Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 8

ቀን ------------------------------------

በጋ/ህ/ብ/ክ/መንግሥት ሠነዶች ም/ማ/ወ/የሥራ ሂደት

ጋምቤላ፣

ጉዳዩ ፡- የውክልና ሥልጣን ማስረጃ

የወካዮች ስም ----------------------------------------

ዜግነት

አድራሻ

ዕድሜ

የተወካይ ስም ----------------------------------------

ዜግነት

አድራሻ

ዕድሜ

እኛ ለተወካይ የምንሰጠው የውክልና ሥልጣን በአባታችን ስም ተመዝግቦ የሚገኝ

የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረት እንዲያስተዳድሩ ፣እንዲሸጡ፣እንዲለውጡ፣ ውል

እንዲዋዋሉ፣ ስም እንዲያዛውሩ፣እንዲያከራዩ፣ ወደ ስማችን እንዲያዛውሩ ፣ በስማችን

በማህበር ተደራጅተውም ሆነ በሊዝ ቦታ እንዲመሩ ፣ ንብረት እንዲረከቡ ፣ ካርታ፣ ፕላንና

የባለቤትነት ደብተር እንዲያወጡ የግንባታ ፊቃድ እንዲያወጡ የግንባታ ግቢያቶችን ግዥ

እንዲፈጽሙ ፣በክልል፣ በክፍለ ከተማ ፣ዞን ፣በወረዳ እና ቀበሌ እኛን በሚመለከት ማንኛውም

ጉዳይ እንዲያስፈፅሙ በአጠቃላይ በማናቸውም መንግሥታዊና ህዝባዊ ድርጅት በመቅረብ

ጉዳይ እንዲያስፈፅሙ ንብረትን በሚመለከት ከአቅም በላይ በሚሆንበት ጊዜ የውክልና

ውክልና እንዲሰጡ በምንከሰስበትም ሆነ በምንከስበት ሁሉ ጠበቃ ቀጥረው እንዲከራከሩ

፣ይግባኝ ለመጠየቅ ፣ ቃለ መሐላና ማረጋገጫ ላይ እንዲፈፅሙ ፣ መልስና የመልስ መልስ

እንዲሰጡ በአጠቃላይ እኛ መፈፀም የሚገባንን ሁሉ እንዲፈጽሙ ፣ይህንን ሙሉ የውክልና


ሥልጣን በፍ/ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 58(ሀ) እና በፍ/ብ/ህ/ቁጥር 2199/2205 መሠረት

መስጠታችንን በፊርማችን እናረጋግጣለን ፡፡

የወካዮች ስምና

ፊርማ

ቀን
ተስፋ ለሚቆርጥ እግዚአብሔር መልስ አለው

ተስፋ ለቆረጠ እግዚአብሔር መልስ አለው።

“…በዚህ ሁኔታ እንድሠቃይ ከምታደርገኝ ይልቅ ብትራራልኝና አሁኑኑ ብትገድለኝ ይሻላል”


ሙሴ

“እግዚአብሔር ሆይ! አሁንስ ይብቃኝ፤ ከቀድሞ አባቶቼ አልበልጥማና ነፍሴን ውሰድ”


ኤልያስ

“ከመኖር ይልቅ መሞት ይሻለኛል”


ዮናስ

የሰይጣን ዓላማ ተስፋ ማስቆረጥ ነው እነዚህ ከላይ ያናበብናቸው ንግግሮች ተስፋ የቆረጡ ሰዎች የተናገሯቸው ናቸው።

እርግጥ ነው ሁሉንም ተስፋ እንዲቆርጡ ያደረጋቸው የተለያዩ ምክንያቶች ነበሩዋቸው። ይሁን እንጂ ሞትን

እስኪመኙበት ድረስ የሚያደርስ ምን ዓይነት ጠንካራ ምክንያት ቢያጋጥማቸው ይሆን ብለን መጠየቃችን አይቀርም።

ተስፋ መቁረጥ ለብዙዎቻችን አዲስ ነገር አይደለም። በሕይወታችን ተስፋ የቆረጥንባቸው የተለያዩ ወቅቶች እንደነበሩ

በቅጡ እናስታውሳለን። ብዙ ጊዜ ተስፋ መቁረጥ ወደ ተስፋቢስነት ወይንም ወደ ተስፋ ማጣት ደረጃ ያደርሳል። ያኔ ነው

አደገኛ የሚሆነው። የጦር መሪ ፍጹም ተስፋ የቆረጡና ፈሪ ወታደሮች ይዞ ጠላትን ለመግጠም ወደ ጦር ሜዳ

አይሄድም።

ምክንያቱም ተስፋ የቆረጡ ወታደሮች ገና ጠላታቸውን ሳይገጥሙ አስቀድመው የተሸነፉ በመሆናቸው ነው። ለዚህ ነው

ወደ ጦር ሜዳ ለመሄድ የሚዘጋጁትን ወታደሮች ሞራል ከፍ ለማድረግ ከፍተኛ ፉከራና ቅስቀሳ የሚደረገው።

ፍጹም ተስፋ የቆረጠ ሰው በኑሮው ላይ የሚጋጥሙትን ልዩ ልዩ እንቅፋቶችና ትግሎች በቆራጥነት ታግሎ በማለፍ ፈንታ

በመሸነፍ እጁን ይሰጣል። ለዚህ ነው ተስፋ የቆረጠ ሰው ተሸናፊ ሰው ነው ያልነው። በመንፈሳዊ ዓለም ውስጥ ሰይጣን

አንድን ክርስቲያን ተዋግቶ ለማሸነፍ ቢፈልግ ወደ አማኝ ሕይወት ታግሎ ሊጥለው የማይችለውን ፈተና መላክ

አያስፈልገውም። በቅድሚያ የሚያደርገው ነገር ቢኖር የዚያን ሰው ስሜትና ፍላጎት ማዳከም ወይንም ቢቻል መግደል

ነው። ያ ሰው በተደጋጋሚ ለሚቀርብለት ውጊያ ሁልጊዜ አሸናፊ ሆኖ መኖር እንደማይችል ማሳመን ብቻ ነው።

እንደምናወቀውና በሕይወታችንም እንደተለማመድነው የሰይጣን ዋና ጥረቱ የእግዚአብሔር ልጆች ገና ትግል ውስጥ

ሳይገቡ “ተሸንፌአለሁ” ብለው ከውጊያው እንዲወጡ ተስፋ ማስቆረጥ ነው። ስለዚህ በዚህ ሰይጣን በሚጠነስሰው

የተስፋ መቁረጥ ስሜት ተሸንፈን እዳንወድቅ በየዕለቱ በንቃትና በትጋት መዋጋት ያስፈልገናል። ይህ የተስፋ መቁረጥ

ስሜት የሚያጠቃው በእምነታቸው ደካማ የሆኑትን ክርስቲያኖችን ብቻ ሳይሆን ብሩቱዎ ችንም ይነካል። የጥንት

መንፈሳዊ አባቶችም በዚህ ስሜት ተጠቅተዋል። ከእነርሱ ውስጥ ሶስቱን ታላላቅ የእግዚአብሔር ሰዎችን ልምምድ

ከዚህ ቀጥሎ እናቀርብላችኋለን።


1. ሙሴ -“አሁኑኑ” ሙሴ እግዚአብሔር በሕይወቱ ብዙ አስደናቂ የሆኑ ነገሮችን ሲሠራ በግልጽ ያየ ሰው ነበር።
የእግዚአብሔርን ትክክለኛና ግልጽ የእጆቹን ሥራ አይቷል በግል ሕይወቱም ከመጀመሪያው ጀምሮ (ዘጸአት 2፥1-10)

ድል በድል እየደራረበ የሰጠው ሰው ነበር። የእሥራኤልን ሕዝብ ከግብጽ ባርነት አውጥቶ በበረሃ ውስጥ መርቶ ወደ ከነዓን

ምድር እንዲያደርስ እግዚአብሔር ያዘጋጀውና በልዩ መንገድ ያሰለጠነው ሰው ነበር።

አርባ ዓመት በዝምታ በምዲያ በረሃ (ዘጸአት 2፥15) እንዲቆይ ካደረገው በኋላ ልዩ ኃይልና ጸጋ አልብሶት ወደ ግብጽ

መለሰው። እግዚአብሔርም ለእሥራኤል ሕዝብ መሪ እንዲሆን ሙሴን እንደመረጠው ምልክትና መረጃ እንዲሆነው ልዩ

ልዩ ተአምራቶች የሚያደርግበት ልዩ ኃይል ሰጥቶ በፈረዖን ፊት እንዲቆም አደረገው (ዘጸአት 4፥1-9)። ሙሴ

እግዚአብሔር እያንዳንዱን የግብጽ ቤት በሞት መትቶ (ዘጸአት 12፥29-30) የእሥርኤልን ሕዝብ ከግብጽ ባርነት

እንዴት እዳወጣቸው ያስታውሳል። ቀይ ባህርን ባቋረጡበት ጊዜ እንዴት በደረቅ ምድር (ዘጸአት 14፥21-25)

እንዳሻገራቸው አይቷል። ሙሴ በተራራው ላይ ከእግዚአብሔር ጋር አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በቆየበት ጊዜ

የእግዚአብሔርን ክብር ከማየቱም በላይ ሥጋ ለባሽ የሆነ ሰው ሊኖረው የማይችለውን ዓይነት ቅድስናና ግርማ ለብሶ

ነበር (ዘጸአት 24፥12-18)። ይህን የመሰለ የድል ሕይወት የነበረው ታላቁ ሙሴ በተስፋ መቁረጥ ስሜት ይሸነፋል ብሎ

መገመት በጣም ያስቸግራል።

መጽሐፍ ቅዱስ የታላላቅ መንፈሳዊ ሰዎችን ድካማቸውን ሳይገልጽ የድል ሕይወታቸውን ብቻ የሚናገር ቢሆን ኖሮ እኛ

ደካማዎች ሰዎች ምን ያህል ቃሉን ገልጸን ለማንበብ በፈራን ነበር። ሙሴ “እኔ ይህን ሁሉ ሕዝብ ብቻዬን መምራት

አልችልም ይህ ኃላፊነት ለእኔ እጅግ ከባድ ነው! በዚህ ሁኔታ እንድሠቃይ ከምታደርገኝ ይልቅ ብትራራልኝና አሁኑኑ

ብትገድለኝ ይሻላል፤ ከዚያም በኋላ ከምታመጣብኝ መከራ እገላገላለሁ” አለ (ዘኁልቁ 11፥14)። ለመሆኑ ሙሴ ይህን

ከመሰለ ተስፋ መቁረጥ ደርጃ እንዲደርስ ያደርገው ምክንያት ምን ይሆን?

1. የእግዚአብሔርን ሸክም “እኔ ካልተሸከምኩ” በማለት ነው የእሥራኤል ሕዝብ በእግዚአብሔርና በእርሱ ላይ


ሲያጉርመርሙ ሙሴ ሰማ። “ሕዝቡ ሁሉ በየድንኳናቸው ደጃፍ ላይ በቡድን በቡድን ቆመው ሲያጉረምርሙ ሰማቸው

እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ተቆጥቶ ስለ ነበር በጣም ተጨነቀ” (ዘኁልቁ 11፥10)። የሕዝቡ ማጉረምረም ሙሴን ስለ

አስጨነቀው “ይህን ከባድ ነገር በእኔ ላይ ስለምን አመጣህብኝ? በእኔስ የማትደሰተው ለምንድነው?” ብሎ

እግዚአብሔርን ጠይቀው (ዘኁልቁ 11፥11)። እግዚአብሔር የእሥራኤልን ሕዝብ እንዲመራ ለሙሴ ኃላፊነቱን ይስጠው

እንጂ፥ እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ የሚኖረውን የራሱን ሥራና ኃላፊነት ትቷል ማለት አልነበረም። ለእሥራኤል ሕዝብ

የሚያስፈልገውን ሁሉ ለመስጠት ከጠላቶቻቸው ሁሉ ለመጠበቅ በበረሃ ጉዞአቸው ሁሉ አብሮአቸው ለመሆን ቃል

የገባላቸው ስለሆነ ቃሉን ማክበር የራሱ ኃላፊነት ነው። ሙሴ ከተስፋ መቁረጥ ደረጃ ላይ ለመድረስ የቻለው

የእግዚአብሔርን ሸክም “እኔ ልሸከም” በማለቱ ነበር። ሕዝቡ “መናው ሰለቸን፤ ሌላ የምንበላው ነገር የለንም” ብለው

ሲያጉረመርሙ፥ ሙሴ ለሕዝቡ ሥጋ የመስጠት ኅላፊነት ያለበት መስሎት ተጨነቀ። ያ ለሙሴ ከሰብአዊ አቅሙ በላይ

ነበር። የእርሱ ኃላፊነት ቢሆን ኖሮ በእርግጥም መጨነቅ ይገባው ነበር። ግን ሥጋ የመስጠት ኃላፊነት የሙሴ ሳይሆን

የእግዚአብሔር ነበር። ሙሴ ግን ያለአግባብ ተጨነቀ። ወዲያው ተስፋ ቆርጦ “መሞት ይሻለኛል” አለ። በእኛም ሕይወት
ውስጥ ተስፋ መቁረጥ የሚደርስብን እግዚአብሔር ሊሠራው የሚገባውን እኛ ካልሠራነው ብለን ስንታገልና የማይቻል

ሆኖ ስናገኘው ነው። የእግዚአብሔርን ኃላፊነት ለእግዚአብሔር ለመተው ትልቅ እምነትን ይጠይቃል። የራሳችንን ድርሻ

ከፈጸምን በኋላ የተቀረውን በእምነት ለእግዚአብሔር መተው ከተስፋ መቁረጥ ሕይወት መዳን ከመቻላችንም በላይ

በክርስትና ሕይወታችን ደስ ብሎን ወደ ፊት መራመድ እንችላለን። መጠንቀቅ ያለብን ግን የራሳችንን ድርሻ ማወቅና

ያንኑ በቅጡ ማከናወናችንን ነው። 2. ሕዝቡ ሲስት እርሱ እንደሳተ አድርጎ በመውሰዱ ሙሴ የእግዚአብሔርን ሸክም

“እኔ ካልተሸከምኩ” ማለቱ ብቻ ሳይሆን የሕዝቡን ማጥፈትና መሳሳት በእርሱ ምክንያት እንደሆነ አድርጎ በመውሰዱም

ተስፋ ወደመቁረጥ ደረጃ ደረሰ። የእሥራኤል ሕዝብ ሲስት እርሱ እንደሳተ አድርጎ ይወስድ ነበር። በማጉረምረማቸው

እምነተ ቢስ በመሆናቸው እርሱን ተጠያቂ እንደሚያደርገው አድርጎ ይወስደው ነበር። ሙሴ በወቅቱ ያተኮረው በራሱ

ሕይወት ላይ ነበር። እግዚአብሔር በዚህ ወቅት ነበር አንድ አዲስ ነገር ማደርግ የጀመረው። ያም ሙሴ ዓይኑን ከራሱ ላይ

እንዲያነሳ ማድረግ ነበር። ይኸውም፥ 1 ኛ ሙሴን በነበረበት ኃላፊነት እንዲያግዙት ሰባ ሰዎች ሰጠው። እነዚህ ሰባ ሰዎች

በሕዝቡ መካከል የሚነሱትን ጥቃቅን ጭቅጭቆች መስመር ሲያሲዙ መሴ ደግሞ ትላልቅ የሆኑትን የአስተዳደር

ሥራዎችን መሥራት ጀመረ። ሙሴ ለእሥራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር ሥጋን እንደሚሰጣቸው ቃል ገብቶላችው ነበር።

“እነሆ አሁን እግዚአብሔር ሥጋ ይሰጣችኋል፤ እርሱንም እስክትጠግቡ ትበላላችሁ። የምትበ ሉትም ለአንድ ወይንም

ለሁለት ቀን፣ ለአምስት፣ ለአሥር ወይም ለሃያ ቀን ብቻ አይደለም፤ እስኪያንገፈግፋችሁና በአፍንጫችሁ እስኪወጣ

ድረስ አንድ ወር ሙሉ ትመገባላችሁ” (ዘሁልቁ 11፥18-20) አላቸው። ሙሴ ለህዝቡ እንደገባላቸው ተስፋ መሠረት

እግዚአብሔር አደረገ። ሙሴ እዚህ ላይ ያደረገው ነገር ቢኖር እግዚአብሔር ፍላጎታቸውን እንደሚያሟላ ብቻ ነገራቸው

እንጂ ሥጋ አልሰጣቸውም። ሙሴ ችግሩን ለብቻው በመሸከም ፈንታ ወደ እግዚአብሔር አስተላለፈው። የተስፋ

መቁረጥ ዋናው ምክንያት አማኝ አይኑን በራሱ ላይ በማሳረፍ አቅም ሳይኖረው አቅም እንዳለው እራሱን በመቁጠር

እግዚአብሔር ያላሸከመውን ኃላፊነት ለመኸከም ሲሞክር ነው። በራሱ ላይ ማተኮር የለመደ ሰው፥ ሁሉንም ነገር

የሚመዝነውና የሚመለከተው በራሱ አንጻርና እርሱን በሚመቸው አቅጣጫ ብቻ ነው። ታዲያ ሁኔታዎች ከእርሱ

እንደሚያስበውና ለራሱ እንደሚመቸው ካልሆኑ ቶሎ ይበሳጫል ቶሎ ተስፋ ይቆርጣል። በሚቀጥለው ክፍል

እንክንገናኝ፥ የጌታ ጸጋና ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን።


ንስሃ

1. አቤቱ መልሰን ፊትህንም አብራ እኛም እንድናለን ፡፡መዝ 80፡3

2. አሁን በዚህ ስፍራ ለሚፀለይ ፀሎት ዓይኖቼ ይገለጣሉ ፤ጆሮቼም ያደምጣሉ 2 ኛ ዜና 7 ፤15

3. በስሜ የተጠሩት ህዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው ቢፀልዩ ፤ ፊቴንም ቢፈልጉ፤ ከክፉ

መንገዳቸውም ቢመለሱ፤ በሰማይ ሁኜ እሰማለሁ ፤ኃጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ ፤

ምድራችዉን እፈውሳለሁ፡፡ 2 ኛ ዜና 7 14

ውጊያ

1. የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ


ቀን 09/04/2016

ለ ENG

ጋምቤላ

ጉዳዩ ፡- አማኑኤል ቼንኮት፣ የሱነሽ እና ጓደኞቻቸው ደረቅ እንጀራ አቅርቦት ህብረት ሽርክና

ማህበር ሥራን ይመለከታል

ከላይ በርዕሱ ለመጥቀስ እንደተሞከረው አማኑኤል ቼንኮት፣ የሱነሽ እና ጓደኞቻቸው ደረቅ

እንጀራ አቅርቦት ህብረት ሽርክና ማህበር 5 አባላትን በማሳተፍ ከተቋማችሁ በተሰጠን

የገንዘብ ድጋፍ ከኅዳር ወር 2014 ዓ/ም ጀምሮ ለሥራው የሚያስፈልጉትን ግብያቶችን

በማሟላት ለረጅም ጊዜያት ሥራውን በጋር በመሥራት ላይ መቆየታችን ይታወቃል ፡፡

ሆኖም በተለያዩ ምክንያቶች ሥራውን መቀጠል ባለመቻሉ ለድርጅቱ ሪፖርት ያደረግን

ሲሆን ለሥራው የሚያስፈልጉትንም ማለትም በእጃችን የነበረውን ንብረቶች ተመላሽ

አድርገናል ፡፡

በመሆኑም አማኑኤል ቼንኮት፣ የሱነሽ እና ጓደኞቻቸው ደረቅ እንጀራ አቅርቦት ህብረት

ሽርክና ማህበር አበላት የነበሩ የማህበሩን ሥራ ለማቋረጥ የቻሉበትም ምክንያት ፡-

1. ወጣት ቼንኮት ጀምስ ሥራው ለቅቆ የትምህርት ዕድል አግኝቶ በጅማ ዩነቨርሲቲ

በትምህርት ላይ የሚገኝ ሲሆን ፤

2. ወ/ሮ የሱነሽ ገ/ሚካኤል ጋምቤላ ከተማን በመልቀቅ ወደ አዲስ አበባ ተዛውረው

እዚያው በመኖር ላይ የሚትገኝ፤


3. ወ/ሮ ሽብሬ አበራ የሥራ ፍላጎት የሌላት እና በተደጋጋሚ ጊዜያት ጥሪ ቢደረግላትም

ለመገኘት ፍቃደኛ አይደለችም ፤

4. ወ/ሮ ጆርጌ ሙሉጌታ የመንግሥት ሥራ አግኝታ ከማህበሩ ለመልቀቅ ችላለች ፡፡

ስለዚህ ድርጅቱም የማህበሩ ሁኔታ ያለበትን ደረጃ ከላይ የተጠቀሰ መሆኑ ታውቆ የዚህ የሥራ

ዕድል ፈጠራ ባለቤት እና አማኑኤል ቼንኮት፣ የሱነሽ እና ጓደኞቻቸው ደረቅ እንጀራ አቅርቦት

ህብረት ሽርክና ማህበር ያቋቋምኩት እኔ ስለሆንኩ ድርጅቱ ይህን ተገንዝቦ በኢትዮጵ ንግድ

ባንክ የሚገኘውን ገንዘብ በማንቀሳቀስ ሥራ ላይ ማዋል እንዲችል ጉዳዩን ለሚመለከታቸው

አካላት እንዲያሳውቅ ሲል አመለክታለሁ ፡፡

“ ከሠላምታ ጋር “

አቶ አማኑኤል ለማ

You might also like