Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 14

የክርስቲያኖችን መታረድ እንዴት እናስቁም?

ከሰይፈስላሴ

በዝቋላ የካቲት ፲፪ ቀን ፳፻፲፮ ዓ/ም ዓለምን ጥለው በምናኔ የሚኖሩ የአገርና የሃይማኖት መሠረቶች፥ የሞራልና የቅድስና ልኬት
በመሆን የትውልድ ብርሃን የደብረ ከዋክብት መነኮሳት ታረዱ። ይህ ባለፉት ፮ ዓመታት ያላመቋረጥ በመላው አገር በተለይ
በኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል እና የኦሮሞ ልዩ ዞን ተብሎ የኦሮሚያ መንግሥት ድጋፍ የማይለያቸው ቦታዎች
የተለመደ ሥርዓታዊና መዋቅራዊ ዘመቻ ነው።

ይሁንና የሚታረዱቱ ከ፸ ሚሊዮኖች የሚበልጡቱ ክርስቲያኖችና በእረኝነት የተሰየሙት ወገኖች በየቀኑ የሚካሄደውን
መዋቅራዊ ክርስቲያኖችን የማረድ፥ የማፈናቀልና የማደኸየት መርሐግብር ቆመው ይመለከታሉ፤ ቢበዛ ክርስቲያኖች ሲታረዱ
እኛ ዜና እየሰራን ፌስ ቡክ ላይና ዩቲዩብ ላይ መጫን፥ ሰልፍ ወጥተን ሻማ እያበራን ጥፋቱን ከማስቀጠል በስተቀር ጥፋቱን
የሚኣስቆም አንዳች የታሰበበት ተግባር አልፈጸምንም።

ይሀን ግልጽ የሆነ የወገን ጥፋት ማስቆም የሚገባን እኛ የሚገባውን ባለማድረጋችን በእግዚአብሔርም ሆነ በትውልድ ፊት
በግድያዎቹን ሁሉ አብረን እየፈጸምን መሆኑን ዘንግተናል። “አንተ ግደል እኛ ደግሞ ሻማ በፊስ ቡክ እናበራለን” ብለን
ከሰይጣን ጋር ውለታ የገባን እስኪመስል ተባባሪ እየሆንን ነው። እኛ ሀላፊነት የለብንምን?

ይህ ለኛ ለኦርቶዶክስ አማኞች የቀረበ ፈተናስ ቢሆን? ፈተናውን እናልፋለን ወይንም እንወድቃለን። በመጨረሻው እኛም
“እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ። (ማቴ 25፥42) ተርቤ አላበላችሁኝምና፥
ተጠምቼ አላጠጣችሁኝምና፥ እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝምና፥ 43 ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፥ ታምሜ ታስሬም
አልጠየቃችሁኝምና” ከመባል አናመልጥም። በመጨረሻው ስንጠየቅ “አይ እኔ በፌስ ቡኬ ሻማ አብርቻለሁ” ወይንም “አቡኑ
እንትና አድርግ ቢሉኝ ኖሮ፤ እነሱ ስላላዘዙኝ ኖሮ አበላ፤ አጠጣ፤ አጠይቅ ነበር ብለን እናመልጥ ይሆን? ወይስ እኔ የወንድሜ
ጠባቂ ነኝን ብለን እንቃየል ለማምታታት እንሞክራለን?

በሥጋ ቆሞ በሠራው ኃጢአት እየዋተተ ተሰዳጅ ነኝ ከሚለው ነፍሰ ገዳዩ ቃየል ይልቅ በሥጋ የሞተው እውነተኛው የአቤል
ደም በእግዚአብሔር ዘንድ ከፍ ያለ ድምጽ አለው። እኛም የቆመን ገዳዮች የሚምሩን መስሎን የወንድሞቻችንን እልቂት
በዝምታ የምናልፈው የቁም ሙቶች የሆንን የዛሬዎቹ ሚሊዮኖች ኦርቶዶክሳውያን ከገዳዮቹ እኩል በሟቹቹ ደም ከሳሽነት
በፈጣሪያችን ፊት እንጠየቃለን። እንደ ቃየል “ እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝን” ብለን ከአምላካችን ጋር መከራከር አንችልም ።
የሚገባን ፍርድ አይቀርም።

የሚያዋጣን ክርስቲያኖችን የሚፈጅ፥ የሚያስፈጅ ፖለቲካዊ ሥርዓት፥ የዘር ፓርቲ፥ የዘር ሕገ መንግሥት፥ የዘር ክልል ተቀብለን
በነፍስም በሥጋም ሙታን ከመሆን ዛሬውን እግዚአብሔር የሚወደውን ግፍና ግፈኞችን በማስወገድ ተግባር እንሰማራ።
በቤተ እምነት ውስጥ መሽገው እረኝነታቸውን በመዘንጋት ለገዳዮችና አስገዳዮች ሽፋን የሚሰጡትን እንደ ነፃ አውጭና
መፍትሔ ሰጭ አድርገን ከሚያጠብቅ የባርያ ስነ ልቦና ነፃ እንውጣና ለሚገፉት መቆምን ስለ መዳናችን ብለን እንፈጽመው!!!
መቼ? ዛሬ! አሁን!

ፈተናው አዲስ አይደለም

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ከርስቲያን ብዙ ግዜ ተፈትና ጠፋች እስከሚባልበት የደረሰችበት ጊዜ ነበር። ይሁንና
በፈጣሪ ድጋፍ የጠነከሩና መከራውን ለመቀበል የተዘጋጁት አንገታቸውን ለሰይፍ እየሰጡ ክርስትናን በዚህ ሀገር አስቀጥለዋል።
በተቃራኒው ይህንን ባለማድረጋቸው ደግሞ እንደ ትላልቅ የክርስትና መአከል የነበሩት እነ ሊቢያ፤ ግብጽ፤ ሱዳን፤ የመን፤
ኢራን፣ ኩርዲስታን፣ ቁስጥንጥንንያ ያሉ ክርስትያኖች ጠፍተዋል። እነዚህ የዮዲት፤ የግራኝ አህመድ፤ የካቶሊክ፤ የግራዚያኒ
ሰይፍ ያላስፈራቸው የክርስቲያን ደሴት የተባለችውን ሀገር ፈጥረው ሰጥተውናል።

ዮዲት

ዮዲት ጉዲት ለ40 አመትታት የኢትዮጵያን ኦርቶደዶክስ እምነት አሳዳ አቃጥላ ጨፍጭፋ ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት
ሞክራለች። በዛን ዘመን የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር በመቶ ሺዎች የሚቆጠር እንጂ ሚሊዮንም አይደርስም። (ወደ ኋላ ሄደን
የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር በ2።5% ያድጋል ብለን ብናስብ የኢትዮጵያ ህዝብ በመቶ ሺዎች እንጂ በሚሊዮን የሚቆጠርም
አልነበረም። ከዚህም መሀከል አሳዳጅ የይሁዳ እምነት ተከታዮችና ተሳዳጆች ደግሞ ክርስቶስኖች ነበሩ።

ክርስትና ገና ጀማሪ ሲሆን የይሁዳ እምነት ደግሞ ስር የሰደደና ጠንካራ ነበር። ይሁንና ክርስቲያኖች በየ ጋራውና ዋሻው
እየተደበቁ ክፉውን ግዜ በማሳለፍ የክርስትናን እምነት ለልጆቻቸው አውርሰው አልፈዋል።

ግራኝ

ግራኝ አህመድ ለ17 አመት ካገር አገር እየዞረ ቤተ ክርሲያኑን አቃጥሏል፤ አስገድዶ እያሰለመ፤ እንቢ ያለውን ደግሞ አንገቱን
በሰይፍ እየቀጠፈ ሌላውን ደግሞ በሰንሰለት እያሰረ ወደ የባርያ ገበያ እያቀረበ (export) አደርጎታል። ዛሬ አንዳንድ የጃማይካ
ታሪክ ጸሀፊዎች እኛ በግራኝ አህመድ ግዜ ከሸዋ ከጀማ ወንዝ አካባቢ ተይዘን የተሸጥን ነን ይላሉ። መልካቸውም ከምስራቅ
አፍሪካ መሆኑን ይጠቁማል።

ይሁንና ግራኝ አህመድ ለ17 ዓመት (በፈረንጆቹ 1527 እስከ 1543) ቀጥቅጧል ይሁንና ክርስትን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት
አልቻለም። ከዚህ ቅጥቀጣ ክርስቲያኑ ሳያገግም ካቶሊኮቹ ደግሞ በግድ ካቶሊክ ካልሆናችሁ ብለው ብዙ ክርስቲያኖች
እንዲያልቁ ምክንያት ሆኑ።
ከዛ የተረፈው ደግሞ ከደቡብ ወደ ሰሜን የፈለሰው በርካታ የደቡብ ክርስቲያኖችን አጥፍቶ ወይም በሞጋሳ ባርያ አድርጎ ለሶስት
መቶ አመታት በላይ ያለ ክርስትና እንዲኖሩ አድርጓል። የወላይታ ህዝብ ታሪክ ማንበብ ይበቃል። ከዛ በድጋሜ ክርስቶስ
የተሰበከለት ከሚኒሊክ ግዜ ቦኋላ ነው። ዛሬ ይግፍ ለምን ተወገደ ብለው ያንን ለመድገም እየሞከሩ የሚገኙ የቱርክና የአረቦቹ
የውስጥ ሠራተኞች ቤተምንግሥትና ጫካ ከሚገኘው የጎሣ ነጻ አውጭ ነኝ ባይ ጋር ተዛዝሎ ፍጅት እየፈጸመ ነው።

ያልገባው ኦርቶዶክሳዊ ይህንን መንግሥት መፍትሔ ስጠኝ እያለ ይጣራል። ኦርቶዶክሳዊ ሆይ አትደንዝዝ፥ ራስህን ነፃ አውጣ!

ጣልያን

ጣልያን ሲመጣምም እንዲሁ ኦርቶዶክስን ለማጥፋት ከካቶሊኩ ጳጳስ (ፓፕ) ጋር አብረው በርካታ ቤተ ክርስቲያንን
አቃጥለዋል። የ Ian Campbell, The Holy War የሚለውን ላነበበ 750 ሺ ሰው ተጨፍጭፋል። መናንያንንና ገዳማትን
አቃጥሏል፤ ከየገዳሙ ቄስና ዲያቆንን እያፈስ ከመቋድሾ ወጣ ብሎ ባቋቋሙት የዲናኔ በምትባል ኮንሰትንትሬሽን ካንፕ ውስጥ
በማጎር ብዙዎችን በሙቀት፡ በረሀብ፤ በጥማትና በኮሌራ ጨርሰዋል። በዚህ መሀከል እንደነ አቡነ ጴጥሮስ በፒያሳ አቡነ
ሚካኤል ደግሞ በጎሬ አደባባይ ተረሽነው ነው ሀይማኖታችንን ያቆዮልን። በእንዚህ ጀግና አባቶች መንፈስ እንጂ የፖለቲካ
ካድሬነትን ድርበው፥ የከተማ ቀምጥለነትና ድሎት ያሰጠማቸውን በጎኃና በዘር የሚደራጁትን የዛሬዎቹን ስንኩልና ሰነፍ
የሐሰት መነኮሳትን መፍትሔ ሰጭ አድርገህ ከመጠበቅ ጤናማ ኦርቶዶክሳዊ አባቶችህን ለይ። ለራስህ ዘብ ቁም!!!

ደርግ

ባለፉት 50 አመታት ውስጥ ደግሞ ማርክስ ሃይማኖት “የጭቁን ህዝብ ማደንዘዣ ሀሺሽ ነው” ብለው ፈረንጆቹ ለተማሪዎቹ
አስጠንተው ላኩዋቸው። ተማሪዎቹ ደግሞ ያጠነትን ይዘም መጥተው ክርስትናን ከዚህ ምድር ለማጥፋት በጣም ደከሙ።
ካሪኩለም ተዘጋጅቶ፤ መጽሐፉ ከሩሲያ ተተርጉሞ፤ የዮኒቨርስቲ ፕሮፌሰሮች ተመርጠው ተማሪው በፊሎዞፊ 101 እና 102
እግዚአብሄር የለም የሚለውም የአይምሮ አጠባ ተሰጥቶት ብዙ ክዶ እርስ በእርሱ ተጨራርሶ አለቀ።

በየ ቀበሌ ማህበሩ (ከነማ)፤ ወጣቶች ማህበር (መኢወማ)፤ በሴቶች (መኢሴማ)፤ ታዳጊዎች ማህበር፤ የገበሬ ማህበር
(መኢገማ)፤ የሰራተኛ ማህበር (መኢሰማ)፤ የመምህራን ማህበር እና በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የማርክሲዝምና የሌኒንዝም
ትምሀርትና ንቃት ተብሎ ሁሉም አርብ ከሰዓት በኋላ ስራ እየቆመ “ሰው ከዝንጀሮ ነው የመጣው፤ ሃይማኖት የጭቁኑ ህዝብ
ማደንዘዣ ሀሺሽ ነው ተብሎ ንቃት እየተሰጠ ሃይማኖትን ለመጨረሻ ግዜ ለማጥፋት ሰርተዋል። ህወሓትም ኮሚኒስት ስለነበረ
በትግራይ ህዝብ መሀል ይሄንን አስተምሮ ነው በመላው ኢትዮጵያ ያስቀጠለው። ። በአቶ ስብሐት ነጋና አባይ ጸሀይ
የሚመራው ቡድን መናንያንን ከገዳም እያወጣ በሰንሰለት እያሰረ ገረፈ ከምንንና ሳይቀር ከማስወጣት ሞክሩዋል። እንደውም
ስብሀት ነጋ አማራውንና ኦርቶዶክሱን አከርካሪውን ሰብረነዋል ብለው በድፍረት አውጀው ነበር።

በዚህ ሂደት ለክርስቶስ አምላክነት፥ ለሰው ልጅ ክብር፥ ለማርክሲዝም ክህደት በምስክርበት የሚቆም፥ በሰማዕተነት የክህደት
ጎርፍን የሚገድብ አባት ከቤተ እምነቶቹ ጠፋ፥ አንዳንድ እምነቶች ኦርቶዶክስ እስከተመታችለት ድረስ የእኔን የበላይነት
ያስገኛል በሚል ስሌት በጥንቃቄ ከአጥፊዎች ጋር ተባበረ፥ አንዳንድ በዘርኝነት ፖለቲካ የታወሩ ድርጅቶችም ደርግን
ተጠቅመው የሚጠሉትን ወገን አስጨፈጨፉ። ደርግ ወደቀ፥ ከደርግ የከፋ ተተካ --- ኦርቶዶክሳውያንን በጎሣ ከፍሎ
የሚያጋድል የ36 ዓመት መከራ ተዘረጋ --- ቤተእምነቶቹ አሁንም ከገዳዮች ጋር እየተሻሹ የመሪዎችን ምቾት በማስጠበቁ ላይ
አተኮሩ።

ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን ሆይ አትፍዘዝ፤ ራስህን ነፃ አውጣ። በቅዱሳት መጽሐፍትና በሐዋርያት ቀኖና ራስህን እየጠበቅህ
አስመሳዮችን ተዋጋቸው!!! ነፃ አውጭ፥ ፍትሔ ሰጭ የለም!!!

አብይ

አብይ የህወሓት ልጅ ነው። ይሁንና የሱ ደግሞ እንደ ግራኝ አህመድን፥ የግራዚያኒንና፤ የኮሚኒስቱን ዘመቻ አቀላቅሎ ነው
የመጣው። በአንድ እጁ በደቡብ አሜሪካ የተጻፈውን የብልጽግና መጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ይዞ ሃይማኖት ቀይሩ፤ ደሀ
የሆናችቡት ከርስቶስ ለደቀመዝሙሮቹ ያስተማራቸውን ስላላከበራችሁ ነው።

በሉቃስ ወንጌል ም 8 ቁ3 ላይ “3 እንዲህም አላቸው። በትርም ቢሆን፥ ከረጢትም ቢሆን፥ እንጀራም ቢሆን፥ ብርም ቢሆን
ለመንገድ ምንም አትያዙ፥ ሁለት እጀ ጠባብም አይሁንላችሁ።” ይህ ስህተት ነው ሀብትም ወርቅም እንድታካብቱ
የአሜሪካኖቹን የስነልቦና መምህራን መጽሐፍ ተቀበሉ ይላል። ከዛ ደግሞ እንደ ግራኝ አህመድ ሰይፍ የታጠቀ ሰው በየገዳሙና
ቤተ ክርስቲያኑ እየሄደ የሚያርድ ይልካል። እንደ ግራዚያኒ ደግሞ በድሮንስ ከሰማይ ይደበድባል፤ እንደ ኮሚኒስቶቹ ደግሞ
ገነት ማለት አበባ ያለባት ቦታ ናትና እዚህ ፈጥሬያለሁና እዙሁ ገነት ግቡ ይላል። እኔንም አምላክ ብላችሁ አክብሩኝ፣ ፍጹምና
የሚተካኝ የሌለን ነኝ እስከማለት ደርሷል።

አብይ አህመድ ከሁሉም ክፋቶች ቀምሞ የመጣ ክፉ መንፈስ ነው። ዮዲት፤ ቫቲካን ካቶሊክና ግራኝ አህምድ ሀይማኖቴን
ቀይሪያለሁ የናንተን ተቀብያለሁ ካሏቸው አይገድሉም ነበር። ግራዚያኒ የሞሶሎኒን ንጉሥነት ተቀብያለሁ ካለ እንደውም ባንዳ
አድርጎ ሾሞ ፓስታና ቪኖ ጠጣ ይል ነበር። ኮሚኒስቶችም በሰማይ ላይ ገነት የለም እዚሁ ነው ብሎ ያመነላቸውን፥ ያዘዙትን
የሚያደርግላቸውን አላጠፋም። አብይ ግን ሁሉንም ብንቀበልለት ስንኳን በህይወት መኖር አይፈቅድልንም።

በዝቋላ የታረዱት መነኩሴዎች አልደረሱበት፤ አልመጡበት፤ ለስልጣንና ለጥቅም ተፎካካሪ አይደሉ። ቆሎ ቆርጥመው ጫካ
ውስጥ ተኝተው አምላካቸውን ቀንም ሌሊትም ሲያወድሱ በመኖራቸው ምን አደረጉት። እነዚህን ምንም ያላደረጉ መናንያንን
ያረደ አቡነ ማትያስን፤ እነ አቡነ ኤርሚያስን እነ ዳናኤል ክብረትን አያርድም ብለን ማሰብ እንችላለን? ለጊዜው ያቆያቸው
የሚሠራውን ሽፋን እየሰጡለት ለ፮ ዓመታት ፕሮጄክቱ ግጭት መስሎ፥ ሸኔ መስሎ፥ የሚያልፍ መስሎ አንዲቀጥል እድል
ስለሰጡት ነው።

ሌላው ሲታረድ እኔ ጋ አይደስም ብሎ በየ ስጋ ቤቱ ቁርጥ እየበላ ክሽን የሚጠጣው የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ መታረዱ
አይቀርም።
ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን ሆይ በግልህ ወስን፤ የዳንኤልን ማጭበርበር፥ የአቡነ አብርሃምን “ተማክረን እንፈተዋለን”፥ የገዳማት
መምሪያውን መነኩሴ “ምንግሥት ምን ያድርግ አንዱን ሲያረጋጋ ሌላው ይፈነዳበታል” የካድሬነት አገልግሎት፥ “የንጹሕ
ኦሮሞው” የአቡነ ገብረኤልን “እኛ ጦርነት አናውጅም፥ ወንጌል እንሰብካለን”፥ የአቡነ ሩፋኤልን “አንብይንና ዘሩን ይባረክ”
ወዘተ ማደንዘዣ አትዋጥ። ቁም! ነፃ አውጭ እና መፍትሔ ሰጭ የለም -- ራስህን ነፃ አውጣ! ከእውነተኞች፥ ሰብአዊነትና አገር፥
ታሪክና እኩልነት ከሚገባቸው የእግዚአብሔር ምሳሌነታቸው ካልተፋቀባቸው ተጋዮች ጋር ቁም!!! በምድርም በሰማይም
ራስህን አድን!

ለምን?

ሃይማኖት የሥጋዊ ተጋድሎ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ ተጋድሎን በተዋህዶ የሚይዝ ሁለገብ ዓይንና ድርጊት ያለው ነው።
እግዚአብሔር የሚጨበጠውን ዓለምና ሆድ ብቻ አልፈጠረም፥ መንፈሳዊውን ርስትና አሁን ያለውን ከትንሳዔ በኋላ የሚኖር
መንፈሳዊ ሰውንም ጭምር እንጂ።

ይህን በሰው የተመሰለ ኣብይ አህመድ የተባለ የ75 ዓመታት የክህደት ጥርቅም ያረፈበት የሕወሐትና የኦነግ ድቅል ሰይጣን
አግዚአብሔር ለምን አመጣው?

ውጭ ያሉ የኢትዮጵያዊነትና የኦርቶዶክሳዊነት ታሪካዊ ጠላቶች ለምን ለ፮ ተከታታይ ዓመታት ደም ሲያፈስ፥ አገር ሲያፈርስ፥
ሃይማኖት ሲያረክስ ደገፉት?

ቱርክና አረቦች ለምን መግደያ ሰጡት?

ጽንፈኞቹ የዘር ፖለቲካን ከአልቃይዳ አይነት እስልምና ጋር ቀላቅለው ለምን ተባበሩት? ወዘተ የሚሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ!!!

መልሱ አንድ ነው ሰይጣን የተሸነፈበትን እና በእርሱ ትምህርት ተመርተው የሰው ልጅን ባርያና ጌታ፥ ባለ ርስትና ርስት አልባ
ያደረጉትን ወገኖች በዚህ ሃይማኖት በኦርቶዶክሳዊ ክርስትና በተሠራ ሕዝብ እንደተሸነፉ ያውቃሉ።

አብይ የእነዚህ ሁሉ ተበቃይ ሠራተኛ ነው። የአብይ ተልእኮ ሃሀይማኖቱን ማጥፋትና “አዲሲቷ” የሚላትን ጣዖት አምላኪ
ኢትዮጵያ መፍጠር ነው። ካልተቻለ ኦርቶዶክሳውያኑን ደምስሶ ትናንሽ በኦነግ-ዉሀቢያ-ኦሮሙማ መንፈስ ሥር ባርያ ሚሆኑ
ዜጎችን የምታቀፍ “ኦሮሚያ” መፍጠር ነው።

ይህንን እየፈጸመ ያለው ከውጪም ከውስጥም የክርስቶስን ተከታዮች በማሳደድ ነው። የሐሰት ጳጳሳት፥ የሐሰት ገዳማት፥
የሐሰት አህጉረ ስበከቶችን በመፍጠር ገዳማትን መናፈሻ፥ አድባራትን ሙዚየም ማድረግን ይጨምራል። ቅርሥ ዘረፋው፥
ኦርቶዶክስን ከሰማያዊ ዓላማ መለየት፣ በአካል ደግሞ በእምነቱ የጸኑትን ከምድርም በጦር መደምሰሱ፥ የክርስቲያን አሻራ
ያላቸውን ከተሞች ሰም መቀየሩ የዚህ ፕሮጄክት አካል ነው። ይህን የተማረው ከሂትለርና ከሞሶሎኒ ነው። የቫቲካን፣ ሂትለር
የሉትር፥ ሞሶሎኒ፣ የአልቃኢዳ አይነት ፀረ ሰው የልጅ ልጅ ናቸው።

ለምሳሌ ጣልያን ኢትዮጵያን ሲወርር እነ አቡነ ጴጥሮስ በፒያሳ፤ እነ አቡነ ሚካኤል በጎሬ ወስዶ ረሽኖ ነበር። በሌላ በኩል
“ሥጋን የሚገድለውን የፈሩ” እንደ አቡነ አብረሃም ደግሞ እነ አቡነ ጴጥሮስ ሲገድሉ ከግራዚያኒ ጵጵስና ተቀብለው ጣልያንን
ለማገልገል የፋሺስት ሲኖድስ ፈጥረው ነበር።

“On 27 November 1937, Marshal Rodolfo Graziani convened an assembly of Ethiopian


clergymen to elect a new archbishop. Abune Abraham, bishop of Gojjam, was elected.
However, the Holy Synod of the Coptic Orthodox Church of Alexandria under Pope John XIX
declared the election illegitimate and excommunicated the new archbishop. Ignoring the
interdiction of the Holy Synod and the Pope, Abune Abraham and his successor Abuna
Yohannes XV (r. 1939–1945) designated eleven bishops in order to constitute a full
ecclesiastical hierarchy before the Italian occupation ended in 1941”

ስለዚህ እነ አቡነ አብረሃምና እነ አቡነ ዮሀንስ የተነሳሳውን ክርስቲያን አመጽ ለማብረድ እሳት የለኮሰበትን የአራዳውን ጊዮርጊስ
ቤተ ክርስቲያን ጣልያን እያደሰው ነው እያሉ ሕዝብ ሲያታልሉ ነበር። የወደመውም የደብረ ሊባኖስን ገዳም እገነባለሁ
ብልዋል እያሉ ለግራዚያኒ አማላጅ ይሆኑ ነበር። ዛሬም እንዲሁ አይነት ለሰይጣን ቅኔ የሚቀኙ ዝማሬ የሚያወጡ ቄሶች አሉ።
እነ አቡነ አብረሃም በሰላም በባርነት እንዲኖር እንዲያስተምሩ ተደርገው ነበር። አቡነ አብረሃም ብዙም ሳይቆዮ ሞቱ ወይንም
ተጠሩ። በእግራቸው አቡነ ዮሀንስ ተተኩ።

የግራዚያኒ ጭካኔ የባሰውን የኦርቶዶክ ክርስቲያኑን አነሳሳብን ብሎ ሞሶሎኒ እራሱ ግራዚያኒን ክአዲስ አበባ አንስቶ ወደታች
ወደ አስመራ አሽቀነጠረው። አብረው የመጡትንም የካቶሊክ ቄሶች አባሮ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መቃጠል እንዲቆም
የተቃጠሉትም ትላልቆቹ እንዲገነቡ አዞ ነበር። ይሁንና አርበኛው ጊዜ ሳይሰጠው ከመሰረቱም ስለተሸነፈ ኮተቱን ጥሎ ወጣ።

ክፋትን ያወገዙት እነ አቡነ ጴጥሮስና አቡነ ሚካኤል ሀውልት ቆሞላቸው ታሪካቸው ለሺ ዘመናት ሲተረክ የሚኖረው
“ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል፤ ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል።”ማቲዎስ ወንጌል 16_25 እንዲል
ቅዱሱ መጽሐፍ በተቃራኒው ስለ ሥጋቸውና ድሎታቸው ከክፉዎች ስር ሰግደው ሕዝብ ሊያሰግዱብየሞከሩትብስም
አጠራራቸው ከዲያብሎስ ጋር ተደምሮ በተቀድሰ ትውልድ ሁሉ “እክሕደከ ሰይጣን” ባሉ ቁጥር በሰይጣን የግብር ልጅነታቸው
ይወገዛሉ።

ፈርተው ስጋቸውን ለማዳን የሞከሩት ስጋቸው እንደማንኛውም ሰው ተቀበረ። ሰለነሳቸውን ግን ማንም አያስውስም። 750ሺ
ኢትዮጵያውያንን ጨርሶ፤ መናንያን፤ ቄሶች፤ ዲያቆኖችና መዕመናኖች ፈጅቶ ሞሶሎኒ እስከነ ውሽማው በሚላን አደባባይ እግሩ
ወደላይ ተደርጎ ተሰቀለ። የኛም በግራዚያኒ 9 ጳጳሳትም ስማቸውም ታሪካቸውም ከነሱ ጋር ተቀበረ።
የዛሬዎቹ የኦነግ-ኦሮሙማው የብልጽግና ባርያ ሳዊሮስ፥ የሕዋት እጅ ሥራ ሠረቀ ብርሃንና የትግራይ ዘረኛ መነኮሳት፥ የጨፌ
ኦሮሚያው ካድሬ “ቄስ” በላይ መኮንን፥ ሳሙኤል ብርሃኑ፥ ኃይለ ሚካኤል፥ “ንጹሕ” ኦሮሞ ተብሎ ክርስቶሳዊነትን አሳንሶ
የተⶄመው “አቡነ” ገብርኤል ወዘተ በጣሊያን ባንዳ አንጻር የአብይ አሽከር ሆነው የተፈጠሩ ናቸው።

የኦሮሚያ፥ የትግራይ ወዘተ እያለ የሊቀ ካህን የጌታችን፥ የመድኀኒታችን እና የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስን ገንዘብ ሥልጣነ
ክህነትን መጫውቻ ያደረጉ፣ ለሰው ልጆች መዳን ወሳኝ መገልገያ የሆነውን የሥልጣነ ክህነትን ጸጋ ለጎሣ ነጻ አውጭዎች
የፖለቲካ ዘርፍና አገልጋይ ያደረጉት ቤተ ክህነቱን መሙላታቸዉም የዚህ ሃይማኖትን የማጥፋት ፕሮጄትክ አካል ነው።

ነገሩ ይህ ክፋት የተተከለው በሕወሐት ነው። ሕወሐት ያገኘው ከቫቲካን ነው። የሕወሐት መጽሐፍ ቅዱስ የቻወቼስካ፥
የኪሲነጀር፥ የማኩሌይ፣ የቫቲካን፥ የማርክስ ወዘተ ማኒፌስቶ ቅይጥ የሰይጣን መመሪያ ነው።

አብይ ሕወሐት የተከለውን የዘረኝነት መርዝ በኦነግ-ኦሮሙማ ኮትኩቶ፥ የክርስቲያን ደም እያጠጣ አሳደገው። የቤተ እምነት
አርኞቹን ሲያዋርዳቸው ልጆቻቸውን አርደው መንበር ገልብጠው ሻሸመኔና ወለጋ እንዲገቡ በማድረግ የአባትነት ክብርን
አዋረደው።

ሳዊሮስ፥ ኤዎስታጤዎስ፥ ዜና ማረቆስ ሰው ባስገደሉብተ ሀገረ ስብከት አባትና እረኛ እንዲባሉ የፈቀደው ሲኖዶስ፥ እነርሱን
ብፁዐንና የሲኖደስ አባላት ብሎ በበጎች ላይ ተኩላውን እረኛ ያደረገው ሲኖዶስም ለአብይ አህመድ ወጥመድ በብልጭልጭ
ኮርቻና የተንቆጠ ፈረስ ከመሆን ያላመለጠ መሆኑን ተግባሩ መስክሮበታል።

ይህን ክፉ ተግባር በሲኖዶሱ ውስጥና በአገልጋዮች መካከል እንዲታይ እንዲሁም ለአብይ አይነት የወደቁ እኩይ ፖለቲከኞች
የሚያገለግል የቤተክርስቲያን መዋቅር መኖሩ ዋናው መንስኤ ቀድሞውኑ ሳያምኑ የመነከሱ፥ የመነኮሱበትን ገደማት ሕግ ጥሰው
ፍትፍትና ሌላም የሥጋ ጉዳይ አስኮብልሏቸው ከተማ ከትመው በገንዘብ ጵጵሳና የገዙ፥ ለሆዳቸው የተካኑ የመንፈስ በሽተኞች
በብዛት በመኖራቸው ነው።

ይህን ሁሉ እውነታ በምሬት ዘርግፈን የምንናገርበት ዋናው ዓላማችን ግልጽ ነው። አርሱም አንድ ምእመን ሃይማኖቱን
ለማስጠበቅ የጳጳስ ትዕዛዝ እንደማያስፈልገው ነባረን ክርስቱያናዊ ባህላችንን ለማስታወስ ነው።

ጳጳስ ኖረም አልኖረም ሃይማታችንን መጠበቅ የእያንዳንዱ ግዴታ ነው። በሌላ ማመካኘት ከፍርድ አይድንም። አዳም ፍሬውን
በልቶ ለምን በላህ ሲባል ይቅርታን አልጠየቀም። ይልቁንም ማመካኘት ነው የመረጠው። ኦሪት ዘፍጥረት 3፡ 12_13 “12፤
አዳምም አለ። ከእኔ ጋር እንድትሆን የሰጠኸኝ ሴት እርስዋ ከዛፉ ሰጠችኝና በላሁ።13፤ እግዚአብሔር አምላክም ሴቲቱን። ይህ
ያደረግሽው ምንድር ነው? አላት። ሴቲቱም አለች። እባብ አሳተኝና በላሁ።”

ማመካኘታቸው ግን በገነት አላቆያቸውም። እኛም ክርስቲያኖች ሲታረዱ ዝም ካልን እንደ ቃዬል “ እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝን”
እንደማለት ነው። ወንድማችንን መጠበቅ ግዴታችን ነው።

ስለዚህ የወንድማችን እረኞች እኛ እንጂ ጥቁር የለበሰ ቆብ የደፋ የጳጳስና የመነኮሱ ሰዌች ኃላፊነት ብቻ አይደለም። ለእነርሱ
ልዩ ድርሻ አላቸው፥ ከዚያ ያለፈ የነፃ አውጭነት ሚና እንዲጫወቱ መጠበቅ ግብዝነት፥ ፍርሀት፥ አላዋቂነትና በስደተኛ ስነ
ልቦና የመታሠር ውጤት ከመሆን አይዘልም።
በቅዱሳት መጽሐፍት፥ በተቀደሰ ትውፊት፥ በቀኖና ቤተክርስቲያን የታወቀውን፥ በሰብአዊነትና በሞራል ልኬት ኅሊና
የሚመሠክረውን ኃጢአትና ወንጀል ማውገዝ ከኃጥአት ጋር ያለመተባበር የእያንዳንዱ ክርስቲያን ሸክም እንጂ የሲኖዶስ
ትእዛዝ፥ የካህን ትምህርትና ምሪት የሚጠይቅ አይደለም።

አንድ ክርስቲያን የማንንም ትዕዛዝና ምሪት ሳይጠብቅ ጽድቅን መሥራት ሲጠመቅና የእግዚአብሔር ልጅ የመሆን ሥልጣንን
በተቀበለበት ጊዜ አብሮት የሚመጣ የሰማያዊ ርስት መውረሻ ኃላፊነቱ ነው። አንድ ሰው በጥምቀት የተሰጠውን የጸጋ ልጣኑን
ዋጋ ከፍሎ በተግባ ካልጠበቀ በስተቀር ከሥልጣኑ እንደሚሻርና ጌታ ዳግም ለፍርድ ሲመጣ “አላውቅህም” የሚያሰኝ
የዘላለም ቅጣት የሚያስከትል ነው።

ወደ ገላትያ ሰዎች ምዕራፍ 6: 4_5 ላይ “ነገር ግን እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ሥራ ይፈትን፥ ከዚያም በኋላ ስለ ሌላው ሰው ያልሆነ
ስለ ራሱ ብቻ የሚመካበትን ያገኛል፤ እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ሸክም ሊሸከም ነውና።”

የወንድማችን ጠባቂነት ለጳጳስና ለመነኩሴ ብቻ የተባለ አይደለምና። እነርሱ ረቂቁን ጠላት የምንጠብቅበትን፥ ጠላት አይ
ልብን ሲጠልፈን የምንነሳበትን ያሳዩናል። እኛ የጥምቀት ልጆች ሁላችን ግን ረቂቁ አድሮባቸው የመጡትን እንደ አብይ
አህመድ የኦነግ-ኦሮሙማ ልቡሳነ ሥጋ ሰይጣናትን፥ ፶ ዓመት ሙሉ ራሱን እያስመለከ ሕዝቡን ከወገኑ እየለየ የሚያዋጋውን
የሰሜኑን ሕወሐትን አይነቱን የሚታይ የሚዳሰስ ሰይጣን መዋጋት ግዴታ ነው።

ዘረኞችና ዘር አጥፊዎች ጨልመው ሲመጡ ብርሃን ሆኖ ማስወገድ የብርሃናውያን ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ የውዴኣታ ግዴታ
የሁላችንም ኃላፊነት ነው። በእርግጥ ሁላችንም እንፈራለን። ስለዚህ እነሱ ቢያደርጉልን ደስ ይለን ነበር። ግን ክርስቲያን ያለ
ፈተናና ችግር አልፎ መንግሥተ ሰማያትን አይወርስም።

እንደኛውን እንደ አንዳንዶቹ እኔ አልጾምም እኔ ክርስቶስ ጾሞልኛል፤ ዋጋ ከፍሎልኛል እንደሚሉት ቅኝ ገዥዎችን የባርያ
ፈንጋዮች አውሮፓውያን የማደንዘዣ እምነት እንደሚከተሉት የባርነት እምነት ተከታይ እንዳንሆን። አንድ አባት ሲያስተምሩ
ክርስቶስ ጦሞልኛል ካልን ለምን ክርስቶስም በልቶልኛል ብለን ምግቡን አልተውነውም ብለው ይጠይቃሉ።

አንዱ የክርስቲያን መገለጫ እና አባቶቻችን ነፃነትን ለእኛ አቆይተው ለመላው አፍሪካና ጥቁር ዘር ምሳሌ የሆኑበት ዋና
የሕይወት ትርጉማቸው ሥጋ የሚገድሉትን ባለመፍራት ለእግዚአብሐር ትእዛዝና እርሱን በመምሰል ለፍትሕ፥ ለስበአዊነትና
ለእውነት ሲባል ፍርሀታቸውን ማሸነፍ መቻላቻው ነው። አባቶቻችን ፈሪ አይጸድቅም፥ ገለባ አይበቅል የሚሉትን ብሂል
በማስታወስ ፍርሀትን ማሸነፍ ግድ ይላል።

2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 1፡7_8 “እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ
አልሰጠንምና። እንግዲህ በጌታችን ምስክርነት ወይም በእስረኛው በእኔ አትፈር፥ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ኃይል መጠን
ስለ ወንጌል አብረኸኝ መከራን ተቀበል”

ሌላው ነገር ፈርተን ከኃጢአት ጋር አለመተባበር ነው። መጽሐፈ ምሳሌ 4፡14_17 “በኃጥኣን መንገድ አትግባ፥ በክፉ ሰዎችም
ጎዳና አትሂድ። ከእርስዋ ራቅ፥ አትሂድባትም፤ ፈቀቅ በል ተዋትም። ክፉ ካላደረጉ አይተኙምና፥ ካላሰናከሉም እንቅልፋቸው
ይወገዳልና። የኃጢአትን እንጀራ ይበላሉና፥ የግፍንም ወይን ጠጅ ይጠጣሉና” ሲራክም “ብዙ ናቸው ብለህ ከኃጥአተኞች
አትተባበር” ብሎ ይገስጻል።

ለጥፋታችን እንደ ሄዋን በማሳበብ አይዳንም፤ በመጨረሻው ፍርድ ጳጳስ ሆነም ምእመን መጠየቃችን አይቀርም። አዳም
በሄዋን፤ ሄዋን ደግሞ በእባብ አመካኝታቸው ከፍርድ ማምለጥ አልቻሉምና ዛሬ በልባችን የያዝነውን ፈጣሪ ያውቃል። ሰውን
ማታለል ይቻላል ፈጣሪን ግን አይቻልም። በወንድም ደም ላይ ፥ ክርስቶስ በደሙ በዋጃት ቤተክርስቲያን ጥፋት ላይ፥ በአገር
መፍረስ ላይ ቆመን “እኔ የእነዚህ ሁሉ ጠባቂ ነኝን” ብንል በአንዲት ነፍስ በከንቱ መሞት “የወንድምህ የአቤል ደም ወደ እኔ
ይጮኻል” ብሎ ቃየልን የተሳሰበው ፈጣሪ የመቶ ሺዎችን መታረድ፥ የሚሊዮኖችን መፈናቀል፥ የገደማትና አድባራትን
መውደም፥ የማኅበረሰቦችን በድውያነ አእምሮ ዘረኛ የፖለቲካ ልሂቃን መፈራረስ ደም፥ ዕንባና ሰቆቃ የማይጠይቀን
ይመስላችኋል?

ከግል ኃላፊነት ለማምለጥ “እነሱ እንዲህ ቢያደርጉ እነሱ ቢጠጠሩ፤ እነሱ ቢያውግዙ፤ እነሱ ቢጾሙ፤ ቢጸልዩ ምህላ ቢገቡ’፥
አገሌ ቢመራን፥ ፋኖ ቶሎ ደርሶ እኛ ሳንቆስል ሳንጎሳቆል ጉሮ ወሸባ እየዘመርን ለካድሬነትና ለፍርፋሪ ለቀማ፥ ለንግድና
ለፋብሪካ ተከላ ብንፋጠን፥ ካባ ለብሰን መምህርና ሰባኪ፥ አባትና ካህን ብንባል በሚል ምኞት በሰው ልጅ ደም ላይ
መረማመድ ቅጣት ማምጣቱ የታወቀ ነው።

ከጸሎትና ከልማት በስተቀር ምንም ክፉ ያልሰሩ ገዳማውያንን የሚያርዱ፥ ወንድና ሴትን የሚደፍሩ፥ ከአስክሬን ጋር የሚተኙ፥
ከሰብእና የወጡ የዘር ፖለቲካ፥ የጣዖትና የጽንፈኞች ስብሰብ ቢለዋ ስሎ እያየን የኛን ልጆች ይምራሉ ብሎ ማሰብ እራስን
ማታለልና በፍርድ ቀን ማቲዎስ ወንጌል 25፡ 41_43 ላይ እንደተጻፈ “በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል። እናንተ
ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ። ተርቤ አላበላችሁኝምና፥ ተጠምቼ
አላጠጣችሁኝምና፥ እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝምና፥ ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፥ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝምና”

አሁን የሚጠየቀው በልባችንን ያለውን ፈጣሪ ያያል። ኃጡአት ሥሩ ግደሉ፤ ስደቡ አልተባለም። ለሚሞቱት ጸልዩ፤ ኃጢአትን
አውግዙ፤ ከኃጢአት ጋር አትተባበሩ፤ ክፋውን ክፋ በሉ፤ የተራቡትን አብሉ፤ የተጠሙትን አጠጡ፤ የታረዙትን አልብሱ ነው።
ይሄንን ብናደርግ ግድያንና ስደትን ለማስቆም ከሚያስችል በላይ ታላቅ አቅምና ቁጥር አለን ለማለት ነው።

እስቲ ፈጣሪ የሰጠንን ጸጋ እንቁጠር

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባላት በቁጥራቸው ከ60 እስከ 70 ሚሊዬን ይደርሳል ይባላል። የኢትዮጵያ
ህዝብ ቁጥር 129 ነው ይላል። ይህም በፈርንጆቹ 2014, 99.7 ሚሊዮን ነበር። ህዝቡ 2.52% ያድጋል የሚለውን ከወሰድን
የኢትጵያ ህዝብ ቁጥር በ 2024 የሚገመተው 129,719,719 ነው የሚል መረጃ ኦንላይን አለ። የህወሐትን ህዝብ ቆጠራ
ለዚያውም ኦርቶዶክሱን ለመቀነስ በሐሰት የሚቀምረውን ስንኳ ከተቀበልን 45% ኦርቶዶክስ ነው ይባላል። ይህ 60 ሚሊዮን
ነው።
ይህን ያህል ክርስቲያን ቁጥር ያለባት ሀገር ኢትዮጵያ ናት። ሩሲያ የህዝብ ቁጥሩ ከኢትዮጵያ ይበልጣል። ይሁን እንጂ የ70
አመቱ የኮሚኒዝም አስተምህሮ በርካታው ኢ_አማኒ እንዲሆን አድርጎታል። የሩሲያ ህዝብ ኦርቶዶክስ ነኝ ቢልም ቤተክርቲያን
የሚሄደው ግን ከ4.4 እስከ 7.4 ሚሊዮን ቢሆን ነው። (The number of practicing Orthodox Christians,
meaning those who regularly attend church services, is estimated to be between 4.4 million
and 7.4 million in Russia). ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ይህ ቁጥር በአንድ ንግሥ ቀን ግልብጥ ብሎ የሚወጣው ህዝብ ነው።
የኢትዮጵያ ህዝብ አማኝ ነው የሚባልበት ምክንያት ከ28 እስከ 38 ሚሊዮን ህዝብ እሁድ ቤተ ክርቲያን ይሳለማል፤
ያስቀድሳል። (The number of regular churchgoers in Ethiopia would be between 28.1 million and
38.8 million)።

ይህ ማለት አለም ላይ ካሉ 190 ሀገራት ውስጥ 150ዎቹ የህዝብ ቁጥራቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ቤተ ክርስቲያን ከሚያስቀድሰው
38 ሚሊዮን ህዝብ ያነሰ ነው። ቤተ ከርስቲያን የሚሄደውም የማይሄደውም ቢደመር ደግሞ በአፍሪካ ውስጥ ናይጄሪያ፤
ግብጽና ኮንጎ ብቻ ናቸው ከኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ አማኞች ቁጥር በላይ ህዝብ ያላቸው።

አማኝ ነው የተባለው እግዚአብሔር ራሱን በገለጠበት ርትዕት ኦርቶዶክሳዊት ሃይማኖት መሥመር ነው። ይህ እምነት በልብ
ብቻ የሚያዝ ሳይሆን በሕይወት የሚገለጥና ጌታችን እናንተ “የዓለም ብርሃን ናችሁ፥ እናንተ የዓለም ጨው ናችሁ” በማለት
በተግባር ጨለማን እንደምናስወግድ፥ አልጫን እንደምናጣፍጥ መንገሩ ይህን ያህል ብዙ ሳለን ጥቂት የጨለማ ልጆች በአገር
ላይ ፶ ዓመታት፥ በተለይ ባለፉት ፮ ዓመታት በገር ላይ መከራ ዶፍ ሳያዘንቡ የት ነበርን። “አማኝ ነን” እያልን እምነታችን
ብርሃን መሆን የተሳነው ነፃ አውጭና መፍትሔ አምጭ ጳጳስ፥ ጀግና፥ ተአምር ስንጠብቅ ነው። ሁሉም የሉም፥ ቢኖሩም
የጥምቀት ልጅ ድርሻውን ካልተወጣ “አማኝ” አይባልም፥ ቢባልም ሥራ የሌለው እምነት ሙት ነውና አይድንም።

ኦርቶዶክሱን ምን ሰለበው?

ታድያ ለምን ይሄንን ያህል ቁጥር ያለው ህዝብ ለዘርና ለሃይማኖት ጥፋት ተጋለጠ ብለን ስንጠይቅ ለሀምሳ አመት የተሰበከው
ርዕዮት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ነፍስን የሚገልውን ሳይሆን ስጋን የሚገለውን እንዲፈሩ የስነ ልቦና እጥበት
ስለተደረገባቸውና እነሱም አምነው ስለተቀበሉት ነው። ከልብስ ላይ መስቀሉና ሰንደቅ አላማውን ልቅደድ ሲባል ተሰልፎ
የሚያስቀድድ የፍርሀት ክፋ መንፈስ የያዘው ይመስላል። በዚያ ላይ የሚሏችሁን አድርጉ የሚሉና ባርነት የሚያለማምዱን
ጳጳሳት በዝተዋል።

“ሞትኩ” ብሎ የቁም ተስካሩን ያወጣው መነኩሴ ሳይቀር ሞትን ይፈራል። ድሎትና ምቾትን ይናፍቃል፤ ለዚህም ሲል
የዘመድና ቋንቋ ማኅበር መሥርቶ ዘረኛና ፈሪ ይሆናል። ይህ ደግሞ በፈጣሪው ላይ እምነት ማጣት ይመስላል። ዋስትናው
ያመነው አምላኩ ሳይሆን ዘሩ፥ መንግሥት፥ ዝቅ ሲል የጎሣ ነፃ አውጭ ቡድኑ ነው፣ ከዚያም የታጠቀው ሽጉጥ፥ ያጠራቀመው
ገንዘብ፥ የሠራው ሕንፃ ይሆናል። ይህ ራሱን የሚያሰማራ እረኛ የሥጋ ሞትን ይፈራል፥ የነፍስ ሞትን ግን ይደፍራል። ከዚህ
መፍትሔ አይጠበቅም!

መጽሐፈ ኢያሱ 1፡9 “በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና ጽና፥ አይዞህ፤ አትፍራ፥ አትደንግጥ ብዬ
አላዘዝሁህምን?”

ዛሬ በብሄር በተሳከረበት አገር አንድ በሕዝብ ቁጥር ብዛት የትንሹን ብሄር ለምሳሌ የአደሬን/ሐረሪን ወይንም የወራቤን ከተማ
የሥልጤን ማኅበረሰብ አባል አንድ ሰው በጥፊ መታ ቢባል ሀገር ይታመሳል። ሁሉም አንድ ላይ ቆመው የግለሰብ ጥልን ወደ
ጎሣና ሃይማኖት ግጭት ወደ መቀየር ሲሯሯጡና በዚህ ምክኒያት በዙ አብያተ ክርስቲያነት ሲቃጠሉ ሰው ሲገድል ይታያል።
ጎነድር መቃብር ቦታ ወጣቶች የተወራወሩትን ድንጋይ ወረቤ አምጥቶ ደም ማፋሰሻና አቢያተክርስቲያነት ማቃጠያ የሚያደርጉ
እኩያን ስነኳ ለክፋት ይደራጃሉ። ኦርቶዶክሳዊው ሰው ግን ለመልካምና ለቅድስና ራሱንና ሌላውን ከክፉዎች ለመጠበቅ አንድ
ሆኖ የማይነሳበት ምክንያት ምን እንደሆነ ከላይ ገልጸናል።

በገዳም ያሉና ከጸሎትና ከልማት ውጭ ምንም፥ ማንንም ያልነኩና የማይነኩ፥ ለ2000 ዓመታት ከመልካምነት ውጭ ክፋት
ያልታየባቸውን መነኮሳት ንጹሀን ሲታረዱ ግን 60 ሚሊዮን በላይ የሚሆነው የኦርቶዶክስ አማኝ አንድ ነገር አያደርግም።

አትግደሉን ብሎ ለመጸለይና ለመጠየቅ እንኳን ይፈራል። አሁን 60 ሚሊዮን የሚሆነው ህዝብ ሌላው ይቅር ከኃጢአት።
ከኢሰብአዊነት፥ ከኢፍትሐዊነት፥ ከዘረኝነት ጋር አልተባበርም ቢል መፍትሄ ማምጣት ያቅተዋል? ኦርቶዶክሳዊው ከዘር
ፖለቲካ ጋር አልተባበርም ቢል ኖሮ ሕወሐትና ኦነግ፥ አንዲሁም የእንረሱ ድቀል ልጅ ብልጽግና ሊያርደን፥ ሊያዋጋን፥
ሊያሳድደን ይችል ነበር?

የመልካም ክርስቲያኖች መተባበርና ክፋትን በግልና በወል መቃወም ለገዳዮች የሚልኩትን ቅጥረኛ፥ ባንዳና ሰላይ ያሳጣቸው
ነበር፥ መረጃ የሚሰጣቸው ይጠፋል፥ ወታደር ሆኖ የሚገድልላቸው አያገኙም፥ ክፉና ዘረኛ፥ ከፋፋይና አጥፊ ሕጎቻቸውናነ
ፖሊሲዎቻቸው የሚተገብር አይኖርም ነበር፤ ካድሬአቸውን የሚያዳምጥ አይገኝም፥ በቤተእምነት ውስጥ ያስገቡትን ምንደኛ
መስቀል የሚሳለም፥ ደሚዝ የሚሰጠው፥ የሚባልጉበትን ሀብት የሚያዋጣ ይጠፋል። በዚህ ነውረኞች ይሸነፋሉ።

የህሊና ጥሪ

ስለዚህ እኔ የወንድሜ ጠባቂ አይደለሁም በሚል ቃየላዊ አመጽ ከቀጠልን በምድርም በተራችን እንታረዳል በሰማይም ደግሞ
እንጠየቃለን።
አንዳንዱ ከኃጢአት ጋር አትተባበር ሲባል አቡነ ጴጥሮስን ሁን የተባለ ያህል ይሸበራል። መትረየስ ፊት ቁም የተባለ
ይመስለዋል፤ ከኃጢአተኞች ጋር እያበርክ ኃጥአትን አትስራ፥ ራስህን አድን ነው። አንተ በሰው ፊት ሰለፈራህ ብልጥ የሆንክ
ይመስልሀል ፈጣሪ ግን የልብን ያያል ነው።

በመጨረሻም በወንድምህ ደም እየቆመርክ በምድር ላይ ይህን የሥጋ ዕድሜ አስረዝመህ በኃጡአጥ ላይ ኃጡአት ከመጨመር
ወደ ቅድስና ስለማትደርስ ነፍስህን ታጣለህ። ረዥም ርኩሰትና ኃጢአጥ ለሚያሸክም ምድራዊ የድሎት ሕይወት ይለቅ
አጭርና ለውእነት ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር እውነት መስክሮ በሥጋ በአጭር የቀጨ ሰማዕት የዘላለም ሕይወትን
አንደሚወርስ የታወቀ ነው። ጊዮርጊስ፥ መርቆሬዎች፥ ቴዎድሮስ ዘሮምና ምሥራቃዊው፥ ፊቅጠሮእን አባድር ሁሉም ወጣቶች
ነበሩ። ክፋትን ተጋፍጠው ስለውእነት በአጭር ተቀጭተው ለዘላለም የብርሃን አምድ ሆኑ።

ጥሪው ከነፍሰ ገዳዮች ጋር አትተባበር፤ አትግደል፤ ሲገደል አውግዝ፤ ለተራበው አብላ፤ የተሰደደውን አጽናና፤ ለታረዙት
አልቅስ፥ የጥምቀት ልጆችን በቋንቋና በሰፈር አትከፋፍል፥ ምንደኛ ቁስና ጳጳስ ተከትለህ በነፍስ አትሙት። ነፍስን ለሚያጠፉ
ዘረኛ፥ ርኩስና ኃጡአትን የፖለቲካ ፖሊሲው ላደረገ የቀሰፈ ድርጅትና ግለሰብ አትታዘዝ።

ክፉዎች የሚያፈስሱት ደም ደሙ ባንተም እጅ ላይ ሆናልና ከዚህ ራስህን ፈጽመ ለይ ነው ጥሪው ። ይህ ደግሞ በሲኖዶስ
የሚታወጅ ሳይሆን አንተ ከፈጣሪህ የተቀበልከው የመዳን መንገድ ነው። ጌታህን አስብ፤ በፈራጆችና በፈሪሳውያን ፊት ፍትሕ
ቢነፈግም እውነት እርሱ ለእውነት ቆሞ ወንበዴ በርባንን መርጠው በምትኩ እውነት እርሱን ሊሰቅሉት በበየኑበት ፊት
ብቻውን ጸንቶ አርአያ የሆነን።

ስለዚህ ከዛሬቷ ቀን ጀምሮ ከኃጥያት ጋር አልተባበርም፤ እጄን በንጹሐን ደም ከሚታጠበው ጋር አላነካካም፤ የስራውም ተባባሪ
አልሆንም። እኔም የወንድሜ ጠባቂ ነኝ እንጂ አራጅ አሳራጅ አይደለሁም በል! ይህን ማለት የሚሳነው ካለ እርሱ ነፍሰ
ገዳይነቱን በገዛ አንደበቱ፥ ልቡና መላ አካሉ የመሰከረ ይሆናል።

የመጨረሻው መልዕክት ብትወድስ ተመስቀሌን ተሸክመህ ከተለኝ


እኛ እያንዳንዳችን ፈተናውን አለፍንም ወድቀንም፤ ሲዖል ገባን ገነትም በግላችን እንጠቀማለን ወይንም እንጎዳለን። ለሌላው
ብለን የምናደርገው አንድም ነገር የለም። ልትድን ብትወድ መስቀሉን ተሸከምህ ከኋላዬ ተከተለኝ በስሙ የተጠምቀነውና
ክርስቶሳውያን የተኘንበት አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገረን።

አንድ የሕግ አዋቂ ክርስቶስን ሊፈትነው ፈልጎ ባልምጀራዮ ማን ነው ብሎ ጠየቀው። ክርስቶስም በሉቃስ ወንጌል ም10፡
29_37 ይህን ምሳሌ ሰጠው” “እርሱ ግን ራሱን ሊያጸድቅ ወድዶ ኢየሱስን። ባልንጀራዬስ ማን ነው? አለው። ኢየሱስም
መልሶ እንዲህ አለ። አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ወረደ በወንበዴዎችም እጅ ወደቀ፤ እነርሱም ደግሞ ገፈፉት
ደበደቡትም በሕይወትና በሞት መካከልም ትተውት ሄዱ ድንገትም አንድ ካህን በዚያ መንገድ ወረደ አይቶትም ገለል ብሎ
አለፈ። እንዲሁም ደግሞ አንድ ሌዋዊ ወደዚያ ስፍራ መጣና አይቶት ገለል ብሎ አለፈ። አንድ ሳምራዊ ግን ሲሄድ ወደ እርሱ
መጣ አይቶትም አዘነለት፥ ቀርቦም ዘይትና የወይን ጠጅ በቍስሎቹ ላይ አፍስሶ አሰራቸው፥ በራሱ አህያም ላይ አስቀምጦት
ወደ እንግዶች ማደርያ ወሰደው ጠበቀውም። በማግሥቱም ሁለት ዲናር አውጥቶ ለባለቤቱ ሰጠና። ጠብቀው፥ ከዚህም በላይ
የምትከስረውን ሁሉ እኔ ስመለስ እከፍልሃለሁ አለው። እንግዲህ ከነዚህ ከሦስቱ በወንበዴዎች እጅ ለወደቀው ባልንጀራ
የሆነው ማንኛው ይመስልሃል? እርሱም። ምሕረት ያደረገለት አለ። ኢየሱስም። ሂድ አንተም እንዲሁ አድርግ አለው።

ለእኛ የቀረበልን ፈተና እንደ ካህኑ፡ እንደ ሌዋዊ ወይንም እንደ ሳምራዊው የመሆን ምርጫ ነው። መንገድ አቋርጠን፤ ቃል
መርጠን፤ የታረዱትን ግጭት ብለን መንገድ ቀይረን የወደቀውን ላለመርዳት መጣደፍ መብታችን ነው። ክርስትና ግን ልትድን
ብትወድ ተከተለኝ ነው። ለወደቀው ግን ባልንጀራው አይቶትም ያዘነለት፥ ቀርቦም ዘይትና የወይን ጠጅ በቍስሎቹ ላይ አፍስሶ
ያሰረለት፤ አህያም ላይ አስቀምጦት ወደ እንግዶች ማደርያ የወሰደውና ሁለት ዲናር አውጥቶ ለባለቤቱ የሰጠው ነው”

ምንም አያሻማም። ለጻድቃንም ለኃጡአተኞችም ቦታ ተዘጋጅቶላቸዋል።

በሰው ፊት እንደ አብይ አህመድ ቅዱስ፤ አዋቂ፤ ገነትን በምድር ላይ ከሸራተን ሆቴል አጠገብ እያልን መደነቅን እንሻለን። በሌላ
በኩል ደግሞ ንጹሀንን 24 ሰዓት፥ 6 ዓመት ያለመጸጸት ደም እናፈሳለን።

እነ አብይ አህመድ፤ ሽመልስ አብዲሳ፤ እነ አዳነች አቤቤ፤ እነ ዳናኤል ክብረት፤ እነ አበባው፥ እነ ደምላሽ በአደባባይ ክርስቲያን
መስለው ለመታየት ይጣጣራሉ። እኛን ማታለል ይሞክራሉ። እኛን ወደንና ፈቅደን ለሆዳችንና የሥጋ ሞት ፈርትን
እንደምንታለልላቸው ፈጣሪያቸውንም የሚያታልሉ ይመስላቸዋል።

በወደቀው በተደበደበው በተሰቃየው ነጋዴ ደም በልባቸው ደስ ብሎአቸው ይፈነድቃሉ። እኛ የልባቸውን አናየውም። ፈጣሪ
ግን የልብን ያያል።
በርካታውም ኦርቶዶክስ ነጠላ ለብሶ እንደ ካህኑና ሌዋዊው መንገድ ቀይሮ የሚሄደው ብዙ ነው። ጥሪው እንደሳምራዊው
ሁላችንም እንድንሆን ነው። ሰው እያለቀ በዓል ማድመቅ፥ ሻማ ለኩሶ የደስታ መዝሙር መዘመር፥ በመጠጥ መናወዝ፥
በአወሮፓ እግር ኳስ ራስን ማታለል፥ ኮነሰርትና ዝሙት መንደር ማደር፥ ሚሊዮኖች በተራቡበት አገር ሽርሽር ብሎ ቤተሰብን
ውድ የቱሪስት አገር ማስጎብኘት፥ የአጥቢያውን ካህን እያስራቡ እየሩሳሌም መሳለም፥ ሚሊዮኖች ካህናትና ቤተክርስቲያን
አጥተው በብዙ መቶ ሚሊዮኖች ዓለምን የኢያስደንቅ ቤተክርስቲያን መገንባትና የሌቦችና ምንደኞች መራኮቻ ማድረግ ---
አያድንም!

የጎዴን፥ የቀብሪዳርን የጅጅጋን፥ የሐረርን፥ የድሬደዋን፥ የበደቦን፥ የጨለንቆን፥ የቀቀሊን፥ የጎሮ ሙጢን፥ የደደርን፥ የቆቦን፥
የኩርፋ ጨሌን፥ የወተርን፥ የጎሮ ጉቱን፥ የካራሚሌን፥ የበሮዳን፥ የዶባን፥ የደበሶን፥ የቦኬን፥ የአሰቦትን፥ የኮፈሌን፥ የሻሸመኔን፥
የሀገረ ማርያምን፥ የባሌ ሮቤን፥ የባሌ ጎባን፥ የዝቋላን፥ የአዳማን፥ የቡራዩን፥ የአንቦን፥ የነቀምትን፥ የአይራ ጉሊሶን፥ የቡለንም፥
የወንበርምማ፥ የአሶሳን፥ የከሚሴን፥ የአጣዬን፥ የአርባ ጉጉን፥ የመተሐራን፥ የማይካድራን፥ የአክሱም መርያም ደንጎላተን፥
የቀራንዮ ወየብላ ኪዳነ ምህረትን፥ የ22 ማዞርያን ከወያኔው የመለስ ዜናዊ እስከ አብይ አህመድ የሚታረደውን ክርስቲያን
አላየሁም፤ የወንድሜ የጠባቂ አይደለሁም በማለት ከእግዚአብሔር ፍርድ ማምለጥ አይቻለም! ትገራይንና አማራን፥ አፋርናና
ኦሮሞን፥ ጋሞና ኮንሶን የሚጨርሰውን የአጋንንት ሥርዓት አላውቀዉም ማለት አይቻለም! ማንም ከአግዚአብሔር ፍርድ
አያመልጥም።

ከፍርድ ለማምለጥና ለመዳን ከፈለግን አዎ እኔ፥ አንተ፥ አንቺ የወንድም እኅቶቻችን ጠባቂዎች ነን በሚል ክርስቲያናዊ መንፈስ
እረኝነቱን እንጀመረው።

እውነት፥ ሰብአዊነት፥ ፍትሕ፥ እምነትን ይዘን መስቀሉን በመሸከም የማናሸንፈው አንዳች ኃይል የለም!!! ይህ የተረጋገጠ
ሰማያዊ ምስክርነት ያለው እውነት ነው።

You might also like