥናት 📜
•ክፍል (፩ )•
► መራ - መርሐ
► ደረሰ - በጽሐ
► አቀረበ - አውጽሐ
► ፈላ - ፈልሐ
► መዘነ - ጠፍልሐ
► አጨበጨበ - ጠፍሐ
► ፈታ - ፈትሐ
► ጮኸ - ጸርሐ
► አመሰቃቀለ - አመልትሐ
► ቆየ - ጸንሐ
► ረዘመ - ኖኀ
► ዘረጋ - ሰጥሐ
📜 የግስ ጥናት 📜
•ክፍል (፪)•
ከዚኽ በታች ያሉ ግሶች ሁሉም ጠብቀው እና ተነሥተው ይነበባሉ።
► ቀሰመ - አጣፈጠ
► ጸለለ - ጋረደ
► ቀበለ - ሸኘ
► ሐቀለ - ቀማ
► መከለ - ቆረጠ
► ኀየለ - በረታ
► የውሐ - አታለለ
► አምኀ - እጅ ነሣ
► ተፈሥሐ - ደስ ተሰኘ
► ነስሐ - ተጸጸተ
► ረውሐ - ቀደደ
► ለቅሐ - አበደረ
############
ተዋሕዶን እንወቅ።:
📜 የግስ ጥናት 📜 ክፍል ፲፩
🔻 ግሱ ሲገሰስ
• ይገብር ➜ ያሠራል
• ይግበር ➜ ይሥራ
• ገባሪ ➜ የሠራ
• ገባሪት ➜ የሠራች
• ግቡር ➜ የተሠራ
• ግብር ➜ ሥራ
• ምግባር ➜ በጎ ሥራ
• ተግባር ➜ ሥራ
➖ አእመረ ➜ አወቀ
• አእመረ ➜ አወቀ
• የአምር ➜ ያውቃል
• ያእምር ➜ ይወቅ
• አእማሪ ➜ አዋቂ
• አእማሪት ➜ አዋቂ
• እሙር ➜ የታወቀ
• ማእምርት ➜ አዋቂ ሴት
• ማእመራት ➜ አሳዋቂዎች ለሴት
########
📜 የግስ ጥናት 📜 ክፍል ፲፫
➖ ባረከ ➜ ባረከ
• ባረከ ➜ ባረከ
• ይባርክ ➜ ይባርካል
• ይባርክ ➜ ይባርክ
• ባርኮ/ባርኮት/ ➜ መባረክ
• ባራኪ ➜ የባረከ
• ባራክያን ➜ የባረኩ
• ባራኪት ➜ የባረከች
• ባራኪ ➜ የሚባርክ
• ቡራኬ ➜ ቡራኬ
• በረከት ➜ በረከት
######
📜 የግስ ጥናት 📜 ክፍል ፲፬
➖ ብህለ ➜ አለ
• ብህለ ➜ አለ
• ይብህል ➜ ይላል
• ይብሃል ➜ ይል ዘንድ
• ይብሃል ➜ ይበል
• በሃሊ ➜ ያለ
• በሃልያን ➜ ያሉ
• በሃሊት ➜ ያለች
• በሃልያት ➜ ያሉ ለሴቶች
• ብሁል ➜ የተባለ
• በሃሊ ➜ የሚል
• ባህል ➜ አባባል
ከላይ በተሰጠው ምሳሌ መሠረት የብህለ ቤት የሆነውን ምዕዘ = ሸተተ የሚለውን ግስ ዘርዝሩ።