የዘመቻ ሪፖርት

You might also like

Download as txt, pdf, or txt
Download as txt, pdf, or txt
You are on page 1of 2

●ተግባሮችን ዞኑ በሰጠው ዳይሬክሽን በ 4 ኮሚቴወች በአጠቃላይ በአስተባባሪው ሁሉንም እየገመገምን ተግባሮቹን እየመራን ቆይተናል::

1.ከህዝብ ግንኙነትና የፖለቲካ ስራ አኳያ


_ከመድረኮች አኳያ ከወረዳ_ቀበሌ የተለያዮ የህብረተሰብ ክፋሎችን አወያይተናል::በመድረኮቹ በአመዛኙ ህዝቡ እንድረዳና ከመንግስት ጎን
እንድሆን ለመግባባት ተሞክሯል::
_ነገር ግን የፖለቲካ ስራው በአንደየ ሰርተን የምናቆመው ሳይሆን በቀጣይም የበለጠ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ነው::
2.ከዘመቻ መምሪያ አኳያ
ከፅጥታ መዋቅሩ ጋር በጋራ እየተገመገመ እየተመራ ነው
በዚህ ውስጥ የኦፕሬሽን ኮሚቴውን ሰ/ደ በራሱ እየመራ ነው::
ከመከላከያ አኳያ
_ተግባሩ ከወረዳ_ቀበሌ በቂ መድረክ ተፈጥሮበታል
_የአመራር ስምሪት በሁሉም ቀበሌ ተሰጥቶበታል
_እቅድ ለሁሉም ቀበሌ ፖቴንሻልን መሰረት አድርገን ሰጥተናል
_የአመራሩ የቀን እቅድ ተሰጥቶታል
_የተሻለ የቅስቀሳ ስራ በኮምኒኬሽን በየቀኑ ተሰርቷል
_ምልስ መከላከያ ተጠቅመናል
_የፅጥታ መዋቅሩ ተግባሩን ለመፈፅም ጥሩ እንቅስቃሴ ነበር
_በዚህም እስከ ቀን 8 100%እንደወረዳ መዝግበናል
_ከዚህ ውስጥ 80 ወጣት ወደ ማዕከል አስገብተን የፖለቲካ ግንባታ ስናደርግ ቆይተናል
_በዚህ ውስጥ የአመራሩ አፈፆፅም ተለይቷል
የፅሁፏ ማስጠንቀቂያ የተሰጠ =
_ቢራዘምም የበለጠ ስራ ሰርተንባቸዋል ከራሳቸው አልፈው ሌላ ወጣት እንዳፈሩ
_ልጆቹ ውሰዱን የሚል አቋም ነበራቸው
_ለዚህ ወረዳውም ህዝቡም ጥሩ እንቅስቃሴ አለው በበጀት
_የበአል ቀን ለተሰውባቸው ቤተሰቦች የበግ ስጦታ አድርገን ስለነበር

3.ከሀይል ማሰለፋ አኳያ እቅዳችን ተሻሽሏል


134 ነው ያስገባነው 3 ተኛ ዙር መኪና ካዘጋጀን በሆላ ቆይ ስለተባለ ነው እንጅ የተሻለ መላክ ይቻላል
አሁንም 40 ሰላም አስከባሪ ወረዳ ላይ ጠርንፈን ይዘናል
4.ከውስጥ ሰላምናደህንነት አኳያ
_እንደወረዳ የፀጥታ ችግር የነበረብን ኮሬብ አካባቢ የነበረው ግድያና ወንጀለኛ አለመያዝ ነበር
_ለዚህ እናደወረዳ በበጀት የተደገፈ የሰላም ኮንፈረንስ ከተለያየ ተቋምና የሀ/አባቶች የተካተቱበት መድረክ ተፈጠረ
_በመድረኩም ህዝቡ ወደራሱ እንዳይና የመፋትሄ አካል እንድሆን በር የከፈተ ነበር
_ከዚህ ተነስቶ የወንጀለኛ ቤተሰብ በሰላም እንድኖር እርቅ በራሳቸው እሴት እንዳካሂዱ ተደረገ
_ከዚህ በሆላ ወንጀለኛን በህግ ቁጥጥር የፅጥታ መዋቅራችን አደረገ በህዝባዊ ድጋፋ ኦፕሬሽኑ ተጠናቋል

■አሁናዊ የፅጥታ ስጋታችን ሀይማኖትን መሰረት ያደረገ ነው


_ጉዳዩ በ 2008 አ.ም የተፈጠረ እና ከለውጡ በሆላ በእንጥልጥል የቆየ ነው
_በክርስትናው ቤተክርስቲያን ተቃጥሎብናል በሙስሊሙ ተገርፈናል የሚል ነው
_በህልውና ዘመቻውና በምርጫ በአንድነት ሲያግዙን ቆይተዋል::
_ነገሩ የሚነሳው የሀይማኖት ተቋምን አስታኮ ይነሳል
_ከዚህ ተነስተን በኛ በኩል ጉዳዩ በዘላቂነት እንድፈታ ሁለቱንም ወገኖች በአስተባባሪና በፅጥታ አመራሮች በጋራ አወያየን ችግሩን በዘላቂነት
እንድፈታ ወደሽምግልና እንድገቡ አስማማተን
_ሂደቱ ከፖለቲካ አመራሩ ገለልተኛ ሁኖ በህዝብ ተወካዮቹና በፅጥታ ተቌም አመራሮች እንድመራ አደረግን
_በሽምግልና ሂደቱ የተሻለ መግባባት ከተደረሰ በሆላ የክርስትና አባት እምቢ አሉ በራሳቸው አማኞች እየተለመኑ
_ጉዳዩን አማካሪ በዛበት የህዝብ ያልሆነውን ወደህዝባዊነት ለመርጨት ህዝብ ላወያይ ተባለ
_ከዛ ፖለቲከኛም ገባበት እንደውም ግድ ታረቁ እየተባልን ጫና እየተደረገብን ነው ወደሚል ቀየሩት
_ለዚህ የወረዱ አመራሮች በግልፅ እጃቸው አለበት በሁለቱም ወገን

■ከዚህ አኳያ አዝማሚያውን ፖለቲካሊ ስናየው


_በሁለቱም በኩል ገፊ አማካሪ አለ
_አመራሩን በዚህ አጀንዳ ለመከፋፈል ፋላጎት አለ ግን የወረዳው የፖለቲካ ሁኔታና የአመራሩ አጠቃላይ ሁኔታ ምቹ ሁኔታ አልሰጣቸውም
_ገፋቶ ወደ መተሳሰርና አንዱ አንዱን ገፋቶ ወንጀል እንድፈጠርና እንድታሰር ማስደረግ ፋላጎት አለ
ለምሳሌ 1.ሙስሊሙ እኛ ሰላማዊ ነን አጥፊው ክርስቲያን ነው ለማለት
2.ክርስቲያኑ ደሞ ሙስሊሙን ዱሮም አቃጠሉ አሁንም ቀጥለዋል በወንጀላቸው ለማስባል::
●በዋናነት ደራውና ፏክክሩ ያለው በሁለቱ ሀይማኖት መሪወች ነው እነሱ ቢስማሙ ከሆላ ያለው ጥቂት ገፊ ይቆማል::
●ህዝቡ እንደህዝብ አንድ ላይ ነው በነሱ ፋጥጫ አልተጋጨም

■ጥሩው ነገር
_አመራሩ ና የፅጥታ አመራሩአንድነትና በገለልተኛነት መገኜቱ
_ከሁለቱም ወገን የመሪወቹን ፋጥጫ በመኮነን እርቅ ይውረድ የሚል አማኝና የጋራ ሽማግሌ መኖሩ ጥሩ ነው

■በቀጣይ ቢሆን ብለን የምናስበው


_የህዝብ አንድነትን በህዝብ ግንኙነት ስራ የበለጠ ማጠናከር
_ከተቻለ በዞን የሀይማኖቶቹ አባቶች ታግዘን እርቁ እንድጠናቀቅ ቢደረግ
_ከዚህ ውጭ በሆነ መንገድ ለህዝብ ግጭት መነሻ የሆነን ማንኛውም አካል ከየትኛውም ይሁን ህግ ማስከበር ::

You might also like